ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
الذهاب إلى القناة على Telegram
2025 عام في الأرقام

133 768
المشتركون
-1024 ساعات
-1197 أيام
-58130 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
አንድ የመሠረት ሚድያ ተከታታይ ለ15 ሰዎች የአንድ አመት subscription ጋብዝልኝ ብሎ ከፍሏል፣ ቀድማችሁ ቴሌግራም @ContactElias ላይ ኢሜይላችሁን የላካችሁ 15 ሰዎች ግብዣውን ታገኛላችሁ።
ውጭ ሀገር ላላችሁ ደግሞ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የ30% ቅናሽ ተደርጓል፣ በዚህ ሊንክ ታገኙታላችሁ ⤵️
https://meseretmedia.substack.com/subscribe?coupon=d75e694d
❤ 255👍 98😁 31🙏 23😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
መሠረት ሚድያ "ነዳጅ የሚቸበችቡት የመንግስት ባለስልጣናት" በሚል ርዕስ የዛሬ ስድስት ወር የሰራው አንድ ዘገባ ነበር።
በዚህ ዘገባ ላይ ትናንት በቁጥጥር ስር የዋሉትን የሲዳማ ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ሀላፊዎች (መጠኑ ያነሰ ቢሆንም በወላይታም ጭምር) በዚህ ህገወጥ ድርጊት ላይ እየተሳተፉ እንደነበር መረጃ ከማስረጃ ጋር ቀርቦ ነበር።
እንደተለመደው የክልሉ ካድሬዎች በወቅቱ የመሠረት ሚድያ ዜናን "የክልሉን እና የአመራሮቹን ስም ለማጥፋት፣ ብጥብጥ ለማስነሳት፣ ሀዋሳን የትርምስ ማዕከል ለማድረግ... " እያሉ ሲንፈራገጡ ነበር።
ስድስት ወር ቢፈጅም... Still, better late than never!
#ግዜደጉ
@EliasMeseret
❤ 557👍 241🙏 31😁 9🤔 8😱 3
Photo unavailableShow in Telegram
አምስት አመት ሙሉ ህግ የተማርኩት ትዝ አለኝ!
ይህ በያሬድ ሀይለማርያም የተከተበ ፅሁፍ ይነበብ ⬇️
በዋስትና ጉዳይ እስከ ሰበር መሄዳችሁ ሳይበቃ የሦስት ፍርድ ቤት ውሳኔን ፖሊስ አላከብርም ካለ ለምን ፍርድ ቤቱን አትዘጉትም?
ፖሊስ በተደጋጋሚ የፍርድ ቤቶችን ውሳኔ እጅግ አስነዋሪ በሆነ መንገድ ሆን ብሎ ሲጥስና በዚህ ደረጃ የፍትህ ሥርዓቱን ሲያዋርድ ማየት ሕግ አስፈጻሚው አካል እራሱ ሕገ ወጥነትን ብቸኛ አፈናን የማጽኛ መንገድ አድርጎ መምረጡን ማሳያ ነው። ይህ ችግር አንዴና ሁለቴ ተፈጽሞ ቢያበቃ ጉዳዩ ፖሊስ ጋር ያለ ችግር እንደሆነ ተደርጎ ይወሰድ ነበር።
ይህ አይነቱ ሕገ ወጥነት ሲደጋገምና እንደ ትክክለኛ አሠራር ሲወሰድ ግን ፍትህ ሚንስትሯን ጨምሮ እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድረስ ስምምነት ተደርጎበት የሚከናወን ሕገ ወጥነትን ሕጋዊ የማድረግ የፖለቲካ ውሳኔ ነው።
- ጋዜጠኛ ተስፋለም ከመጀመሪያ ፍርድ ቤት አንስቶ ሰበር ድረስ በዋስትና እንዲለቀቅ በየደረጃው ሦስት ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ ግለሰቡ ዋስትናውን ካስያዘ በኋላም ፖሊስ አለቅም የሚለው በምን አግባብ ነው?
- የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ማይክ መላኩም እንዲሁ ከአመት በላይ አታሰረ በኋላ በቅርቡ 300ሺ ብር ዋስትና ተጠይቆበት ገንዘቡን አስይዞ ከማረሚያ ቤት ሲወጣ በር ላይ ጠብቀው አቃቤ ሕጉና ደህንነቶች አፍነው ሰውረውታል፣
- በሌሎችም በርካታ የፖለቲካ ተከሳሾች ላይ ፍርድ ቤት ዋስትና ከፈቀደ በኋላ ፖሊስ አለቅም እያለ ዜጎች ለእንግልት ይዳረጋሉ።
- በሕጉ በዋስትና በሚያስለቅቁ ጉዳዬች ከይግባኝም አልፎ እስከ ሰበር መሄድ ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው?
ቅጥ ያጣ ሥርዓት አልበኝነት ይቁም!
@EliasMeseret
❤ 472😢 149👍 89🤔 28🙏 10🕊 3
Photo unavailableShow in Telegram
#መልካምዜና የሁላችሁም ድምፅ የሆነው መሠረት ሚድያ ከእኔ ጫንቃ እና ኪስ ተላቆ ራሱን ችሏል 🎊
ምናልባትም በሀገራችን የሚድያ ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ ሙሉ በሙሉ ከአባልነት (subscription) በሚገኝ መዋጮ ላይ ብቻ ተመርኩዞ የሚንቀሳቀስ እንዲሆን ታስቦ የዛሬው ወር የተጀመረው ስራ ተሳክቷል።
ለዚህ የሚሆን በቂ ሰዎች subscriber ሆነዋል፣ ለሪፖርተሮች ክፍያ እና ሌሎች ወጪዎች ራሱን ችሎ የሚንቀሳቀስ ሚድያ ሆኗል ማለት ነው። ይህም ሚድያው ከተመሰረተ በ10 ወራት ውስጥ ብቻ ከህዝብ ላገኘው ተቀባይነት ትልቅ ማሳያ ነው።
ከዚህ በኋላ 'subscribe አርጉ' ከተባለ ለሚድያው ድጋፍ ለማረግ ሳይሆን ልዩ መረጃዎችን እና የምርመራ ዘገባዎችን ከመሠረት ሚድያ እንድታገኙ ለመጠቆም ብቻ ይሆናል። ሊንክ: https://substack.com/@meseretmedia
ሁላችሁንም በሚድያው ስም አመሰግናለሁ 🙏🏽
@EliasMeseret
👍 1 339❤ 286🙏 52😁 40🕊 16🤔 4😱 3
#ዜናመሠረት የኢትዮጵያ ኢንሳይደር መስራች ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ መታሰሩ ታወቀ
በአዲስ አበባ ከሚገኘው ግዮን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋለው ተስፋለም ሌሊቱን እስጢፋኖስ አካባቢ በሚገኝ የፖሊስ መምሪያ ሕንፃ ውስጥ ወንበር ላይ እንዲያሳልፍ መደረጉን ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ገልጿል።
https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/82f?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
🤔 101😢 79❤ 55👍 17😱 5🕊 5
Photo unavailableShow in Telegram
እንደዛማ ከሆነ እኔም የደሞዝ ጥያቄ አለኝ! እስካሁን ከኪሴ ገንዘብ እያወጣሁ እና በነፃ እያገለገልኩ ያቋቋምኩት መሠረት ሚድያ ከዚህ በኋላ ደሞዝ ሊከፍለኝ ስለሚገባ Subscribe አርጉ፣ እድሜ ልክ በነፃ ማገልገል የለም 🙃 ⤵️
https://substack.com/@meseretmedia
😁 1 306❤ 134👍 74🤔 23😢 12
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ!
ኢድ ሙባረክ!
@EliasMeseret
👍 151❤ 60🙏 6
ከመንግስት እና ከግል ሰራተኞች ደመወዝ ላይ 'ለአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ' ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ የነበረው ሀሳብ መቅረቱ ተሰምቷል!
በዚህ የኑሮ ውድነት ይህን የሌለ ሀሳብ ያመጣውን ግለሰብ ነበር ህገ መንግስታዊ ስርዐቱን በሀይል ለመናድ፣ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ከሆኑ የውጭ ሀይሎች ጋር በመተባበር እና የከተማ ውስጥ ሁከት ለማነሳሳት በማሴር የሚል ጠብሰቅ ያለ ክስ መክሰስ ነበር።
@EliasMeseret
😁 1 748👍 305❤ 163🕊 9🤔 7😱 3😢 2
Photo unavailableShow in Telegram
ቅጣት እንደ ቋሚ ገቢ ምንጭ?
ለምን በሌላው ሀገር እንደሚደረገው በመጀመርያ ለህዝብ በስፋት ግንዛቤ መፍጠር፣ ከዛ ፕላስቲኮችን ሰብስቦ ለ recycling እንዲውሉ ከሳንቲም ጀምሮ ክፍያ እንዲኖረው ማትጊያ/ማበረታቻ ማዘጋጀት፣ ምናልባት ይህ ካልተሳካ በመጨረሻ ወደ ቅጣት አይኬድም (ቅጣት የሚባል ነገር ብዙ ሀገራት ከነጭራሹ ባይኖርም?
ነው ወይስ ቅጣት በይፋ የመንግስት የገቢ ምንጭ እንዲሆን ታስቧል?
@EliasMeseret
😁 827👍 247❤ 166🤔 151😢 77🙏 54😱 9🕊 7
Photo unavailableShow in Telegram
"በቴሌኮም ዘርፍ እጅግ ተወዳጅ የኢትዮጵያ ብራንድ"
ውድድሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ጋር ከሆነ ታድያ ከማን ጋር ተወዳድሮ ነው? ኧረ ተዉ ግን 🤔
@EliasMeseret
😁 1 227🤔 37❤ 35😢 11😱 10🙏 7🕊 4
Photo unavailableShow in Telegram
ክፋት በሩ ላይ እንደሚጠብቀው እያወቀ እንኳን ያመነበትን ከመናገር ወደኋላ የማይለው አቶ ታዬ ደንደአ!
ሀሳብን በሰላማዊ መንገድ ማህበራዊ ሚድያ ላይ መግለፅ ለእስር ከዳረገ ለሌላው ዜጋ የሚሰጠው መልእክት ምንድን ነው?
@EliasMeseret
❤ 958👍 257😢 121🤔 26😁 16😱 10🙏 7
በዚህ ምክንያት ህይወቱን ያጣ፣ ኑሮው የተመሳቀለ እና የማይወጣው ችግር ውስጥ የገባው ብዙ ነው።
እነዚህ ዜጎች አሁንም ፍትህ የማያገኙ ከሆነ የምርመራ ዘገባው ከጀርባ ሆነው ይህን ድርጊት ከለላ የሰጡት ላይ ትኩረት በማድረግ ይቀጥላል።
https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/33c?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
👍 311😢 238❤ 76😱 29😁 7
Photo unavailableShow in Telegram
መሬት ላይ እየሆነ ካለው ነገር ባልተናነሰ እውነታውን ለመሸሸግ የሚደረገው ሙከራ ያሳስባል!
@EliasMeseret
😁 951😢 274❤ 76👍 76🤔 60🙏 41🕊 11😱 10
ትክክለኛ እርምጃ!
#FreedomOfSpeech
#FreedomOfExpression
#FreedomOfThePress
#ዜናመሠረት አሜሪካ በዜጎቿ እና በነዋሪዎቿ ላይ የሶሻል ሚድያ እቀባ የሚያደርጉ መንግስታት ሀላፊዎችን ቪዛ ልትከለክል መሆኑ ተሰማ
- "የውጭ ሀገራት መንግስታት በአሜሪካ ምድር ላይ ተኹኖ ለተፃፈ የሶሻል ሚድያ ፅሁፍ ማስፈራርያ ወይም የእስር ትእዛዝ ማቅረብ አይቻላቸውም"- ማርኮ ሩቢዮ
https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/cf6?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
👍 410❤ 98😁 42🙏 9🤔 8😱 5
Photo unavailableShow in Telegram
ይህ የዛሬ የኬንያው 'ዴይሊ ኔሽን' ጋዜጣ እትም ነው፣ በፊት ገፁ ላይ 'State Terror' ወይም 'መንግስታዊ ሽብር' በማለት የሀገሪቱ መንግስት በአንዳንድ ፖለቲከኞች ላይ እየፈፀመ ነው ያለውን የወንጀል ድርጊት ያጋልጣል።
ወደ እኛ ሀገር ስንመጣ ሪፖርተር ጋዜጣ ፓርላማ ተገኝቶ በይፋ የተባለውን፣ የተነገረውን ለህዝብ ስላቀረበ ፓርላማ ተገኝቶ እንዳይዘግብ ይታገዳል።
The difference is uncanny!
@EliasMeseret
🙏 672👍 255😁 88😢 82❤ 58🤔 39😱 8
Photo unavailableShow in Telegram
አንድ ዶክተር በመሠረት ሚድያ ኢሜይል በኩል ይህን አጋርቶኝ ማለፍ ከበደኝ! ይነበብ!
"ሰላም ጤና ይስጥልኝ! አንድ ሁሌ የማስበውን ነገር ላጋራችሁ፣ ይህም ምን ያክል የጤና ስርዓታችን እጅግ የወደቀ እና የተበላሸ እንደሆነ ማሳያ ነው።
እኔ በአንድ የሀገራችን ትልቅ ሆስፒታል ሬዚደንት ሀኪም ነኝ። የምንሰራቸው ቀዶ ህክምናዎች አብዛኛውን ጊዜ ረዥም ሰዓት የሚወስዱ ናቸው። አንድ ቀን ግን በጣም ረዥም ሰዓት ነበር የወሰደብን፣ ማለትም 18 ሰዓት ነበር የፈጀው። አስባችሁታል ለ18 ሰዓት ያለ እረፍት ቆመን የረባ ቁርስም ሳንበላ፣ ምሳም እራትም ሳንቀምስ ሌሊት 9 ሰዓት ነበር የወጣነው።
ከዛ ምን እንደፈለግን ታውቃላችሁ በጣም? ከምግብ ይልቅ ውሃ ! ውሃ! ግን ከየት ይገኛል በዛ ሌሊት? የትም! የሰውነታችን ፈሳሽ ስላለቀ ራሱ ከንፈራችን ተሰነጣጥቆ ነበር። እና ታካሚያችንን ወደ ICU ካስገባን በኋላ ትንሽ ጋደም እንበል ብለን ገባን ወደ ዲዩቲ ሩም። ከዛ አንድ ነገር በአእምሮዬ እየተመላለሰ አላስተኛ አለኝ። ምን ዓይነት ጨካኝ ሀገር ላይ ነን ግን? አልኩኝ።
- ካድሬውን በየስብሰባው፣ በየቢሮው 15 ደቂቃም ይሰብሰብ በየጠረጴዛው ቆሎ፣ ውሃ ብፌ ምግብ ቁርጥ ስጋ የሚያቀርብ፣ በቢራ በውስኪ የሚያራጭ እኔንና ጓደኞቼን በጠኔ የሚደፋ
- ይባሱኑ ረብጣ ረብጣ አበል የሚከፍል ለኔና ጓደኞቼ ሲሆን መቀነቱ ባዶ የሚሆን፣ ጉልበቱም የሚደክመው እና ንፉግነቱን የሚያሳየኝ ለምን ይሆን?
-ሌላ ሌላውንስ ውስጡን ለቄስ፣ በእውነት እስኪ ፍረዱኝ ጥያቄዬ የህግም ብቻ ሳይሆን የህሊና ፍርድ ይሻል።
Dr Anonymous
ፎቶ: ፋይል
@EliasMeseret
😢 2 221👍 388❤ 153🙏 46🤔 40😱 13😁 7🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
በጣም ትክክለኛ ያልሆነ መግለ ነው 🙏🏽🙏🏽🙏🏽
በዚህ ልክ ውሸት ግን...
@EliasMeseret
😁 1 269👍 106😢 55🤔 31😱 21❤ 20🙏 5🕊 4
የጤና ባለሙያዎች ዘር፣ ሀይማኖት፣ የፖለቲካ አስተሳሰብ ወዘተ ሳይሉ በመላው የሀገሪቱ ክፍል ለመብታቸው መከበር በህብረት እያሰሙት ያለው ድምፅ ለሀገራችን ፖለቲከኞችም ትልቅ ትምህርት ይሆናል ብዬ አስባለሁ።
ትርፍ ልዩነትን አቻችሎ መሄድ ለራስም፣ ለሀገርም እንደሚጠቅም ከዚህ በላይ ማስረጃ የለም።
@EliasMeseret
👍 1 385❤ 146🙏 33😁 21🤔 6😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
መብትን መጠየቅ እንዴት ነው እንደ ሃጢያት ተቆጥሮ እንዲህ የሚያስብለው?
ኧረ በልክ! አንተ ከህብረተሰቡ የወጣህ አይደለህም እንዴ?
@EliasMeseret
👍 1 109😢 196❤ 49😁 31🤔 17😱 9🕊 8🙏 5
