YeneTube
الذهاب إلى القناة على Telegram
2025 عام في الأرقام

107 362
المشتركون
-5724 ساعات
-4017 أيام
-2 12730 أيام
أرشيف المشاركات
ዛምቢያ ነፃ ትምህርትን በሕጋዊ መብትነት ለመደንገግ የትምህርት ሕግ ማሻሻያዎችን አስጀመረች
የቀረቡት ማሻሻያዎች እንዲጣሩ ለፍትሕ ሚኒስቴር ተላልፈዋል ሲሉ የትምህርት ሚኒስትር ዳግላስ ስያካሊማ ተናግረዋል።
"ነፃ ትምህርትን ተግባራዊ ማድረግ ለሀገሪቱ ያመጣቸውን ከፍተኛ ጥቅሞች አይተናል፡፡ እናም ይህ ፖሊሲ በሕግ እንዲደገፍ እንፈልጋለን" ብለዋል።🎒ከዚህ ቀደም በትምህርት ክፍያ የተገደበው የትምህርት ጥያቄ፤ በትምህርት ቤቶች በሚታየው የተማሪዎች ቁጥር መጨመር በግልጽ ይታያል ሲሉ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
"አሁን የምንፈልገው ጥራት ያለው የትምህርት አቅርቦት ማረጋገጥ ነው" ሲሉም አክለዋል።@Yenetube @Fikerassefa
❤ 16
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ደስ አለን።
ከ22 አመታት ብኃላ ኢትዮጵያን ለአፍሪካ ከ17 አመት በታች ዋንጫ ማሳለፍ ችላለች።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 18
Photo unavailableShow in Telegram
የአለም ጤና ድርጅት ለውፍረትእንደ ኦዜምፒክ ያሉትን የGLP-1 የስኳር በሽታ መድኃኒቶችን መጠቀምን መከረ
የዓለም ጤና ድርጅት ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ቢሊዮን ሰዎችን የሚያጠቃውን ውፍረት ለማከም ለስኳር በሽታ እና ክብደት ለመቀነስ የሚያገለግሉ የመድኃኒት ክፍልፋዮችን ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው ብሏል።
ከእነዚህ መድኃኒቶች አንዱ ኦዜምፒክ ነው።
ክብደት ለመቀነስ ይህን በመርፌ የሚወሰድ መድኃኒት የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።
የዓለም ጤና ድርጅት ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ኦዜምፒክ እና ዌጎቪ ያሉ መድኃኒቶች ለውፍረት ሕክምና እንዲታዘዙ እየመከረ ነው።
እነዚህ በመርፌ የሚወሰዱ መድኃኒቶች የደም ስኳር ቁጥጥርን ያሻሽላሉ፣ የምግብ ፍላጎትን ይቀንሳሉ እንዲሁም ክብደት ለመቀነስ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።
የመጀመሪያው የዓለም ጤና ድርጅት በግሉካጎን መሰል ፔፕታይድ-1 (GLP-1) ሕክምናዎች ላይ ያወጣው መመሪያ፣ ሴማግሉታይድን የመሰሉ መድኃኒቶችን የሚያካትት ሲሆን፣ ውፍረት ላለባቸው አዋቂዎች ይመክራቸዋል።
ፍትሐዊ ተደራሽነት እንዲኖር ያበረታታል እንዲሁም በአስፈላጊ መድኃኒቶች ዝርዝር ውስጥ ያካትታቸዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ይህ ሞዴል ዝርዝር በአሁኑ ጊዜ መሰረታዊ እና ሁለንተናዊ የጤና ስርዓት ለማግኘት ድርጅቱ አስፈላጊ ናቸው ብሎ የሚያምንባቸውን 532 ሕክምናዎች ይዟል።
ሰኞ ዕለት የጸደቀው የዓለም ጤና ድርጅት አቋም፣ የጤና ስርዓቶች የህዝብ ፖሊሲዎቻቸውን እንዲመሩ በመርዳት ለእነዚህ መድኃኒቶች ተደራሽነት እንዲሻሻል ያበረታታል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 21👀 4
በእሳት አደጋ የ3 ህፃናት ህይወት አለፈ!
በስልጤ ዞን በሚቶ ወረዳ፣ በሰሶ ቀበሌ፣ በቀጠና ሁለት ልዩ ስሙ አበልቾ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፣ በትላንትናው እለት 10:30 ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ ሦስት ህጻናት ህይወታቸው ማለፉ ተጠቆመ፡፡
የሚቶ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ሀላፊና የህዝብ ግንኙነት ተወካይ ረዳት ኢንስፔክተር ነጅሙዲን ዋበላ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት፤ ህፃናቶቹ በቆርቆሮ ቤት ውስጥ እየተጫወቱ በነበረበት ሰዓት በቦታው የነበረ ገለባ በእሳት በመያያዙ በውስጡ የነበሩ የ6 ዓመት ሁለት ወንድና ሴት መንታ ልጆች እና የ2 ዓመት ሴት ህፃን ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል፡፡
ህይወታቸው ያለፈው ህፃናት የታናሽና የታላቅ እህትማማች ልጆች ሲሆኑ፤ ከአያታቸው ጋር ነበር የሚኖሩት ተብሏል፡፡ የሁለቱ መንታ ልጆች እናት ህይወቷ ያለፈ ሲሆን፤ የ2 ዓመቱ ህፃን እናት ደግሞ ለስራ ውጭ አገር በመሄዷ ህፃናቱ በአያታቸው ቤት ይኖሩ እንደነበር ኢንስፔክተር ነጅሙዲን ዋበላ ተናግረዋል፡፡
የአደጋው መንስኤ ለጊዜው ባለመታወቁ ፖሊስ እያጣራ ሲሆን፤ የህፃናቱ አስከሬን ለምርመራ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል መላኩን ኢንስፔክተሩ ገልጸዋል፡፡
ወቅቱ በጋ ነፋሻማ በመሆኑ ድንገተኛ የእሳት አደጋዎች ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ኢንስፔክተር ነጅሙዲን ዋበላ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
😭 41❤ 21🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ምንም አይነት የማርበርግ ቫይረስ ታካሚ የለም ተባለ!
-በቫይረሱ ተይዘው ህክምና ላይ የነበሩ ሁለት ወጣቶች ከበሽታው አገገሙ
የጤና ሚንስቴር የማርበርግ ቫይረስ ሁኔታን አስመልክቶ ትላንት ባወጣው ዕለታዊ ሪፖርት የቫይረሱ ምንነት ከተረጋገጠበት ህዳር 5/ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ምንም አይነት የቫይረሱ ታካሚ አለመኖሩን አስታወቀ።
በዕለቱ ከተደርጉ 179 የላቦራቶሪ ምርመራዎች ቫይረሱ የተገኘበት ሰው አለመኖሩ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ቫይረሱ የተከሰተበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ደግሞ በቫይረሱ ተይዘው የህክምና ክትትል ሲደረግላቸው የቆዩ ሁለት ወጣቶች አገግመው ከህክምና ማዕከል መውጣታቸውን አስታውቋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ እንደገለፁት ሁለቱ ወጣቶች ቀደም ሲል በማርበርግ በሽታ ቫይረስ ተይዘው ህይወታቸው ካለፈ አባታቸው ጋር ንክኪ የነበራቸው ሲሆኑ የበሽታውን ምልክት አሳይተው የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው ቫይረሱ ስለተገኘባቸው የህክምና ክትትል ሲያደርጉ እንደነበር አስረድተዋል።
በዚህም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር በአጠቃላይ አራት የደረሰ ሲሆን እስካሁን በ667 ሰዎች ላይ በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው 12 ሰዎች መሆናቸው እና በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ደግሞ 8 ሰዎች መሆናቸው ይታወሳል።
በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በግምት ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆኑ የቫይረሱ መከላከያ ቁሳቁሶችን የማርበርግ ቫይረስ ለተከሰተበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አበርክቷል።
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 32😁 9👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
በመዲናዋ ግብር ከፋዮች ቅሬታ የሚያቀርቡበት አዲስ አሰራር ከፊታችን ሐሙስ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተባለ!
ከአዲስ አበባ የግብር አሰባሰብና የገቢዎች አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚኖረውን ማንኛውም አይነት ቅሬታ መፍታት የሚያስችል አዲስ አሰራር በከንቲባ ፅ/ቤት ሥር መዋቀሩ ተገልጿል።በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢዎች ቢሮ ሥር የተዘረጋው የቅሬታ አፈታት ስርዓት እንደተጠበቀ ሆኖ በዚያ ያልረካ ግብር ከፋይ ከንቲባ ፅ/ቤት ማንኛዉንም አይነት ከገቢ አሰባሰብ፣ ከሠራተኞች ሥነ-ምግባር እና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር የሚነሱ የግብር ከፋዮች ቅሬታዎችን ለመፍታት ዘወትር ሐሙስ ኃላፊዎች በተገኙበት የሚደመጥ እና ተጣርቶ ምላሽ የሚሰጥበትን አሰራር መዘርጋቱን ነው የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ፅ/ቤት ያስታወቀው።
በዚህም መሠረት በሚስጥር ጥቆማ የሚሰጥበትን ነፃ የጥሪ ማዕከል 9977 ፣ የሚስጥር ሳጥንን ጨምሮ በተጨባጭ ቅሬታዉን በአካል ለበላይ አመራር ማቅረብ የሚችልበትን አሰራር ወደ ተግባር ይገባል ተብሏል።
በመሆኑም ከመጪው ሐሙስ ሕዳር 25 ቀን 2018 ጀምሮ ጠዋት ከ 2 ሰዓት እስከ 7 ሰአት ድረስ ከገቢዎች ጋር ብቻ የተያያዘን ቅሬታ አመራሩ ተቀብሎ የሚስተናግድ መሆኑን በመረዳት፤ በከንቲባ ፅ/ቤት ተጨባጭ ቅሬታ ያላቸው ግብር ከፋዮቭ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን የከተማው አስተዳደር አስታውቋል።
Via Ahadu
@YeneTube FikerAssefa
❤ 19👎 10👍 4
Repost from YeneTube
Photo unavailableShow in Telegram
Summer realstate
በካሬ 73,318 ብር ብቻ
10% ቅድመ ክፍያ
50% ባንክ የተመቻቸላቸው
Location እንግሊዝ ኢምባሲ አጠገብ
✅ አፓርትመንቶች ቤቶች እንግሊዝ ኢምባሲ ደስ እሚል እይታ ያላቸው ቤቶች በሺያጭ ላይ ነን ከባለ 2 መኝታ - ባለ 4 መኝታ ደረስ
☑️ እስታንድ ባይ ጀኔኔትር
☑️5ሊፍት ያለው
☑️የዋና ገንዳ
☑️ፓርኪንግ
☑️ጅም, እስፓ ,ሚኒ ማርኬት,
☑️ቴራስ
✅ ባለ 2 መኝታ
134.6 ካሬ
137.6 ካሬ
155.6 ካሬ
✅ ባለ 3 መኝታ
183.8 ካሬ
156.9 ካሬ
197.8 ካሬ
✅ ባለ 4 መኝታ
260 ካሬ
ለበለጠ መረጃዎች
📞 0912355631
❤ 1
Repost from YeneTube
Photo unavailableShow in Telegram
አዲሱ #Kiwiday መተግበሪያ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው እና በአይነቱ ብቸኛው የሆነ ትምህርታዊመተግበሪያ ነው። ለ1ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ሁሉንም ነገር ያለዉ መተግበሪያ ነው። በአዲስ ሥርዓተ ትምህርት ላይ የተመሠረተ እና በአግባቡ ጥቅም ላይ ከዋለ የተማሪዎችን ውጤት ከ 75% በላይ እንደሚቀይር ባለሙያዎቻችን ይተነብያሉ።
✅ ለኦሮሚያ፣ ለአዲስ አበባ፣ ለአማራ እና ለሁሉንም ክልል ተማሪዎች
✅ ለወላጆች እና ለተማሪዎች የኪዊ አፈጻጸም ክትትል (KPT)
✅ ያለ ኢንተርኔት ለአንድ ሙሉ ዓመት ይሰራል
✅ አማርኛ / አፋን ኦሮሞ / እንግሊዝኛ ይጠቀማል
✅ ያልተገደበ የኪዊዴይ ፈተና (KQ) በየቀኑ
✅ የተደራጁ የኪዊ ማስታወሻዎች ፣ሁሉም የመማሪያ መጽሐፍት እና ማጣቀሻዎች
✅ አንድ መተግበሪያ = አንድ ተማሪ የሚያስፈልገውን ሁሉ የያዘ
✅ ቀላል፣ ፈጣን እና ተማሪዎች ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ያግዛል
✅ አስጠኚን ሊተካ የሚችል
✅ Free: 0 ብር ለ አንድ ዐመት
✅ Basic: 200 ብር ለ አንድ ዐመት
✅ Premium: 1000ብር ለአንድ ዐመት
ከGoogle Play ለማዉረድ ▶️https://play.google.com/store/apps/details?id=com.KiwiEducation.learningApplication
⚠️ለመጠቀም ከመጀመርዎ በፊት ወይም የሚፈልጓቸውን ነገሮች ካላገኙ፡ ‹የትምህርት ይዘቶችን› ን ተጭነው ያውርዱ።
ቻናላችንን ይቀላቀሉ በእነዚህ ያግኙን
Phone number: 0981333522
Telegram: https://t.me/Kiwidayapp
Website: www.kiwielearning.com
Tiktok: https://www.tiktok.com/@kiwidayapp
Youtube: https://www.youtube.com/@Kiwidayapp
#Education #Ethiopia
❤ 1😭 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሁለተኛዉ ሩብ ዓመት የውጭ ምንዛሪ ጨረታ መርሐ ግብር መሰረት መደበኛ የሆነውን የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ነገ ማክሰኞ፣ ህዳር 23፣ 2025 እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
ባንኩ በ11ኛው ዙር ጨረታ የዋጋና የውጭ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማስፈን በሚያደርገው ጥረት አካል ነዉ ያለዉን 50 ሚሊዮን ዶላር ለሽያጭ አቅርቧል።
ይህ የጨረታ መጠን በዘጠነኛዉ እና አስረኛዉ ዙር በየዕለቱ ቀርቦ ከነበረዉ 150 ሚሊዮን ዶላር አኳያ ዝቅተኛ መሆኑ ተመላክቷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ በፊት ህዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ፣ ለሶስተኛው ሩብ ዓመት የውጭ ምንዛሪ ጨረታ 420 ሚሊዮን ዶላር መመደቡንና በተጨማሪም በኅዳርና ታህሳስ ወር ለሚያካሂደው ጨረታ 100 ሚሊዮን ዶላር በመደመር፣ በአጠቃላይ 520 ሚሊዮን ዶላር ለመመደብ ማቀዱን አስታውቆ እንደነበር ይታወሳል።
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 18
Photo unavailableShow in Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ አምባሳደር በትረ መንግስቱን የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ዴኤታ አድርገው ሾመዋል።
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 29👎 11👍 6😁 2🔥 1
በትራፊክ አደጋ በአንድ ዶልፊን ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ 11 ሰዎች በሙሉ ሕይወታቸው አለፈ!
በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጉቢ ቦርደዴ ወረዳ በትናንት ሕዳር 20 ቀን 2018 ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በደረሠ የትራፊክ አደጋ አንድ ዶልፊን የጫናቸው አስራ አንድ ሠዎች ሕይወታቸው ማለፉን የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ አስታውቋል።
የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የትራፊክ ደሕንነት ና ቁጥጥር አስተባባሪ ምክትል ኢንስፔክተር ዳኙ ሶሪ ለአሐዱ እንደገለጹት፤ መነሻውን ከሚኤሶን ከተማ ያደረገ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-96835 ኦሮ ዳልፊን የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ዘጠኝ ተሣፋሪዎችን ጭኖ ወደ አዋሽ ከተማ ሲጓዝ በተቃራኒ መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ ሲጓዝ የነበረ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-A-11805 ኢቲ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴ ቁቢ ቦርደዴ ወረዳ ጨቱ ቀበሌ ፊለፊት በመጋጨታቸው አደጋው ተከስቷል።
በአደጋውም በዶልፊኑ ውስጥ የነበሩ አሽከርካሪውን ና ረዳቱን ጨምሮ የስምት ወንድ እና የሦስት ሴት በአጠቃላይ በሙሉ 11 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን ገልጸዋል።የአደጋው መንሴ የዶልፊኑ ተሽከርካሪ መስመሩን ለቆ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ በመግባቱ ና ፊለፊት ከነዳጅ ጫኝ ቦቴው ጋር ፊለፊት በመጋጨቱ ሲሆን፤ የነዳጅ ቦቴ አሽከርካሪው ለጊዜው መሠወሩን ምክትል ኢንስፔክተር ዳኙ ተናግረዋል።
ፖሊስ ከተሽከርካሪው ውስጥ የመንጃ ፈቃዱን ና ሌሎች መረጃዎችን በማግኘቱ ክትትላይ መሆኑንም ገልጸዋል።የሟቾች አስክሬን ለምርመራ ወደ ሆስፒታል የተላከ ሲሆን በአንድ አደጋ ሙሉ ተሣፋሪ ሕይወቱ ያለፈበት አጋጣሚ የተመዘገበ እንደሌለ ምክትል ኢንስፔክተር ዳኙ ሶሪ ጨምረው አስታውቀዋል።
Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
😭 73❤ 26😁 2
Repost from YeneTube
Photo unavailableShow in Telegram
Summer realstate
በካሬ 73,318 ብር ብቻ
10% ቅድመ ክፍያ
50% ባንክ የተመቻቸላቸው
Location እንግሊዝ ኢምባሲ አጠገብ
✅ አፓርትመንቶች ቤቶች እንግሊዝ ኢምባሲ ደስ እሚል እይታ ያላቸው ቤቶች በሺያጭ ላይ ነን ከባለ 2 መኝታ - ባለ 4 መኝታ ደረስ
☑️ እስታንድ ባይ ጀኔኔትር
☑️5ሊፍት ያለው
☑️የዋና ገንዳ
☑️ፓርኪንግ
☑️ጅም, እስፓ ,ሚኒ ማርኬት,
☑️ቴራስ
✅ ባለ 2 መኝታ
134.6 ካሬ
137.6 ካሬ
155.6 ካሬ
✅ ባለ 3 መኝታ
183.8 ካሬ
156.9 ካሬ
197.8 ካሬ
✅ ባለ 4 መኝታ
260 ካሬ
ለበለጠ መረጃዎች
📞 0912355631
❤ 4
Repost from YeneTube
Photo unavailableShow in Telegram
አዲሱ #Kiwiday መተግበሪያ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው እና በአይነቱ ብቸኛው የሆነ ትምህርታዊመተግበሪያ ነው። ለ1ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ሁሉንም ነገር ያለዉ መተግበሪያ ነው። በአዲስ ሥርዓተ ትምህርት ላይ የተመሠረተ እና በአግባቡ ጥቅም ላይ ከዋለ የተማሪዎችን ውጤት ከ 75% በላይ እንደሚቀይር ባለሙያዎቻችን ይተነብያሉ።
✅ ለኦሮሚያ፣ ለአዲስ አበባ፣ ለአማራ እና ለሁሉንም ክልል ተማሪዎች
✅ ለወላጆች እና ለተማሪዎች የኪዊ አፈጻጸም ክትትል (KPT)
✅ ያለ ኢንተርኔት ለአንድ ሙሉ ዓመት ይሰራል
✅ አማርኛ / አፋን ኦሮሞ / እንግሊዝኛ ይጠቀማል
✅ ያልተገደበ የኪዊዴይ ፈተና (KQ) በየቀኑ
✅ የተደራጁ የኪዊ ማስታወሻዎች ፣ሁሉም የመማሪያ መጽሐፍት እና ማጣቀሻዎች
✅ አንድ መተግበሪያ = አንድ ተማሪ የሚያስፈልገውን ሁሉ የያዘ
✅ ቀላል፣ ፈጣን እና ተማሪዎች ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ያግዛል
✅ አስጠኚን ሊተካ የሚችል
✅ Free: 0 ብር ለ አንድ ዐመት
✅ Basic: 200 ብር ለ አንድ ዐመት
✅ Premium: 1000ብር ለአንድ ዐመት
ከGoogle Play ለማዉረድ ▶️https://play.google.com/store/apps/details?id=com.KiwiEducation.learningApplication
⚠️ለመጠቀም ከመጀመርዎ በፊት ወይም የሚፈልጓቸውን ነገሮች ካላገኙ፡ ‹የትምህርት ይዘቶችን› ን ተጭነው ያውርዱ።
ቻናላችንን ይቀላቀሉ በእነዚህ ያግኙን
Phone number: 0981333522
Telegram: https://t.me/Kiwidayapp
Website: www.kiwielearning.com
Tiktok: https://www.tiktok.com/@kiwidayapp
Youtube: https://www.youtube.com/@Kiwidayapp
#Education #Ethiopia
❤ 4👍 3🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ቲክቶከሯ ዩቲናስ የገዛችውን መኪና አስመረቀች።
የመኪናው አሸናፊ አዶናይ ሆኗል እንኳን ደስ አለህ! ያለች ሲሆን ይህን መኪና እናንተ ኮፒ ሊንክ ባደረጋችሁት ማስታወቂያ ሰርቼ የገዛውት አመሰግናለሁ! ስለሆነውም ስላልሆነውም አላምዱሊላህ ብላለች።
@Yenetube @Fikerassefa
👍 105😁 58❤ 54😭 6👎 4👀 1
Photo unavailableShow in Telegram
ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ዩጋንዳ ኢትዮጵያን 3 ለ 0 አሸንፋለች።
ዩጋንዳ ለፍፃሜ ስትደርስ ኢትዮጵያ ለደረጃ ትጫወታለች።
@Yenetube @Fikerassefa
😁 19😭 11❤ 9👎 7🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
Summer realstate
በካሬ 73,318 ብር ብቻ
10% ቅድመ ክፍያ
50% ባንክ የተመቻቸላቸው
Location እንግሊዝ ኢምባሲ አጠገብ
✅ አፓርትመንቶች ቤቶች እንግሊዝ ኢምባሲ ደስ እሚል እይታ ያላቸው ቤቶች በሺያጭ ላይ ነን ከባለ 2 መኝታ - ባለ 4 መኝታ ደረስ
☑️ እስታንድ ባይ ጀኔኔትር
☑️5ሊፍት ያለው
☑️የዋና ገንዳ
☑️ፓርኪንግ
☑️ጅም, እስፓ ,ሚኒ ማርኬት,
☑️ቴራስ
✅ ባለ 2 መኝታ
134.6 ካሬ
137.6 ካሬ
155.6 ካሬ
✅ ባለ 3 መኝታ
183.8 ካሬ
156.9 ካሬ
197.8 ካሬ
✅ ባለ 4 መኝታ
260 ካሬ
ለበለጠ መረጃዎች
📞 0912355631
❤ 5
አዲሱ #Kiwiday መተግበሪያ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው እና በአይነቱ ብቸኛው የሆነ ትምህርታዊመተግበሪያ ነው። ለ1ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ሁሉንም ነገር ያለዉ መተግበሪያ ነው። በአዲስ ሥርዓተ ትምህርት ላይ የተመሠረተ እና በአግባቡ ጥቅም ላይ ከዋለ የተማሪዎችን ውጤት ከ 75% በላይ እንደሚቀይር ባለሙያዎቻችን ይተነብያሉ።
✅ ለኦሮሚያ፣ ለአዲስ አበባ፣ ለአማራ እና ለሁሉንም ክልል ተማሪዎች
✅ ለወላጆች እና ለተማሪዎች የኪዊ አፈጻጸም ክትትል (KPT)
✅ ያለ ኢንተርኔት ለአንድ ሙሉ ዓመት ይሰራል
✅ አማርኛ / አፋን ኦሮሞ / እንግሊዝኛ ይጠቀማል
✅ ያልተገደበ የኪዊዴይ ፈተና (KQ) በየቀኑ
✅ የተደራጁ የኪዊ ማስታወሻዎች ፣ሁሉም የመማሪያ መጽሐፍት እና ማጣቀሻዎች
✅ አንድ መተግበሪያ = አንድ ተማሪ የሚያስፈልገውን ሁሉ የያዘ
✅ ቀላል፣ ፈጣን እና ተማሪዎች ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ያግዛል
✅ አስጠኚን ሊተካ የሚችል
✅ Free: 0 ብር ለ አንድ ዐመት
✅ Basic: 200 ብር ለ አንድ ዐመት
✅ Premium: 1000ብር ለአንድ ዐመት
ከGoogle Play ለማዉረድ ▶️https://play.google.com/store/apps/details?id=com.KiwiEducation.learningApplication
⚠️ለመጠቀም ከመጀመርዎ በፊት ወይም የሚፈልጓቸውን ነገሮች ካላገኙ፡ ‹የትምህርት ይዘቶችን› ን ተጭነው ያውርዱ።
ቻናላችንን ይቀላቀሉ በእነዚህ ያግኙን
Phone number: 0981333522
Telegram: https://t.me/Kiwidayapp
Website: www.kiwielearning.com
Tiktok: https://www.tiktok.com/@kiwidayapp
Youtube: https://www.youtube.com/@Kiwidayapp
#Education #Ethiopia
7.23 MB
❤ 13👍 1🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሰበር
ከፋኖ ታጣቂ ኃይሎች መስራች እና ከፍተኛ አመራሮች መሀል አንዱ የሆነው ማስረሻ ሰጤ እጅ መስጠቱ እየተሰማ ነው።
አማራ ክልል ከመንግስት ጋር መሳሪያ አንስተው ግጭት ውስጥ ከገቡ የፋኖ መሪዎች መካከል ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ትናንት ምሽት እጁን ለመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የመስጠቱ ዜና ጭምጭምታ እየተሰማ ነው።
በፋኖ መዋቅር ራሱን የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት/አፋህድ) በማለት የሚጠራው አደረጃጀት ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ማስረሻ ሰጤ እና መሥፍን አባተ (መስፍን ከፈለኝን) ከአመራርነት ማገዱን አሳውቆ ነበር።
ከዚህ ዜና በኋላ ነው ማስረሻ እጁን ለመንግስት እንደሰጠ እየተሰማ ያለው። እንደተሰማው ጭምጭምታ ከሆነ ማስረሻ ከ18 ሰዎች ጋር ነው እጅ የሰጠው እየተባለ ነው።
@Yenetube @FikerAssefa
❤ 41😁 28🔥 2😭 2👍 1
