ar
Feedback
Addis Ababa Education Bureau

Addis Ababa Education Bureau

الذهاب إلى القناة على Telegram

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

إظهار المزيد
2025 عام في الأرقامsnowflakes fon
card fon
150 232
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+677 أيام
+34630 أيام
أرشيف المشاركات
إظهار الكل...
14
إظهار الكل...
إظهار الكل...
7
إظهار الكل...
6
إظهار الكل...
38👎 11👍 9👏 1
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪው ዶክተር ቁልቁሉ ስለ ኢሬቻ በአል አከባበር እና የገዳ ስርአትን በተመለከተ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበው ውይይት ተካሂዷል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
إظهار الكل...
👎 25 21👍 4
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢሬቻ በአልን አስመልክቶ የፓናል ውይይት አካሄደ። (መስከረም 22/2018 ዓ.ም) የፓናል ውይይቱ "ኢሬቻ ለሃገር ማንሰራራት!" በሚል መሪ ቃል በሽማግሌዎች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የማኔጅመንት አባላትን ጨምሮ አጠቃላይ ሰራተኞችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ኢሬቻ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ታላቅ አክብሮት ከሚሰጣቸው በአላት አንዱ የሆነ የማንነት መገለጫ የአንድነትና የአብሮነት መሰላል ነው ሲሉ ተናግረዋል:: የኢሬቻ በአል ከኦሮሞ ህዝብ ባሻገር ሁሉም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የሚያከብሩት በአል መሆኑን የተናገሩት ቢሮ ኃላፊው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮም የዘንድሮው በአል እሴቶቹን ጠብቆ እንዲከበር ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ አዲስ አበባ ከተማ የሚመጡ እንግዶችን ከመቀበል ጀምሮ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ በመግለጽ የዛሬው ፓናል ውይይት ከኢሬቻ በአል አከባበር ጋርም ሆነ ከገዳ ስርአት ጋር በተገናኘ በቂ ግንዛቤ የሚፈጥር መሆኑን አመላክተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በበኩላቸው የኢሬቻ በአል አንድነትን እና ወንድማማችነትን የሚያጠናክር በአል እንደመሆኑ የ2018 ዓ.ም የኢሬቻ በአል እሴቱን ጠብቆ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ የቢሮው ሰራተኞች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
إظهار الكل...
51🤬 7
إظهار الكل...
10
إظهار الكل...
12
إظهار الكل...
10👎 1
إظهار الكل...
ለሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ እንግዶቹን ለመቀበል ዝግጁ የሆነው የኢሬቻ ፓርክ አሁናዊ የምሽት ድባብ
إظهار الكل...
👎 58👍 38 29😁 7👏 4
ለሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ እንግዶቹን ለመቀበል ዝግጁ የሆነው የኢሬቻ ፓርክ በምስል፤
إظهار الكل...
69👎 24👍 10🥰 4
ስልጠናው የትምህርት ሚኒስትር ሥራና ተግባር ትምህርት ዴስክ ኃላፊ በሆኑት አቶ ማተቤ አለማየሁ ኃላፊ የተሰጠ ሲሆን የ11ዱ ክፍለከተሞች ስርዓተ ትምህርት አስተባባሪዎች ፣ የአማርኛና አፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት ቡድን መሪዎች ፣ የክፍለ ከተማ CTE ተጠሪ ባለሙያዎች ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ምክትል ርዕሰ መምህራን ስልጠናውን ወስደዋል:: መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
إظهار الكل...
21
ሥራና ተግባር ትምህርት (CTE) ነጥብ እና ሰርተፍኬት አሰጣጥ ላይ ስልጠና ተሰጠ:: (መስከረም 21/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስርዓተ ትምህርት ማበልፀግና ትግበራ ዳይሬክቶሬት የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ሥራና ተግባር ትምህርት ውጤት አሰጣጥና ምስክር ወረቀት አሰራር ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ሰጠ:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በስልጠናው መክፈቻ የሥራና ተግባር ትምህርት ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በ11ኛ ክፍል መሰጠት መጀመሩን አስታውሰው በ2018 የትምህርት ዘመን በውጤት አሰጣጥና ሰርተፍኬት አዘገጃጀት ላይ በቂ መረጃ ለመፍጠር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም ትምህርቱ አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በአተገባበር የታዩ ክፍተቶችን በመለየት የማስተማር ስነዘዴና ውጤት አሰጣጥ ላይ ወጥ የሆነ አሰራር እንዲኖር ማድረግ ስልጠናውን ከሚወስዱ አካላት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል:: ቢሮው የሥራና ተግባር ትምህርት አተገባበርን ውጤታማ ለማድረግ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ትስስር በማድረግ ለመስራት እቅድ መያዙን የተናገሩት ምክትል ቢሮ ኃላፊው ትምህርት ቤቶች በተቋም ደረጃ የውስጥ አቅምን እንዴት መለየት እንዳለባቸውና የነጥብ አሰጣጥና ሰርተፍኬት አዘገጃጀት ላይ ብሎም ተማሪዎች የሙያ ምርጫና ምዝገባ አካሄድ በመለየት የሙያ ትምህርት ውጤታማነትን ለማረጋገጥ በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል::
إظهار الكل...
30👍 4🔥 1
የ1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ተካሄደ:: (መስከረም 21/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትል ግምገማ እና ሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬቶች የ 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ አካሂደዋል:: ሪፖርት ግምገማው ቀደምሲል በሥራ ክፍሎቹ በኩል የተደረገ መሆኑን የገለፁት የቢሮ ኃላፊ አማካሪና የዘርፉ አስተባባሪ ወ /ሮ አበበች ነጋሽ በሩብ አመቱ የነበሩ ሥራዎች ከእቅዱ አንፃር የተሳካ እንደነበር የድጋፍና ክትትል ሥራ ውጤት ግብረ መልስ የሚያሳይ መሆኑን አብራርተው ከቢሮ እስከ ትምህርት ቤት የተሰጠ እውቅና ለዚህ ማሳያ እንደሚሆን ተናግረዋል:: በስኬት የተጠናቀቀውን 1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ለማስቀጠል ሁሉም በትጋት ስራን ማከናወን እንዳለበት ያብራሩት አማካሪዋ በሪፎርምና ቁልፍ ውጤት አመላካች ሥራዎች የተሻለ ውጤት አስመዝግበው እውቅና የወሰዱ አካላት ውጤቱን ያስመዘገቡት ምን ሰርተው እንደሆነ ሌሎች ልምድ እንዲቀስሙ ምርጥ ተሞክሯቸውን እስከ ጥቅምት ወር መጀመሪያ ሳምንት ድረስ ጠምረው እንዲያቀርቡ በወረደው አቅጣጫ መሰረት ወቅቱን ጠብቀው እንዲያቀርቡና ቀጣይ ሥራዎችን በተቀራራቢ አፈፃፀም ማጠናቀቅ እንዲቻል አሳስበው ቀጣይ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል:: በውይይቱ የስራ ክፍሎቹን የሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀም ሪፖርት የእቅድ በጀት ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ጌታሁን ለማ አማካኝነት ቀርቦ በሥራ ክፍሉ ባለሙያዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
إظهار الكل...
18👎 7👍 1
ትራንስፎርም ለመደረግ የተመረጡ ትምህርት ቤቶችም የክፍል ውስጥ ግብዓቶቹን ለታለመለት አላማ ብቻ በማዋል የተማሪን ስነልቦናና እድሜ ደረጃ ያገናዘበ የማስተማር ስነዘዴን በመጠቀም ብቁ ዜጋ መፍጠር እንደሚገባቸው አሳስበዋል:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ወንድሙ ዑመር በበኩላቸው ቢሮው የትምህርት ተደራሽነትን ከማረጋገጥ አንፃር እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕፃናትን ወደ ትምህርት ማምጣትና ምቹ የመማሪያ አካባቢን በመፍጠር ሰፊ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን ተናግረው ከነዚህ ተግባራት ውስጥ መምህራንን በጨዋታ የማስተማር ስነዘዴ በስልጠና ዝግጁ በማድረግና ትምህርት ቤቶቹን በግብዓት ማደራጀት ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን ተናግረዋል:: አቶ ወንድሙ አያይዘውም ትራንስፎም የሚያደርጉ ትምህርት ቤቶች ግብዓቶቹን በአግባቡ ለማስተዳደር የሚያስችል ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት ቢሮው በቀጣይ በሚደረግ ክትትል ተግባራዊነቱን እንደሚፈትሽ አብራርተዋል:: በግብዓት ርክክብ መርሐ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ፣ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዑመር ፣ የቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፈቃዱ የሁሉም ክፍለ ከተሞች ቡድን መሪዎች እና የቅድመ አንደኛ ደረጃ አስተባባሪዎች እንዲሁም ርዕሰ መምህራንና ንብረት ክፍል ባለሙያዎች ተገኝተዋል:: መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
إظهار الكل...
31👍 6
የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራምን ትራንስፎርም ለማድረግ ለተመረጡ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የክፍል ውስጥ ግብዓቶች ስርጭት ተካሄደ:: (መስከረም 21/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2018 ትምህርት ዘመን በቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም ትራንስፎርም ለማድረግ ከ11 ዱ ክፍለ ከተሞች ለተመረጡ 20 ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የክፍል ውስጥ ግብዓቶች ርክክብ አድርጓል:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በግብአት ስርጭቱ ወቅት ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ቢሮው የቅድመ አንደኛ ትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥና ትራንስፎርም ለማድረግ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ሀላፊነት ውጤታማ ለማድረግ ሰፊ ሥራዎች እየሰራ መሆኑን ተናግረው ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት የሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ የግብዓቶች ማሟላት የትምህርት ስራችንን ስኬታማ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል:: በጨዋታ የማስተማር ስነዘዴን ተግባራዊ ማድረግ ህፃናቱ አካባቢያቸውን ፤ ሳይንሳዊና ማህበራዊ ጉዳዮችን ጠንቅቀው እንዲያውቁ ያደርጋል ያሉት ዶክተር ዘላለም በታችኛው የትምህርት እርከን ላይ ትኩረት በመስጠት ትምህርት ቤቶችን በማዘመንና በግብዓት በማሟላት እንዲሁም ሞዴል የሆነ የትምህርት ስርዓት ለመዘርጋት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል::
إظهار الكل...
28
Photo unavailableShow in Telegram
በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስደው በአማካይ ውጤታቸው 49.50 - 49.99 በመቶ ያመጡ ተማሪዎች ውጤታቸው ወደ 50 በመቶ የሚጠጋጋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህም 49.50 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች፥ ዝቅተኛውን 50 በመቶ የማለፊያ ነጥብ ያሟሉ ሆኖ የተወሰነ መሆኑን በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን መስከረም 20/2018 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከ ደብዳቤ ያሳያል።  በመሆኑም 49.50 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመግባት መማር እንደሚችሉ ሚኒስተሩ ገልፀዋል። በዚህ ውሳኔ መሠረት 300 ነጥብ የነበረው የየኒቨርሲቲ መግቢያ ወደ 297 የተጠጋጋ መሆኑ ተገልፃል።
إظهار الكل...
119👏 19👍 14👎 14🖕 3
ማስታወቂያ! (መስከረም 20/2018 ዓ.ም) መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
إظهار الكل...
99👍 27🔥 12🖕 9🍾 5🤔 1