YeneTube
الذهاب إلى القناة على Telegram
2025 عام في الأرقام

107 335
المشتركون
-4624 ساعات
-3747 أيام
-2 08430 أيام
أرشيف المشاركات
በትምህርት ቤቶች ዉስጥ ሲከበሩ የሚታዩት እንደ Crazy Day፣ Gentle Day ፣ Oldies Day፣ Valentine Day፣ Color Day፣ Pyjama Day ከዚህ በኋላ እንዳይከበሩ ተከለከለ
ደንቡ የኢትዮጵያውያንን ባህልና ወግ የሚቃረኑ ተብለው በግልጽ የተዘረዘሩ አሉታዊ መጤ ድርጊቶችንና ክብረ በዓላትን በትምህርት ቤቶችና አካባቢ መፈጸም ሙሉ በሙሉ ይከለክላል።
የሀገሪቷን ባህልና ወግ ይቃረናል ከተባሉት ድርጊቶች ዉስጥ Crazy Day፣ Gentle Day ፣ Olds Day፣ Valentine Day፣ Color Day፣ Pyjama Day የሚሉት ይገኙበታል መባሉን ዳጉ ጆርናል ከካፒታል ዘገባ ተመልክቷል።
በተጨማሪም የትምህርት አዋኪ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ ግለሰቦች እና ተቋማት እስከ 150,000 ብር ቅጣት በአዲሱ ደንብ ይጠብቃቸዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ተቋማትና አካባቢያቸው የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያለመ አዲስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ ማውጣቱን አስታውቋል።
ይህ ደንብ ከኢትዮጵያውያን ወግና ልማድ ጋር ይቃረናሉ ተብለው የተለዩ የውጭ ባህላዊ ልማዶችን ጨምሮ፣ እየጨመረ የመጣውን አዋኪ ጉዳዮች ለመግታት ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።
የደንቡ ዋና ዓላማ በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የሚስተዋሉ አዋኪ ጉዳዮችን በመከላከል፣ ሁለንተናዊ ስብዕናው የተሟላ፣ በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፀና ግብረ-ገብነትን የተላበሰ ብቁ ትውልድ እንዲፈጠር ማስቻል ነው።
ትምባሆ (ሲጋራ፣ ሺሻ)፣ ጫት፣ አልኮል፣ የናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ ዝርያ ያላቸው አደገኛ ህገ ወጥ መድኃኒቶችና ሱስ አስያዥ ዕፆች በትምህርት ቤቶችና አካባቢ መገኘት፣ መጠቀም፣ መሸጥ፣ ማብቀል፣ ማምረት ወይም መለወጥ የተከለከለ መሆኑን አስታውቋል።
የአልኮል መሸጫና ማከፋፈያ ቤቶች፣ የሲጋራ መሸጫ ሱቆች፣ ሺሻ ቤቶች፣ ጫት መሸጫና መቃሚያ ቤቶች፣ ጭፈራ ቤቶች፣ ቁማር ቤቶች፣ የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች እና የሰውነት መታሻ (ማሳጅ) ቤቶች በአዲሱ ደንብ ተከለክለዋል።
እንዲሁም ፊልም ማጫዎቻ ቤቶች፣ ፕሌይ ስቴሽን ቤቶች፣ ዲ.ኤስ.ቲቪ ቤቶች፣ ከረንቡላ ፑል፣ ጆተኒ፣ ቢንጎ እና የስፖርት ቁማር መጫወቻ ቤቶችም እገዳ ከተጣለባቸው ድርጊቶች መካከል ዉስጥ ተካተዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 95👍 49👎 5😁 5
በትምህርት ቤቶች ዉስጥ ሲከበሩ የሚታዩት እንደ Crazy Day፣ Gentle Day ፣ Oldies Day፣ Valentine Day፣ Color Day፣ Pyjama Day ከዚህ በኋላ እንዳይከበሩ ተከለከለ
ደንቡ የኢትዮጵያውያንን ባህልና ወግ የሚቃረኑ ተብለው በግልጽ የተዘረዘሩ አሉታዊ መጤ ድርጊቶችንና ክብረ በዓላትን በትምህርት ቤቶችና አካባቢ መፈጸም ሙሉ በሙሉ ይከለክላል።
የሀገሪቷን ባህልና ወግ ይቃረናል ከተባሉት ድርጊቶች ዉስጥ Crazy Day፣ Gentle Day ፣ Olds Day፣ Valentine Day፣ Color Day፣ Pyjama Day የሚሉት ይገኙበታል መባሉን ዳጉ ጆርናል ከካፒታል ዘገባ ተመልክቷል።
በተጨማሪም የትምህርት አዋኪ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ ግለሰቦች እና ተቋማት እስከ 150,000 ብር ቅጣት በአዲሱ ደንብ ይጠብቃቸዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ተቋማትና አካባቢያቸው የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያለመ አዲስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ ማውጣቱን አስታውቋል።
ይህ ደንብ ከኢትዮጵያውያን ወግና ልማድ ጋር ይቃረናሉ ተብለው የተለዩ የውጭ ባህላዊ ልማዶችን ጨምሮ፣ እየጨመረ የመጣውን አዋኪ ጉዳዮች ለመግታት ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።
የደንቡ ዋና ዓላማ በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የሚስተዋሉ አዋኪ ጉዳዮችን በመከላከል፣ ሁለንተናዊ ስብዕናው የተሟላ፣ በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፀና ግብረ-ገብነትን የተላበሰ ብቁ ትውልድ እንዲፈጠር ማስቻል ነው።
ትምባሆ (ሲጋራ፣ ሺሻ)፣ ጫት፣ አልኮል፣ የናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ ዝርያ ያላቸው አደገኛ ህገ ወጥ መድኃኒቶችና ሱስ አስያዥ ዕፆች በትምህርት ቤቶችና አካባቢ መገኘት፣ መጠቀም፣ መሸጥ፣ ማብቀል፣ ማምረት ወይም መለወጥ የተከለከለ መሆኑን አስታውቋል።
የአልኮል መሸጫና ማከፋፈያ ቤቶች፣ የሲጋራ መሸጫ ሱቆች፣ ሺሻ ቤቶች፣ ጫት መሸጫና መቃሚያ ቤቶች፣ ጭፈራ ቤቶች፣ ቁማር ቤቶች፣ የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች እና የሰውነት መታሻ (ማሳጅ) ቤቶች በአዲሱ ደንብ ተከለክለዋል።
እንዲሁም ፊልም ማጫዎቻ ቤቶች፣ ፕሌይ ስቴሽን ቤቶች፣ ዲ.ኤስ.ቲቪ ቤቶች፣ ከረንቡላ ፑል፣ ጆተኒ፣ ቢንጎ እና የስፖርት ቁማር መጫወቻ ቤቶችም እገዳ ከተጣለባቸው ድርጊቶች መካከል ዉስጥ ተካተዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
Photo unavailableShow in Telegram
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ያለ ረዳት አገልግሎት የሚሰጡ የህዝብ ማመለሽ ተሽከርካሪዎችን እቀጣለሁ አለ።
ቢሮው ያለ ረዳት አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች በከተማዋ እየበዙ ነው ያለ ሲሆን ከዚህ በኋላ በመመሪያው መሰረት #ረዳት የሌላቸውን ታክሲዎች እቀጣለሁ ብሏል።
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ክትትልና ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ታመነ ያለ ረዳት ማሽከርከር ገንዘብ በመቀበል፣ ገቢና ወራጅ በመቆጣጠር የሹፌሩን ትኩረት ስለሚሰርቅ ለአደጋ ያጋልጣል ብለውናል።
ኃላፊው ከዚህ ቀደም ለሌሎች የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ብቻ ትኩረት በመስጠታችን ረዳት ያላቸውና የሌላቸውን ተሽከርካሬዎች የመለየት ውስንነት ታይቶብናል ብለዋል።
ከዚህ በኋላ ግን የታክሲ ረዳት መኖር አንዱ የትራፊክ ደህንነት አካል በመሆኑ ሁሉም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ላይ ክትትል እናደርጋለን ብለዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 41👍 18😁 3🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
"ከ10,900 በላይ ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ መንገድ ከሃገር ሊወጡ ሲሉ ተይዘዋል" - የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውጪ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት መሰረት በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት (ከሐምሌ - መስከረም) ፦
- አጠቃላይ 545,491 ፓስፖርት ለዜጎች መሰጠቱን ገልጿል።
- ከአጠቃላይ ለ373,000 በላይ ዜጎች መደበኛ፣ ከ136 በላይ ለሚሆኑት አስቸኳይ ፣ ከ14,000 በላይ ኢ-ፓስፖርት እንዲሁም ከ20,000 በላይ ለሚሆኑት ደግሞ በቆንጽላ በኩል አገልግሎት ያገኙ ናቸው።
- ከ3400 በላይ የውጪ ዜጎች ወደ ሃገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ሲሆን ከ10,900 በላይ ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ መንገድ ከሃገር ሊወጡ ሲሉ ተይዘዋል።
- ከሰጠው አገልግሎት 11 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 10.5 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል።
- ሃሰተኛ የጉዞ ሰነድ ያቀረቡ 860 ኢትዮጵያውያንና የውጪ ሃገር ዜጎች ተጠያቂ ተደርገዋል፤
- 96 የውጭ ሀገር ዜጎች የተጭበረበረ የጉዞ ሰነድ ሲጠቀሙ ተይዘዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 19👍 5😁 2👀 2😭 1
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰራተኛ ምዘናና ምደባ ሊያካሄድ ነው
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰራተኛ ምዘና እና ምደባ ሊያካሂድ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ዩኒቨርሲቲው የሰራተኛ ቅነሳ ሊያደርግ እንደሆነ የተሰራጨው መረጃም ትርጉም የማይሰጥ መሆኑንም አመላክተዋል።
ዩኒቨርሲቲው የ75ኛ ዓመት አልማዝ ኢዮቤልዩ አከባበር እና የራስገዝነት ሪፎርም አፈፃፀምን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
በዚህም ወደ ራስገዝነት የሚያደርገው ሽግግር የእስካሁን ጉዞ፤ ሥራው የደረሰበትን ደረጃ እና ቀጣይ ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በዚሁ ወቅት ሳሙኤል (ዶ/ር) እንደገለፁት፤ የሠራተኞች ምደባና ሥምሪት ማስፈፀሚያ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ፣ ውይይት ተደርጎበት ወደ ሥራ ገብቷል፡፡
በዚህም የሰራተኛ መልሶ ሥምሪትና ምደባ የሚከናወንበት የጊዜ ሰሌዳ ፀድቆ ለሚመለከታቸው አካላት ተልኳል ያሉት ተጠባባቂ ፕሬዚዳንቱ፤ ለሰራተኞች መመዝገቢያና የመረጃ ማጥሪያ ኦንላይን ፎርም ተዘጋጅቶ ምዝገባ ተከናውኗል ብለዋል፡፡
እንደ ሳሙኤል (ዶ/ር) ገለጻ፤ ከደረጃ 08 በላይ ላሉት አንድ ሺህ 500 ለሚደርሱ የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች ፈተና በመስጠት ብቃትና ውጤታማነትን ማዕከል በማድረግ ምደባ ይሰጣል፡፡
ሌሎች ከደረጃ 08 በታች ላሉ የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች በሰነድና በነበራቸው የግምገማ ውጤት በውድድር ምደባ እንደሚሰጥ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንቱ አመላክተዋል፡፡
እንዲሁም የአካዳሚክ ሰራተኞች፣ ተመራማሪዎች፣ የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳቶች እና በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጤና ሙያተኞች በውድድር ላይ የተመሰረተ ልየታ በማድረግ ስምሪት እንደሚሰጥም ተናግረዋል፡፡
ተጨማሪ የሰው ኃይል በሚያስፈልግበት ቦታ ላይ የተዘጋጀውን የመውጫ ስትራቴጂ በመመርኮዝ ወደ ስራ የማስገባት ተግባር እንደሚከናወንም ጨምረው ገልጸዋል።
ተጠባባቂ ፕሬዚዳንቱ ጋዜጠኞች ዩኒቨርሲቲው ሰራተኞቹን ሊቀንስ ነው ተብሎ የተሰራጨውን መረጃ በሚመለከት ላቀረቡላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡም፤ የተሰራጨው መረጃም “ትርጉም የማይሰጥ” ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አክለውም በዩኒቨርሲቲው 4 ሺህ የአስተዳደር ሰራተኞች ያሉ መሆኑን ጠቅሰው፤ እነሱም በተዘጋጀው የሰራተኛ ስምሪት ማዕቀፍ መሰረት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አንስተዋል።
በዩኒቨርሲቲው በሁሉም መዋቅሮች “በቂ ሰራተኛ አለ ማለት ሁሉም ይቀጥላሉ ማለት አይደለም፤ በቅድሚያ ብቃት ያላቸው ሰራተኞች ቦታውን መያዝ አለባቸው” ብለዋል፡፡
Via :- ጋዜጣ_ፕላስ
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 42👎 8👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና ሩሳል ኩባንያ በ ኢትዮጵያ 500,000 ሜትሪክ ቶን የማምረት አቅም ያለው የአሉሚኒየም ማቅለጫ ለመገንባት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ!
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በ ኢትዮጵያ ውስጥ መጠነ-ሰፊ የአሉሚኒየም ማቅለጫ ፋብሪካ ለማቋቋም የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነትን በዓለምአቀፍ ደረጃ ግዙፍ የአልሙኒየም አምራቾች መካከል አንዱ ከሆነው የሩሲያው ሩሳል ኩባንያ ጋር ተፈራርሟል።
ፋብሪካው በየዓመቱ 500,000 ሜትሪክ ቶን የማምረት አቅም ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ኢትዮጵያን በቀጠናዊና በዓለምአቀፍ የአሉሚኒየም ገበያዎች ተወዳዳሪ አቅራቢ እንድትሆን እንደሚያደርጋት ተጠቁሟል።
ፕሮጀክቱ እያደገ የመጣውን የሀገር ውስጥ ፍላጎት ለማሟላት፣ የኢንዱስትሪ ልማትን ለመደገፍ፣ እንዲሁም በአሁኑ ጊዜ አሉሚኒየምን ወደ ሀገር ማስገባት ሂደት ወቅት የሚያስወጣውን የውጭ ምንዛሪ ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ ያለመ ነው ተብሏል።
ይህ የተገለፀው ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በዩሮኤዥያ ቀዳሚ የዲጂታል መድረክ በሆነው ዋይልድ ቤሪስ መካከል የኢትዮጵያን የኢ-ኮሜርስ እና የዲጂታል መሠረተ ልማት ልማት ለማፋጠን ከተፈረመው የአጋርነት ስምምነት በኋላ ነው።
እንደ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ መረጃ መሠረት፣ የአሉሚኒየም ፋብሪካ ግንባታው ከሦስት እስከ አራት ዓመታት ይጠናቀቃል የተባለ ሲሆን፣ ለ50 ዓመታት ያህል አገልግሎት እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
Photo unavailableShow in Telegram
የቀድሞው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የዩክሬይን ጦር መሳሪያ ማምረቻ ተቋም አማካሪ ሆኑ፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ማይክ ፖምፒዮ ለበርካታ አመታት በዲፕሎማሲ ስራ ላይ ተሰማርተው የቆዩ ናቸው፡፡
ቀደም ሲል የአሜሪካ የስለላ ተቋም (ሲአይኤ) ሀላፊ የነበሩት ፖምፒዮ 70ኛው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን የትምህርት ዝግጅታቸውም በህግ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
ዛሬ እንደተሰማው ግን እኚህ የ61 አመቱ አንጋፋ የቀድሞ ባለስልጣን ‹‹ከዲፕሎማሲ ወደሚሳኤል›› ተሸጋግረዋል፡፡ ማይክ ፖምፒዮ የዩክሬይን ረጅም ርቀት ሚሳኤል ማምረቻ የሆነው ፋየር ፖይንት ፋብሪካ አማካሪ ቦርድ አባል መሆናቸውን አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ ፋየር ፖይንት ማለት ሩሲያ ውስጥ ዘልቀው በመግባት ጥቃት መፈፀም የሚችሉ ሚሳኤሎችን የሚያመርት ሲሆን በዚህ ፋብሪካ ከተመረቱት ውስጥ ፍላሚንጎ የተሰኘው ሚሳኤል አንዱ ነው፡፡
ፍላሚንጎ እስከ 3 ሺ ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት መጓዝ የሚችል እንደሆነ የተገለፀለት ሲሆን ባለፈው ሳምንት ይህንን ሚሳኤል ሩሲያ ላይ መሞከራቸውን ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 22👎 7😁 1
የቀድሞው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የዩክሬይን ጦር መሳሪያ ማምረቻ ተቋም አማካሪ ሆኑ፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ማይክ ፖምፒዮ ለበርካታ አመታት በዲፕሎማሲ ስራ ላይ ተሰማርተው የቆዩ ናቸው፡፡
ቀደም ሲል የአሜሪካ የስለላ ተቋም (ሲአይኤ) ሀላፊ የነበሩት ፖምፒዮ 70ኛው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን የትምህርት ዝግጅታቸውም በህግ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
ዛሬ እንደተሰማው ግን እኚህ የ61 አመቱ አንጋፋ የቀድሞ ባለስልጣን ‹‹ከዲፕሎማሲ ወደሚሳኤል›› ተሸጋግረዋል፡፡ ማይክ ፖምፒዮ የዩክሬይን ረጅም ርቀት ሚሳኤል ማምረቻ የሆነው ፋየር ፖይንት ፋብሪካ አማካሪ ቦርድ አባል መሆናቸውን አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ ፋየር ፖይንት ማለት ሩሲያ ውስጥ ዘልቀው በመግባት ጥቃት መፈፀም የሚችሉ ሚሳኤሎችን የሚያመርት ሲሆን በዚህ ፋብሪካ ከተመረቱት ውስጥ ፍላሚንጎ የተሰኘው ሚሳኤል አንዱ ነው፡፡
ፍላሚንጎ እስከ 3 ሺ ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት መጓዝ የሚችል እንደሆነ የተገለፀለት ሲሆን ባለፈው ሳምንት ይህንን ሚሳኤል ሩሲያ ላይ መሞከራቸውን ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
Photo unavailableShow in Telegram
እንጀራ በሸቀጣ ሸቀጦች ሱቅ መሸጥ ተከለከለ
የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣንን የተለያዩ ሸቀጣሸቀጦች በሚሸጡባቸው ሱቆች ውስጥ እንጀራ መሸጥ ተከለከለ።
የባለስልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ እንጋ እርቀታ የተለያዩ መርዛማ ነገሮች ሳሙና እና ለጤና ጠንቅ የሆኑ ሸቀጦች በሚሸጡባቸው ሱቆች በቀጥታ ለምግብነት የሚውሉትን እንጀራ እና ዳቦን መሸጥ ልክ ባለመሆኑ ለመከልከል መገደዳቸውን ተናግረዋል ሲል ነው ዘገባው የጠቀሰው።
እንጀራ እና ዳቦ መሸጥ ያለባቸው በምግብ ቤቶች፣ በዳቦ ቤተች እና በባልትና ወይም ለዚሁ መሻጫነት በተፈቀደ ቦታ ብቻ መሆኑንም በማንሳትም ያልተፈቀደላቸው ነጋዴዎችም ሲሸጡ ከተገኙ አስፈላጊው የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስገንዝበዋል ሲል ገልጿል።
Vai:- AMN
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 62😁 30👍 10👎 5
Photo unavailableShow in Telegram
የፓርቲዎች የእጩ ምዝገባ ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የእጩ ምዝገባ ከዛሬ ጀምሮ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ::
የግል ዕጩዎች ምዝገባ የሚጀመርበት ጊዜ በቀጣይ ይፋ እንደሚሆንም ጠቁሟል።
ምርጫ ቦርድ በጠቅላላ ምርጫ ለሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ባደረገው ጥሪ እጩዎቻቸውን ቦርዱ በገለጸው ሲስተም ተጠቅመው እንደሚያስመዘግቡ ጥሪ አቅርቧል።
ምዝገባውን ለማከናወን የሚያስችሉ አስፈላጊ መረጃዎችን በማሟላት ከህዳር 8 እስከ ህዳር 23 ቀን 2018 ምዝባው ይካሄዳል
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 21😁 4👎 3👍 2
በነዳጅ ምርቶች ላይ የተጣለዉ አጠቃላይ የ30 በመቶ ግብር በቀጣይ ወር ተግባራዊ እንደሚሆን ተገለፀ
የኢትዮጵያ መንግሥት ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን የነዳጅ ድጎማ ቀስ በቀስ ለማስወገድ ከሚወስዳቸው ሰፋፊ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች አንዱ የሆነው አዲስ የግብር አወቃቀር ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ተግባራዊ ሊሆን ነው።
ይህ አዲስ እርምጃ በነዳጅ ምርቶች ላይ 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና 15 በመቶ ኤክሳይዝ ቀረጥን ያካተተ አጠቃላይ 30 በመቶ ታክስ መጣል ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከአንድ ወር በኋላ ታክሱን መሰብሰብ ይጀምራል።
በአዲሱ መመሪያ መሠረት፣ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅቱ የተሰበሰበውን ግብር በሙሉ ለገቢዎች ሚኒስቴር ማስገባት ግዴታው ሲሆን፤ መንግሥት በዚህም እስከ ታኅሣሥ 2018 ዓ.ም ድረስ ለቤንዚንና ናፍጣ መሸጫ ዋጋዎች ሁሉንም ህጋዊ የግብር መጠን ጨምሮ ሙሉ ወጪን የመሸፈን ግብ ላይ ለመድረስ አቅዷል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ከአዲሱ በጀት ዓመት ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች ላይ አጠቃላይ 30 በመቶ ግብር ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሊያደርግ ማቀዱን ከሁለት ወራት በፊት መዘገቡን አስታዉሶ ካፒታል አስነብቧል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
👎 37❤ 24😭 8😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
የጂንካ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ለመገናኛ ብዙሀን መረጃ መስጠታቸውን ተከትሎ ከሀላፊነታቸው ተነሱ!
የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር በአካባቢው ስለተከሰተው “የሔሞሬጂክ ፊቨር” እንደሆነ በተገመተው ተላላፊ በሽታ ሰዎች መሞታቸውን ገልፀው ለመገናኛ ብዙሀን መረጃ መስጠታቸውን ተከትሎ ከሀላፊነታቸው ተነሱ።
ዋዜማ ከደቡብ ክልል ጤና ቢሮና ከሆስፒታሉ ምንጮች እንደሰማችው የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ቢንያም አስራት ለአንድ አለማቀፍ ሚዲያ “የሔሞሬጂክ ፊቨር” እንደሆነ በተገመተው በሽታ ሳቢያ ሀኪሞችን ጨምሮ ሰዎች መሞታቸውን ገልፀው መረጃ በመስጠታቸው ከሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ምስጢሩ ሐምደኪ በተጻፈ ደብዳቤ ከሕዳር 5 ቀን 2028 ዓ.ም ከሀላፊነታቸው መነሳታቸው ተነግሯቸዋል።
ዳይሬክተሩ ከሃላፊነት ከመነሳታቸው በፊት ወደ ሆስፒታሉ መጥተው ከታከሙት አራት በሽተኞች አንዱ በህይወት እንዳለ እና የተሻለ የሚባል የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልፀው ሁለት የሆስፒታላቸው የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ እስካሁን ስድስት ሰዎች ተመሳሳይ ምልክቶችን በማሳየት ህይወታቸው ማለፉን ለዶቸ ቨለ ራዲዮ በይፋ ገልፀው ነበር።
https://cutt.ly/5teYmr83
@YeneTube @FikerAssefa
😭 74❤ 23👀 6👍 3
ይድረስ ለየኔቲዩብ
በሶማሌ ብሔራዊ ክልል በሚሠሩ የጤና ባለሙያዎች እየተፈፀሙ ያሉ በደሎች
ክፍል 1
የሶማሌ ክልል በሥሩ ከ18 በላይ ሆስፒታሎች ፣ 40 በላይ ጤና ጣቢያዎች እና በርካታ ጤና ኬላዎች አሉት። በእነዚህ የጤና ተቋማት የሚሠሩ በርከት ያሉ የጤና ባለሙያዎች አሉ። በክልሉ የሚሠሩ የጤና ሙያተኞች እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የመንግሥት ሠራተኛ በተለይ ደግሞ እንደ ጤና ባለሙያ የሚያነሷቸው በርካታ ጥያቄዎች አሏቸው።
የሶማሌ ክልል ከሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች በልዩነት የአየር ንብረቱ እንዲሁም የመሠረተ ልማት ዝርጋታው አስቸጋሪ እና ኋላቀር የሚባል ነው።
በክልሉ ያሉ የጤና ሙያተኞች ብዙ አስቸጋሪ ነገሮችን ታግሰው እየሠሩ ቢገኙም በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ የክልሉ ጤና ቢሮ እና በተዋረድ ያሉ የጤናው ዘርፍ አመራሮች በሠራተኛው ላይ ኅልቆመሳፍርት ግፎችን በመፈፀም ላይ ይገኛሉ። ከበደሎቹ በጥቂቱ ከደሞዝ እና ከሙያ እድገት ጋር የተገናኙትን እንጥቀስ፡-
1 . መንግሥት ለጤና ባለሙያዎች ያደረጋቸውን የደሞዝ ማሻሻዎች ተከትሎ ሊስተካከሉ የሚገባቸው የዲዩቲ እና የውሎ አበል ክፍያዎች አለመስተካከላቸው።
ሀ . ጥቅምት 2017 ዓ.ም ጀምሮ የደሞዝ ማስተካከያ ሲደረግ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ይከፈል የነበረው በአሮጌው ደሞዝ ነበር። ሠራተኛው በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም ከሚመለከታቸው አካላት አጥጋቢ ምላሽ አልተሰጠውም። ከዚህ በላይም ሠራተኛው ላይ ፍረጃ እና ለያይቶ ማጥቃትን ሲተገብሩ በተደጋጋሚ ታዝበናል። ጥያቄ የሚያነሱ ሙያተኞችን በማናለብኝነት ከቃል ማስጠንቀቂያ እስከ ማባረር የደረሱ እርምጃዎችን ሲወስዱ ታዝበናል።
ለ . በዚህ ዓመት ከመስከረም ወር ጀምሮ የተተገበረውን አዲሱን የደሞዝ ማሻሻያ ክልሉ መተግበር አልቻለም። እንደተለመደው የዲዩቲ ክፍያውን 2ቱንም ማሻሻዎች በመተው ሁለት እርከን ወደ ኋላ በመመለስ በድሮው እየከፈለ ይገኛል። በአዲሱ የደሞዝ ማሻሻያ መሠረትም የመስከረም ወር ተጨምሮ መከፈል ያለበት ክፍያ (Backpayment) ሳይጨመር ተከፍሏል። የክልሉ መንግሥት በተለይ የጤና ጥበቃ ቢሮው እና በሥሩ ያሉ ተቋማት ለሠራተኛው ክብር የሌላቸው (Disrespect) ፣ የሠራተኛውን የሥራ ወኔ የሚያጠፉ (Discourage) እንዲሁም ሠራተኛውን እንደ ባሪያ የሚያዩ እና ራስ ወዳድ (Slavery ideation and Selfish) ) - DDS ናቸው። እኛ የጤና ሙያተኞች የሚከፈለን ክፍያ በቂ አይደለም በሚል ሀገራዊ ንቅናቄ ላይ ባለንበት ሁኔታ የሶማሌ ክልል በዚህ ልክ አግላይ እና ጨቋኝ ባይሆን መልካም ነበር።
2 . ሠራተኛው ለሥልጠና እና ለሌሎች ሙያዊ ጉዳዮች ሲወጣ የውሎ አበል አይታሰብም፣ የትራንስፖርት አገልግሎት የለም። የውሎ አበሉ በደሞዝ ደረጃ እና ሙያተኛው እንደተጓዘበት ከተማ እንደሚለያይ የፌደራል መንግሥቱ መመሪያ ይገልፃል። ሆኖም ግን በሶማሌ ክልል ውስጥ የሚሠሩ የጤና ሙያተኞች ለተደጋጋሚ እንግልት ሲዳረጉ ከአመራሮች ዘንድ አጥጋቢ ምላሽ አይሰጥም። የሠራተኛውን ቅሬታ ለማድመጥም ፈቃደኛ አይደሉም።
3 . ለጤና ሙያተኞች የሥራ ልምድ ደብዳቤ በሁሉም የክልሉ የጤና ተቋማት ማለት በሚያስችል ሁኔታ አይሰጥም። የጤና ሙያተኛው የሥራ ልምድ ደብዳቤ የማግኘት ሕጋዊ መብት እያለው በክልሉ ያሉ የጤና ዘርፍ አመራሮች ግን ለየትኛውም ሙያተኛ የሥራ ልምድ ደብዳብዴ ለመስጠት ፈቃደኞች አይደሉም።
ሀ . ሠራተኛው ሕጋዊ ዝውውር እንዲያደርግ አይፈቅዱም።
ለ . ሠራተኛው በሕጋዊ መንገድ ከሚሠራበት የጤና ተቋም መልቀቅ አይችልም።
ሐ . የጤና ሙያተኛው የደረጃ እድገት በጊዜ እንዳያገኝ እና የሙያ እድገቱን ተከትሎ የደሞዝ ማሻሻያ ባለማድረግ።
መ . በየጤና ተቋሙ በልዩ ልዩ ዘርፍ ኃላፊነት ላይ ያሉ ሙያተኞች የተመደበላቸውን ክፍያ ከመቀነስ እስከ መንፈግ የደረሰ ዓይን ያወጣ ዝርፊያ መኖሩ።
ክልሉ በማናለብኝነት ሠራተኛው ላይ እየፈፀመ ያለውን በደል የፌደራል መንግሥቱ ጣልቃ ገብቶ እንዲያስተካክልልን ስንል እንጠይቃለን።
የሶማሌ ክልል ጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ
❤ 47😭 9👍 7
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት፣ ነጻ የምርት ዝውውር ላይ መሰናክል የሚፈጥሩ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተቋቋሙ ሕገወጥ ኬላዎች በሙሉ እንዲነሱ ውሳኔ አሳለፈ።
የክልሉ መንግሥት፣ "ለታክስ"፣ "ለቀረጥ" እና "ለአካባቢ ልማት" በሚሉ ሽፋኖች በየመንደሩ እና በየመንገዱ የተቋቋሙ ሕገወጥ ኬላዎች በሙሉ መነሳት እንዳለባቸው መወሰኑን ዛሬ ዓርብ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሠራጨው መግለጫ ገልጧል።
ኬላዎች ምርቶች በነጻነት እና በተቀላጠፈ መንገድ ለገበያ እንዳይቀርቡ በማድረግ፣ ዜጎች በሥራቸው ልክ እንዳይጠቀሙ እንቅፋት ሆነው ቆይተዋል ያለው የክልሉ መንግሥት፣ ይህ ውሳኔ የክልሉ አርሶ አደሮች እና ነጋዴዎች ምርታቸውን ያላንዳች እንቅፋት እና ተጨማሪ ወጪ በቀጥታ ለገበያ እንዲያቀርቡ ዕድል በመፍጠር የክልሉን እና የአገሪቱን ኢኮኖሚ የማሳደግ ዓላማ እንዳለው ገልጧል።
ከእንግዲህ በክልሉ ውስጥ በሕግ የተፈቀዱ ኬላዎች፣ የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል እና ለጸጥታ ሥራ ሲባል አግባብ ባላቸው የክልሉ ወይም የፌዴራል መንግሥት አካላት ተፈቅደው የተቋቋሙ ኬላዎች ብቻ ይሆናሉ እንደሚኾኑ የክልሉ መንግሥት አስታውቋል።
ይህንኑ ውሳኔ ተግባራዊ የማያደርጉ የክልሉ የመንግሥት መዋቅሮች፣ የሥራ ኃላፊዎች እና ሌሎች ተዋናይ አካላት በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ የክልሉ መንግሥት በዚህ መግለጫው አስጠንቅቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 65😁 3
የክብር ዶክትሬትን በመጠሪያነት መጠቀም አይቻልም - የትምህርት ሚኒስቴር
የህዝብ ተወካዮች የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት የትምህርት ዘርፉን የ1ኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀም ተመልክቷል።የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዚሁ ወቅት፥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን የወጥነት ችግር እንደነበረበት አንስተዋል።
በክብር ዶክትሬት አሰጣጡ ወጥ አሠራር መከተል በማስፈለጉ ሀገራዊ መመሪያ ተዘጋጅቶ ለትግበራ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም ከዚህ በኋላ ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን በመመሪያው መሠረት መፈጸም እንደሚኖርባቸው ጠቁመዋል።የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ለመስጠት በመመሪያው የተቀመጡ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው ብለዋል።
በሙያው የተለየ ሥራ ያበረከተ ኢትዮጵያዊም ሆነ ሌላ ዜጋ በመመሪያው የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ማግኘት እንደሚችል ገልጸዋል።ይሁን እንጂ የተሰጠውን የክብር ዶክትሬት ለመጠሪያነት መጠቀም እንደማይቻል ተናግረዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 42😁 32👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
የጤና ሚኒስቴር ተከናዉኗል ባለዉ የዘረመል ምርመራ፣ ቀደም ሲል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጅንካ ከተማ መከሰቱ የተገለጸው የሄሞራጅክ ፊቨር በሽታ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) መሆኑን ማረጋገጡን አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ተደርጓል ባለዉ ምርመራ ከቀናት በፊት በበሽታዉ መጠርጣራቸዉን ካሳወቀዉ 8 ሰዎች ዉጪ አዲስ በበሽታው የተጠረጠረ አለመገኘቱን ገልጿል።
ቫይረሱን የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራዎችን ለማጠናከር የተለያዩ የሙያ ስብጥር ያካተተ ከፍተኛ ፈጣን ምላሽ ሰጭ ቡድን ወደ ክልሉ መላኩን ጠቁሟል።
በምርመራው መሰረት፣ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ የተገኘው የቫይረስ ዝርያ ከዚህ በፊት በሌሎች ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ላይ ከተከሰቱት ጋር ተመሳሳይ ዝርያ ያለው መሆኑ ታውቋል።
ይህን ተከትሎ በሃገር አቀፍ እንዲሁም በክልል ደረጃ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች የክስተት አስተዳደር ስርዓት (IMS) ተቋቁሞ የምላሽ ስራዎች እየተስተባበሩ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል።
በ ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም የሚመራዉ የአለም ጤና ድርጅት በጂንካ አካባቢ የተከሰተውን ወረርሽኝ ለመከላከል 300 ሺህ ዶላር ከድርጅቱ አስቸኳይ ፈንድ በኩል መልቀቃቸውን መግለፃቸው ይታወሳል።
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 45👍 3🔥 2😭 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኤርትራን "የግዛት አንድነት ጥሰቶች" በተመለከተ መንግሥት የያዘው "የመታቀብ" አቋም "ሁሌም እንደማይቀጥል" ዶ/ር ጌዲዮን አሳሰቡ!
ኤርትራ በኢትዮጵያ "ሉዐላዊነት እና የግዛት አንድነት" ላይ የምትፈጽማቸው "ጥሰቶችን" በተመለከተ የፌደራል መንግሥት የያዘው እርምጃ ከመውሰድ "የመታቀብ" አካሄድ "ሁሌም የሚቀጥል እና ገደብ የለሽ ተደርጎ መወሰድ እንደሌለበት" የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተናገሩ።
ዶ/ር ጌዲዮን፤ ኢትዮጵያ "ከኤርትራ መገንጠል በፊት እና በኋላ" በአሰብ ወደብ ላይ "ባፈሰሰችው ከፍተኛ ሀብት ምክንያት"፤ አሰብ በፌደራል መንግሥት "በዋነኛነት ቅድሚያ የሚሰጠው" ጉዳይ እንደሆነ መግለጻቸውም ተዘግቧል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ይህንን የተናገሩት ትናንት ሐሙስ ኅዳር 4/2018 ዓ.ም. "ሆርን ሪቪው" የተባለው ቲንክ ታንክ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ባካሄደው የፖሊሲ ፎረም ላይ ነው።
ዶ/ር ጌዲዮን፤ አምባሳደሮችን ጨምሮ የተለያዩ አገራት ዲፕሎማቶች በታደሙበት በዚህ መድረክ ላይ በአፍሪካ ቀንድ የታዩ ሰሞነኛ ሁኔታዎች በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥትን ፖሊሲ እና ምልከታ አቅርበዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገለጻ በተለይም ያተኮረው በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነት ላይ ነው።በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ለዘመናት የዘለቀው ግጭት መነሻ ከድንበር ውዝግብ ወይም ከባህር በር ፍላጎት የተሻገረ መሆኑን እንዳብራሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረ ገጹ ባወጣው የዶ/ር ጌዲዮን ሙሉ ንግግር ላይ ሰፍሯል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cn405yzj780o
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 39😁 10👎 4👍 3🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
በ #ኢትዮጵያ 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች የስኳር በሽታ ታማሚ መሆናቸው ተገለፀ
በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች ከስኳር ሕመም ጋር ይኖራሉ ሲል የኢትዮጵያ ስኳር ሕመም ማህበር ገለፀ።
የማህበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጌታሁን ታረቀኝ÷ የስኳር ሕመም በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለፉት ዓመታት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያም በስኳር ሕመም የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ገልፀው÷ በተለይም ትክክል ባልሆነ የአኗኗር ዘይቤ ሳቢያ የሚከሰተው አይነት ሁለት የስኳር ሕመም እየተስፋፋ መምጣቱን አመልክተዋል፡፡
በዚህም በኢትዮጵያ እድሜያቸው ከ20 እስከ 79 ዓመት የሆኑ ከ2 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ሰዎች ከስኳር ሕመም ጋር አብረው እንደሚኖሩ መረጃዎች ያመላክታሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም በአሁኑ ጊዜ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ውስጥ የስኳር ሕመም በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ ያደርገዋል ያሉት ዶ/ር ጌታሁን÷ ወደፊትም የታማሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምር መረጃዎች ያመላክታሉ ብለዋል፡፡
ጤናማ የሆነ የአኗኗር ዘይቤን በመከተል አይነት 2 የስኳር ሕመምን እስከ 80 በመቶ መከላከል እንደሚቻል ገልፀው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ እና አመጋገብን ማስተካከል በተለይም ልጆች የሚመገቡትን በፋብሪካ የተቀነባበሩ ከፍተኛ የስኳርና ስብ መጠን ያላቸውን ምግቦች መቀነስ እንደሚገባ መግለጻቸውን የዘገበው ኤፍ ኤም ሲ ነው፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 22😭 9
የኡጋንዳ የወደብ ጥያቄ
ለ8ተኛ ጊዜ ለፕሬዝደንትነት እየተወዳደሩ የሚገኙት የኡጋንዳው መሪ ሙሴቪኒ አገሬ ወደብ ያስፈልጋታል ማለታቸው ኬንያን እጅግ አስቆጥቷል::
ከኡጋንዳ ዋና ከተማ 1,134 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውን የኬንያውን ሞንባሳ ወደብ የምትጠቀመው ኡጋንዳ ህንድ ውቅያኖስን በኬንያ ምክንያት ልጠቀም አልቻልኩም የሚል ቅሬታ በማቅረቧ ኬንያ ቁጣዋን እየገለፀች ነው።
ሙሴቬኒ በቅርቡ ባደረጉት ንግግር ወደብ የሌላቸው ሀገራት ጦርነት ሊያነሱ ይችላሉ ሲሉ ተደምጠዋል።
የሚሴቪኒ ልጅ የሆነው ጄነራል ሙሁዚ የአባቴን ሀሳብ እጋራለሁ ብለዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 38😁 11
Photo unavailableShow in Telegram
ናይጄሪያ ለልጆች በአፍ መፍቻ ቋንቋ የሚሰጠውን ትምህርት አስቀርታ በእንግሊዝኛ ተካች
የናይጄሪያ መንግሥት የመጀመርያ ደረጃ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ የሚያዘውን አወዛጋቢ ፖሊሲ መሰረዙን አስታወቀ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ቱንጂ አላኡሳ ከሦስት ዓመት በፊት ተግባር ላይ የዋለው ይህ ፕሮግራም የታለመለትን ግብ ስላልመታ ከአሁን ጀምሮ ጥቅም ላይ እንዳይውል ተወስኗል ብለዋል።
በዚያ ምትክ ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ድረስ እንግሊዘኛ የትምህርት መስጫ ቋንቋ ሆኖ ያገለግላል ብለዋል።
አሁን የተሰረዘው በአፍ መፍቻ እንዲማሩ የሚያዘው ፖሊሲ ሥራ ላይ የዋለው በቀድሞው የትምህርት ሚኒስትር አዳሙ አዳሙ ሲሆን፣ ሕጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ይበልጥ ይማራሉ ሲሉ ይከራከራሉ።
አዳሙ ሕጻናት "በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሲማሩ" ጽንሰ ሃሳቦችን በቀላሉ ለመረዳት ያስችላቸዋል ብለዋል።
ይህ የቀድሞው ሚኒስትር ሃሳብ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በቅድመ መደበኛ ትምህርት ላይ ባካሄዳቸው በርካታ ጥናቶች ላይም ተቀባይነት ያገኘ ነው።
የናይጄሪያ ትምህርት ሥርዓት በትምህርት ጥራት ማነስ፣ በቂ የሆነ የማስተማሪያ መሣሪያ ባለመኖር፣ በዝቅተኛ የመምህራን ደሞዝ እና በርካታ የትምህርት ማቆም አድማዎች በመካሄዳቸው ተግዳሮቶች ገጥሞታል።
በአገሪቱ ውስጥ 85 በመቶ የሚሆኑ ሕጻናት ወደ መጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት ቢሄዱም ሁለተኛ ደረጃን ግን የሚያጠናቅቁት ግማሽ ያህሉ ብቻ ናቸው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 41👍 18👎 8😁 3
