ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
الذهاب إلى القناة على Telegram
2025 عام في الأرقام

133 780
المشتركون
-1024 ساعات
-1197 أيام
-58130 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ!
መልካም በዓል ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን።
@EliasMeseret
🙏 146❤ 86👍 41😁 35🤔 8😢 4
Photo unavailableShow in Telegram
ከቅርብ ወራት በፊት በመግስት ሚድያዎች "ንፁሀን ዜጎችን ሲገድሉ፣ ሲደፍሩ፣ ሲዘርፉና ሲያፈናቅሉ ነበሩ" የተባሉ ታጣቂዎች አሁን "የወርቅ ማሽንና ትራክተር ቀረበላቸው" ተብሎ በነዚሁ የመንግስት ሚድያዎች ሲነገር መልዕክቱ ምን ይሆን? ነፍጥ አንግቦ መንቀሳቀስ ወርቅ ያስገኛል?
የቀድሞ ታጣቂዎችን በስርዐቱ እና የሀገር አቅም በፈቀደ መጠን ማቋቋም ተገቢ ነው፣ በዚህ መልኩ ያውም በመንግስት ሚድያ 'ወርቅ በወርቅ ሊሆኑ ነው' አይነት ዜና ሎሎችን ወደ ትጥቅ እንቅስቃሴ ሊስብ ስለሚችል ቢታሰብበት።
As the saying goes, messaging is everything!
@EliasMeseret
👍 457😢 140❤ 123😁 73🤔 24😱 6🙏 5🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ ላላት 130 ሚልዮን ገደማ ህዝብ ያለው 42 የሚሆን የመንግስት ዩኒቨርስቲ ነው፣ ይህም ለ3 ሚልዮን ህዝብ አንድ ዩኒቨርስቲ ማለት ነው። ከህዝብ ብዛት ስሌት በመነሳት የዩኒቨርስቲ ቁጥሮች ሲታይ ኢትዮጵያ በአለም ይቅርና በአፍሪካም እጅግ ዝቅተኛ የዩኒቨርስቲ ቁጥር (density) ካላቸው ሀገራት አንዷ ነች።
በየዓመቱ ደግሞ 40 ሚልዮን ተማሪ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ እየተማረ ዩኒቨርስቲ ለመግባት ይጥራል፣ ያልማል።
ታድያ በዚህ መሀል እነዚህ ዩኒቨርስቲዎች መስፈት ካላሟሉ እንኳን እንዲያሟሉ ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ የሚገባው የትምህርት ሚኒስቴር ዘግቷቸው አዳሪ ትምህርት ቤት ሊያረጋቸው እንደሚችል ይዝታል።
እርግጥ ነው በመላ ሀገሪቱ የአዳዲስ መንገዶች፣ የኢንደስትሪ ፓርኮች፣ የዩኒቨርስቲዎች፣ የሆስፒታሎች ወዘተ ግንባታ ድሮ ከነበረበት ፍጥነት ካሽቆለቆለ ዓመታት ተቆጥረዋል።
በዚህ አያያዝ ግን ቀድመው የተሰሩ መንገዶችን መጠገን ስላልተቻለ ይታረሱ፣ ኢንደስትሪ ፓርኮች ማምረት ስላልቻሉ የካድሬ ማሰልጠኛ ይሁኑ... እንዳይባል ስጋት ያለው ሰው ቢኖር አይደንቅም።
@EliasMeseret
❤ 518😁 237👍 87🙏 56😢 52🤔 11😱 7🕊 4
Photo unavailableShow in Telegram
ይህ የማዳበርያ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ሊሳካ መሆኑ የሀገራችንን ኢኮኖሚ ከርካታ ቢሊዮን ዶላሮች ወጪ ከመታደጉ በተጨማሪ በማዳበርያ እጦት ለሚሰቃየው አርሶ አደር ትልቅ ብስራት ነው። ዳንጎቴ በዘርፉ የካበተ ልምድ ስላለው በተባለው 40 ወራት ግዜ ውስጥ ያጠናቅቀዋል ተብሎ ተስፋ ተጥሏል።
#ThisIsBig
❤ 742👍 351🙏 67😁 39🤔 11🕊 5😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
ይህ ድርጊት በተለይ በአዋሽ ባንክ እና በአማራ ባንክ በስፋት እየተስተዋለ ነው። የሚሰቃዩት ሰራተኞች አፋጣኝ ምላሽ ይፈልጋሉ... በዚህ መልኩ ሰራተኛን ማሰቃየት ተገቢ አይደለም፣ ጉዳዩ መፍትሄ ካልተሰጠው መሠረት ሚድያ በዚህ ዙርያ ተከታታይ ዘገባዎቹን ማቅረብ ይቀጥላል፣ ከብሔራዊ ባንክ ምላሽ አካተን በቅርቡ ሌላ መረጃ እናቀርባለን።
https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/b4c?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
👍 287❤ 130😢 53🙏 42😁 18🤔 10🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
ይሄ መልካም ዜና ነው፣ መንግስት የሰራተኛውን ችግሩን ተረድቶ መፍትሄ መስጠቱ ይበል ያሰኛል።
አሁንም ጭማሬውን ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ እንደ የቤት ኪራይ እና የሸቀጦች ዋጋ ላይ ትኩረት ማድረግ እንዲሁም ከሁሉም በላይ የብርን የመግዛት አቅም ማረጋጋት ላይ ስራ ከተሰራ ቢያንስ የተወሰነ ርቀት ሊጓዝ ይችላል።
ሙሉ መረጃው: https://www.facebook.com/share/p/1LrEyZSAzd/
👍 532❤ 144😁 38🙏 31🕊 10🤔 6😱 5😢 5
"የጋዜጠኞች ከሕግ አግባብ ውጪ መሰወር በአስቸኳይ ይቁም
ሁለት ጋዜጠኞች መሰወራቸውን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር የተሰጠ መግለጫ"
👍 310😢 45❤ 34🙏 10😁 4😱 2
ከጥቂት ቀናት በፊት ህፃናት እና እናቶችን ጨምሮ 157 ኢትዮጵያውያን ባህር ላይ ሰጥመው ህይወታቸው በአሰቃቂ መልኩ ሲያልፍ አንድ ነገር ሳይተነፍሱ የቀሩት የመንግስት ሀላፊዎች፣ የመንግስት ሚድያዎች እንዲሁም መንግስታዊ ተቋማት በዛሬው ዕለት ያረፈውን አርቲስት ደበበ እሸቱን በማስመልከት በመቶዎች የሚቆጠሩ መግለጫዎችን ሲያወጡ ስናይ ውግንና እንጂ ሰብዐዊነት የሚባል ነገር ምን ያህል ከውስጣችን ተሟጦ እንዳለቀ ቁልጭ አርጎ ያሳያል።
አርቲስቱ ለማንም ይወግን፣ ማንንም ይደግፍ የግል ምርጫው ነው። በማረፉም አዝኖ መግለጫ ማንም ማውጣቱ መብቱ ነው... ግን ሞታቸው እንደሰው ያልታየላቸው እነዛ ሁሉ ዜጎች ያውም እድሜያቸውን ኖረው ጨርሰው ሳይሆን በድንገተኛ አደጋ ከምድር ገፅ ሲጠፉ አለም አዝኖ መግለጫ ሲያወጣ ዝም ተብሎ አሁን ይህን ስናይ እጅግ ያሳዝናል።
ለሁሉም ነፍስ ይማር!
😢 1 103👍 326❤ 162🙏 59😁 20🤔 17🕊 8😱 6
Photo unavailableShow in Telegram
#መሠረትሚድያ ለትርፍ የተቋቋመ ስላልሆነ ትርፍ ሲኖር መልሶ ነፃ የፕሪሚየም አባልነት ለተከታታዮቹ በእጣ ይሰጣል፣ አልፎ አልፎም የፕሪሚየም አባልነት ቅናሽ በማቅረብ መረጃዎቹ ብዙ ሰው ጋር እንዲደርስ ያደረጋል።
በዚህም መሠረት ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የ30 ፐርሰንት የፕሪሚየም አባልነት ቅናሽ አድርጓል። ይህን ሊንክ ተጠቅመው አሁኑኑ የፕሪሚየም ቦታዎን ይያዙ: https://meseretmedia.substack.com/30pcoff
ለወደፊትም ለበርካታ ሰዎች ለመድረስ የምናደርገውን ጥረት እንቀጥላለን።
👍 207❤ 91😁 68🤔 7🙏 6
Photo unavailableShow in Telegram
የፌደራል ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አርማን (logo) ለመቀየር ባንኩ የሄደበትን መንገድ በፍጥነት ማስቆማቸው ይበል የሚያሰኝ ነው።
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አርማ በመቀጠል እጅግ ልዩ የሆነ ዲዛይን ያለው እና ከአምስት አስርት ዓመታት በላይ ያገለገለውን አርማ ምስሉ ላይ በሚታየው አርማ ባለፈው ሳምንት ለመቀየር ታስቦ እንደነበር ሰራተኞቹ መረጃ ሲያደርሱኝ ነበር፣ ለአዲሱ አርማ በሚገርም ሁኔታ 600 ሚልዮን ብር እንደወጣበትም ሪፖርተር ዘግቧል።
በርካታ አለም አቀፍ ባንኮችም ሆኑ ሌሎች ተቋማት አርማ ሲቀይሩ የቀደመውን ተንተርሰው ይቀይራሉ፣ አገልግሎቱንም ያስታውሳሉ/ይዘክራሉ።
ከሰማንያ ዓመት በላይ ታሪክ ያለው ባንክን በዚህ መልኩ በአንዴ መቀየሩ የባንኩን እሴት፣ ታሪክ (heritage) አውጥቶ ይጥላል። አንድ የብራንድ ዲዛይን ባለሙያ "አዲሱ ሎጎ የአንድ የቴክ ስታርትአፕ ወይም አንድ የትኛውም አለም ላይ የሚገኝ ድርጅት አርማ ሊሆን ይችላል። ክቡ አርማ ግን ልዩ ነው፣ በዛን ወቅት ኮምፒውተር ሳይኖር እንዴት ሰሩት ብዬ ሳስብ ይደንቀኛል" ብሏል። ሌላኛው ደግሞ 'Always reliable bank' የሚለው ራሱ የ grammar ችግር አለበት።
ይልቅ አርማ ከመለወጥ ወደ አገልግሎት ጥራት ላይ ትኩረት ቢደረግ ሳይሻል አይቀርም።
መልካም ቀን!
@EliasMeseret
❤ 871👍 358😁 86🤔 18😱 15😢 13🙏 4🕊 2
Photo unavailableShow in Telegram
ደንብ አስከባሪዎች ላይ ድብደባ መፈፀም ተገቢ አይደለም፣ ድርጊታቸው ተጣርቶ ፍትህ እንደሚያገኙ ተስፋ እናድርግ!
ከዛ ውጪ ግን የነዚህን ተጠርጣሪዎች ፎቶ እንዲህ ለጥፈው እንዳቀረቡት ሁሉ የከተማውን ህዝብ እና በመንገድ ዳር ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ዜጎችን ሲቀጠቅጡ የሚውሉ ደንብ አስከባሪዎችም ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል፣ ሀሉም ዜጋ እኩል መብት ስላለው።
(ተጠርጣሪዎች እንጂ ፍርደኛ ስላልሆኑ መልካቸውን ሸፍኜዋለሁ)
@EliasMeseret
👍 839❤ 159🙏 60😁 32🤔 14
Photo unavailableShow in Telegram
ከ68 በላይ የሆኑ ዜጎቻችንን ህይወት አጥተናል! ብሔራዊ የሀዘን ቀን የሚያሳውጅ ከፍተኛ አደጋ ቢሆንም እስካሁን አንድ አጭር መግለጫ በፌስቡክ ገፁ ላይ ያወጣው ውጭ ጉዳይ ብቻ ነው (እሱም በዋናው ገፁ አይደለም)። ከ30 በላይ አለም አቀፍ ሚድያዎች የዘገቡት ትልቅ አሳዛኝ አደጋ ሆኗል።
ከታይታ ፕሮጀክት በመላቀቅ የወጣቱን ህይወት የሚቀይር ስራ በመስራት ህይወቱን ታደጉት።
ነፍስ ይማር ወገኖቻችን!
@EliasMeseret
😢 940❤ 128🙏 56👍 12🤔 11😁 3🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
714 ሚልዮን ዛፍ በአንድ ቀን... ቁጥሮቹ ሲፈተሹ!
በመጀመርያ፣ በቅርቡ በሌላ አንድ ፅሁፌ ላይም እንዳነሳሁት ሰባም ይሁን ሰባት መቶ ሚልዮን ችግኝ መትከል በጎ ስራ ነው፣ መንግስት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መሀል የማደንቀው አንዱ ነው።
ይሁንና እንደ አንድ ተራ ዜጋም ሆነ የሚድያ ባለሙያ ቁጥሮች ላይ ፍተሻ ማድረግ ይጠቅማል ብዬ አስባለሁ፣ ቁጥሮቹ ዞረው ዞረው የደን ፖሊሲ የሚዘጋጅባቸው ግብዐቶች ስለሆኑ።
1ኛ: በዛፍ ተከላው ላይ 30 ሚልዮን ገደማ ኢትዮጵያዊ (ከኢትዮጵያ ህዝብ 25 ፐርሰንት ገደማው) ተሳትፏል ተብሏል። በዚህ ዙርያ ያነጋገርኳቸው እና በፕሮግራሙ ዙርያ የሰሩ ሰዎች ይህ ፍፁም ሊሆን እንደማይችል፣ በተለይ ዘንድሮ የመንግስት ሰራተኞች እና በአንዳንድ ስፍራዎች አርሶ አደሮችን ማሳተፍ ተቻለ እንጂ ከቀድሞ አመታት ያነሰ የሰው ቁጥር እንደነበር ተናግረዋል። በእለቱ ህፃናትን፣ አዛውንቶችን፣ ታማሚዎችን ጨምሮ ከአራት ኢትዮጵያዊ አንዱ ችግኝ ተክሏል? የሚለውን እጅግ ገራሚ ቀጥር እንያዝ
2ኛ: በእለቱ 714 ሚልዮን ችግኝ ተተክሏል የተባለው አንድ ሰው 24 ችግኝ ሲተክል ነበር ተብሎ ነበር። በድጋሚ በዚህ ዙርያ ያሉኝ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ብዙ ቦታ የችግኝ እጥረት እንደነበር፣ ምናልባት አንድ ሰው በአማካኝ በዛ ከተባለ አምስት እና ስድስት ሲተክል እንደነበር ይጠቁማሉ። ገፋ እናርገው እና 10 ችግኝ ተከለ ብንል 714 ሚልዮን ችግኝ ለመትከል 71.4 ሚልዮን ኢትዮጵያዊ (ማለትም ከኢትዮጵያ ህዝብ ከግማሽ በላይ) ችግኝ ሲተክል ነበር ማለት ነው። ይህንንም እንያዝ።
3ኛ: የግብርና ሚኒስቴር ዳታዎች እንደሚያሳዩት አንድ ችግኝ ለመትከል 4*4 የሆነ መሬት ጥቅም ላይ ይውላል፣ 14 ሜትር ስኩዌር ማለት ነው። በዚህ ስሌት 714 ሚልዮን ችግኝ ለመትከል 11.4 ቢልዮን ሜትር ስኩዌር (ወይም 1.142 ሚልዮን ሄክታር) መሬት ያስፈልጋል። ይህ ደግሞ ከኢትዮጵያ የቆዳ ስፋት 1 ፐርሰንት ነው። ይህን ያህል መሬት በአንድ ቀን በደን ተሸፍኗል? ይህን ያህል ግዙፍ ቦታ ማን ለችግኝ ተከላ አዘጋጀው? ይህንንም እንያዝ።
4ኛ: ኢትዮጵያ ተመሳሳይ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ከዛሬ ስድስት አመት ጀምሮ ስታካሂድ ቆይታለች፣ ለምሳሌ እ.አ.አ በ2019 ዓ.ም 350 ሚልዮን ችግኝ ተተክሏል ተብሎ ነበር። ይሁንና የዛፎቹ የማደግ/መፅደቅ ምጣኔ 20 ፐርሰንት ገደማ ነው ብንል እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው መሬት በደን ተሸፍኗል። ይሁንና እንደ FAO እና Global Forest Watch ያሉ ተቋማት የሚያወጡት መረጃ ይህን አያሳይም።
ይህ ምን ይነግረናል?
ብዙ ግዜ በሀገራችን ቁጥሮችን እንደፍራለን፣ ለማመን የሚያስቸግሩ ቁጥሮችን መጥራት እየተለመደ ነው። በተጨማሪም እንዲህ አይነት 'performance-based policymaking' መሬት ላይ ተሰርቶ ውጤት ከማየት ይልቅ የተሰራው ስራን በብዛት ማስተጋባት በራሱ ውጤት ይሆናል።
ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱት 5 ነጥቦች ሳይመለሱ፣ አንድም ነፃ አካል ሳያረጋግጠው፣ እንደ ሳተላይት ያሉ ማስረጃዎች ሳይቀርቡ ወዘተ የተሰራውን ስራ በዚህ መልኩ ማቅረቡ ካሁኑ ሀይ ካልተባለ በችግኝ ተከላ ዙርያ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ዘርፍ መቀጠሉ አይቀርም።
እርግጥ ነው የግብርና ሚኒስትሩ ችግኝ ተከላው ካለፈ ከአንድ ቀን በኋላ ከስራ ተሰናብተዋል፣ ስንብታቸው ከዚህ ካነሳሁዋቸው ነጥቦች ጋር እንደሚያያዝ ፍንጮች አሉ።
In the absence of transparency and independent verification, bold reforestation claims may serve more as public relations exercises than true climate action. Tree planting is vital — but not if it’s treated like a numbers game disconnected from ecological and logistical realities.
ስራው የሚደነቅ ነው፣ ነገር ግን የቁጥሮችን ነገር በልክ!
ለዚህ ምላሽ የሚሰጥ አካል ካለ ለአንባቢዎች በቀጥታ አቀርበዋለሁ።
መልካም ምሽት።
@EliasMeseret
❤ 811👍 278😁 98🤔 20🙏 15🕊 2😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
መሸለም፣ መበረታታት ሲገባው ጭራሽ እስር። እውነትን መናገር የሚያሳቅቅ፣ ውሸትን በድፍረት መናገር ኩራት የሆነበት ግዜ ሆነ።
የሚገርመው ራሱ ኢቢሲ ከወራት በፊት በተቋሙ ሰራተኞች ላይ ባደረገው የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ ሂደት የ400 ሰራተኞቹ ሰነድ ፎርጂድ/ሀሰተኛ መሆኑን እንዳረጋገጠ አንድ ሾልኮ የወጣ ዶክመንት ጠቁሞ ነበር።
ይህ ሆኖ እያለ የተቋሙ ሀላፊዎች እርምጃ እንዳይወሰድ ይህን መረጃው እንደደበቁ፣ በጥቆማ አቅራቢዎች ላይም ዛቻ እና ማስፈራርያ እያደረሱ እንደኮነ በወቅቱ የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለጠቅላይ አቃቤ ህግ የፃፈው ደብዳቤ አሳውቆ ነበር።
https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/ed9?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
@EliasMeseret
😢 234❤ 109👍 15😱 9🤔 7🙏 6
Photo unavailableShow in Telegram
መሠረት ሚድያ ከተቋቋመ ገና አንድ ዓመት ባይሞላውም የሚያቀርባቸው መረጃዎች ተፅእኖ መፍጠር ቀጥለዋል፣ የሚመለከታቸው አካላት በፍጥነት ማጣራት ሲያደርጉ እና እርምጃ ሲወስዱ ይታያል።
በቅርቡ ስራውን በቪድዮ እንዲሁም በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ ቋንቋዎች ማቅረብ ይጀምራል። አሁኑኑ የፕሪሚየም አባል በመሆን ትክክለኛ ሀገራዊ መረጃን ይከታተሉ። ሊንክ ⤵️
https://meseretmedia.substack.com/subscribe?coupon=d75e694d
🙏 191❤ 78👍 46😁 21
Photo unavailableShow in Telegram
ይህ ትክክለኛ እና ወቅታዊ ጥሪ ነው፣ የማህበራዊ ሚድያውን ተፅእኖ ከግምት ውስጥ በማስገባት በትብብር ለመስራት መፈለግ በራሱ አንድ ለውጥ ነው።
በርካታ የሙስና ተግባራትን እየተከታተለ መረጃ እያቀረበ የሚገኘውን መሠረት ሚድያን ተባባሪ አድርጋችሁ መዝግቡልን!
@EliasMeseret
🙏 216❤ 67👍 42😁 33🤔 5
Photo unavailableShow in Telegram
በመላው አለም አንድን እክል ለመሸፈን ታክቲካል የህዝብ ግንኙነት (PR) ስራ በብልጠት ይሰራል፣ እኛ ሀገር እክሉን ይበልጥ የሚያጎላ የሚድያ ጋጋታ በማብዛት የህዝብ መሳለቂያ ይሆናል።
'የኮሪደር ልማቱ እንደ ኖህ መርከብ አተረፋችሁ እንጂ'... አይነት ነገር እየተነገረን ነው 🤔
በዚህ ዙርያ ኢንጅነር ዮሐንስ መኮንን የሰጠውን ሙያዊ አስተያየት ስናነብ እንዲህ ይላል:
"ወንዝ ላይ አነስተኛ ዉኃ መከተርያም ሆነ ግድብ ሲሠራ ባለሙያዎች የወንዙን ተፋሰስ መጠን (Catchment area) በማጥናት እና ከሜትሪዮሎጂ መረጃ በማስላት ያልተጠበቀ ጎርፍ የሆነ ቀን ቢመጣ ማስተንፈሻ መንገዶችን አስቀድመው ያበጃሉ::
መስቀል አደባባይ አጠገብ እምብዛም ዉኃ በሌለው መሀል አዲስ አበባን አቋርጦ በሚሄደው ጅረት ላይ በቅርቡ አልፎ አልፎ አነስ አነስ ያሉ መከተሪያዎችን (ግድብ ላለማለት) ታስቦ ወራጁ ወንዝ ላይ በኮንክሪት ተሠርቷል:: ከእነኚህ አንደኛው ባለፉት 7 ዓመታት ኢሬቻ የሚከበርበት ቦታ እንደመሆኑ ተጨማሪ ዉኃ ለመከተር ታስቦ የተገነባው ነው::
በተያያዝው ቪዲዮ ላይ እንደምትመለከቱት (https://www.facebook.com/share/v/1Bt5eWvywu/) ሙያዊ ባልሆነ መንገድ የተገነባው ይህ የኮንክሪት መከተሪያ የጎርፍ መጠን ሲጨምር ማስተንፈሻ አማራጭ ስላልታሰበለት የዛሬውን በመጠኑ ትንሽ ክፍ ያለ ዝናብ ማስተናገድ አቅቶት ከተፈጥሮአዊው ከመፋሰሻው ወጥቶ አካባቢውን አጥለቅልቆ ጉዳት አድርሷል::
በአካባቢው ያሉ ሕንጻዎች ምድር ቤታቸው ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ ሲሆኑ በርካታ መኪኖችም በጎርፍ ተውጠው ከፊሎቹም እየተንሳፈፉ ሲሄዱ በአከባቢው የነበርን በኅዘን እያየን ነበር:: አንዳንድ ባለመኪኖችም ወገባቸው ድረስ በጎርፍ ተውጠው መኪናቸውን ለማዳን ጥረት ሲያደርጉ ይታዩ ነበር::
የኮሪደርም ሆነ የወንዝ ዳርርቻ ልማት ተብሎ የተጀመረውን ሥራ ከተማን የማሳመርም ሆነ የእግረኛ እና የብስክሌት መንገዶች የመገንባት ሃሳቡ መልካም እና የሚደገፍ ሆኖ ትግበራው ግን "ካድሬአዊ" ሳይሆን "ሙያዊ" ይሁን የሚል ሀሳብ ሲቀርብ "ጥድፊያ ላይ ስለሆንን ለምክር እና ለዲዛይን ጥናት ጊዜ የለንም" የሚሉ ባለሥልጣናት ቢያንስ ይህንን ከመሰለ ስህተታቸው እንዲማሩ እመኛለሁ::
ሥራን በሠከነ እና ሙያዊ በሆነ መንገድ አለመሥራት ውጤቱ ከዚህ ውጪ ሊሆን አይችልም:: ለታይታ እና ለምርቃት ብቻ በመጉዋጉዋት በችኮላ እና በግርግር ዕውቀት እና ልምድ የሚፈልግን ሥራ ጠቅልሎ በኮሚቴ እና በካቢኔ ውሳኔ አየገነቡ እና እያፈረሱ መሄድ የሀገርን ሀብት ለብክነት መዳረግ ነው::
@EliasMeseret
❤ 578👍 199😁 46🤔 14😱 4🙏 1🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በሚፈለገው መጠን ባይሆንም አቅም በፈቀደ መጠን ዜጎች ሲፈናቀሉ፣ ሲገደሉ እና ሰብአዊ መብታቸው ሲገፈፍ ተከታትሎ የሚያጣራ ተቋም ነበር... ኮሚሽኑ አዲስ ኮሚሽነር ከተሾመለት በኋላ ግን እሱ አበቃለት፣ ዛሬ ደግሞ የነበረው እንጥፍጣፊ ተስፋ ተሟጦ አልቆለታል። ከዚህ በኋላ ዜጎች ሲሰቃዩ የሚያስተባብል ተቋም ይኖረናል ተብሎ ይገመታል።
ለተሰናባች ሰራተኞች ግን ከፍ ያለ ምስጋና!
@EliasMeseret
❤ 391😢 167🙏 45👍 38🤔 11😁 3😱 3
Photo unavailableShow in Telegram
የደሞዝ ገቢ ግብር ከ2 ሺህ ብር ጀምሮ ሆኖ መፅደቁ ህግ አፅዳቂው አካልም ሆነ መንግስት ምን ያህል ከህዝቡ ኑሮ በእጅጉ ርቀው እንዳሉ አንድ አመላካች ነው።
ባለፉት ሁለት አመታት ብቻ ምግብ ነክ ምርቶች እስከ 200 ፐርሰንት በጨመሩበት ወቅት እንዲሁም መንግስት የራሱን በጀት ሲያደላድል የኤሌክትሪክ፣ የውሀ፣ የቴሌ፣ የንግድ ግብር፣ የኪራይ ግብር፣ የጣርያ/ግድግዳ፣ የዳኝነት ክፍያ፣ የነዳጅ ድጎማ ማስቀረት... ወዘተ እያለ ባለበት ግዜ የሁለት ሺህ ብር ደሞዝ ገንዘብ ሆኖ ታክስ ሲጥል ማየት በእጅጉ ያሳዝናል።
አንዱ ሀላፊማ ይህ የደሞዝ ታክስ ከ600 ብር ወደ 2 ሺህ ብር ማደጉን ለማስረዳት '12 መንገድ ይገነባ ነበር' ብሎ ሲሳለቅ ነበር... ይህንንም እኛ ስለሆንን ነው አይነት አመክንዮ።
#ReallySad
@EliasMeseret
😢 1 109❤ 170👍 69🤔 33😁 28🙏 23😱 7🕊 6
Photo unavailableShow in Telegram
#ጥሩዜና መሠረት ሚድያ በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ ቋንቋዎች መረጃ ማቅረብ ለመጀመር ዝግጅት እያረገ ነው።
#እጣ አንድ ወዳጅ ለመሠረት ሚድያ 20 ተከታታዮች የፕሪሚየም አባልነት ክፍያ ለመፈፀም ቃል ገብቷል፣ እንደተለመደው ቴሌግራም @ContactElias ላይ ኢሜይላችሁን በመላክ እጣ ውስጥ መግባት ትችላላችሁ።
#ፕሪሚየም ሚድያው እንዲህ ለሌሎች እንዲዳረስ ስጦታ ለሌሎች ማበርከት የምትፈልጉ info@meseretmedia.org ላይ ልትፅፉ ትችላላቹ። በቀጥታ የፕሪሚየም አባል ለመሆን ደግሞ ⤵️
https://meseretmedia.substack.com/subscribe?coupon=87fb8725
👍 288❤ 118😁 28🙏 24😢 2😱 1
