ar
Feedback
Tikvah-University

Tikvah-University

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
2025 عام في الأرقامsnowflakes fon
card fon
352 906
المشتركون
-2224 ساعات
+1617 أيام
+1 84730 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የግልጋሎት ሞዴል ፓተንት ሰጥቶቷል። ባለስልጣኑ በፈጠራ፣ አነስተኛ ፈጠራ እና ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ አዋጅ ቁጥር 123/1987 አንቀጽ 42 መሰረት፤ ከአሜሳ እፅዋት ባዮአክቲቭ ውህዶችን የማውጣት እና የመለየት ዘዴ (Bioactive Compound Extracted from the Ameessa Plant) የግልጋሎት ሞዴል ፓተንት ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መስጠቱን ገልጿል። @tikvahuniversity
إظهار الكل...
18👍 9
Photo unavailableShow in Telegram
#ተጨማሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የትምህርት ማስረጃ በኦንላይን የማረጋገጥ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ አገልግሎት ለማግኘት የምታመለክቱ ተገልጋዮች ልታሟሏቸው የሚገቡ ቅድመ-ሁኔታዎች መሟላታችሁን ካረጋገጣችሁ በኋላ፤ ከላይ የተጠቀሱትን ሁሉም ማስረጃዎች አንድ አንድ ስካን (Scan) በማድረግ ባሉበት ሆነው በበይነ መረብ https://neta.gov.et ማመልከት ትችላላችሁ፡፡ በተጨማሪ ቀጠሮ አስይዘው በአካል ሲሔዱ በባለጉዳዩ ወይም ሕጋዊ የውክልና ሰነድ ባላቸው ተወካዮች አማካኝት ሁሉንም የትምህርት ማስረጃ ዋናውን ይዘው መቅረብ ይኖርብዎታል። @tikvahuniversity
إظهار الكل...
19
Photo unavailableShow in Telegram
#ETA በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ አገልግሎት ለማግኘት የምታመለክቱ ተገልጋዮች ልታሟሏቸው የሚገቡ ቅድመ-ሁኔታዎች፦ ➫ በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊና ሬጅስትራር ፊርማና ማህተም ያለበት ኦሪጅናል (Temporary) ዲግሪ፣ ➫ በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊና ሬጅስትራር ፊርማና ማህተም ያለበት ኦሪጅናል ትራንስክሪፕት (Student Copy) ፣ ➫ ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘ ኦሪጅናል ዲፕሎማ ወይም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት፣ ➫ ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘው የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ከሆነ በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልገሎት ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ፣ ➫ ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘው ዲፕሎማ ከሆነ ዲፕሎማው በተገኘበት ክልል የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ወይም የዞን/የከተማ መስተዳደር የሥራና ስልጠና ቢሮ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የደረጃ 4 ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት (COC) ፤ ➫ የዲግሪ መግቢያው ከውጭ ሀገር በተገኘ የትምህርት ማስረጃ ከሆነ ከባለሥልጣኑ የተገኘ የአቻ ግመታ ደብዳቤ፣ ➫ የሁለተኛ (የማስተርስ) ዲግሪን ለማረጋገጥ ከሆነ በቅድሚያ የመጀመሪያው ዲግሪ ከላይ በተገለፀው መንገድ መረጋገጥ ይኖርበታል፣ ➫ የስም ለውጥ ካለ የፍርድ ቤት ውሳኔ የተላፈበት ማስረጃ፣ ➫ የማመልከቻ ክፍያ በኤሌክትሮኒክ ክፍያ በቴሌ ብር እና በሲኢቢ ብር፣ ➫ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የፋይዳ ልዩ ቁጥር FIN፣ ➫ ስካን የተደረገ 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፡፡ @tikvahuniversity
إظهار الكل...
25👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
📢 ሰልጥነው ይቀጠሩ! የሥራ ዘርፎች፦ ✔️ Customer Service ✔️ Call Center Agent ✔️ Sales and Marketing ✔️ Social Media Management 2ኛ ዙር ምዝገባ ተጀምሯል! 🔔 የአንድ ወር ስልጠና ወስደው የሥራ ባለቤት ይሁኑ! ውስን ቦታ ነው ያለን! ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም ይመዝገቡ👇 https://forms.gle/zSmdnuLY6mbv72H46 ☎️ ይደውሉ 👉 0977448467 Geez and Pan African Education and Skills
إظهار الكل...
8👍 4🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን! 👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና 👉 Advanced Graphic + Video Editing + Motion Graphic + Digital Marketing በአንድ ላይ 👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት ☎️ 0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
إظهار الكل...
31👏 4👍 2🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
በአማራ ክልል ከ27 ሺህ በላይ ለሚሆኑ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ ምዘና ይሰጣል። በአማራ ክልል በዚህ ዓመት ከ27 ሺህ በላይ ለሚሆኑ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ ምዘና ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ደምስ እንድሪስ ገልፀዋል። ለ21,669 ነባር እና 5,559 ከመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለሚመረቁ እጩ መምህራን ምዘና እንደሚሰጥ እንደሚሰጥ ምክትል ኃላፊው ጠቁመዋል። መምህራኑ እና የትምህርት ቤት አመራሮቹ የሙያ ፈቃድ ምዘና ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መያዛቸው የበለጠ ተወዳዳሪ ለመሆን ያስችላቸዋል ተብሏል። በሞዴል እና አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር መምህራን ከሚጠየቁት ማስረጃዎች መካካል የሙያ ፈቃድ ምዘና ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት መሆኑ ይታወቃል። @tikvahuniversity
إظهار الكل...
82👏 8👍 5👎 1🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
አሁንም በSMS ጨዋታ ፈታ 💬🎊 እያልን በየቀኑ እንሸለም! 🎁 ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'START’ ብለን ወደ 34000 በመላክ  ወይም ወደ *799# በመደወል እንወዳደር! እናሸንፍ! በአንድ መልስ 1ብር ብቻ! #SafaricomEthiopia #1Wedefit #FurtherAheadTogether
إظهار الكل...
27👎 1🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ጥቆማ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን በማጠናቀቅ የምስክር ወረቀት ወስደዋል፡፡ እርስዎም ስልጠናውን በነጻ በመውሰድ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ይቀበሉ። የስልጠና ዘርፎች፦ 🌐 ዌብ ፕሮግራሚንግ 🤖 አንድሮይድ ማበልፀግ 📊 ዳታ ሳይንስ 🧠 አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ይመዝገቡ 👇 https://www.ethiocoders.et/8 ሳምንታት ውስጥ ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ፥ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ያገኛሉ። @tikvahuniversity
إظهار الكل...
66👍 60👎 21👏 7😱 6🥰 5🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
የጋዜጠኝነት ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን! ስልጠናው፦ 👉 መሠረታዊ የጋዜጠኝነት መርሆች፣ የመገናኛ ብዙሃን እና የጋዜጠኝነት ዓይነቶች  👉 የዜና አሰራር እና የቃለመጠይቅ አደራረግ 👉 የመዝናኛ ፕሮግራም ጋዜጠኝነት፣ የፕሮግራም ዝግጅት፣ የማስታወቂያ አሰራር እና የዶክመንተሪ ዝግጅት 👉 የሞባይል ጋዜጠኝነት እና የዩቲዩብ ጋዜጠኝነት አካቷል፡፡ ☎️   0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
إظهار الكل...
53👍 3👏 3👎 1🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
#Update የ2018 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም የመውጫ ፈተና የምዝገባ ጊዜ ተራዝሟል። የምዝገባ ጊዜው ከተቋማት በቀረበ ጥያቄ እና ሌሎች ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት እስከ አርብ ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ስዓት ድረስ የተራዘመ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። ሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞች እንዲሁም የግል ተፈታኞች ምዝገባችሁን በተራዘመው ጊዜ እንድታጠናቅቁ ተብሏል። @tikvahuniversity
إظهار الكل...
👍 121 94👎 13😢 12🙏 9👏 5😱 4
Photo unavailableShow in Telegram
#JinkaUniversity በ2018 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች በሙሉ የማርበርግ ቫይረስ ሙሉ በሙሉ መጥፋቱ በጤና ሚኒስቴር ተረጋግጦ ጥሪ እስከሚደረግላችሁ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል። በሌላ መረጃ፤ ከአሪ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች በሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዳችሁ የሪሚዲያል ትምህርት ለመከታተል ከጂንካ ዩኒቨርሲቲ ውጪ በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደባችሁ ተማሪዎች ታህሳስ 15 እና 16/2018 ዓ.ም ወደ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ገብታችሁ የ21 ቀናት Quarantine ወስዳችሁ በዩኒቨርሲቲው ነፃ የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት እያገኛችሁ በመቆየት ከማርበርግ ቫይረስ ነፃ መሆናችሁ ሲረጋገጥና የምስክር ወረቀት ከተሰጣችሁ በኋላ ወደየተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንድትገቡ ትምህርት ሚኒስቴር ወስኗል። @tikvahuniversity
إظهار الكل...
114😢 37👍 15😱 7👏 3
Photo unavailableShow in Telegram
ዛሬ ይጠናቀቃል!! በጥር ወር 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ ዛሬ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡ መዝገባው ከታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል። የመውጫ ፈተናውን በድጋሜ ለመውሰድ ምዝገባ ያድርጉ 👉🏽 https://exam.ethernet.edu.et @tikvahuniversity
إظهار الكل...
30😢 10👏 3👍 1😱 1🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
3ኛው የተግባር ተኮር ዩኒቨርሲቲዎች የጋራ ፎረም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት እየተካሔደ ነው፡፡ መንግሥት 15 ዩኒቨርሲቲዎችን የተግባር ተኮር ዩኒቨርሲቲዎች (Applied Sciences Universities) በማለት መለየቱ ይታወቃል፡፡ ‎በፎረሙ የአስራ አምስቱ ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶች እና ምክትል ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም የትምህርት ሚኒስቴር ተወካዮች እየተሳተፉ ነው፡፡ @tikvahuniversity
إظهار الكل...
16
Photo unavailableShow in Telegram
📢 ሰልጥነው ይቀጠሩ! የሥራ ዘርፎች፦ ✔️ Customer Service ✔️ Call Center Agent ✔️ Sales and Marketing ✔️ Social Media Management 2ኛ ዙር ምዝገባ ተጀምሯል! 🔔 የአንድ ወር ስልጠና ወስደው የሥራ ባለቤት ይሁኑ! ውስን ቦታ ነው ያለን! ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም ይመዝገቡ👇 https://forms.gle/zSmdnuLY6mbv72H46 ☎️ ይደውሉ 👉 0977448467 Geez and Pan African Education and Skills
إظهار الكل...
21👍 2😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን! 👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና 👉 መሠረታዊ የአካውንቲንግ እና የኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ 👉 ስልጠናው ከፒስቺሪ በተጨማሪ በExcel፣ Word እና ተግባራዊ ዶክመንቶች ታግዞ የሚሰጥ ነው። የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 ☎️   0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
إظهار الكل...
24👏 3
#SpecialBoardingSchools በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተወዳድረው ያለፉና የተመደቡ ተማሪዎች ወደየተመደቡበት ተቋም በመግባት ላይ ይገኛሉ። ወሊሶ የተመደቡ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሀጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ፣ ቡኢ የተመደቡ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ቦንጋ የተመደቡ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ፣ እንዲሁም ጅግጅጋ የተመደቡ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ እየገቡ መሆኑ መሆኑ ተገልጿል። ተራዝሞ የነበረው ጋምቤላ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመደቡ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከታህሳስ 12-15/2018 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል። @tikvahuniversity
إظهار الكل...
124🙏 15👎 11👏 3
Photo unavailableShow in Telegram
የህንድ መንግሥት ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ነጻ የሦስተኛ ዲግሪ የትምህርት ዕድል ሰጥቷል። በትምህርት ሚኒስቴር እና በህንድ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች መካከል የተደረሰው ነጻ የትምህርት ዕድል ፕሮግራም በይፋ የማስጀመሪያ መርሐግብር ተካሂዷል። ፕሮግራሙ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት አቅም በመገንባት በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ትልቅ ሽግግር ለማድረግ እንደሚያግዝ የከፍተኛ የትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ ገልፀዋል። ‎ ‎ፕሮግራሙ በተለይ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በኢንጂነሪንግ እና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለውን የሦስተኛ ዲግሪ ባለሙያዎች እጥረት እንደሚያቃልል ተገልጿል። ‎በህንድ ካሉ 8 የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች ጋር በተደረሰ ስምምነት መሠረት በዓመት 250 ፤ በአምስት ዓመት 1,250 ተማሪዎች ነጻ የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት ዕድል እንደሚያገኙ የአካዳሚክ ፕሮግራሞች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተናግረዋል። ‎ @tikvahuniversity
إظهار الكل...
52👎 9
#SpecialBoardingSchools በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተወዳድረው ያለፉና የተመደቡ ተማሪዎች ወደየተመደቡበት ተቋም በመግባት ላይ ይገኛሉ። ወሊሶ የተመደቡ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሀጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ፣ ቡኢ የተመደቡ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ቦንጋ የተመደቡ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ፣ እንዲሁም ጅግጅጋ የተመደቡ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ እየገቡ መሆኑ መሆኑ ተገልጿል። ተራዝሞ የነበረው ጋምቤላ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመደቡ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከታህሳስ 12-15/2018 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል። @tikvahuniversity
إظهار الكل...
19