ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
الذهاب إلى القناة على Telegram
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot 🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
إظهار المزيد2025 عام في الأرقام

221 247
المشتركون
-14824 ساعات
-6057 أيام
-2 63230 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
በመሃል ፒያሳ አራዳ ፓርክ ፊት ለፊት በምናስገነባው ሳይት ላይ
ባለ 1 መኝታ ከ441ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ
ባለ 2 መኝታ 855ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ
ባለ 3 መኝታ ከ1.1 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ ያወጣን ሲሆን
70% ለሚከፍሉ ደንበኞች ደግሞ 30% off የምናደርግ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ በእነዚህ ስልኮች ይደውሉ
0957504151
0995232706
❤ 40🔥 3
Photo unavailableShow in Telegram
በአዋሽ ፈንታሌ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ‼️
በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ዛሬ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል አለ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ሕዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት።
በዩኒቨርሲቲው የሶሲሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ አታላይ አየለ (ፕ/ር)፥ በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 8 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ለፋና ዲጂታል አረጋግጠዋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ24 ደቂቃ አካባቢ መከሰቱን ገልጸዋል።
የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረትም አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ የተለያዩ አካባቢዎች ድረስ መሰማቱን ነው የገለጹት።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 165👍 17😭 15👏 13😱 8🔥 5😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
የዩክሬን ደጋፊ አገራት የሩሲያን ነዳጅ ከዓለም አቀፍ ገበያ 'ለማስወጣት' ቃል ገቡ‼️
ከ20 በላይ አገራት ዩክሬንን በመደገፍ "የሩሲያን ነዳጅ እና ጋዝ ከዓለም አቀፍ ገበያ ለማስወጣት" ቃል ገቡ።
አገራቱ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጦርነቱን እንዲያቆሙ ጫና በማሳደር ከዩክሬን ጎን እንደሚቆሙ ገልጸዋል።
የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር እንዳሉት አገራቱ የተሰባሰቡት "በበጎ ፈቃደኛነት" ነው።
ስታርመር ለአገራቱ የጋራ ጉባዔ አዘጋጅተዋል።
አሜሪካ በሁለቱ የሩሲያ ነዳጅ አምራች ድርጅቶች ሮስኔፍት እና ሉክኦይል ላይ አዲስ ማዕቀብ መጣሏ ይታወሳል።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 115😁 53👍 19😡 15🕊 7💔 5👌 2
Photo unavailableShow in Telegram
ስምረት ፓርቲ አቶ ጌታቸው ረዳን ፕሬዚዳንቱ አድርጎ መረጠ‼️
መስራች ጉባኤውን ያካሄደው የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ስምረት (ስምረት) ፓርቲ አቶ ጌታቸው ረዳን የፓርቲው ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጧል፡፡
ነጋ አሰፋ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ሃፍቱ ኪሮስ ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም ሰብለ አሰፋ የፓርቲው ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተመርጠዋል።
ፓርቲው መስራች ጉባኤውን ሲያካሂድ ከፓርቲው ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት በተጨማሪ ሰባት ጉዳይ ፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም 31 የምክር ቤት አባላትን መርጧል፡፡
ፓርቲው የቁጥጥር ኮሚሽን እና ኢንስፔክሽን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበርንም መርጧል፡፡
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 145😁 59👍 18😱 17👏 10😡 4😭 1
የራያ አላማጣ ሃገረ ስብከት አመራር በታጠቁ ኃይሎች ታፍነው መወሰዳቸው ተዘገበ‼️
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፣ የራያ ሃገረ ስብከት አመራር ከሦስት ቀን በፊት በታጠቁ ሰዎች ታፍነው መወሰዳቸውን የሃገረ ስብከቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አስታውቀዋል፡፡
ታፍነው የተወሰዱት የአገረ ስብከቱ የሂሳብ ክፍል ኃላፊ መሆናቸውን ለሃራምቤ የተናገሩት የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ ሊቀ ስዩማን ሃብቱ አየነው፤ በትግራይ ክልል የተቋቋመው የመንበረ ሰላማ አገረ ስብከት ደጋፊ የሆኑ የህውሓት ታጣቂዎችን ለድርጊቱ ተጠያቂ አድርገዋል፡፡
ከህውሓትም ሆነ ከመንበረ ሰላማ አገረ ስብከት እስካሁን በጉዳዩ ላይ የተሰጠ ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ ባይኖርም፣ በኃይማኖት አባቶች ላይ የሚፈጸመው ተደጋጋሚ አፈና፣ ደብደባ፣ ዘረፋና እንግልት እያሳሰበው መምጣቱን ሃገረ ስብከቱ መግለጹ ተዘግቧል፡፡
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 139😭 72👏 21💔 12🔥 4😱 3😡 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ፤ በመጪው ግንቦት 24፤ 2018 ለማድረግ ምክረ ሃሳብ አቀረበ‼️
-ቦርዱ በምርጫው የሚገኘውን ውጤት ይፋ ለማድረግ፤ በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው ያስቀመጠው ዕለት ሰኔ 3 ነው።
ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ የጠቅላላ ምርጫውን ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ አዘጋጅቶ ለውይይት ያቀረበው፤ ከትላንት በስቲያ ሰኞ ጥቅምት 10 ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባደረገው ምክክር ላይ ነበር። በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው በዚህ ውይይት ላይ ከ60 በላይ በህጋዊ መንገድ የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች መሳተፋቸውን፤ በመድረኩ የታደሙ ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
መገናኛ ብዙሃን ባልተገኙበት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ፤ ምርጫ ቦርድ የ7ተኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳ አቅርቧል። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው የጊዜ ሰሌዳ፤ 37 ተግባራት የሚከናወኑባቸውን ጊዜያት በቀን እና በወራት ከፋፍሎ አስቀምጧል።
በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው፤ ከህዳር መጀመሪያ እስከ ወሩ አጋማሽ ድረስ በምርጫ ለሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል ዕጩዎች የምዝገባ ጥሪ ለማድረግ ታቅዷል።
የምርጫ አስፈጻሚዎችን ዝርዝር ለፖለቲካ ፓርቲዎች እና ለህዝብ ይፋ ማድረግ፤ ህዳር 19 ተጀምሮ በጥር የመጀመሪያ ሳምንት ላይ ለማጠናቀቅ ታስቧል። ይህ መርሃ ግብር በሁለት ዙር የሚከናወን መሆኑ በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው ላይ ተመልክቷል።
በምርጫ የሚሳተፉ ዕጩዎች ምዝገባ እንዲከናወን የታቀደው ከታህሳስ መጀመሪያ እስከ ጥር መጀመሪያ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው። የምረጡኝ ቅስቀሳ ከታህሳስ 10 እስከ ግንቦት 19 ድረስ እንዲከናወን ቦርዱ አቅዷል።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 227😁 30😭 15👍 13👏 11😱 3🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
በኦሮሚያ ምዕራብ ሸዋ በኖኖ ወረዳ 12 ነዋሪዎች እና 22 ታጣቂዎች መገደላቸውን የአካባቢው አስተዳደር ገለፀ‼️
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ከጉራጌ ዞን የተነሱ ናቸው የተባሉ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን እና የፀጥታ ኃይሎች ደግሞ 22 መግደላቸውን ነዋሪዎች እና የአካባቢው ባለሥልጣን ለቢቢሲ ተናገሩ።በኖኖ ወረዳ ሀሎ ዲኒቂ መንደር ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 8/2018 ዓ. ም. ምሽት ላይ በተፈጸመው ጥቃት 22 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ሲናገሩ የኖኖ ወረዳ አስተዳዳሪ ግን የተገደሉት 12 ሰዎች መሆናቸውን ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ገልጸዋል።
ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በአካባቢው ተሰማርተው እርምጃ መውሰዳቸውን የገለፁት የኖኖ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ወንዳፍራሽ ሉሌሳ "የተገደሉት 22 ናቸው የሚባለው ውሸት ነው።12 ናቸው የተገደሉት። ከ22 በላይ የተገደሉት ከታጣቂዎቹ ወገን ነው" ብለዋል።
ጥቃቱ የተፈጸመበት መንደር ነዋሪዎች ጥቃት "ከጉራጌ ዞን ተሻግረው የመጡ በፋኖ ታጣቂዎች" ቅዳሜ ምሽት ላይ "አሰቃቂ ጥቃት" ፈጽመዋል ሲሉ ከስሰዋል።ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ነዋሪ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ እንደገለጹት፤ ታጣቂዎቹ "ከጉራጌ ዞን በመነሳት በፈጸሙት ጥቃት ሕጻናትን ጨምሮ ንጹኃን ዜጎች ላይ" ጥቃት ፈጽመዋል።
ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈጸምበት በነበረው ኖኖ ወረዳ አሁን በተፈጸመው ጥቃት "ቤታቸው ውስጥ እና ከቤት ውጪም የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 22 ደርሷል" በማለት ነዋሪው ገልጸዋል።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 198😭 55👏 16💔 16😁 14👍 6🔥 3
Photo unavailableShow in Telegram
ለተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስከሬን የዱዓና ሰላት ሥነ ሥርዓት እየተከናወነ ነው‼️
ለተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስከሬን ለ40 ዓመታት ባስተማሩበት ኑር መስጅድ የዱዓ (ፀሎት) እና ሰላት ሥነ ሥርዓት እየተከናወነ ነው፡፡
በመር ሐግብሩ ኡለማዎች፣ ደረሳዎች፣ ኡስታዞች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል፡፡
በኑር መስጅድ የዱዓና ሰላት ሥነ ሥርዓት ከተካሄደ በኋላ በሚሊኒዬም አዳራሽ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት ሽኝት ይደረጋል፡፡
ከቀኑ 10 ሰዓት ላይም ሥርዓተ ቀብራቸው የሚፈጸም መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 196💔 62👍 28😭 21🔥 9😁 7😡 2
إظهار الكل...
😭 705💔 164❤ 117😁 20😱 18👍 6🎉 6
የአዲስ አበባ ከተማ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነው ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ መካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩ በሩብ ዓመቱ የታቀዱ እና የ90 ቀን አበይት ተግባራት የደረሱበት ደረጃ እንደሚገመገም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡
በመዲናዋ የተለየ ትኩረት የሚሹ ተግባራት ተለይተው ቀጣይ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡም ነው የገለጹት፡፡
በተጨማሪም የተገኙ ውጤታማ አፈጻጸሞች ተጠናክረው የሚቀጥሉበትና የታዩ ጉድለቶች የሚታረሙበት የግምገማ መድረክ እንደሚሆን ከንቲባዋ አመልክተዋል፡፡
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 170😁 16👍 15👏 7😡 5
መንግሥት የካንሰር መድኃኒቶችን 63 በመቶ ወጪ እንደሚሸፍን አስታወቀ‼️
መንግሥት የካንሰር መድኃኒቶች (ኬሞ ቴራፒ) አቅርቦት ላይ ያለውን ችግር ለማቃለል እና ተደራሽነቱን ለማሳደግ፣ ከጠቅላላው ወጪው 63 በመቶ ያህሉን እየሸፈነ እንደሚገኝ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።ይህ የድጎማ ሥርዓት ውድ የሆኑ የካንሰር መድኃኒቶች እጥረት እንዳይኖር ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።
በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈፃሚ ህይወት ሰለሞን (ዶ/ር) ለአሐዱ እንደገለጹት፤ የኬሞቴራፒ መድኃኒት እጅግ ውድ ከመሆኑ ባሻገር የሚከሰት እጥረትን ለመከላከል መንግሥት ከፍተኛውን ወጪ በመሸፈን አገልግሎቱ በድጎማ እንዲቀርብ የማድረግ ሥራ እየሰራ ይገኛል።
መሪ ሥራ አስፈጻሚዋ አክለውም፤ የካንሰር ሕክምና ሰጪ ማዕከላትን በማስፋት፣ ታካሚዎች በወረፋና መሰል ችግሮች እንዳይጋለጡ ሰፊ ሥራዎች እየተሰሩ ስለመሆኑ ተናግረዋል።አንድ ብቻ የነበረውን የጨረር ሕክምና ማዕከላት ቁጥር ወደ 5 ከፍ መደረጉንም ገልጸዋል። እንዲሁም ሁለት ተጨማሪ የካንሰር ጨረር ሕክምና ማዕከላት በሂደት ላይ ሲሆኑ፤ አገልግሎቱን የሚሰጡ ባለሙያዎችን የአቅም ማጎልበት ሥራዎች መሰራታቸውን አስረድተዋል።
ዶክተር ህይወት የካንሰር መድኃኒት አቅርቦትን ከፍ ለማድረግ እና በድጎማ የሚቀርብበትን ሁኔታ በማጠናከር እንደሚሰሩ ተናግረዋል። በተጨማሪም ሁሉም ዜጋ ለከፋ ችግር ሳይጋለጥ የቅድመ ምርመራ እንዲያደርግ እና ተገቢውን የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኝ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ላይ በትኩረት መሰራት እንደሚገባም አመልክተዋል።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 241👍 48😁 13👌 6😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
የትግራይ ኃይል አባላት ሰልፈኞች ለአራተኛ ቀን ዛሬ የመኪና መንገድ ዘግተዋል‼️
ዛሬ ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም የትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዋና ከተማ ወደ ሆነችው የዓዲግራት ከተማ የሚያስገቡና የሚያስወጡ ሶስት ዋና መንገዶች ተዘግተዋል።
ትናንት ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ከዓድዋ ወደ ዓዲግራት መንገድ ተዘግቷል።
ከጥቅምት 3/2018 ዓ.ም ወዲህ ከክልሉ ምስራቃዊ ፣ ደቡባዊ ዞኖች ወደ መቐለ የሚወስዱ መንገዶች በኣጉላዕና ፣ በመኾኒ ወደ እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ የሚወስድ መንገድ በእንዳባጉና ከዓድዋ ወደ ዓዲግራት የሚወስድ በሴሮ ተዘግተው በዚያው ቀን በተለያዩ ሰዓቶች መከፈታቸው ይታወሳል።
የክልሉ ካቢኔ በመንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ በኩል ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፤ የሰራዊቱ አባላት ያነሱት የደመወዝ ጭማሪ የጥቅማ ጥቅምና የመሬት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል መመሪያ ማውጣቱን ትላንት አሳውቆ ነበር።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 171👍 45😁 19🕊 11😱 4
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርት ሱዳን የበረራ አገልግሎት ዳግም ጀመረ‼️
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርት ሱዳን የሚያደርገውን በረራ ከጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዳግም ማስጀመሩን አስታወቀ።
አየር መንገዱ ወደ ፖርት ሱዳን ከጥቅምት 5 ቀን ጀምሮ በቀን አንድ ጊዜ በረራ እንደሚያደርግ ገልጾ በቀጣይ ከጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ግን በረራዎቹን በቀን ወደ ሁለት ጊዜ እንደሚያሳድግ ጠቁሟል።
በሱዳን ጦር ሰራዊት እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ (RSF) መካከል ግጭት ከተቀሰቀሰበት ሚያዚያ 2015 ወዲህ የሱዳን መንግሥት ዋና ከተማዋን ካርቱምን በመልቀቅ አገሪቱን ሲያስተዳድር የቆየው በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል በምትገኘው ፖርት ሱዳን ከሚገኝ ጊዜያዊ መቀመጫው እንደነበር ይታወሳል።
ይህንንም ተከትሎ አየር መንገዱ ወደ ፖርት ሱዳን ተከታታይ በረራዎችን ሲያደርግ የነበረ ሲሆን ከወራት በፊት በሀገሪቱ እንደገና ባገረሸው ግጭት ሳቢያ ወደ ፖርት ሱዳን ሲያደርግ የነበረውነ በረራ ለማቋረጥ ተገዶ ቆይቷል።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 121👍 16👏 3😱 3
Photo unavailableShow in Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በራይላ ኦዲንጋ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ‼️
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀድሞው የኬኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኤክስ ገጻቸው ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ፤ በቀድሞ የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ህልፈት በኢትዮጵያ መንግስት ስም የተሰማኝን ሀዘን እገልጻለሁ ብለዋል።
የቀድሞው የኬኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ባደረባቸው የልብ ሕመም ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተዘግቧል፡፡
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 154😁 36👍 27💔 25😭 17😱 2
ከዓመታት ስቃይና ደም መፋሰስ በኋላ የጋዛ ጦርነት አብቅቷል‼️
🗣ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ
ከዓመታት ስቃይ እና ደም መፋሰስ በኋላ የጋዛ ጦርነት አብቅቷል ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ፡፡
አሜሪካ፣ ቱርኪዬ፣ ግብፅ እና ኳታር በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱ የተፈረመው በግብፅ እየተካሄደ በሚገኘው የሻርም ኤል ሼክ የሰላም ጉባኤ ላይ ነው፡፡
ስምምነቱን የሀገራቱ መሪዎች የፈረሙ ሲሆን፤ ሰነዱ ቀጣዩን የጋዛ አስተዳድር በተመለከተ፣ በቀጠናው ዘላቂ ሰላም ማስጠበቅ በሚቻልበት ሁኔታ እና በመልሶ ግንባታ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስምምነቱ በይፋ ከተፈረመ በኋላ ባደረጉት ንግግር፤ ከዓመታት ስቃይ እና ደም መፋሰስ በኋላ የጋዛ ጦርነት አብቅቷል ብለዋል፡፡
ይህ ለውጥ እንዲመጣ ላደረጉ የአረብ እና የሙስሊም አገራትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
አሁን በጋዛ የመልሶ ግንባታ ስራ ተጀምሯል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህ ቀን እንዲመጣ በቀጠናው እና በአለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ሲጥሩ፣ ሲመኙ እና ሲጸልዩ ነበር ብለዋል፡፡
ዛሬ የተፈረመው የጋዛ የተኩስ አቅም ስምምነት ሰነድ ታሪካዊ ነው ሲሉም መግለፃቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
በሰላም ውይይቱ ላይ 20 የሚሆኑ የሀገራት ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን፤ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ የቱርኪዬ፣ የፍልስጤም፣ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን፣ ኳታርና የሌሎች ሀገራት መሪዎች እንዲሁም የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ተሳታፊ ሆነዋል።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 233👏 27👍 12😁 11🕊 7😭 4🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
መኪናዎን #በአስቸኳይ መሸጥ ከፈለጉ ከታች የተዘረዘሩትን መረጃዎች 👇👇ሞልተው
☎️🦈🏌🏽♀ 0911407105 🔫 ላይ ደውለዉ ያሳውቁን። ስለመረጡን እናመሰግናለን👏
➕የመኪናው ዓይነት___
🔤የመኪናው ሞዴል___
➕ትራንስሚሽን___
🔤የዞረ/ያልዞረ___
🧮የተነዳው ኪ.ሜ___
🧮ስለመኪናው አቋም አጭር ማብራሪያ___
🔤በተለያየ አቅጣጫ የተነሳ ፎቶ___
🔤የመሸጫ ዋጋ___
🔤የባለቤት ስልክ___
🎱 0911407105 🔫 ይደውሉልን
➧ቻናላችንን በመቀላቀል የተለያዩ አዳድስና ያገለገሉ መኪኖችን ማግኘት 🫴 Link ይችላሉ !!!
https://t.me/Poppycarmarket
❤ 20🔥 1👏 1😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን እየተከበረ ነው‼️
18ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ ሁነቶች መከበር ጀምሯል።በዓሉ “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተከበረ የሚገኘው።
የሠንደቅ ዓላማ ቀን አሁን ላይ በኢፌዲሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሪነት በተለያዩ አካባቢዎች በተለያዩ ሥነ ሥርዓቶች መከበር ጀምሯል፡፡
4፡30 ሰዓት ላይም በፌደራል የመንግስት ተቋማት፣ በክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች፣ በመከላከያ ሰራዊት ካምፖች እንዲሁም በኤምባሲዎችና የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ሠንደቅ ዓላማ የመስቀል ሥነ ሥርዓት ይከናወናል።በተጨማሪም በሠንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ መሐላ የመፈጸም መርሐ ግብር እንዲሁም ሌሎች ዝግጅቶች የሚከናወኑ ይሆናል፡፡
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 143👍 47😁 21👏 12🕊 4😱 2🎉 1
Photo unavailableShow in Telegram
🔥በመሀል ፒያሳ ከአራዳ ፓርክ ትይዩ ከወዳጅነት ፓርክ እንዲሁም አብርሆት ቤተ መፅሀፍት በቅርብ ርቀት ላይ
🌟ለ15 ቤቶች ብቻ በማስታወቅያ ዋጋ ቅንጡ አፓርትመንቶች ቀረበልዎት
🏡ከባለ አንድ እስከ ባለ ሶስት መኝታ በ 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ
ቀሪውን ዘና ብለው የሚከፍሉት
💎 ባለ 1 መኝታ በ 441,000 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 855,000 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 1,170,000 ሺ ብር ቅድመ ክፍያ
ለ 15 ቤቶች ብቻ❗️
- ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 30% የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው
ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelMERITRealtor)
#whatsapp
