TIKVAH-ETHIOPIA
الذهاب إلى القناة على Telegram
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። መረጃ እና መልዕክት ፦ 0998999899 ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም 0979333111 @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
إظهار المزيد2025 عام في الأرقام

1 572 176
المشتركون
-51224 ساعات
-2 3697 أيام
-3 44030 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
ዛሬ የት የት አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ይቆረጣል ?
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጥገና ስራ ለማከናወን በአዲስ አበባ አፋር እና ሸገር አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ኃይል እንደሚቋረጥ አሳውቋል።
ከጠዋቱ 1፡30 እስከ 8፡00 ድረስ በበአዲስ አባበ መካኒሳ የኃይል ማካፋፊያ ጣቢያ ላይ የጥገና ስራ ለማከናወን ፦
- በላፍቶ ኢንዱስትሪ፣
- ሃና ማሪያም ቤ/ክ፣
- ሰፈራ ኮንዶሚኒየም፣
- አብርሃሙ ሥላሴ ቤ/ክ፣
- 72 ካሬ የማህበር ቤቶች፣
- ጀሞ 3 ኮንዶሚኒዬም፣
- ለቡ፣
- ጀሞ 1 ኮንዶሚኒዬም፣
- ካሳ ሳይት፣
- አርሴማ ቤ/ክ፣
- አፍሪካ ዱቄት ፋብሪካ፣
- ጅግጅጋ ሰፈር፣
- አንበሳ ገራዥ፣
- ቆሼ፣ ሱቂ ማሪያም፣
- ኃይሌ ጋርመንት፣
- ኦሮሚያ እና አዲስ አበባ ኮንዶሚኒዬም፣
- ተክለሃይማኖት፣
- ቫርኔሮ፣
- ስፖንጅ ፋብርካ፣
- ካፒታል ስሚንቶ፣
- ሁጃን ፋብሪካ፣
- ጀርመን አደባባይ፣
- ፊውቸር ትምህርት ቤት፣
- ፋሚሊ ወተት፣
- ለፍቶ መስቀለኛ፣
- ላፍቶ ቪው፣ እና አካባቢው ላይ የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡
በተመሳሰይ እስከ ቀን 6፡00 ድረስ በገፈርሳ የኃይል ማካፋፊያ ጣቢያ ላይ የጥገና ስራ ለማከናወን ሲባል ፦
• በጎልድ ውሃ፣
• ድሬ ዩኒቲ፣
• ሙገር ሲሚንቶ፣
• ኬብርን ፋብሪካ፣
• ቶፕ ውሃ፣ እና አካባቢው ላይ የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡
በአፋር ሎጊያ፣ ዱብቲ፣ ሚሌ፣ አሳይታ፣ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ ሰመራ እና እና አካባቢው ላይ የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡
#EEU
@tikvahethiopia
❤ 1 172🙏 67😢 62😡 59😭 52👏 20🕊 20🥰 19😱 17🤔 4
" በጎማ ንግድ ላይ በተሰማሪ ነጋዴዎች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ኦፕሬሽን 15 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል ! " - ገቢዎች ቢሮ
➡️ " በቀጣይ ቀናት በሌሎችም ዘርፎች ይቀጥላል! "
በአዲስ አበባ በተሽከርካሪ ጎማዎች ንግድ በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ በተካሄደ የታክስ ኦፕሬሽን በ11 የንግድ ድርጅት ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ 15 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አሳውቋል።
ቢሮው ዛሬው ዕለት #ድንገተኛ የኦፕሬሽን ተግባር ማካሄዱን ለዚህም ለረጅም ቀናት ጥናት ሲደረግ እንደነበር ገልጿል።
በቁጥጥር ስር የዋሉት 15 ከፍተኛ እና መካከለኛ የመኪና ጎማ የሚሸጡ ነጋዴዎች ናቸው ብሏል።
" ግለሰቦቹ ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ እጅ ከፍንጅ ተገኝተው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት " ያለው ቢሮው " የኦፕሬሽን ተግባሩ መርካቶን ጨምሮ በተመረጡ 12 የከተማዋ የጎማ መሸጫ ቦታዎች ላይ ነው የተከናወነው " ሲል ገልጿል።
የኦፕሬሽን ተግባሩ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት የተካሄደ መሆኑን አመልክቷል።
ያለደረሰኝ ሽያጭ በመፈፀም ወንጀል ተጠርጥረው የተያዙት ግለሰቦች ጉዳያቸው በፖሊስ ተይዞ ለፍርድ የሚቀርቡ ይሆናል ተብሏል።
በቀጣይ ቀናት ድንገተኛ የኦፕሬሽን ተግባር በሌሎችም ዘርፎች ላይ እንደሚኖር የገቢዎች ቢሆን አመልክቷል።
የንግዱ ማህበረሰብ ግብይቶችን በደረሰኝ ብቻ እንዲፈፅም አሳስቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
❤ 946😡 268😭 63🤔 48👏 42🙏 36😢 29🕊 21🥰 13💔 7
#Update
#Gambella
" በሁለት ቀናት እስከ 20 ሰዎች ተገድለዋል፣ በአንድ ወረዳ ብቻ። በሌሎችም አሉ። ከሁለት ቀናት በፊትም በአቦል ወረዳ ቁጥራቸው በትክክል ያልታወቁ በርካቶች ሞተዋል " - የጋምቤላ ነዋሪዎች
➡️ " በርካታ ቁስለኞች ወደ ህክምና ይላካሉ። በኛ ሆስፒታሉ የመጡት ብቻ ወደ 8 ይደርሳሉ። ጉዳት የደረሰባቸው ሦስት ሰዎች ወደ ጅማ ሪፈር ተደርገዋል" - በክልሉ በሚገኝ ሆስፒታል የሚሰሩ ሀኪም
በጋምቤላ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች በተለይ ከህዳር 30 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ በተፈጠረው የሰላም መደፍረስ የበርካታ ንጹሐን ህይወት እየተቀጠፈ መሆኑን የሟች ቤተሰብ፣ ነዋሪዎችና በሆስፒታል የሚሰሩ ሀኪም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
አንዳንዶቹ የሟቾችንና ቁስለኞችን ቁጥር "ከ50 እስከ 60" ያደረሱት ሲሆን፣ ሌሎቹ ደግሞ "ከዚያም የበለጠ ነው" ይላሉ። ከቀናት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ አንድ የክልሉ ባለስልጣን "የሟቾች ቁጥር ከ10 በላይ ሊሆን ይችላል" ብለው ነበር።
የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ማበር ኮር ደግሞ፣ ሰዎች መሞታቸውን አምነው፣ ብዛታቸው ግን "10 እንደማይሆን" ሰሞኑን ነግረውን የነበረ ሲሆን፣ ነዋሪዎችና ጤና ባለሙያዎች ዛሬ እንደነገሩን ከሆነ ደግሞ ጥቃቱ ባለመቆሙ የሟቾና ተጎጅዎች ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ ነው።
በሆስፒታል የሚሰሩ ሀኪምና ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?
ነዋሪዎቹ በሰጡን ቃል፣ "በሁለት ቀናት እስከ 20 ሰዎች ተገድለዋል በአንድ ወረዳ ብቻ። በሌሎችም አሉ። ከሁለት ቀናት በፊትም በአቦል ወረዳ ቁጥራቸው በትክክል ያልታወቁ በርካቶች ሞተዋል" ብለዋል።
የ27 አመት ወጣት በጸጥታው ችግር የተገደለባቸው ነዋሪ፣ "በጥይት ተመትቶ ነው ያረፈው። ብዙ መንገዶች ዝግ ስለሆኑ በጥይት የተመቱ ሰዎች ህክምና ሳያገኙ እየሞቱ ነው። ወደ ህክምና ለመሄድ ጭምር መንገድ ዝግ ናቸው" ሲሉ በሀዘን ስሜት ገልጸዋል።
ሌሎች ነዋሪዎችም፣ በርካቶች ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውን ገልጸው፣ "የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ገብተው ጥቃት እያደረሱ ነው" የሚሉ መረጃዎች እየሰሙ መሆኑንም ተናግረዋል። የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ደግሞ “ውሸት ነው” ሲል ሰሞኑን መግለጹ ይታወሳል። ሌላኛው ለቲክቫህ ኢትየጵያ ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪ ደግሞ፣ "እርስ በእርሳችን ነው የተጋጨነው እውነቱን ለመናገር" ይላሉ።
"ግን 'የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ገብተዋል የሚሉም' አሉ። አሁንም ሰው እየሞተ ነው። መንገድ ዝግ ነው። ቁስለኞች ህክምና የሚገኙበት ሁኔታ የለም። እንዲያውም ትናንት የቀበርነው ሰው የተመታው እግሩ ላይ ነበር ህክምና ስላላገኘ በመሀል ሞተ" ሲሉም ይናገራሉ።
የጸጥታ ችግር ባለባቸው ቦታዎች ያሉ ነዋሪዎች የሰሞንኛው ግጭት መነሻ ሲያስረዱ፣ ከላሬ ወረዳ የተነሰኑ ሁለት ተሽከርካሪዎች አቦል ወረዳ አካባቢ ሲደረሱ በተከፈተ የተኩስ ጥቃት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን፣ በዚሁ መነሻ ተኩሱ ተስፋፍቶ ህጻናት ጭምር እንደተገደሉ፣ አቦል ወረዳ ላይም የእርስ በእርስ ግጭት እንደተከፈተ አስረድተዋል።
በክልሉ በሚገኝ ሆስፒታል የሚሰሩ ሃኪም በሰጡን ቃል ደግሞ፣ "ከጸጥታው ሁኔታ ጋር በተያያዘ የተጎዱ ሰዎች ወደኛ እየተላኩ ነው" ብለዋል።
በተለይ ከባድ ጉዳት ለደረሰባቸው ቁስለኞች ህክምና ለመስጠት ከመንገድ መዘጋጋት ጋር ተያይዞ የመድኃኒት እጥረት ችግር መኖሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
"መንገዶች ወደ 14 ቀናት በመዘጋታቸው የህክምና የግብዓት እጥረቶች አሉ። በማህበረሰቡ የሚደርሰው ጥቃት አልቆመም። ግን መኪና ስለማይንቀሳቀስ የመድኃኒት ግብዓት የለም። እጃችን ላይ ያለው የተወሰነ ብቻ ነው። በተለይ ወሳኝ መድኃኒቶች ምንም የሉንም" ነው ያሉት።
ካለው የጸጥታ ስጋት አንጻር ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን ተጎጂዎች የሚያክም ከፍተኛ ሀኪም እጥረት መኖሩንም አስረድተው፣ "የጸጥታ ችግሩ አልቆመም። ህዝቡ አሁንም እየቆሰለ ወደሆስፒታል እየተላከ ነው" በማለትም ገለጸዋል።
"በርካታ ቁስለኞች ወደ ህክምና ይላካሉ። በኛ ሆስፒታሉ የመጡት ብቻ ወደ 8 ይደርሳሉ። ከትላንት ወዲያ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሦስት ሰዎች ወደ ጅማ ሪፈር ተደርገዋል። እየደረሰ ያለው ጉዳት ከባድ ነው። ስፔሻሊስት ዶክተር ያስፈልጋል” ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ፦
- የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኦሞድን፣
- የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ማበር ኮርን፣
- የክልሉን ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡጁሉ ጊሎን ለምን ጥቃቱ ማስቆም እንዳልተቻለ፣ ጥቃቱን ለማስቆም ምን እየተሰራ እንደሆነ፣ "የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ጋምቤላ ክልልን ጥሰው ገብተዋል" ስለመባሉ ማብራሪያ እንዲሰጡት በተደጋጋሚ ቢሞክርም ለጊዜው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኞች አልሆኑም።
በቀጣይ ምላሻቸው ሲገኝ ይቀርባል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
❤ 703😢 192😭 99🕊 24😡 24🙏 22🤔 9🥰 6💔 6😱 5
" ልጆቼን እንዳይገደሉብኝ ጠብቅልኝ እያልኩ አምላኬን እየለመንኩ ነው ያለሁት " - ልጆቻቸው የታገቱባቸው የ90 አመት አረጋዊ
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ አምስት የአንድ ቤተሰብ አባላት በታጣቂዎች ታግተው መሰዳቸውን፣ ሁለቱ ቢመለሱም ሦስቱ ባለመለቀቃቸው የአካባቢው አመራሮች ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ ነዋሪዎችና ቤተሰቦቻቸው ጠየቁ።
እገታው የተፈጸመው ከአርሲ ሮቤ 6 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ "አኪያ" በሚባል ቦታ መሆኑን ገልጸው፣ "አምስት የአንድ ቤተሰብ ወንዶች አዝመራ በውቂያ ሳሉ በአካባቢው ባሉ የሸኔ ታጣቂዎች ተወስደዋል" ሲሉ ነዋሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የታጋቾች አባትና አያት የሆኑ የ90 አመት የእድሜ ባለጸጋ ደግሞ፣ ሦስት ልጆቻቸው እና ሁለት የልጅ ልጆቻቸውን በታጣቂዎች ታግተው መወሰዳቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
" ይህን ሊያሰማኝ አቆየኝ " በማለት ሳግ የሚተናነቃቸው እኚሁ የእድሜ ባለጸጋ በገለጹት መሰረት፣ ልጆችና የልጅ ልጆቻቸው እህል ለመውቃት ነዶ ወደአውድማ እያስገቡ ባለበት ነው " ከጫካ በወጡ የሸኔ ታጣቂዎች " ታግተው የተወሰዱት።
እኝሁ አባት፣ " ሐሙስ ታህሳስ 9 ቀን 2018 ዓ/ም ጠዋት 2 ሰዓት ተኩል ነው የእህል ነዶ እያጋዙ ባለበት የተወሰዱት። ነዶውን አውድማ አስገብተው ሊወቁ ነበር " ነው ያሉት።
ምን ያክል ሰዎች እንደተወሰዱ ሲያስረዱም፣ "መጀመሪያ የተወሰዱት አምስት ናቸው፤ መጀመሪያ የተወሰዱት ሁለቱ የልጅ ልጆቼ ነበሩ ለቀቋቸው። ሦስቱን እንደወሰዷቸው ቀሩ ሦስቱ ልጆቼ ናቸው። ወደ ቄርቄር ውስጥ ከረዩ ስር ነው የወሰዷቸው" ብለዋል።
"አቆሙንና 'የማናችሁ? አሉን'፣ 'የአምዴ ነን አልናቸው'፤ 'በሉ እናንተ ተመለሱ አሉን'" ሲሉ ከእገታ ተመላሾች መግለጻቸውን አስረድተው፣ "የተለቀቁት አባት አብሮ የታገተ ነው፤ የወሰዷቸው ከጫካ የወጡ ባለትጥቅ ናቸው" ብለዋል።
"እዚህ ነው ያሉት እንኳ አልተባልንም፤ ዝም ብለን ቁጭ ብለናል፤ ልጆቼን እንዳይገደሉብኝ ጠብቅልኝ እያልኩ አምላኬን እየለመንኩ ነው ያለሁት። አቅም የለኝም ከቤት የዋልኩ የ90 አመት ሽማግሌ ነኝ" ሲሉ አዝነዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የወረዳና የዞን አመራሮችን ለጉዳዩ ያላቸውን ምላሽ ለማካተት ቢሞክርም አልተሳካም፤ ፈቃደኞች ከሆኑ ጥረቱ ይቀጥላል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TilvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
😭 962❤ 484🙏 47💔 46😡 39🕊 21😢 17🤔 9👏 3🥰 1
#EFFORT
ለ14 ቀናት ታግዶ የቆየው የኢፈርት ካምፓኒዎች የባንክ ሂሳብ እገዳ እንዲነሳ ተደርጓል።
ጉባኤ ያካሄደው የእነ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) የኢፈርት ቦርድ ህገ-ወጥ ነው ብሏል የፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት።
" ነባሩ የኢፈርት ቦርድ ሕጋዊ ነው " በማለት የወሰነው ችሎቱ ከህዳር 24/ 2018 ዓ.ም ጀምሮ የታገደው የካምፓኒዎቹ የባንክ ሂሳብ ቁጥር መልሶ እንዲከፈት አዟል።
የፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት ታህሳስ 3/2018 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ፤ የትእምት ካምፓኒዎች የባንክ ሂሳብ ቁጥር በነባር የቦርድ አባላት ይንቀሳቀሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
❤ 361🕊 21😡 16🥰 10🤔 10👏 7🙏 7😭 6😢 2💔 1
" 98 በመቶ የመንግስት አገልግሎቶች ዲጂታል ይሆናሉ " - ኢትዮ ቴሌኮም
የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ 2025 መዝጊያ እና የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ማስጀመሪያ ይፋ ማድረጊያ ስነ ስርአት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተከናውኗል።
በተጠናቀቀው የ2025 ዲጂታል ስትራቴጂ በቴሌኮም ዘርፎች ማሳካት የተቻሉትን ስኬቶች ያብራሩት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ 97 ሚሊዮን ዜጎችን የቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።
በ2030 አዲስ የስትራቴጂ አመትም የዘርፉን ተጠቃሚዎች ተደራሽነት ወደ 128 ሚሊዮን ማድረስ የተቋማቸው እቅድ መሆኑን አክለዋል።
በተጨማሪም 76 በመቶ የነበረው የ4G ተጠቃሚ ቁጥር ወደ 99 በመቶ ማሳደግ እና በ27 ከተሞች ላይ ብቻ ተወስኖ የነበረው የ 5G አገልግሎት ወደ 100 ከተሞች ማሳደግ የመጪው 2030 ዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ አላማዎች መካከል እንደሆነ ጠቅሰዋል።
የዲጂታል ክፍያ ስርዓቱን አሁን ካለበት 82 በመቶ ወደ በ720 በመቶ ከፍ ማድረግ ትኩረት ተሰቶ እንደሚሰራበት ተናግረዋል።
የ2030 ዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ይፋ ማድረጊያ ስነ ስርአት ወቅት ስትራቴጂያቸውን ለማሳካት በየዘርፉ ሊሰሩ በታቀዱ ስራዎች ዙሪያ ፦
- የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አገልግሎት ፣
- የኢትዮጵያ ብሄራዊ መታወቂያ አገልግሎት ፣
- የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዩት፣
- የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ፣
- የገቢዎች ሚኒስቴር እና ሌሎችም መንግስታዊ ተቋማት በእቅዶቻቸው ዙሪያ ማብራሪያቸውን አቅርበዋል።
የብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት ዋና ዳይሪክተር የሆኑት አቶ ዮዳሄ አርአያ ስላሴ በያዝነው ዓመት መገባደጃ ላይ የፋይዳ መታወቂያ ተጠቃሚውን አሁን ካሉበት 30 ሚሊየን ወደ 90 ሚሊዮን የማሳደግ ዓላማ እንዳላቸው በገለጹበት ወቅት ለዚህም ዓላማ በ 14 ክልሎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
❤ 925😡 281👏 53😭 28💔 19🙏 11🕊 11🥰 10😱 9😢 6🤔 3
በዛሬው እለት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በይፋ ተጀመረ።
ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ፥ " ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የታለመለትን ግብ አሳክቶ ተጠናቋል " ብለዋል።
" በዛሬው እለት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በይፋ አስጀምረናል።
- ተደራሽነትን ማስፋት፣
- ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር
- በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሰረታዊ ትልሞች ናቸው " ብለዋል።
" እነዚህ ትልሞች እንዲሳኩ በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ ይከናወናል " ያሉ ሲሆን " ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል " ሲሉ ገልጸዋል።
" በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግስት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ ናቸው " ሲሉ አክለዋል።
@tikvahethiopia
Photo unavailableShow in Telegram
#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom
ለደዋዮ ለየት ያለ የጥሪ ማሳመሪያ ሙዚቃ መጋበዝ እንደሚችሉ ሰምተዋል? አገልግሎቱን ለማግኘት አሁኑኑ ወደ *722# ይደውሉ!
#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
❤ 87🙏 9😡 5😢 2
" አስቸኳይ ጉዞ የምታደርጉ መንገደኞቻችን ሌላ የጉዞ አማራጭ ተጠቀሙ " - የኢትዮጵያ የአየር መንገድ
በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ጭጋጋማ እና ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ፀባይ እንዳጋጠመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።
አየር መንገዱ ከሚቲዎሮሎጂ አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት ይህ የአየር ፀባይ ለተወሰኑ ቀናት ይቀጥላል።
በዚህ ምክንያት ወደተወሰኑ የሀገራችን ክፍሎች የሚያደረጉ በረራዎች ለማቋረጥ መገደዱን አሳውቋል።
" የአየር ፀባዩ እስከሚስተካከል እና በረራዎችን መቀጠል እስከምንችል ድረስ መንገደኞች ታገሱን " ብሏል።
" አስቸኳይ ጉዞ የምታደርጉ መንገደኞቻችን ሌላ የጉዞ አማራጭ እንድትጠቀሙ በአክብሮት ለማሳወቅ እንወዳለን " ሲል ገልጿል።
አየር መንገዱ በአየር ፀባይ ምክንያት የተስተጓጎሉ በረራዎች ወደ መደበኛ አገልግሎታቸው እንደተመለሱ ለመንገደኞች እንደሚያሳውቅ ገልጾ በዚህ ምክንያት ለሚፈጠሩ መጉላላቶች ይቅርታ ጠይቋል።
@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የጤና ሠራተኞች የትርፍ ሰዓት የሚፈቀድበት ሁኔታ እና ክፍያ ለመወሠን የወጣው መመሪያ በፍትህ ሚኒስቴር መመዝገቡን ገልጿል።
"የመንግሥት ጤና ተቋማት ሠራተኞች የትርፍ ሰዓት የሚፈቀድበት ሁኔታ እና ክፍያ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 1119/2018" በሚል የተመዘገበው መመሪያ በሚመለከታቸው ተቋማት ተግባራዊ እንዲሆን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ታህሳስ 7/2018 ዓም በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል።
ረቂቅ መመሪያው የተዘጋጀው በጤና ሚኒስቴር ሲሆን ረቂቁ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከታየ እና ከተገመገመ በኋላ በፍትህ ሚኒስትር መመዝገቡን ደብዳቤው ያትታል።
ቲክቫህ መመሪያው ትክክለኛ ስለመሆኑ እና ተግባራዊ እንዲሆን ስለመላኩ ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አረጋግጧል።
(በዝርዝር መመሪያውን ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ)
@tikvethiopia
" በውይይቱ በጎ የሚባል መግባባት ላይ ተደርሷል! "
ከሰሞኑን ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ታደሰ ወረደ (ሌተናል ጀነራል) አንዱ ጉዳያቸው ከሀገራዊ ምክክሩ ጋር ለመምከር መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለማወቅ ችሏል።
በዚህም ፕሬዚዳንቱ የትግራይ ክልል አጀንዳ የማሰባሰብ ጉዳይን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር ትናንት እንደተወያዩ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
" የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ትናንት ከምክክር ኮሚሽኑ ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ በትግራይ ክልል ምክክሩ ስለሚካሄድበት ሁኔታ ነው " ተብሏል።
የደረሰን መረጃ " በውይይቱ በጎ የሚባል መግባባት ላይ ተደርሷል " የሚል ሲሆን፣ በጎ ነገሩ ምንድን ነው? ታዲያ በክልሉ አጀንዳ መቼ እንደሚሰባሰብስ ተወስኗል? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄ፣ "መቼ የሚለው ብቻ አልተወሰነም" የሚል ምላሽ አግኝቷል።
"በጎ ነገር አለ" መባሉ ደግሞ "በአስተዳደሩ በኩል ኮሚሽኑ ወደ ክልሉ እንዲገባ ፍላጎት" መኖሩን የሚያመላክት መሆኑ ተገልጿል።
ፕሬዚዳንት ታደሰ (ሌ/ጀ) ከሰሞኑ ወደአዲስ አበባ ማቅናታቸው፣ ያቀኑትም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ሊወያዩ እንደሆነ ተነግሮ የነበረ ሲሆን፣ ይሁን እንጅ ከኮሚሽኑ ጋር መወያየትም ወደ አዲስ አበባ ያቀኑበት ሌላኛው ዋነኛ ጉዳይ መሆኑ ታውቋል።
ከኮሚሽኑ ጋር ያደረጉት ውይይት ወደ አዲስ አበባ "ከመጡባቸው ጉዳዮች አንዱ ነው እንጅ እግረመንገዳቸውን አይደለም። ቀጠሮ ነበራቸው" ሲሉ የውስጥ አዋቂዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በመጀመሪያ የተሰጠው ሦስት ዓመት ባለመብቃቱ ተጨማሪ አንድ አመት በፓርላማ የተሰጠው ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብና ዋናውን ሀገራዊ ጉባዔ ማካሄድ የሚጠበቅበት ሲሆን፣ ተጨማሪ ጊዜውን ለማጠናቀቅ ሁለት ወራት ቢቀሩትም በትግራይ ክልል እንኳ አጀንዳ ገና አላሰባሰበም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
❤ 656🕊 94😡 47🙏 17🤔 8😢 5😭 2
#እንድታውቁት
እይታን የሚያድኑ ቀላል የዓይን እንክብካቤ ምክሮች !
ጥሩ እይታ ለዕለት ተዕለት ሕይወት፣ ለመማርና ለመስራት በጣም አስፈላጊ ነው። ብዙ የዓይን ችግሮች በቀላል እንክብካቤ መከላከል ወይም መቆጣጠር ይቻላል።
ዓይናችንን በመንከባከብ መዳን ከሚችሉ በሽታዎች እራሳችንን እንጠብቅ።
1. መደበኛ የዓይን ምርመራ ያድርጉ
ህመም ወይም የእይታ ችግር ባይኖርም መደበኛ የዓይን ምርመራ ማድረግ እንደ ግላኮማ፣ የዓይን ሞራ (cataract) እና የእይታ መዛባት (refractive errors) ያሉ በሽታዎችን በቀላሉ ለመገንዘብ ይረዳል።
ቀደም ብሎ የ ዓይን ችግርን ማወቅ እይታን ያድናል።
2. ዓይኖትን ንጹህ ያድርጉ
ዓይን ከመንካት በፊት እጆችዎን ይታጠቡ። በተለይ በቆሻሻ እጅ ዓይንን ማሸት የዓይን ኢንፌክሽንን ሊያመጣ ስለሚችል ይቆጠቡ።
3. ዓይኖትን ከጉዳት(injury) ይጠብቁ
በአቧራ ቦታ፣ ከኬሚካል ጋር ሲሰሩ ወይም ዓይን ሊጎዳ በሚችል ስራ ላይ ከተሰማሩ ቦታው ወይም ከስራው ጋር የሚሄድ የመከላከያ መነጽር ይጠቀሙ።
የዓይን ጉዳት (eye injury) ዘላቂ የእይታ እክል ሊያመጣ ይችላል።
4. ከስክሪን ጫና ይቆጠቡ (Reduce screen strain)
ስልክ፣ ኮምፒውተር ወይም ቴሌቪዥን ሲጠቀሙ መደበኛ እረፍት ይውሰዱ። የ20–20–20 ህግን ይከተሉ፤ ከ20 ደቂቃ የስክሪን ቆይታ በኋላ 20 ጫማ ርቀት ያለ ነገርን ለ20 ሰከንድ ይመልከቱ።
5. በተቻለ አቅም ጤናማ ምግብ ይመገቡ
ቫይታሚን A፣ C፣ E እና ኦሜጋ-3 ያሉት ምግቦች ለዓይን ጤና ጠቃሚ ናቸው። በተቻለ አቅም አትክልት፣ ፍራፍሬ ፣ እንቁላል ፣ አሳ እና ወተት ይመገቡ።
6. ሲጋራና ከመጠን በላይ መጠጥ ይተዉ
ሲጋራ ማጨስ የዓይን ሞራ፣ የግላኮማ እና የማኩላር በሽታ( macular degeneration) አደጋን ይጨምራል። እነዚህን ልማዶችን መተው እይታን ይጠብቃል።
7. የ ዓይን ችግር ሲያጋጥም ፈጣን ሕክምና ያግኙ
የዓይን መቅላት፣ ህመም፣ ዓይናር፣ የእይታ መደብዘዝ ወይም ድንገተኛ የእይታ መጥፋት ቢታይ ወዲያውኑ ወደ ዓይን ህክምና ይሂዱ።
ቀድሞ ሕክምና ማግኘት ሊመጣ ከሚችል ከባድ ችግሮች(complications) ይጠብቃል።
💬 ቀላል ጤናማ የዕለት ተዕለት ልማዶች ዓይን ጤናን በጣም ሊጠብቁ ይችላሉ። ዛሬ ዓይንን መጠበቅ ለወደፊት ግልጽ እይታና ለተሻለ ሕይወት ጠቃሚ ነው።
ምንጮቻችን ፦ WebMD እና CDC ናቸው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily
@tikvahethiopia
❤ 858🙏 119👏 19🥰 13🤔 7🕊 3
Photo unavailableShow in Telegram
ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ይገናኙ ፦
📱 ለመረጃ እና ጥቆማ እንዲሁም ማንኛውም አይነት ሃሳብ ለማቅረብ ብቻ ፦
1. 0998999899 (SMS/የቀጥታ ስልክ) @tikvahethiopiaDM
2. @tikvahethiopiaBOT
3. Direct Message ከእያንዳንዱ ፖስት ስር 💬 DM ማድረግ ይቻላል።
🆕 ለፕሮሞሽን አገልግሎት ብቻ ፦
1. 0979222111 (@TikvahEthiopiaMarketing1)
2. 0979333111 (@TikvahEthiopiaMarketing2)
ለማስታወቂያ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያስፈልጋል።
በተጨማሪም ፦
🚫" በትምህርት ሆነ በስራ ውጭ ሀገር እንልካለን " የሚሉ ድርጅቶች፤
🚫" ቅድመ ክፍያ ክፈሉና ይሄን አድርጉ/ይሄን ግዙ " የሚሉ ድርጅቶች፤
🚫የአልኮል መጠጥ ፣ የጭፈራ ቤቶች፤
🚫ከአልኮል መጠጥ ጋር የተገናኙ ዝግጅቶች፤
🚫ማንኛውም ሃይማኖታዊ ጉዳዮች፤
🚫አድራሻና መገኛ የሌለው የኦንላንይ ንግድ፤
🚫ተገቢው ፍቃድ የሌላቸው ስልጠናዎች፣ ትምህርቶች እና የቴክኖሎጂ ውጤቶች፤
🚫የማህበረሰብን እሴት የማያከብሩ ማንኛውም ይዘቶች፤
🚫ሪልስቴት እና ተያያዥ ድርጅቶች፤
🚫 ከሚመለከተው አካል ፍቃድ የሌለው ከጤና ጋር የሚገናኝ ማንኛውም ማስታወቂያ ... #አይስተናገዱም።
ለስራ ጀማሪ ወጣቶች (ስታርትአፕ) ፦ እንደ ከዚህ ቀደሙ ለናተ የሚሆን ክፍት ቦታ በነጻ አለ። ስራውን ከጀመራችሁ ከአመት በታች እንደሆናችሁ የሚገልጽ ማስረጃ በማቅረብና በማሳየት መጠቀም ትችላላችሁ።
ውድ ቤተሰቦቻችን ፦ ትክክለኛ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ማህበራዊ ሚዲያ አድራሻዎች ከላይ የተገለጹት ብቻ ናቸው። በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስም የሚያጭበረብሩ አካላትን ስትመለከቱ ጥቆማ በመስጠት ተባበሩን።
@tikvahethiopia
❤ 437👏 80🙏 30🕊 1
አፋልጉኝ !
" ልጃችንን ያለችበትን የምታውቁ ጠቁሙን ! "
ለምለም ለገሠ በቀን 08/04/2018 ወደ ማታ 11 አካባቢ ኮልፌ ልኳንዳ 04 ክበብ አካባቢ እንደወጣች አልተመለሠችም።
" ለምለምን ያየ ያለችበትን የሚያውቅ እባካቹ ተባበሩን " ሲሉ ቤተሠቦች ተማፅነዋል።
ስልክ ፦
+251963096743
+251910084868
🔴
" ከ2015 አጋማሽ ጀምሮ የት እንዳለች አናውቅም ! "
ብሪቱ ታዬ ጫላ የትውልድ ቦታዋ ወለጋ፣ ላሎ አሳቢ ወረዳ ነው።
በ2013 ዓ/ም ወደ የUAE አቡዳቢ ሄዳ ነበር።
በ2015 ዓ/ም አድራሻዋን ወደ ቤሩት የቀየረች ሲሆን ከ2015 ዓ/ም አጋማሽ ጀምሮ አድራሻዋን ማግኘት ያለችበትን ማወቅ አልተቻለም።
ያለችበትን የሚያውቅ ወይም ስለሷ ጉዳይ መረጃ ያላችሁ ፦
በ 0940506025 ላይ ደውላችሁ እንድታሳውቋቸው ቤተሰቦቿ ተማፅነዋል።
🔴
" ያለበትን የምታውቁ ንገሩን ! "
ግዛቸው አዲስ ምህረት (ኪሩብ) በምዕራብ ጎጃም ደምበጫ ወረዳ ነው የተወለደው።
በ1979 በደርግ ሰዓት የኢትዮጵያን ጦር የተቀላቀለ ሲሆን እስከ ጥቅምት ወር 1983 ዓ/ም ድረስ ለቤተሰቦቹ የሰላምታ ደብዳቤ ይፅፍ ነበር።
ከዛ በኃላ ግን ያለበት የደረሰበት አይታወቅም። በህይወት ይኑር አይኑር አይታወቅም።
ለቤተሰብ ልጅ በህይወት ይኑር አይኑር አለማወቅ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ በመረዳት ያለበትን የምታውቁ፤ እንደው በአጋጣሚ ስለሱ የሰማችሁ፣ አይታችሁትም የምታውቁ ፦
በ 0920311816
በ 0918436218 ላይ ደውላችሁ እንድታሳውቋቸው ቤተሰቦች ከምስጋና ጋር ተማፅነዋል።
🔈 ከቀናት በፊት ጠፍተው የነበሩት አባታችን ሹሚ ኢዳ ኬንቴሪ አካባቢ በሰላም ተገኝተዋል። ቤተሰቦቻቸው ለትብብራችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ያክብርልን ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamily
@tikvahethiopia
Photo unavailableShow in Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
❤ 117😡 30👏 20😭 13🤔 11🕊 7💔 4
ዋሪት ፈርኒቸር
ክቡራን ደንበኞቻችን! መጪው በዓል የሰላም፤የፍቅር እና የስኬት እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ ከልብ እየተመኘን፡ ምቾታቸውን እና ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶቻችንን በሁሉም የማሳያ ቅርንጫፎቻችን ከበዓል ቅናሽ ጋር እስከ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም. አዘጋጅተን እንጠብቅዎታልን!!
Visit us today @
📍 22 - ዋሪት ህንፃ
📍 ጉርድ ሾላ - ሴንቸሪ ሞል
📍 ለቡ - ቫርኔሮ ፊት ለፊት
📍 አዳማ - ሶረቲ ሞል
📍 ቡልቡላ- ልዑል ህንፃ ፊት ለፊት
📍 ወሎ ሰፈር- Ethiolife life real estate
📍 ጦር ሀይሎች- ኩዊንስ ፊት ለፊት
ዋሪት ፈርኒቸር
ትክክለኛ ምርጫ!
ለተጨማሪ መረጃ: ☎️ 0911210706/07
https://t.me/warytfurniture
tiktok:/warytzefurniture
❤ 204🙏 4😢 3😭 3😱 1🕊 1💔 1
" ልጃችን መንገድ ላይ ተገድላ ከ600 ሺህ ብር በላይ ተወስዶባታል " - የቡናዬ ቤተሰቦች
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ኬሌ ከተማ መቅሬዲ ቀበሌ ነዋሪዋና የቀድሞ የእግርኳስ እና ቦክስ ስፖርቶች በክልል ደረጃ ተወዳዳሪ አሁን ላይ ታታሪ ነጋዴ ቡናዬ ብርቅነህ በትናንትናው ዕለት ከኮሬ ዞን ወደ አጎራባች ምዕራብ ጉጂ ዞን ለገበያ በመጓዝ ላይ እያለች እስካሁን ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች መገደሏን ቤተሰቦቿ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የቡናዬ ወላጅ አባት አቶ ብርቅነህ ባሩድ እና ታላቅ ወንድሟ መምህር አዳነ ብርቅነህ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ለቲክቫህ በሰጡት ቃል፥ ቡናዬ ገና የ29 ዓመት ወጣት መሆኗን የቀድሞውን የደቡብ ክልልን በመወከል የቦክስና እግር ኳስ ተወዳዳሪ የነበረች ስፖርተኛ እንደነበረች ግለጸዋል።
ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ደግሞ የቀንድ ከብት እንዲሁም የሸቀጣሸቀጥ ነጋዴ በመሆን እየሰራች እንደነበር ጠቁመው በትናንትናው ዕለት ከምዕራብ ጉጂ ዞን ጋላና ሻሞሌ ሺዳ ቀበሌ ወደ ሚገኘው ፋታ ገበያ በመጓዝ ላይ እያለች በጥይት ተመታ መገደሏንና በሬና ፍየሎችን ለመግዛት የያዘችዉ ከ600 ሺህ ብር በላይ እንዲሁም የእጅ ስልኳ መዘረፉን ተናግረዋል።
ቡናዬ የ4 ዓመት ልጅ እናት እንደነበረች የገለፁት ቤተሰቦቿ ፥ ሴት ልጅ በዚህ ሁኔታ ስትገደል ይህ የመጀመሪያው መሆኑንና የሁለቱ ዞን መንግስታት የልጃቸዉን ገዳዮችን ለሕግ እንዲያቀርቡ ጠይቀዋል።
የኮሬ ዞን ፖሊስ ምን አለ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገራቸው የኮሬ ዞን ፖሊስ አዛዥ ም/ኮማንደር ሲዳሞ ማዳሞ ፤ በምዕራብ ጉጂና ኮሬ ዞኖች አዋሳኝ አከባቢ ወ/ሮ ቡናዬ ብርቅነህ በኮሬ ዞን ኬሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ታካሚ የነበረችን የምዕራብ ጉጂ ነዋሪ አንዲት እናት በሞተር ጭና ወደ ጋላና ወረዳ ሻሞሌ ሺዳ ፋታ ገበያ በመጓዝ ላይ እያለች (ከታማሚዋ ጋር ምንም ዝምድና የሌላት ሲሆን እየሸኘቻት ነበር) ለጊዜው ማንነታቸዉ ባልታወቁ ሰዎች ጥቃት ተፈፅሞባቸዉ ሕይወቷ ማለፉን ተናግረዋል።
የገላና ወረዳ ፖሊስ አስክሬኑን ለኮሬ ዞን ማስረከቡን ገልፀው አብራት የነበረችው ግለሰብ ተርፋ ወደ ቤተሰቦቿ መወሰዷ እንደተነገራቸው ገልፀዋል።
በአከባቢው የሚንቀሳቀስና እራሱን ' ሸኔ ' ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ሃይል ቢኖርም የገዳዮችን ትክክለኛ ማንነት ለመለየት ግን የሁለቱ መዋቅር ፖሊስ በትብብር እያካሄደ ያለዉን ምርመራ መጠበቅ ያስፈልጋል ብለዋል።
የገለላና ወረዳ ፖሊስ ምን አለ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ ለማግኘት ወደ ገላና ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፐክተር ባራቃ ሀንቆ የእጅ ስልክ በተደጋጋሚ ቢደዉልም ስልኩ ባለመነሳቱ ለጊዜው ምላሻቸዉ አልተካተተም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
@tikvahethiopia
😭 1 751❤ 1 272💔 129😢 76🕊 57🙏 33😡 30🥰 20😱 17🤔 16👏 5
" ከተጠናቀቁ ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት ለሆናቸው ፕሮጀክቶች በ3 ዓመታት ውስጥ በድምሩ 2.96 ቢሊዮን ብር በጀት ተመድቧል ! "
➡ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲዎች ለተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች በየአመቱ በጀት ሲመደብ ነበር !
ፕሮጀክቶች ከተጠናቀቁ በኋላ ከአንድ እስከ ሦስት ዓመት ለሚሆን ጊዜ በየዓመቱ በጀት ሲመደብላቸው መቆየቱን የፌዴራሉ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ካቀረበለት የኦዲት ሪፖርት ያረጋገጠው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ጉዳዩ በአስቸኳይተመርምሮ ሪፖርት እንዲቀርብለት አዘዘ።
ሰሞኑን በሕ/ተ/ም/ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአገራዊ የልማት ፕሮጀክቶች የክትትልና የቁጥጥር ሥርዓት ላይ የፌዴራሉ ዋና ኦዲተር ያካሄደውን የክዋኔ ኦዲትና በኦዲቱ የተገኙ ክፍተቶችን መሠረት አድርጎ፣ ጉዳዩ ከሚመለከተው የፕላን ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አድርጎ ነበር።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሺመቤት ደምሴ (ዶ/ር) ፥ የፌዴራል ዋና ኦዲተር የክዋኔ ኦዲት ግኝትን መሠረት በማድረግ የአዋጭነት ጥናት ሳይጠና በጀት የተመደበላቸው ፕሮጀክቶች መኖራቸውን፣ የፋይናንስና የፊዚካል ሪፖርት የማያቀርቡና በተቀመጠላቸው ጊዜና በጀት ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን በመጥቀስ ሚኒስቴሩ ይህንን ለማስተካከል የወሰደውን ዕርምጃ ጠይቀዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ተጠናቀው ሥራ ለጀመሩ ፕሮጀክቶች በጀት ሲመደብ መቆየቱን በመግለጽ፣ ይህ እንዴት ሊሆን እንደቻለ ሚኒስቴሩ ማብራሪያ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል።
የፌዴራል ዋና ኦዲተር ባለፈው ዓመት የኦዲት ግኝት ሪፖርቱን ለሕ/ተ/ም/ቤት ማቅረቡ የሚታወስ ሲሆን፣ የክዋኔ ኦዲት ካደረገባቸው ተቋማት እንዱ የፕላን ልማት ሚኒስቴር ነበር።
በዚህ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርቱ ላይም ናሙና በመውሰድ ኦዲት ካደረጋቸው የመንግሥት ፕሮጀክቶች ውስጥ በ2 ዩኒቨርሲቲዎች የተገነቡ በርካታ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ሥራ ከጀመሩ ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት የቆዩ መሆናቸውን፣ ነገር ግን ለእነዚህ ፕሮጀክቶች በየዓመቱ በጀት ሲመደብ እንደነበር አረጋግጧል፡፡
የተጠቀሱት ዩኒቨርሲቲዎች ፦
➡ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ
➡ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ናቸው።
በነዚህ ሁለት ዩኒቨርሲቲዎች ከተጠናቀቁ ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት ለሆናቸው ፕሮጀክቶች ከ2013 እስከ 2016 ዓ.ም. ባሉት ዓመታት ውስጥ በድምሩ 2.96 ቢሊዮን ብር በጀት መመደቡን፣ በጀቱም ለተባሉት ፕሮጀክቶች #አለመዋሉን የኦዲት ሪፖርቱ ይጠቁማል።
ከዚህም በተጨማሪ በጀቱ ለተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች የተመደቡ መሆኑ ታውቆ ለገንዘብ ሚኒስቴር እንዲመለስ አለመደረጉ ፤ ከገንዘብ ሚኒስቴርና ከዩኒቨርሲቲዎቹ በተገኘ የአይቤክስ መረጃ፣ የዶክመንት ክለሳና የአካል ምልከታ መረጋገጡን ያስረዳል።
በሌሎች 5 ዩኒቨርሲቲዎች ለቀረቡ ፕሮጀክቶች ደግሞ በአጠቃላይ 1.1 ቢሊዮን ብር በጀት ተለቆ እንደነበር፣ ነገር ግን የተለቀቀው በጀት ለተባሉት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ አለመዋሉን የኦዲት ሪፖርቱ ያስረዳል።
በአጠቃላይ ተጠናቀው ሥራ ለጀመሩ ፕሮጀክቶችና በጀት ተለቆላቸው ላልተከናወኑ ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ 4.07 ቢሊዮን ብር በጀት ተመድቦ መገኘቱን፣ ዋና ኦዲተር በኦዲት ግኝት ሪፖርቱ አስታውቋል።
የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ምን አሉ ?
የመንግሥት ፕሮጀክቶችን የመቆጣጠር ሥልጣን ለተቋማቸው በአዋጅ መሰጠቱን ጠቅሰው፣ ይህንን ተከትሎ በፕሮጀክቶች ዙሪያ ያሉ ክፍተቶችን ለማረም በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን ዋና ኦዲተር ባከናወነው ኦዲት የቀረቡ አብዛኞቹ ግኝቶች ከአዋጁ በፊት የነበሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ምን አሉ ?
የክዋኔ ኦዲት ግኝቱ በአዋጁ መሠረት መከናወኑን ገልጸዋል።
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ አራሬ ሞሲሳ ምን አሉ ?
በተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ላይ በጀት ሲመደብ የነበረበትን ምክንያት በሚመለከተው አካል ጥናትና ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲሰፍን በማድረግ፣ ሚኒስቴሩ ለቋሚ ኮሚቴው ሪፖርት እንዲያቀርብ አሳስበዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።
@tikvahethiopia
❤ 750😭 188😱 38🤔 36💔 23😡 21👏 17🙏 13🥰 11🕊 9😢 8
" በዐውደ ርዕዩ እና የጃን ፎረም መድረክ ላይ በርካታ ዓለም አቀፍ ጥናታዊ ጹሑፎች እና “Defending the ancient faith” የተሰኘ መጽሐፍ ይመረቃል " - የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ (ኢጃት)
➡️ " 3ኛው የአእላፋት ዝማሬ በመስቀል አደባባይ እንዲደረግ ተፈቅዶ ዝግጅት እየተደረገ ነው ! "
የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ (ኢጃት) ፥ የአእላፋት ሳምንት የተሰኘ ዐውደ ርዕይና የፎረም መድረክ ከታኅሣሥ 16 ቀን ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በግዮን ሆቴል ግራውንድስ ላይ ለማከናወን ዝግጅት መጠናቀቁን አሳውቋል።
የዚህ ዝግጅት ዋና አላማው ፦
- የአብነት ት/ቤቶች፣ አድባራትና ገዳማት ሥራዎቻቸውን እንዲያቀርቡ ማድረግ፤
- ቀደምት የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት፣ ደራሲያን፣ ዘማርያንና የታሪክ ሰዎች የሚዘከሩበት ዓመታዊ መድረክ ማዘጋጀት፤
- ምሁራን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በዘላቂነት ታትሞ የሚሰራጭ የዐውደ ጥናት መድረክ ለማሰናዳት ጥናታዊ ጽሑፎቻቸውን የሚያቀርቡበት መድረክ መፍጠር እንደሆነ ገልጿል።
" ሌላው የዚህ ዝግጅት አላማ እራሳችንንም በኢኮኖሚ መገንባት ነው። የማህበራችን አላማ ከሆኑት ውስጥም አንዱ ነው። እንደሚታወቀው በዓላት በመጡ ቁጥር ወደ ልመና ነው የምንወጣው፣ ምዕመናኑን ነው ሁሌም የምንለምነው፣ እኛ ማህበራቶች ደግሞ ከዚህ መላቀቅ መቻል አለብን " ብሏል።
" በርካታ አገልግሎቶች አሉብን፣ እነዚህን አገልግሎቶች ሊያከናውን የሚያስችችል የኢኮኖሚ አቅም መፍጠር አለብን። ይህንን ለማድረግ ደግሞ በንግድና ፈጠራ ሥራ የተሰማሩ ጥሩ የኢኮኖሚ አቅም ያላቸው ኦርቶዶክሳውያን የሚተዋወቁበት መድረክ መፍጠር ያስፈልጋል " ሲል ገልጿል።
" በተጨማሪም በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በከለላ ወረዳ የሚገኘው የደብረ ባሕርይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫና አቡነ በጸሎተ ሚካኤል አንድነት ገዳም ጋር በመተባበር “ ኢትዮጵያዊው ነባቤ መለኮት ” በሚል ርዕስ የቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ 600ኛ ዓመት ይከብራል፣ ይዘከራል። የ2018 ዓ.ም የገና መባዕ ለዚሁ ገዳም እንዲሆን ተወስኗል " ብሏል።
የኢጃት የአገልግሎት አመራር ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ቢኒያም አህመድ፥ " ኢጃት ሲባል በሰዎች አዕምሮ ዘንድ ቀድሞ የሚመጣው እና በስፋት ጎልቶ የሚታየው የአእላፋት ዝማሬ ነው፣ ዐውደ ርዕዩ እና የፎረም መድረኩን ያዘጋጀነው ከዚህ ጥያቄ መውጣት የምንችልበትን አግባብ እንዲፈጥርልን ነው " ብለዋል።
በዚህ 8 ቀን ዐውደ ርዕይ እና የጃን ፎረም መድረክ ላይ በርካታ ዓለም አቀፍ ጥናታዊ ጹሑፎች እና “Defending the ancient faith” የተሰኘ መጽሐፍ ይመረቃል።
ሁሉንም ዝግጅቶች ለማየትና ለመታደም መግቢያ ዋጋ ብር 300 (#ሶስት_መቶ_ብር) ሲሆን ይህ ገቢ ዐውደ ርዕዩን ለማዘጋጀት ማኅበሩ ያወጣውን ከፍተኛ ወጪ ለመሸፈን የሚያግዝ የኢጃትንም አገልግሎት ለመደገፍ የሚውል ነው ተብሏል።
በሌላ በኩል ፥ በዘንድሮው አመት የሚደረገው 3ኛው የአእላፋት ዝማሬ መርሐግብር ታኅሣሥ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ፣ በድሬ ለገሀር አደባባይ እና በሌሎች 8 ቦታወች እንደሚካሄድም ተገልጿል።
በቦሌ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በተደረጉ ሁለት ዙር የአእላፋት ዝማሬ ዝግጅቶች ላይ በተደረገው ጥናት በመጀመሪያው 50 ሺህ እና በ2ኛው ዝግጅትም እስከ 80 ሺህ የሚደርሱ ምዕመናን ታድመዋል። በዚህም የቦታ ጥበት ተፈጥሮ በርካቶች ከቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውጭ ለመሆን ተገደው ነበር።
ይህንኑ ስርአት በተሻለ ሁኔታ ለማካሄድ ፤ ህጻናትም በነጻነት የሚንቀሳቀሱቀት ቦታ አግኝተው፣ በዓለ ልደቱን እንዲያከብሩ ለማድረግ ታስቦ የሚመለከተውን አካል በማስፈቀድ ዝግጅቱ በመስቀል አደባባይ እንዲደረግ ተፈቅዶ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ኢጃት አሳውቋል።
በአእላፋት ዝማሬ ዙሪያ አንዳንድ አካላቶች በማህበራዊ ትስስር ገጾች እያዘዋወሯቸው ያሉ እና ውዝግብ እየፈጠሩ ባሉ ሃሳቦችና ጉዳዮች ላይ እለቱ ሲደርስ ዝርዝር መግለጫ እንደሚሰጥ ኢጃት ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
" ልጃችንን አፋልጉን ! "
ነህምያ ሽመልስ (ችፑ) የ12 ዓመት ታዳጊ ነው።
አዲስ አበባ አየር ጤና ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ እሁድ ጠዋት ቤተክርስቲያን ብሎ ከወጣ በኋላ ወደቤቱ አልተመለሰም።
ልዩ ምልክት የፊት ጥርሱ ተሸርፏል። ከቤት ሲወጣ የለበሰው ግሬይ ከለር ሹራብ፣ ክሬም ከለር ቱታ ሱሪ፣ ክሬም ከለር ሱፍ ነጠላ፣ ቡኒ ነጠላ ጫማ ነው።
ቤተሰቦቹ እጅግ በጣም ተጨንቀዋል።
" ልጃችንን ያያችሁ (ያገኛችሁ) ወይም ያለበትን የምታውቁ በስልክ ቁጥር፦
091173 3666
0913445385 በመደወል ያሳውቁን " ሲሉ ተማፅነዋል።
🔔
" አፋልጉን ! "
ግርማ ደርቤ በአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆን እሁድ ታህሣሥ 5/4/2018 ጠዋት ሥራ ብሎ እንደወጣ ደብዛው መጥፋቱን ቤተሰቦቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።
እስካሁን ያለበት አይታወቅም ፤ ወደ ቤቱም አልተመለሰም።
እናት፤ ቤተሠብ ተጨንቋል እባካችሁ ያያችሁ ያለበትን የምታውቁ ወይም የሠማችሁ በ0920335526 ብታሳውቁን ወሮታውን እንከፍላለን ብለዋል ፈላጊ ቤተሰቦቹ።
-----
🙏 ከቀናት በፊት መጥፋቷ የተገለጸው የ10 ዓመቷ ሰላም ጥበብ ሰበታ ተፍኪ አለፍ ብሎ መገኘቷን ቤተሰቦቿ ከምስጋና ጋር ገልጸዋል።
#TikvahEthiopiaFamily
@tikvahethiopia
❤ 746😭 232🙏 123🕊 21🤔 20😱 15😢 8👏 5💔 2
