ar
Feedback
💛 የ መዝሙር ግጥሞች 💛

💛 የ መዝሙር ግጥሞች 💛

الذهاب إلى القناة على Telegram

🇪🇹 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ ቆየት ያሉና አዳዲስ👇👇 👏 የቸብቸቦ መዝሙራት 🎻 የበገና መዝሙራት   👑 የቅዱሳ መዝሙራት ⛪️ የንግስ መዝሙራት 💍 የሠርግ መዝሙራት 🌦 ወቅታዊ መዝሙራት መገኛ 📢ለ ማስታወቂያ ስራዎች @Miki_Mako

إظهار المزيد
2025 عام في الأرقامsnowflakes fon
card fon
142 941
المشتركون
+6124 ساعات
-2137 أيام
+1 06530 أيام
أرشيف المشاركات
Old telegram ግሩፖች ያላችሁ ✍️የ Group ሜምበር ብዛት አያስፈልግም ✍️በተመጣጣኝ ዋጋ እየገዛን እንገኛለን ዋጋ 🟥  🔂አሁን ያለው የ group ዋጋ ✍️2018- 900ብር ✍️2019- 850ብር ✍️2020- 800ብር ✍️2021- 750ብር ✍️2022- 700ብር ✍️2023-650 ብር ✍️2024-300 ብር (Jan And Feb) ✍️2024-100 ብር (March-May) ✔️ክፍያ : 🏦 🏦 🏦 🏦 🏦 🏦 🏦 ለመሸጥ ምትፈልጉ  inbox 👉 @dag_arshavin ⚠️ ማሳሰቢያ ❗️ የግሩፑ Member ብዛት ''0'' ይሁን  ዋጋው እኩል ነው ❗️እኛ የምንፈልገው የተከፈተበትን አመተ ምህረት ብቻ መሆኑን ይገንዘቡ two step verification ኦን መሆኑን check አርጉ    ➡️በተጨማሪም 📱ቴሌግራም premium እና 💎ቴሌግራም star  ከፈለጉ ያናግሩን @dag_arshavin TIKTOK እንገዛለን, እንሸጣለን ✔️                                                     FOR MORE  @ArshavinStore
إظهار الكل...
13👍 5🏆 2
🫶•➢ ጳጉሜን ለምን እንጠመቃለን እና ሌሎች ጥያቄዎችን መልስ ያገኙበታል 👇👇👇
إظهار الكل...
💯 1
ለምን እንጠመቃለን⁉️
ባሕረ ሀሳብ(አቡሻክር)
🌻የእንቁጣጣሽ ዝማሬ🤲
✍2018 አፅዋማት
✞ ሩፋኤል ብዬ ✞ ሩፋኤል ብዬ ስጠራው ሚስጥሬን ሁሉ ሳወራው ትላንት የረዳኝ ጸሎትህ ዛሬም ይድረሰኝ ለልጅህ ሩፋኤል ብዬ አንደበቴ ለምዶት ስምህን ሩፋኤል ብዬ ልጅነቴ ቀምሶት ፍቅርህን ሩፋኤል ብዬ የህይወቴ ቅጥር ሲላላ ነፍሴ ትጮሀለች ሩፋኤል ሩፋኤል ብላ አዝ= = = = = ሩፋኤል ብዬ ከአምላኬ ስትላክ ለምህረት ሩፋኤል ብዬ ስትጠብቀኝ ቀንና ለሊት ሩፋኤል ብዬ ባስከፋህ በትግስት እለፈኝ ምልጃህ እረድኤት ያግዘኝ እኔን ይደግፈኝ አዝ= = = = = ሩፋኤል ብዬ ህመሜ እንዳይጸና ክፋቱ ሩፋኤል ብዬ መድሐኒት እንዲሆን ሀሞቱ ሩፋኤል ብዬ ካጠገቤ እንዳትርቅ ከጎኔ ትዳሬ እንዲጸና ሩፋኤል እንዲበራ አይኔ አዝ= = = = = ሩፋኤል ብዬ ከአምላኬ ስትላክ ለምህረት ሩፋኤል ብዬ ስትጠብቀኝ ቀንና ለሊት ሩፋኤል ብዬ ባስከፋህ በትግስት እለፈኝ ምልጃህ እረድኤት ያግዘኝ እኔን ይደግፈኝ መዝሙር ዘማሪ ሚኪያስ መንገሻ ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮    @yamazemur_getemoche ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
إظهار الكل...
ሩፋኤል ብዬ .mp33.11 MB
108👏 6🔥 1
ሼር🔥
Photo unavailableShow in Telegram
"ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ።" ጦቢት፲፪፥፲፭ የዋህ የምህረትና የረድኤት መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ከስራዎቹ አንፃር በተለያየ ስም ይጠራል ለአብነት ያክል፦ "ፈታሄ ማህጸን"ይባላል። እናቶች ሲወልዱ ምጥ እንዳይበዛባቸዉ የሚራዳ መልአክ ስለሆነ አያሌ ክርስቲያኖች ማርገዛቸዉን ካወቁ ጀምሮ ድርሳኑን በማንበብ መልኩን በመድገም ጠበሉን በመጠጣት ሰዉነታቸዉን በመቀባት ይለምኑታል፡፡እንደ እምነታቸዉ ጽናት ይደረገላቸዋል፡፡ "ዐቃቤ ኖኀቱ ለአምላክ"ይባላል፡፡ ሰማያዉያን መዛግብት በእጁ የሚጠበቅ በመሆኑ ። "መራሔ ፍኖት"ይባላል፡፡ ጦቢትን በቀና መንገድ መርቶታልና፡፡ "መልአከ ክብካብ"ይባላል፡፡ ጦቢያና ሣራን ያጋባ ጋብቻቸዉን የባረከ በመሆኑ፡፡ "የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።" መዝ፴፬፥፯ ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮ @yamazemur_getemoche ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
إظهار الكل...
101👍 7🕊 5😍 1
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወርኀ ጳጕሜን የዓለም ፍጻሜ መታሰቢያ ተደርጋ ትታሰባለች፡፡ በዚህ የተነሣ ምእመናን በጾምና በጸሎት (በሱባዔ) ያሳልፏታል፡፡ በተለይም በቅዱስ ሩፋኤል ዕለት ሰማያት የሚከፈቱበት (ርኅዎተ ሰማይ) መኾኑን በማመን ምእመናን ጸሎታቸውን ከምንጊዜውም በበለጠ ያቀርባሉ፡፡ ወደ ወንዞች በመሔድና በሚዘንበው ዝናብ ይጠመቃሉ፡፡ ወርኀ ጳጕሜን የጌታችን ምጽአት የሚታሰብባት በመኾኗ የሚዘመረው መዝሙር፣ የሚነበቡ ምንባባትና ቅዱስ ወንጌሉ እንደዚሁም የሚሰበከው ምስባክ ይህንኑ ምሥጢር የሚያሳዩ ናቸው፡፡ በወርኀ ጳጉሜን ከሚታሰቡ እና ከሚከበሩ በዓላት መካከል በየዓመቱ ጳጕሜን ፫ ቀን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይከበራል፡፡ የቅዱስ ሩፋኤል በዓሉ የሚከበርባቸው ምክንያቶችም ሁለት ናቸው፤ እነርሱም አንደኛው በዓለ ሢመቱን ምክንያት በማድረግ ሲኾን፣ ሁለተኛው ደግሞ ቅዳሴ ቤቱ ነው፡፡ ‹ሩፋኤል› የሚለው የስሙ ትርጓሜ ‹ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ› ማለት ነው፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ያለ ማቋረጥ ፈጣሪያቸው ልዑል እግዚአብሔርን ከሚያመሰግኑ ቅዱሳን መላእክት አንዱ ነው፡፡  "ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ።"እንዲል (ጦቢት ፲፪፥፲፭)፡፡ የሰው ልጆች ከተያዙበት የኀጢአት ቍስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው፡፡ "በበሽታ ዅሉ ላይ በሰው ልጆችም ቍስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው።" በማለት ሄኖክ ከእግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ጽፏል (ሄኖክ ፲፥፲፫)፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ኾነ ቍስል ይፈውስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡"በሰው ቍስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው።"እንዳለ ሄኖክ (ሄኖክ ፮፥፫)፡፡ ለቈሰሉ ፈውስን የሚያሰጣቸው፤ ላረገዙ ሴቶች ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል አይለያትም፡፡ ሕፃኑ (ኗ) በማኅፀን እያለ (ች) ተሥዕሎተ መልክዕ (በሥላሴ አርአያ መልኩ /ኳ/ መሳል) ከጀመረበት ቀን አንሥቶ እስከሚወለድበት ቀን ድረስ ቅዱስ ሩፋኤል በጥበቃው አይለያቸውም፡፡ በመውለጃቸው ቀን ሴቶች ከሚደርስባቸው ጭንቀትና ሕመም ስሙን ጠርተው ይማጸኑታል፡፡ ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ሩፋኤልም ጭንቀታቸውን ያቀልላቸዋል፡፡ አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሰቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል (ጦቢት ፫፥፰-፲፯)፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል"ዳግመኛም እግዚአብሔር ሩፋኤልን፣ አዛዝኤልን እጁን እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ ጣለው አለው።"ተብሎ እንደ ተጻፈ (ሄኖክ ፫፥፭-፯)፡፡ ለቃየን ልጆች ሰይፍና ሾተል መሥራትን፣ የምንዝር ጌጥ ማጌጥን፣ መቀንደብን ያስተማረ አዛዝኤል የተባለውን ጋኔን በእሳት ሰይፍ እየቀጣ በረቂቅ አስሮ ወደ ጥልቁ የጣለው ይኸው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ነው (ሄኖክ ፪፥፲፰)፡፡ የጦቢትን ልጁ ጦቢያን በሰው አምሳል ተገልጦ ከተራዳው በኋላ ወደ ሰማይ በሚያርግበት ጊዜ ራሱን ሲገልጥ "የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረ ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነትም ከሚያገቡ ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ አላቸው"ጦቢት ፲፪፥፲፭)፡፡ በቅዱስ ሩፋኤል ተራዳዒነት ከተደረጉ ተአምራት መካከል በእስክንድርያ አቅራቢያ በምትገኝ ደሴት በታነጸች ቤተ ክርስቲያኑ ያደረገው ተአምር አንደኛው ነው፡፡ በመጽሐፈ ስንክሳር እና በድርሳነ ሩፋኤል እንደ ተጻፈው ብዙ ምእመናን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እያሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ፈጽማ ተናወጠች፤ ያቺ ደሴት በታላቅ አንበሪ ጀርባ ላይ የቆመች ናትና፡፡ የሰዎች ብዛትም በከበደው ጊዜ ዓሣ አንበሪው ቤተ ክርስቲያኒቱን ያፈርሳት ዘንድ ሰይጣን አነሣሣው፡፡ ምእመናኑም ወደ ክብር ባለቤት እግዚአብሔር በከበረ መልአክ ሩፋኤል ስም ጮኹ፡፡ ያን ጊዜ ቅዱስ ሩፋኤል ያንን አንበሪ በጦሩ ወግቶ ‹‹እግዚአብሔር አዝዞሃልና ከቦታህ ሳትናወጥ ጸጥ ብለህ ቁም!›› ባለው ጊዜ አንበሪው ጸጥ ብሎ ቆሟል፡፡ በውስጧም ድንቆች ተአምራቶች ተገልጠዋል፡፡ ለሕሙማንም ፈውስ ኾኗል፡፡ የቅዱስ ሩፋኤል ተራዳዒነት አይለየን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ ምንጭ፦ ማኅበረ ቅዱሳን በዲያቆን ዮሴፍ ይኵኖአምላክ ጳጕሜን ፫ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮ @yamazemur_getemoche ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
إظهار الكل...
75👍 2
ሼር ያድርጉ
🫶•➢ ጳጉሜን ለምን እንጠመቃለን እና ሌሎች ጥያቄዎችን መልስ ያገኙበታል 👇👇👇
إظهار الكل...
1
ለምን እንጠመቃለን⁉️
ባሕረ ሀሳብ(አቡሻክር)
🌻የእንቁጣጣሽ ዝማሬ🤲
✍2018 አፅዋማት
የጳጉሜን 3 የቅዱስ ሩፋኤል ወረብ https://youtube.com/watch?v=tgMTRMloqbs&si=qcSFZhgGHjtPtT8k
إظهار الكل...
45
Repost from TgId: 1204066070
Photo unavailableShow in Telegram
🔊 እንግሊዝኛን በአንድ ወር ውስጥ አቀላጥፎ ማውራት ይፈልገሉ❔ 🧾 አዎን እፈልጋለሁ ካሉ     🌟እንግዲያውስ አሪፍ ቻናል ልጋብዛችሁ ያለ ምንም ጥርጥር ትወዱታለችሁ! ✅ JOIN አድርጉና እንግሊዝኛን በአማርኛ ይማሩ። የቻናሉ Link👇 https://t.me/LEARN_ENGLISH_LANGUAGE_USA/13342 https://t.me/LEARN_ENGLISH_LANGUAGE_USA/9353
إظهار الكل...
6
በነፃ ይማሩ📖
የጳጉሜን 3 የቅዱስ ሩፋኤል ወረብ https://youtube.com/watch?v=tgMTRMloqbs&si=qcSFZhgGHjtPtT8k
إظهار الكل...
53
✞ያለፈው ዘመኔ✞ ያለፈው ዘመኔ ይበቃኛል(፪) በአምላክ መታመኔ ይሻለኛል(፪) እውነት በሌለበት በውሸቱ ኑሮ ነፍሴ እየባዘነች በኃጢአት ቀጠሮ አሁን ግን ተረዳሁ ይበቃኛል እግዚአብሔር አምላኬ ይሻለኛል አዝ= = = = = ካራን ተሰሎንቄ ባቢሎንና ግብፅ አይኔን ቢጋርዱኝ በእግዚአብሔር እንዳምፅ ዛሬ ግን ማዳኑን አየሁት ያዳነኝን አምላክ ወደድኩት አዝ= = = = = ጌታን ባለማወቅ በውሸቱ ጉዞ በኃጢአት በእርኩሰት ህሊናዬ ናውዞ ሰማሁት አወቅኩት ቃልህን በእርሱ ላይ አቀናሁ መንገዴን አዝ= = = = = እረፍት ያጣሁበት ያለፈው ዘመኔ ዛሬ ጠፍቶልኛል ተወግዷ ከአይኔ ህግህ ለመንገዴ ብርሃን ነው አዲስ ሰው የሆንኩት በአንተው ነው              መዝሙር      ሲስተር ሕይወት ተፈሪ "የአህዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት …… ያለፈው ዘመን ይበቃልና …" ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮    @yamazemur_getemoche ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
إظهار الكل...
ያለፈው ዘመኔ.mp34.32 MB
112🥰 12💯 4🕊 3
ሼር 💛
📖የስልክ ቁጥሮን የመጨረሻ ቁጥር ይምረጡ። እግዚአብሔር በአንድም በሌላም መንገድ ያስተምራል። ኑና የእግዚአብሔርን ቃል አብራችሁን ተካፈሉ።
إظهار الكل...
😍1
😍2
😍3
😍4
😍5
😍6
😍7
😍8
😍9
🥰0
​​በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ጾመ ዮዲት በናቡከደነጾር ዘመነ መንግሥት ንጉሡ ሥልጣኑን መከታ በማድረግ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በግድ እያስገደደ እጅ መንሻ ይቀበል ነበር፡፡ የመንግሥቱን ትእዛዝ ያልተቀበለውንም እየገደለ፣  ጭፍሮቹ ኃያልነቱንና ገናናነቱን በዓዋጅ በጦር አዛዦች ጭምር እያሳወጀ፣ በርካታ የጦር ሠራዊቶችን አሰልፎ ከአይሁድ ከተማ ገባ፡፡ በዚያም ነዋሪዎችን በማስፈራራት የመንግሥቱን ትእዛዝ ያልተቀበሉትን ሁሉ እያሳደደ ስላስጨነቃቸው ማቅ ለብሰው፣ አመድ ነስንሰውና ድንጋይ ተንተርሰው ወደ ፈጣሪያቸው በመጮህ መለመን ጀመሩ። በጭካኔ የተሞላው የጦር አበጋዙ ሆሎፎርኒስም ይበልጥ እጅግ እንዲሰቃዩ ውኃ የሚቀዱበትን ስፍራ ተቆጣጠረው፤ በግዴታ ማርኮም እጅ እንዲሰጡ እንዳደረጋቸው በመጽሐፈ ዮዲት ፪፥፪ ላይ ተጽፏል፡፡ በአካባቢው ይኖር የነበረ ዖዝያን የተባለ አንድ ሰው የአባቶቻቸው አምላክ ጸሎታቸውን እንዲሰማቸው ለአምስት ቀናት በትዕግሥት ይጾሙና ይጸልዩ ዘንድ ሕዝቡን መከራቸው፤ እነርሱም በትዕግሥት ሊጠብቁ ተስማሙ፡፡ የእስራኤል ልጆች የናቡከደነጾርን ጦር ብንችል ተዋግተን እንረታለን፤ ካልሆነም እጅ እንሰጣለን በማለት ይመካከሩ ጀመር። በዚያን ጊዜ ባሏ የሞተባትና በንጽሕና ተጠብቃ፣ በጸሎትና በሕገ እግዚአብሔር የምትኖር ዮዲት የተባለች ሴት ነበረች። (ዮዲት ፯፥፲) እግዚአብሔርን የምትፈራ ብቸኛዋ ሴት እርሷ ነበረችና ምክክራቸውን ስትሰማ ለምን «እግዚአብሔር ያድነናል አትሉም» ብላ ገሠጸቻቸው፡፡ ማቅ በመልበስ፣ አመድ በመነስነስና ድንጋይ በመንተራስም ሱባኤ ገባች። በሦስተኛው ቀንም እግዚአብሔር አምላክ ሕዝቧን የምታድንበትን ጥበብ ገለጸላት፤ ዮዲትም እግዚአብሔር የሰጣትን ውበት ተጠቅማ ሕዝቧን ከጥፋት የምትታደግበትን ጥበብ ተረዳች። የክት ልብሷን ለብሳ፣ ሽቱ ተቀብታና ተውባ የጠላት ሠራዊት ወዳሉበት የጦር ሰፈር በድፍረት አመራች፡፡ ሠራዊቱም ውበቷን አይተው እጅግ በመደነቅ «ይህችስ ለአለቃችን ትገባለች» ተባብለው ከጦር መሪያቸው ዘንድ ወሰዷት። እርሷም ቀድማ ማምለጫ መንገድ አዘጋጅታ ነበርና ወደ አዛዡ ከገባች በኋላ «ክቡር ጌታዬ ሆይ ርስት ተወስዶብኛል፤ እንድትመልስልኝ አስቀድሜ ደጅ ልጠና መጥቻለውና ርዳኝ፤ ትብብርህ አይለየኝ» አለችው፡፡ በስሜት ፈረስ ታውሮ የነበረው የሠራዊቶቹ አዛዥም የጠየቀችውን እንደሚፈጽምላት ቃል ገባላት። ባማረ ድንካን እንዲያስቀምጧት ሎሌዎቹን አዘዘ። ዮዲትም የተሰጣትን ጥበብ ተጠቅማ፣ መውጣት ስትፈልግ የምትወጣበትን እና የምትገባበትን ዕድል በእግዚአብሔር አጋዥነት ዐወቀች፡፡ ከቀናት በኃላ የጦር አበጋዙ ለሠራዊቱ የምሳ ግብዣ አዘጋጅቶ ዮዲትን ከጎኑ አስቀመጣት፤ ከበሉና ከጠጡ በኋላም ሁሉን ሰው አስወጣ፤ እልፍኙን በመዝጋት ከእርሷ ጋር ብቻውን ሆነ፤ ነገር ግን እንቅልፍ ጣለው፡፡ (ዮዲት ፰፥፪) እርሷም ወደ አምላኳ ጸለየች፤ ፈጣሪዋ እንዲረዳትም አጥብቃ ለመነች። በኋላም ከራስጌው ሰይፍ አንስታ አንገቱን ቀላችው፤ በድኑንም ከመሬት ጣለችው። የሆሎፎርኒስን ሞት ሠራዊቱ ሲሰሙ አውራ እንደሌለው ንብ ተበተኑ፤ ከፊሎቹ ሞቱ። እስራኤላውያንም ከሞት ተርፈው በእግዚአብሔር ኃይል ድል አደረጉ፤ በደስታም ፈጣሪያቸውን አመሰገኑ። ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክ የሚያስረዳን ዮዲት ጠላቶቿን ድል ያደረገችው በጾምና በጸሎት እንደሆነ ነው፡፡ ለእኛም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ምንም እንኳ ወርኃ ጳጉሜን የፈቃድ ጾም ቢሆንም በሀገራችን የተጋረጠውን ችግር እናልፍ ዘንድ በፈቃደኝነት እንጾማለን። እግዚአብሔር አምላካችን ለሁላችንም ጥበብ ሰጥቶናል። ይህም ችግሮችን ሁሉ የምንፈታበት መንገድ ነው። በዚህም የዓመተ መሸጋገሪያና የክረምቱ ወር ማብቂያ በመሆኑ ዕለተ ምጽአት ስለሚታሰብበት በየዓመቱ በጳጉሜ ወር ከሌሊት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያን ተገኝተን ጠበል በመጠመቅ፣ በማስቀደስና በመጸለይ እንዲሁም ሥጋ ወደሙን በመቀበል ልናሳልፍ ይገባል። ዕለተ ምጽአትም ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው ዓለም መሸጋገሪያችን ነውና በቀኙ እንቆም ዘንድ እንጾማለን፡፡ የሚመጣውን አዲስ ዘመንም በንጽሕና ለመቀበል ስላለፈው ዓመት ኃጢአታችን ንስሓ የምንገባበት ጾምም ነው።    ከተጋረጠብን ችግር «እግዚአብሔር ያድነናል» በማለት ልክ እንደ ዮዲት ሱባኤ ገብተን፣ ማቅ ለብሰን፣ አመድ ነስንሰንና ድንጋይ ተንተርሰን አብዝተን ልንጾምና ልንጸልይ ይገባል፡፡ ሊለያየን፣ ሊነጣጥለን፣ ሊበታትነን እና ሊገድለን ካሰበው እንዲሁም ፍቅርን፣ መተሳሰብንና አንድነትን ሊነፍገን ከቃጣው ጠላትና ሃይማኖታችንን ሊያስተወን ከሚመጣ ፀረ ሃይማኖት እንድናለን። ስለዚህ ከፊታችን ያለችውን ስድስቱን የጳጉሜን ቀን በፍቅር፣ በአንድነትና በሃይማኖት ጸንተን፣ ጾመን፣ ጸልየን ለዘመነ ዮሐንስ እንድንደርስ እግዚአብሔር አምላካችን ይርዳን፤ አሜን። ምንጭ፦ ከማኅበረ ቅዱሳን በዲያቆን ዮሴፍ በቀለ ስብሐት ለእግዚአብሔር ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮ @yamazemur_getemoche ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
إظهار الكل...
106👍 10💯 4🥰 3🕊 3😍 2
ሼር ያድርጉ
Photo unavailableShow in Telegram
☦#Orthodox profile pictures ☦#ኦርቶዶክስ_ፕሮፋይሎችን_እዚህ_ታገኛላችሁ_ተቀላቀሉ
إظهار الكل...
90😍 11
Join ✅
❤️ከ 170ሺ በላይ ተከታይ ያፈራው ተወዳጁ መንፈሳዊ ቻናል እንዲቀላቀሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እናሳስባለን።                👇👇👇      @EOTC_-OPEN_channel      @EOTC_-OPEN_channel      @EOTC_-OPEN_channel      @EOTC_-OPEN_channel
إظهار الكل...
4
⛪️ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ዜናዎች⛪️
👳‍♂ምክረ አበው👳‍♂
🗣ኦርቶዶክሳዊ ስነምግባር👨🏾
⛪️ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ⁉️
❤️መንፈሳዊ አገልግሎት ለማግኘት ይቀላቀሉ❤️
⛪️የኦርቶዶክስ ሥርዓት የጠበቁ ትምህርቶች ይፈልጋሉ?
إظهار الكل...
👍 4
አዎ እፈልጋለሁ✅
አልፈልግም🚫
ዘንድሮ የማንሰማው ጉድ የለም https://youtube.com/shorts/EvmD0wilAYI?si=Iyksi6wiUKGfKnLT
إظهار الكل...
17
የተመረጡ መዝሙሮችን ይፈልጋሉ
إظهار الكل...
አዎ
አይ
Photo unavailableShow in Telegram
ይሄንን ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ መዝሙሮችን የሚተላለፉበት ቴሌግራም ቻናል መቀላቀል አለባችሁ!!! •✥•🍁  @Abel_Mekebeb 🍁•✥• •✥•🍁  @Abel_Mekebeb 🍁•✥• •✥•🍁  @Abel_Mekebeb 🍁•✥• በተጨማሪም 👇👇👇👇👇👇
إظهار الكل...
5
👤ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
💿 የቀድሞ መዝሙራት
📱 አዳዲስ ዝማሬዎች
Old telegram ግሩፖች ያላችሁ ✍️የ Group ሜምበር ብዛት አያስፈልግም ✍️በተመጣጣኝ ዋጋ እየገዛን እንገኛለን ዋጋ 🟥  🔂አሁን ያለው የ group ዋጋ ✍️2018- 900ብር ✍️2019- 850ብር ✍️2020- 800ብር ✍️2021- 750ብር ✍️2022- 700ብር ✍️2023-650 ብር ✍️2024-300 ብር (Jan And Feb) ✍️2024-100 ብር (March-May) ✔️ክፍያ : 🏦 🏦 🏦 🏦 🏦 🏦 🏦 ለመሸጥ ምትፈልጉ  inbox 👉 @dag_arshavin ⚠️ ማሳሰቢያ ❗️ የግሩፑ Member ብዛት ''0'' ይሁን  ዋጋው እኩል ነው ❗️እኛ የምንፈልገው የተከፈተበትን አመተ ምህረት ብቻ መሆኑን ይገንዘቡ two step verification ኦን መሆኑን check አርጉ    ➡️በተጨማሪም 📱ቴሌግራም premium እና 💎ቴሌግራም star  ከፈለጉ ያናግሩን @dag_arshavin TIKTOK እንገዛለን, እንሸጣለን ✔️                                                     FOR MORE  @ArshavinStore
إظهار الكل...
5