ETHIO-MEREJA®
الذهاب إلى القناة على Telegram
News & Media Company® USA : Washington Addisababa, Ethiopia🇪🇹 . Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja . ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!! 👉 @ethio_merejabot ✔
إظهار المزيد2025 عام في الأرقام

110 293
المشتركون
-4624 ساعات
-2877 أيام
-1 28930 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
ዛሬ ታህሳሥ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ሕንፃ ቁጥር 2 ውስጥ ጥገና በሚሰራበት ቦታ ከብረት ብየዳ በተፈጠረ ፍንጣቂ አንዲት ትንሽ ክፍል ውስጥ እሳት ተከስቶ የነበረ ሲሆን ምንም አይነት ጉዳት ከማድረሱ በፊት ወድያውኑ እንዲጠፋ ተደርጓል። በክስተቱ ምክንያት በመንገደኞች መውጫ እና መግቢያ ላይ የተከሰተ ምንም አይነት መስተጓጎል አለመፈጠሩን ለማሳወቅ እንወዳለን።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤
❤ 40👏 12👍 8👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ሰበር፡ #ኤርትራ ከ #ኢጋድ አባልነቷ በድጋሚ መውጣቷን አስታወቀች፣ "የቀጠናውን ፍላጎት ማሳካት ተስኖታል" ስትል ለመውጣቷ በምክንያትነት አቅርባለች
ኤርትራ ቀጣናዊ ህብረት ከሆነው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) መውጣቷን የሀገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በይፋ አሳወቀ።
አስመራ ለኢጋድ ዋና ጸሐፊ በላከችው መልእክት፤ ለውሳኔው መነሻ የሆነው "ተቋሙ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ድክመት በማሳየቱ" እና በቀጣናው ጉዳዮች ላይ በሚጫወተው "ጎጂ ሚና" መሆኑን ገልጻለች።
ኤርትራ እ.ኤ.አ. በ1993 ኢጋድ እንደገና ሲዋቀር፣ ለቀጣናዊ ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ለኢኮኖሚ ትስስር መጠናከር እንደ ዋና መሣሪያ ሆኖ የሚያገለግል ተቋምን ለመገንባት ከሌሎች አባል ሀገራት ጋር በመስራት ወሳኝ ሚና እንደተጫወተች አስታውሳለች።
ይሁን እንጂ መግለጫው፣ በሂደት እና በተለይም ከ2005 ጀምሮ (እ.ኤ.አ)፣ ኢጋድ የቀጣናውን ህዝቦች ተስፋና ፍላጎት ከማሳካት ይልቅ፣ በተወሰኑ አባል ሀገራትና በተለይም በኤርትራ ላይ እንደ መጠቀሚያ መሣሪያ በመሆን ጎጂ ሚና ተጫውቷል ብሏል። በእነዚህም ድርጊቶች ምክንያት አስመራ በጎርጎሮሳውያኑ ሚያዚያ ወር 2007 ከአባልነቷ ለመውጣት መገደዷን መግለጫው አክሎ አብራርቷል።
ኤርትራ ኢጋድ ለሪፎርም ያቀረበችውን ጥሪ ሰምቶ ያለፈውን ታሪኩን ያስተካክላል በሚል ተስፋ፣ በጎርጎሮሳውያኑ ሰኔ 2023 አባልነቷን እንደገና አጠናክራለች። ሆኖም፣ የሀገሪቱ መንግሥት ተቋሙ ሕጋዊ ግዴታዎቹን መካድ ቀጥሏል ያለ ሲሆን፤ ይህም ጠቀሜታውንና ሕጋዊ ሥልጣኑን እያዳከመው መጥቷል ብሏል።
❤ 60👍 14👏 4
Photo unavailableShow in Telegram
🌟 የጀርመን ቋንቋ ትምህርት
🎓 የ Goethe ፈተና ዝግጅት ተካትቷል።
🌟 German Language Course
Learn German quickly and confidently!
🗣️ Improve speaking & listening
✍️ Enhance reading & writing
🌍 Connect globally
🎓 Goethe Exam preparation included
💡 Fun, interactive, and practical lessons
☎️
0989747878
0799331774
ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ : @merahyan
❤ 10🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
ETHIO SPARK COMPUTER & ACCESSORIES
ETHIO SPARK ፈጣን እና ዘመናዊ የሆኑ የዓለምችንን ምርጥ
🖥 አዳዲስ ላፕቶፖች
🖥 ጌሚንግ ላፕቶፖች
🖥 ቢዝነስ ላፕቶፖች
🖥 ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች እና
🖥 የተለየዩ የላፕቶፕ አክሰሰሪዎችን ከ አንድ አመት ዋስትና ጋር እንዲሁም ከልዩ መስተንግዶ ጋር እንጠብቆታለን።
ይደውሉ 👇
☎️+251974967884
የፁሁፍ መልዕክት 👇👇
💌 @Dm4ethio
📍 Location: 📌 Addis Ababa, Megenagn
Telegram link: https://t.me/EthioSpark16
You tube link:https://www.youtube.com/@EthioSpark0
Instagram link: https://www.instagram.com/ethiopark16/
Facebook :https://www.facebook.com/share/177eogKin1/
Tiktok link: tiktok.com/@ethiospark
🌐 Website:www.ethiospark16.com
❤ 15👍 4🤔 1
ከሀገራችን ባህልና ወግ ባፈነገጠ መልኩ የማህበራዊ ሚዲያን ሲጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
ከማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርም አንዱ የሆነውን ቲክቶክ በመጠቀም ከሀገራችን ባህልና ወግ ያፈነገጡ መልዕክቶችና ምስሎችን ሲያስተላልፉ የነበሩ ግለሠቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል።
በቲክቶክ ስሙ Lil_jay ወይም ጎይጋር ኮት ውይዋል እና ከእርሱ ጋር ያልተገባ አፀያፊ ድርጊት ስትፈጽም የነበረችው ኸሊሌ ጊቦ አያና የተባሉ ግለሠቦች የቲክቶክ አካውንት በመጠቀም ለመልካም ጠባይና ስነ ምግባር ተቃራኒ የሆነ መልዕክትንና ተንቀሳቃሽ ምስልን በቀጥታ ሲያስተላልፉ በመገኘታቸው ታህሳስ 02 ቀን 2018 ዓ/ም በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ፍሊንትስቶን ሆምስ ከሚባል ቦታ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በተመሳሳይ ዜና በቲክቶክ ስሙ ፕሬዚዳንት ማሜ ወይም ባህሩዲን ሙሰማ ከሀገራችን ባህልና ወግ ያፈነገጡ መልዕክቶችን ሲያስተላልፍ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ቦሌ ሚካኤል ጃፋር መስጅድ አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባራትና ትውልድን ለማነጽ መጠቀም ሲገባ ትውልድን ወደ አላስፈላጊ ድርጊት እንዲገባ የሚያስተምሩና የሚገፋፉ መሠል እኩይ ተግባራትን በሚፈጽሙ ግለሠቦችና ቡድኖች ላይ የሚወሰደው ህጋዊ ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል ።
❤ 60👏 53👍 19😁 6👎 1🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ከባንክ ሥርዓት ጋር የማጣመር ሥራ በይፋ ተጀመረ
የፋይናንስ ዘርፍ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ወሳኝ ምዕራፍ የሆነው የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ከባንክ ሥርዓት ጋር የማጣመር ሥራ በይፋ ተጀምሯል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጉዳዩን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
❤ 56🤔 9🥰 5👍 2👎 1
#ነዳጅ
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋን ይፋ ማድረጉን አረጋግጧል።
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር የዓለም የነዳጅ ዋጋን መነሻ በማድረግ ከታህሳስ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀነ-6፡00 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋን ነው ይፋ ያደረገው።
የአውሮፕላን፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ አና የከባድ ጥቁር ናፍጣ መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ የሚቀጥል ሲሆን ፤ የቤንዚን፣ የነጭ ናፍጣ እና የኬሮሲን ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ግን ጭማሪ ተደርጎበታል።
በእዚህም መሰረት ፦
- ቤንዚን 129.12 ብር በሊትር
- ነጭ ናፍጣ 129.12 ብር በሊትር
- ኬሮሲን 129.12 ብር በሊትር እንዲሸጡ የተወሰነ መሆኑ ታውቋል።
የአዲሱ የነዳጅ ችርቻሮ ዋጋ ማሻሻያ የደረሳቸው መሆኑን ከነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ደስታው መኳንንት አረጋግጧል።
❤ 23🤔 1😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
🚀 30% ቅናሽ በሁሉም ስልጠናዎቻችን!
Day / Night / Online ከAdvanced Level እና 90% Practical ተሞክሮ ጋር!
👉 ዛሬውኑ ጀምሩ !
🎓 ጀማሪ ቢሆኑ ወይም ችሎታዎን ለመሻሻል ቢፈልጉ!
🧑🏫 ከብዙ የስራ ልምድ ያላቸው መምህራን ትምህርት ታገኛላችሁ
የምንሰጣቸው ኮርሶች :
✅ ዲጂታል ማርኬቲንግ
✅ ዌብሳይት ይዛይን
✅ ፕሮጀክት ማኔጅመንት
✅ አካውንቲንግ
✅ አርት
✅ የጋዜጠኝነት ስልጠና
✅ ግራፊክ ዲዛይን
✅ ሞሽን ግራፊክስ
✅ ቪዲዮ ኤዲቲንግ
✅ 3D ዲዛይን
✅ ፎቶግራፊ
✅ ኢምፓርት ኤክስፖርት
✅ ቋንቋ : ጀርመንኛ 🇩🇪 ፣ አረብኛ🇸🇦 ፣ ፈረንሳይኛ🇫🇷 ፣ ቻይንኛ🇨🇳
○ 100% ተግባራዊ ስልጠና
○ ከስልጠና በኋላ Internship እድል
○ ለመማር ተስማሚ ቦታ
○ ባለሙያ እና ተሞክሮ ያላቸው መምህራን
○ ሁሉም ኮርሶች ከAdvanced ትምህርት እና ቀጣይ ድጋፍ ጋር
📍 አድራሻ: 22 ፣ ከጐላጐል ወደ ቦሌ ሚወስደው ከHanan K plana አጠገብ ቢጫ ፎቅ ግራውንድ ፍሎር 10B
📞 ስልክ:
0989747878 | 0799331774
❤ 28🤔 1
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሀገራችን ባህልና ሥነ-ምግባር ያፈነገጠ አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የታዩ ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ!!
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ3ኛው የG-Power TikTok Creative Award ላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህልና ሥነ-ምግባር ባፈነገጠ አኳሃን ሰውነታቸውን የገላለጠ አለባበስ ለብሰው በአደባባይና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የታዩ ተጠርጣሪዎችን ከነግብረ-አበሮቻቸው በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ ማጣራት መጀመሩን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን በሀገራችን አዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው 3ኛው የG-Power TikTok Creative Award ላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህል እና መልካም ሥነ-ምግባር በተቃራኒ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት የታዩ፣ ዝግጅቱን በስፖንሰርነት የደገፋ እና ፕሮግራሙን ያቀነባበሩ ተጠርጣሪዎች:-
1ኛ. ወንጌላዊት ገብረ እንድርያስ በርሄ፣
2ኛ. በርከት ፀጋዬ ጅፋር፣
3ኛ. መቅድም ደረጄ መንግስቱ፣
4ኛ. ግሩም ገዛሀኝ ቀጭኔ እና
5ኛ. ዮሃንስ መኮንን ሀ/ማርየም የተባሉ ግለሰቦች መሆናቸውን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከህብረተሰቡ ባህልና እሴት ያፈነገጡ አለባበሶችና መጤ ባህሎች ተስፋፍተው በትዉልዱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳያስከትሉ ተጠርጣሪዎቹ ላይ የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታውቃል።
❤ 132👍 60👏 10😱 1
የ2026 ዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ!!
ለመጀመርያ ጊዜ 48 ሀገራት የሚሳተፉበት የ2026 የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል በአሜሪካ ይፋ ሆኗል፡፡
በዋሽንግተን የተካሄደውን የምድብ ድልድል መድረክ የቀድሞው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን እና የማንችስተር ዩናይትድ ተከላካይ ሪዮ ፈርዲናንድ እና ሳማንታ ጆንሰን መርተውታል፡፡
በ12 ምድብ ተከፍሎ በሚደረገው ትልቁ መድረክ የ2022 የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮኗ አርጀንቲና ምድብ 10 ላይ ከኦስትሪያ፣ አልጄሪያ እና ጆርዳን ጋር ተደልድላለች፡፡
ፖርቹጋል ደግሞ በምድብ 11 ከኮሎምቢያ፣ ኡዝቤኪስታን እና (ከዴሞክራቲክ ኮንጎ፣ ጃማይካ እና ኒው ካልዶኒያ) አሸናፊ ጋር ተደልድላለች፡፡
❤ 79👍 11
Photo unavailableShow in Telegram
የ22 የስፖርት ውርርድ ድርጅቶች (ቤቲንግ ቤቶች) ፈቃድ ታገደ!
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ በሀገሪቱ ውስጥ ሲሰሩ የነበሩ የ22 የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች ፈቃድ ከ ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ታግዷል።
በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አማካኝነት ፈቃዳቸው የታገደባቸውን ዋና ዋና የስፖርት ውርርድ ድርጅቶች እነሆ፡
1. ዳሽ ቤት ባለ አንድ አባል ኃ/የተ/የግ/ማህበር
2. ዋልያ ስፖርት ኃ/የ/የግ/ማህበር
3. ኤክስኔት ሶሎሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር (ቱ ኤክስ ቤት)
4. ኤች ዲ ኤም /አፍሮ/ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
5. ብላክ ፐርል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
6. አይከኒክ ስፖርት ኢንተርቴይመንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
7. ጃምቦ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
8. ዳአባአክ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
9. ኢቲኤል (ኪዉክ) ኃ/የ/የግ/ማህበር
10. ቤት አራዳ ስፖርት እና ኢንተርቴመንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር (ሱፐር)
11. ቫሞስ ኢንተርቴይመንት ኃ/የ/የግ/ማህበር
12. ፍላሽ ስፖርት ውርርድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
13. ሁለገብ ኦንላይን ሶሎሽን ኃ/የ/የግ/ማህበር
14. ዘመን ስፖርት ቤቲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
15. ሁሉ ጌሚንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
16. አዲስ ቴልኮ ሰርቢስ አክሲዮን ማህበር (ቤቲካ ስፖርት ውርረድ)
17. ዩኒክ /መላ/ ስፖርት ቤቲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
18. ቶቶ ስፖርት ሶልሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
19. ኩኩሉ ስፖርት ስፖርት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
20. መርኬ ቤቲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (ሻምፒዮን)
21. ቤት ዘጠኝ ዘጠና አራት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
22. ሀሪፍ የስፖርት አገ/ኃ/የተ/የግ/ማህበር
Via ብሔራዊ ሎተሪ (National Lottery)
❤ 60👍 3🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
መፈንቅለ መንግስት በትግራይ? ወይስ ሌላ የፖለቲካ ጨዋታ ?
የህወሓት ታጣቂዎች የድምፂ ወያነ ቢሮ እና ፕረዝዳንት ፅሕፈት ቤት (ደጀን ቢሮ) ተቆጣጥረዋል።
ሰራተኞችን ከቢሮ አስወጥተዋል። ሁለቱን ቢሮዎች መቆጣጠራቸውን ካረጋገጡ በኋላ በሐውልት (የህወሓት ፅሕፈት ቤት) የደስታ ቶክስ ወደ ሰማይ ተተኩሷል።
የትግራይ ኃይል ታጣቂዎች የክልሉ አስተዳደር
ሕንጻ ላይ ከበባ መፈጸማቸው ተነገረ
በመቀለ ነዋሪዎች ዘንድ ስጋት ተፈጥሯል
የታጠቁ የትግራይ ኃይል አባላት "ደመወዝ ዘገየብን" በሚል ቅሬታ መቀለ የሚገኘው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ሕንጻ ላይ ከበባ መፈጸማቸውን ተነገረ።
የትግራይ ኃይል አርሚ 31 የተባለው ክፍል ከ70 በላይ የሚሆኑ አባላት ረቡዕ ኅዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ምሽት አራጉር (እንደርታ) ከተባለ ቦታ ተነስተው ነው ዛሬ ሐሙስ በአስተዳደሩ ሕንጻ ላይ ከበባ የፈጸሙት። የሠራዊት አባላቱ የነፍስ ወከፍ መሣሪያ የሆነውን ክላሽንኮቭ ጨምሮ ዲሽቃ የተባለውን የቡድን መሣሪያ የታጠቁ መሆናቸውን የዐይን እማኞች ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአርሚ 31 የቅርብ አዛዦች ክስተቱን ለማርገብ ሊያናግሯቸው ቢሞክሩም "ከፍተኛ ባለሥልጣናት መጥተው ያናግሩን" በሚል ሳይቀበሏቸው መቅረታቸው ተገልጿል።
የታጣቂዎቹ እንቅስቃሴ ከትናንት ጀምሮ የታየ መሆኑን ነዋሪዎች ያመለከቱ ሲሆን በዚህም ሳቢያ በመቀለ ነዋሪዎች ዘንድ ስጋት ተፈጥሯል። የክልሉ ባለሥልጣናት ውጥረቱን ለማርገብ ጥረት እያደረጉ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ከዕኩለ ቀን በኋላ ታጣቂዎቹ ከጊዜያዊ አስተዳሩ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ውይይት መጀመራቸውን አሁን የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
❤ 83👍 10😁 5🥰 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
በአዲስ አበባ ያለው የኤች አይ ቪ/ኤድስ ስርጭት ምጣኔ በአገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው በእጅጉ ከፍ ያለ ነው ተባለ‼️
በኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር 600 ሺሕ አልፏል።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባካሄደው ጥናት፣ በአዲስ አበባ ያለው የስርጭት መጠን 3 ነጥብ 14 በመቶ ሆኖ ሲገኝ፤ የሀገር አቀፉ ምጣኔ ደግሞ 0 ነጥብ 83 በመቶ እንደሆነ አስቀምጧል።
የቫይረሱ ስርጭት ከ0 እስከ 14 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሕጻናት 16 በመቶ፣ ከ15 እስከ 24 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወጣቶች 34 በመቶ እንዲሁም፤ 25 ዓመት እና ከዛ በላይ የሆኑ አዋቂዎች ደግሞ 51 በመቶ የሚሆነውን ቁጥር ይሸፍናሉ።
እ.ኤ.አ በ2024/2025 በጀት ዓመት አዲስ በኤች አይ ቪ ተይዘዋል ተብለው የተገመቱ ዜጎች ቁጥር 7 ሺሕ 962 ሲሆን፤ በየዓመቱ በአማካይ 9 ሺሕ 560 ሰዎች በኤች አይ ቪ/ኤድስ ምክንያት ሕይወታቸውን እንደሚያጡ ተገልጿል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከኤች አይ ቪ/ኤድስ ጋር እንደሚኖሩ ከሚገመተው ሰዎች መካከል 94 በመቶ የሚሆኑት ተመርምረው ራሳቸውን አውቀው መድኃኒት እንደጀመሩ በጥናቱ ተረጋግጧል ተብሏል፡፡
❤ 52😱 5
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ ከ22 ዓመት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈች
ከ17 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኬንያን በማሸነፍ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉን አረጋግጧል።
ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው የደረጃ ጨዋታ የኢትዮጵያ ወጣት ቡድን የኬንያ አቻውን 3 ለ 0 በማሸነፍ ነው ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ የተመለሰው።
ዳዊት ካሳው ቢኒያም አብርሃ እና ብሩክ እይላቸው የኢትዮጵያን ግቦች አስቆጥረዋል።
ወጣቱ አጥቂ ዳዊት ካሳው በአጠቃላይ ስምንት ግቦችን በማስቆጠር ውድድሩን አጠናቋል።
በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሴካፋ ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን የሚያገኝ ሲሆን ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ ለዋንጫ የሚጫወቱ ይሆናል።
❤ 88👍 20👏 13😁 9🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
ETHIO SPARK COMPUTER & ACCESSORIES
ETHIO SPARK ፈጣን እና ዘመናዊ የሆኑ የዓለምችንን ምርጥ
🖥 አዳዲስ ላፕቶፖች
🖥 ጌሚንግ ላፕቶፖች
🖥 ቢዝነስ ላፕቶፖች
🖥 ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች እና
🖥 የተለየዩ የላፕቶፕ አክሰሰሪዎችን ከ አንድ አመት ዋስትና ጋር እንዲሁም ከልዩ መስተንግዶ ጋር እንጠብቆታለን።
ይደውሉ 👇
☎️+251974967884
የፁሁፍ መልዕክት 👇👇
💌 @Dm4ethio
📍 Location: 📌 Addis Ababa, Megenagn
Telegram link: https://t.me/EthioSpark16
You tube link:https://www.youtube.com/@EthioSpark0
Instagram link: https://www.instagram.com/ethiopark16/
Facebook :https://www.facebook.com/share/177eogKin1/
Tiktok link: tiktok.com/@ethiospark
🌐 Website:www.ethiospark16.com
❤ 29👍 2
"ልቤን" እያለ አረፈ
ኮሜድያን ወንደወሰን አውራሪስ በድንገተኛ የልብ ህመም በዳግማዊ ምንልክ ሆስፒታል በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ሕይወቱ አልፏል።
ትናንት "ልቤን" ብሎ ወደ ህክምና አምርቶ ነበር።
ለሊቱን ሁሉ ሕክምና እየወሰደ ከአንድም ሁለት ጊዜ አሰቸጋሪ ደረጃ እየደረሰ በሕክምና ህይወቱ ተመልሷል።
ይሁንና የአንዲት ሴት ልጅ አባት የሆነው ኮሜድያን ወንደወሰን አውራሪስ ዛሬ ማለዳ ላይ አርፏል።
😭 116❤ 40😢 9🤔 1
በሆንግ ኮንግ 128 ሰዎችን ለሕልፈት የዳረገው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ
በሆንግ ኮንግ በጋራ መኖሪያ ቤት ሕንጻዎች ላይ በተከሰተው የእሳት አደጋ የሟቾች ቁጥር 128 ደርሷል አሉ የአካባቢው ባለስልጣናት፡፡
ባሳለፍነው ረቡዕ ዕለት በተከሰተው የእሳት አደጋ ለሕልፈት ከተዳረጉት በተጨማሪ ከ200 በላይ ሰዎች እስካሁን ያሉበት አልታወቀም፡፡
ከ4 ሺህ 600 በላይ ሰዎች በሚኖሩባቸው የጋራ መኖሪያ ቤት ሕንጻዎች የተከሰተውን የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የሆንግ ኮንግ የደህንነት ኃላፊ ክሪስ ታንግ ገልጸዋል፡፡
አደጋውን ለመቆጣጠር ከ2 ሺህ በላይ የእሳት አደጋ ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን ÷ በአደጋው ምክንያት በጊዜያዊ መጠለያ ለሚገኙ ሰዎች ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
ኃላፊው በሰጡት መግለጫ በሁሉም ሕንጻዎች ላይ የተገጠሙ የእሳት አደጋ የጥንቃቄ መልዕክት መሳሪያዎች አገልግሎት እየሰጡ እንዳልነበር አመልክተዋል፡፡
የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ፖሊስ በይፋ ምርመራ መጀመሩንና መረጃዎችን እያሰባሰበ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት፡፡
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
❤ 70😢 13🤯 6👍 3🙏 3
Photo unavailableShow in Telegram
በሃዋሳ ከተማ በማርበርግ ቫይረስ የተያዘ ሰው መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ተናገረ።
ግለሰቡ በጂንካ ከተገኘው የመጀመሪያው የማልበርግ ቫይረስ ተጠቂ ጋር ንክኪ የነበረው ወደ አካባቢው ተጉዞ ወደ ሃዋሳ ተመላሽ የነበረ ነውም ተብሏል።
ይህ የተባለው የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በማርበርግ ቫይረስ ዙሪያ እየሰሩት ያለውን ስራ በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።
በዚህም ወቅት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ላሉ ሰዎች በየእለቱ የላብራቶሪ ምርመራ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
ቫይረሱ ከተከሰተበት ከህዳር 5 ቀን እስከ ህዳር 17 ቀን 2017ዓ.ም ድረስ 73 የላብራቶሪ ምርመራዎች ተደርገዋል ያሉት ሚኒስትሯ በዚህም 11 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፤ 6ቱ ህይወታቸው አልፏል፤ 5ቱ ደግሞ በህክምና ላይ ናቸው ሲሉም አስረድተዋል።
በሌላ በኩል ሌሎች ሃገራት ላይ ተሞክሮ ለውጥ ያመጣ ዶሚድስፔር የተባለ ፀረ ህዋስ መድሃኒት ወደ ሃገር ቤት በማስገባት ለ16 የህክምና ባለሙያዎች እንዲሁም በህክምና ላይ ላሉት 5 የቫይረሱ ተጠቂዎች ሰጥተናል ብለዋል።
መድሃኑቱ ለውጥ እያመጣ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር መቅደስ በህክምና ላይ ያሉት 5ቱ ተጠቂዎች የማገገም ሂደት ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።በፅኑ ህሙማን ክፍል 1ታማሚ እንዳለ የተነገረ ሲሆን አስፈላጊው ክትትል እየተደረገለት ነው ተብሏል።(ሸገር ራዲዮ)
❤ 75😱 11😭 9👍 5🤔 2👎 1🤯 1
Photo unavailableShow in Telegram
ከማርበርግ ቫይረስ ታካሚዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ነው - ዶ/ር መቅደስ
ከማርበርግ ቫይረስ ታካሚዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው 349 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ነው አሉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ።
ሚኒስትሯ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ፥ እስካሁን የማርበርግ ቫይረስ ምርመራ ከተደረገላቸው 73 ሰዎች መካከል 11ዱ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።
በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን እና አምስቱ ደግሞ የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡
ከታካሚዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው 349 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን÷ ከእነዚህ ውስጥም 119 ሰዎች ነጻ መሆናቸው ተረጋግጦ ከማዕከል መውጣታቸውን ጠቁመዋል። የማርበርግ ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ብሔራዊ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬከተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ በበኩላቸው፥ የቫይረሱን ሥርጭት ለመቆጣጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በየኬላዎች የሚደረገውን ቁጥጥር የማጠናከር፣ የቅኝት ሥራዎችን የማስፋትና ለሕብረተሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጥ ላይ ትኩረት ተደርጓል ነው ያሉት፡፡ ማሕበረሰቡ ከጤና ሚኒስቴር የሚሰጡ የጥንቃቄ መመሪያዎችን በመተግበርና ጥቆማዎችን በመስጠት ሃላፊነቱን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።
❤ 42👍 3👎 1😁 1😱 1
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለከፍተኛ ግብር ከፋዮች የሚሰጠውን የመጀመሪያውን የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ሰጠ
ለከፍተኛ ግብር ከፋዮች በልዩ መልኩ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ማግኘት እንዳለባቸው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር አብይ አህመድ (ዶክተር ) መናገራቸው ይታወሳል ፤ ክቡር ጠቅላይ ሚንስተሩ ባስቀመጡት መመሪያ መሰረት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመጀመሪያውን የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ሰቷል ።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመጀመሪያውን የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ለአቶ ብዙአየሁ ታደለ የኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ እና የናሽናል ሲሚንቶ ሆልዲንግ ሼር ካምፓኒ ቦርድ ሊቀመንበር ሰቷል።ለከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ አምባሳደሮች ፣ ለሀገር ባለውለታዎች ለከፍተኛ ግብር ከፋዮች ልዩ ግልጋሎት የሚሰጥበት መገልገያ ቦታ መኖሩን ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።
❤ 45😁 12👍 5👎 1
