ar
Feedback
Addis Ababa Education Bureau

Addis Ababa Education Bureau

الذهاب إلى القناة على Telegram

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

إظهار المزيد
2025 عام في الأرقامsnowflakes fon
card fon
150 232
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+677 أيام
+34630 أيام
أرشيف المشاركات
በየካ ክፍለ ከተማ ስር ባሉ በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡ (መስከረም 5/2018 ዓ.ም) በየካ ክፍለ ከተማ በሚገኙ በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመደበኛ ትምህርት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የክብር እንግዶች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ በደጃዝማች ወንድራድ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን በይፋ ያስጀመሩት የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ ትምህርት ቤቶች የነገ ሀገር ተረካቢዎች የሚፈሩበት ተቋም በመሆኑ መንግስት የመማር ማስተማር ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ ምቹ የመማሪያ ቦታ በመፍጠር እና ተገቢውን ቁሳቁስ የማሟላት ስራ በየጊዜው እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው መምህራን እና ወላጆች ልጆቻቸውን በስነ ምግባር የታነፁ የማድረግ ስራ አበክረው እንዲሰሩም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ መንግስት ለተማሪዎች የትምህርት አቅርቦቱን የተሟላ ለማድረግ ከቅርብ አመታት ወዲህ በርካታ ስራዎች ማከናወኑን ገልፀው በቀጣይ ጊዜያት ሀገር መቀየር የሚችሉ እና ከሌሎች ሀገራት ጋር ተፎካካሪ መሆን የሚችል ዜጋ ለማፍራት የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት ላይ በስፋት እየተሰራ ያለው ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
إظهار الكل...
25👍 3
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2018 ትምህርት ዓመት መማር ማስተማር በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ተጀመረ። (መስከረም 5/2018 ዓ.ም) ‎የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና፣የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ድሪባ፣ወላጆች መምህራንና ተማሪዎች በተገኙበት በገላን ቁጥር ሁለት የመጀመሪያና መካከለኛ ትምህርት ቤት የ2018 የትምህርት ዘመን መማር ማስተማር ማስጀመሪያ የችቦ ማብራት ስነ ስርዓት ተካሄዷል። ‎ ‎በመርሃ ግብሩ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እና የተማሪዎች ምገባ የማስጀመር መ የተካሄደ ሲሆን በትምህርት ዘመኑ የተማሪ ውጤት እና ባህሪ ማሻሻል ላይ መምህራን እና ወላጆች ትኩረት በመስጠት ሊሰራ ይገባል በማለት የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና አሳስበዋል። ‎ ‎የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ድሪባ ንግግር ሲያደርጉ እንደገለጹት የተማሪ ውጤት ከማሻሻል ጎን ለጎን በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የትምህርት ተቋማት ደረጃ ማሻሻል ላይም መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል። ‎ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
إظهار الكل...
21
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ አሊ ከማል ለትምህርት ዘመኑ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት በማስተላለፍ ለተማሪዎች ስኬታማነት የመምህራን እና የወላጆች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ወላጆች እና መምህራን ትውልድ በመቅረፅ ላይ እያሳረፉት ላሉት አሻራ ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይም ይሄ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። በመረሃ ግብሩ ላይ የተገኙ የክቡር እንግዶች በትምህርት ቤቱ በትምህርት ለትውልድ የተሰሩ የተለያዩ የልማት ስራዎችን የጎበኙ ሲሆን ለተማሪዎች የትምህርት ግብአቶች የመስጠት እንዲም የ2018 የተማሪዎች ምገባንም አስጀምረዋል፡፡ በተጨማሪም በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ ችቦ የማብራት እና ቅብብሎሽ በማከናወን የ2018 በጀት ዓመት የትምህርት ዘመን መደበኛ ትምህርት በይፋ የማስጀመርያ መርሃ ግብር ተከናውኗል፡፡ በዛሬው ዕለት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ባሉ ሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የ2018 ትምህርት ዘመን በይፋ ተጀምሯል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
إظهار الكل...
13🙏 2
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የ2018 የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡ (መስከረም 5/2018 ዓ.ም) በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በሚገኙ በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የ2018 በጀት ዓመት የትምህርት ዘመን ትምህርት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሂዷል፡፡ በክፍለ ከተማዉ አቡነ ባስሊዮስ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተካሔደዉ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የክፍለ ከተማዉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል፣ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ አሊ ከማል ፣ የአዲስ አበባ ከተማ የምገባ ኤጀንሲ የፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አስጨንቅ ብርሀኑ ፣የክፍለ ከተማዉ ትምህርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ገነነ ዘዉዴን ጨምሮ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች እና መምህራን የተማሪ ወላጆች ተገኝተዋል፡፡ በትምህርት ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የክፍለ ከተማዉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል ለትምህርት ዘመን መክፈቻ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት በማስተላለፍ ትምህርት ቤቶች የነገ ሀገር ተረካቢዎች የሚፈሩበት ተቋም መሆኑን ገልፀው ተማሪዎች ፣መምህራን እንዲሁም የወላጆች ድጋፍን በማጠናከር የተማሪ ውጤት እንዲሻሻል በተሻለ ትኩረት መስራት እንደሚገባቸው ገልፀዋል። ወላጆች ልጆቻቸውን በስነ ምግባር የታነፁ የማድረግ ስራ እንዲሰሩም ጥሪቸውን አስተላለፈዋል፡፡ አቶ ቴዎድሮስ አክለው የክፍለ ከተማው አስተዳደር ለትምህት ዘርፍ እያደረገ ያለውን ድጋፍ እንደሚያጠናክርም ተናግረዋል።
إظهار الكل...
14
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የ2018 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሂደት በደማቅ ሁኔታ ተጀምሯል፡፡ (መስከረም 5/2018 ዓ.ም) በትምህርት ለትውልድ መርሀ-ግብር እና በሌሎችም ተመሳሳይ ተግባሮች ክረምቱን ትምህርት ቤቶችን በመማር ማስተማሩ ምቹ የማድረግ ሂደት ሲሰራ እንደነበረ በዚሁ የትምህርት ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ ተገልጿል፡፡ በትምህርት ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ ላይ የክፍለከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ምስክር ነጋሽ፣በክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አምደ አያሌው ፣ የትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃድ ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች እንዲሁም ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የመጡ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ትምህርት ቤቶቹ ያሉበትን ሁኔታም ጎብኝተዋል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
إظهار الكل...
22🤷‍♂ 1
በልደታ ክ/ከተማ በሚገኙ ሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤቶች የ2018 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደት በይፋ ተጀምራል፡፡ (መስከረም 5/2018 ዓ.ም) በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ የልደታ ክፍለ ከተማ ስራ አስፈጻሚ ልዕልቲ ግደይ ፣ የትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ ፣ ሌሎች አመራሮች በመገኘት የመማር ማስተማር ሂደቱን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። የ2018 የትምህርት ዘመን የመመር ማስተማር ሂደት በክፍለ ከተማው በሚገኙ ሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤቶች ተጀምረዋል። በክ/ከተማውም ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል ከዘርፉ ባለድርሻች ጋር በቅንጅት መሰራት እንዳአለበት ተነስቷል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
إظهار الكل...
22🔥 1
በእቴጌ መነን የልጃገረዶች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2018 ትምህርት ዘመን ትምህርት ተጀምራል:: (መስከረም 5/2018 ዓ.ም) በእቴጌ መነን የልጃገረዶች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2018 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ቀን ትምህርት ማስጀመር ስነስርዓት ሲካሄድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት ወ/ሀና ፀጋዬ ፣ ምክትል ርእሳነ መምህራን ፣ መምህራንና ተማሪዎች ተገኝተዋል:: በትምህርት ማስጀመር ስነስርዓቱ ላይ ለተማሪዎችና መምህራን መልእክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ ለ2018 ትምህርት ዘመን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል:: አያይዘውም በ 2017 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ትምህርት ቤቱ ሁሉንም ተማሪዎች በከፍተኛ ውጤት በማሳለፍ ላስመዘገበው ውጤት የውጤቱ ባለቤት የሆኑ ተማሪዎች እና መምህራን እንዲሁም የትምህርት ቤቱ ማህበረሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ ብለው ፤ በዚህ የትምህርት ዘመንም የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በትጋት እንድትሰሩ ሲሉ አሳስበዋል:: የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት ወ/ሪት ሀና ፀጋዬ በ2018 ትምህርት ቤቱን ለተቀላቀሉ አዲስ ተማሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል:: በ2017 ትምህርት ዘመን ትምህርት ቤታችን ያስመዘገበውን ድል ለመድገም በ2018 ትምህርት ዘመን ተማሪዎችና መምህራን በቂ ዝግጅት በማድረግ ለበለጠ ውጤት ራሳችሁን እንድታዘጋጁ ብለዋል :: በቀን አንድ ትምህርት ማስጀመር ስነስርዓቱ ላይ የችቦ ማብራት ስነስርዓት ተካሂዷል :: መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
إظهار الكل...
30
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ለ2018 የትምህርት ዘመንና የተማሪ ወላጆችና አጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፍተኛ ተነሳሽነት ለተጠናቀቀው ህዳሴ ግድብ ምርቃት እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል:: አማካሪዋ የጉለሌ ክፍለ ከተማ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በ2017 በርፎርም ፣ በሳይንስ ሙዚየም አጠቃላይ ምዘና ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገበበት የትምህርት ዘመን እንደነበር አስታውሰው በዚህ ዓመትም የተገኘውን ውጤት የበለጠ ለማሳደግ ከቀድሞው የበለጠ ተነሳሽነትና ተማሪዎች ለትምህርት ትኩረት በመስጠት መልካም ውጤት የምታስመዘግቡበት እንዲሆን ከሁሉም የትምህርት አካላት ይጠበቃል ብለዋል:: የጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮና የሚመለከታቸው አካላት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የመማሪያ ቁሳቁስ ምገባ እና መሰል የመማር ማስተማር ስራውን የሚያግዙ ቅድመ ዝግጅቶች ማድረጉን ገልፀው ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ በመከታተል ራሳቸውን ለውጤታማነት እንዲያዘጋጁ አሳስበዋል:: በቀን አንድ ትምህርት ማስጀመር ስነስርዓቱ ላይ የተገኙ አመራሮች ፣ የትምህርት ቤቱ መምህራንና ተማሪዎች ዕለቱን በማስመልከት ችቦ ማብራት ስነስርዓት አካሂደዋል:: መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
إظهار الكل...
13🤯 1
በጉለሌ ክፍለ ከተማ የ2018 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ስራ ተጀመረ:: (መስከረም 5/2018 ዓ.ም) በትምህርት አጀማመሩ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ፣ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራ ፣ የመምህራን ማህበር ሰብሳቢ አቶ ድንቃለም ቶሎሳ የተ.ወ.ማህበር ሰብሳቢ አቶ ሐሰን ሽፋ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ሥራ አስፈፃሚ አቶ በሀይሉ እምወድ በጋራ በመሆን ጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው እየሩሳሌም ቅድመ መደበኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው የ2018 ትምህርት ዘመን ትምህርት አስጀምረዋል:: በትምህርት ማስጀመር ስነስርዓቱ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ ለመማር ዝግጁ ሆናችሁ የመጣችሁ ተማሪዎች እንዲሁም ተማሪዎችን በእውቀት ለማስታጠቅ የተዘጋጃችሁ መምህራንና የትምህርት ማህበረሰቦች እንኳን ለ 2018 ትምህርት ዘመን እና የሁላችንም አሻራ ያረፈበት ህዳሴ ግድብ ምርቃት ወቅት አደረሳችሁ ብለዋል:: አያይዘውም ለትምህርት ጥራት ምቹ የመማሪያ አካባቢ ለመፍጠርና በትምህርት ዘርፉ ውጤታማ ለመሆን ከተማ አስተዳደሩና ክፍለ ከተማችን እያደረገ ያለውን ጥረት በ2018 ትምህርት ዘመንም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል::
إظهار الكل...
22🤯 1
Photo unavailableShow in Telegram
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል፡፡ (መስከረም 5/2018 ዓ.ም) የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች የሚያገኙበት አድራሻዎችም ይፋ ተደርጓል፡፡ ዌብ ሳይትና ቴሌግራም አድራሻ የሚጠቀሙ ተፈታኞች ጊዜያዊ ሰርቲፊኬታቸውን ወዲያውኑ አውርደው (download አድርገው) መውሰድና መጠቀም ይችላሉ፡፡ ተብሏል:: ውጤት ለመመልከት አድራሻዎች:- 1. በዌብ ሳይት፡ https://result.eaes.et 2. በቴሌገራም፡ https://t.me/EAESbot 3. በአጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS)፡ 6284 ላይ ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋ አድርጓል:: https://t.me/EthiopianEducationalTelevision መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
إظهار الكل...
56👍 15🥱 12👎 1👏 1
በከተማ አስተዳደሩ የ2018 ዓ.ም ትምህርት በሁሉም የትምህርት ተቋማት በዛሬው እለት መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ አስታወቁ። (መስከረም 5/2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የ2018ዓ.ም የትምህርት አመት መጀመሩን እና በሁሉም ተቋማት የትምህርት አጀማመር ሂደቱን የሚከታተሉ የትምህርት አመራሮች እና ባለሙያዎች መመደባቸውን ኃላፊው በጋራ ጉሪ ቅድመ አንደኛ እና አደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተገኙበት ወቅት ገልጸዋል። በከተማ አስተዳደሩ በ2017 ዓ.ም የበጀት አመት በትምህርት ሴክተሩ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር በተከናወኑ ተግባራት በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ከመመዝገቡ ባሻገር በትላንትናው እለት ይፋ በተደረገው የ12ኛ ክፍል ውጤትም በከተማ አስተዳደሩ አበረታች ውጤት መመዝገቡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ጠቁመው በ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት አምና የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻል በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል። በከተማ አስተዳደሩ የ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት ስኬታማ እንዲሆን አዳዲስ የመማሪያ ክፍሎችን የያዙ በርካታ ህንጻዎች እና የመመገቢያ አዳራሾች ከመገንባታቸው ባሻገር ለተማሪዎች የደንብ ልብስን ጨምሮ የተለያዩ የመማሪያ ግብአቶች በከፍተኛ በጀት ዝግጁ መደረጋቸውን ገልጸው የትምህርት አመቱ ውጤታማ እንዲሆን የተማሪ ወላጆችን ጨምሮ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ የሚጠበቅባቸው መሆኑን አስገንዝበዋል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
إظهار الكل...
29👍 4🔥 3😁 2😈 2
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም ትምህርት በዛሬው እለት ተጀመረ። (መስከረም 5/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ ፣ከትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር ፣ከምገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፀዳለ ተክሉ እንዲሁም ከትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሌሊስቱ ተስፋዬ ጋር በመሆን በዱዱቢሳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው የአዲሱን አመት ትምህርት በማስጀመር ተማሪዎችን አበረታተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በከተማ አስተዳደሩ በ2017 ዓ.ም በትምህርት ሴክተሩ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር በተከናወኑ ተግባራት በዘርፉ በርካታ ውጤት መመዝገቡን ጠቁመው በ2018ዓ.ም የትምህርት አመት አምና የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻል ሁሉም ባለድርሻ ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው ዱዱቢሳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በክፍለ ከተማው በርካታ ተማሪዎችን ተቀብለው ከሚያስተምሩ የትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ እንደመሆኑ በ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት በተቋሙ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን የያዘ ህንጻን ጨምሮ የመመገቢያ አዳራሽ እና የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ መገንባቱን ገልጸው የክፍለ ከተማው አስተዳደር ለትምህርት ቤቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አመላክተዋል። በትምህርት ቤቱ የ2018 ዓ.ም ትምህርት መጀመሩን የሚያበስር ችቦ ከመብራቱ ባሻገር የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ በክብር እንግዶች አማካይነት ለተማሪዎች ተሰቷል።
إظهار الكل...
45👍 3🔥 1🫡 1
إظهار الكل...
26👍 8🤪 4
አዲስ አበባ በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በርካታ ተፈታኞችን በማሳለፍ ከሀገሪቱ ቀዳሚ ሆነች፡፡ (መስከረም 4/2018 ዓ.ም) https://youtu.be/CfaTT2F8NJk
إظهار الكل...
56🤣 27🖕 7🤔 5🕊 5👎 4🔥 3🙏 3🥰 1
إظهار الكل...
😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ደስ አላችሁ! (መስከረም 4/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2017 ዓ.ም ያስፈተናቸው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በሁሉም ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ ችለዋል፡፡ በ2016 የትምህርት ዘመን 21.5 የነበረው በ2017 ዓ.ም 29 ፐርሰንት የሚሆኑት ተማሪዎች 50 እና ከዛ በላይ በማምጣት ከፍተኛ ውጤት ተመዝግባል፡፡ እንደ ሀገር 100 ፐርሰንት ካሳለፉ 50 ትምህርት ቤቶች መካከል 15ቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ናቸው፡፡ ምንም ያላሳለፉ ትምህርት ቤት በከተማ አስተዳደሩ የሌሉ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈተናውን ያስፈተኑ ሁለቱ አዳሪ ትምህርት ቤቶች 100 ፐርሰንት ለማሳለፍ ችለዋል፡፡ ከ500 በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች በ2016 ዓ.ም 484 የነበሩ ሲሆን በ2017 ዓ.ም 888 ተማሪዎች ሆነዋል፡፡ ሚኒስቴር መስራቤቱ የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 8.4 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን በዛሬው እለት አሳውቋል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
إظهار الكل...
155👍 25👎 18🔥 11🖕 9😨 8👏 4😁 2
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደረጃ የዘንድሮው የ2018 ትምህርት ዘመን ነገ መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይጀመራል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
إظهار الكل...
41👎 12👍 8😭 8🔥 6🥰 3😁 3🫡 3
Photo unavailableShow in Telegram
የ2018 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ነገ ይጀመራል። (መስከረም 4/2018 ዓ.ም) በ2018 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን የተሻለ ውጤታማ እና በሥነ ምግባር የታነፁ ለማድረግ የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገለጹ። የቢሮው ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ በአዲሱ የትምህርት ዘመን የተሻለ ትምህርት እና ትውልድ ለመፍጠር በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል። በ2017 የመማር ማስተማር ሂደትን የተሳለጠ ለማድረግ የመማሪያ አካባቢዎችን የተመቻቹ ማድረግ ብሎም የትምህርት ቤቶች እድሳት ለተማሪዎችና ለመምህራን ምቹ እንዲሆኑ ለማደረግ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በአዲሱ የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ የተሻለ ውጤት እና ሥነ ምግባር እንዲኖራቸው ለማደረግ አሰራር ተቀምጦ ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል። ለዚህም የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራሮች እንዲጎለብቱና የተማሪዎችና መምህራን ተሳትፎ እንዲያድግ የማድረግ ተግባር ተጠናክሮ ይሰራል ብለዋል። ለትምህርት ዘመኑ የተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁሶች፣ ዩኒፎርም እና የምገባ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል። ኃላፊው አክለውም፤ በትምህርት ዘመኑ ተማሪዎች ላይ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚደርሰውን ተጽዕኖ ለመቀነስ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። ለዚህም የሃይማኖት አባቶች፣ የጸጥታ ተቋማት፣ የሚዲያ ባለሙያዎችና የሚመለከታቸው አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ወላጆችና የትምህርቱ ማህበረሰብ የተማሪዎችን የትምህርት ሁኔታ በመከታተል የመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ በቂ የሆነ ተሳትፎ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።
إظهار الكل...
59👍 4👎 2🤔 1💩 1
إظهار الكل...
19👍 3
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለምረቃ መብቃቱን በማስመልከት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተካሄደ የሚገኘው ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በፎቶ:- #ኢትዮጵያ ችላለች
إظهار الكل...
71👎 28👍 10👏 9🖕 4🔥 2🫡 2