ar
Feedback
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

الذهاب إلى القناة على Telegram

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot 🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

إظهار المزيد
2025 عام في الأرقامsnowflakes fon
card fon
221 465
المشتركون
-8724 ساعات
-5427 أيام
-2 53630 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
ከ100 የሚበልጡ ስደተኞች በሜድትራንያን ባህር ላይ ህይወታቸው አለፈ 117 ሰዎችን ጭኖ ከሊቢያ በመነሳት አውሮፓ ለመድረስ የሞከረ መርከብ ከሰጠመ በኋላ 116 ሰዎች ሲሞቱ በህይወት የተረፈው አንዱ ብቻ ነው። አደጋው ባለፈው ሳምንት ማጋጠሙ የተዘገበ ሲሆን በህይወት የተረፈው ግለሰብ ወደ ሆስፒታል መወሰዱ ተነግሯል። በህይወት የተረፈው ግለሰብ የተገኘው አደጋው ከደረሰ ከሁለት ቀናት በኋላ ነው ሲባል ያገኙት በእንጨት በተሰራ ጀልባ አሳ የሚያጠምዱ ቱኒዛውያን ናቸው። መርከቧ ከሊቢያ ተነስታ ጥቂት እንደተጓዘች ድጋፍ እንደሚያስፈልጋት መልዕክት ብትልክም በሳተላይትም በአየር ፍለጋም ልትገኝ አልቻለችም። በህይወት የተረፈው ግለሰብ ከሊቢያ ጥቂት እንደተጓዙ መጥፎ የአየር ንብረት መፈጠሩን ገልጿል። በወቅቱ በሰዓት 40 ኪሎ ሜትር የሚነፍስ ነፋስ ነበር ሲባል አደጋውም በዚህ ምክንያት እንደደረሰ ታምኗል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
😭 115 74💔 27
Photo unavailableShow in Telegram
#በመሃል_አዲስ አበባ #ዋና መስቀለኛ_መንገድ  ዳር  እጅግ ዘመናዊ  አፓርትመንት በሽያጭ ላይ ነን 50% ባንክ  ከወለድ ነጻ 8% ብቻ በመክፈል ቤትወን ይምረጡ ማለትም       80ካሬ=472,960ብር 110ካሬ=650,320ብር 117ካሬ=691,704ብር 120ካሬ=7,803,840ብር 140ካሬ=827,680ብር 165ካሬ=975,480ብር ብቻ በመክፈል ቤትወን ዛሬውኑ  ይምረጡ ለበለጠ  መረጃ   💚በ+251944301786ይደውሉልኝ
إظهار الكل...
15
Photo unavailableShow in Telegram
በናይጄሪያ መስጊድ በሰላት ወቅት ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ ቢያንስ 5 ሰዎች ሲገደሉ 35 ሰዎች ቆሰሉ‼️ በናይጄሪያ ሰሜናዊ ምስራቅ ቦርኖ ግዛት ሀሙስ በምሽት ሰላት ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ ቢያንስ አምስት ሰዎች ሲገደሉ 35 ያህል ሰዎች ቆስለዋል ሲሉ የፖሊስ ቃል አቀባይ ኤኤስፒ ናሆም ዳሶ ኬኔት የማህበራዊ ሚዲያ ድረ-ገጽ በሆነዉ ፌስቡክ ላይ ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡ በመግለጫው መሰረት፣ ባለስልጣናት በግዛቱ ዋና ከተማ ማይዱጉሪ የተፈጸመው ፍንዳታ በአጥፍቶ ጠፊ ፍንዳታ ነው ብለው እንደሚጠረጥሩ በማንሳት ምስክሮች ከሰጡት ቃል እና በአጥፍቶ ጠፊነት ከተጠረጠረው ልብስ ውስጥ ቁርጥራጮች መገኘታቸውን ገልጸዋል። ኃላፊዎቹ የችግሩን መንስኤና ሁኔታ ለማወቅ ምርመራውን ቀጥሏል ብለዋል ።የቦርኖ ግዛት ለዓመታት በታጣቂዉ ቦኮ ሃራም እና መሰል ቡድኖች ስትታመስ ቆይታለች። @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
😭 99 94👍 12🔥 7👏 2😁 2
ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ‼️ ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ መልዕክቶች ተደራሽነታቸው የበዛ በመሆኑ በትውልዱ ላይ የሚያሳድሩት አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑን የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ማህበራዊ ሚዲያን በአግባብና በኃላፊነት መንፈስ ከተጠቀሙበት ትውልድን በስነ ምግባር ለማነፅና ለማፅናት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አመልክቷል፡፡ ነገር ግን ከዚህ በተፃራሪ የተሰለፉ አንዳንድ ግለሰቦች ለማየትና ለመስማት አጸያፊ የሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ ይዘቶችን ሲሰሩ እንደሚታዩ ፖሊስ ገልጿል፡፡     በዚህም መሰረት ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ ከነበሩ ግለሰቦች አንዱ የሆነውን ነዋሪነቱ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የሚገኝ ናትናኤል ባደግ ገብሬ የተባለን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን ነው የአዲስ አበባ ፖሊስ የገለፀው፡፡ ተጠርጣሪው የማህበራዊ ሚዲያን በተለይም ዩቱዩብ እና ቲክቶክን በመጠቀም በንግግር ልቅ ፆታዊ ግንኙነትን የሚያበረታታና የሚያስፋፋ አፀያፊ መልዕክቶችን ሲያሰራጭ መቆየቱ ተጠቁሟል። ተጠርጣሪው በተለምዶአዊው ንግግር ሊገለፁ የማይችሉ አስፀያፊ ቃላትን በመጠቀም በትውልዱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር እንደነበር እና መሰል ይዘቶችን በተደጋጋሚ ጊዜ በመስራት በማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም ሲያሰራጭ እንደነበርም ፖሊስ አብራርቷል፡፡ ፖሊስ በቁጥጥር ስር በዋለው ናትናኤል ባደግ ወይም "የማህበራዊ ሚዲያ አንቂ ወይም ይዘት ፈጣሪ ነኝ" በሚለው ግለሰብ ላይ ምርመራ መጀመሩን ጠቅሷል። በአንዳንድ ኃላፊነት በማይሰማቸው ግለሰቦች በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከህብረተሰቡ ሞራል ባህልና እሴት ባፈነገጠ ሁኔታ አሉታዊ መረጃዎች እየተሰራጩ መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ፤ ይህም በማህበረሰቡ በተለይም ታዳጊ በሆኑ ህፃናት ሥነ-ልቦናና ሞራል ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን ገልጿል፡፡     የአዲስ አበባ ፖሊስ አክሎም፤ በቀጣይ ተመሳሳይ ድርጊት ውስጥ በሚገቡ ግለሰቦች ላይ ተገቢውን ህጋዊ ርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል፡፡ @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
212👍 66👏 26💔 16😡 4

1
👍 39😁 11 9😱 1
በአዲስ አበባ ከተማ በአጥር የተዘጉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በግብረ ኃይል የማስከፈት ስራ ተጀመረ‼️ በአዲስ አበባ በከተማ ተለያዩ አካባቢዎች በአጥር የተዘጉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በግብረ ኃይል የማስከፈት ስራ በትናንትናው ዕለት  መጀመሩን የከተማዋ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ።ባለስልጣኑ ይህን እርምጃ መውሰድ የጀመረው፣ ከሳምንታት በፊት በከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን አጥረው የዘጉ ግለሰቦች መንገዶቹን ከታኅሣሥ 4 ቀን 2018 ዓ.ም.  ጀምሮ ባሉት ሰባት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ክፍት እንዲያደርጉ የሰጠው ማስጠንቀቂያ ተግባራዊ ባለመሆኑ ነው። ባለስልጣኑ ትናንት ባጋራው መረጃ፣ የደቡብ አዲስ አበባ መንገድ ኔትዎርክ ማኔጅመንት ቡድን መሪ ኢንጅነር ቢሊሱማ በዬቻ፤ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በግለሰቦች በአጥር መዝጋታቸው፤ የህብረተሰቡን በመንገድ መሰረተ ልማት የመጠቀም መብት የሚጋፋና ለትራፊክ ፍሰት መስተጓጎል መንስኤ እየሆነ እንደሚገኝ ገልፀዋል ብሏል፡፡ በመሆኑም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቃሊቲ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ጀርባ፤ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በአጥር የዘጉ አካላት፣ አጥሩን እንዲያነሱ ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ቢሆንም፤ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ባለመነሳቱ ከወረዳው የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በግብር ኃይል እንዲነሳ መደረጉን ገልጸዋል። የደቡብ አዲስ አበባ የመንገድ ኔትዎርክ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት የአስተዳደርና ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ አብይ ኪዳኑ በበኩላቸው፤ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በአጥር በመዘጋታቸው ነፍሰጡር እናቶች ሌሊት ላይ ወደ ህክምና ተቋም ለመሄድና የአደጋመካከል ሥራዎችን በአግባቡ ለማከናወን አስቸጋሪ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ፤ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የተበላሹ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ለመጠገን የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ጭምር እያስተጓጎለ መምጣቱን የጠቀሱት አቶ ዓብይ ፤ በግብረ ኃይል እንዲነሳ መደረጉ በየአካባቢው ህብረተሰቡ ለሚያነሳው የመንገድ አገልግሎት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡በቀጣይ ቀናትም ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ይህንኑ ተግባር በሁሉም የከተማዋ ክፍሎች አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል፡፡ @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
157👍 9😁 2
18😁 9
Photo unavailableShow in Telegram
#በመሃል_አዲስ አበባ #ዋና መስቀለኛ_መንገድ  ዳር  እጅግ ዘመናዊ  አፓርትመንት በሽያጭ ላይ ነን 50% ባንክ  ከወለድ ነጻ 8% ብቻ በመክፈል ቤትወን ይምረጡ ማለትም       80ካሬ=472,960ብር 110ካሬ=650,320ብር 117ካሬ=691,704ብር 120ካሬ=7,803,840ብር 140ካሬ=827,680ብር 165ካሬ=975,480ብር ብቻ በመክፈል ቤትወን ዛሬውኑ  ይምረጡ ለበለጠ  መረጃ   💚በ+251944301786ይደውሉልኝ
إظهار الكل...
22😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
የሌሊትና የማለዳ ቅዝቃዜ እስከ ታህሳስ መጨረሻ ይቀጥላል‼️ የሌሊትና የማለዳው ቅዝቃዜ እስከ ታህሳስ ወር መጨረሻ ድረስ በተለይም በደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለጋዜጣ ፕላስ በላከው መረጃ እንዳመለከተው፤ ከሳይቤሪያ የሚነፍሰው ከፍተኛ የአየር ግፊት ወደ ኢትዮጵያ የሚዘልቅ በመሆኑ ደረቅ፣ ጸሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ይስተዋላል። በተለይም በሰሜን፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛውና በደቡብ ደጋማ አካባቢዎች የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ ከአምስት ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ሊመዘገብ እንደሚችል ተጠቁሟል። ይህ ቅዝቃዜ እስከ ወሩ ማጠናቀቂያ ድረስ የሚዘልቅ በመሆኑ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
134🔥 10🎉 4🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
#በመሃል_አዲስ አበባ #ዋና መስቀለኛ_መንገድ  ዳር  እጅግ ዘመናዊ  አፓርትመንት በሽያጭ ላይ ነን 50% ባንክ  ከወለድ ነጻ 8% ብቻ በመክፈል ቤትወን ይምረጡ ማለትም       80ካሬ=472,960ብር 110ካሬ=650,320ብር 117ካሬ=691,704ብር 120ካሬ=7,803,840ብር 140ካሬ=827,680ብር 165ካሬ=975,480ብር ብቻ በመክፈል ቤትወን ዛሬውኑ  ይምረጡ ለበለጠ  መረጃ   💚በ+251944301786ይደውሉልኝ
إظهار الكل...
16🎉 1
ከጥር 23 ጀምሮ ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶችን መጠቀም፣ ማምረትና ወደሀገር ውስጥ ማስገባት ያስቀጣል‼️ ከጥር 23 ጀምሮ ለአንድ ጊዜ አገልግሎት ብቻ የሚውሉ ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶችን የሚጠቀሙ፣ የሚያመርቱና ወደሀገር ውስጥ የሚያስገቡ አካላትን መቅጣት ሊጀመር መሆኑን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ። ለአንድ ጊዜ አገልግሎት ብቻ የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶችን ማምረት፣ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትና ይዞ መገኘት የሚከለክለው አዋጅ ከሐምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የጸደቀ ቢሆንም፣ ባለስልጣኑ የስድስት ወራት የሽግግር ጊዜ ሰጥቶ ቆይቷል። የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ዴስክ ኃላፊ ዋሲሁን ዓለሙ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ አዋጁ እንደወጣ የወረቀትና ሌሎች አማራጭ ከረጢቶች ወደ ገበያ በመምጣታቸው የፕላስቲክ ስርጭት ቀንሶ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን በድጋሚ በገበያው ውስጥ እየታዩ ይገኛሉ። ባለስልጣኑ በዚህ የሽግግር ወቅት አዋጁን ሙሉ በሙሉ ለመተግበር የሚያስችሉ የዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል። በዚህም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የፕላስቲክ አምራቾች፣ ተጠቃሚዎች እንዲሁም አማራጭ የወረቀት ከረጢት አምራቾች ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። የወረቀትና ሌሎች የከረጢት ዓይነቶችን ማምረት የሚፈልጉ አካላትን ወደ ገበያ ለማስገባት ማሽኖችን ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡና የብድር አቅርቦት እንዲያገኙ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል። የሽግግር ጊዜው ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚያበቃ የገለጹት ኃላፊው፤ ከዚህ ዕለት በኋላ ሕገወጥ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኙ አካላት ተጠያቂ ስለሚሆኑ ሁሉም አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርግ አሳስበዋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
140😁 42👍 7🔥 7😭 7😱 6😡 2
Photo unavailableShow in Telegram
#በመሃል_አዲስ አበባ #ዋና መስቀለኛ_መንገድ  ዳር  እጅግ ዘመናዊ  አፓርትመንት በሽያጭ ላይ ነን 50% ባንክ  ከወለድ ነጻ 8% ብቻ በመክፈል ቤትወን ይምረጡ ማለትም       80ካሬ=472,960ብር 110ካሬ=650,320ብር 117ካሬ=691,704ብር 120ካሬ=7,803,840ብር 140ካሬ=827,680ብር 165ካሬ=975,480ብር ብቻ በመክፈል ቤትወን ዛሬውኑ  ይምረጡ ለበለጠ  መረጃ   💚በ+251944301786ይደውሉልኝ
إظهار الكل...
23😁 2
በቂርቆስ ክ/ከተማ የ1 ዓመት ከ8 ወር ህጻን ሰርቆ ለማምለጥ የሞከረ ተጠርጣሪ እጅ ከፍንጅ ተይዞ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለጸ‼️ ተጠርጣሪው የወንጀል ድርጊቱን ፈጽሟል የተባለው ታህሳስ 5 ቀን 2018 ዓ/ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በተለምዶ ሃዲድ ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ ነው። የህጻን አቢያለው ተክሉ ወላጅ እናት ወ/ሮ ማርሸት ሞገስ ቤቷ ውስጥ ስራዋን እያከናወነች በነበረበት ወቅት ህጻኑ ከቤታቸው አካባቢ እየተጫወተ በነበረበት ወቅት ማንነቱን የማያውቁት ግለሰብ ህጻን አቢያለውን ታቅፎ ይዞ ሲሄድ ያዩት የአካባቢው ነዋሪዎች እንደነገሯት ተናግራለች። አድማሱ አገዘ የተባለው ተጠርጣሪ ከመኖሪያ ቤቱ በራፍ አካባቢ ሲጫወት የነበረን ራሱን መከላከል የማይችል የ1 ዓመት ከ8 ወር ህጻን ታቅፎ በመሄድ ላይ እያለ በስራ ላይ የነበሩ የፖሊስ አባላት ባደረባቸው ጥርጣሬ  ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር እጅ ከፍንጅ ተይዞ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ  አስታውቋል። ፖሊስ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ ምርመራ የማስፋት ተግባሩን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በቀጣይም ክስ እንደሚያስመሰርት በማስታወቅ ህጻኑንም ለቤተሠቡ አስረክቧል። ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን አስቀድሞ ለመከላከል የህጻናት ወላጆች ልጆቻቸውን በጥንቃቄ መያዝ እና እንደዚህ አይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲመለከቱ አጥፊዎች በህግ አግባብ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ለፀጥታ አካላት ጥቆማ መስጠት እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
289👍 58👏 25🔥 11😭 6😱 5😁 3
Photo unavailableShow in Telegram
#በመሃል_አዲስ አበባ #ዋና መስቀለኛ_መንገድ  ዳር  እጅግ ዘመናዊ  አፓርትመንት በሽያጭ ላይ ነን 50% ባንክ  ከወለድ ነጻ 8% ብቻ በመክፈል ቤትወን ይምረጡ ማለትም       80ካሬ=472,960ብር 110ካሬ=650,320ብር 117ካሬ=691,704ብር 120ካሬ=7,803,840ብር 140ካሬ=827,680ብር 165ካሬ=975,480ብር ብቻ በመክፈል ቤትወን ዛሬውኑ  ይምረጡ ለበለጠ  መረጃ   💚በ+251944301786ይደውሉልኝ
إظهار الكل...
29👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
እግዱ ተነስቷል‼️ በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት በማድረግ መንግሥት በሱር ኮንስትራክሽን ስር የሚተዳደሩ 22 ተቋማት ላይ ለማጣራት በሚል ጊዚያዊ እግድ ጥሎ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ የማጣራት ስራው ስለተጠናቀቀ እግዱ እንዲነሳ ፍትህ ሚኒስቴር ለሁሉም ባንኮች በደብዳቤ አሳውቋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
113👍 27😁 21
Photo unavailableShow in Telegram
#በመሃል_አዲስ አበባ #ዋና መስቀለኛ_መንገድ  ዳር  እጅግ ዘመናዊ  አፓርትመንት በሽያጭ ላይ ነን 50% ባንክ  ከወለድ ነጻ 8% ብቻ በመክፈል ቤትወን ይምረጡ ማለትም       80ካሬ=472,960ብር 110ካሬ=650,320ብር 117ካሬ=691,704ብር 120ካሬ=7,803,840ብር 140ካሬ=827,680ብር 165ካሬ=975,480ብር ብቻ በመክፈል ቤትወን ዛሬውኑ  ይምረጡ ለበለጠ  መረጃ   💚በ+251944301786ይደውሉልኝ
إظهار الكل...
17
Photo unavailableShow in Telegram
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌትናንት ጀኔራል ታደሠ ወረደ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ አቀኑ‼️ ጀኔራል ታደሠ የጊዜያዊ አስተዳደሩን ልዑካን ቡድን አስከትለው ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት፣ ባንዳንድ አጠቃላይ ጉዳዮች ዙሪያ ከፌዴራል መንግሥቱ ባለሥልጣናት ጋር ለመወያየት እንደኾነ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ማምሻውን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሠራጨው መረጃ ገልጿል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
109😁 39👍 33😱 3💔 2
Photo unavailableShow in Telegram
በመተት አስፈራርታ 3 መቶ ሺ ብር ከግል ተበዳይ ልትቀበል ያለች ተጠርጣሪ መያዙን ፖሊስ ገለጸ‼️ 3መቶ ሺ ብር በባንክ ካላስገባህ በመተት በቤተሰብህ ላይ ጉዳት አደርሳለሁ እያለች ስታስፈራራ የነበረችን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። ግለሰቧ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ወሎ ሰፈር አካባቢ ከሚገኝ አንድ ፕላዛ ውስጥ በጽዳት ሰራተኝነት እና በአሳንሰር ተቆጣጣሪነት ተቀጥራ የምትሰራ ሲሆን የግል ተበዳይ በዚሁ ህንጻ ላይ ከሚገኝ የአንድ የግል ድርጅት የፋይናስ ኃላፊ ናቸው። ተበዳይ ለፖሊስ በሰጡት ቃል የኔሰው የሚባል ግለሰብ ከአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ቢኮሎ ከሚባል አካባቢ እንደሚደውል ገልጸው 3መቶ ሺ ብር በባንክ ካላስገባህ ልጅህን የሰይጣን መሳቢያ አደርጋታለሁ የሚል የማስፈራሪያ መልዕክት በማያውቁት ስልክ ተደውሎ እንደደረሳቸው ተናግረዋል። ተጠርጣሪዋ የግል ተበዳይን በመከታተል ካጠናች በኋላ ማንነቷን በመደበቅ እና ድምጿን በመቀየር አስፈራርታ 25ሺ ብር  በባንክ እንዲያስገቡላት ካደረገች በኋላ ቀሪ 275ሺ ብር ለማስላክ ስትሞክር የግል ተበዳይ ለፖሊስ በሰጡት መረጃና ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ልትያዝ ችላለች። በተጨማሪም ፖሊስ ግለሰቧ ለግል ተበዳይ ለመላክ ያዘጋጀችው የማስፈራሪያ  ጽሑፍ የእጅ ስልኳ ላይ መገኘቱን የገለጸ ሲሆን በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተጣራባት አስታውቋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
إظهار الكل...
184😁 101👍 21😭 4

24