Addis Ababa Education Bureau
الذهاب إلى القناة على Telegram
ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡
إظهار المزيد2025 عام في الأرقام

150 232
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+677 أيام
+34630 أيام
أرشيف المشاركات
5. ከክፍለከተማ ትምህርት ጽ/ቤቶች በKPI እና በሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት እንዲሁም በተማሪ ውጤት ምዘና ተሸላሚዎች
1ኛ፡- ጉለሌ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ፤ 2ኛ፡- ቂርቆስ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ፤ 3ኛ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ፤ 3ኛ፡- የካ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት፤
6. ከወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች በKPI እና በሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት እንዲሁም በተማሪ ውጤት ምዘና ተሸላሚዎች፡- ቂርቆስ ክፍለከተማ ወረዳ 03 ትምህርት ጽ/ቤት 3ኛ ፤ ን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ትምህርት ጽ/ቤት 2ኛ፤ ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ትምህርት ጽ/ቤት 1ኛ
7. ከ1ኛና መካ/ደረጃ ትም/ቤቶች በKPI እና በሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት እንዲሁም በተማሪ ውጤት ምዘና ተሸላሚዎች፡- ቦሌ ህብረተሰብ 1ኛና መካ/ደረጃ ት/ቤት 5ኛ ፣ አብዮት 1ኛና መካ/ደረጃ ት/ቤት 4ኛ ፣ ብሩህተስፋ 1ኛ/መ/ደ/ት/ቤት 3ኛ ፣ ጀ/ታደሰ ብሩ ቁ.1 1ኛና መካ/ደረጃ ት/ቤት 2ኛ እና ዋልያ 1ኛና መካ/ደረጃ ት/ቤት 1ኛ
8. ከ2ኛ ደረጃ ትም/ቤቶች በKPI እና በሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ምዘና ተሸላሚዎች፡- እድገት ጮራ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት 3ኛ ፣ ጀነራል ታደሰ ብሩ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት 3ኛ ፣ ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት 2ኛ እና ኮከበ ጽባህ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት 1ኛ
9. ከአዳሪ ትምህር ቤቶች በKPI እና በሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት እንዲሁም በተማሪ ውጤት ምዘና ተሸላሚዎች፡- ገላን የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤት
10. ከ1ኛና መካ/ደረጃ ትምህርት የሱፐርቪዥን ክላስተር ማእከላት ምዘናና ተሸላሚዎች፡- ህዳሴ የ1ኛና መካ/ደ/ትምህርት ሱፐርቪዥን ክላስተር ማእከል 3ኛ ፣ ጎፋ የ1ኛና መካ/ደ/ትምህርት ሱፐርቪዥን ክላስተር ማእከል 2ኛ እና ፈለገ ዮርዳኖስ የ1ኛና መካ/ደ/ትምህርት ሱፐርቪዥን ክላስተር ማእከል 1ኛ
11. ከ2ኛ ደረጃ አጠቃላይ ትምህርት የሱፐርቪዥን ክላስተር ማእከላት ምዘናና ተሸላሚዎች፡- ደጃ/ባልቻ አባ ነፍሶ የ2ኛ ደ/ ትምህርት ሱፐርቪዥን ማእከል 3ኛ ፣ ቦሌ የ2ኛ ደ/ትምህርት ሱፐርቪዥን ማእከል 2ኛ እና ከፍተኛ 23 የ2ኛ ደ/ ትምህርት ሱፐርቪዥን ማእከል 1ኛ
12. ከአፋን ኦሮሞ ትምህርት የሱፐርቪዥን ክላስተር ማእከላት ምዘናና ተሸላሚዎች፡- የካ ክ/ከተማ የአፋን ኦሮሞ ትም/ሱፐርቪዥን ማእከል 3ኛ ፣ ለሚኩራ ክ/ከተማ የአፋን ኦሮሞ ትም/ሱፐርቪዥን ማእከል 2ኛ እና አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የአፋን ኦሮሞ ትም/ሱፐርቪዥን ማእከል 1ኛ
13. በ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሁሉንም ተፈታኞች በአማካይ ውጤት ከ80% በላይ እንዲያመጡ በማድረግ ወደ 7ኛ ክፍል በማዛወር፡- ሴሎ ትምህርት ቤት 2ኛ እና ቃሊቲ ማረሚያ 1ኛ
14. በ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሁሉንም ተፈታኞች በአማካይ ውጤት ከ80% በላይ እንዲያመጡ በማድረግ ወደ 7ኛ ክፍል በማዛወር፡- ገላን የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤት
15. በት/ዘመኑ ለቢሮው ስራ ውጤታማነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ፡- የአ/አ/ ከተማ መምህራን ማህበር ፣ የአ/አ/ ከተማ ተማሪ ወላጅ ማህበር እና የአ/አ/ከተማ አካል ጉዳተኞች ማህበር፤
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 133👍 24🔥 2
በ32ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ሽልማትና ዕውቅና ያገኙ ተማሪዎች የሽልማት መርሀ ግብር፡፡
(ነሀሴ 27/2017 ዓ.ም) በጉባኤው በ2017 የትምህርት ዘመን የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ትምህርት ቤቶች ፣ ወረዳ ት/ጽ/ቤቶች ፣ ክላስተር ማዕከላት ፣ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤቶች ፣ የቢሮ ዳይሬክቶሬቶች ፤ እንዲሁም በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች እና በ2017 ዓ.ም በትምህርት ልማት ስራዉ ላይ ከፍተኛ አበርክቶ ለነበራቸዉ ተቋማት እውቅና ተሰጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት፡-
1. ከትምህርት ቢሮ ከዓላማ ፈጻሚ የሥራ ክፍሎች በKPI እና በሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ምዘና ተሸላሚዎች፡-1ኛ፡- የቀዳማይ ልጅነትና ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ፤ 2ኛ፡-የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ፤ 3ኛ፡- የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት
2. ከትምህርት ቢሮ ደጋፊ የሥራ ክፍሎች በKPI እና በሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ምዘና ተሸላሚዎች፡-
1ኛ፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
1ኛ፡- የሪፎርም አገልግሎት አሰጣ ድጋፍ ክትትል ምዘና ዳይሬክቶሬት
2ኛ፡-የእቅድና በጀት ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬት
3. ከትምህርት ቢሮ ዳይሬክቶሬቶች መካከል ከ2013 ዓ.ም እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ ባለፉት 5 አመታት በተከታታይ ውጤታማ በመሆን ተሸላሚ
የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
4. ከ2013 ዓ.ም እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ ባለፉት 5 አመታት በተከታታይ ውጤታማ በመሆን ተሸላሚ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ጀ/ታደሰ ብሩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
❤ 68👏 5👻 5👍 3
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው የ32ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ተ ሳታፊዎች ውጤታማ ውይይት በማድረግ በቀጣይ የርብርብ ማዕከል የሆኑ ጉዳዮችን መለየታቸውን እና ከነዚህ ተግባራት መካከል የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ማሻሻል፣ የመምህራንን አቅም ማሳደግ፣የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርትን ውጤታማ ለማድረግ የተጀመረውን ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል፣ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ማሳደግ እንዲሁም የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሆን ትምህርት ቤቶችን ሞዴል ማድረግ እና በትምህርት ተቋማት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስርአት ማስፈን በቀጣይ ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች ሆነው በጉባኤው መለየታቸውን አመላክተዋል።
የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ወይዘሮ አየለች እሸቴ በጉባኤው ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ በጀት በመመደብ በትምህርት ተቋማት የምገባ ፕሮግራም ተግባራዊ ማድረጉ እና ለተማሪዎች የመማሪያ ግብአት ማቅረቡ የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከማበርከቱ ባሻገር ክልሎች ልምድ የሚቀስሙበት ተግባር መሆኑን ተቋማቸው በየጊዜው በሚያደርገው ድጋፍና ክትትል ማረጋገጡን ገልጸው በከተማ አስተዳደሩ በ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ የጉባኤው ተሳታፊዎች በቅንጅት መስራት የሚገባቸው መሆኑን አስታውቀዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 66👍 11👎 3👏 1😁 1🕊 1
በዕውቀት እና ክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር እናደርጋለን በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው 32ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በበጀት አመቱ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተማሪዎችና ተቋማት ዕውቅና በመስጠት ተጠናቀቀ።
(ነሀሴ 27/2017 ዓ.ም) በጉባኤው የሴክተሩ የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም የበጀት አመት የትኩረት አቅጣጫ ከመቅረቡ ባሻገር በ2017 ዓ.ም በየክፍል ደረጃ የተመዘገበው የተማሪዎች ውጤት ትንተና ለጉባኤተኛው ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በጉባኤው ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ እየተከናወነ የሚገኘው ስራ ውጤታማ እንዲሆን መንግስት ለትውልድ ግንባታው ትኩረት አድርጎ በመስራት ላይ መሆኑን ጠቅሰው ከተማ አስተዳደሩ የመማር ማስተማር ስራው ውጤታማ እንዲሆን እና የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ ለሴክተሩ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስገንዝበዋል።
❤ 34🤣 4
32 ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ የሁለተኛ ቀን መርሀ ግብር መካሄድ ጀምራል፡፡
(ነሀሴ 27/2017 ዓ.ም) 32 ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ "በዕውቀትና በክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር እናደርጋለን!" በሚል መሪ ሀሳብ የሁለተኛ ቀን ውሎ መካሄድ ጀምራል።
ጉባኤው በዛሬው እለት የሚጠናቀቅ ሲሆን በመርሀ ግብሩ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ምገስ ባልቻ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣ የካቢኔ አባላት ፣ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮች ፣ ባለሙያዎች ርዕሳነ መምህራን ፣ መምህራን ፣ ተማሪዎች እና ወላጆችን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
ጉባኤው በዛሬው ውሎው የተቋማት የ2017 ዓ.ም ምዘና ውጤት አፈፃፀም ሪፓርት ፣ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እና የላቀ አፈፃፀም ላላቸው ተቋማት እውቅና የሚሰጥ ይሆናል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 45👍 15👎 6🤔 2
8. ለተማሪዎች ዩኒፎርም እና መማሪያ ቁሳቁሶች እንዲቀርቡ መደረጉ፤
9. የት/ቤት ምገባ መርሃ ግብርን አጠናክሮ በማስቀጠል መቻሉ፤
10. የመምህራንን ችግር በማጤን ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አመራሮች በማህበር በማደራጀት ቅድሚያ ቤት መስራት የሚችሉበትን ማዕቀፍ መዘርጋቱና ወደ ስራ መገባቱ፤
11. በአለማቀፍና በግል ትምህርት ቤቶች ላይ ይታዩ የነበሩ ጥሰቶችን በአግባቡ በመፈተሸ ይስተዋሉ የነበሩ ክፍተቶች እንዲታረሙ መደረጉ፤
12. በቴክኖሎጂ የዳበረ ትውልድ ከመፍጠር አካያም የመማር ማስተማር ስራዉን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድግ ስራዎች መከናወናቸው ፤
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 69👎 9👍 3👌 1
የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ “በዕውቀትና ክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር እናደርጋለን!" በሚል መሪ ሀሳብ በመካሄድ ላይ በሚገኘው በ32ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ያነሳቸው ነጥቦች፡-
(ነሀሴ 26/2017 ዓ.ም)
1. የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ትራንስፎርም በማድረግ ሞዴል ተቋማተን በመገንባታ ለአለም ፣ ለአፍሪካና ለክልል አመራሮች ተሞክሮ ማካፈል መቻሉ፤
2. በ2017 የትምህርተ ዘመን በተሰጡ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተናዎች ማለትም በ6ኛ ክፍል በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች አማካኝ 50ና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ከነበረበት 94.3% ወደ 95% እንዲሁም በ8ኛ ክፍል አማካኝ 50ና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ከነበረበት 78.9% ወደ 88.79 % መድረሱ የተመዘገበው ውጤት ከዚህ ቀደም ከተመዘገቡት አንጻር ስንመለከተው የላቀ መሻሻል የታየበት መሆኑ ፤
3. የትምህርት ጥራትን የማረጋገጥ ሥራ ተሰናስሎ መሰራትን ፣ ሁለንተናዊ ርብርብን እና በቅንጅታዊ ትግበራ መንቀሳቀስን የሚጠይቅ መሆኑ ፤
4. የትምህርት ተቋማት ደረጃቸዉን እንዲጠብቁ ፤ ምቹና ማራኪ እንዲሆኑ እንዲሁም እድሜያቸዉ ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ለማድረግ እና የትምህርት ባለድርሻ አካላት በትምህርቱ ስራ ላይ በባለቤትነት እንዲሳተፉና ባለቤት እንዲሆኑ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የሰራናቸው ስራዎች እመርታዊ ለውጦችን ማሳየት መቻላቸው፤
5. የሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ስራ እና በባለቤትነት የመንቀሳቀሱ ተግባር ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ የሚኖረው ሚና እጅግ የጎላ መሆኑ ፤
6. የከተማ ግብርና ስራ በሁሉም ት/ቤቶች ላይ መተግበሩ፤
❤ 55👍 6👎 2
የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ “በዕውቀትና ክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር እናደርጋለን!" በሚል መሪ ሀሳብ በመካሄድ ላይ በሚገኘው በ32ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ያነሳቸው ነጥቦች፡-
(ነሀሴ 26/2017 ዓ.ም)
1. “በዕውቀትና ክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር እናደርጋለን!" በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄው 32ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ መሪ ሀሳብ ላይ የተመላከተው በዕውቀትና ክህሎት የበቃ ትውልድን ለማፍራትና ኢትዮጵያን ተምሳሌት ለማድረግ ትጋት እና ብቁ የሆነ የትምህርት ማህበረሰብ መሰረት መሆኑ፤
2. የትምህርት ዘርፉን ስብራት ለመጠገን በተከናወኑ ተግባራት በዕውቀት እና በክህሎት የታነጸ ትውልድ ለማፍራት የሚያስችሉ ተጨባጭ እርምጃዎች ተወስደው ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸው፤
3. የከተማ አተዳደሩ ለትምህርት ዘርፍ የሚያደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ፤
4. በትምህርት ማህበረሰቡ የተመዘገቡ በርካታ ውጤቶችን በማስመዝገብ ረገድ የመምህራን፣ የተማሪ ወላጆች እና የተማሪዎች በአጠቃላይ የትምህርት ማህበረሰብ ሚና ትልቅ መሆኑ፤
5. የተመዘገቡ ውጤቶችን የበለጠ ለማላቅና ዘርፉ በትውልድና አገር ግንባታ የሚጠበቅበትን ሚና በአግባቡ እንዲወጣ ፣ ውጤቶች ይበልጥ እንዲልቁ ፣ የታዩ ክፍተቶች እንዲታረሙ ይበልጡን ተቀራርቦ መስራት እንደሚገባ፤
6. ትምህርት ቤቶችን ከአዋኪ ድርጊቶች በማፅዳት ለመማር ማስተማር ስራ ምቹ እየተደረገ መሆኑ፤
7. በጉባኤው የ2016 ዓ.ም የትምህርት ስራ ዕቅድ አፈጻጸምን በመገምገም ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ እና አስፍቶ መቀጠል እንደሚገባና በታዩ እጥረቶች ላይ በጥልቀት መነጋገር እንደሚገባ፤
❤ 48👍 9😁 3🔥 2
የእለቱ ጉባኤም በአቶ ታረቀኝ ወልደሀና አማካኝነት የአቋም መግለጫ ቀርቦ የተጠናቀቀ ሲሆን ጉባኤው በነገው እለትም በመቀጠል የተቋማት የ2017 ዓ.ም ምዘና ውጤት አፈፃፀም ሪፓርት ፣ የ2017 የትምህርት ዘመን የትኩረት አቅጣጫ ፣ የላቀ አፈፃፀም ላላቸው ተቋማት እውቅና የሚሰጥ ይሆናል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 38🔥 1
32ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በከሰዓት ውሎው በተለያዩ የትምህርት ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ የዛሬ ውሎውን አጠናቋል ።
(ነሀሴ 26/2017 ዓ.ም) ጉባኤው "በዕውቀትና ክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር እናደርጋለን!" በሚል መሪ ሀሳብ በመካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ቆይታ ያደርጋል።
ጉባኤው በ2017 የትምህርት ዘመን በትምህርት ዘርፉ በተመዘገቡ የትምህርት ስራዎችና በ31ኛው የትምህርት ጉባኤ እቀጣጫ ላይ መሰረት ተደርጎ በቀረበው ሪፓርትና በተማሪዎች ውጤት ትንተና ላይ እንዲሁም በ2018 የትምህርት ዘመን የትኩረት መስኮች ላይ መሰረት በማድረግ ዉይይት ተካሄዳል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በጉባኤው ላይ የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል ፣ ስላማው መማር ማስተማርን ማጽናት ፣ የትምህርት ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ፣ የመምህራንና የትምህርት አመራሩን ብቃትና ሙያዊ ስነምግባር ማሻሻል ፣ የሂሳብና የእንግሊዘኛ ትምህርትን ማሻሻል ፣ የቅንጅታዊ አስራር ውጤታማነትን ማጎልበት ፣ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል ፣ የከተማ ግብርናን በሁሉም ደረጃ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ መተግበር ፣ የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ላይ መስራት ፣ ሰፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በትምህርት ተቋማት ማጠናከር ፣ በቀዳማይ ልጀነት ላይ በትኩረት መስራት ፣ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን መሰረት ያደረገ ንቅናቄ ማከናወን እና በተማሪዎች ምዝገባ ላይ በትኩረት መስራት የሚሉትን የ2018 የትምህርት ዘመን የትኩረት አቅጣጫዎች በጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይ ካቀረቡ በሃላ በጉባኤተኛች በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡
❤ 44👍 3🥰 1
32ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በዕውቀትና ክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር እናደርጋለን በሚል መሪ ቃል በመካሄድ ላይ ይገኛል።
(ነሀሴ 26/2017 ዓ.ም) ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በመካሄድ ላይ በሚገኘው ጉባኤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች፣ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮች እና ባለሙያዎች ፣ ርዕሳነ መምህራን ፣ መምህራን እንዲሁም የመምህራን ማህበር እና የተማሪ ወላጅ ማህበር አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ የ2017 የትምህርት ዘመን የ31ኛው የትምህርት ጉባኤ የትኩረት አቅጣጫዎችን መሰረት ያደረገ የአፈጻጸም ሪፖርት እንዲሁም የቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ የ2017 ዓ.ም የውጤት ትንተና ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
በትምህርት ጉባኤው የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ እና የኢትዮጲያና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተማሪ ወላጅ ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ሃሰን ሽፋ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 59👏 7😁 7🔥 1
ክብርት ከንቲባዋ አያይዘውም በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ የተደረገው የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም እና የትምህርት ግብአት አቅርቦት የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል እያበረከተ የሚገኘው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀን የሚካሄደው 32ኛው የትምህርት ጉባኤ በ2017 ዓ.ም በዘርፉ የነበሩ አፈጻጸሞች በአግባቡ ተገምግመው በ2018 ዓ.ም የተሻለ ስራ በመስራት የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ አቅጣጫ የሚቀመጥበት ጉባኤ መሆን እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው 32ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ማብሰሪያ እና የብልጽግናችን አሻራ የሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ በሚመረቅበት ዋዜማ መካሄዱ ለየት እንደሚያደርገው ጠቁመው ጉባኤው በ2017 ዓ.ም የነበሩ አፈጻጸሞችን በመገምገም በ2018 ዓ.ም ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስርአት በማስፈን የተማሪዎች ውጤት እና ስነምግባር እንዲሻሻል አቅጣጫ የሚቀመጥበት እና በ2017 ዓ.ም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እና በየደረጃው ለሚገኙ ተቋማት ዕውቅና የሚሰጥበት መሆኑን አስታውቀዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 52👍 9👏 5🖕 4😁 3🥰 1
32ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በዕውቀትና ክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር እናደርጋለን በሚል መሪ ቃል መካሄድ ጀመረ።
(ነሀሴ 26/2017 ዓ.ም) ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በመካሄድ ላይ በሚገኘው ጉባኤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች፣በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮች እና ባለሙያዎች ፣ ርዕሳነ መምህራን ፣ መምህራን እንዲሁም የመምህራን ማህበር እና የተማሪ ወላጅ ማህበር አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በጉባኤው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ለትምህርት ሴክተሩ በተሰጠ ልዩ ትኩረት በከተማ አስተዳደሩ በርካታ ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ተቋማት ተገንብተው አገልግሎት እንዲሰጡ ከመደረጉ ባሻገር በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ህብረተሰቡን በማስተባበር የትምህርት ቤቶች ደረጃ እንዲሻሻል መደረጉን አመላክተዋል።
❤ 37👎 5
32 ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ "በዕውቀትና በክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር እናደርጋለን!" በሚል መሪ ሀሳብ ከጥቂት ደቂቃዎች በሃላ መካሄድ ይጀምራል።
(ነሀሴ 26/2017 ዓ.ም) ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣ የካቢኔ አባላት ፣ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮች ፣ ባለሙያዎች ርዕሳነ መምህራን ፣ መምህራን ፣ ተማሪዎች እና ወላጆችን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
በጉባኤው በ2017 የትምህርት ዘመን በትምህርት ዘርፉ የተመዘገቡ ውጤቶችን በመገምገም እንዲሁም የላቀ አፈጻጸም ላላቸው ተቋማት ፣ ባለሙያዎችና ፣ ተማሪዎች እውቅናና ሽልማት በመስጠትና በ2018 የትምህርት ዘመን የሚተገበሩ ስራዎች ላይ የሚወያይ መሆኑ ከወጣው መርሀ ግብር ያሳያል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 57👍 5👎 3👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
32ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ
YAA’II BARNOOTAA 32FFAA SADARKAA MAGAALAA
(ነሀሴ 25/2017 ዓ.ም)
በዕውቀትና በክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር እናደርጋለን!
DHALOOTA BEEKUMSAAFI DANDEETTIIN GAHOOME HORACHUUDHAAN ITIYOOPHIYAA BIYYA FAKKEENYAA NITAASIFNA!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 82👍 25🥰 4👏 1
إظهار الكل...
❤ 16🍾 1
إظهار الكل...
❤ 37🔥 8👍 3
ትላልቅና መካከለኛ ካፌዎች ፤ 41 መጸዳጃ ቤቶች ፤ 9 የህጻናት መጫወቻ ቦታዎች እና 7 የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎችን ጭምሮ 4 ፕላዛዎች እና 130 ሄክታር የሚሸፍን የወንዝ ዳርቻ አረንጓዴ ልማትንም አካቷል።
ይህ የኮሪደር ልማት እንደ ሌሎቹ ኮሪደሮች ሁሉ ለነዋሪዎቻችን ሰፊ የስራ እድል የፈጠረ፣ ፅዱ፣ አረንጓዴ እና ምቹ የመኖሪያ አካባቢ የፈጠረ፣ አካታች እና ሁሉንም ሰዉ ከልማቱ ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ ከ320 በላይ ህንፃዎች እድሳት በማድረግ እና ከ350 በላይ የንግድ ሱቆች በመክፈት የንግድ እንቅስቃሴው በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር ያደረገ፣ የመንገድ መጨናነቅን ችግር በመፍታት የትራንስፓርት ፍሰቱን የሚያቀላጥፍ እና የተለያዩ የአገለግሎት መስጫዎችን ያሻሻለ ውጤታማ ስራ ነው።
ይህ ኮሪደር በታለመለት ጊዜ እና በጀት እንዲጠናቀቅ ደከመን ሰለቸን ሳትሉ ለተሳተፋችሁ ባለሞያዎች፤ አመራሮች እና የአካባቢው ማህበረሰብ በሙሉ በከተማ አስተዳደሩ እና በራሴ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቧቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 78
የረዳን ፈጣሪ ይመስገን!
(ነሀሴ 24/2017 ዓ.ም) ዛሬም ሌላኛው ብስራታችን የሆነውን ከአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን-ጎሮ-ቦሌ አየር መንገድ ቪአይፒ ተርሚናል ኮሪደር አጠናቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።
የሁል ጊዜ ህልማችን እውን የሚሆነው በየእለቱ፣ በየሰዓቱ፣ በየደቂቃው ያለዕረፍት በመስራታችን እና በፈጣሪ እርዳታ ነው።
በ2ኛ ዙር ከጀመርናቸዉ ስምንቱ ኮሪደሮች አንዱ እና ከተጠናቁት ደግሞ 4ኛዉ ሲሆን አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማእከልን ከቦሌ ኤርፖርት ቪአይፒ ተርሚናል የሚያገናኝ፣ ከአንበሳ ጋራዥ - ጃክሮስ ጐሮ እና በኮሪደር አንድ ከተሰራው ቦሌ ኤርፖርት መገናኛ ሲኤምሲ ጋር የሚገጥም ነው።
የኮሪደሩ አጠቃላይ ስፋት ከ290 ሄክታር በላይ ሲሆን 12.74 ኪሎ ሜትር ርዝመት እንዲሁም 29.446 ኪሜ የሚረዝም የእግረኛ መንገድ ያለው ነው።
በተጨማሪም 15.27 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መንገድ፤ ከ550 በላይ ታክሲና ባሶችን የመያዝ አቅም ያላቸው 5 የባስና የታክሲ ተርሚናሎች፤ ከ800 በላይ መኪኖችን የመያዝ አቅም ያላቸው 4 ፓርኪንግን ጨምሮ ታክሲና ባስ መጫኛና ማውረጃ 17 ቤይ ተሰርቶለታል።
ዛሬ ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ያደረግነው ይህ ኮሪደር 5 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማት እና 2 ድልድዮች እንዲሁም 12 ኪ.ሜ የጎርፍ መውረጃ ቱቦ ዝርጋታን ጨምሮ 3.6 ኪ.ሜ የመጠጥ ውሃ ዝርጋታ እና 669 የመንገድ ዳር መብራቶች ተሰርቶለታል።
❤ 56👍 11👎 4🥰 1
