ar
Feedback
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

الذهاب إلى القناة على Telegram

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

إظهار المزيد
2025 عام في الأرقامsnowflakes fon
card fon
44 133
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
-22730 أيام
أرشيف المشاركات
የተባበሩት መንግስታት በ2026 ዓመት የሰዉ ኃይሉን በመቀነስ በጀቱን በ577 ሚሊዮን ዶላር ይቀንሳል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እንደተናገሩት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ2026 በጀቱን 15.1 በመቶ እና ሰራተኞቹን በ18.8 በመቶ እንደሚቀንስ ተናግረዋል፡፡ ከአባል ሀገራት ያልተከፈለ ክፍያ ወደ 1.59 ትሪሊየን ዶላር ከፍ ብሏል ሲሉ አክለዋል።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሃላፊ የሚቀጥለውን አመት በጀት ያሳወቁ ሲሆን ከ2025 ዓመት በ577 ሚሊዮን ዶላር የቀነሰ በ 3.24 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን ይፋ አድርገዋል፡፡ ከሴፕቴምበር ጀምሮ ቅናሹ የመጣው ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ከቻይና፣ ከሩሲያ እና ከሜክሲኮ ያልተከፈለ ክፍያ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መግለጫ አመልክቷል።ጉቴሬዝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ ከፍተኛ ፍላጎት ምክንያት ወጪዉ እንደተጠበቀ ይቆያል ብለዋል ። ጉሬሬዝ “በጋዛ በተደረገው አጠቃላይ የሰብአዊ ምላሽ ላይ ተጽእኖ ከሚያስከትሉ ማናቸውም ቅነሳዎች የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲን ነፃ ለማድረግ ወስኛለሁ” ብለዋል ።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበርካታ የተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎች ውስጥ 2,681 የስራ መደቦችን ይቀንዳል ፣ “በእኛ አስተያየት ፣ በሌሎች በተሻለ ሊከናወኑ ወይም በቅልጥፍና ሊተገበር ከሚችሉ እንቅስቃሴዎች ጋር ይዛመዳሉ” ብለዋል ። ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስራ መደቦች ውስጥ 18 በመቶ ያህሉ ያልተከፈሉ የአባላት መዋጮ እና ሌሎች እዳዎች እየተከሰቱ ባለበት የፈጣን ችግር ምክንያት ክፍት ናቸው ሲሉ ዋና ፀሃፊው ተደምጠዋል። “እነዚያ ክፍት ቦታዎች በስትራቴጂካዊ ቅድሚያ ከሚሰጠው ፖለቲካዊ ውሳኔ ጋር አይዛመዱም ፣ ግን በቀላሉ ሰዎች በመልቀቃቸው እና በቀውስ ምክንያት ተተኪውን ለመክፈል የሚያስችል ገንዘብ የለንም” ብለዋል ። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
14👎 4
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
👉 ከአምስት ቀናት በኃላ አንድ በማርበርግ ቫይረስ የተያዘ ሰው ተገኘ 👉 ለአምስት ተከታታይ ቀናቶች በነበረው የምርመራ ውጤቶች  በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸው ሁሉም ነፃ እንደነበሩ ያሳያል። 👉 በዚህም መሰረት ዛሬ ህዳር 23/ 2018 የማርበርግ ቫይረስ በተደረገው ምርመራ 221 ሰዎች የተመረመሩ ሲሆን 1 ሰው በቫይረሱ ተይዟል። 👉ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 4 የደረሰ ሲሆን 3 ከሆስፒታሉ ወጥተዋል ። 👉አሁን ላይ አንድ ሰው በህክምና ላይ እንዳሉ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። 👉 በአጠቃላይ እስካሁን 888 ሰዎች ተመርምረው 13 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 8ቱ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል። 👉 በተጨማሪም አንዱ በህክምና ላይ ያሉት ታማሚ ከዚህ በፊት ከተገለፀው ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጂንካ ከተማ በለይቶ ማቆያ የነበሩ ሲሆኑ በተመሳሳይ ቦታም የህክምና ክትትላቸውን እያደረጉ እንደሚገኝ ብስራት ሬዲዮ ከጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
12🙏 2
ለኩላሊት እጥበት ህክምና አገልግሎት የጤና መድህን ሽፋን አይሰጥም ተባለ     👉 በኢትዮጵያ 84 በመቶ የሚሆነው ህዝብ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና ተጠቃሚ ሆኗል በተለያዩ አጋጣሚዎች  ለውጪ ሀገር ህክምና ፤በስራ ተቋማት ውስጥ ለሚያጋጥሙ አደጋዎች ፤ሶስተኛ ወገን ሽፋን ያላቸው ፤ ለኩላሊት እጥበት ታካሚዎች እና ለውበት መጠበቂያ ለሚወጡ ህክምናዎች በጤና መድህን ሽፋን ማግኘት  እንደማይቻል የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት አስታውቋል ፡፡ የጤና እክል አጋጥሞት ወደ ውጪ ሀገር ሄዶ እንዲታከም ለሚደረግ ታካሚ በጤና መድህን የተሰበሰበውን ገንዘብ አንድ ሰው ላይ ማዋል እንደሆነ እና ፍትሀዊ አገልግሎት አሰጣጥ  እንደማይሆን ለብስራት ሬዲዮ የተናገሩት በኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት የዋና ዳይሬክተር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳምጠው ጥላሁን ናቸው፡፡እንዲሁም ለኩላሊት ህመምተኞች ለሚደረግ የእጥበት አገልግሎት ላይም የጤና አገልግሎት የጤና መድህን ሽፋን መስጠት አስቸ ጋሪ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ከእነዚህ ህክምናዎች ውጪ ግን ምንም አይነት የገንዘብ ገደብ ሳይደረግ የጤና መድህን ተጠቃሚዎች የህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡ በኢትዮጵያ በአሁን ጊዜ 84 በመቶ የሚሆነው ህዝብ የማህበረሰብ አቀፍ ተጠቃሚ ሆኗል፡፡የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት በ1ሺ195 ወረዳዎች ስር  ከ4ሺ347 ጤና ተቋማት ጋር  ውል በማሰር  የጤና ተቋማቱ ለማህበራዊ ጤና መድህን ተጠቃሚዎች የዱቤ አገልግሎት እንዲሰጡ ያደርጋል፡፡ በመጨረሻም ኦዲት ተደርጎ  ለጤና ተቋማቱ ክፍያው እንደሚፈፀምላቸው ገልፀዋል ፡፡በ2018 ዓ.ም ደግሞ የወረዳ ሽፋኑን አሳድጎ ለ1ሺ320 ወረዳ  የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ማቀዱን በኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት የዋና ዳይሬክተር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ዳምጠው ጥላሁን ጨምረው ተናግረዋል፡፡ በምህረት ታደሰ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ሚስቱንና ጎረቤቱን ገድሎ የተሰወረውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ህዳር 04 እና 05 ቀን 2018 ዓ/ም በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ልዩ ቦታው 23 ቀበሌ መዝናናኛ ክበብ አካባቢ ነው፡፡ ተከሳሽ እሱያውቃል ቢያዝን ከባለቤቱ ከወ/ሮ ሐመልማል አለምነው ጋር በትዳር ተጣምረው መኖር ከጀመሩ አራት ወራትን አስቆጥረዋል፡፡ ተጠርጣሪው ባለቤቱን ከሌላ ወንድ ጋር ስልክ ትደዋወያለሽ ከሌላ ሰው ፍቅር ጀምረሻል በሚል አጉል ጥርጣሬ ህዳር 4 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 4 ሠዓት አንገቷን አንቆ በመግደል ህይወቷ እንዲያልፍ በማድረግ በር ዘግቶባት ከአካባቢው ይሰወራል፡፡ በተጨማሪም ከአንድ ቀን በኋላ ህዳር 05 ቀን 2018 ዓ/ም ወደ መኖሪያ ግቢው ተመልሶ በመምጣት የ2 ልጆች አባት የሆነውን ወርቁ በቀለን ከምሽቱ 1ሰዓት በመኖሪያ ቤት ውስጥ በስምንት ጥይት ተኩሶ በመግደል ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረግ ከአካባቢው ይሰወራል፡፡ የአቶ ወርቁ በቀለ በጥይት ተመተው መሞት መረጃ የደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራና ክትትል ክፍል የወንጀል ስፍራው ላይ በመገኘት እና መረጃ በማሰባሰብ ላይ ባሉበት ሁኔታ የገዳይ መኖሪያ ቤት ውስጥ ሰው መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ ሙከራ ሲደረግ መኖሪያ ቤቱ ውስጥ የሐመልማል አለምነው አስከሬንም ሊገኝ ችሏል፡፡ ወንጀል ፈፃሚውን በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ሞላሌ ከተማ ከተደበቀበት አልጋ ቤት ውስጥ የግድያ ወንጀሉን ከፈፀመበት ኢኮልፒ ሽጉጥ እና ከ23 ጥይቶች ጋር ህዳር 19 ቀን 2018 ዓ/ም በቁጥጥር ስር ሊያውለውም ችሏል፡፡ ግለሰቡ የወንጀል አፈፃጸሙን አስመልክቶ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ/ም መርቶ ማሳየቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል። ምንጭ:- አ.አ ፖሊስ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
💔 25 15👏 3
የሰላሌ ዩኒቨርስቲ ከ 3ሺህ በላይ ለሚሆኑ  አቅመ ደካማ የሕብረተሠብ ክፍሎች የነፃ የሕግ አገልግሎት መስጠቱን አስታወቀ የሰላሌ ዩኒቨርስቲ የሕግ አገልግሎት ለሚያስፈልጋቸው ሶስት ሺ አራት መቶ ዘጠና ስድስት  አቅመ ደካማ የማህበረሰብ አካላት የተለያዩ የሕግ አገልግሎት ሰጥቷል። የዩኒቨርስቲ የሕግ አገልግሎት ዲን አቶ አቤል ከተማ እንደገለፁት የነፃ የሕግ አገልግሎቱ የተሰጠው አቅመ ዳካማ ለሆኑ ፣ በእድሜ ለገፉ፣ ጥቃት ለደረሠባቸው ሴቶች ና ሕፃናት፣በከፍተኛ ሕመም ለሚገኙ እና በማረሚያ ቤት ሆነው የፍርድ ሂደታቸውን ለሚከታተሉ ታራሚዎች የነፃ የሕግ አገልግሎት ነው ብለዋል። በዚህም ለሁለት ሺህ ሠባት መቶ ሀምሳ ስድስት ወንዶች እንዲሁም ለሰባት መቶ አርባ ሴቶች አገልግሎቱ ተሰጥቷል። በነፃ አጉልግሎቱ ስድስት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ ብር ከወጪ ማዳን የተቻለ ሲሆን የሰላሌ ዪኒቨርስቲ በስሩ የሚተዳደሩ አራት ቋሚ የሕግ አገልግሎት መስጫና  እና አንድ ተንቀሳቃሽ  የሕግ ማዕከል አቋቁሞ በመንቀሣቀስ በተለየ መልኩ በሕፃናት እና ሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን እንደዚሁም ያለ እድሜ ጋብቻ፣የቤተሰብ ግጭቶች እና ትንኮሳዎች ላይ  ሰፊ የሕግ መሰረት ያደረገ አገልግሎት መስጠቱን አቶ አቤል ከተማ ጨምረው ገልፀዋል:: ፆታዊ ጥቃትን በተመለከተ ከጋብቻ ውጭ የተወለዱ እና የሚጣሉ ሕፃናት ማቆያ ለመገንባት ከፍትህ አካላት ጋር የጋራ ስምምነት የተደረሠ ሲሆን ባለፈው አመት ሶስት ሕፃናት ተጥለው የተገኙትን የሠላሌ ዩኒቨርስቲ ተረክቦ በአበበች ጐበና ካምፖሱ ባለው ጊዚያዊ ማቆያ በማቆየት በሕጋዊ መንገድ ለጉዲፈቻ ተሰጥተዋል። በዩኒቨርስቲ ውስጥ የሴት ተማሪዎች ላይ የሚደርሰውን ትንኮሳ እና ጥቃት ለመከላከልም የተቋቋመ ኮሚቴ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ሲሆን በአጠቃላይ የፍትሕ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት የተደረገው ስምምነት ከፍተኛ ውጤት እንደሚያመጣም ተመላክቷል። በሰብል አበበ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
12👏 3🤔 1👌 1
Photo unavailableShow in Telegram
የዩናይትድ ስቴትስ የጅምላ ግድያ በ2025 ዓመት ባለፉት 20 ዓመታት ከተመዘገበዉ ዝቅተኛ ሆነ በዩናይትድ ስቴትስ በ 2025 ዓመት ከሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ዝቅተኛው የጅምላ ግድያ ተመዝግቧል ሲል እንደዚህ ያሉ ክስተቶችን የሚከታተል የመረጃ ቋት ይፋ አድርጓል።በቅርቡ በስቶክተን ካሊፎርኒያ በተደረገ የቤተሰብ ስብሰባ ላይ አራት ሰዎችን የገደለው ተኩስ በዚህ አመት 17ኛው የጅምላ ግድያ መሆኑን አሶሺየትድ ፕሬስ ከዩኤስኤ ቱዴይ እና ከኖርዝ ኢስት ዩኒቨርሲቲ ጎን ለጎን የመረጃ ቋቱን የሚይዘው  አካል ማክሰኞ ዘግቧል። ይህ አሃዝ ግን ገና የታህሳስ ወር ባለመጠናቀቁ ሊጨምር ቢችልም፣ ከ2019 ከነበረዉ 59 በመቶ የሚጠጋ ቅናሽ አለዉ፡፡ በ2019 ዓመት ሪከርድ የሆነው 41 የጅምላ ግድያ ተመዝግቧል። የመረጃ ቋቱ የጅምላ ግድያዎችን ለመከታተል የፖሊስ እና የኤፍቢአይ ዘገባዎችን፣ የሚዲያ ዘገባዎችን እና የፍርድ ቤት መዝገቦችን ይጠቀማል፣ እነዚህ ክስተቶች መደበኛ ወንጀለኛን ሳይጨምር አራት እና ከዚያ በላይ ሰዎች ሆን ተብሎ በ24 ሰአት ውስጥ የተገደሉበት ክስተትን የሚያካትት ነው። የመረጃ ቋቱን የሚያስተዳድረው የኖርዝ ኢትስ ዩኒቨርሲቲ የወንጀል ተመራማሪ የሆኑት ጀምስ አላን ፎክስ ለአሶሺየትድ ፕሬስ እንደተናገሩት የ2025 የተመዘገበው ውጤት ከ2024 ጋር ሲነፃፀር በ24 በመቶ ቀንሷል፣ በተጨማሪም ከ2023 ጋር ሲነጻጸር የ20 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።የቁጥሩ ማሽቆልቆል የስታቲስቲክስ ባለሙያዎች "ወደ አማካይ መመለሻ" ብለው የሚጠሩት ሊሆን እንደሚችል ተናግሯል፣ ይህም ባለፉት ዓመታት ያልተለመደው ጭማሪ ወደ አማካይ የወንጀል ደረጃዎች መመለስን ያሳያል።እ.ኤ.አ. በ2025 በአሜሪካ ከተፈጸሙት የጅምላ ግድያዎች 82 በመቶ ያህሉ ከጦር መሳሪያ ጋር የተያያዙ ናቸው።የመረጃ ቋቱ በ2006 ከተከፈተ ጀምሮ 3,234 ሰዎች በጅምላ ሲገደሉ 81 በመቶ ያህሉ ተጎጂዎች ተተኩሶባቸዋል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
10
1
Photo unavailableShow in Telegram
ባለፉት ሶስት ወራት አክሱም ዩንቨርስቲ ኮምፕርሄሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 453 ዋና ዋና ቀዶ ህክምና መስጠቱን አስታወቀ በአክሱም ዩኒቨርስቲ ኮምፕርሄሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ላለፉት ሶስት ወራት የዋና ቀዶ  ህክምና አገልግሎት ያገኙ 453 ታካሚዎች መሆናቸውን ሆስፒታሉ አስታውቋል። እንዲሁም 42 ሺህ 831 ጠቅላላ በተመላላሽ የህክምና አገልግሎት ያገኙ ታካሚዎች በሆስፒታሉ አገልግሎት እንዳገኙ የአክሱም ዩንቨርስቲ ኮምፕርሄሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ፀጋዬ ተክለሀይማኖት ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በተጨማሪም በሆስፒታሉ 35ሺህ ታካሚዎች የላብራቶሪ አገልግሎት ማግኘታቸውን እንዲሁም ጠቅላላ ተኝቶ ማከሚያ ውስጥ ደግሞ 1ሺህ 544 ታካሚዎች አገልግሎት እንዳገኙ ገልጸዋል፡፡ ሆስፒታሉ በበጀት አመቱ ከ24 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ለማስገባት ማቀዱንም የአክሱም ዩንቨርስቲ ኮምፕርሄሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ፀጋዬ ተክለሀይማኖት ለብስራት ሬዲዮ ጨምረው ተናግረዋል። በሰመሀር አለባቸው #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
22👎 1
የኤል ቻፖ ልጅ በአሜሪካ የአደንዛዥ ዕፅ ክስ ጥፋተኛ ነኝ ሲል ተናገረ የሜክሲኮ የአደንዛዥ ዕፅ ንጉስ ልጅ የሆነው ጆአኩዊን "ኤል ቻፖ" ጉዝማን ልጅ ጆአኩዊን ጉዝማን ሎፔዝ በቺካጎ ፍርድ ቤት በሁለት የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች እና የተደራጁ የወንጀል ክሶችን በሜክሲኮ ታዋቂው ሲናሎአ ካርቴል ውስጥ በፈጸመው ተግባር ጥፋተኛ ነኝ ሲል አምኗል።ጉዝማን ሎፔዝ ጥፋተኛ ነኝ ሲል በቁጭት ተናግሯል። በችሎቱ መጀመሪያ ላይ ለሰሜን ኢሊኖይ አውራጃ የዩናይትድ ስቴትስ ዲስትሪክት ፍርድ ቤት ዳኛ ሻሮን ኮልማን ፊት ቀርቦ ምን እንደሰራ ተጠይቋል፡፡ ጉዝማን ሎፔዝ “የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ነዉ” ሲል መልሷል።በጉዝማን ሎፔዝ ላይ የጥፋተኝነት ክስ በመመስረቱ ከአሜሪካ አቃቤ ህግ ጋር በመተባበር የፈፀመውን ወንጀል የሚወክል የ80 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ በመክፈል ከህይወት ዘመን እስራት እንደሚያመልጥ ይጠበቃል ሲል ዘገባዎች አመላክተዋል።ይህም ሆኖ ግን ቢያንስ የ10 አመት እስራት እንደሚጠብቀው የፌደራል መንግስት ጠበቃ የሆኑት አንድሪው ኤርስስኪን ተናግረዋል።ጉዝማን ሎፔዝ በዳኛ ቅጣት የሚተላለፍ ሲሆን ይግባኝ ለማለት ግን እድል አይኖረውም ሲል ዘገባዎች ያስረዳሉ። የጉዝማን ሎፔዝ ተከላካይ ጠበቃ ጄፍሪ ሊችማን ከችሎቱ በኋላ “መንግስት እስካሁን ከጆአኩዊን ጋር በጣም ፍትሃዊ ነው” ብለዋል።ሊችማን “የሜክሲኮ መንግሥት ጣልቃ አለመግባቱን አደንቃለሁ” ብለዋል።የቺካጎ ትሪቡን ዘገባ እንደሚያመለክተው በ35 ገፁ የይግባኝ ስምምነት ላይ ጉዝማን ሎፔዝና ወንድሞቹ ለባለሥልጣናቱ ጉቦ በመስጠት እና የጦር መሳሪያ እና ሌሎች መሳሪያዎችን በማሰማራት የህግ አስከባሪዎችን፣ ተቀናቃኝ አዘዋዋሪዎችን እና ሌላው ቀርቶ የራሳቸው ድርጅት አባላትን ያነጣጠረ ጥቃት እንዲፈጽሙ በማድረግ የአደንዛዣ እጽ ዝዉዉር ቡድን እንቅስቃሴ እንዳሳደጉ አምነዋል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
18😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ ባለፋት አራት ወራት ለሽያጭ ካቀረበችው የስጋ ምርት ከ37 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች ኢትዮጵያ ባለፋት አራት ወራት ለሽያጭ ካቀረበችው የተለያዪ የስጋ ምርቶች ከእቅድ በላይ ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ እንስሳት ልማት ኢንስቲትዮት አስታውቋል።በኢንስቲትዮቱ የማህበራዊ ኢኮኖሚክስና እሴት ሰንሰለት አስተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ  ዶክተር ሳህሉ ሙሉ ለብስራት ሬድዮ  እንደተናገሩት በዚህ ጊዜ ውስጥ 6 ሺህ 7መቶ ቶን የስጋ ምርቶችን ለውጪ ገበያ ማቅረብ ተችሏል ። ለውጪ ገበያ ከቀረቡት ምርቶች 35 ነጥብ 29  ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ እንደነበር ያስረዱት ዶክተር ሳህሉ  ከእቅድ በላይ 37 ነጥብ 69 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማግኘት እንደተቻለ አስረድተዋል ።ከስጋ ዘርፋ በተገኘው ገቢ ከእቅድ በላይ 107  በመቶ አፈፃፀምን ማስመዝገብ እንደተቻለ የተገለፀ ሲሆን የበግ፣የፍየል ፣የዳልጋ ከብትን ጨምሮ ሌሎች ምርቶች ለሽያጭ ቀርበዋል። ሳውዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ  ዋነኛ  እና ነባር የስጋ ንግድ መዳረሻ ሀገራት መሆናቸው ተገልጿል።በዘርፋ ለተሰማሩ የማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች በተገቢው መልኩ የእርድ እንስሳቶች  እንዲቀርብላቸው በመደረጉ ባለፋት አራት ወራት ከእቅድ በላይ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ሲል ኢንስቲትዮቱ አስታውቋል። በቅድስት ደጀኔ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
👎 22 14👍 3🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ፑቲን እና ትራምፕ ልዑክ በሞስኮ  በዩክሬን ጉዳይ ውይይት ሊያደርጉ ነው የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዛሬው የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍን በሞስኮ ያገናኛሉ። ዋይት ሀውስ የዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም ከስምምነት ላይ ለመድረስ "በጣም ብሩህ ተስፋ" እንዳለው አስታውቋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አማች ያሬድ ኩሽነር በዲፕሎማሲያዊ ንግግሮች የውጭ አማካሪ ሆነው እያገለገሉ በመሆኑ በዉይይቱ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ መድረክ የተዘጋጀው በፍሎሪዳ ለሁለት ቀናት የዩክሬይን እና የአሜሪካ ባለስልጣናት ዊትኮፍ እና ኩሽነርን ጨምሮ በአሜሪካ የሚደገፈውን የሰላም ስምምነት እቅድ ለሩሲያ ይጠቅማል ተብሎ የተነገረውን የማጣራት ድርድር ተከትሎ የመጣ ነው። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ውይይቱን “ገንቢ” ሲሉ ገልጸውት “አሁንም ሊሰሩባቸው የሚገቡ አንዳንድ ከባድ ጉዳዮች አሉ” ሲሉ ሀሳብ ሰጥተዋል። የዊትኮፍ ከፑቲን ጋር የሚያደርጉት ስብሰባ በዛሬው እለት ይካሄዳል ሲሉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል። ሰኞ እለት ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በፓሪስ ከተገናኙ በኋላ ዘሌንስኪ እንደተናገሩት የኪየቭ የሰላም ድርድር ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች የዩክሬንን ሉዓላዊነት ማስጠበቅ እና ጠንካራ የፀጥታ ዋስትናዎችን ማረጋገጥ ነው ብለዋል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
24🕊 2
በስልጤ ዞን በተነሳ የእሳት አደጋ 3 ህፃናት ህይወታቸው  አለፈ      👉 ህፃናቶቹ የታላቅ እና ታናሽ ልጆች ናቸው በስልጤ ዞን በሚቶ ወረዳ በሰሶ ቀበሌ በቀጠና ሁለት ልዩ ስሙ አበልቾ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በትላንትናው እለት 10:30  የእሳት አደጋ ደርሷል። የሚቶ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ሀላፊ እና  ህዝብ ግንኙነት ተወካይ ረዳት ኢንስፔክተር ነጅሙዲን ዋበላ ከብስራት ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት ህፃናቶቹ በቆርቆሮ ቤት ውስጥ እየተጫወቱ በነበረበት ሰዓት በቦታው የነበረ ገለባ በእሳት በመያያዙ በውስጡ የነበሩ የ6 ዓመት ሁለት ወንድ እና ሴት መንታ ልጆች እና የ2 ዓመት ሴት ህፃን ወዲያውኑ ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል። ህይወታቸው ያለፉት ህፃናቶች የታናሽ እና የታላቅ እህትማማች ልጆች ሲሆኑ በአያታቸው መኖሪያ ቤት ይኖራሉ።የሁለቱ መንታ ልጆች እናት ህይወቷ ያለፈ ሲሆን የ2 ዓመቱ ህፃን እናት ደግሞ ለስራ ከሀገር ውጭ በመኖሯ ህፃናቶቹ በአያታቸው ቤት እንደሚኖሩ ነው  ኢንስፔክተር ነጅሙዲን ዋበላ  የገለፁት። የአደጋው መንስኤ ለጊዜው ምክንያቱ ባለመታወቁ ፖሊስ እያጣራ ሲሆን የህፃናቶቹ አስከሬን ለምርመራ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ተልኳል።ወቅቱ በጋ እና ነፋሻማ  በመሆኑ ድንገተኛ የእሳት አደጋዎች ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ  አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል ሲሉ ኢንስፔክተር ነጅሙዲን ዋበላ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። ሳምራዊት ስዩም #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
💔 44 14😭 8🔥 1
I
إظهار الكل...
ሲጠናቀቅ የ6 ሰዓት ጉዞን ወደ 1 ሰዓት ተኩል የሚያሳጥረዉ የደብረኤሊያስ- ተምጫ እና ጭምት መገንጠያ -ጭምት ከተማ መንገድ ግንባታ ዳግም ተጀመረ በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ከሁለት ዓመታት በፊት የግንባታ ሂደቱ ተስተጓጉሎ የነበረው የደብረማርቆስ - ደብረኤሊያስ -ተምጫ እና ጭምት መገንጠያ - ጭምት ከተማ መንገድ ግንባታ  ሂደት ማስቀጠል መቻሉ ተገልጿል ። የመንገድ ፕሮጀክቱ በ2012 ዓ.ም ተጀምሮ ሲከናወን የቆየ ቢሆንም ከ2 ዓመታት በፊት የግንባታው አጠቃላይ አፈጻጸም 52 ነጥብ 8 በመቶ ከደረሰ በኋላ በጸጥታ ችግር ምክንያት የግንባታ ሂደቱ ተስተጓጉሎ ነበር ። አሁን ላይ የመንገድ ዳር የዲች ሥራ በመከናወን ላይ ሲሆን ግንባታውን በሙሉ አቅም ለማስቀጠል የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ ናቸው። የመንገድ ፕሮጀክቱ 80 ነጥብ 9 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን መሆኑ ተገልጾ ለግንባታው 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በፌደራል መንግስት በጀት ተይዞለታል ። የመንገድ ግንባታው ሲጠናቀቅ በነባሩ ጠባብ የጠጠር መንገድ ይወስድ የነበረውን 6 ሰዓት የጉዞ ጊዜ ወደ 1 ሰዓት ተኩል ያሳጥረዋል መባሉን ብስራት ሬዲዮ ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ያገኘዉ መረጃ ያመለክታል ። #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
40
3👎 3
ከፀረ ተባይ መድኃኒት ጋር ተጭኖ ሲጓጓዝ የተገኘ የለስላሣ መጠጥ እና የቅመማ ቅመም ምርት በቁጥጥር ስር ዋለ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አብቹ እና ፕዓ ወረዳ ከፀረ ተባይ  መድኃኒት ጋር የተጫነ በርካታ የለስላሳ መጠጥና የቅመማ ቅመም ምርት በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታዉቋል። የአብቹ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኢንስፔክተር ጋዲሣ አደሬ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት የሰሌዳ ቁጥር ኤ -31549 ኢቲ የሆነ የጭነት ተሽከርካሪ ከአዲስ አበባ ወደ ደቡብ ወሎ ከለላ ከተማ የተለያዩ የለስላሳ እና የቅመማ ቅመም ምርቶች ጋር የፀረ ተባይ ማጥፍያ መድኃኒት ጋር ጭኖ ሲጓዝ መንዲዳ ከተማ በተደረገ የኬላ ፍተሻ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል። ተሽከርካሪው በርካታ የጁስ እና የለስላሳ መጠጦች፣ለምግብነት  ማጣፈጫ የሚውሉ እንደ ዝንጅብል፣ኮረሪማ፣ጥቁር አዝሙድ እንዲሁም የሻይ ቅመሞችን ከምግብ እና  መጠጥ ምርቶች ጋር ሊጓጓዙ የማይፈቀድላቸውን የፀረ ተባይ  መድኃኒት በአንድ ላይ በመጫን ሲጓዝ በመገኘቱ እንደሆነ ገልፀዋል። መድኃኒቱ አይጦችን በፍጥነት የሚገድል እና ለጤና አደገኛ የሆነና ወዲያው ሊገድል የሚችል እንደሆነ ከኢትዮጵያ የምግብ ና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የተገኘው ማስረጃ አረጋግጧል። አሽከርካሪውም ሆነ የንብረቱ ባለቤት የሰው ልጅ ጤና ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል መርዛማ መድኃኒት ከምግብ እና መጠጥ ምርቶች ጋር አብሮ ሲያጓጉዙ በመገኘታቸው በፖሊስ ምርመራቸው ተጠናቆ ለሚመለከተው የፍትህ አካል ይላካል ሲሉ  ኢንስፔክተር ጋዲሣ አደሬ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በሳምራዊት ስዩም #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
25😁 8👌 3👎 2