ar
Feedback
ETHIO-MEREJA®

ETHIO-MEREJA®

الذهاب إلى القناة على Telegram

News & Media Company® USA : Washington Addisababa, Ethiopia🇪🇹 . Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja . ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!! 👉 @ethio_merejabot

إظهار المزيد
2025 عام في الأرقامsnowflakes fon
card fon
110 313
المشتركون
-4924 ساعات
-2787 أيام
-1 26930 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
#ሰበር: እስራኤል ለሶማሊላንድ የአገርነት እውቅና በይፋ መስጠቷን አስታወቀች የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አገራቸው የሶማሊላንድ ሪፐብሊክን እንደ ነጻ እና ሉዓላዊት ሀገር በይፋ መቀበሉን አስታወቁ። ይህም በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ለውጥ መሆኑ ተገልጿል። ኔታንያሁ ባወጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ዕውቅናው የተረጋገጠው ከእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር እና ከሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን መሐመድ አብዱላሂ ጋር በጋራ በተፈረመ "የሁለትዮሽ ስምምነት" አማካኝነት ነው። ጠ/ሚሩ በመግለጫቸው ቀደም ሲል በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አነሳሽነት የተፈረመውን "የአብርሃም ስምምነት" መንፈስን የተከተለ መሆኑን ገልፀዋል። ነታንያሁ ፕሬዝዳንት አብዲራህማንን "ታሪካዊ መግለጫ" ባሉት በዚህ ስምምነት ላይ እንኳን ደስ ያለዎት ያሏቸው ሲሆን፤ ለሰላም እና ለመረጋጋት ላሳዩት ቁርጠኝነትና አመራር ምስጋና አቅርበውላቸዋል። በተጨማሪም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት በእስራኤል ይፋዊ ጉብኝት እንዲያደርጉ ግብዣ አቅርበውላቸዋል። እንደ ኔታንያሁ ገለጻ፣ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን በወሰዱት እርምጃ ደስታቸውን ገልጸው፤ እስራኤል ሽብርተኝነትን በመዋጋትና ቀጣናዊ ሰላምን በማስፈን ረገድ ለምትጫወተው ሚና ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ ሂደት መሳካት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ሳር፣ የሞሳድ ዳይሬክተር ዴቪድ ባርኒያ እና የእስራኤል የደህንነት ተቋማት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና ሰጥተዋል። ነታንያሁ እንደገለጹት፤ እስራኤል በግብርና፣ በጤና፣ በቴክኖሎጂ እና በኢኮኖሚ ዘርፎች በሚደረጉ ሰፊ ትብብሮች አማካኝነት ከሶማሊላንድ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማስፋፋት አቅዳለች።
إظهار الكل...
53👍 18😁 5😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
ቲክቶከሮች ግብር ሊከፍሉ ነው 📌በኦንላይን ይዘት ገቢ ላይ ግብር ሊጣል ነው የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ቲክቶክና ዩቲዩብን ጨምሮ ከሌሎች የዲጂታል ገጾች ገቢ የሚያገኙ አካላት ግብር እንዲከፍሉ የሚያስገድድ አሰራር እየዘረጋ መሆኑን አስታውቋል። ባለፈው ዓመት በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ መሰረት፥ በኦንላይን ይዘቶች ገቢ የሚያገኙ አካላት በሙሉ በገቢዎች ቢሮ ተመዝግበው የግብር መለያ ቁጥር የማውጣት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። ቢሮው ይህን ሥራ ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከንግድ ቢሮ እና ከፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ነው የገለጸው። የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ገቢያቸውን በፈቃደኝነት እንዲያሳውቁ ጥሪ ቀርቦላቸዋል መባሉን ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል። ቁጥጥሩ ከይዘት ፈጣሪዎች ባለፈም ምርትና አገልግሎት የሚያስተዋውቁ ነጋዴዎችንም ይመለከታል ነው የተባለው።
إظهار الكل...
😁 40 15
የአዲስ አበባ ፖሊስ "በትውልዱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር ነበረ "ያለውን ቲክቶከር ናትናኤል ባደግን አስሮ ምርመራ እያከናወነ መሆኑን ገለፀ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ ነበረ በማለት ናትናኤል ባደግ (ሞን) የተባለ ቲክቶከር ዛሬ ማሰሩን ገልፇል። ተጠርጣሪው በተለምዶአዊው ንግግር ሊገለፁ የማይችሉ አስፀያፊ ቃላትን በመጠቀም በትውልዱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር እንደነበር እና መሰል ይዘቶችን በተደጋጋሚ ጊዜ በመስራት በማህበራዊ ሚዲያ (YouTube እና tiktok platform) በመጠቀም ሲያሰራጭ እንደነበር ፖሊስ አብራርቷል፡፡ ፖሊስ በቁጥጥር ስር በዋለው ናትናኤል ባደግ ወይም "የማህበራዊ ሚዲያ አንቂ ወይም ይዘት ፈጣሪ ነኝ" በሚለው ግለሰብ ላይ ምርመራ መጀመሩንም ገልፇል።
إظهار الكل...
56😁 36👍 20👏 12
አሌክሳንደር ኢሳክ ለወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ተረጋገጠ የሊቨርፑል የፊት መስመር ተጫዋች አሌክሳንደር ኢሳክ ለወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ተረጋግጧል፡፡ አልክሳንደር ኢሳክ በ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሊቨርፑል ቶተንሃም ሆትስፐርን ባሸነፈበት ጨዋታ ጉዳት አጋጥሞት ተቀይሮ ከሜዳ መውጣቱ ይታወቃል፡፡ ተጫዋቹ ያጋጠመውን ጉዳት ተከትሎ በትናንትናው ዕለት ቀዶ ህክምና አድርጓል፡፡ በዚህም ስዊድናዊው የፊት መስመር ተጫዋች አሌክሳንደር ኢሳክ ቢያንስ ለሁለት ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ማረጋገጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ የ26 ዓመቱ የፊት መስመር ተጫዋች ለሊቨርፑል በሁሉም ውድድር ባደረጋቸው 16 ጨዋታዎች ሦስት ግቦች አስቆጥሮ አንድ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል፡፡ አሌክሳንደር ኢሳክ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ከኒውካስል ዩናይትድ በ125 ሚሊየን ፓውንድ ሊቨርፑልን መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡
إظهار الكل...
44😢 6😁 4🤯 3👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ጥንቃቄ!! ከአጭበርባሪዎች ተጠበቁ!!! 📌ማንኛውንም በስልክ የሚመጣ ጥያቄ ባለመቀበል እራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች ጠብቁ!!! ''ባንካችን ብሔራዊ ባንክ ያወጣውን መመሪያ መሰረት በማድረግ ደንበኞቻችን በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ የባንክ ሒሳብ ቁጥራቸውን ከፋይዳ መታወቂያቸው ጋር እንዲያጣምሩ ያስተላለፈውን መልእክት እንደ አጋጣሚ በመጠቀም አጭበርባሪዎች ደንበኞቻችን ጋር እየደወሉ አገልግሎቱ በስልክ እንደሚሰጥ እንዲሁም የባንክ ሂሳብ በዚህ ምክንያት እንደሚዘጋ በማስመሰል ለማጭበርበር እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ ደርሰንበታል። በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን ሒሳብን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር የማጣመሩ ሥራም ሆነ ሌሎች ከሞባይል ባንኪንግ ጋር የተያያዙ እና ማናቸውም አገልግሎቶች እርስዎ በአካል ወደ ቅርንጫፍ ካልሄዱ/ካልቀረቡ በስተቀር በስልክ ተደውሎ የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ በስልክ ለሚመጡ ጥያቄዎች ምላሽ ባለመስጠት እራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች እንድትጠብቁ በአክብሮት እናሳውቃለን!'' የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
إظهار الكل...
72👍 28👏 2😁 2🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
"የአእላፋት ዝማሬ" በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለሦስተኛ ጊዜ ይካሄዳል የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ (ኢጃት) ከታኅሣሥ 16 እስከ ታኅሣሥ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በግዮን ሆቴል ግራውንድስ ላይ የሚቆይ "የአእላፋት ሳምንት" የተሰኘ ዘርፈ ብዙ ዐውደ ርዕይና የጃን ፎረም መድረክ ማዘጋጀቱን አስታወቀ። ማኅበሩ በዛሬው እለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተገለጸው የመርሐግብሩ ዋና ዓላማ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሊቃውንት፣ ደራሲያንና ታሪካዊ ሰዎችን መዘከር፣ የምሁራን ጥናታዊ ጽሑፎችን ማቅረብ፣ የአብነት ትምህርት ቤቶችንና ገዳማትን ማስተዋወቅ እንዲሁም የኦርቶዶክሳውያን የንግድ ትስስር መድረክ መፍጠር መሆኑ ተገልጿል። በዐውደ ርዕዩ ላይ የኢትዮጵያዊው ነባቤ መለኮት የቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ 600ኛ ዓመት መታሰቢያ ከደብረ ባሕርይ ገዳም ጋር በመተባበር የሚከበር ሲሆን የዘንድሮው የገና መባዕም ለዚሁ ገዳም እንዲውል ተወስኗል። በመድረኩ ላይ መምህር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ፣ ረዳት ፕሮፌሰር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል፣ ዲያቆን ምሕረት መላኩ፣ ጆናታን ፒያዦ እና ሌሎች ታዋቂ ምሁራን በነገረ መለኮት፣ በዕቅበተ እምነትና በሥነ-ልቦና ዙሪያ ጥናታዊ ጽሑፎችን ይቀርባሉ። የአእላፋት ዝማሬ አስመልክቶ ማህበሩ በሰጠው መግለጫ መሠረት በበዓለ ልደት ዋዜማ ታኅሣሥ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለሦስተኛ ጊዜ እንዲሁም በድሬደዋ ከተማ ለገሀር አደባባይ ለሁለተኛ ጊዜ በድምቀት እንደሚካሄድ ገልጿል። ዘንድሮ ከአዲስ አበባ እና ከድሬዳዋ ከተማ ባሻገር ለመጀመሪያ ጊዜ በአሰላ፣ በአሶሳ፣ በሆለታ፣ በአምቦ፣ በደሴ፣ እንዲሁም በሲያትልና በኡጋንዳ የአእላፋት ዝማሬ እንዲካሄድ የልምድ ልውውጥና ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።   T.me/ethio_mereja         ኢትዮ-መረጃ
إظهار الكل...
144👍 23👎 15🙏 7😁 3🤯 2🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
ETHIO SPARK COMPUTER & ACCESSORIES ETHIO SPARK   ፈጣን እና ዘመናዊ  የሆኑ የዓለምችንን ምርጥ 🖥  አዳዲስ  ላፕቶፖች 🖥  ጌሚንግ  ላፕቶፖች 🖥  ቢዝነስ  ላፕቶፖች 🖥  ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች እና 🖥  የተለየዩ የላፕቶፕ  አክሰሰሪዎችን ከ አንድ አመት ዋስትና ጋር እንዲሁም  ከልዩ  መስተንግዶ ጋር    እንጠብቆታለን።  ይደውሉ 👇 ☎️+251974967884 የፁሁፍ መልዕክት 👇👇 💌    @Dm4ethio 📍 Location: 📌 Addis Ababa, Megenagn Telegram link: https://t.me/EthioSpark16 You tube link:https://www.youtube.com/@EthioSpark0 Instagram link: https://www.instagram.com/ethiopark16/ Facebook :https://www.facebook.com/share/177eogKin1/ Tiktok link: tiktok.com/@ethiospark 🌐 Website:www.ethiospark16.com
إظهار الكل...
8
Photo unavailableShow in Telegram
ታዋቂው የቪዲዮ ማጋሪያ መተግበሪያ ቲክቶክ፣ በአሜሪካ ከተደቀነበት የእገዳ አደጋ ለመዳን ሲባል የአሜሪካውን የቢዝነስ ዘርፉን ለሶስት ግዙፍ የአሜሪካ ኢንቨስተሮች ለመሸጥ ከስምምነት ላይ ደረሰ። ገዢዎቹ ኦራክል፣ ሲልቨር ሌክ እና ኤምጂኤክስ የተባሉ ኩባንያዎች ናቸው። ይህ ስምምነት ተወዳጁ መተግበሪያ በአሜሪካ ምድር ያለ ምንም ገደብ አገልግሎቱን እንዲቀጥል የሚያስችለው እንደሆነ ተገልጿል። አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው፣ ሽያጩ በመጪው ጃንዋሪ 22 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። በስምምነቱ መሠረት የሚቋቋመው አዲሱ የ"ቲክቶክ ዩ.ኤስ." የሽርክና ኩባንያ የባለቤትነት ድርሻ እንደሚከተለው ተዋቅሯል። አዲሱ የባለሀብቶች ስብስብ በአጠቃላይ 50 በመቶውን ድርሻ ይይዛሉ። ከዚህ ውስጥ ኦራክል፣ ሲልቨር ሌክ እና ኤምጂኤክስ እያንዳንዳቸው 15 በመቶ ድርሻ ይኖራቸዋል። የቲክቶክ እናት ኩባንያ የሆነው የባይትዳንስ ነባር ባለሀብቶች ተባባሪዎች 30.1 በመቶ ይይዛሉ። የቻይናው ኩባንያ ባይትዳንስ በበኩሉ 19.9 በመቶ ድርሻ ብቻ ይዞ ይቆያል። ይህ ስምምነት የተደረገው የአሜሪካ መንግስት "ቲክቶክ ከቻይናው ኩባንያ ቁጥጥር ካልወጣ በብሔራዊ ደህንነት ስጋት ምክንያት ይታገዳለ" የሚል ህግ ካወጣ በኋላ ነው። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የፈረሙት ይህ ህግ [PAFACA Act]፣ መተግበሪያው የአሜሪካውያንን መረጃ ለቻይና መንግስት አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል በሚል ስጋት ላይ የተመሰረተ ነበር። በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው ቲክቶክን ለማገድ ሞክረው የነበሩት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በ2024 ምርጫ አሸናፊ ሆነው ከተመለሱ በኋላ አቋማቸውን በማለዘብ ለእገዳው የተቀመጠውን የጊዜ ገደብ አራዝመውት ነበር።
إظهار الكل...
36🥰 2
ከመቅደላ የተዘረፈ የወርቅ የፀጉር ማስያዣ ሊመለስ ነው በ19ኛው ክፍለ ዘመን ከመቅደላ የተዘረፈየወርቅ የፀጉር ማስያዣ በጥር ወር መጀመሪያ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለስ ተገለፀ። ይህ ቅርስ የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ሁለተኛ ባለቤት የነበሩት የእቴጌጥሩወርቅ ውቤ ሲሆን፥ አሁንም በቀድሞው ጌጣጌጥ ማቅረቢያ ሣጥኑ ውስጥ ተጠብቆ ይገኛል። ጥንታዊ ቅርሱ ከ150 ዓመታት በላይ በግል ንብረት ስብስቦች ውስጥተይዞ ቆይቷል። የፀጉር ማስያዣው በቅርቡ ከተመለሰው የ1868ቱ የመቅደላ ጦርነት ጋሻ ጋር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ለዕይታ እንደሚቀርብ ስፑትኒክ ዘግቧል።
إظهار الكل...
57👍 12
ከ60 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ወርቅ ይዘው በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ!! የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከ60 ሚሊየን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለው ወርቅ እና ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ይዘው በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን ከእነኤግዚቢቱ በአሶሳ ከተማ አምባ አንድ በሚባል ቦታ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል፡፡ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረው ወርቅና ጥሬ ገንዘብ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ የኮንትሮባንድ ቁጥጥር ፖሊስ መምሪያ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ባደረገው ክትትል መሆኑን በመምሪያው ሬጅመንት አንድ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ዳኘ አለማየሁ ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እያጣራባቸው መሆኑን ዋና ኢንስፔክተሩ ገልጸው፤ የተያዘው ወርቅና ጥሬ ገንዘብም ለአሶሳ ከተማ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ገቢ መደረጉን ተናግረዋል። ፖሊስ ኮንትሮባንድና ሕገ-ወጥ ንግድ በሀገር ኢኮኖሚ እና በሕጋዊ ነጋዴዎች ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት በመገንዘብ ከሕዝብና ከመንግሰት የተጣለበትን አደራ ለመወጣት ሕዝብን ባሳተፈ መልኩ ስኬታማ የመከላከል ሥራ እያከናወነ መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር ዳኜ አለማየሁ ጠቁመዋል።
إظهار الكل...
43👍 11👎 1🥰 1
ዲሞክራሲ ተምሳሌቷ የብራዚል ሐዉልት ወደቀች ! የነፃነት የዲሞክራሲ የእኩልነት ማሳያ እንደሆነች የሚነገርላትና ዋናዋ በፓሪስ የምትገኘዉ መሰሎቿ በተለያዩ ሀገራት የቆሙላትና በብራዚልም የምትገኘዉ የሊበርቲ ሐውልት በዚህ ዲሞክራሲ ተረስቶ ዲሞግራፊ ባዩበት ከመቼውም ጊዜ በላይ መርሆች በተጣሱበት ከቃል በላይ በተግባር በማይታይበት ዘመን መቆም አልፈልግም በማለት መዉደቋ ተሰማ ። በደቡባዊ ብራዚል ታህሳስ 15 ቀን በተነሳ በኃይለኛ ነፋስ በ24 ሜትር ቁመት ላይ ያላት ግዙፍ የሊበርቲ ሐውልት ቅጂ መዉደቁን ተከትሎም ሰኞ እና ማክሰኞ በብዛት በጎግል ፍለጋ ከተደረገባቸው ጉዳዮች ተቀዳሚ ሁኗል። በእለቱ በቀኑ መጀመሪያ ላይ የአካባቢው ባለስልጣናት ነዋሪዎቹን ስለ ከባድ ንፋስ አደጋ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ህዝቡ በቤት ውስጥ እንዲቆይ፣ ቤቶቻቸውን እንዲጠብቅ እና የኤሌክትሪክ መሳሪያዎችን እንዲያላቅቅ የሲቪል መከላከያ ቡድኑ አሳስቧል። እነዚህ መመሪያዎች ቢተላለፉም፣ ኃይለኛው ነፋስ ታዋቂውን ቅጂ ከስሩ ገንድሶ መጣል ችሏል። የሐውልቱ ባለቤት የሆነው የሃቫን የችርቻሮ ሰንሰለት ክስተቱን አረጋግጦ ከባለስልጣናት ጋር በመተባበር የውድቀቱን ሁኔታ ለመመርመር ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል። የሲቪል መከላከያ ተወካዮች የውድቀቱን ምክንያቶች ለመረዳት እና ለወደፊቱ ተመሳሳይ ክስተቶችን ለማስወገድ ምክሮችን ለመስጠት የቴክኒክ ግምገማ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።
إظهار الكل...
25😁 22😢 2🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ በወርልድ ቴኳንዶ ወንዶች የወርቅ ሜዳልያ አገኘች ‎አብረሃም አዱኛ በወርልድ ቴኳንዶ ወንዶች 51 ኪሎ ግራም ውድድር ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ አስገኝቷል፡፡ በአንጎላ ሉዋንዳ እየተደረገ በሚገኘው 4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታ አብረሃም አዱኛ ግብፃዊውን ማዚን አህመድን 2-0 በማሸነፍ ነው የወርቅ ሜዳልያ ያሸነፈው። በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት በተደረጉ ውድድሮች በሴቶች ሦስት የነሐስ ሜዳልያዎች የተገኙ ሲሆን፥ በ68 ኪሎ ግራም ወንዶች አብረሃም በቀለ ለሀገሩ ተጨማሪ የነሐስ ሜዳልያ አስገኝቷል፡፡ ነገም ውድድሮች ቀጥለው ሲደረጉ በወርልድ ቴኳንዶ በወንዶችም በሴቶችም ኢትዮጵያ በ6 ውድድሮች ትካፈላለች።
إظهار الكل...
43👏 16
Photo unavailableShow in Telegram
ህወሓት የነዳጅ እጥረትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መገታትን በመጥቀስ፣ በትግራይ ክልል አዲስ ከበባ መጣሉን ገለፀ ህወሓት “የፌዴራል መንግሥት ላለፉት አሥር ወራት በትግራይ የነዳጅ አቅርቦት መገደቡ፣ በትራንስፖርት፣ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እና መሠረታዊ ማኅበራዊ አገልግሎቶች ላይ መስተጓጎል ፈጥሯል” ሲል ገለፀ፤ ይህም የፕሪቶሪያው ስምምነት አተገባበር ላይ ሥጋት መፍጠሩን ጠቅሷል። ህወሓት ትናንት ታኅሣሥ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ የፌዴራል መንግሥት ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የሚያስተላልፈውን የበጀት ድጋፍ ማገዱን ገልጿል። ይህም የጤና፣ የትምህርት፣ የውኃ እና የጽዳት አገልግሎቶችን ጨምሮ የመንግሥት የሥራ እንቅስቃሴዎች እንዲስተጓጎሉ ከማድረጉም በላይ፣ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ሳይከፈላቸው እንዲቀሩ ማድረጉን አስታውቋል። መግለጫው አክሎም በትግራይ መልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (ኤፈርት) ሥር ያሉ ኩባንያዎች የባንክ ሂሳብ መታገዱን ኮንኗል። ይህም የድርጅቶቹ የሥራ እንቅስቃሴ እንዲቆም እና በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች ያለ ደመወዝ እንዲቀሩ ማድረጉን ገልጿል። “የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ትግራይ የሚገባውን የነዳጅ አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ ከገደበው አሥር ወራት ሊሞላው ተቃርቧል” ያለው ህወሓት “ይህም የሕዝብና የጭነት ትራንስፖርትን፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም ለሴቶችና ለሕፃናት የሚሰጡ የድንገተኛ አምቡላንስ አገልግሎቶችን ጨምሮ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ሽባ አድርጓል” ሲል ገልጿል።
إظهار الكل...
26👍 1😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
ETHIO SPARK COMPUTER & ACCESSORIES ETHIO SPARK   ፈጣን እና ዘመናዊ  የሆኑ የዓለምችንን ምርጥ 🖥  አዳዲስ  ላፕቶፖች 🖥  ጌሚንግ  ላፕቶፖች 🖥  ቢዝነስ  ላፕቶፖች 🖥  ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች እና 🖥  የተለየዩ የላፕቶፕ  አክሰሰሪዎችን ከ አንድ አመት ዋስትና ጋር እንዲሁም  ከልዩ  መስተንግዶ ጋር    እንጠብቆታለን።  ይደውሉ 👇 ☎️+251974967884 የፁሁፍ መልዕክት 👇👇 💌    @Dm4ethio 📍 Location: 📌 Addis Ababa, Megenagn Telegram link: https://t.me/EthioSpark16 You tube link:https://www.youtube.com/@EthioSpark0 Instagram link: https://www.instagram.com/ethiopark16/ Facebook :https://www.facebook.com/share/177eogKin1/ Tiktok link: tiktok.com/@ethiospark 🌐 Website:www.ethiospark16.com
إظهار الكل...
10
Photo unavailableShow in Telegram
🌟 የጀርመን ቋንቋ ትምህርት 🎓 የ Goethe ፈተና ዝግጅት ተካትቷል። 🌟 German Language Course Learn German quickly and confidently! 🗣️ Improve speaking & listening ✍️ Enhance reading & writing 🌍 Connect globally 🎓 Goethe Exam preparation included 💡 Fun, interactive, and practical lessons ☎️ 0989747878 0799331774 ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ : @merahyan
إظهار الكل...
13👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በገንዘብ ዘርፍ እየታየ ያለውን ዓለም አቀፍ ለውጥ ተከትሎ "የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ገንዘቦችን" በተመለከተ ጥናት በማድረግ ላይ መሆኑን አስታወቀ። የብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ዲጂታል ግብይቶች በእጅጉ እያደጉ ቢሄዱም፣ ጥሬ ገንዘብ አጠቃቀም ሙሉ በሙሉ አይጠፋም የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። "ምናልባትም ዲጂታል ግብይቶች በጥልቀት የሚሰፉበት እና በከፍተኛ ደረጃ የሚያድጉበት፣ ነገር ግን ለጥሬ ገንዘብ ግብይቶችም ምቹ ሁኔታ የሚኖርበት ባለ ሁለት ገፅታ መዋቅር ሊኖር ይችላል ብለን እንጠብቃለን" ያሉት ገዢዉ፣ "በእኛ ሀገር ከፍተኛ መጠን ያለው መደበኛ ያልሆነ ኢኮኖሚ፣ የገጠሩ ዘርፍ እና ሌሎችም አሉን። ስለዚህ የገንዘብ ግብይቶች ይቀጥላሉ ብዬ እጠብቃለሁ" ብለዋል። እዮብ ተካልኝ ፤ በተለይም ወደ አዲሱ የፋይናንስ ዓለም በሚደረገው ሽግግር፣ ማዕከላዊ ባንኮች በዲጂታል ዘመን ለገጠማቸው ከባድ ፈተናዎች እውቅና ሰጥተዋል። "ማዕከላዊ ባንኮች አሁን የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ገንዘቦች ምን እንደሆኑ መረዳት አለባቸው.. ያ ገንዘብ የተለየ መልክ ሊይዝ ይችላል፣ ግን አሁንም ያ ገንዘብ ይኖራል" ብለዋል። በጉዳዩ ላይ ብሔራዊ ባንክ ጥናት እያካሄደ መሆኑን አረጋግጠው።   T.me/ethio_mereja       ኢትዮ-መረጃ
إظهار الكل...
58👏 2🤯 1
Photo unavailableShow in Telegram
ከዛሬ ጀምሮ የሁሉም የስፖርት ውርርድ ድርጅቶች ፈቃድ ተሰረዘ በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ፈቃድ ተሰጥቷቸው ሲሰሩ የቆዩ የሁሉም የስፖርት ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ መሰረዙን አገልግሎቱ አስታወቀ፡፡ ውሳኔው በሥራ ላይ ባሉትና ቀደም ሲል በይፋ በታገዱት በሁሉም የውርርድ ድርጅቶች በእኩልነት ተፈጻሚ የሚሆን ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሂደት ላይ ያለው ምርመራ በዘርፉ ውስጥ የተንሰራፋ ሕገ ወጥ አሰራር፣ የፈቃድ ውል ጥሰት እና ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት የሚሆኑ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውሮች እንዳሉ በግልጽ አመላክቷል። አገልግሎቱ ለሚመለከታቸው አካላት መመሪያ አስተለልፏል፡፡ በዚህም መሰረት፡- 1. ለስፖርት ውርርድ ድርጅቶች እና ሲስተም ኦፕሬተሮች/አቅራቢዎች ከታሕሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአካል፣ በዲጂታል ወይም በሌላ መንገድ የሚካሄድ ማንኛውንም የውርርድ ሥራ ወዲያውኑ ማቋረጥ ይጠበቅባቸዋል። ሁሉም የገንዘብ ማስገቢያ መንገዶች አገልግሎት መስጠት ማቆም አለባቸው። አዲስ ውርርድ መቀበል ፈጽሞ አይቻልም። ሁሉም የሰርቨር መረጃዎችን፣ የፋይናንስ መዝገቦችንና የተጠቃሚ መረጃዎችን በጥብቅ ጠብቀው የማቆየት ግዴታ አለባቸው። ማስረጃን ማጥፋት፣ መቀየር ወይም ማሸሽ በወንጀል ሕጉ መሰረት ያስቀጣል። 2. ለፋይናንስ ተቋማት (ባንኮች፣ ፔይመንት ኢንስቱርመንት ኢሹወርስ እና ፔይመንት ሲስተም ኦፕሬተሮች) ከታሕሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ፣ የሁሉም የውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ በመሰረዙ፣ በተቋማቱ በኩል የውርርድ ድርጅቶቹ የሽያጭ እንቅስቃሴ እንዳያከናውኑ እንዲያደርጉ ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷል። የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ይህን ውሳኔ ከሁሉም የመንግሥት ተቋማት ጋር በመተባበር በጥብቅ የሚከታተል መሆኑን አስታውቋል።   T.me/ethio_mereja       ኢትዮ-መረጃ
إظهار الكل...
50😁 11😭 3👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ETHIO SPARK COMPUTER & ACCESSORIES ETHIO SPARK   ፈጣን እና ዘመናዊ  የሆኑ የዓለምችንን ምርጥ 🖥  አዳዲስ  ላፕቶፖች 🖥  ጌሚንግ  ላፕቶፖች 🖥  ቢዝነስ  ላፕቶፖች 🖥  ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች እና 🖥  የተለየዩ የላፕቶፕ  አክሰሰሪዎችን ከ አንድ አመት ዋስትና ጋር እንዲሁም  ከልዩ  መስተንግዶ ጋር    እንጠብቆታለን።  ይደውሉ 👇 ☎️+251974967884 የፁሁፍ መልዕክት 👇👇 💌    @Dm4ethio 📍 Location: 📌 Addis Ababa, Megenagn Telegram link: https://t.me/EthioSpark16 You tube link:https://www.youtube.com/@EthioSpark0 Instagram link: https://www.instagram.com/ethiopark16/ Facebook :https://www.facebook.com/share/177eogKin1/ Tiktok link: tiktok.com/@ethiospark 🌐 Website:www.ethiospark16.com
إظهار الكل...
13
Photo unavailableShow in Telegram
🚀 30% ቅናሽ በሁሉም ስልጠናዎቻችን! Day / Night / Online ከAdvanced Level እና 90% Practical ተሞክሮ ጋር! 👉 ዛሬውኑ ጀምሩ ! 🎓 ጀማሪ ቢሆኑ ወይም ችሎታዎን ለመሻሻል ቢፈልጉ! 🧑‍🏫 ከብዙ የስራ ልምድ ያላቸው መምህራን ትምህርት ታገኛላችሁ የምንሰጣቸው ኮርሶች : ✅ ዲጂታል ማርኬቲንግ ✅ ዌብሳይት ይዛይን ✅ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ✅ አካውንቲንግ ✅ አርት ✅ የጋዜጠኝነት ስልጠና ✅ ግራፊክ ዲዛይን ✅ ሞሽን ግራፊክስ ✅ ቪዲዮ ኤዲቲንግ ✅ 3D ዲዛይን ✅ ፎቶግራፊ ✅ ኢምፓርት ኤክስፖርት ✅ ቋንቋ : ጀርመንኛ 🇩🇪 ፣ አረብኛ🇸🇦 ፣ ፈረንሳይኛ🇫🇷 ፣ ቻይንኛ🇨🇳 ○ 100% ተግባራዊ ስልጠና ○ ከስልጠና በኋላ Internship እድል ○ ለመማር ተስማሚ ቦታ ○ ባለሙያ እና ተሞክሮ ያላቸው መምህራን ○ ሁሉም ኮርሶች ከAdvanced ትምህርት እና ቀጣይ ድጋፍ ጋር 📍 አድራሻ: 22 ፣ ከጐላጐል ወደ ቦሌ ሚወስደው ከHanan K plana አጠገብ ቢጫ ፎቅ ግራውንድ ፍሎር 10B 📞 ስልክ: 0989747878 | 0799331774 ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ : @merahyan
إظهار الكل...
17🥰 1🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ (DBE) የአመራር ለውጥ አደረገ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ (DBE) ከፍተኛ ሹመቶች እና በአመራር ምደባ ዙሪያ የተነሳ አለመግባባትን ተከትሎ፣ የባንኩ ከፍተኛ አመራር በአዲስ መልክ ተዋቅሯል። ​ዶ/ር ኢሣያስ ካሣ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶ/ር ብሩክ ታዬ ደግሞ የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው ተሰይመዋል። ​ፎርቹን ባየው መግለጫ እና የውስጥ ደብዳቤ ላይ ዶ/ር ብሩክ የአመራር ለውጡን ያደረጉት “ተቋማዊ ውጤታማነትን ለማስመለስ እና የልማት ባንኩን ከብሔራዊ ልማት ቅድሚያዎች ጋር ለማጣጣም ያለመ ሰፊ የማሻሻያ አጀንዳ” አካል መሆኑን ገልጸዋል። ​የቀድሞ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ እና ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶ/ር እመቤት መለሰ (ዓርብ፣ ታኅሣሥ 3 ቀን 2018 ዓ.ም.) የተተኩት፣ በምክትል ፕሬዝዳንቶች ሹመት እና ለከፍተኛ ሠራተኞች የብቃት ፈተና አሰጣጥ ዙሪያ በቦርዱ እና በዋና ሥራ አስፈጻሚው መካከል የነበረው አለመግባባት ከጠነከረ በኋላ ነው። ​ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ፣ ይህ የተካረረ ልዩነት ስትራቴጂያዊ የውሳኔ አሰጣጥን እያደናቀፈ ነበር። ​ለባንኩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንዳሉት፣ አለመግባባቱን ለማርገብ የመጨረሻ ጥረት የተደረገው ከአንድ ሳምንት በፊት ሲሆን፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ እና የማዕከላዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ በአቶ ተክለወልድ እና በዶ/ር እመቤት መካከል ስብሰባ ጠርተው ነበር። ሆኖም ውይይቱ ልዩነቱን ማጥበብ እንዳልቻለ ምንጮቹ ገልጸዋል። ​ዶ/ር ኢሣያስ ካሣ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን (ECMA) ሲመሠረት በዶ/ር ብሩክ ይመራ የነበረው መስራች ሥራ አስፈፃሚ አካል ውስጥ ነበሩ።
إظهار الكل...
56👍 6😁 4🤔 1