2025 عام في الأرقام

127 466
المشتركون
-3524 ساعات
-2137 أيام
-70030 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
#JinkaUniversity
በ2018 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች በሙሉ የማርበርግ ቫይረስ ሙሉ በሙሉ መጥፋቱ በጤና ሚኒስቴር ተረጋግጦ ጥሪ እስከሚደረግላችሁ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል።
በሌላ መረጃ፤
ከአሪ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች በሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዳችሁ የሪሚዲያል ትምህርት ለመከታተል ከጂንካ ዩኒቨርሲቲ ውጪ በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደባችሁ ተማሪዎች ታህሳስ 15 እና 16/2018 ዓ.ም ወደ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ገብታችሁ የ21 ቀናት Quarantine ወስዳችሁ በዩኒቨርሲቲው ነፃ የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት እያገኛችሁ በመቆየት ከማርበርግ ቫይረስ ነፃ መሆናችሁ ሲረጋገጥና የምስክር ወረቀት ከተሰጣችሁ በኋላ ወደየተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንድትገቡ ትምህርት ሚኒስቴር ወስኗል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#ለማሳወቅ
በዛሬው ዕለት ማለትም እሁድ ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም በሃይል ማሻሻይ ጥገና ምክንያት በአዲስአበባ ፣ አፋር እና ሸገር ላይ መብራት ከ ጠዋቱ 1:30 ጀምሮ እንደማይኖር ይፋ ሁኗል !
ይሄንን አውቃቹ ቅድማቹ አስፈላጊውን ነገር እንዳተደርጉ እኛም ልናሳውቃቹ ወደድን ፤ የነገ ሰው ይበለን !
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#MoE
የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የ2018 ዓ.ም የመረጃ አሰባሰብ (HEMIS) ያለበት ሁኔታ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሪፎርም ሥራዎችን የተመለከተ የምክክር መድረክ በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቷል።
መድረኩ ታህሳስ 14 እና 15/2018 ዓ.ም ይካሔዳል።
በዚህም ስማችሁ ከላይ በምስሉ የተዘረዘሩ ተቋማት፣ የተቋም ባለቤት/የበላይ አመራር እና ከተገለፀው ሥራ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው አንድ ባለሙያ የተቋሙን የተሟላ መረጃና ለሥራ የሚሆን ላፕቶፕ በመያዝ ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 በትምህርት ሚኒስቴር ትንሹ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ ጥሪ ተላልፏል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
በቀጣይ ራስ ገዝ ሆነው የሚቋቋሙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለሚያደርጉት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ግብዓት የሚሆን የሽግግር ረቂቅ መመሪያ ላይ ምክክር ተደረገ።
በመጪው ዓመት ራስ ገዝ ለመሆን እየሠሩ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች፥ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተጀመረው ራስ ገዝ የመሆን ሂደት የተገኙ ተሞክሮዎች እና ፈተናዎችን በመለየት በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አሳስበዋል።
በመድረኩ ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የራስ ገዝነት ሽግግር የተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ውይይት ተደርጎበታል።
ረቂቅ ሰነዱ ለራስ ገዝነት ሽግግር የሚያበቁ መስፈርቶችና ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች የተካተቱበት ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲዎች በዚህ ረቂቅ መመሪያ እየተመዘኑ ሽግግር የሚያደርጉ መሆኑ ተገልጿል።
በመድረኩ በቀጣይ ራስ ገዝ በመሆን ለሚቋቋሙ ዩኒቨርሲቲዎች ተሞክሮ እንዲሆን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዝነት ሽግግርን የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ ወይይት ተደርጎበታል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#ማስታወሻ
በ2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ትምህርታችሁን በመከታተል ላይ የምትገኙ ተማሪዎች የፋይዳ መታወቂያ ማውጣት ይጠበቅባችኋል።
የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ያላደረጋችሁ በከተማዋ የምትገኙ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ቅዳሜ እና እሑድ በሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች በመገኘት ምዝገባ በማድረግ መታወቂያውን መውሰድ ትችላላችሁ።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
አሜሪካ በየዓመቱ የምታካሂደውን የዲቪ ሎተሪ አቆመች።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት በብራውን ዩኒቨርሲቲ በተፈጸመ የጅምላ ጥቃት ሁለት ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ የአሜሪካን ግሪን ካርድ ሎተሪን (ዲቪ) አገዱ።
ጥቃቱን ፈጽሟል ተብሎ የተጠረጠረው እና ሐሙስ ዕለት ሞቶ የተገኘው ፖርቹጋላዊው በአውሮፓውያኑ 2017 ዲቪ ሎተሪ አሸንፎ ወደ አገሪቱ የገባ ሲሆን ግሪን ካርድም ተሰጥቶታል።
የአገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስትር የሆኑት ክሪስቲ ኖም " በዚህ አስከፊ ፕሮግራም አሜሪካውያን ከእንግዲህ እንዳይጎዱ ለማረጋገጥ " በሚል ትራምፕ በሰጡት መመሪያ መሠረት የቪዛ መርሃ ግብሩን ለጊዜው እንዲቋረጥ መደረጉን ተናግረዋል።
የአሜሪካ ባለሥልጣናት ተጠርጣሪው የ48 ዓመቱ ክላውዲዮ ኔቭስ ቫለንቴ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም ፕሮፌሰር ኑኖ ሉሬሮንም ገድሏል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
የዲቪ ሎተሪ ፕሮግራሙ በአሜሪካ በስደተኝነት በቂ ድርሻን ላላገኙ አገራት ዜጎች በየዓመቱ 50 ሺህ ቪዛዎችን ይሰጣል። ይህ ደግሞ የአሜሪካ ዜግነትን ለማግኘትም በር ከፋች ነው።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ ነው።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
#ExitExamUpdates
በጥር ወር 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ ከታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል።
ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የምትወስዱ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባችሁን በተቋም ደረጃ በተጠቀሱት ቀናት አድርጋችሁ መረጃችሁ በምትማሩበት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም አማካኝነት ለትምህርት ሚኒስቴር የሚላክ ይሆናል፡፡
⏩ የክፍያ ጉዳይ፦ ቴሌብር በመጠቀም Payment የሚለውን በመጫን ከዛም Education fee የሚውን በመንካት ከሚመጡ ዝርዝሮች "Educational Assessment and Examinations Service" የሚለውን በመጫን የፈተና አስተዳደር ክፍያ 750 ብር መፈፀም ይጠበቅባችኋል፡፡ (ምስል 2)
⏩ የመውጫ ፈተናውን በድጋሜ የምወስዱ አመልካቾች ምዝገባ የምታደርጉት በራሳችሁ ነው 👉🏽 https://exam.ethernet.edu.et
⏩ የመፈተኛ Password እና የመግቢያ ትኬት የፈተና ጊዜው ሲደርስ የሚሰጣችሁ ይሆናል፡፡
⏩ Username የረሳችሁ forgot username በመጠቀም ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
⏩ ከዚህ ቀደም በተለያየ ሁኔታ ከአንድ ጊዜ በላይ ከተመዘገባችሁ ሲስተሙ ሁሉንም Username ያሳያል፤ አንዱን በቻ ይዛችሁ መመዝገብ ይኖርባችኋል፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ የመምህራን የሥራ ቦታ ዝውውር በቅርቡ ያስጀምራል፡፡
መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች ከታህሳስ 30/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 10/2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት የዝውውር ፎርም እንደሚሞሉ ተገልጿል።
ዝውውሩ ገቢራዊ ከመሆኑ በፊት ዝውውሩን ለማስፈፀም ተሻሽሎ በተዘጋጀ መመሪያ ላይ በዘርፉ ለሚገኙ ባለሙያዎች ስልጠና የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
#MoE #ExitExam
ትምህርት ሚኒስቴር በጥር ወር 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ይሰጣል። ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ ትናንት ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን እስከ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም ይቆያል።
እነዚህ ተማሪዎች በተቋም ደረጃ ምዝገባቸውን በተጠቀሱት ቀናት አድርገው መረጃቸው ለትምህርት ሚኒስቴር የሚላክ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የፈተና አስተዳደር ክፍያ 750 ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት በኩል በመክፈል፥ የከፈሉበትን ኦሪጅናል ደረሰኝ ከነሙሉ ስማቸው ለየትምህርት ክፍላቸው መላክ ይጠበቅባቸዋል።
የመውጫ ፈተናውን በድጋሜ የሚወስዱ አመልካቾች ምዝገባ የምታደርጉት ደግሞ በራሳቸው እንደሆነ ተገልጿል።
ፈተናውን በድጋሜ የሚወስዱ ምዝገባቸውን
https://exam.ethernet.edu.et ላይ ማከናወን ይችላሉ።
የምዝገባ ሒደቱን የሚያሳይ ቪዲዮ👇
https://youtu.be/C9KkQ9AHd2o
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#ERMP
የ2018 ዓ.ም የብሔራዊ ህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና (Ethiopian Residency Matching Program/ERMP) ምዝገባ ተጀምሯል፡፡
ጤና ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በህክምና ዲግሪ ያላቸውንና የስፔሻሊቲ ስልጠና በ2018 ዓ.ም መከታተል የሚፈልጉ አመልካቾችን በብሔራዊ የህክምና ስፔሻሊቲ መግቢያ ፈተና አወዳድሮ ለማሰልጠን ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የዘንድሮው ስልጠና በ22 የማሰልጠኛ ተቋማት እና በ23 የህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች ይሰጣል፡፡
የምዝገባ ጊዜ፦
ታህሳስ 06-20/2018 ዓ.ም
ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች በጤና ሚኒስቴር ድረ-ገፅ (https://www.moh.gov.et) ላይ በመግባት በምትፈልጉት የጤና ስፔሻሊቲ መስክ ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#MekelleUniversity
በ2018 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (ሪሚዲያል ፕሮግራም) መቐለ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ከዛሬ ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ የተዘጋጀውን የGoogle Form (https://forms.gle/FYhfCg3dLhTFyQ477) በመጠቀም መረጃችሁን እንድትሞሉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።
የምዝገባ ቦታ፦
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ፣
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዓዲ-ሓቂ ግቢ።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ12ኛ ክፍል ውጤት መግለጫ፣
➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ፓስፖርት መጠን ጉርድ ፎቶግራፍ፣
ከላይ የተዘረዘሩትን የትምህርት ማስረጃዎች እና ፎቶግራፍ ስካን በማድረግ በተዘጋጀው ሊንክ https://forms.gle/FYhfCg3dLhTFyQ477 ላይ ማያያዝ/መላክ ይጠበቅባችኋል።
የለሊት አልባሳት ማለትም አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
በጥር 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና የሚወስዱ እጩ ምሩቃን ዝርዝርና ሙሉ መረጃ መሙያ ቅፅ
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
DATA_TEMPLATE_LATEST_2018_UPDATED_PRIVATE.xlsx0.20 KB
Photo unavailableShow in Telegram
#ETA
የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና በዓመቱ አጋማሽ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡
በዚሁ መሰረት የተፈታኞች ምዝገባ ከዛሬ ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለማካሔድ የታቀደ መሆኑን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ሰርኩላር ገልጿል፡፡
በዚህም አስፈታኝ የሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምዝገባ ከታህሳስ 06-13/2018 ዓ.ም ስለሚካሄድ በተጠቀሱት ቀናት ብቻ ተፈታኞች እንዲመዘገቡ አስፈላጊውን እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡
ተቋማቱ ፈቃድ በተሰጣቸው የትምህርት መስኮች፣ የትምህርት ደረጃ፣ መርሐግብር እና ካምፓስ በ2018 ዓ.ም አጋማሽ ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ እጩ ምሩቃን ዝርዝር መረጃ ከታች በተያያዘው ቅፅ መሰረት ዝርዝር መረጃውን በተጠቀሱት ቀናት ከዚህ በፊት በምታስገቡበት ሲስተም እንደታስገቡ ባለሥልጣኑ አሳስቧል፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#ExitExam
በጥር ወር 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ለመውሰድ ምዝገባ ያድርጉ!
የተፈታኞች የምዝገባ ጊዜ፦
ከታህሳስ 06-13/2018 ዓ.ም
የመውጫ ፈተናውን የምትፈተኑ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባችሁን በተጠቀሱት ቀናት ማድረግ ይጠበቅባችኋል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Repost from TgId: 1401419976
Photo unavailableShow in Telegram
🚨2 ቀን ቀረዉ 😰
አሁኑኑ ተቀላቅላችሁ , በ4 ወር ዉስጥ ጥሩ የሚባል የ Cyber Security እውቀት ይያዙ . 🧑💻
አሁኑኑ ተመዝገቡ 👨💻
🆘LINK: https://course.geezsecurity.com/course/gtst
✅ ለበለጠ መረጃ
✅ @geezsecsupport
📞 +251953537820
ℹ️ info@geezsecurity.com
#geeztech #gtst @geeztechgroup
Photo unavailableShow in Telegram
🚨2 ቀን ቀረዉ 😰
አሁኑኑ ተቀላቅላችሁ , በ4 ወር ዉስጥ ጥሩ የሚባል የ Cyber Security እውቀት ይያዙ . 🧑💻
አሁኑኑ ተመዝገቡ 👨💻
🆘LINK: https://course.geezsecurity.com/course/gtst
✅ ለበለጠ መረጃ
✅ @geezsecsupport
📞 +251953537820
ℹ️ info@geezsecurity.com
#geeztech #gtst @geeztechgroup
Photo unavailableShow in Telegram
#MoE
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተወዳድራችሁ ያለፋችሁና በየትምህርት ቤቶቹ የተመደባችሁ የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 11 እና 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
ወደ ትምህርት ቤታችሁ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ለ9ኛ ክፍል የሚያስፈልጉ የመማሪያ ቁሳቁሶች (ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ ቦርሳ፣ የስፖርት ትጥቅ፣ ወዘተ)
➫ የመኝታ አልባሳት (አንሶላ እና ብርድ ልብስ)
➫ ስትማሩ ከነበረበት ትምህርት ቤት መሸኛ እና የትምህርት ውጤት
ዩኒፎርም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ውል ከያዘበት አቅራቢ ድርጅት በራሳችሁ ወጪ የሚሸፈን መሆኑ ተመላክቷል።
ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞ ወይም ዘግይቶ ወደ ትምህርት ቤቶቹ መሔድ እንደማይቻል ተገልጿል።
Ethical Hacking በአማርኛ እየተየቃቹ ከ0 ጀምራችሁ ተማሩ ✅
ይሄን በመንካት ይመዝገቡ 🔗 https://course.geezsecurity.com/course/gtst
Contact Us
✅ @geezsecsupport
📞 +251953537820
📬 info@geezsecurity.com
#geeztech #gtstv2 @geeztechgroup
Photo unavailableShow in Telegram
#DillaUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
የምዝገባ ቦታ፦
➫ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ የተመደባችሁ አዳያኣ ግቢ፣
➫ በማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የተመደባችሁ ሀሴደላ ግቢ።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ መጠኑ 3x4 የሆነ አራት ፎቶግራፍ፣
➫ ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#WolaitaSodoUniversity
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ትምህርት ወደ ተቋሙ ለተመደቡ ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል።
የሪሚዲያል ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም እና በቦዲቲ ካምፓስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ጥር 01/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
የምዝገባ ቦታ፦
➫ ስማችሁ ከ A-B የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቦዲቲ ካምፓስ፣ ቦዲቲ ከተማ
➫ ስማችሁ ከ C-R የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ዋናው ግቢ፣ ወላይታ ሶዶ ከተማ
➫ ስማችሁ ከ S-Z የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ፣ ታርጫ ከተማ
➫ ስማችሁ ከ A-B የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቦዲቲ ካምፓስ፣ ቦዲቲ ከተማ
➫ ስማችሁ ከ C-S የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዋናው ግቢ፣ ወላይታ ሶዶ ከተማ
➫ ስማችሁ ከ T-Z የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ፣ ታርጫ ከተማ
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና 2 ኮፒ፣
➫ ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣
➫ ብርድ ልብስ፣አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
