YeneTube
الذهاب إلى القناة على Telegram
2025 عام في الأرقام

107 389
المشتركون
-5724 ساعات
-4017 أيام
-2 12730 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
ስልኮ መልክዎን እያበላሸው ይሆን
ቆዳችንን ከፀሐይ ጨረር ለመጠበቅ እንጠነቀቃለን፤ ነገር ግን በቀን ለሰዓታት ከምንመለከተው ስልክና ኮምፒውተር የሚወጣው "ሰማያዊ ብርሃን" (Blue Light) ተመሳሳይ ወይም የከፋ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ጥናቶች እያመለከቱ ነው።
እንደ "Journal of Investigative Dermatology" ያሉ የቆዳ ጤና ጥናት ተቋማት ላይ የወጡ ጥናቶች፤ ለረጅም ሰዓታት ለዲጂታል ስክሪኖች መጋለጥ የቆዳን ጥንካሬ በማዳከም ቆዳችን ያለዕድሜው እንዲሸበሸብ ያደርጋል ይላሉ።
ከስክሪን የሚወጣው ሰማያዊ ብርሃን ወደ ቆዳችን ጥልቅ ክፍል (Dermis) ዘልቆ በመግባት የቆዳን ወጣትነት የሚጠብቀውን ኮላጅን (Collagen) እና ኤላስቲን (Elastin) ይሰብራል። ይህም ቆዳ እንዲላላ፣ እንዲዝልና ጥቁር ነጠብጣቦች እንዲፈጠሩ ያደርጋል።
የቆዳ ሐኪሞች እንደሚመክሩት፤ በስልካችን ላይ "Blue Light Filter" ወይም "Night Mode" ማብራት የብርሃኑን ኃይል ለመቀነስ ይረዳል።
በተጨማሪም፣ የቆዳን መከላከያ አቅም የሚጨምሩ በ"አንቲ-ኦክሲዳንት" የበለጸጉ የቆዳ ቅባቶችን መጠቀምና ከስክሪን ራቅ ያለ ጊዜን ማዘውተር ለቆዳ ጤና ወሳኝ እንደሆነም ያስቀምጣሉ።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 25👍 15
🚀 Get Found. Get Hired. Get Work Done.
Are you a professional looking for job opportunities?
Are you an employer or service seeker searching for skilled talent?
✅ Register on Jitume and make your profile visible to employers and clients across Ethiopia.
🔹 Open to ALL professions
🔹 Free & easy registration
🔹 Employers can directly find and contact you
🔹 Service seekers can choose verified professionals
👉 Register now and be visible:
🌐 https://jitume.gebeya.com/?utm_source=Jasper&utm_medium=tesfaye_guta_367010&utm_campaign=Jasper
📣 Don’t wait for opportunities—put yourself where opportunities find you!
❤ 4
Photo unavailableShow in Telegram
እርሶስ አገልግሎት ሳይሰጥ በዚህ መልክ የተቀመጠ ያገለገለ እቃ አሎት?
ካሎት ባሉበት ሆነው ፎቶ አንስተው በመላክ ብቻ በቀላሉ ይሽጡት። ያገለገለ እቃ መሸጥ ዘምኗል ቀሏል
ወይም በሌሎች ሰወች ፖስት የተደረጉ ያገለገሉ እቃዎችን ፎቶ ፣ አድራሻ ፣ ዋጋ እና የእቃውን ባለቤት ስልክ ቁጥር በ ET Creatives ያገኛሉ።
✅ JOIN 👉 https://t.me/ET_Creatives_Family
ET Creatives
❤ 2😁 1
በጥቁር ገበያውና በመደበኛው መካከል ያለው የዶላር ምንዛሬ ልዩነት በ4 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ ማለቱ ተገለጸ!
በ2018 በጀት አመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ውስጥ ይፋ በተደረገ ጥናት በጥቁር ገበያውና በመደበኛው መካከል ያለው የዶላር ምንዛሬ ልዩነት፤ ከ18 ነጥብ 4 በመቶ ወደ 13 ነጥብ 7 በመቶ በመውረድ ልዩነቱ ወደ 4 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ ማለቱን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ለአሐዱ ሬዲዮ አስታውቋል።
ከማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ በኋላ የውጪ ምንዛሬ ሁኔታው ምን ላይ እንደሚገኝ እና የብርና የዶላር ምንዛሬ በገበያ ላይ ስላለው ሁኔታ ጥናት መደረጉን የገለፁት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ከፍተኛ ተመራማሪ ናስር የኑስ (ዶ/ር) ናቸው።
በጥናቱም በ2018 በጀት ዓመት ሩብ ዓመት ውስጥ ቀደም ሲል ከነበረው አንፃር የዶላር ምንዛሬ በመደበኛ እና በጥቁር ገበያው መካከል ያለው ልዩነት በአንፃራዊነት መጥበብ መቻሉን አንስተዋል።
ከተያዘው ሩብ ዓመት በፊት በመደበኛውና በጥቁር ገበያው መካከል ያለው የዶላር ምንዛሬ 18 ነጥብ 4 በመቶ ልዩነት የነበረው ሲሆን በዚህ ሩብ ዓመት ግን ወደ 13 ነጥብ 7 በመቶ መውረዱን ተናግረዋል።
ከዚህ ባሻገር እንደአጠቃላይ ያለው የብር ዋጋን በሚመለከት ግን አሁንም ድረስ የዶላርና የብር ምንዛሬ የተረጋጋ ሁኔታ ላይ አለመሆኑን ያነሱ ሲሆን፤ 2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ሩብ ዓመት ውስጥ ብር ከዶላር ጋር ያለው የምንዛሬ መጠን በ8 ነጥብ 1 መቀነሱን ተናግረዋል።
ይህም በ2017 የመጨረሻ በጀት ዓመት ሩብ አመት ጋር ከነበረው ከ4 በመቶ በላይ መጨመሩን ገልጸዋል።
ይህም አሁንም ድረስ ገበያው ትክክለኛ የሆነ መረጋጋት ላይ አለመሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፤ ብር ከዶላር አንፃር ያለው ዋጋ መቀነሱ በገበያው ላይ ጫና እንደሚፈጥር አንስተዋል።
ኢትዮጵያ በርካታ ምርቶችን ከውጪ የምታስገባ ከመሆኗ አንፃር የብር ዋጋ በቀነሰ ቁጥር ምርቶች እየተወደዱ እንደሚመጡ የገለጹት ከፍተኛ ተመራማሪው፤ ወደ ሀገር ውስጥ የራሳቸው የሆነ የዋጋ ግሽበትን በማምጣት የዋጋ መረጋጋት እንዳይኖር አስተዋጽኦ እንደሚያሳድሩ ተናግረዋል።
የዋጋ መረጋጋት ከሌለ ሰዎች በብር እርግጠኛ ስለማይሆኑ ያላቸውን ሀብት በዶላር ለመያዝና ወደሌላ ሀገር ለማሸሽ በሚሞክሩበት ወቅት ምጣኔ ሀብቱን እንደሚያዛባ አንስተዋል።
በመሆኑም ይህንን ለማስተካከል የሀገር ውስጥ አቅርቦትን መጨመርና የምጣኔ ሀብቱን መዋቅር ማስተካከል እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ በብዛት ወደውጭ የምትልከው የግብርና ምርቶችን መሆኑን የሚያነሱት ከፍተኛ ተመራማሪው እነዚህ ምርቶች ደግሞ ኢትዮጵያ የምትፈልገውን የውጪ ምንዛሬ በሚፈለገው መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንድታገኝ እያስቻሉ አይደለም ብለዋል።
ስለዚህ እነዚህ ችግሮች መቀረፍ፣ የውጪ ኢንቨስትመንትም ማደግና የሀገር ውስጥ ገቢው ከትይዩ ገበያ ወጥቶ ወደ ሕጋዊ መስመር መግባት እንደሚጠበቅበት በመግለጽ፤ ይህ ካልሆነ ግን ያለው አለመረጋጋት እየጨመረ ሊሄድ እንደሚችል አሳስበዋል።
Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 33😁 17👎 2⚡ 1🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ይሸጣል ብሎ መለጠፍ ድሮ ቀረ
ያገለገለ እቃዎትን ባሉበት ፎቶ በማንሳት ይሽጡ - መግዛትም ይቻላል
✅ ልብ ይበሉ ሁላችንም ቤት አንድ የማንፈልገውና የማንጠቀምበት ያገለገለ እቃ አለ በተቃራኒው ደግሞ ያንን እቃ የሚፈልጉ ግን የት እንደሚገኝ የማያውቁ ሰዎች አሉ።
አላማችን እርሶ የማይጠቀሙበትን ያገለገለ እቃ በቀላሉ ካሉበት ሆነው ፖስት በማስደረግ እንዲሸጡ ማስቻል ሲሆን ያገለገለ እቃ መግዛት ሲፈልጉ ደግሞ በቀጥታ ከእቃው ባለቤት በጥሩ ዋጋ እንዲገዙ ማገዝ ነው።
ስለሆነም እርሶም ቤት አገልግሎት ሳይሰጥ ቦታ ይዞ የተቀመጠ ያገለገለ እቃ ካሎት ፎቶ አንስተው ይላኩልን ወይም በሌሎች ሰወች ፖስት የተደረጉ ያገለገሉ እቃዎችን ፎቶ ፣ አድራሻ ፣ ዋጋ እና የእቃውን ባለቤት ስልክ ቁጥር በ ET Creatives በቀላሉ ያገኛሉ
✅ JOIN 👉 https://t.me/ET_Creatives_Family
ET Creatives
❤ 6
🚀 Get Found. Get Hired. Get Work Done.
Are you a professional looking for job opportunities?
Are you an employer or service seeker searching for skilled talent?
✅ Register on Jitume and make your profile visible to employers and clients across Ethiopia.
🔹 Open to ALL professions
🔹 Free & easy registration
🔹 Employers can directly find and contact you
🔹 Service seekers can choose verified professionals
👉 Register now and be visible:
🌐 https://jitume.gebeya.com/?utm_source=Jasper&utm_medium=tesfaye_guta_367010&utm_campaign=Jasper
📣 Don’t wait for opportunities—put yourself where opportunities find you!
❤ 4
Photo unavailableShow in Telegram
አሜሪካ በየዓመቱ የምታካሂደውን የዲቪ ሎተሪ አቆመች!
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት በብራውን ዩኒቨርሲቲ በተፈጸመ የጅምላ ጥቃት ሁለት ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ የአሜሪካን ግሪን ካርድ ሎተሪን (ዲቪ) አገዱ።ጥቃቱን ፈጽሟል ተብሎ የተጠረጠረው እና ሐሙስ ዕለት ሞቶ የተገኘው ፖርቹጋላዊው በአውሮፓውያኑ 2017 ዲቪ ሎተሪ አሸንፎ ወደ አገሪቱ የገባ ሲሆን ግሪን ካርድም ተሰጥቶታል።
የአገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስትር የሆኑት ክሪስቲ ኖም "በዚህ አስከፊ ፕሮግራም አሜሪካውያን ከእንግዲህ እንዳይጎዱ ለማረጋገጥ" በሚል ትራምፕ በሰጡት መመሪያ መሠረት የቪዛ መርሃ ግብሩን ለጊዜው እንዲቋረጥ መደረጉን ተናግረዋል።የአሜሪካ ባለሥልጣናት ተጠርጣሪው የ48 ዓመቱ ክላውዲዮ ኔቭስ ቫለንቴ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም ፕሮፌሰር ኑኖ ሉሬሮንም ገድሏል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
የዲቪ ሎተሪ ፕሮግራሙ በአሜሪካ በስደተኝነት በቂ ድርሻን ላላገኙ አገራት ዜጎች በየዓመቱ 50 ሺህ ቪዛዎችን ይሰጣል። ይህ ደግሞ የአሜሪካ ዜግነትን ለማግኘትም በር ከፋች ነው።ኖም በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ትራምፕ ቀደም ሲል በኒው ዮርክ ከተማ ስምንት ሰዎች በጭነት መኪና ተገጭተው ከተገደሉ በኋላ ፕሮግራሙን ለማስቆም "ታግለዋል" ብለዋል።
ኖም እንዳሉት የኡዝቤኪስታን ተወላጅ የሆነው ሳይፉሎ ሳይፖቭ፣ የኢስላሚክ ስቴት ደጋፊ የሆነ እና ለተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት ግለሰብ በዲቪ1 ፕሮግራም መሠረት ወደ አሜሪካ ገብቷል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cpq4p51zzg4o
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 40😭 13👍 3⚡ 2🔥 2😁 1
ከ60 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ወርቅና ከ4ሚሊየን ብር በላይ ይዘው በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ!
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከ60 ሚሊየን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለው ወርቅና ከ4ሚሊየን ብር በላይ ይዘው በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ከእነኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀ።ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአሶሳ ከተማ አምባ አንድ በሚባል ቦታ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ከእነ ወርቅና ጥሬ ገንዘቡ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻሉት በፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል የኮንትሮባንድ ቁጥጥር ፖሊስ መምሪያ ከህበረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ባደረገው ክትትል መሆኑ ተጠቁሟል።
በኮንትሮባንድ ቁጥጥር ፖሊስ መምሪያ ሬጅመንት አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ዳኘ አለማየሁ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እያጣራባቸው መሆኑን ጠቅሰው የተያዘው ወርቅና ጥሬ ገንዘብም ለአሶሳ ከተማ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ገቢ መደረጉን ተናግረዋል።
አክለውም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮንትሮባንድና ሕገ-ወጥ ንግድ በሀገር ኢኮኖሚ እና በሕጋዊ ነጋዴዎች ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት በመገንዘብ ከሕዝብና ከመንግሰት የተጣለበትን አደራ ለመወጣት ሕዝብን ባሳተፈ መልኩ ስኬታማ የመከላከል ሥራ እያከናወነ መሆኑን መግለጻቸውን ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 21🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኦፓልን ጨምሮ ሌሎች የማዕድን ምርቶችን በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኩል ማገበያየት ሊጀመር ነው
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የኦፓል ማዕድንን ጨምሮ ሌሎች የማዕድን ምርቶችን ማገበያየት ለመጀመር የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለጸ።
የምርት ገቢያው በአሁኑ ወቅት ቡና፣ ሰሊጥ፣ ጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎች እና ቅመማ ቅመሞችን ጨምሮ ወደ 28 የግብርና ምርቶችን በማገበያየት ላይ ይገኛል።
ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መርጊያ ባይሳ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አዋጅ ከተሻሻለ በኋላ ተቋሙ ከግብርና ውጭ የሆኑ ማዕድንና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ማገበያየት የሚችልበት ኃላፊነት እንደተሰጠው ገልጸዋል።
ይህንኑ ተከትሎ የኦፓል ማዕድንን ወደ ገበያ ለማስገባት ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።
ከኦፓል በተጨማሪ ሌሎች ማዕድናትን ለማገበያየት የሚያስችል ራሱን የቻለ የግብይት ሥርዓት ለመዘርጋት በምርት ገበያው በኩል ሲደረጉ የነበሩ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን አስታውቀዋል።
በማዕድን ሚኒስቴር በኩል መጠናቀቅ ያለባቸው ጉዳዮች ሲፈጸሙ የማገበያየት ስራው እንደሚጀመር ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።
ኢዜአ
❤ 28
Repost from YeneTube
Photo unavailableShow in Telegram
🟦 LinkedIn rental
LinkedIn account አሎት እንግዲያውስ እኛ ጋር ሲመጡ👉
•100-299 connections: $8 በየሳምንቱ
• 300-499 connections: $13 በየሳምንቱ
• 500-999 connections: $15 በየሳምንቱ
• 1000-1999 connections: $20 በየሳምንቱ
• 2000+ connections: $25 በየሳምንቱ
📱በኢትዮጵያ ትልቁ እና ታማኙ የሊንኪደን አካውንት ተከራይ አሁንም በርካታ አካውንቶችን ተከራይቶ ለቢዝነስ አላማ ማስተዳደር ይፈልጋል።
📱ከፍተኛ ኮኔክሽን ወይም ረጅም አመት ያስቆጠሩ አካውንቶች የተሻለ ክፍያ ያገኛሉ፡፡
in የእርስዎን አካውንት ደህንነት እንደራሳችን አካውንት አድርገን እንጠብቀዋለን።
📱 የእርስዎን አካውንት ከማከራየት ጎን ለጎን ሰው በመጋበዝዎ ኮሚሽን እንከፍላለን
in ስምንት ወር እና 1ዐዐ ኮኔክሽን ዝቅተኛው መስፈርት ነው
📱 ጥራት ያላቸው አካውንቶች እንዲሁም ከ3ዐዐ+ በላይ የሆኑ አካውንቶች welcoming reward ወዲያውኑ ተፈፃሚ ይሆናል።
📱 ዝርዝር መረጃዎችን ከፈለጉ በዚህ አድራሻ ያለዎትን የኮኔክሽን እና የተከፈተበትን አመት
👤Contact Us Now:
📱: @Melech4
☎️: 0967033154
Our telegram channel 👉
https://t.me/linkedinrent255work
🔥 2❤ 1👎 1
Repost from YeneTube
00:40
Video unavailableShow in Telegram
🥁 65% /35%
🌬እንኳን ደስ አላችሁ💫💫💫
🌬 አሁን ቀደም ያመለጣችሁ ደንበኞቻችን ወርቃማ እድል በዲፕሎማቲክ መንደር በሳርቤት ቫቲካን ኤምባሲ አጠገብ ለውስን ቤቶች ብቻ
🌴ቴምር ፕሮፐርቲስ
🌬 65% ሲከፍሉ 35% እኛ ልዩ ቅናሽ አቅርበናል።
🏠 80 ካሬ ሜትር ባለ ሁለት መኝታ
🥁ሙሉ ክፍያ 5,770,050ብር
🏠139 ካሬ ሜትር ባለሶስት መኝታ
🥁ሙሉ ክፍያ 9,938,,000 ብር
✅ መገልገያዎች
👉 ሁለት ዘመናዊ የሰው እና አንድ የእቃ ሊፍቶች
👉 የመኪና ማቆሚያ ቦታ
👉 ቴራስ
👉 ያልተገደበ የውሃ አቅርቦት
👉 የመጠባበቂያ ጀነሬተር
👉 የደህንነት ካሜራ
👉ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ እና ኢንተርኮም ሲስተም
እንዲሁም
⛳️ ገላን ኮንደምንየም
🗣ሱቆች ከ23 ካሬሜትር ጀምሮ
በ500,000ብር ቅድመ ክፍያ እንዲሁም 2.3 ሚሊዬን ሙሉ ክፍያ ለውስን ሱቆች ብቻ እየሸጥን እንገኛለን።
🚴🏿♂️ይፍጠኑ🚴🏽♀️
🕹ለበለጠ መረጃ:- 0931835733
ይደውሉ! በwhatsapp ያገኙናል።
Telegram @momsra16
ይፍጠኑ🗣
12.33 MB
❤ 5🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዩክሬን በፈጸመችዉ የድሮን ጥቃት በሩሲያ ሮስቶቭ ውስጥ 3 ሰዎች ተገደሉ
ዩክሬን በሩሲያን ደቡባዊ ክልል ሮስቶቭን በፈጸመችዉ የሰዉ አልባ አዉሮፕላን ጥቃት የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ።ይህዉ ጥቃት የተፈጸመዉ የአውሮፓ ሀገራት ኪየቭን ለመርዳት የሩሲያን ንብረቶች እገዳን በተመለከተ እና ጦርነቱን ለማቆም በዩናይትድ ስቴትስ የሚመራው ጥረቶች እየተወያዩ ባለበት ወቅት ሲሆን እስካሁን ተጨባጭ ውጤት ላይ መድረስ ግን አልቻሉም፡፡የሮስቶቭ ክልል ተጠባባቂ የክልል ገዥ ዩሪ ስሊሳር በቴሌግራም ሐሙስ ዕለት እንዳስታወቁት ጥቃቱ በጭነት መርከብ ላይ የእሳት ቃጠሎ አስከትሏል፣ በጥቃቱ ሁለት መርከበኞች ሲሞቱ ሌሎች ሶስት ሰዎች ቆስለዋል።
ገዥው አክለዉ እንዳስታወቁት በተጨማሪም የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች በወደብ መገልገያ አቅራቢያ በምትገኘው ባታይስክ ከተማ አንድ ሲቪል እንደገደለ ገልጸው ሁለት ቤቶች ሲቃጠሉ በግንባታ ላይ ያለ አንድ አፓርታማ ተጎድቷል። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ከእሮብ እኩለ ሌሊት ጀምሮ እስከ ሀሙስ ማለዳ ድረስ ሠራዊቱ 47 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች አላማቸዉን እንዲስቱ ማድረጉን ባወጣዉ መግለጫ አስታዉቋል፡፡
31 ሰው አልባ አውሮፕላኖች በብራያንስክ ግዛት፣ አምስቱ በጥቁር ባህር ውሃ ላይ፣ አራቱ ሞስኮ በኃይል በያዘችዉ ክራይሚያ፣ አራት በቤልጎሮድ እና ሶስት በሮስቶቭ ክልል ላይ የተላኩት የዩክሬን ድሮኖች ጥቃት ማድረስ እንዳይችሉ ማድረግ ተችሏል፡፡በሌላ በኩል የአውሮፓ ኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሌየን በብራስልስ ከሚካሄደው የመሪዎች ጉባኤ አስቀድመዉ ለጋዜጠኞች ባደረጉት ንግግር ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።"ለዩክሬን ፋይናንስ መፍትሄ ከሌለ ምክር ቤቱን አልለቅም" ሲሉ ፕሬዝዳንቷ ተደምጠዋል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 21👀 1
ጋምቤላ ክልል “ የመከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ” መግባቱን ርዕሰ መስተዳድሯ ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ!
በጋምቤላ ክልል ተቀስቅሶ የነበረውን “ ግጭት ” ተከትሎ “ የመከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ወደክልሉ መግባቱን ” የክልሉ ፕሬዝዳንት አለሚቱ ኡሙድ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።በተለያዩ አቅጣጫዎች ተኩስ እና ግጭቶች እንደተፈጠሩ መዘገቡን ተከትሎ ከአዲስ ማለዳ ጥያቄ የቀረበላቸው የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሙድ አጭር ማብራሪያን ሰጥተዋል፡፡
ርዕሰ መስተደዳድሯ በክልሉ “ የጸጥታ ችግር ተፈጥሮ እንደነበር “ አልሸሸጉም። የግጭቱ መንስኤ በተመለከተ ሲናገሩ “ አንድ የፖሊስ አዛዥ በመገደሉ ምክንያት መሆኑን “ ገልፀው አዛዡ ከመገደሉ በፊትም የፀጥታ ችግሮች በአካባቢው ሲፈጠር እንደነበር አስታውሰዋል።
ይሁን እንጂ ከግድያው በኋላ አካባቢው ሠላም የነበረ ቢሆንም አንዳንድ አከባቢዎች ላይ የተለያዩ የተኩስ ድምጿች ሲሰሙ ነበር ብለዋል።
“ በክልሉ የተነሳው ግጭት አሁን ላይ እየተረጋጋ፣ የከተማው እንቅስቃሴ ሰላማዊ መሆኑንና በከተማው የሚያሰጋ ነገር እንደሌለ “ ርዕሰ መስተዳድሯ ለአዲስ ማለዳ ነግረዋታል፡፡ግጭቱን ለማረጋጋት እና የከተማውን ሠላም ለመጠበቅ ወደ ክልሉ የመከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ መግባቱንም አስረድተዋል።ከዚህ በተጨማሪ “ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ችግሮች መኖራቸውን “ ገልፀው በቦታው ሠላም ለማስፈን እየተሠራ ነው ብለዋል።
በእርሳቸው ርዕሰ መስተዳድርነት የሚመራው የጋምቤላ ክልል ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ በርካታ ያላቸውን ነገር ግን በቁጥር ያልገለጻቸውን ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቋል፡፡ይህም ብቻ ሳይሆን ከጸጥታ አካላት ውጪ የጦር መሣሪያ የያዘ ግለሰብ ወይም ቡድን አሰፈላጊ ሲል የጠራው እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል፡፡
Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 30👍 1🔥 1😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
"ምርጫው በትግራይ ካልተካሄደ፣ በአዲስ አበባ እወዳደራለሁ" - ባይቶና
በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀስ የቆየው ተቃዋሚው ባይቶና ፓርቲ በመጪው ግንቦት በሚደረገው አገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ዋዜማ ዘግባለች።
ፓርቲው በትግራይ ክልል ምርጫ ካልተካሄደ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ለመወዳደር ወጥኖ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ተረድተናል ብላለች፡፡
ፓርቲው በአማራና አፋር ክልሎች የመወዳደር ውጥን ያለው ቢሆንም፣ ሆኖም በሁለቱ ክልሎች በምርጫው ለመሳተፍ አስቻይ ሁኔታ የለም ብሎ እንደሚያምን መረዳት ተችሏል።
ፓርቲው፣ በትግራይ ክልል ምርጫ ማካሄድ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ንግግር መጀመሩም ተዘግቧል፡፡
የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ተከትሎ የፓርቲው ፍቃድ ተሰርዞ የቆየ ሲሆን፣ በሚያዚያ ወር 2016 ዓ፣ም ግን ፓርቲው በአገር ዓቀፍ ደረጃ ለመንቀሳቀስ የሚያስችለውን ፍቃድ እንዳገኘ ይታወሳል።
@YeneTube @FikerAssefa
😁 24❤ 17👀 3🔥 1
00:05
Video unavailableShow in Telegram
Samsung A06 5G
Memory: 128/6GB
Condition: Brand New
Battery: 5000mAh
Price: 17500ETB
Call: 0924769665
DM: @adagioandante
1.68 MB
❤ 10
Photo unavailableShow in Telegram
ዋና መሥሪያ ቤቱን በሌጎስ ናይጄሪያ ያደረገውና በአፍሪካ ግንባር ቀደም ከሆኑ የፋይናንስ ተቋማት አንዱ የሆነው ዜኒት ባንክ፣ በኢትዮጵያ አዲስ በተከፈተው የባንክና የፋይናንስ ዘርፍ ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት ገለጸ።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዝናቡ ይርጋ ከባንኩ ተወካዮች ጋር በነበራቸው ውይይት፣ ኢትዮጵያ ግዙፍና ታማኝ የሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማትን ለመቀበል ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ በኢኮኖሚ ጥንካሬዋ ሦስተኛ ደረጃ ላይ መገኘቷ እና እየተገነቡ ያሉ ታላላቅ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ለፋይናንስ ዘርፉ ምቹ ሁኔታ መፍጠራቸውንም ምክትል ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።
የዜኒት ባንክ የዓለም አቀፍ ገበያ መስፋፋት የቡድን ኃላፊ ኦሉካዮዴ አኪንቢኑ በበኩላቸው፣ ባንካቸው በኢትዮጵያ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ባለው ኢኮኖሚ እና በተደረጉት የዘርፍ ማሻሻያዎች መሳቡን ገልጸዋል።
ባንኩ በተለይም በዲጂታል የፋይናንስ መፍትሄዎች እና በመንግስት የሚመሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በገንዘብ በመደገፍ ረገድ ያለውን ዕድል እያጠና መሆኑን ተናግረዋል።
ዜኒት ባንክ በአሁኑ ወቅት በኮርፖሬት፣ በችርቻሮ እና በዲጂታል ባንክ አገልግሎቶች የሚታወቅ ሲሆን፣ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱም የሀገሪቱን የፋይናንስ ሥነ-ምህዳር ለማጠናከርና የካፒታል አቅምን ለማሳደግ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል። የኢንቨስትመንት ኮሚሽንም ባንኩ በኢትዮጵያ ሥራ እንዲጀምር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ በውይይቱ ወቅት አረጋግጧል።
Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 17
የጋምቤላ ከተማ የፖሊስ አዛዥ መገደልን ተከትሎ ግጭት ተቀሰቀሰ፤ የፀጥታ መዋቅሩ “በጎሳ መከፋፈሉ” ስጋት መደቀኑ ተገለጸ
በጋምቤላ ከተማ በትላንትናው ዕለት የከፍተኛ ፖሊስ አመራር መገደላቸውን ተከትሎ ግጭት የመቀስቀሱን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የቀደሞ የክልሉ የፀጥታ አመራር እና አንድ የክልሉ ባለስልጣን ለአዲስ ስታንዳርድ ገለፁ። የተቀሰቀሰው ግጭት አሁንም ቀጥሎ እንደሚገኝና የክልሉ "የጸጥታ መዋቅር በጎሳ ክፍፍል ምክንያት ሁኔታውን መቆጣጠር እንዳልቻለም" ተናግረዋል።
ትላንት ማክሰኞ ታኅሣሥ 7 ቀን 2018 ዓ.ም. ረፋድ ላይ፣ የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ በጥይት ተመተው መገደላቸውን ባለስልጣናት ተናግረዋል። የክልሉ ባለስልጣን ድርጊቱን ሲያብራሩ “ፖሊስ አዛዡ የተገደለው በሥራ ቦታው ላይ ነው፤ የገደሉትም አብረውት የሚሰሩ ናቸው። ይሄ በጎጥ እና በዘር ተለይቶ የተፈጸመ በጣም አሳዛኝ ድርጊት ነው” ብለዋል።
ሌላኛው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የጸጥታ አመራር የነበሩ ምንጫችን በበኩላቸው፣ አዛዡና ምክትላቸው ከተለያዩ ጎሳዎች በመሆናቸው ግድያው ከአዛዡ ጀርባ በነበረ “ሴራ” የተፈጸመ እንደሆነ አመልክተዋል።
በከተማዋ ለተፈጠረው ቀውስ ዋነኛው ምክንያት የጸጥታ መዋቅሩ አባላት “በጎሳ ተከፋፍለው ግጭቱ ውስጥ መሳተፋቸው እንደሆነ” ሁለቱም ባለሥልጣናት አረጋግጠዋል።
የጸጥታ አመራሩ “ፖሊስ ሆነው ነገር ግን አማፅያን ሆነው ታጥቀው የሚዋጉ አባላት አሉ፤ ይሄ ደግሞ አይካድም” በማለት ገልጸዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ
https://addisstandard.com/Amharic/?p=10152
❤ 25😭 9👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በትግራይ ክልል ላይ የሚወሰዱ ኢኮኖሚያዊ እርምጃዎች እና የፕሪቶሪያ ስምምነት አፈፃፀምን በተመለከተ ሕወሃት አስቸኳይ ጉዳይ የሰጠው መግለጫ።
@Yenetube @Fikerassefa❤ 12👎 4👍 2😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌትናንት ጀኔራል ታደሠ ወረደ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ አቀኑ።
ጀኔራል ታደሠ የጊዜያዊ አስተዳደሩን ልዑካን ቡድን አስከትለው ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት፣ ባንዳንድ አጠቃላይ ጉዳዮች ዙሪያ ከፌዴራል መንግሥቱ ባለሥልጣናት ጋር ለመወያየት እንደኾነ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ማምሻውን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሠራጨው መረጃ ገልጧል።
[ዋዜማ]
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 27🔥 5😁 3
Photo unavailableShow in Telegram
🟦 LinkedIn rental
LinkedIn account አሎት እንግዲያውስ እኛ ጋር ሲመጡ👉
•100-299 connections: $8 በየሳምንቱ
• 300-499 connections: $13 በየሳምንቱ
• 500-999 connections: $15 በየሳምንቱ
• 1000-1999 connections: $20 በየሳምንቱ
• 2000+ connections: $25 በየሳምንቱ
📱በኢትዮጵያ ትልቁ እና ታማኙ የሊንኪደን አካውንት ተከራይ አሁንም በርካታ አካውንቶችን ተከራይቶ ለቢዝነስ አላማ ማስተዳደር ይፈልጋል።
📱ከፍተኛ ኮኔክሽን ወይም ረጅም አመት ያስቆጠሩ አካውንቶች የተሻለ ክፍያ ያገኛሉ፡፡
in የእርስዎን አካውንት ደህንነት እንደራሳችን አካውንት አድርገን እንጠብቀዋለን።
📱 የእርስዎን አካውንት ከማከራየት ጎን ለጎን ሰው በመጋበዝዎ ኮሚሽን እንከፍላለን
in ስምንት ወር እና 1ዐዐ ኮኔክሽን ዝቅተኛው መስፈርት ነው
📱 ጥራት ያላቸው አካውንቶች እንዲሁም ከ3ዐዐ+ በላይ የሆኑ አካውንቶች welcoming reward ወዲያውኑ ተፈፃሚ ይሆናል።
📱 ዝርዝር መረጃዎችን ከፈለጉ በዚህ አድራሻ ያለዎትን የኮኔክሽን እና የተከፈተበትን አመት
👤Contact Us Now:
📱: @Melech4
☎️: 0967033154
Our telegram channel 👉
https://t.me/linkedinrent255work
❤ 8🔥 2😁 2
