ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
الذهاب إلى القناة على Telegram
The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man
إظهار المزيد2025 عام في الأرقام

44 133
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
-22730 أيام
أرشيف المشاركات
ገዳ ባንክ ለተደራጁ ወጣቶች 10 ተሽከርካሪዎች በብድር ሰጠ
👉 ባንኩ ከናይስ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል
ገዳ ባንክ ሸገር አሶሴሽን ኢንተርፕራይዝ የተባለ ክህሎት እና የስራ ፈጠራ ያላቸው ወጣቶችን አሰልጥኖ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያገኙ እየሰራ ካለ ተቋም ጋር በመተባበር ከአካባቢ ብክለት ነፃ የሆነ ተሽከርካሪዎችን ከናይስ ትሬዲንግ ወጪ ቆጣቢ ተሽከርካሪዎችን እንዲያገኙ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉን አስታውቋል።በዚህም መሰረት ከናይስ ትሬዲንግ ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ድርጅት ጋር የመግባቢያ ሰነድ በዛሬው እለት ተፈራርሟል።
የናይስ ትሬዲንግ ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መስራች ዶክተር ጃለታ ሙላቱ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት በሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ ተሽከርካሪዎችን ግዢ የሚደረግበትን ወጪ ባንኩ እንዳመቻቸላቸው አስታውቀዋል።በስድስት ወራት ውስጥ ከ600 በላይ ተሽከርካሪዎችን ማስገባት ታቅዷል ሲሉ የተናገሩት ዶክተር ጃለታ በአንድ ዓመት ውስጥ እስከ 1ሺህ ለመድረስ እቅድ አለን ሲሉ ተናግረዋል።ተሽከርካሪዎቹ የማህበረሰቡን ችግር ይቀርፋል የተባለ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሰራ እንዲሁም አቅጣጫ ጠቋሚ ጂፒኤስ ያለው ነው።
ተሽከርካሪው እስከ 15 የሚሆኑ ሰዎችን በጋራ ሆነው ሊጓጓዝ የሚችሉበት ሲሆን ወጪ ቆጥበው መጓጓዝ የሚችሉበት የክፍያ ስርዓቱም በኪው አር ኮድ እና የራሱ የሆነ ካርድ ያለው ሲሆን በአንድ ፌርማታ ክፍያው 30 ብር ነው።አዲስ አበባ ከ10ሺህ በላይ በኤሌክትሪክ የሚሰራ እና ለተሳፋሪዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የህዝብ ትራንስፖርት እንደሚያስፈልጋት በመድረኩ ተገልጿል፡፡
ሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 22😁 8👎 1
ብሪቲሽ ካውንስል ስለ ጥልቅ መረዳት በተመለከተ ለወጣቶች ስልጠና ሰጠ!
ብሪቲሽ ካውንስል ኢትዮጵያ ከተለያዩ ተቋማት ለመጡ ወጣቶች ስለ ጥልቅ መረዳት (deep listening) የተመለከተ ስልጠና ሰጥቷል።
የብሪቲሽ ካውንስል ም/ል ዳይሬክተር ወ/ሮ መፅናናት ሳህለ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት፣ ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር በመተባበር የ deep listening ስልጠና የሰጡት የቢቢሲ የቀድሞ ጋዜጠኛ የነበሩት ኤሚሊ ካስሬል ናቸው።
የብሪቲሽ ካውንስል ዓላማ፣ በዩናይትድ ኪንግደም እና በመላው ዓለም በሚገኙ ሰዎች መካከል ግንኙነትን፣ መግባባትን እና መተማመንን በመገንባት ሰላምን እና ብልጽግናን መደገፍ ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የብሪቲሽ ካውንስል ም/ዳይሬክተር ወ/ሮ መፅናናት ሳህለ ተናግረዋል።
ብሪቲሽ ካውንስል ኢትዮጵያ ለሁለት ቀን በሚቆየው "የጥልቅ መረዳት" ስልጠና ከ70 በላይ የሚሆኑ ሰልጣኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ ያሉት ም/ል ዳይሬክተሯ ስልጠናው በዓለም አቀፍ ደረጃ የ deep listening ባለሙያ የሆኑት ኤሚሊ ካስሬል አማካኝነት በመስጠት ላይ እንገኛለን ሲሉ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።
ስልጠናውን የሰጡት በእንግሊዝ አገር የኪንግስ ኮሌጅ የፖሊሲ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የምርምር ባልደረባ የሆኑት ኤሚሊ ካስሬል መሆናቸውን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።
ሰላማዊ ነጋሲ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 14👍 1🤔 1
ብሪቲሽ ካውንስል ኢትዮጵያ ስለ ጥልቅ መረዳት በተመለከተ ለወጣቶች ስልጠና ሰጠ!
ብሪቲሽ ካውንስል ኢትዮጵያ ከተለያዩ ተቋማት ለመጡ ወጣቶች ስለ ጥልቅ መረዳት (deep listening) የተመለከተ ስልጠና ሰጥቷል።
የብሪቲሽ ካውንስል ም/ል ዳይሬክተር ወ/ሮ መፅናናት ሳህለ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት፣ ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር በመተባበር የ deep listening ስልጠና የሰጡት የቢቢሲ የቀድሞ ጋዜጠኛ የነበሩት ኤሚሊ ካስሬል ናቸው።
የብሪቲሽ ካውንስል ዓላማ፣ በዩናይትድ ኪንግደም እና በመላው ዓለም በሚገኙ ሰዎች መካከል ግንኙነትን፣ መግባባትን እና መተማመንን በመገንባት ሰላምን እና ብልጽግናን መደገፍ ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የብሪቲሽ ካውንስል ም/ዳይሬክተር ወ/ሮ መፅናናት ሳህለ ተናግረዋል።
ብሪቲሽ ካውንስል ኢትዮጵያ ለሁለት ቀን በሚቆየው "የጥልቅ መረዳት" ስልጠና ከ70 በላይ የሚሆኑ ሰልጣኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ ያሉት ም/ል ዳይሬክተሯ ስልጠናው በዓለም አቀፍ ደረጃ የ deep listening ባለሙያ የሆኑት ኤሚሊ ካስሬል አማካኝነት በመስጠት ላይ እንገኛለን ሲሉ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።
ስልጠናውን የሰጡት በእንግሊዝ አገር የኪንግስ ኮሌጅ የፖሊሲ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የምርምር ባልደረባ የሆኑት ኤሚሊ ካስሬል መሆናቸውን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።
ሰላማዊ ነጋሲ
#
❤ 2👎 2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በአስር ዓመት ታዳጊ ላይ ግድያ የፈጸመ ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነበት
በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር የአስር ዓመት ታዳጊ ናትናኤል ማይክልን በማገት እና በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ተከሳሽ ወርቅነህ አሰፋ በሞት እንዲቀጣ የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወስኗል።
ተከሳሹ የቀድሞ የመምህርነት ሥራውን ተጠቅሞ ታዳጊውን ናትናኤል ማይክልን ከትምህርት ቤት ሲመለስ ጠልፎ ወደ መኖሪያ ቤቱ ወሰዷል።
ተከሳሹ ልጁን በቦክስ ከመምታት በኋላ በአፍና አፍንጫው ላይ በፕላስተር በማሸግ አፍኖታል። ልጁ ለማምለጥ ሲታገል ተመልሶ በመምጣት በአንሶላ አንቆ ሕይወቱን ካጠፋ በኋላ አስከሬኑን መፀዳጃ ቤት ውስጥ በመደበቅ ለመሰወር ሞክሯል።
የወንጀል ሕግ አንቀጽ 539(1)(ሐ) እና 590/2/(ሠ)ን የተላለፈው ተከሳሽ፣ አስቀድሞ በሕፃኑ ቤተሰብ ላይ ገንዘብ የመጠየቅና የራሱን ኑሮ የመቀየር አደገኛ አስተሳሰብ አንግቦ መሆኑ በክሱ ተገልጿል።
የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዐቃቤ ሕግን ክስና ማስረጃዎች አጥጋቢ ሆኖ በማግኘቱ፣ ተከሳሹ በጭካኔ በተሞላበት መንገድ የፈጸመው አስቦ የመግደልና ታዳጊን የመጥለፍ ወንጀል ተረጋግጦበት፣ በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል።
#ዳጉ_ጆርናል
👍 51❤ 11🙏 3😭 2💯 1
በሆንግ ኮንግ በከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ የሟቾች ቁጥር ቢያንስ 55 ደረሰ
በሆንግ ኮንግ ታይፖ አውራጃ ውስጥ በሕዝብ መኖሪያ ቤቶች ላይ በደረሰዉ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ቢያንስ 55 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ ከ270 የሚበልጡ ሰዎች እስካሁን ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ አልተቻለም፡፡ባለሥልጣናቱ ሐሙስ ጠዋት አደጋዉን አስመልክቶ እንደተናገሩት በእሳቱ ከተጎዱት ሰባት ሕንፃዎች መካከል በአራቱ ውስጥ ያለዉን አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን እና የተቀሩትን ህንጻዎች እስከ ምሽት ካልሆነም አርብ ማለዳ ድረስ ለማብረድ ተስፋ አድርገዋል ።
እሳቱ ጋብ ሲል፣ እሳቱ መጀመሪያ እንዴት እንደተቀሰቀሰ እና ማን ሊጠየቅ ይገባል የሚሉ ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚያገኙ ይጠበቃል፡፡ሶስት የኮንስትራክሽን ድርጅት ስራ አስፈፃሚዎች እሳቱ በፍጥነት እንዲዛመት አስችለዋል ከሚባሉ ተቀጣጣይ ቁሶች ጋር ተያይዞ በሰው ግድያ ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል።የቻይና ኩባንያዎች እሳት አደጋዉን በቁጥጥር ስር ለማዋል እና የማገገሚያ ጥረቶችን ለማገዝ የገንዘብ ድጋፍ እየሰጡ ይገኛል፡፡
የስፖርት አልባሳት ኩባንያ አንታ ግሩፕ በጥሬ ገንዘብ እና በመሳሪያ የ3.8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለግሷል።የሸማቾች ቴክኖሎጂ ኩባንያ ዢኦሚ 10 ሚሊዮን የሆንግ ኮንግ ዶላር ድጋፍ ሲለግስ የቲክ ቶክ የወላጅ ኩባንያ ባይትዳንስ 10 ሚሊዮን የሆንግ ኮንግ ዶላር እንዲሁም የአሊባባ መስራች ጃክ ማ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጃክ ማ ፋውንዴሽን 30 ሚሊዮን የሆንግ ኮንግ ዶላር ለመስጠት ቃል ገብተዋል፡፡
በሆንግ ኮንግ ያለው ስሜት ከድንጋጤ ወደ ቁጣ ተቀይሯል፣ ለቃጠሎው ተጠያቂው ማን ነው የሚለው ጥያቄዎች እየጨመሩ ይገኛል፡፡በተለይ በርካታ ነዋሪዎች እሳቱ ሲነሳ የእሳት ማስጠንቀቂያ እንዳልሰሙ በቃለ መጠይቅ ከተናገሩ በኋላ ቁጣው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተስፋፋ መጥቷል።ባለፈው ዓመት በህንጻዎቹ እድሳት እቅድ ላይ ነዋሪዎች ያቀረቡት ቅሬታዎችም እንደገና ብቅ ብለዉ መሰማት ጀምረዋል፡፡
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
😱 10❤ 8🕊 3😭 3👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በሀሰተኛ የቴሌግራም አካውንት የአመራሮችን ፎቶ በመጠቀም ችግር ገጥሟቸው ሆስፒታል ሰው እያስታሙ ነው በማለት ነጋዴዎችን ገንዘብ ሲያስልኩ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ስውር የቴለግራም አካውንት በመክፈት በአመራር ስም ከንግዱ ማህበረሰብ ገንዘብ ሲሰበስቡ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ግለሰቦቹ የአመራሮችን ፎቶ ፕሮፋይል በማድረግ የቴሌግራም ፌክ አካውንት በመክፈት ሃሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨትና አመራሩ ማህበራዊ ችግር ገጥሞት ገንዘብ እንደሚያስፈልገውና ገንዘብ እንዲልኩ በመግለጽ ከንግዱ ማህበረሰብ ገንዘብ ሲሰበስቡ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሚዛን አማን ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ምናሉ ታደሰ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
አጭበርባሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋልና ለህግ የማቅረቡ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የገለጹት ኮማንደር ምናሉ ህብረተሰቡ በተለይ የንግዱ ማህበረሰብ ከነዚህ አጭበርባሪዎች ራሱን መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል።
ይህን መሰል የማጭበርበር ወንጀል ሲገጥም ማህበረሰቡ ለፖሊስ ጥቆማ መስጠት እንዳለበት የተገለጸ ሲሆን በተለይ ከገቢ፣ ንግድና ሌሎች አመራሮችን ፎቶ ፕሮፋይል በመጠቀም ነጋዴውን የማታለል ስራ መስራት በዘርፉ የሚሰሩ አመራሮችን ስም የማጥፋት ተግባር በመሆኑ ወንጀለኞችን ለህግ የማቅረቡ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ሚዛን አማን ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ምናሉ ታደሰ ከብስራት ሬዲዮ በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል።
ሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 17😁 17👍 5🤔 3🤣 2
Photo unavailableShow in Telegram
የናይጄሪያ ተማሪዎች ከታገቱ ከአንድ ሳምንት በኃላ 24ቱ ተለቀቁ
ከአንድ ሳምንት በፊት ከአዳሪ ትምህርት ቤታቸው ታፍነው ከተወሰዱት ተማሪዎች መካከል 24ቱ የናይጄሪያ ልጃገረዶች መፈታታቸውን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አስታወቁ።የታጠቂ ቡድን አባላት በናይጄሪያ ኬቢቢ ግዛት የመንግስት ልጃገረዶች አጠቃላይ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በወረሩበት ወቅት አንድ ሰራተኛ ገድለው 25 ተማሪዎችን አግተዋል። አንደኛዋ ተማሪ ብዙም ሳትቆይ ማምለጥ ችላለች።
የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኒዩ የጸጥታ ሃይሎችን ለችግሩ “ፈጣን ምላሽ” መስጠታቸዉን አመስግነዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ በሰጡት መግለጫ ግን እንዴት የታገቱት ተማሪዎች ሊለቀቁ እንደቻሉ ግልፅ አላደረጉም።በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ቀዳሚ በሆነችዉ ናይጄሪያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሰዎች እገታ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፡፡ ባለፈው አርብ ከ250 በላይ ሕፃናት ከካቶሊክ ትምህርት ቤት ታግተው እስካሁን ድረስ የደሰረሱበት አልታወቀም፡፡
የፕሬዚዳንቱ ልዩ አማካሪ በሰጡት መግለጫ በኬቢ ግዛት ከሚገኙት ትምህርት ቤቶች የተወሰዱ ልጃገረዶች በሙሉ ተጠያቂ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፣ ክስተቱ በሌሎች ሁለት የናይጄሪያ ግዛቶች መፈጸሙን ጠቁመዋል። አማካሪዉ ኒኒፉ እንዳሉት ተጨማሪ የአፈና አደጋዎችን ለመከላከል የጸጥታ ኃይሎች ወደ ተጋላጭ አካባቢዎች እንደሚሰማሩ ተናግረዋል ።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 16
Photo unavailableShow in Telegram
በዛሬው እለት ሁለት ሰዎች በማርበርግ ቫይረስ ህይወታቸው ሲያልፍ ፤ሁለት ሰዎች አገግመዋል ተጨማሪ ሁለት ሰዎችም በቫይረሱ ተይዘዋል
#ዳጉ_ጆርናል
😭 22❤ 6🙏 2
በአዲስ አበባ ያለደረሰኝ ጭነት በመያዝ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 907 የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በመዲናዋ ባለፉት አራት ወራት ከ5 ሺህ በላይ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የደረሰኝ ቁጥጥር በመካሄድ ከ954 ሚሊዮን ብር በላይ ደረሰኝ እንዲቆረጥ ማድረጉን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት አራት ወራት በ5 ሺህ 203 የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪዎች ላይ የደረሰኝ ቁጥጥር ማካሄዱን ገልፆል፡፡
የደረሰኝ ቁጥጥሩ በሁሉም የከተማዋ አቅጣጫዎች ወደ ከተማዋ በሚገቡ፣ከከተማዋ በሚወጡና በከተማዋ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ፣ሚኒባሶችና አነስተኛ ሽፍን መኪኖች ላይ እየተካሄደ ነው፡፡በዚህም ያለደረሰኝ ጭነት በመያዝ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 907 የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን 1 ሺህ 39 ግብር ከፋዮች ደረሰኝ እንዲቆርጡ 997 ግብር ከፋዮች ላይ ደግሞ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በተደረገው የቁጥጥር የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪዎቹ የጫኗቸው ሸቀጦች ላይ የ954 ሚሊዮን 803 ሺህ ብር ደረሰኝ እንዲቆረጥባቸው ለማድረግም ተችሏል፡፡በአሁኑ ወቅትም የደረሰኝ ቁጥጥሩ በቀን ብቻም ሳይሆን በለሊት ጭምር ተጠናክሮ መቀጠሉ የተገለፀ ሲሆን ደረሰኝ ሳይዙ ሸቀጥ በመጫን በሚንቀሳቀሱ ተሸከርካሪዎች ላይ ከሚወሰድ አስተዳደራዊ እርምጃ በተጨማሪ በቀጣይ የደረቅ ጭነት አሽከርካሪዎቻቸው ላይም የህግ ተጠያቂነት እንዲሰፍን የሚደረግ መሆኑ ቢሮዉ አስታውቋል።
#ዳጉ_ጆርናል
👎 26❤ 10
በኒውዚላንድ ሁለት ልጆቿን በመግደል ሻንጣ ዉስጥ ደብቃለች የተባለችዉ እናት በእድሜ ልክ እስራት ተቀጣች
በኒውዚላንድ ሁለት ልጆቿን ገድላ አስከሬናቸውን በሻንጣ የደበቀችው እናት በእድሜ ልክ እስራት ተቀጣች።በሴፕቴምበር ወር የስምንት ዓመቷ ዩና ጆ እና የስድስት ዓመቷ ሚኑ ጆ አስደንጋጭ ግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ሆና የተገኘችው ሃኪዩንግ ሊ፣ ለይቅርታ ብቁ ሆና ከመጠየቋ በፊት ቢያንስ 17 አመታትን በእስር ቤት መቆየት እንዳለባት ተወስኗል፡፡
የ45 ዓመቷ ሊ እ.ኤ.አ በ2018 ግድያ በተፈፀመበት ወቅት የአእምሮ የጤና ችግር እንደነበረባት ተከራክራለች፣ ይህ የሆነው ባለቤቷ ከሞተ ብዙም ሳይቆይ ነበር። የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ጂኦፍሪ ቬኒንግ እንዳሉት የሊ የአእምሮ ጤና በጉዳዩ ላይ ድርሻ ነበረው፣ ነገር ግን የወንጀል ድርጊቷ የተሰላ ነው ብለዋል።የልጆቹ አስከሬን የተገኘው እ.ኤ.አ. በ 2022 በኦክላንድ ውስጥ የሚገኘዉን መኖሪያ ቤት በጨረታ ባሸነፉ ጥንዶች የተነሳ ነው።
ከሁለት ሳምንት በላይ በዘለቀው የፍርድ ሂደት የሃኪዩንግ ሊ ተከላካይ ጠበቆች ባለቤቷ ጆ ከሞተ በኋላ የአእምሮ ጤንነቷ መባባሱን እና የተቀሩት ቤተሰቦች አብረው ቢሞቱ ጥሩ እንደሆነ አምናለች ብለዋል።ሊ ራሷን እና ልጆቿን በጁስ ውስጥ የተቀላቀለውን ኖርትሪፕቲላይን የተባለውን የጭንቀት መድሀኒት በከፍተኛ መጠን በመስጠት ራሷን ለመግደል ሞክራለች ፣ነገር ግን መጠኑን ተሳስታ ከእንቅልፏ ስትነሳ ልጆቿ ሞተው እንዳገኘቻቸዉት ጠበቆቿ ተናግረዋል።
አቃቤ ህግ ግን የሊ ድርጊት "እራሷን ከወላጅነት ሸክም ብቻ ለማላቀቅ የራስ ወዳድነት ተግባር" ነው ሲሉ ተከራክሯል።ከግድያው በኋላ ሊ ስሟን ቀይራ ኒውዚላንድን ለቅቃ ወጥታለች። ከተሸሸገችበት የትዉልድ ሀገሯ ደቡብ ኮሪያ ተይዛ በዚያው ዓመት ወደ ኒው ዚላንድ ተላልፋ ተሰጥታለች። የሊ እናት ቾን ጃ ሊ በህዳር 2017 የልጄ ባለቤት በካንሰር ከሞተ በኋላ "የመኖር ፍላጎት እንዳልነበራት" በመግለጽ ልጄን ወደ አማካሪ ባለወሰዴ ተጸጽቻለዉ በማለት በአቃቤ ህግ በተነበበ ስሜታዊ መግለጫ ላይ ሀሳቧ ተገልጿል፡፡
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
💔 14❤ 13
በኒውዚላንድ ሁለት ልጆቿን በመግደል ሻንጣ ዉስጥ ደብቃለች የተባለችዉ እናት በእድሜ ልክ እስራት ተቀጣች
በኒውዚላንድ ሁለት ልጆቿን ገድላ አስከሬናቸውን በሻንጣ የደበቀችው እናት በእድሜ ልክ እስራት ተቀጣች።በሴፕቴምበር ወር የስምንት ዓመቷ ዩና ጆ እና የስድስት ዓመቷ ሚኑ ጆ አስደንጋጭ ግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ሆና የተገኘችው ሃኪዩንግ ሊ፣ ለይቅርታ ብቁ ሆና ከመጠየቋ በፊት ቢያንስ 17 አመታትን በእስር ቤት መቆየት እንዳለባት ተወስኗል፡፡
የ45 ዓመቷ ሊ እ.ኤ.አ በ2018 ግድያ በተፈፀመበት ወቅት የአእምሮ የጤና ችግር እንደነበረባት ተከራክራለች፣ ይህ የሆነው ባለቤቷ ከሞተ ብዙም ሳይቆይ ነበር። የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ጂኦፍሪ ቬኒንግ እንዳሉት የሊ የአእምሮ ጤና በጉዳዩ ላይ ድርሻ ነበረው፣ ነገር ግን የወንጀል ድርጊቷ የተሰላ ነው ብለዋል።የልጆቹ አስከሬን የተገኘው እ.ኤ.አ. በ 2022 በኦክላንድ ውስጥ የሚገኘዉን መኖሪያ ቤት በጨረታ ባሸነፉ ጥንዶች የተነሳ ነው።
ከሁለት ሳምንት በላይ በዘለቀው የፍርድ ሂደት የሃኪዩንግ ሊ ተከላካይ ጠበቆች ባለቤቷ ጆ ከሞተ በኋላ የአእምሮ ጤንነቷ መባባሱን እና የተቀሩት ቤተሰቦች አብረው ቢሞቱ ጥሩ እንደሆነ አምናለች ብለዋል።ሊ ራሷን እና ልጆቿን በጁስ ውስጥ የተቀላቀለውን ኖርትሪፕቲላይን የተባለውን የጭንቀት መድሀኒት በከፍተኛ መጠን በመስጠት ራሷን ለመግደል ሞክራለች ፣ነገር ግን መጠኑን ተሳስታ ከእንቅልፏ ስትነሳ ልጆቿ ሞተው እንዳገኘቻቸዉት ጠበቆቿ ተናግረዋል።
አቃቤ ህግ ግን የሊ ድርጊት "እራሷን ከወላጅነት ሸክም ብቻ ለማላቀቅ የራስ ወዳድነት ተግባር" ነው ሲሉ ተከራክሯል።ከግድያው በኋላ ሊ ስሟን ቀይራ ኒውዚላንድን ለቅቃ ወጥታለች። ከተሸሸገችበት የትዉልድ ሀገሯ ደቡብ ኮሪያ ተይዛ በዚያው ዓመት ወደ ኒው ዚላንድ ተላልፋ ተሰጥታለች። የሊ እናት ቾን ጃ ሊ በህዳር 2017 የልጄ ባለቤት በካንሰር ከሞተ በኋላ "የመኖር ፍላጎት እንዳልነበራት" በመግለጽ ልጄን ወደ አማካሪ ባለወሰዴ ተጸጽቻለዉ በማለት በአቃቤ ህግ በተነበበ ስሜታዊ መግለጫ ላይ ሀሳቧ ተገልጿል፡፡
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
የጣና ሀይቅ እና ገዳማትን በአለም አቀፍ ቅርስነት ለማስመዝገብ የዮኔስኮ ቡድን ለሚያደርገው ግምገማ ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ነዉ ተባለ
በአማራ ክልል የሚገኙ የመስህብ ሀብቶችን በማልማትና በማስተዋወቅ የባህልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪውን በማሳደግ የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሚገኝ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ እምቢአለ ለብስራት ሬዲዮ አንደተናገሩት የጣና ሀይቅ፣ ደሴተ ገዳማትን እና አዋሳኝ ባህር ሸሽ መልክአ ምድር የተፈጥሮ እና የባህል መካነ ቅርስን በዩኔስኮ አለም አቀፍ ቅርስነት መዝገብ ውስጥ እንዲሰፍሩ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል።
ከጉዳዮ ጋር በተያያዘ የአለም አቀፍ ቅርስ መምረጫ ሰነድ እና የቅርስ አስተዳደር እቅድ ዝግጅት ስራዎችን ቢሮው ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን እንዲሁም ከአንድ የሆቴልና ቱሪዝም አማካሪ ድርጅት ጋር በመተባበር ሲያከናውን መቆየቱ ይታወሳል።እንደዚሁም የጣና ሀይቅ ደሴት ገዳማትና አዋሳኝ ባህር ሸሽ መልክአ ምድር ባህላዊና ተፈጥሮአዊ ቅርሶች ስር የተከለሉ ስፍራዎችን ሊያመለክት የሚያስችል ረቂቅ ደንብን ለማዘጋጀት ጥረት ሲደረግ እንደነበር ቢሮው ማስታወቁ አይዘነጋም።
አሁን ላይ ይህን ስፍራ በቅርስነት ለማስመዝገብ እንዲቻል የዩኔስኮ ገምጋሚ ቡድን ከመምጣቱ በፊትና በግምገማው ወቅት የሚከናወኑ ተግባራት ተለይተዋል ሲል ቢሮው አስታውቋል ።በግምገማው ወቅት የተለዮት ተግባራትም ባለቤት ተሰጥቶቸው እየተሰሩ ይገኛሉ በማለት አቶ አበበ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል ፡፡
በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 15👎 6👍 3
የዩክሬን ሩሲያ የሰላም እቅድ በጥቂት አለመግባባቶች ላይ ብቻ ተሻሽሏል ሲሉ ትራምፕ ተናገሩ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የሰላም ስምምነት እንዲፈጠር መገፋፋትን የቀጠሉ ሲሆን ባለፈው ወር በሁለቱም ወገኖች ጦርነት ቢያንስ 25 ሺ ወታደሮች መሞታቸውን ተናግረዋል ።ትራምፕ በዩናይትድ ስቴትስ የተነደፈው የመጀመሪያው ባለ 28 ነጥብ የሰላም እቅድ አሁን "ከሁለቱም ወገኖች ተጨማሪ ግብአት ጋር በጥሩ ሁኔታ ተስተካክሏል እና ጥቂት የቀሩት አለመግባባቶች አሉ" ብለዋል ።
ትራምፕ በማህበራዊ ድረ-ገጽ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት "የሰላም ሂደቱ በተቻለ ፍጥነት እንደሚጠናቀቅ ሁላችንም ተስፋ እናድርግ" ብለዋል፡፡ባለፈው ሳምንት በትራምፕ አስተዳደር የተደገፈዉ ባለ 28 ነጥብ የሰላም ሃሳብ ከዩክሬን እና ከአውሮጳ አጋሮች የሩስያን ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ የተቀበለ ለሞስኮ ያዘነበለ የሰላም እቅድ በሚል ትችት ቀርቦበት እንደነበር ይታወሳል።ዕቅዱ ከዚያ በኋላ ተሻሽሏል ቢባልም በዉስጡ የሰፈረዉ ጽሑፉ ግን ገና ይፋ አልተደረገም፡፡
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮልደሚየር ዜለንስኪ ኪየቭ በአዲሱ ረቂቅ መሰረት “ወደ ፊት ለመራመድ” ተዘጋጅታለች ይህ የሚሆነዉ ግን በሰላም እቅዱ ላይ “አስደንጋጭ ነጥቦች” እስካልተገኙ ድረስ ብቻ ነዉ ብለዋል።በሌላ በኩል ትራምፕ ከፑቲን ጋር ለመነጋገር መልዕክተኛውን ስቲቭ ዊትኮፍን ወደ ሩሲያ በመላክ “ስምምነት ላይ እየደረስን ነው” ብለዋል።የአዲሱ እቅድ ይዘት ዝርዝር መረጃ በጣም አናሳ ነው፣ ነገር ግን በርካታ ቁልፍ ነጥቦች ካለፈው ሳምንት አንጻር ተቀይረዋል ተብሏል፡፡የዩክሬን ሀይሎችን ከዶንባስ ክልል ማስወጣትን እቅዱ አያካትትም ፤ ነገር ግን ኪየቭ የኔቶ አባል እንድትሆን እና ወታደራዊ ኃይሏን እንድትቀጥል ይፈቅዳል ስትል የአልጀዚራዋ ዩሊያ ሻፖቫሎቫ ዘግባለች።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 9👍 2😁 2
Photo unavailableShow in Telegram
የዉጪ ሀገር ቱሪስቶች ክፍያን በዶላር መፈፀማቸዉ ከዘርፉ የሚገኘው ገቢ ከዕቅድ በላይ እንዲሆን አድርጓል ተባለ
የአርባምንጭ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ባለፉት 3 ወራት ከቱሪስቶች የተገኘዉ ገቢ ከዕቅድ በላይ መሆኑን ገልጿል ።ወደ ከተማዋ የሚመጡ ቱሪስቶችን ቁጥር ለመጨመር ሲሰራ መቆየቱ የተገለፀ ሲሆን ባለፉት 3 ወራት የዉጪ ሀገር ቱሪስቶችን ፍሰት ወደ 10ሺህ ለማሳደግ ታቅዶ 5ሺህ 155 መከናወኑ ተገልጿል ።
በተመሳሳይ መልኩ የሀገር ዉስጥ ጎብኚዎችን ፍሰት ወደ 75 ሺህ ለማሳደግ ታቅዶ 58ሺህ 695 ቱሪስቶች ጉብኝት ማድረጋቸዉ ተነግሯል። ከዉጪ ሀገር ቱሪስቶች 20 ሚሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ የነበረ ሲሆን ከሆቴሎች ፣ሎጆች ፣ሪዞርቶችና ፔንሲዮኖች ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት የልማት ዕቅድ ባለሙያ ህይወት ወንድሙ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
ገቢዉ ከዕቅድ በላይ የጨመረበት ምክንያት የዉጪ ሀገር ቱሪስቶች በዶላር ክፍያ መፈፀማቸዉ መሆኑን ባለሙያዋ አንስተዋል ። ከሀገር ዉስጥ ጎብኚዎች የሚገኝ ገቢ 58 ሚሊዮን ብር ታቅዶ የነበረ ሲሆን ባለፉት 3 ወራት ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱ የተገለፀ ሲሆን ይህም ሊሆን የቻለዉ በከተማዋ የሚካሄዱ ስልጠናዎች እና ስብሰባዎች ረዘም ያለ ቆይታ ስለሚኖራቸው ነዉ ተብሏል ።
በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 9😁 2
