ar
Feedback
Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

الذهاب إلى القناة على Telegram

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

إظهار المزيد
2025 عام في الأرقامsnowflakes fon
card fon
228 752
المشتركون
-18824 ساعات
-1 0407 أيام
-4 59130 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
"…በነገራችን ላይ… "…ከርእሰ አንቀጹ ንባብ በፊት ስለ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ዘሰሜን መቀሌ የሆነች ነገር ልበል። በሰፊው እስክመጣበት ድረስ ነው። በዚህ ልጅ ጉዳይ ሰሞኑን የሆነች ነገር ተናገርክ ብለው ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ትግሬዎች እና ያስደወሉብኝ ፈረንጂ ለምን በኃይለኛው ጓ እንዳሉብኝ እንጃ። እንዴኤኤ ብዬ በደንብ እንድመረምረው እና በደንብ እንድሄድበት ነው ያደረጉኝ። ፕሮግራሚንግ አይደል ነገሩ እሄድበታለሁ ስልህ። ተንጫጫ፣ በረኪና ጠጣ፣ ጧ በል አልኩህ። ተደርጎ በማያውቅ መልኩ በፈረንጅ አፍ ያስፈራራኛል እንዴ? ኦሆሆ…! "…አፍራሽ አይደል ስሜ… በእመቤታችን ስም ስር ተደብቀህ፣ ተሸሽገህማ አትሸውደኝም። ሕዝቡን አላልኩም። እኔን ነው ያልኩህ። መንጋውንማ እንዳሻህ ንዳው። ኦኮ ወዴት ወዴት? ወይ ንቅንቅ? "…ኢማጂን 😂 ከ40 ተማሪ 39 ነኛ ይወጣ የነበረ ሰው። ዴየደብ የነበረ ተማሪ፣ ከዚያ ገንዘብ ተከፍሎ ለናሳ ምርምር ጣቢያ ተመርጦ አማሪካ ሎሳንጀለስ እንዲከትም ተደረገ። ደደቡ ልጅ ማለት ነው። ከዚያ በሎሳንጀለስ አማሪካ ድራግ ውስጥ ቆይቶ ካናዳ ሄዶ የካናዳ ዜግነት ተሰጥቶት ሲያበቃ አባቶቹ በአንቀጽ 39 የበጣጠሷትን ኢትዮጵያን ከ40 ተማሪ 39ነኛ ይወጣ የነበረ ዴደብ ተማሪ በብዙ ማስታወቂያ፣ ግርግር፣ የገንዘብ ምንጩ በማይታወቅ፣ በማይመረመር፣ በማይነገር የገንዘብ ጎርፍ የተጥለቀለቀን ነውረኛ አምጥተህ ማርያም ማርያም ብሏል፣ እመቤታችንን ይወዳልና አትንኳው ብትለኝ እኔ ዘመዴ መች እሰማህ እና። አይደለም ማርያም ማርያም ብሎ የሚመጣ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚሉት እንኳ መች ይገቡና። "…አክሱም ሲገባ ጋርድ አያስፈልገኝም፣ መቀሌ ሲሄድ ጠባቂ አያሻኝም በማለት ባንኮፍ አሜሪካ ባዘጋጀው የኃይሌ ገብረ ሥላሴ ታላቁ ሩጫ ላይ ጋርድ ተቀጥሮለት፣ ታላቁን የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሰግጥ ፈምስ ብሎ የዘበተበትን ከእኔ የባሰ ዴየደብ በብዙ እንድንሰማው፣ ራሱም እንደነገረን "ከሰሜን ይመጣል የተባለው ቴዎድሮስ" ነው እና እናዳምጠው፣ እንከተለው ብትለኝ አብጄ ነው? ሞቼ ነው ቆሜ የምሰማህ? ኧረ ጥፋ። ድራሽ አባክ ይጥፋና። ለፈረንጁ ድራሽ አባክ ይጥፋ እንዴት ብዬ ልንገረው? 😂 ኧረ ሱሬ ድረስ። • "አዶናይ" የሚለው ለአምላክ ብቻ የሚሰጥ ስም ለዚህ ሎሳንጀለሳዊ ድራጋም የካናዳ ዜጋ ደፋር የትግሬ ቀዌ እንዴት ተሰጠው? ገና እጠይቃለሁ። በእናትህ ዘመዴ አትናገረው ይለኛል እንዴ? ፈረንጅ ይፈራል ብለህ ነው በፈረንጅ የምታስጨቀጭቀኝ አባው። መስሚያዬ ጥጥ ነው። • ወደ ርእሰ አንቀጹ ከመሄዴ በፊት ከመሬት ተደውሎ ውይይት ቢጤ ስለያዙኝ ነው የዘገየሁት። ቀይ አንዴ ብለው ስላዘገዩኝ ነው ርእሰ አንቀጹ ያልተለጠፈው። እስከዚያው ድረስ በባዶ ከምትቀመጡ ይሄን በራሱ አፍልቶ በአሯሯጡ የሚያስታውቀው፣ በጊዜም አፍልቶ የሚቆምን ደፋር መመርመር፣ መጠየቅ እንደምንጀምር የሚያስገነዝበውን የማንቂያ ደውል እያነበባችሁ ጠብቁኝ። • የመሬቱን ልጨርስና መጣሁ።
إظهار الكل...
star reaction 2 998👍 355🙏 126🏆 28😡 10🕊 9💔 8 6👌 6 1🤯 1
Photo unavailableShow in Telegram
መልካም… "…ይቅርታ ስብሰባ ላይ ነበርኩ። በቀጠሮዬ ሰዓት ያልተገኘሁት ለዚያ ነው። አሁን ተመልሻለሁ። በተለይ ለአርበኛ ሳሙኤል ባለድል እና ለአርበኛ ሀብቴ ወልዴ የሚደርስ አስቸኳይ የጥንቃቄ መልእክት ያዘለ አንብባችሁ ታደርሱልኝ ዘንድ፣ በአጠቃላይ እየጠራ ያለውን የፋኖ ትግልም ትመለከቱበት ዘንድ ያዘጋጀሁላችሁን ርእሰ አንቀጽ ወደ እናንተ አደርሳለሁ። • አላችሁ አይደል…? ዝግጁ…?🫡🫡🫡
إظهار الكل...
star reaction 1 698👍 350🙏 81🏆 23🔥 9 6🕊 4🤔 2😡 2
Photo unavailableShow in Telegram
"…ወንድምም ሁሉ ያሰናክላልና፥ ባልንጀራም ሁሉ ያማልና እናንተ ሁሉ ከባልንጀሮቻችሁ ተጠንቀቁ፥ በወንድሞቻችሁም አትታመኑ። ኤር 9፥4  "…ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም አምባ ነውና ለዘላለም በእግዚአብሔር ታመኑ። ኢሳ 26፥6 "…እንደምን አደራችሁ? "…እንደምን አረፈዳችሁ? "…እንደምን ዋላችሁ? "…እንደምን አመሻችሁ?
إظهار الكل...
star reaction 3🙏 938 268👍 110🕊 16 8🔥 6🤔 6🏆 5😱 3🤯 2😡 1
እንግዲህ መቃብር ጠንክረህ ተማር ዕውቀት ተሸክሞ መጣልህ መምህር "…ከአባታቸው ከክቡር በላይ ፈንታ እና ከእናታቸው ከክብርት ይታይሽ ወርቄ በዳንግላ ወረዳ አብሽካን ጊዮርጊስ ተወለዱ። ሦስት ዓመት ዓመት ሲሆናቸው ገና ሕፃን ሳሉ በአቸፈር ወረዳ ጊረረጊሽታ ጊዮርጊስ ጥቂት ጊዜ ከቆዮ በኋላ ልክ አምስት ዓመት ሲሞላቸው ወደ ናዳ ማርያም መጥተዋል። የቤተ ክህነቱን ትምህርት በስድስት ዓመታቸው እንደጀመሩ የሚናገሩት የኔታ ይባቤ ዘከራ ላይ ከመሪጌታ ተአምር እንዳለው መዝሙረ ዳዊት ተማሩ፣ ከዚያም ከመምህሩ ታናሽ ወንድማቸው ከመሪጌታ አበበ እንዳለው ዘንድ ደግሞ የቀሯቸውን ትምህርቶች ከላልሰው ከተማሩ በኋላ ጾመ ድጓን መማር ፈልገው መማሪያ መጽሐፉን የሚገዙበት አቅም ስላልነበራቸው እሱን ትተው መምህራቸው ቅኔ ይማሩ ዘንድ ስለፈቀዱላቸው ወደ ቅኔ ቤት ሄደዋል። በ1964 ዓም ደብረ ማርቆስ በመሄድ መጋቢት 21/1964 ዓም ዲቁና የተቀበሉት የኔታ ይባቤ በ1966 ዓም ወደ አሥሩ ደብር አቸፈር ወረዳ በመሄድ ቅኔ ከመምህር መንክር ስንሻው ዘንድ ለአንድ ዓመት ከተማሩ በኋላ ወደ ናዳ ማርያም ተመልሰው በመምጣት፣ ወደተለያዩ መምህራን ዘንድ በመሄድ ተምረዋል። "…የኔታ ቅኔ ለመማር በገቡ በዓመቱ ተቀኙ፣ ወዲያው ቅኔ በተቀኙ በዓመቱ አስነጋሪ ሆኑ፣ ቅኔ አስነጋሪ በሆኑ በዓመቱ ደግሞ ቅኔ ዘራፊ ሆኑ። በመቀጠል ሀዲሳት ተማሩ፣ ከአቶ ገብረ አምላክ ብሉይ ኪዳንን፣ መርጡለ ማርያም በመሄድ ከመምህር ኃይለ ኢየሱስ ዘንድ ፍትሐ ነገሥት፣ ኅፁፃኑን ተምረዋል። ጵጵስናን፣ እልቅናን እምቢኝ ያሉት የኔታ ይባቤ አቡሻኸርም ተምረዋል። ወደ ጎንደር እና ጫካ ዋልድባም ለመሄድ አስበው ፈቃደ እግዚአብሔር ሳይሆን ቀርቶ ተመልሰው ሐሙስ ጥቅምት 20/1979 ዓም ወደ ናዳ ማርያም ገብተው ሕይወታቸው እስከአለፈበት ዕለት ድረስ ጉባኤ ቤት ዘርግተው ዕልፍ ሊቃውንት አፍርተው አልፈዋል። "…የዐማራ ፋኖ ትግል ከተጀመረ በኋላ ግን የኦሮሙማው ብልፅግና አገዛዝ በጎጃም ክፍለ ሀገር በዐማራ ፋኖ ኃይሎች ለደረሰበት ሽንፈት ሽንፈቱን መቀበልና ማመን ሲያቅተው ቆይቶ የጦስ ዶሮ ሲፈልግ የጦስ ዶሮ ይሆኑት ዘንድ በዚያውም ኦርቶዶክስን ከምንጩ ለማድረቅ ይረዳው ዘንድ ፋኖ አልሸነፍ ያለው፣ እንደ እነ የኔታ ይባቤ ያሉ ሊቃውንት ስለሚጸልዩለት ወዘተ ነው በማለት፣ ከዚያም አልፎ አርበኛ ዘመነ ካሤን ይነግሥ ዘንድ ቅብአ መንግሥት የቀቡት የኔታ ይባቤ ናቸው በማለት፣ መጀመሪያ የአብነት ትማሪዎችን፣ በመቀጠል መሪጌቶችን እና ካሕናትን ከገደሉ፣ ከጨፈጨፉ በኋላ በመጨረሻም በጎንደሬው የፖለቲካ ቅማንት የትግሬ ዲቃላው ፋፍሕዴን አፋሕድ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም፣ በመቀጠል በአቢይ አሕመድ አማካሪ በዳንኤል ክብረት፣ በሸንጎና በኦሮሙማው ኃይል ውትወታ በብአዴኖቹ በእነ አቀንጭራ አያሌው መንበሩ ጭቅጨቃ በመከላከያ ሠራዊቱ ቁጥጥር ስር ውለው ወደ አዲስ አበባ ሊወስዷቸው የነበሩ ቢሆንም በመላው ጎጃም፣ በዐማራ ሙሉ ብአዴንን ጨምሮ ብዙዎች በማጉረምረማቸው ከእስር ሊፈቷቸው ችለዋል። "…ትናንት አንድ አርቲስት ወንደሰን አውራሪስ የሚባል ሰው ልክ እንደ አርቲስት ሚኪያ ኃይሉ፣ አርቲስት ኢዮብ መኮንን፣ አርቲስት ታምራት ደስታ፣ አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ልቤን እንዳሉ አፍታም ሳይቆዩ እንደሞቱት ይሄ አርቲስትም ልቤን እንዳለ በድንገት ታሞ መሞቱ ከተነገረ በኋላ ቀን ላይ ተማሪዎቻቸውን ሲባርኩ የዋሉት እና ያመሹት የኔታ ወደ ማደሪያቸው ገብተው ጠዋት አርፈው ተገኝተዋል ተብሏል። እኔ በእግዚአብሔር ሥራ አልገባም። በረከታቸው ይደርብን። አሜን። "…የነደደኝ ነገር ግን ሊቁን ሲሰድባቸው የከረመው አቀንጭራው የፓስተር ምስጋናው ደቀመዝሙር አያሌው መንበር የሊቁን ሞት ተከትሎ "ተቀሰፉ" ብሎ ጮቤ መርገጡን ሳይ እንዲሁም ይሄ በደቡብ ጎንደሬነት ስም የብልፅግና አሽከር ሆኖ ፀረ ጎጃም ትግል የሚታገለው ሰው ለወትሮው የፌስቡክ የኮመንት መስጫ ሰንዱቁን በሩን ቆልፎ ይደነፋ የነበረ ሰው ባልተለመደ መልኩ በየኔታ ሞት ካላገጠ በኋላ እንደ ጠበቀው ከጎንደር ዐማራ ዘንድ ተደርቦ የኔታን የሚሰድብ፣ አብሮትም ጮቤ የሚረግጥ ሰው ሲያጣና ከራሱ ከጎንደር ሰዎች የተቃውሞ ናዳ ሲደርስበት የለበጣ "ይቅርታ" ለመጠየቅ ተገድዷል። • የአባታችን በረከታቸው ይደርብን። አሜን። • ማስታወሻ፥ በነገው ዕለት ብልፅግና የጎንደር ዐማራን የበላይን ዕዝ ለመበተን ሊወስደው ስላቀደው አሰቃቂ ሴራ የደረሰኝን ቅድመ ማስጠንቀቂያ እፅፍላችኋለሁ። አርበኛ ሀብቴ ወልዴም፣ አርበኛ ሳሚ ባለድልም አብዝታችሁ ጸልዩ። ሁላችሁም የፋኖ መሪዎች ከወትሮው በተለየ ሁናቴ የሚጠብቅ እግዚአብሔር ቢሆንም እናንተም ቢሆን ንቁ፣ ጥንቁቅም ሁናችሁ ተገኙ። • የነገ ሰው ይበለን። ደኅና እደሩ።
إظهار الكل...
5.81 MB
star reaction 4 1 029🙏 328💔 166👍 121🕊 22🔥 13🤔 9🏆 7 6👌 6🤯 3
Photo unavailableShow in Telegram
"…በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚጥፍ የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አዲሱ መጣፊያ አሮጌውን ይቦጭቀዋል፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል። በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል የወይኑም ጠጅ ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ። • እንደምን አደራችሁ? • እንደምን አረፈዳችሁ? • እንደምን ዋላችሁ? • እንደምን አመሻችሁ?
إظهار الكل...
star reaction 2🙏 935 235👍 121🕊 7 5🤔 3🏆 1
Photo unavailableShow in Telegram
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር "…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ልክ 2:00 ሲሆን በዘመድ ቴቪ መርሀ ግብሩ ይጀምራል። እንደተለመደው ገባ ገባ በሉና ጠብቁን። • ቲክቶክ 👉 http://tiktok.com/@zemedkun.b • ZemedTv 👉 zemedtv.com/live.html • በትዊተር (×) 👉 x.com/i/broadcasts/1OwxWeEmdLpGQ • በራምብል 👉 rumble.com/v72fbd8--zemede-november-30-2025.html?e9s=src_v1_cbl%2Csrc_v1_upp_a • በሳታላይት ቴሌቭዥን 👉 Yahsat 52.5° East                       11977 H 27500 • ላይ ይከታተሉን። "…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ። 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል። • ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁን…!
إظهار الكل...
star reaction 1 362👍 131🙏 38👌 10🕊 8🏆 7🤔 6🔥 4😡 4🤯 1
Photo unavailableShow in Telegram
"…ነጭ ነጯን እየተዘጋጀን ነው። • አላችሁ አይደል…?
إظهار الكل...
star reaction 1 295👍 101🙏 35 5😡 3🕊 2🏆 2
Photo unavailableShow in Telegram
"…ነጭ ነጯን እየተዘጋጀን ነው። • አላችሁ አይደል…?
إظهار الكل...
👍 8🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
“…ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት። እግዚአብሔር ለሕዝቡ፥ በውስጥዋም ለተወለዱት አለቆችዋ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል። በአንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ እንደሚላቸው ይነግራቸዋል። ” መዝ 87፥ 5-7 • የዛሬው የኅዳር ጽዮን ማርያም በዓል ስለ 8 ዓበይት ነገሮች ይከበራል። ••• ፩፣ ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለን ስመ ጥር የአህዛብ ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበት ዕለትን በማሰብ። 1ኛ ሳሙ 1-6። ፪፣ ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተ መቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ። 1ኛ፣ ነገ 8፥ 1-66። ፫፣ ታቦተ ጽዮን በንግሥት ሳባ ልጅ በቀዳማዊ ምኒልክ አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ ምድር የገባችበትን ዕለት በማሰብ። ፬፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት በአብርሀ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት መሆኗ የታወጀበት ዕለት በመሆኑ። ፭፣ በብሉይ ኪዳን መስዋዕተ ኦሪት/የእንስሳት ደም ከሚሰዋባት ሙኵራብ / ወደ ሀዲስ ኪዳን/ አማናዊው በግ የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ የሚፈተትበት /" ጽዮን ማርያም ተብላ ወደ ቤተ ክርስቲያንነት የተቀየረችበት ዕለት በመሆኑ።  ፮፣ የቀደሙ ነብያት ስለ እመቤታችን በተለያየ ህብረ አምሳል ያዩበት፤ ለምሳሌ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ። ፯፣ በአረመኔዋ ዮዲት ጉዲት ከመፍረሱ በፊት፤ በሁለቱ ደጋግ ወንድማማች የኢትዮጵያ ነገሥታት በነበሩት በዘመነ አብርሀ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ የተሠራው ባለ አሥራ ሁለት ክፍሉ ቤተመቅደስ ሥራው ተጠናቅቆ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበትን ዕለት በማሰብ። ፰፣ በአረመኔዋ ዮዲት ጉዲት መነሳት ምክንያት ለ600 ዓመታት ያህል ወደ ዝዋይ ገዳም ተሰድዳ የነበረችው ታቦተ ጽዮን የስደት ዘመኗን ፈጽማ ወደ መንበረ ክብሯ አክሱም ጽዮን የተመለሰችበት ዕለት በመሆኑ፤ ይህንና ይህን በመሳሰሉ ምክንያቶች የህዳር ጽዮን በዓል በታላቅ ድምቀት ይከበራል። እንኳን አደረሳችሁ። • ለማንኛውም… "…እንደምን አደራችሁ? "…እንደምን አረፈዳችሁ? "…እንደምን ዋላችሁ? "…እንደምን አመሻችሁ?
إظهار الكل...
star reaction 8 1 002🙏 482👍 107🔥 16🏆 10🕊 7 4
04:51
Video unavailableShow in Telegram
• ሀኪሞች እንዲህ እያሉ ነው… "…በኦሮሙማው የብልፅግና አገዛዝ ትኩረት ባይሰጠውም የዚህ የማርቡርግ ቫይረስ ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል እያሉ ነው የህክምና ባለሙያዎች። የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን በሙሉ በአቢይ አሕመድ የመደመር ብልፅግና ወንጌል ሰበካና ጥቅሶች፣ ማኅበራዊ ሚዲያውም በቲክቶከር ቀልደኞች የተሞላ በመሆኑ በቫይረሱ ጉዳይ ቸልተኝነት እየበዛ ስለሆነ ዋጋ ሳያስከፍለን አይቀርም ነው የሚሉት። "…ለመጀመሪያ ጊዜ እዚሁ እኔ በስደት በምኖርባት በሀገረ ጀርመን በማርበርግ ከተማ እንደተከሰተ የሚነገርለት አደገኛና ገዳይ መድኃኒትም ሆነ ክትባት ያልተገኘለት ማርበርግ በኢትዮጵያ ጂንካ የጥቂት ሰዎችን ሕይወት ማጥፋት እንደጀመረ ሁኔታው ያሳሰበው የጂንካ ሆስፒታል ሓላፊ የነበረ ሀኪም ለዓለምአቀፍ ሚዲያዎች የቫይረሱን መከሰት መረጃ በመስጠቱ ምክንያት ከሥራው እንደተባረረ ይታወሳል። ይህ አደገኛ ቫይረስ ከደቡብ ክልል ከጂንካ ከተማ ተነስቶ መጀመሪያ ወደ ሀዋሳና አሩሲ ከዚያም አዲስ አበባ ከገባ በኋላም ጥንቃቄ ባለመደረጉ አሁን ላይ በተለይ ከታላቁ ሩጫ በኋላ በከፍተኛ ሁኔታ ውስጥ ውስጡን እየተስፋፋ መሆኑን ነው የህክምና ባለሙያዎች የሚናገሩት። አገዛዙ የሚወቀሰው እዚህ ላይ ነው። ይሄን ገዳይና አደገኛ ቫይረስ ሰዉ እንዲጠነቀው እያደረገ አይደለም። በተለይ በድህነት ኑሮአቸውን የሚገፉ የጤና ባለሙያዎች ቀዳሚ ተጠቂዎች እየሆንንም ነው እያሉ ነው። "…ማርበርግን እንደ ኮሮና በማስክ፣ እንደ ኤድስ በኮንዶም የምንከላከለው ቫይረስ አይደለም። ቫይረሱ የሚተላለፈው በቀጥተኛ ንክኪና በግብረ ሥጋ ግኑኝነት ወቅት በወንድ ዘር እና በብልት ፋሳሽ አማካኝነት ጭምር ይተላለፋል። ቫይረሱ ከህመምተኛው ጋር በሚደረግ ቀጥተኛ የደም ንክኪ፣ እንባ፣ ሽንት፣ ሰገራና ወዘተ በመሳሰሉት ይተላለፋል ነው የሚሉት። ህመምተኛው በተኛበት አልጋ፣ በለበሰው ልብስ፣ በተጠቀመበት መርፌ መጠቀምም በቫይረሱ እንድትያዝ ያደርጋልም የሚሉ አሉ። ቫይረሱ በሳል እና በትንፋሽ አይተላለፍም። ቫይረሱ ከኢቦላም የከፋ እጅግ አደገኛ ገዳይ ቫይረስ ነው። ግን ትኩረት አልተሰጠውም። "…እንዲያውም ይህን የማርበርግ ቫይረስ በተመለከተ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ማዕከል ፕሮፌሽናል ነርስ እና የማኅበረሰብ ጤና ባለሞያ የሆኑት የጤና ባለሙያ ባምላኩ አበባው የጻፉትን አጋራችኋለሁ። 1፦ በሽታው ምንድን ነው? • የቫይረሱ ዓይነት፦ ማርበርግ ቫይረስ የፋይሎቫይረስ (Filoviridae) ቤተሰብ አባል ሲሆን ይህም ኢቦላ ቫይረስ የሚገኝበት ቤተሰብ ነው። ለዚህም ነው ሁለቱም በሽታዎች ተመሳሳይ የሕመም ምልክቶች እና የሞት መጠን ያላቸው። • ክብደት፦ በሽታው ከባድ እና ከፍተኛ የሞት መጠን ያለው ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜ በተከሰቱ ወረርሽኞች በበሽታው ከተያዙት ውስጥ እስከ 88% የሚደርስ ሰዎች ሞተዋል። (እንደ ወረርሽኙ ሁኔታ ሊለያይ ይችላል) • ታሪክ፦ በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ በ1967 ዓ.ም በጀርመን ማርበርግ እና በፍራንክፈርት እንዲሁም በሰርቢያ ቤልግሬድ ከተሞች ተከስቷል። ቫይረሱ የመጣው ከዩጋንዳ በመጡ የላብራቶሪ ምርምር ዝንጀሮዎች አማካኝነት ነው ይባላል። 2፦ ስርጭት (በሽታው እንዴት ይተላለፋል?) • ዋናው ምንጭ፦ የማርበርግ ቫይረስ ተሸካሚዎች ፍራፍሬ ላይ የሚያዘወትሩ የሌሊት ወፎች (Rousettus bats) ናቸው። ሰዎች በቫይረሱ ሊያዙ የሚችሉት በእነዚህ የሌሊት ወፎች ባሉበት ዋሻዎች ወይም ማዕድናት ውስጥ በመገኘት ነው። • ከሰው ወደ ሰው የሚኖረው ስርጭት፦ ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በበሽታው የተያዘ ሰው ወይም እንስሳት በሚወጡ ፈሳሾች (ደም፣ ምራቅ፣ ማስታወክ፣ ሰገራ፣ ሽንት፣ የዘር ፈሳሽ እና ሌሎች) ጋር በቀጥታ በመገናኘት ነው። 3፦ ምልክቶች የበሽታው ምልክቶች በአብዛኛው ከ2 እስከ 21 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ ይታያሉ። የሚከተሉትን እንመልከት፦ • የመጀመሪያ ደረጃ ላይ፦ ከፍተኛ ትኩሳት፣ ከባድ ራስ ምታት፣ ከባድ የጡንቻና የመገጣጠሚያ ህመም፣ ድካም ስሜት። • ሁለተኛ ደረጃ (ከጥቂት ቀናት በኋላ) ከባድ ተቅማጥ፣ የሆድ ቁርጠት፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ የደረት እና የጉሮሮ ህመም። • የከፋ ደረጃ (ከ5-7 ቀናት በኋላ) ከባድ የደም መፍሰስ (ከአፍንጫ፣ ከድድ፣ ከዓይን እና የቆዳ ስር)፣ የጉበት እና የኩላሊት ድካም፣ የንቃተ ህሊና መሳት፣ የብዝሃ-አካል ሥራ መቆም (Multi-organ failure) እና ሞት። ከዚህ በተጨማሪ የዓይን መቅላት፣ የቆዳ ሽፍታ (በተለይ በደረት፣ ጀርባና ሆድ አካባቢ)። 4፦ የሚሰጠው ህክምና እና መከላከያ መንገዶች፦ •ፈውስ፦ ለጊዜው ቫይረሱን የሚያጠፋ የተረጋገጠ መድኃኒት ወይም ክትባት የለም። • ህክምና፦ የሚሰጠው ህክምና ምልክቶችን ለማስታገስ (Supportive Care) ነው። • ፈሳሽ መተካት (IV fluids)፦ በከፍተኛ ተቅማጥ እና ማስታወክ የጠፋውን ፈሳሽ መሙላት ነው። • የደም መፍሰስ ቁጥጥር፦ የደም ግፊትን ማረጋጋት እና የደም መርጋት መከላከል/ማከም። • የተጎዱትን የአካል ክፍሎች (ኩላሊት፣ ጉበት) ድጋፍ መስጠት። ~ በጣም አስፈላጊው ነጥብ፦ የግል መከላከያ ቁሳቁስ (PPE): የጤና ባለሙያዎች የታመሙ ሰዎችን ሲያክሙ ጓንት፣ ጋውን፣ ጭንብል እና የዓይን መከላከያ የግድ መጠቀም አለባቸው። ንጽህና: እጅን በአግባቡ በሳሙና መታጠብ፣ በተለይ የታመመ ሰው የነካን ወይም የጎበኘን ከሆነ በማለት ይመክራሉ። "…በጂንካ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ቆሟል። ከታላቁ ሩጫ በኋላ ብዙ ሰው በበሽታው ስጋት ላይ ወድቋል። አሜሪካኖቹ መጥተው ጤና ጥበቃ ሚንስቴርን፣ የውጭ ጉዳይን እና የገንዘብ ሚንስቴርን ሰብስበው ማብራሪያ ጠይቀዋል። አገዛዙ ግን ለሕዝብ ዘላቂ ጥቅም የሚሰጡ እንደ ትምሕርት እና የጤና መስኮች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ትቶ በየጫካው ለቱሪስቶች መዳሪያ አርቤርጎ ሲሠራ ስለከረመ፣ አልጋ ፈላጊ ደምበኛ ፈረንጆች ፈርተው በትሪልየን የሚቆጠር ገንዘብ የከሰከሰባቸው ሪዞርቶቹ ኦና እንዳይሆኑበት፣ በቡናቤት መብራት ያስጌጠው ልማት ተብዬው ማደናገሪያ ተመልካች እንዳያጣ በሚል ገዳዩን ቫይረስ ችላ ብሎታል። "…የቫይረሱን በኢትዮጵያ መገኘትና ሰዎችን መግደል መጀመር፣ መጀመሪያ ጀተገኘበት ስፍራም ሰብሮ ወጥቶ በሀገሪቱ መሰራጨት ዓለምአቀፍ ሚዲያዎች እየዘገቡት ነው። ቫይረሱ በሌላው ዓለም ከፍተኛ ድንግጤን ፈጥሯል በኢትዮጵያ ግን ይሄ ቀሽም የካድሬ ስብስብ የሆነ መንግሥት ችላ ብሎት ከባድ አደጋ ከፊታችን ተደቅኗል። ለምሳሌ ጂንካ ከተማ ደንታቢሱ አገዛዝ ይሁነኝ ብሎ ችላ ያለውንና በቴሌቭዥን 5 ሰው ሞቶ በቃ ጠፍቷል የሚል ይዘት ያለው ዜና መነገሩ ያበሳጨው፣ እንዲሁም በየቀኑ የሚሞተው ሕዝብ መጨመሩ ግራ የገባው ሕዝብ በራሱ ተነሳሽነት ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት መላክ እንዳቆመ ነው የሚነገረው። ሀገር ምድሩ ከተዳረሰ፣ ታላቁ ሩጫ፣ ኮንሰርት እያለ በደንብ ካቀባባ በኋላም፣ ዛሬ እንኳ የቲክቶክ አዋርድ እያለ በአዳራሽ ሰብስቦ ሕጻናት ሳይቀር እያስተሻሸ በቀጥታ ስርጭት ሀገሪቷ ምንም የሌለባት ይመስል የገፅታ ግንባታ በቲክቶከር ሲያስደሰኩር በደቡብ የአሪ ዞን ወደ ጂንካ ከተማ የሚገቡም ሆነ የሚወጡ ሰዎች እንዳይኖሩ በማገድ የትራንስፖርት አገልግሎት ማቋረጡን ዐውጇል። ከባድ ነው። • ከእግዚአብሔር ጋር ጥንቃቄ እናድርግ። በቅርቡ ለሁለተኛ ጊዜ ለአገዛዙ ጥያቄ ለማቅረብ እና የሥራ ማቆም አድማ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ያሉ የሕክምና ባለሙያ ወዳጆቼ መልእክት ነው።
إظهار الكل...
12.37 MB
star reaction 1 801🙏 190👍 142😱 14🏆 12 9🕊 7👌 5🤯 4🔥 3
• በዚህ ነገር ላይ ጥቂት ብንወያይ…! "…ይሄን ነገር ያሳየን አልሸባብ አይደለም። ሻአቢያም አይደለም። ኦነግም ቦኮሃራምም አይደለም። አይደለም። ይሄን ካርታ ሠርታ የተቀመጠችው ታላቋ የምትባለዋ ሀገር ሀገረ አሜሪካ ናት። "…አሜሪካ አክቲቪስት አይደለችም ተራ ስህተትም አትሳሳትም። አሜሪካ ይሄን ካርታ ሥላው ያሰቀመጠችውን ከሰንዱቋ አውጥታ ነው እዩት፣ ተመልከቱት የደገስኩላችሁን ድግስ ያለችን።  "…አሜሪካ ዋሽንግተን ካለው ከነጩ ቤተ መንግሥት አይደለም ካርታውን የለጠፈችው። የአፍሪካ የጦር መሪዋ ከአረመኔው አቢይ አሕመድና ከጨፍጫፊዎቹ ነፍሰ በላ የኦሮሙማ አረራጆች ከብራኑ ጁላና ከይልማ መርዳሳ ጋር ተመካክሮ ከወጣ በኋላ እዚያው ሽሮ ሜዳ አዲስ አበባ ከሚገጀው ከአሜሪካ ኤምባሲ ተቀምጦ ነው። "…ኤምባሲው እስከአሁን በጉዳዩ ላይ ይቅርታ አልጠየቀም። ኦሮሙማዎቹም የሚያፈቅሯት፣ የሚወዷት፣ ከአፋቸው የማትጠፋዋ ኢትዮጵያ፣ ያውም ቀይባህርን ስትመኙ ሙከጡሪ ድረስ ለኤርትራ ካርታ ሥለን ሰጥተናታል በማለት አሜሪካኖቹ በድፍረት ይሄን ካርታ ሲለጥፉ ምነው ዝም አሉ? እነ አያና ከአማሪካ ምነው ትንተና አልሰጡበት? "…ዘወትር የትግሬና የኦሮሞ ፖለቲከኞች ማንም ሳይጠይቃቸው ሲመቻቸው ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ ሳይመቻቸው ሲቀር ኢትዮጵያ ብትንትኗ ይወጣል የሚሉት ምን አይተው፣ ምንስ ሰምተው ነው? ሶሪያ፣ ሱዳን፣ ፍልስጤም፣ ሊቢያ፣ የመን፣ ኢራቅ፣ ሶማሊያ ሊያደርጉን ወስነዋል ማለት ነው አሜሪካኖቹ? "…እነ አያሌው መንበርስ ቢሆን ወልቃይት ካልተነካ በቃ የሚወዷት ኢትዮጵያ፣ ያቺ የሚያፈቅሯት ኢትዮጵያ በአሜሪካ እንዲህ ስትቦደስ ምነው ዝምታን መረጡ? • እደግመዋለሁ አሜሪካ ምንድነው ከኢሳያስ እና ከአቢይ ጋር የደገሰችልን? ኤርትራና ትግሬን ገንጥሎ አንድ ሀገር፣ ዐማራን እና ኦርቶዶክስን አጥፍቶ ኦሮማይዝድ የሆነ ሌላ ሀገር፣ ሶማሌን ገንጥሎ ሌላ ሀገር፣ ጋምቤላን ከደቡብ ቆርጦ ለደቡብ ሱዳን፣ ያስባሉ የሚባለው ሀሜት ልክ ነው፣ እውነት ነው ማለት ነው? • እስቲ ሀሳብ ስጡበት። እስከአሁንም ለእዚህ አደገኛ ዕቅድ እንቅፋት ብሎ የተፈረጀው ዐማራው እና ኦርቶዶክስም በሚፈለገው መጠን አላልቅ ብሏቸው እንጂ አጠዳድፈውት ሞቃዲሾ አድርገውን ነበር ብንል ማጋነን አይሆንም። • ሃሳብ ሓሳብ ዐሳብ…✍✍✍
إظهار الكل...
3.14 MB
star reaction 1 634👍 215💔 40🙏 31🤔 17🏆 13 11🔥 5🤯 5🕊 4👌 2
Photo unavailableShow in Telegram
መልካም… "…እንደተለመደው እግዚአብሔር ስሙን ጽፈን፣ ጠርተንም እናመሰግነው ዘንድ የፈቀደልን ተጠባቂዎቹ አንድ ሺ ሰዎች እግዚአብሔር ይመስገን በማለት መልስ ሰተን ያመሰግን ዘንድ የሚጠበቀውን የአመስጋኞች ቁጥር ሞልተናል። ለዚህም እናመሰግነው ዘንድ የፈቀደልን እግዚአብሔር ይመስገን። "…በመቀጠል ከአሁን ሰዓት ጀምሮ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ አንዳንድ ሓሳቦችን እያነሳን በቴሌግራም መንደራችን ስንወያይ ብናመሽ ምን ይላችኋል…? "…መቼም በዚህ በቴሌግራም መንደር እንደ እኔ እንደዘመዴ ቤት ሓሳብን በነፃነት የሚገለጽበት፣ ከፀያፍ ስድብ በቀር ከእኔም ጋር ሆነ እርስ በእርስ በተጻፈው ጉዳይ ላይ ብቻ አሁንም በጨዋ ደንብ፣ ክርክር፣ ሙግት፣ ውይይት የሚደረግበት ቤት የለም። በኢትዮጵያ ቴሌግራም እንዲወደድ ካደረጉት መሃል አንዱና ምንአልባትም ዋነኛው ይህ የእኛ ፔጅ ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም። "…ማኅበራዊ ሚዲያ የተፈጠረው ለእንደዚህ ዓይነት ጉዳይ ነው። ሰዎች ሓሳባቸውን በነፃነት ነገር ግን በጨዋነት፣ ደግሞም በጉዳዩ ላይ በቂ መረጃ እና መጠነኛም ቢሆን ዕውቀት ይዘው እንደ ዜጋ ስለሀገራቸው፣ እንደ አማኝ ስለ ሃይማኖታቸው ሓሳባቸውን ያሰፍሩ ዘንድ ነው የተፈጠረው። ማኅበራዊ ሚዲያ ከተፈጠረለት ዓላማ ውጪ ከሌላው ዓለም በተለየ መልኩ የተዋረደው እኛ ሀገር ሲገባ ብቻ ነው። ተሳዳቢዎች ተፅእኖ ፈጥረው መኪና የሚሸለሙበት ሃገር እኮ ሆናለች የዛሬይቱ የኦሮሙማዋ ኢትዮጵያችን። "…እኔ ዘመዴ እንደ ዳንኤል ክብረት የራሴን ሓሳብ አስታውኬ፣ አስመልሼ ሳበቃ ሌላው ሆዱን እየጎረበጠው ቋቅ የሚልበት ባያስመልስ እንኳ የሚያገሳበት መድረክ አልከለክለውም። እንደ አያሌው መንበር ተንኮል፣ ወንጀል መሥራቱን ሲያውቅ በሩን ጠርቅሞ ሲያበቃ ፋኖን እና የጎጃም ዐማራን የሚያሰድብ ነው ብሎ የሚያምንበት ልጥፍ ሲኖር የኮመንት መስጫ ሰንዱቁን ከፍቶ ሰገጤው አራዳ አራዳ እንደሚጫወትበትም አይደለም። ሰንዱቄ ክፍት ነው። መናገር ስትፈልግ ግን በጨዋነት ብቻ ይሁን። እኔ ተንፍሼ፣ ከጨጓራ በሽታም ተፈውሼ፣ ደም ግፊትና ስኳር እንዳይዘኝ አድርጌ አንተን እንዳትተነፍስ ማድረግ ወንጀልም፣ ኃጢአትም ነው። "…የእኛ ፔጅ እንደ ቴሌቭዥን ፕሮግራም የሚታይ ነው። እንደተወዳጅ የራዲዮ ጣቢያም የሚደመጥ ነው። እንደ ተወዳጅ ተናፋቂ ጋዜጣና መጽሔትም የሚነበብ ነው። የእኛ ቤት ከምር ልዩ ነው። "…ደሀ ተበደለ፣ ፍርድ ተጓደለ የሚባልበት ፔጅ ከእኛ ፔጅ በቀር ሌላ የትም ብትፈልጉ አታገኙም። ለሆድ የማይገዛ፣ ለፍቅረ ነዋይ የማይነበረከክ፣ ፊት ዓይቶ የማያዳላ፣ ወገኔ ነው፣ አባቴ፣ እናቴ፣ እህቴ፣ ወንድሜ ነው የማይል። አውቀዋለሁ፣ ጓደኛዬ ነው የማይል። በመልክ፣ በሀብት፣ በዘር፣ በጎጥ፣ በፖለቲካ አስተሳሰብ እቀርበዋለሁ ብሎ ያ አካል ከመስመር ከወጣ የማይምር ፔጅ ቢኖር ይሄ የዘመዴ ፔጅ ብቻ አይደለም እንዴ? ሌላ ይኖራል ግን ደግሞ አልገጠመኝም። በቀን ሺ ሰው እግዚአብሔር ይመስገን ብሎ የሚያስመልክ ከዘመዴ በቀር ከወዴት ልታመጣ ነው? "… ብዙ ሰው እኛ ቤት ሲመጣ ከተለጠፈው መልእክት እኩል በሚሰጡት ገንቢና አወያይ አስተያየቶች ተምሮ፣ ተዝናንቶ ነው የሚሄደው። የሰው አይን የሚያቆሽሽ ኮመንት እኔ ባላየው እንኳ ሕዝቡ በፉጨት እየጠራኝ "ዘመዴ block" ስለሚለኝ ተመልሼ መጥቼ እቀስፈዋለሁ። ለዚህ ነው የእኔ ፔጅ የማይሸተው፣ የማይገማው፣ የማይከረፋው፣ የማይቆንሰው፣ የማይጠነባው። ገባችሁ ኣ…? "…ስንቱ ሰው አማርኛ አጻጻፍ ለመደ። ፊደል፣ ሆሄያቱን በሙሉ ጠንቅቆ ዐወቀ። ሌላው ቢቀር እግዚአብሔር ብሎ በትክክል እንዲጽፍ ያደረግነው ቢቆጠር በሚልዮን ይደርሳል። በዚህ ፔጅ ስንቱን ገዳም ረዳንበት፣ ስንቱን ስደተኛ አገዝንበት፣ 3 ሚልዮን ዶላር ሰብስበን በኦሮሚያ የኦሮሞ ወሀቢያ እስላም ያረዳቸውን ቤተሰቦች፣ የተፈናቀሉት ሁላ ረዳንበት። ይሄ ፔጅ የተለየ የሆነው እናንተ ጨዋ፣ ሃይማኖተኛ፣ ዐዋቂ ኢትዮጵያውያን ከጀርባዬ ስላላችሁ ነው። አይደለም እንዴ? "…በዚህ ፔጅ ስንቱን ቃሪያ በሚጥሚጣ የሆነ ተግሳጽ አቅምሰን አስነጠስነው፣ ኮሶ፣ መቅመቆ የሆነ ርእሰ አንቀጽ እየጋትነው ፈወስነው። ስንቱን የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ ገላለጥነው፣ ስንቱን ነፍሰ በላ አጭቤ ሾተላይ ነቃቅለን ኦና አደረግነው። ስንቱ እዩኝ እዩኝ ባይ እንዲደበቅ አደረግነው። በአንጻሩ ስንትና ስንት የሳቱ፣ የጠፉትን ደግሞ በጅራፍ፣ በአለንጋ፣ በክትክታ ዱላ በመሰለ ጦማሬ ዠልጬ ዠልጬ መለስኩት፣ አደብም አስገዛሁት። ገና ወደፊትም እንቀጥላለን። "…በዚህ አቋሜ ጠላት ባይኖረኝም እንደ ጠላት የሚያዩኝ እንኳ ስጠፋ እናፍቃቸዋለሁ። አስሬ ቴሌግራማቸው ገብተው ይፈልጉኛል። ሲብስባቸው ይጽፉልኛል አልያም ይደውሉልኛል። እንደ መስታወት የሚያዩኝ ይጠቀሙብኛል። ሴራውን ስለማከሽፍበት ከጉረሮው ላይ ነጥቄ እንዳስጣልኩት አዳኝ ነብር ይቆጣኝ ይሆናል እንጂ የሚጋተተኝ የለም። አይኖርምም። ይሄን አሜሪካ ሄጄም፣ እዚህ ጀርመንም አይቼዋለሁ። "…በመጽሔት፣ በጋዜጣ የጀመርነው ትግል በፌስቡክ፣ በዩቲዩብ አልፎ ዛሬ በቴሌግራምና በዘመድ ቴቪ የሳታላይት ቴሌቭዥን ላይ ደርሷል። ይሄ ዝም ብሎ የሚመጣ ይመስልሃል አባው? እግዚአብሔር እንደ በልአም አህያ ሊጠቀምብህ ካልፈለገ በቀር እንዲሁ ስለለፈለፍክ፣ ስለቀባጠርክ ብቻ የሚሳካ ይመስልሃል? ያውም ወዳጅ ለማፍራት በማይመቸው ምላሴ፣ ማባበል በማያውቀው ብእሬ፣ መለማመጥ በማይመቸው ጠባዬ እዚህ የሚደረስ ይመስልሃል? በፍጹም ይሄ ከእግዚአብሔር ብቻ ነው። ከእግዚአብሔር አልኩህ። "…መልካም ዛሬም አጫጭር የመወያያ ተንኳሽ ሀሳቦችን በማንሳት ምሽታችንን አእምሮአችንን በማሠራት አብረን እናመሻለን። ኣ… ምን ትላላችሁ…?
إظهار الكل...
star reaction 1🙏 434 223👍 164🏆 17 8🔥 5🕊 5🤯 3🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
"…ልናገር እንደሚገባኝ ያህል እገልጠው ዘንድ ጸልዩልኝ። ቆላ 4፥4 "…እንደምን አደራችሁ? "…እንደምን አረፈዳችሁ? "…እንደምን ዋላችሁ? "…እንደምን አመሻችሁ?
إظهار الكل...
🙏 858 238👍 103🕊 19🤔 4 2
"…የግድያ ዜና እና የኮንሰርት ዜና። "…የግድያው ዜና በምሥራቅ አርሲ እንቆሎ ዋቤ ወረዳ በመጭቱ በቀቅሳ ቀበሌ ነዋሪዎች በነበሩ 11 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ የተፈጸመ መሆኑ የተነገረ ሲሆን አሁንም ታግተው ያሉና የመታረጃ ቀናቸውን የሚጠብቁ፣ በሰማይም፣ በምድርም የሚደርስላቸው የሌለ ምስኪኖች እንዳሉ ነው የሚሰማው። "…ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ ክረምት ሲገባ፣ በረዶው ሲበረታ፣ ቆፈን ብርዱ ሲያስቸግር፣ ስትረስ ጫን ሲል፣ ቫይታሚን ዲ ሲያጥር ዘና ፈታ ብለው ከሚኖሩበት አሜሪካ ለእረፍት ወደ አዲስ አበባ የሚሄዱት መምህራኖቻችን በአዲስ አበባ በሚሊንየም አዳራሽ ታላቅ የሆነ የገቢ ማሰባሰቢያ ኮንሰርት ማዘጋጀታቸውም ተነግሯል። "…በፊት በፊት ሀገር ሰላም በነበረ ጊዜ በአማሪካ በረዶና ክረምት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት መጻፍ፣ ካሴት፣ ሲዲና ቪሲዲ በመቸብቸብ፣ ሸቀጣቸውን በነፃ ወደቧ፣ ቀረጥና ቫት በማታውቀው ቤተ ክርስቲያን ላይ አራግፈው፣ በዚያውም በጨርጨር ሥጋ ቤት፣ በባልደራስ ጠጅ በሸነና ብለው፣ አለፍ ሲል በእከካም፣ በቋቁቻና በደረቆቻ ዘመናቸው በሚያወረቋቸው ወዳጅ ዘመድ ጓደኞቻቸው ላይ አነጅበው፣ ሀብታም ሀብታም ተጫውተው፣ እንቁልልጬ ብለው የእረፍት ጊዜአቸውን ጨርሰው ይመለሱ የነበሩት ዕንቁ የተዋሕዶ አርበኛ መምህራኖቻችን አሁን በሀገሪቱ ሰላም በመጥፋቱ፣ ከአዲስ አበባ ወጥቶ ማገልገል አይደለም ማገልገል ቤተሰብ መጠየቅ ራሱ በመቅረቱ አዲስ አበባ ቆይተው፣ የቻሉቱ ሰይፉ ፋንታሁን፣ ብላ ብላ ቀርበው፣ ደስኩረው፣ ያልቻሉቱ ደግሞ በየአጥቢያው በክብር እንግድነት ተጠርተው በጳጳስ ክብር እየተጋበዙ ያን ወንጌል የጠማውን፣ መምህራን አልቀው አስተማሪ አጥቶ የመምህር ያለህ ብሎ ለሚጸልየው አዲስ አበቤ ቃሉን መግበው እነሱም ጨርጨር ተመግበው ይመለሳሉ። "…የአሁኑ ለየት የሚለው የሄኖክ ኃይሌ የገና ዋዜማ ኮንሰርት እየደረሰ ስለሆነ፣ የሰሜኑን የደብረ ሮሀ ቅዱስ ላሊበላን ቤዛ ኩሉ እንዲሸፍን በኦሮሙማው ስፖንሰር እየተደረገ፣ የመንግሥታዊ ሚዲያ ሽፋን እየተሰጠው፣ በሮም ካቶሊክ፣ በጎጃም ቅባት እና በትግሬ መንበረ ሰላማ ስፖንሰር ተደርጎ ለሚቀርበው ዳንኪራ የፕሮሞሽን ሥራ ለመሥራትም ስለታሰበ በመቄዶንያ ስም በሚሊንየም አዳራሽ አዳሜና ሔዋኔ 300 የኢትዮጵያ ብር እየከፈለ እንዲገባ የጥሪ ማስታወቂያ ለጥፈው ታይተዋል። "…ለእኔ ቀሲስ ተስፋዬም፣ ቀሲስ ዘበነም ሁለቱም ወንድሞቼም፣ በክህነት አባቶቼ ናቸው። ነገር ግን መምህሮቼ ሊሆኖ እንደማይችሉ ከወሰንኩ ቆይቻለሁ። በአሜሪካ ሁለቱም ቤተ ክርስቲያን አላቸው። ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ የአርሴማ ገዳም ድረስ ጋብዞኝ ሄጄ አይቼዋለሁ። ሁለቱም የአሜሪካንን ምዕመናን አያያዙን በደንብ ያወቁበት መምህራነ ወንጌል ናቸው። በተለይ ተስፋዬ መቆያ 17 ስታዲየም የሚያህል መሬት በዋሽንግተን አቅራቢያ የገዛና የቅድስት አርሴማን ገዳም የገደመ ጀግና ወንድም ነው። ቅድስት አርሴማን የገዙት እናቶች እና አባቶች ቤተሰቦች በኢትዮጵያ እየታረዱ፣ እየተጨፈጨፉ አያዩ፣ ከተናገርን ከአገዛዙ ጋር እንቀያየማለን፣ ከተቀያየምን ደግሞ ቢዝነሳችንን ውኃ ይበላዋል ብሎ በመፍራት አፍን ለጉሞ ኢትዮጵያ እየተመላለሱ ሾው ማሳየት ኢደብራል። "…ከሁሉ የሚገርመኝ ቀሲስ ዘበነ ለማ ነው። ዘመዶቹ፣ ቤተሰቦቹ አሩሲ ናቸው። በአሩሲ ኦርቶዶክሱ እየጸዳ፣ ዘሩ እየተጨፈጨፈ ነው። የእሱም ዘመዶች አደጋ ላይ እንደሆኑ ነው የሚሰማው። ቀሲስ ዘበነ ያሳደገችው፣ ታዋቂ ያደረገችው፣ ተጽእኖ ፈጣሪም ያደረገችው፣ ከትቢያ አንስታ ዶላር ላይ የዘፈዘፈችው፣ እንደ ንጉሥ እንዲከበር ያደረገችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት። በተለይ ዛሬ የሚታረዱት የዳር ሀገር ክርስቲያኖች እነ ቀሲስ ዘበን ጨምሮ አሁን ያሉትን አገልጋዮች በሙሉ ጉባኤ እየጠሩ፣ ሰንጋ አርደው፣ ሆቴል አሳርፈው፣ የኪስ ገንዘብ አበል አሸክመው፣ ካሴትና መጻሕፍቶቻቸውን አራግፈውባቸው፣ ጭቅቅት፣ እከካቸውን ያራገፉላቸው ናቸው። አንዳቸውም ባላቸው ተጽእኖ ፈጣሪነት ተጠቅመው ለዚህ ለሚሞት ለሚረግፍ ሕዝብ ድምጽ አለማሰማታቸው ነው የሚነደኝ። መሞታችሁ እንደሁ አይቀር። • አሁን ላይ ለእነዚህ አስመሳይ ሰው መሳይ በሸንጎዎች፣ የቤት ቀጋ የውጭ አልጋዎች፣ ከአዲስ አበባ የማይወጡ የሀረር ሰንጋዎች፣ አብጠው ሊፈነዱ የደረሱ ባሉን ፊኛ መሳይ ባለሻኛዎች፣ ሀገር ተርቦ ሕዝቤ አመዳም የአሸቦ ዕቃ በመሰለበት ሀገር እንደ ሞዴላ ሞዴል የቀሚስ ዓይነት እየቀየሩ፣ እንደ አቢይ አህመድ ቡቶክስ እየተወጉ፣ በሜካፕ አብደው በየመድረኩ እየዞሩ ከርሳቸውን የሚሞሉ፣ የመድረክ ሱሳቸው፣ የመታየት ሀራራቸው አዙሮ ሊደፋቸው ሲያሰቃያቸው በሜቄዶንያ ስም ተከሰቱ። ያናደደኝ ይሄ መሸሸጊያ ምሽጋቸው ነው። "…ከምር አሁን ሜቄዶንያ ነው የአሩሲ ኦርቶዶክሳውያን ርዳታ፣ እገዛ፣ መጽናናት የሚያስፈልጋቸው? ከንቱዎች። አስመሳይ ቀጣፊዎች። ምናምን ብዬ ጓ ልል አልኩና፣ አሰብኩና ኦሆሆ ደግሞ ዕንቁ መምህራኖቻችንን አትናገሩብን ብለው እነ ዮኒ ማኛ፣ እነ ሞጣ ቀራኒዮ፣ እነ ቤታዮ፣ እነ ማማር ዘመቻ እንዳይከፍቱብኝ ብዬ ከአፌ መለስኩት። ለትንሽ ተሳስቼ ነበር። • አሁን ላይ ይቅርታ አድርጉልኝ አትቀየሙኝና ለእኔ ከመቄዶንያ የአሩሲ ጭፍጨፋ ይበልጥብኛል። • የመግቢያ ዋጋ 300 ብር ነው እንዳትረሱ።
إظهار الكل...
star reaction 4 968🙏 210👍 180💔 67🤔 25🏆 17🔥 15🕊 10 3
• እንዴት አገኛችሁት…? "…ሰሞንን የአሜሪካ መንግሥት በአፍሪቃ የወታደሮቿን አለቃ ልካ ከአቢይ አሕመድ፣ ከብራኑ ጁላና ከይልማ መርዳሳ ጋር በምን ጉዳይ እንደሆነ ባይታወቅም ብቻ ተመካክረው ከተለያዩ በኋላ ኦቦ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ "አሜሪካም ወደ ቀይ ባሕር እንድንወጣ ትፈልጋለች" ብሎ መግለጫ ከሰጠ በኋላ የአማሪካው ወታደሩ ሰውዬ እዚያው አዲስ አበባ በአማሪካ ኤንባሲ መግለጫ ሲሰጥ ይሄንን ካርታ ተጥቅሞ ነበር አሉ። "…ካርታው የምትመለከቱት ነው። ከታች ከአፋር ጫፍ ወሎን፣ ትግራይን፣ በጎንደር ወልቃይትን ለዐማራ ትቶ ግዙፍ የሆነ ካርታ ነው አሜሪካ ያሳየችን። ሲመስለኝ ወደ ቀይባህር፣ ወደ ወደብ፣ ወደ አሰብ ለመሄድ የምትሞክሩ ከሆነ ጭራሽ የያዛችሁትንም ታጣላችሁ ዓይነት መልእክት ያዘለ ይመስላል። የፌስቡክም ሆነ የትዊተሩ ልጥፍ ለአንድ ሰዓት ያህል እንዲቆይ፣ ሻአቢያም፣ ብልጽግናም፣ ወያኔም ኦነግም፣ ሱማሊያም ግብጽም። እስራኤልም ፍልስጤምም፣ አውሮጳም እስያም እንዲያዩት ከተደረገ በኋላ ልጥፉ እንዲነሣ ተደርጓል። "…አንዲት እህቴ ከዓመታት በፊት እንዲህ ብላ አጫውታኝ ነበር። እስራኤል ሀገር ለጉብኝት ሄጄ አለችኝ፣ እስራኤል ሀገር ለጉብኝት ሄጄ በአንድ ባለኮከብ ሆቴል ነበር ያረፍኩት። ኤርትራ ከተገነጠለች በኋላ ነበር የሄድኩት። በሆቴሉ ውስጥ በትልቁ የኢትዮጵያ ካርታ ተለጥፎ አየሁ። ጠጋ ብዬ ሳየው ካርታው አሁን አሜሪካ የለጠፈችውን ካረረታ የመሰለ እና ከታች የድሮው ሐረርጌ፣ ከምዕራብ ጋምቤላ አካባቢ ከኢትዮጵያ አካል የተለዩ ሆኖ የተሣለ ካርታ ነበር ያየሁት አለች። ወዳጄ ባለሙያም ስለነበረች የሆቴሉን ሥራ አስኪያጅ ጠርታ ይሄ ምን ማለት ነው ብላ ጠይቃው እንደነበርና ምንም ዓይነት በቂ ምላሽ እንዳላገኘች ነበር ያጫወተችኝ። የሆነ የቆየ የተደገሰ ነገር አለ ማለት ነው። "…አቢይ አሕመድ በአሜሪካ ድጋፍ መጥቶ ሥልጣን እንደያዘ የመጀመሪያ ሥራውን ያደረገው በጽ/ቤቱ በራፍ ላይ ሦስት ቦታ የተጎመደች ኢትዮጵያን ነበር በሃውልት ቀርጾ በማስቀመጥ ነጩም፣ ጥቁሩም፣ አረቡም ሲመጣ እንዲጎበኘው ያስደረገው። ይሄንኑ ካርታ በሃውልት ቀርጾ ካስቀመጠ 8ተኛ ዓመቱን ይዟል። "…አሜሪካ የትዊተር እና የፌስቡክ ልጥፏን አንሥታለች። ከእኛ አእምሮ ግን ተለጥፎ እንደተቀመጠ ነው። ለሀገረ እስራኤል ምሥረታ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉባኤ ላይ በነበረው የድምፅ አሰጣጥ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ድጋፍ በመንፈግ፣ ከዐረቦቹም ጋር ከምቃቃር በድምፀ ተአቅቦ ልለፈው በማለት ለእስራኤል ድጋፍ ባለመስጠታቸው ምክንያት ቂም እንደተያዘባቸውና በዚያው የዘውድ ሥርዓቱም፣ የኢትዮጵያ አንድነትም ሞት እንደተፈረደበት የሚናገሩ አንዳንድ መተርጉማን አሉ። ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ፣ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት ነኝ እያሉ እንዴት ለዐረቦቹ ያደላሉ ብለው ነው አሉ የፈረዱባቸው። "…ከላይ እስከታች ከውኃው አራቁን። አሁን ደግሞ ኤርትራን ደብረ ሲና ጣርማ በር ድረስ ስበው ካርታ ይሥሩልን? 😂 … ሳቁ እናንተማ ምን አለባችሁ። ለአዲስ አበባ 189 ኪሜ የቀረው የኤርትራ ካርታ፣ ግሸንንና ላሊበላን ለኤርትራ የሰጠ ካርታ። ከወልቃይት በቀረ እስከ ዳባት አጅሬ ጃናሞራ ድረስ የተዘረጋ ካርታ ሠርተው ያሳዩን? ምን አስበው ነው? "…የመጀመሪያው ቪድዮ ካርታውን አስገብተው የለቀቁት ሲሆን ሁለተኛው ቪድዮ ግን ያንን አውርደው ግብዳዋን ኤርትራን አውጥተው የለጠፉት ነው አማሪካኖቹ።  • እስቲ ሓሳብ ስጡበት።
إظهار الكل...
3.14 MB
3.05 MB
star reaction 2 604🙏 122👍 116🤔 28🔥 13😱 8🏆 8🕊 7🤯 6 4
Photo unavailableShow in Telegram
"…ጻድቃን ድል ባደረጉ ጊዜ ብዙ ክብር አለ፤ ኀጥኣን ከፍ ከፍ ባሉ ጊዜ ግን ሰው ይሸሸጋል።” ምሳ 28፥12 "…እንደምን አደራችሁ? "…እንደምን አረፈዳችሁ? "…እንደምን ዋላችሁ? "…እንደምን አመሻችሁ?
إظهار الكل...
star reaction 1🙏 905 197👍 90💔 69🕊 12 3
Photo unavailableShow in Telegram
"…ልዩ መልር ግብር ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር "…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ዛሬ ረቡዕ ምሽት ልክ 2:10 ሲሆን በዘመድ ቴቪ መርሀ ግብሩ ይጀምራል። እንደተለመደው ገባ ገባ በሉና ጠብቁን። • ቲክቶክ 👉 http://tiktok.com/@zemedkun.b • ZemedTv 👉 zemedtv.com/live.html • በትዊተር (×) 👉 x.com/i/broadcasts/1ZkKzZdmmWvKv • በራምብል 👉 rumble.com/v72bbim--zemede-november-11-2025.html?e9s=src_v1_cbl%2Csrc_v1_upp_a • በሳታላይት ቴሌቭዥን 👉 Yahsat 52.5° East                       11977 H 27500 • ላይ ይከታተሉን።
إظهار الكل...
👍 373 149🙏 42🔥 10 5🕊 3😡 3🤯 1🏆 1
Photo unavailableShow in Telegram
መልካም… "…ምሽት 2:00 ሰዓት በቀጠሮአችን መሠረት በዘመድ ቴቪ ቀጥታ የሳታላይት ስርጭት እና በዘመድ ቴቪ የራምብል እና የትዊተር ገጾች ከች እንላለን። በዘመድ ቲክቶክም ጠብቁን። • ዛሬ እጅ እና ጆሮ ቆራጩን ሰሞነኛ የብልጽግናን አጀንዳም ለሕዝብ ፍርድ እናቀርበዋለን። • ቆራጩ ማነው? • ከነማን ጋር የነበረ ነው? አጥበን እናሰጠዋለን። የዲያብሎስ ሴራማ መፍረስ አለበት። አይደለም እንዴ? • ጥቂት ቆይቼ ከስቱዲዮ ሊንክ እንደተላከልኝ እለጥፍላችኋለሁ። • አላችሁ አይደል…?
إظهار الكل...
🙏 334👍 151 92 10🔥 3🤔 2🕊 2🤯 1🏆 1
"…እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥ ማቴ 24፥15 • እንደምን አደራችሁ? • እንደምን አረፈዳችሁ? • እንደምን ዋላችሁ? • እንደምን አመሻችሁ?
إظهار الكل...
star reaction 1🙏 761 200👍 89💔 23 14😡 11🕊 10🔥 8🤔 1
"…እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥ ማቴ 24፥15 • እንደምን አደራችሁ? • እንደምን አረፈዳችሁ? • እንደምን ዋላችሁ? • እንደምን አመሻችሁ?
إظهار الكل...