Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
الذهاب إلى القناة على Telegram
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን! Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf! Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
إظهار المزيد2025 عام في الأرقام

163 169
المشتركون
+324 ساعات
+1157 أيام
+40130 أيام
أرشيف المشاركات
ዛሬ ከሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል።
Today, I met with President Hassan Sheikh Mohamud of the Federal Republic of Somalia, for discussions on bilateral and regional issues of mutual interest.
08:01
Video unavailableShow in Telegram
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተጀመረው የፍትህ አሰጣጥ ቴክኖሎጂ በሁሉም ክልሎች ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።
55.00 MB
ቴክኖሎጂ መር አዘማኝነት ላይ የሚያተኩረው የዲጂታል 2025 ስትራቴጂ በስኬት መጠናቀቅን ተከትሎ አሁን በበለጠ የማሽን ግብዓት (አቶሜሽን) በመጠቀም አገልግሎት አሰጣጥን የሚያጠናክረውን ዲጂታል 2030ን አስጀምረናል። የፍትኅ ተደራሽነት ለዜጎች እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ መሆኑን እውቅና በመሥጠትም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፈጣን፣ ግልጽ እና ውጤታማ የሆነ ሥርዓት ለመገንባት በጽናት እየሠራ ይገኛል።
ዛሬ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት የፍርድ ሂደቶች በአግባቡ መቀዳታቸውን ለማረጋገጥ ድምጽን ወደ ጽሁፍ የሚቀይር ብሎም በአስተማማኝ ሁኔታ ተጠብቀው የሚቆዩበትን ስማርት የፍርድ ሥርዓት አልምቶ በመመልከቴ ደስታ ተሰምቶኛል። ሥርዓቱ ፍትኅ ፈላጊዎች ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው በአካል በችሎት መገኘት ሳይጠበቅባቸው ካሉበት ሆነው ጉዳያቸውን ለመከታተል ያስችላቸዋል። በተጨማሪም የለሙት የNetwork Operation Center እና Integrated Case Management System የፍርድ ሂደት ባለጉዳዮች በዲጂታል አውታሮች ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ያስችላሉ። በአሁኑ ወቅት 24 የፌደራል ቅርንጫፎች በሥርዓቱ የተሸፈኑ መሆኑ አበረታች ሲሆን በቅርቡ ወደ ክልሎችም እንደሚስፋፋ ተስፋ አለን።
ረቡዕ በሀላባ እና ከምባታ ዞኖች የነበረንን የሞዴል የገጠር መንደሮች ርክክብ ሥነሥርዓት በመቀጠል ዛሬ ደግሞ በሀዲያ እና ስልጤ ዞኖች የተገነቡትን አስረክበናል። እነኚህ ባለሶስት መኝታ ቤት መኖሪያዎች ለማብሰል የሚያገለግል የባዮጋዝ መሣሪያ፣ የፀኃይ ኃይል ማመንጫ፣ የዶሮ ማርቢያ፣ የተለየ የእንስሳት በረት የተሟላላቸው ሲሆን በተመጣጣኝ አነስተኛ ወጪ ከአካባቢ በሚገኙ ግብዓቶች የተሻለ መኖሪያ ከማስገኘት አንፃር ለገጠሩ ማኅበረሰብ ብልጽግና ያለንን ሕልም የሚያሳይ ነው።
እንደ ማኅበረሰብ አዲስ ሀሳቦች ሲፈልቁ “አይቻልም” በሚለው የቆየ አስተሳሰብ የመፈተን ተግዳሮት ይደቀንብን ይሆናል። ይሁንና በተጨባጭ በሚታየውና በተገኘ ውጤት ላይ ወደ አለማመን እና አለመቀበል በሚመራን የሀሳብ ወጥመድ ውስጥ መውደቅ የለብንም። ዜጎች ለውጥ እንደሚቻል ሀብቶቻችንን ወደ ትክክለኛ የቅድሚያ ትኩረቶቻችን ካዋልንም ማኅበረሰብን በርግጥም ማሻገር እንደምንችል ማመን ይገባቸዋል። በአራቱ ዞኖች የተሠራው ሥራ በመላው ክልሉ መደገም ይኖርበታል። የክልሉ አመራር ይኽን ታላቅ ስራ እንደሚፈጽመውም እምነት ጥያለሁ።
06:32
Video unavailableShow in Telegram
For Africa, now is not the time to wait and watch.
We have the people, creativity, and natural wealth to build a prosperous and fair future. What we need is to connect our efforts and act with common purpose.
13.44 MB
ዛሬ በናይሮቢ፣ ኬንያ “ዲጂታላይዜሽንን ለቀጠናዊ የእሴት ሰንሰለት መጎልበት በመጠቀም ለዘላቂ እና አካታች እድገት ማዋል” በሚል ጭብጥ በተካሄደው 24ኛው የCOMESA መሪዎች ጉባኤ ላይ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የአፍሪካን የኢኮኖሚ ታሪክ የመቀየር ልዩ እድል እንዳቀረበልን አፅንኦት ሰጥቼ አንስቻለሁ። እንደ አኅጉር የየሀገሮቻችንን ጥረቶች ለማጣመር እና ቀጠናዊ ትስስሮችን ለማፋጠን ክሂሎቱ እና መሠረቱ አለን።
በኢትዮጵያ ዲጂታል ክሂሎትን ለማበልጸግ እና አስፈላጊ መሠረተ ልማት ለመገንባት ጥሩ ርምጃዎች ተራምደናል። የጋራ ዲጂታል ነጋችንን ለማሳደግ በትብብር ለመሥራት ዝግጁ ነን።
At the 24th COMESA Summit of Heads of State and Government held today in Nairobi, Kenya, under the theme “Leveraging Digitalization to Deepen Regional Value Chains for Sustainable and Inclusive Growth,” I emphasized that digital transformation presents a unique opportunity to rewrite Africa’s economic story. As a continent, we possess the talent and digital foundations needed to connect national efforts and accelerate regional integration.
In Ethiopia, we are making significant strides in developing digital talent and building the necessary infrastructure. Undoubtedly, we stand ready to collaborate in advancing our shared digital future.
13:46
Video unavailableShow in Telegram
ወረዳው ፣ ዞኑ፣ ክልሉ ዋና ስራው የዜጎቹን ህይወት ማሻሻል ነው።
33.23 MB
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የነበረንን ቆይታ አጠናቀን ወደ አዲስ አበባ ተመለሰን የሳይፕረስ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኮንስታንቲኖስ ኮምቦስ እና የልዑካን ቡድናቸውን በጽሕፈት ቤታችን ተቀብለናል። ሁለቱ ሀገሮቻችን የዲፕሎማቲክ ግንኙነታችንን ለማጠናከር ብሎም ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ትብብሮችን ለማጎልበት ጠንካራ ፍላጎት አለን። በመሆኑም እነዚህን የጋራ አላማዎች ለማራመድ የሚጠቅሙንን ሰፊ አድማስ ያላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል።
Following a busy field day in the Central Ethiopia Region, I had the pleasure of receiving Dr. Constantinos Kombos, Minister of Foreign Affairs of the Republic of Cyprus, and his delegation at my office later this afternoon in Addis Ababa. Our two countries share a strong interest in deepening diplomatic relations and enhancing economic and political cooperation. Accordingly, we discussed a range of issues aimed at advancing these shared objectives.
