ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
الذهاب إلى القناة على Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም አስተያየት @Zimaredawitmessanger ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን። YouTube Page - https://bit.ly/2O1Z3d8 Facebook Page - https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR
إظهار المزيد2025 عام في الأرقام

166 299
المشتركون
-4924 ساعات
+677 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
ማስታወቂያ!
የ2018 አዳዲስ ዲዛይኖቻችንን ለእናንተ ለውድ ደንበኞቻችን ውብ በሆነ መልኩ ሰርተን በማቅረብ ላይ እንገኛለን። ከፊታችን ለሚመጣው የጥምቀት በዓልም ለእናንተ በጣም በቅናሽ ለማድረስ እየሰራን እንገኛለን፡፡ ዲዛይነሮቻችንም እናንተን ለማስደሰት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
ትዕዛዝ መቀበል ጀምረናል፡፡ ማዘዝ የምትፈልጉ ማህበራት ለእናንተ ልዩ ቅናሽ (Package) አዘጋጅተናል፡፡ ከእናንተ የሚጠበቀው ቀደም ብላቹ ማዘዝ ብቻ ነው፡፡ ክፍለ ሀገር የምትገኙ ደንበኞቻችን እንደ ከዚህ ቀደሙ ትዕዛዝ የሚቀበሉ ሰዎችን ስለመደብን ለአገልግሎት ጥራትና ለተደራሽነት ዝግጁ ሆነን እየሰራን ነው፡፡
KABA Digital Print
0965875219 / 0922501999
Join አድርጉ 👇👇👇
https://t.me/KABAPrint
https://t.me/KABAPrint
❤ 20🥰 8
እግዚአብሔር የሚከብርበትን ስራ በእግዚአብሔር እረዳትነት ሰራን። የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን።
ከፈጣሪ በታች በእናንተ በዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች እገዛ ይህ ከላይ የምትመለከቱትን ሁለት መጎናጸፊያ ከነቀጸላው እና ሦስት የግሪክ ጽንሐሕ ገዝተን በዛሬው እለት ለገጠር አብያተ ክርስቲያን ልከናል።
በዚህ አገልግሎት ከጎናችን ለነበራችሁ፤ በገንዘባችሁ ለረዳችሁን፤ በጸሎት ላሰባችሁን ሁሉ እግዚአብሔር አምላክ በስውር የሰጣችሁት በግልጥ ይመልስላችሁ።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለዐቢይ ጾም እንዲሁ በጋራ አንድ የበረከት ስራ እንሰራለን። የዛ ሰው ይበለን።
❤ 85
Repost from TgId: 2131344856
Photo unavailableShow in Telegram
ምዝገባ
ጀ
መ
ረ
የ1 ሳምንት የምዝገባ ጊዜ ብቻ
በአጭር ጊዜ እጅግ በማይገመት
ፍጥነት ተወዳጅ የሆኑት ኮርሶቻችንን
በጥቂት ወራት 6 ዙሮችን አሳክተን
7ኛውን ዙር ደግሞ ታኅሣሥ 26
ቀን 10፡00 ልንጀምር ነው
ቤታቹ ሆናቹ
በ300 ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ
(4500 ጠቅላላ ክፍያ )
~ 2 ወር ምን ተአምር ሊሠራበት
እንደሚችል ገብታችሁ እዩ ፣
« ካልወደዳችሁት ደግሞ ገንዘባችሁን
የማስመለስ ምርጫቹ የናንተ ነው »
ሌላ የምሥራች 🎉
በዚህ ዙር አሸናፊውን
የቪዲዮ ኤዲቲንግ ኮርስ
በነጻ ልንሸልም ነው🤭
መስፈርቱን የምታሟሉ ብቻ
አሁኑኑ እዚህ ላይ ተመዝገቡ
@Greenbirdtechnology
@greenbirdtechs
@greenbirdtechs
የለውጥዎ ክንፍ 🔑 🐥
❤ 23
አማኑኤል ተመስገን
አማን በአማን /4/
አማኑኤል ተመስገን
ለዚህ ፍቅርህ ምን እንበልህ
መድኃኔዓለም ተመስገን
ለዚህ ፍቅርህ ምን እንበልህ
አዝድብቁን ኃጢአት አንተ ብትገልጠው ይቅር ብለኸኝ ባትሸፋፍነው እንደ ሰው በቀል ቢኖርህ ጌታ ለእኔ ኃጢአትስ የለውም ቦታ
አዝበየደቂቃው ኃጢአት ስሠራ ስሰርቅ ስበድል አንተን ሳልፈራ አንተ ግን ፊትህ ምንም ቢቀየም በቁጣህ በትር አልገረፍከኝም
አዝምሕረትህን ልከህ አድነኝ ዛሬ ታክቶኛልና በኃጢአት መኖሬ ዓለም በኃጢአት እየሳበችኝ በጽድቅህ ደስታ መኖር አቃተኝ
አዝየኃጢአት ጉዞ ጣፋጭ ቢመስልም ውጤቱ መሮ ፍጹም አይጥሞም እንደ በደሌ ስላልከፈልከኝ ተመስገን እንጂ ሌላ ምን አለኝ የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
አማኑኤል_ተመስገን_ሊቀመዘምራን_ይልማ_ኃይሉ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ_ኅ.mp33.65 MB
❤ 74🥰 5
Photo unavailableShow in Telegram
ታሕሳስ ፲፯ /17/በዚች ቀን የቅዱስ ሉቃስ ዘዓምድ የሥጋው ፍልሰት ሆነ። እርሱም ከፋርስ አገር ነው በመጀመሪያ በመቶ ጭፍራ ላይ መኰንን ሁኖ ተሹሞ ነበር ከዚህም በኋላ ሹመቱን ትቶ የምንኵስና ልብስን ለበሰ። በአንድ ገዳም ውስጥ ገብቶ በብዙ መጋደል ጀመረ በዚያም ቅስና ተሾመ። ከዚህም በኋላ ከዓምድ ላይ ወጥቶ በላዩ ሦስት ዓመት ቆመ በስሙም መልአክ ጠርቶት ከአንድ ገዳም አደረሰው። ከዚህም በኋላ የማይናገር ሆነ ከሰው ጋር ከቶ እንዳይናገር ከአፉ ውስጥ ደንጊያ ጐረሰ ዳግመኛም ወደ ቊስጥንጥንያ አገር ዳርቻ ይሔድ ዘንድ መልአክ አዘዘው። ለእርሷም አቅራቢያ ወደ ሆነች ወደ አንዲት ቦታ ሔደ ከምሰሶ ላይም ወጥቶ ታላቅ ተጋድሎን እየተጋደለ በላዩ አርባ አምስት ዓመት ኖረ እግዚአብሔርም የመፈወስን ሀብት ሰጠው አስደናቂዎች ተአምራትን በማድረግ ወደርሱ የሚመጡትን ብዙዎች በሽተኞችን ፈወሳቸው። እግዚአብሔርም ከዚህ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው በፈቀደ ጊዜ በዚህ ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን አረፈ የሚያገለግለውም ረድ ለጳጳሳት አለቆችና ለካህናት አለቆች ስለ ዕረፍቱ ነገራቸው እነርሱም መስቀሎችን፣ ጽንሐዎችን፣ መብራቶችን ከመያዝ ጋር በዚያን ጊዜ ተነሥተው ወደ መኖሪያው ሔዱ በላዩም ጸልየው ተሸክመው ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ ወሰዱት። በአረፈ በሦስተኛው ቀን ታኅሣሥ ዐሥራ ሰባት በዚች ቀን አደረሱት ወደ ቤተ መቅደስም አስገብተው የከበረ ሥጋው በአለበት እንደ ሚገባ ጸሎትን ፈጸሙ። ከእርሱም ተባረኩ የተሰበሰቡትም ሁሉ ተባረኩ ከዚህም በኋላ ከእርሱ አስቀድሞ የቅዱሳን ሥጋቸው ወዳለበት ሣጥን ውስጥ ጨመሩት። የቅዱሳን በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❤ 107🕊 6🥰 3
ተወልደ ኢየሱስ
ተወልደ ኢየሱስ በቤተልሔም /2/
ዘይሁዳ በቤተልሔም
ተወልደ ኢየሱስ በቤተልሔም /2/
ዘይሁዳ በቤተልሔም
አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ /2/
በቤተልሔም
አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ /2/
በቤተልሔም
ተወልዷል ኢየሱስ በቤተልሔም /2/
በይሁዳ በቤተልሔም
ተወልዷል ኢየሱስ በቤተልሔም /2/
በይሁዳ በቤተልሔም
የጢሮስ ልጆች ሁሉ ያን ጊዜ ይሰግዳሉ /2/
በቤተልሔም
የጢሮስ ልጆች ሁሉ ያን ጊዜ ይሰግዳሉ /2/
በቤተልሔም
ተወልደ ኢየሱስ በቤተልሔም /2/
ዘይሁዳ በቤተልሔም
ተወልደ ኢየሱስ በቤተልሔም /2/
ዘይሁዳ በቤተልሔም
አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ /2/
በቤተልሔም
አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ /2/
በቤተልሔም
የአእላፋት ዝማሬ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ተወልደ_ኢየሱስ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ_ኅብረ_ዝማሬ_የተዘመረ.mp32.95 MB
❤ 57🔥 2🥰 1
እግዚአብሔር ይመስገን። 🎉🎉🎉
እንኳን ደስ አላችሁ። ለአንድ የገጠር ቤተ ክርስቲያን የሚሆን የሶስት ጽንሐሕ እና የሁለት መጎናጸፊያ መግዣ ብር ሰብስበን ጨርሰናል።
ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ማስገባት አቁሙ።
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ዛሬ 10 ሰዓት ላይ ለመግዛት ወስነናል።
በስውር የሰጣችሁን በሙሉ እግዚአብሔር አምላክ አብዝቶ በግልጥ ይመልስላችሁ።
❤ 186🥰 4
4 ሺህ ብር ብቻ ቀርቶናል። በጣም ትንሽ ብር ናት። የቀረን ቀን ዛሬ ብቻ ነው።
እግዚአብሄር የፈቀደላችሁ አቅማችሁ የፈቀደ በቀረችን ጥቂት ግዜ እንድናሳካው አግዙን።
🔥 10❤ 9
7 ሺህ ብር ብቻ ቀርቶናል። በጣም ትንሽ ብር ናት። የቀረን ቀን ዛሬ ብቻ ነው።
እግዚአብሄር የፈቀደላችሁ አቅማችሁ የፈቀደ በቀረችን ጥቂት ግዜ እንድናሳካው አግዙን።
❤ 17
9 ሺህ ብር ብቻ ቀርቶናል። በጣም ትንሽ ብር ናት።
እግዚአብሄር የፈቀደላችሁ አቅማችሁ የፈቀደ በቀረችን ጥቂት ግዜ እንድናሳካው አግዙን።
❤ 6
Photo unavailableShow in Telegram
ዛሬን ብቻ ነው የምንሰበስበው።
የደረስንበት 107,723 ብር
የሚያስፈልገን 119,000 ብር
የቀረን 11,227 ብር ብቻ
ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
🏦 1000142059022
ሁላችሁም በቀረችን ቀን በመረባረብ የአቅማችሁን እንድትለግሱ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
❤ 16
Photo unavailableShow in Telegram
ታሕሳስ ፲፮ /16/በዚች ቀን ከእስራኤል መሳፍንት አንዱ ጌዴዎን አረፈ። እግዚአብሔርም ወደ ጌድዮን መልአኩን ልኮ ሕዝበ እስራኤልን ከምድያም እንደሚያድናቸው ለጌድዮን ነገረው። እርሱም መልአኩ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደተላከ ፈተነውና አወቀ።ከዚህም በኋላ ጌድዮን ብዙ ሰዎችን ሰበሰበ። እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው ከእናንተ የሚፈራ የሚደነግጥ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይመለስ ብለህ ለሕዝቡ ንገራቸው። ሕዝቡም ከገለዓድ ተመለሱ ከሕዝቡም ሁለት እልፍ ከሁለት ሽህ ተመልሰው እልፍ ሰዎች ቀሩ። እግዚአብሔርም ጌዴዎንን ገና ብዙ ሕዝብ አሉ ወደ ውኃ አውርደህ በዚያ ፈትናቸው እኔ ይሒዱ የምልህ ሰዎች እነሳቸው ካንተ ጋር ይሒዱ አለው ሕዝቡንም ወደ ውኃ አወረዳቸው ። እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንደ ውሻ የሚጠጣውን ለብቻው አቁመው ተንበርክከው በእጃቸው የሚጠጡትን ሁሉ ለብቻው አቁመው አለው። እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንደዚህ በእጃቸው ውኃን በጠጡት በሦስት መቶ ሰዎች አድናችኋለሁ አለው። በዚያችም ሌሊት እሊያ ሦስት መቶ ሰዎች መለከትን ነፉ ይህ የእግዚአብሔር ኃይልና የጌዴዎን ጦር ነው ብለው ጮኹ። የምድያምም ሰዎች የመለከቱን ድምፅ በሰሙ ጊዜ እግዚአብሔር በልባቸው ፍርሀትን አሳድሮባቸው ደንግጠው ሸሹ እግዚአብሔርም ያንዱን ሰይፍ ወዳንዱ ወደ ጓደኛው መለሰ በሠራዊቶቻቸው ሁሉ እርስበርስ መተላለቅ ሆነ መኳንንቶቻቸውን ኄሬብንና ዜብን ነገሥቶቻቸው ዛብሄልንና ስልማናንም ገደሏቸው ከምድያምም ሠራዊት ፈረሰኞችና ጦረኞችን አንድ መቶ ሁለት ሽህ ገደሉ። በጌዴዎንም ዘመን ምድር አርባ ዘመን አረፈች። ከዚህም በኋላ በሰላም በፍቅር አረፈ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❤ 92🕊 8🥰 3
14 ሺህ ብር ብቻ ቀርቶናል። በጣም ትንሽ ብር ናት።
እግዚአብሄር የፈቀደላችሁ አቅማችሁ የፈቀደ በቀረችን ጥቂት ግዜ እንድናሳካው አግዙን።
❤ 30
15 ሺህ ብር ብቻ ቀርቶናል። በጣም ትንሽ ብር ናት።
እግዚአብሄር የፈቀደላችሁ አቅማችሁ የፈቀደ በቀረችን ጥቂት ግዜ እንድናሳካው አግዙን።
❤ 13🕊 3
19 ሺህ ብር ብቻ ቀርቶናል። በጣም ትንሽ ብር ናት።
እግዚአብሄር የፈቀደላችሁ አቅማችሁ የፈቀደ በቀረችን ጥቂት ግዜ እንድናሳካው አግዙን።
❤ 5
20 ሺህ ብር ብቻ ቀርቶናል።
አቅማችሁ የፈቀደ በቀረችን ጥቂት ግዜ እንድናሳካው አግዙን።
❤ 9
Photo unavailableShow in Telegram
አንድ ቀን ብቻ ቀረን!
የደረስንበት 95,623 ብር
የሚያስፈልገን 119,000 ብር
ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
🏦 1000142059022
ሁላችሁም በቀረችን ቀን በመረባረብ የአቅማችሁን እንድትለግሱ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
❤ 40
ታሕሳስ ፲፭ /15/በዚች ቀን ያለ ደም መፍሰስ ሰማዕት የሆነ የአርማንያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ጎርጎርዮስ አረፈ። ይህንንም ቅዱስ ለንጉሡ አማልክት አልሠዋም ስላለ የአርማንያ ንጉሥ ድርጣድስ ደረቅ ጒድጓድ ውስጥ ጨመረውና በዚያ 15 ዓመት ኖረ። አንዲት ሴትም በድብቅ ምግቡን ታመጣለት ነበር። ድርጣድስም ቅድስት አርሴማን ሊአገባት ሽቶ ነበርና በእርሷ ምክንያት ደናግሎችን ገደላቸው። ሥጋቸውም በተራራ ወድቆ ቀረ። ንጉሡም ስለ ገደላቸው ደናግል ይልቁንም ስለ ቅድስት አርሴማ አብዝቶ የሚያዝን ሆነ። ከዚህም በኋላ ወገኖቹ እንዲህም አሉት አውሬ ታድን ዘንድ ወደ ዱር እንውጣ የልብህም ኀዘን ይወገድልሃል። እርሱም ወደ ዱር ወጣ ። ወዲያውኑ ሰይጣን አደረበትና እንደ እሪያ አደረገው። የንጉሡ እኅት ግን ጎርጎርዮስን ከጒድጓድ ካላወጡ እንደማይድኑ በራዕይ አየችና ነገረቻቸው። ጎርጎርዮስም ከዚያ አውጥተው ወደ ቤተ መንግሥት አደረሱት። በዚያንም ጊዜ ንጉሱ ያስገደላቸውን የደናግሉን ስጋ ሰብስቦ በክብር አኖረው። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ጸለየ ከንጉሡም ላይ በእሪያ አምሳል የነበረውን ሰይጣንን አስወጣው። ዳግመኛ እንዳይታበይ ከእግሩ ላይ የእሪያ ጥፍር አስቀረ ከዚህ በኋላም የቤተ መንግሥት ሰዎችን ሁሉንም አዳናቸው ከላያቸውም አጋንንትን አስወጥቶ ሰደዳቸው። ከዚህም በኋላ ያጠምቋቸው ዘንድ ወደ አርማንያ ሊቀ ጳጳስ መልክተኞችን ልኮ አጠመቃቸው ዳግመኛም ሊቀ ጳጳሳቱ የአርማንያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ይሆን ዘንድ ቅዱስ ጎርጎርዮስን ሾመው። በዚያም መልካም ጎዞውን ፈጸሞ በሰላም አረፈ። በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❤ 162🕊 9🥰 5
Repost from ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
ማስታወቂያ!
የ2018 አዳዲስ ዲዛይኖቻችንን ለእናንተ ለውድ ደንበኞቻችን ውብ በሆነ መልኩ ሰርተን በማቅረብ ላይ እንገኛለን። ከፊታችን ለሚመጣው የጥምቀት በዓልም ለእናንተ በጣም በቅናሽ ለማድረስ እየሰራን እንገኛለን፡፡ ዲዛይነሮቻችንም እናንተን ለማስደሰት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
ትዕዛዝ መቀበል ጀምረናል፡፡ ማዘዝ የምትፈልጉ ማህበራት ለእናንተ ልዩ ቅናሽ (Package) አዘጋጅተናል፡፡ ከእናንተ የሚጠበቀው ቀደም ብላቹ ማዘዝ ብቻ ነው፡፡ ክፍለ ሀገር የምትገኙ ደንበኞቻችን እንደ ከዚህ ቀደሙ ትዕዛዝ የሚቀበሉ ሰዎችን ስለመደብን ለአገልግሎት ጥራትና ለተደራሽነት ዝግጁ ሆነን እየሰራን ነው፡፡
KABA Digital Print
0965875219 / 0922501999
Join አድርጉ 👇👇👇
https://t.me/KABAPrint
https://t.me/KABAPrint
❤ 42😍 4🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
ሁለት ቀን ብቻ ቀረን!
የደረስንበት 94,723 ብር
የሚያስፈልገን 119,000 ብር
የቀረን 24,277 ብር ብቻ
ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
🏦 1000142059022
ሁላችሁም በቀረችን ቀን በመረባረብ የአቅማችሁን እንድትለግሱ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
❤ 43
