ar
Feedback
ግጥም ብቻ 📘

ግጥም ብቻ 📘

الذهاب إلى القناة على Telegram

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13@wegoch @Words19@seiloch @shiyach_bicha@zefenbicha @leul_mekonnen1

إظهار المزيد
2025 عام في الأرقامsnowflakes fon
card fon
65 782
المشتركون
-1524 ساعات
-357 أيام
-31130 أيام

جاري تحميل البيانات...

سحابة العلامات
لا توجد بيانات
هل تواجه مشاكل؟ يرجى تحديث الصفحة أو الاتصال بمدير الدعم الخاص بنا.
الإشارات الواردة والصادرة
---
---
---
---
---
---
جذب المشتركين
ديسمبر '25
ديسمبر '25
+150
في 0 قنوات
نوفمبر '25
+202
في 0 قنوات
Get PRO
أكتوبر '25
+124
في 0 قنوات
Get PRO
سبتمبر '25
+154
في 0 قنوات
Get PRO
أغسطس '25
+182
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '25
+171
في 0 قنوات
Get PRO
يونيو '25
+164
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '25
+257
في 1 قنوات
Get PRO
أبريل '25
+265
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '25
+292
في 0 قنوات
Get PRO
فبراير '25
+245
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '25
+343
في 0 قنوات
Get PRO
ديسمبر '24
+394
في 0 قنوات
Get PRO
نوفمبر '24
+201
في 0 قنوات
Get PRO
أكتوبر '24
+217
في 0 قنوات
Get PRO
سبتمبر '24
+90
في 0 قنوات
Get PRO
أغسطس '24
+141
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '24
+178
في 0 قنوات
Get PRO
يونيو '24
+255
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '24
+378
في 0 قنوات
Get PRO
أبريل '24
+468
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '24
+410
في 0 قنوات
Get PRO
فبراير '24
+263
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '24
+188
في 0 قنوات
Get PRO
ديسمبر '23
+229
في 0 قنوات
Get PRO
نوفمبر '23
+232
في 0 قنوات
Get PRO
أكتوبر '23
+194
في 0 قنوات
Get PRO
سبتمبر '23
+189
في 0 قنوات
Get PRO
أغسطس '23
+147
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '23
+56
في 1 قنوات
Get PRO
يونيو '23
+7
في 2 قنوات
Get PRO
مايو '23
+287
في 0 قنوات
Get PRO
أبريل '23
+68
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '23
+295
في 0 قنوات
Get PRO
فبراير '23
+210
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '230
في 0 قنوات
Get PRO
ديسمبر '220
في 0 قنوات
Get PRO
نوفمبر '220
في 0 قنوات
Get PRO
أكتوبر '22
+37
في 0 قنوات
Get PRO
سبتمبر '22
+170
في 0 قنوات
Get PRO
أغسطس '22
+193
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '22
+181
في 0 قنوات
Get PRO
يونيو '22
+222
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '22
+320
في 0 قنوات
Get PRO
أبريل '22
+333
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '22
+713
في 0 قنوات
Get PRO
فبراير '22
+281
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '22
+97 014
في 0 قنوات
التاريخ
نمو المشتركين
الإشارات
القنوات
26 ديسمبر0
25 ديسمبر0
24 ديسمبر+16
23 ديسمبر+5
22 ديسمبر+1
21 ديسمبر+4
20 ديسمبر+6
19 ديسمبر+8
18 ديسمبر+9
17 ديسمبر+6
16 ديسمبر0
15 ديسمبر+7
14 ديسمبر0
13 ديسمبر+7
12 ديسمبر+6
11 ديسمبر+15
10 ديسمبر+4
09 ديسمبر+1
08 ديسمبر+7
07 ديسمبر+4
06 ديسمبر+3
05 ديسمبر+9
04 ديسمبر+2
03 ديسمبر+10
02 ديسمبر+12
01 ديسمبر+8
منشورات القناة
እሳት ///////////////// እንደ ከሰል ፍሙ ንዳድሽ ቃጠሎ፣ ባናገርሽኝ ቁጥር ንዴቴ አይሎ፣ ጨጓራ ኩላሊት ምን የቀረሽ አለ ባንቺ ውስጤ ተቃጥሎ። ከፍምም ፍም አንቺ፣ ምታንገበግቢ የምታስደስቺ ። ሙቀትሽ ሙቅ አይደል በጣሙን ያነዳል፣ ማንስ አንቺን ችሎ ሁሌ ይቃጠላል። እኔ፣ አንቺን እያፈቀርኩ ብታፈን ብቃጠል፣ እኔ እየቀለጥኩኝ አረኩሽ ነበልባል። ፍቅር ይሉት እሳት አንቺ የሱ ትኩሳት፣ ንዳድ ከቃጠሎ አርገውት ልቤን ቤት። ምድጃ አካሌ ውስጥ እሳት ሆነሽ አንቺ፣ ፍቅርሽ ውሃ አድርጎ አዛመደኝ ካንቺ። አቃጥይ አንድጂኝ መላ አካሌ እስኪተን፣ የዘነብኩኝ ለታ እንዳደርግሽ ሰከን። @abela_black @getem @getem @getem

2 805200

2
በጅምር የቀረ //////////////// ከትላንቷ ሚያርቅ ከነገ ሚያግባባት፣ ከዝሙት አለሟ አሽሽቶ ሚያርቃት። ያቺ ዘማዊ ሴት ትልቅ ግንብ ገነባች፣ ሰራችው ቆለለች ከትላንት ራቀች፣ የሀጢያት ቡትቶን አውልቃ እየጣለች። ከዘመናት በኋላ መኖርን ስትጀምር፣ ታሪኳን የሚያውቁ፣ የድንጋይዋን ክምር ይገፉባት ጀመር። ወንጭፋቸው የእሳት የጠጠር ግርፋት፣ የስሜት ልባቸው ተመለሺ እያላት። ሴትነቷ ጎልቶ ሰውነት ተረስቶ፣ የዝሙት እጃቸው ካብ ድንጋይ አንስቶ። ደጋግመው ወገሯት ደጋግመው ገፉባት ፣ የኔ ያለችው አጥር እማይሆን ሆነባት፣ ትላንት ከሷ በራፍ እንሙት እንዳላሏት፣ ትላንት ከሷ ገላ አንውጣ እንዳላሏት፣ ስንት ቃል ውለታ እንዋል እንዳላሏት። በገንዘብ በቁጥር የገዙትን ገላ፣ በዲናር የያዙት የሴትነት ወዟ። አውልቃው ብትወጣ መኖር ልትጀምር፣ በግንቧ ፍርስራሽ ከተቷት መቃብር። @abela_black @getem @getem @getem
4 745
3
እግዜር ስላንቺ ይፈራኛል እክለፈለፋለሁ የመልዓክት ስልኮች ላንቺ ሲደውሉ ይወስዱሻል ብዬ እኔ ሳዋራቸው ይኮላተፋሉ..... ይርበተበታሉ.... የማፍቀሬን ስስት ልኩንም ያውቃሉ ተላኪ መልዓክት ከወደቅሽባቸው የህመም አልጋዎች መጠው ቢፈልጉም የቱ ጋር ነው የወደቅሽው ከእኔ በቀር እንኳ መልዓክትም አላወቁም ደብቄሻለሁና ከእግዜር ጋ አኩኩሉ ሞትም እኔን ፈርቶ እግዜሩን ይዋሻሉ ቢዋሹም ስዋዋል የሰማይን መሬት ለእረፍትሽ እንዲሆን ገነት ታንሳለች የእቅፌን ሚዛን የመዘንኩት እንደሆን ጉሙን አጭጄው ለወደቅሽበት ትራስ ለማድረግ ደረት ላለው ልብ ምን ይሰራል ከቶ ቁስን ማፈላለግ .....ልክ እንደሰርግ መልዓክት ይፈሩኛል ሊጠሩሽ ሲመጡ ሰፈር ሲጠይቁ የስስቴን መጠን የማፍቀሬን መጠን ልኩን ስለሚያውቁ እግዜር ይፈራኛል አንቺን በመውድ ውስጥ እኔ እንዳልወሰድ ታማ አልጋ ለተኛች ፍቅረኛ ላለችው ታስፈራለችና ሞት የሚሏት መንገድ ንዴቴ እጥፍ ነው ያውቁታል ስስቴን የመንሰፍሰፍ ጦሩ ያልታዘዙትን ሟች እንደሚያመጡ ሲያውቁ መልዓክትም ፈሩ ለምን...? ስልኩን ሲደውሉ አንቺን ጠራው ብለው እኔን ስለሚጠሩ ግዕዝ ሙላት @GEEZ_MULAT ስለ ሁለቱ የሞቱ ፍቅረኞች መታሰቢያ @getem @getem @getem
5 198
4
የፈገግታዬ ጦር ////////////////// በጥርሴ የገደልኩት የጠላት ጋጋታ፣ ሶምሶምን ያስንቃል ቢወዳደር ላፍታ። የወንጭፍ ውርወራ የበትር ዱላቸው፣ የቃላት የስድብ የንቀት ጦራቸው፣ የጠለፈኝ ገመድ የነሱ እቅዳቸው። የወደኩኝ ለታ ያረፈብኝ ትቢያ፣ ቀና አልኩኝ ሲባል ጠላቴ እንደ አጥቢያ። ከከፍታ ቆሞ ዝቅ ብሎ ቢያየኝ፣ በሳቄ ገደልኩት ገና ቀና እንዳልኩኝ። @abela_black @getem @getem @getem
6 015
5
             ናፍቆ.... ቦታ ምረጫ ትቶ ሲበላ ከኔውጋ እረፍት አየነሳ አልተኛ እስኪነጋ መባነን ልማዴ በሸለብታው መሀል አምጣልኝ እያለ ናፍቆትሽ ይጮሀል ሊያይሽ አስቦ በአካል እንድትመጪ ቢጠራሽ ደመና ጋርዶሻል አትወጪ ላላለቀው ፍቅር መለየት ለቀጣው ተሸክሜ ምዞር ከልቤ አላጣው ግር እንዳለኝ ግራው ለኔ አዘምብሎ ከአይኔ ሲያውለው ያለፈውን ስሎ አካላቴ ደክሞ አልታዘዝ ብሎ የሚያረገው ጠፍቶት በትዝታ ዝሎ ዛሬም ማዶ ያያል ፀሀይ ብትወጣ ከተራበሽ ልቤ ይዛሽ እንድትመጣ...። By #nimo @getem @getem @getem
7 373
6
ባልጀራዬ ላልኩት ሚስጥር ብዬ ብነግረዉ ፤ እሱም ለባልንጀራዉ አትንገር ብሎ ነገረዉ፤ ሲቀንስና ሲጨምር ለራሱ እንደተመቸዉ፤ ዞረ ዞረና ሚስጥሬ እኔ ጋር ደርሶ አረፈዉ። [ ዔደን ታደሰ ] @topazionnn @getem @getem
7 928
7
ነጠብጣብ ሀሳቦች (በእውቀቱ ስዩም) በዘመን አየር ፤ ጫጫታው ከብሮ በጩኸት መሀል፤ ዜማ ተቀብሮ ጆሮ ግንባር ላይ፥ ቤቱን ለመስራት እንዳልፈለገ ወደ ማጅራት አፈገፈገ:: **** የሞሰቡን ወግ፥ ፌስታሉ ወርሶት ለምለሙ እንጀራ ፥ ረድኤት አንሶት ቢጎርሱት እንባ ፥ ቢውጡት ብሶት ! **** ምንገዱ ሁሉ ፥የሚያሰናክል ቁልቁለት ሲያዝል ፥ የዳገት ያክል ስኬት በስኒ፥ ላባችን በጋን በወግ ለመሞት ሁሌ እየተጋን መኖር ዘነጋን:: By Bewuketu seyum @getem @getem @paappii
7 835
8
ዉርደት እና ኩነት እንደአካሄዳቸው በመንታ መንገድ ላይ ፍቱን ታዳኝ ናቸው... አንዱ በጋለው ናስ ከሰል ይደርባል... ሌላኛል ሲደላው... ደርቦ ሲሞቀው ውስጥ ውስጡን ይቀልጣል ውጪው እንደከሰል ጠቁሮ ሳያበቃ... ከማገዶው ገደል... ከፍሙ ስር ያድራል ሊነቃ ይልና.... .................. በዘብ ጣሩ ዘልቆ ፍሙ ለገረፈው... አንድ ጥያቄ አለው... .......................... ማጀት ባልጠፋበት ምቾት ሀገር ሆኖ ከተድላው ሰመመን በደን ስንከራተት.... እሳቱ ሳይነካኝ ፍሙ ስር ተኝቼ ባድር ምን አለበት??... በኢያሱ ከበደ ታህሳስ 7, 2018 ዓ.ም @getem @getem @paappii
8 009
9
(ምን መሰለሽ? ) ሌላን ሴት ጠይቀው ‘እሺ’ የተባሉ … በርግጥ ለአንዲት ቀን ፈክተው ይስቃሉ። ፡ ሆኖም የገረመን ፡ አንቺን ተለማምጠው ‘እንቢ’ ብለሽ እንኳን ድግስ ደግሰዋል.. ዳስ ጥለዋል ድንኳን። ፡ ‘እርሷን ሞክሪያለሁ’ ብለው ስላወሩ ስንቱን ሰው አየነው ኮርተው ሲከበሩ። (ሚካኤል አ) @getem @getem @paappii
7 386
10
'ደሀ አይደለሽም!' ~~~~~ ተወጣጠርሽ አሉ    ቆዳሽ እስኪጠብሽ ተመፃደቅሽ አሉ    መልክሽ እስኪበልጥሽ፤ ደግሞም ብለሽ ብለሽ    ንቀት ጀመርሽ አሉ ትናንትን ረስተሽ፣ ዛሬን ብትጎብዢ    በሰው 'ሰው' ብትሆኚ ሰውነትን ትተሽ! ~~~~ የሆነውስ ሆኖ ወቃሽ ተቺሽ በዝቶ     ብንጠላሽም እኛ፣ ማድረግሽ አይቀርም   በገንዘብ በሀብትሽ     እኛኑ ዘበኛ፤ እሱ አልበቃ ብሎም   በአሽሙር በሀሜት      ወጋ ቢያደርጉሽም፣ ይፈሩሻልና   ፊትለፊትሽ መጥተው     አይናገሩሽም..... ም ክ ን ያ ቱ ም    ደሀ አይደለሽም!!!!!!!! By @Weyblann    ያቡ @getem @getem @getem
9 750
11
እኔ ባይተዋር የእፍታ ብናኝ በየሄድኩበት ዕምባ ሚቀናኝ፤ በዬጥላው ስር የምሰባበር ያለ በረሃ የማላውቅ ሀገር፤ ከቁር ከሐሩር የተወዳጀሁ ገና ሽል ሳለሁ ኑሬ ያረጀሁ፤ ድስቴ ምጣዴ ያልተሟሸልኝ ፤ ከማማጥ በቀር ወልዶ መደሰት የማይኾንልኝ፤ - እኔ ባይተዋር የዕጣ ፍርደኛ ለጊዜ በደል የሌለኝ ዳኛ፤ የጊዜ ንጉስ ያለገላጋይ የሚበድለኝ ከማደግ በቀር ጥላት የሌለኝ፤ ልክ እንደ ብናኝ ያነስኩ የሳሳሁ ስበርር የምኖር እየተገፋሁ፤ ድንገት ተነስቶ ሰው የሚርበኝ በየትከሻው ማልቀስ የሚያምረኝ፤ በየትከሻው ጎጆ የሰራሁ ከሰው የምኖር ሰው እየፈራሁ፤ - እኔ ባይተዋር የምርጫ ጌታ፤ ሀገሬ ማዶ ከጉም ኮረብታ፤ ለብሶ የሚኖር የጭጋግ ኩታ፤ ዘሬ መከራ አድባሬ ዋይታ የማይሞላልኝ ሳስር ስፈታ ፤ አባቴ ለቅሶ እናቴ ለቅሶ ሕይወት ያቆመኝ ያለ ምሶሶ፤ ቢገልጡኝ ቁስል ቢነኩኝ ቁስል ቶሎ ሚደክመኝ ገና አረፍኩኝ ስል፤ - እኔ ባይተዋር ፎካሪ ሽፍታ ጫካ የማድር ድቤ ስመታ ፤ ሐዘኔን ትቼ የማልሰደድ ያለ በረሃ ሀገር የማልለምድ ፤ እንጀራዬ ዕውር ወጤ ደንቆሮ ሳለቅስ የምውል ግዋሮ ለግዋሮ፤ እኔ ባይተዋር የድብርት ራት ከወዳጅ በቀር የሌለኝ ጥላት። By Tewodros kassa @getem @getem @paappii
9 138
12
ጥበብ ////////////////////////// የቆሰለች ጉድፍ ነብሴን፣ አውሬ የሆነች ማንነቴን። አንቺ ቀርበሽ አላመድሻት፣ በመዳበስ ዝም አስባልሻት። የኔ ሂሶጵ ከጉድፌ ያነፃሽኝ፣ ዘማዊ ነህ ብለሽ እንክዋን ያልገፋሽኝ፣ አንቺን ላጠምድ ልሰርቅሽ ስል የሰረቅሽኝ፣ ሌባ ስሆን ዘብ ጠባቂሽ ያደረግሽኝ፣ ከሺ እንዳልሄድኩ ካንቺ እንዳልርቅ ያለገመድ የጠለፍሽኝ። ቃልሽ አስማት እጅሽ ደግሞ የአስማት በትር፣ ከነካሽኝ ተቀይሬ ካንቺ ስር ነው እኔ ማድር። ያንቺስ ይገርማል፣ ሰለሞንስ ያውቀው ይሆን ይህን ጥበብ፣ በነካው ሰው መጠበቅን ወይ መከበብ። በታሪክስ ይኖር ይሆን ቁርጥ አንቺን የመሰለ፣ ተቅበዝባዥን በማላመድ ከቤቱ ስር ሰው ያዋለ። እሷ ያጠመደች እኔን አሳ፣ ያለመረብ በዳበሳ። የያዘችኝ እኔን እሳት፣ ያለውሃ በእጅዋ ብልሃት። እኔም ብሄድ ዞሬ ከስዋ፣ ይሄ ልቤ ፍቅር አይረሳ። ማን አስተማራት ይህን ጥበብ፣ በዝምታ ዳብሳ አገኘች የኔን ልብ፣ ማን አስተማራት? ማን አስተማረሽ? ማን? @abela_black @getem @getem @getem
7 971
13
« የት ጠፋህ አንተዬ? » ታምሜ! ታምሜ ስሞት ከማይ ቆሜ ጥበቡን ባላውቅም መድሃኒት ልለቅም ፤ ከሰዎች ርቄ... ከጫካው ዘልቄ ቅጠል ሥራሥሩን ሞራ፥ ሥቡን፥ ማሩን አመዱን አፈሩን አፍሼ ለቅሜ ጨቅጭቄ ቀምሜ ወዙን አንጠፍጥፌ ባፍንጫዬ ባፌ አስርጌ ጠጥቼ ሕሊናዬን ስቼ ሞቼ ሞቼ ሞቼ ሞቼ ተነስቼ ..፤ « ሞት ተፋህ አንተዬ! » እውነትም ሞት ተፍቶኝ በሽታዬም ትቶኝ ሲታደስ ጤናዬ 'የሰው ልጅ ነኝ' ብዬ፤ እንደኔው ያመመው መንደሬን ላክመው መድሃኒት ታቅፌ፡ ብመለስ ከቅዬው ሰዉና ህመሙን ፡ ምን ብዬ ልለየው? « ምን አልከኝ አንተዬ? » ከደዌ በሽታው ማንም ላያፋታው፤ እየተዋሃደ ፡ በስጋ በደሙ ሰው ስለተጋባ፡ ከገዛ ሕመሙ ተወግዞ ጠበቀኝ፡ የመድሃኒት ሥሙ። መች ሰማሁ እኔማ? ህመሜን ልታገል፡ እንዳልራቅኩኝ ከሰው ስሽር በዳንኩበት ፡ ጥበብ ልፈውሰው፤ ደዌ ካጠላበት ፡ ህዝቤ መሃል ስገኝ ሰው አውቆ ሰው አልቆ ፡ ሞት አቅፎ ጠበቀኝ። « ከፋህ ወይ አንተዬ? » ፍፁም አልከፋኝም የልክ የሥህተቱ ፡ ወሰን ቢያለፋኝም የህይወት የጊዜ ፡ ትርጉም ቢጠፋኝም፤ አልከፋኝም ፍፁም ባይሆን ከቃል ልፁም ፤ ብዬ ነው የጠፋሁ... «ውሸት! ሀቅን አትሽሻት የደረሰብህን የሆንከውን ነገር እውነቱን ተናገር የት ጠፋህ አንተዬ? » ግጥም ልቅዳ ብዬ ከሰው ተነጥዬ ከድፍርስ ጽዋዬ በልቅልቅ ዋንጫዬ፤ ያንጠፈጠፍኩትን ለብ ያለ ጠብታ ፉት ብዬው ላፍታ ቃናው እየሸሸኝ ስላንገሸገሸኝ፤ ተፍቼ ብጭብጩን ደፍቼ ጭላጩን ልፈልገው ምንጩን፤ ከሰው ተነጥዬ ግጥም ልቅዳ ብዬ ጥዑም ልፃፍ ብዬ...፤ አልፎ የሚያገድመው ዘግኖ ከሚቅመው ከቆሎው ከዜናው ከንፍሮው ከዝናው ፤ ከወሬ ማንደጃው ከሰደድ መረጃው ከልብልቡ ርቄ ከልቤ ዘልቄ ፤ «ግን ቀናህ አንተዬ? » ተረከዝ ያልዳጠው ሰው ያልተረገጠው ከሀሳብ ለምለሙን ከቃል ቀለማሙን ፤ ከሐረግ እርጥቡን ከስንኝ ቁጥቡን አርቄ አምቄ ለቅሜ ጨምቄ ፤ ጠጥቼ ነቅቼ ሰው ላድን ጓጉቼ ከሻረው ህመሜ ከፀጤ ከዝሜ ህብረቃል ቀምሜ ፤ ስመልስ ከዱሩ በያዝኩት መድሃኒት ተጠለቅልቋል ምድሩ። «ምን ጉድ ነው አንተዬ?» አዬ! አዲስ ልፍጠር ብዬ ከሰው ተገልዬ ፤ ያሰብኩ ያረቀቅኩት የፃፍኩ ያነበብኩት ከፍታ ጣራዬ ብርቁ ፈጠራዬ ውድ ሆኖ የታየኝ ፤ በየሰው በራፍ ተጥለቅልቆ የሚገኝ ርካሽ ተደራሽ እዳ ሆኖ ቆየኝ። « ሞተሃል አንተዬ! » ኧረግ ኧረግ ኧረግ ሞት ቢሉህ የሞት ጥግ! የታመመ ወገን ፡ መድሃኒት ሳይፈልግ ፤ የማቀቀ ሁሉ፡ ሲስማማ ከደዌው መፍትሄ ፍለጋ ፡ ርቆ ከቅዬው የእድሜውን ግማሽ፡ ጫካ ለሚቆየው ለቀማሚው ወየሁ! ላፍታ በመዳኑ ፡ ላይልቅ ከታመሙት ፈውስ ፃፍ እያሉ፡ አንዱንም ላይሰሙት ቃላት በማስቀመም፡እድሜውን ለቀሙት ለገጣሚው ወየሁ ! ቃል ማሰር መፍታቱ ከእድል ጋር ትግሉ፡ ከቀን ጋር ሙግቱ መፍትሔ ፍለጋ ፥ መጣር መቃተቱ ታሞ ራሱ ድኖ ፡ ሰው ሊያድን መሻቱ ይሄ ድካም ኑሮ ፡ ምን ይሰራለታል ? ሞት ያራራለታል? ( እኔስ ይሄ ድካም ፡ ምን ይሰራልኛል? ሞት ይራራልኛል? ) Red-8 @getem
8 984
14
ቃል ሁኚልኝ //////////// እኔ ገጣሚ ነኝ አንቺ ባለሽበት ሃሳብ ማይጠፋኝ፤ ባየሁሽ ቁጥር ነው ከሃሳቤ ቀለም ብእር ማገናኝ፤ የሚያምር ቃል ጽፌ ሰው እንዳላስዋብኩኝ፤ የሚያምሩ ቃላትን ላንቺ አድናቆት ብዬ እንዳልደረደርኩኝ፤ የወረቀት ገላን አንቺን ባየሁ ቁጥር ስገርፍ እያደርኩኝ፤ ደግሜ ሳይሽ ግን የገጠምኩትን ቃል በማፍረስ ገደፍኩኝ፤ ስጽፍ የኖርኩትን አንደበት አጥቼ የምልሽ ሲጠፋኝ፤ ወይ እውቀት አልሆነኝ፤ ወይ ካንቺ አላግባባኝ፤ አንቺን ባየሁ ቁጥር አካሌ ሲከዳኝ፤ ሽባ ራሴን መተርተር ነው የተረፈኝ፤ እስኪ ባክሽ ወንድ ከሆንሽ ቃል ሁኚልኝ። በወረቀት ሳሰፍርሽ ነው በብእሬ ስጽፍ ማድር፤ ብዬ እንዳልል ወንድ አትሆኚ እኔም ካንቺ ውዬ አላድር። ከቻልሽ እስኪ አንዴ ባክሽ ቃል ሁኚልኝ፤ በሱ መልኩ አንችን ማግኘት ከቀለለኝ፤ እባክሽን ቃል ሁኚልኝ ። @abela_black @getem @getem @getem
8 622
15
<አድናቂና ቀልቡ> ለግርዶሽ ቢኳሉ ዝለው የሰቀሉት... ይከብድ የለ ቅሉ ሲንከባለል ውሎ ወጪት በአፍ ጢሙ ከመውደቁ በፊት ----------------------- በተመልካች ገመድ ታስሮ ነበር ቢሉ... ለቅሉ የተደፉ.... አንዳቸው ሳይተርፉ ቅሉ ግን የኋሊት... |ሽቅብ መንጠልጠሉ|       ተፃፈ : በኢያሱ ከበደ        ህዳር 30, 2018 ዓ.ም @getem @getem @getem
9 263
16
(በከሪም) ከመዉደዴ ጀርባ    ከመዉደዴ መሃል ከመውደዴ ዉስጠት  ቅንጣት የምታህል ከኢምንት ያነሰች  ትንሽ ክብር ቢጤ ከግብሬ ስጣረስ   ያልተዋጠች ድምጤ ነፍስ ዘራች መሰል  ትሰማኝ ጀመረ                                  ትቀር ትሆን ሆና ልረሳሽ ነው መሰል  ቢቀር ጊዜ መና                                    ይሄው ሆነ ወና በተስፋ ላይ ተስፋ ቆርጦ                              እስካይሆን ላልሆነው የሆነው እስኪሆን  የወደዴሽ ልቤ                                  ይወድሽ ተሳነው @getem @getem @getem
10 316
17
አርበኛው አያቴ . . ጋቢዉን ደርቦ ጠሀይዋን ይሞቃል፤ ሲለዉ እያነባ ሲያሻዉ ይስቃል። ትክ ብሎ ሲያየዉ የጋቢዉን ጥለት፤ ፊቱን አረጠበዉ እንባዉ ከመቅፅበት። እጉያዉ ሸጉጦ አይን አይኔን እያየኝ፤ በለስላሳ እጆቹ እየደባበሰኝ፤ የጥለቱን ምስጢር.... ከስር መሰረቱ አመሰጠረልኝ። ይቺ ክቡር ሰንደቅ.......... ከሞት ለመዳኑ፤ የኖህ ቃልኪዳኑ። በሰሜን አስታከን በደቡብ ስንወጣ፤ ምስራቅን ጨርሰን ከምዕራብ ስንመጣ፤ በማርያም መቀነት አየናት ተቀልማ፤ ለምድር ምስክር ለመሐላ ቆማ። ከሳቅ ይልቅ ዉብ እንባ ነች፤ ከልብ ምት ትረቃለች። ይቺን ክቡር ሰንደቅ... በአልባስሽ ተዋቢባት፤ በመኖርሽ ድመቂባት፤ በእንቶፈንቶ አትለዉጫት፤ እስከሞትሽ ታገይላት። ብሎ መከረኝ አያቴ...... [ዔደን ታደሰ ] @topazionnn @getem @getem
10 269
18
ረፍዷል ---------- ያሻኝን አግኝቼ በእጄ እንዳስገባሁት፣ የእኔው እንደሆነ መፈለጌን ተውኩት ። አለምን አየኋት ቀልቤንም ማረከኝ፣ ስህተቱ እንኳን ልክ ሆኖ እየታየኝ፣ አታለለኝ ። ፍላጎቴን አላውቅ ተቅበዝባዥ ሆኛለሁ፣ አላፊ አግዳሚውን ልሆን እመኛለሁ። አሁን ወስኛለሁ እንዳልኩኝ በቅፅበት፣ መልአከ ሞት ያዘኝ ወሰደኝ ሰማይ ቤት። @abela_black @getem @getem @getem
9 529
19
ወይን ሙዚቃ ዳንስ'ና ቡና የማያክመው ፤ የጋለ ገላ የጋለ ፍቅር የማያድነው፤ የነፍስ ኮርኒስ የልብ ጥላ የማይሸፍነው፤ እንቅልፍና ሞት መንገድና ዕድሜ የማይበግረው፤ አለ አንድ ድብርት ድንገት ብቅ የሚል ሄደ ስንለው። By Tewodros Kassa @getem @getem @paappii
10 048
20
እልፍ አዕላፍ ሰዎች..... ይኖሩ ይመስል በምድር ዘላለም፤ ዳግም ላይፋቱ ተጋብተው ከአለም፤ የጊዜን ምንነት ወርቅነት ሳያዉቁ፤ ከእድሜያቸዉ ላይ ዘመናት ሰረቁ። ............................................ ✍ዔደን ታደሰ @topazionnn @getem @getem
9 412