ar
Feedback
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

الذهاب إلى القناة على Telegram

Journalist-at-large

إظهار المزيد
2025 عام في الأرقامsnowflakes fon
card fon
133 748
المشتركون
-1024 ساعات
-1197 أيام
-58130 أيام
أرشيف المشاركات
የዘርፉ ባለሙያዎች አስረዱን! ታሪካዊ ቅርስ ሲታደስ በዚህ መልኩ የቀድሞ መልኩን እስኪቀይር እንዲህ ይደረጋል? ወይስ አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ይህንኑ ያሳያሉ? @EliasMeseret
إظهار الكل...
👍 682😢 427😱 156😁 99🤔 96 36🙏 22🕊 11
Photo unavailableShow in Telegram
ከጥቂት ሳምንታት በፊት መሠረት ሚድያ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሰራተኞች ከስራቸው ሊቀነሱ እንደሆነ መረጃ አቅርቦ ነበር መረጃው በወጣ በነጋታው የመንግስት ሀላፊዎች ተሯሩጠው "ውሸት ነው፣ አዲስ የፀደቀው የሰራተኞች አዋጅ ተቋማት ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲፈፅሙ የሚያስችል ብቻ ነው" ብለው ነበር። ዛሬስ? እንደ አንበሳ አውቶቡስ አገልግሎት፣ ፖስታ አገልግሎት፣ የተለያዩ የክፍለ ከተማ ፅህፈት ቤቶች... ወዘተ በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ማሰናበት ጀምረዋል። በዚህ ሳምንት ብቻ 450 የፖስታ አገልግሎት ሰራተኞች "በሪፎርም ምክንያት" በሚል ከስራቸው ተነስተው በሌሎች ተተክተዋል፣ ድርጊቱ በዘመድ፣ በእውቅ እና በብሄር ተለይቶ እንደሆነ ሰራተኞቹ ነግረውኛል። አሁን በዚህ የኑሮ ውድነት የእነዚህ ሰራተኞች እና ቤተሰብ እጣ ምንድን ነው? ጎዳና ላይ መውጣት? @EliasMeseret
إظهار الكل...
😢 971👍 210🤔 41 29😱 21😁 9🕊 8🙏 4
Photo unavailableShow in Telegram
ኢሚግሬሽን አላማው ለህዝብ አገልግሎት መስጠት ነው ወይስ ለትርፍ መስራት? ኧረ የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ሚና እንኳን እየለየን?! @EliasMeseret
إظهار الكل...
👍 1 152😢 368😁 144🤔 45🙏 22 19😱 15🕊 7
Photo unavailableShow in Telegram
አንዳንድ ግዜ እነዚህ እኔ ላይ ሲደረጉ የነበሩ ዘመቻዎችን መለስ ብዬ ሳስብ ይገርመኛል! መንግስት በወቅቱ 'ታጋሽ' ሆኖ ይሁን እነዚህ የ 'እሰሩት' ጥሪዎች ውሸት እንደሆኑ ተገንዝቦ ባላውቅም እኔ ላይ አልደረሱም። የሚገርመው ደግሞ እነዚህ የውጭ ጋዜጠኞችን በአካልም፣ በኢሜይልም፣ ወይም በሌላ መንገድ አናግሬያቸው የማላውቅ ናቸው። አግኝቼ አስተርጓሚ ብጠቁማቸውም ምንም ችግር የሌለበት ትብብር ነበር። ግዜ ደጉ፣ ይህን ለእኔ ሲመኙ የነበሩት አሁን የት ናቸው? አንዱ ሳውዲ ለእስር ተዳርጎ፣ በቅርቡም ተላልፎ ተሰጥቶ ሀገር ቤት እስር ላይ ይገኛል። አንደኛው የጦርነት አራራው ወጥቶለት ይመስለኛል የስፖርት ተንታኝ ሆኗል። ለሱሌማን አብደላ ሳይታሰር በፊት በአንድ ጉዳይ ሊያናግረኝ ደውሎ ስህተት እንደሰራ ነግሬ ለውሸቱ ወቅሼዋለሁ፣ አሁንም ትክክለኛ ፍትህ እንዲያገኝ እና ለቤተሰቡ እንዲበቃ እመኛለሁ። #Karma @EliasMeseret
إظهار الكل...
👍 664😁 112 55🤔 28🕊 8
ተቀጣሪ ወይም ነጋዴ ሆነህ ቤት ብትገነባ - ከገቢህ 35% የገቢ ግብር - የመሬቱ ሊዝ - የጣራና ግድግዳ ግብር - ለግንባታው የባንክ ብድር ወለድ - በምትከፍለው እያንዳንዱ ትራንዛክሽን ባንክ ቻርጅና ቫት - አሁን የንብረት ግብር - በሁሉም ክፍያ ላይ ቫት - ከሆነ ባለሥልጣን ጋር ከተነጃጀስክ ውርስ - 30% ግሽበት - ያለምክንያት መዋጮ - ያለዕድሜህ ሽበት - የማይቆም ጦርነት => መፍትሔ:- ባገኘኸው የትኛውንም safe መንገድ ስደት Via Abdulkadir Hajj Nureddin @EliasMeseret
إظهار الكل...
👍 1 655😢 547 86😁 59🤔 45🕊 32😱 26🙏 23
Photo unavailableShow in Telegram
የዛሬ 14 አመት>>> የህዳሴ ግድብን ጀምሮ ለማጠናቀቅ 80 ቢልዮን ብር ይፈጃል ዘንድሮ>>> የግድቡ 97.6 ፐርሰንት ግንባታ ቢያልቅም ቀሪውን 2.4 ፐርሰንት ለመጨረስ 80 ቢልዮን ብር ያስፈልጋል ይህ በራሱ መገበያያ ገንዘባችን ብር ምን ያህል እየወደቀ እንደሆነ ማሳያ ቢሆንም 2.4 ፐርሰንት ስራ ለመጨረስ ይህን ያህል ገንዘብ ያስፈለገበትን ምክንያት የሚመለከታቸው አካላት ለህዝብ በግልፅ ሊያስረዱ ይገባል። Figures via Sheger FM @EliasMeseret
إظهار الكل...
😁 669👍 446🤔 89😢 46 41🙏 28😱 11
ኦቪድ የተባለው ድርጅት የዛሬ አመት ገደማ በሸጣቸው ቤቶች ላይ ቅሬታ ያላቸው ቤት ገዢዎች ለመሠረት ሚድያ ተከታታይ መረጃ ሲልኩ ነበር የቅሬታቸው መሰረትም ቃል በተገባላቸው መሰረት የቤቶቹ ግንባታ እየተካሄደ አይደለም የሚል ነበር፣ ለዚህም የሳይቶቹ የምስል እና የቪድዮ ማስረጃ አለ። ይሁንና በዚህ ያልተደሰቱት ኦቪዶች ሁለት ነገር አደረጉ: አንደኛው የመሠረት ሚድያ ፕላስ (Meseret Media+) የዩትዩብ ቻናል ሞኒታይዜሽንን ሪፖርት አርገው አዘጉ፣ በሌላ በኩል እኔን አናገሩ። ቻናሉን ማዘጋታቸው ትክክል እንዳልሆነ ነግሬያቸው (እንዳዘጉ የተናገሩበት የድምፅ ቅጂ/ሪከርድ ሙሉው አለ) በዜናው ላይ ማንኛውም አይነት ቅሬታ እና ትክክል አይደለም ብለው የሚያስቡት ነገር ካለ ላኩት እና አጣርተን ስህተት ከሆነ ሌላ የእርምት ዜና እንሰራለን አልኩ። እሺ ተባብለን ከጨረስን በሗላ ግን "በአምስት ቀን ውስጥ የመረጃዎቻችሁን ምንጭ አምጡ፣ ወይም እንከሳለን" ብለው ማስፈራርያ መሰል 'ድንፋታ' በኢሜይል ላኩ 🙂 ማስፈራርያው መሠረት ሚድያ ላይ እና ኢትዮ ፎረም ላይ እንደሆነ በሶሻል ሚድያ ገፆቻቸው ፅፈው አየሁ። የሚገርመው ዜናው መሠረት ሚድያ ላይ ከወጣ በኋላ ቤት ገዢዎችን ጠርተው መዘግየት የተፈጠረው በአዲሱ 'ሴት ባክ' ህግ ወዘተ እንደሆነ እና በቅርቡ ግንባታ እንደሚጀመር ራሳቸው ተናግረዋል። ዜናው ውሸት ነው ብለው ካሰቡ ቀላሉ ማስረጃ በዜናው ላይ የተጠቀሱትን የጉለሌ እና የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሳይቶቻቸውን በምስል እና ቪድዮ አስደግፈው አቅርበው የመሠረት ሚድያ ዜናን ውሸት ማጋለጥ ነበር፣ ግን አላረጉም። ሁሉ በእጃቸው እና በደጃቸው የሆነ መስሏቸው ይሁን መንግስት አዲስ አበባ ሊያገኝ ያልቻላቸውን ጋዜጠኞች በዚህ በባለቤትነቱ ዙርያ ብዙ ህዝብ ጥያቄ በሚያቀርብበት ድርጅት በኩል ድምፅ ማፈን የሚችል መስሎት አይታወቅም ይህን ተግባር ፈፅሟል። አንድ ነገር ማለት ይቻላል... በዚህ ዘመን የህዝብን እውነት እና የሚድያን ስራ ማፈን አይቻልም። የፈለገ ያህል ሀብት ያለህ የቢዝነስ ድርጅት ሁን፣ ቱባ ባለስልጣን ሁን። You are selling properties to the public so you remain in the public eye, and no authority can silence criticism or dissenting voices. The voice of the people cannot be suppressed! @EliasMeseret
إظهار الكل...
👍 2 888 312🙏 112🤔 25😁 24😢 12😱 5
ይህ በምስሉ ላይ የሚታየው ማጎርያ ካምፕ ከቃሊቲ ማሰልጠኛ ውሀ ልማት ጀርባ የሚገኝ ሲሆን በርካታ በዝቅተኛ ስራ የሚተዳደሩ ታዳጊዎች እና የጎዳና ተዳዳሪዎች እየታፈሱ የሚገቡበት ነው መሠረት ሚድያ የዛሬ ሁለት ሳምንት በሰራው ዘገባው እድሜያቸው ከ15 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ጭምር በየግዜው እየገቡበት እንደሆነ እና ካምፕ ውስጥ ከገቡ በኋላም ህይወታቸው ያለፈ እንዳሉ ጠቁሞ ነበር። መንግስታዊው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ትናንት ባወጣው መግለጫው ድርጊቱ በቦታው እየተፈፀመ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን ከጎዳና ላይ የተነሱ በርካታ ሰዎች መኖራቸውን እና ድርጊቱ አሁንም መቀጠሉን አረጋግጧል። "ወደ ማቆያው ከገቡት ሰዎች መካከል በማእከሉ ከመቆየት እና የእርሻ ሥራ ከመሥራት እንዲመርጡ በማድረግ የእርሻ ሥራ ለመሥራት የመረጡ ሰዎች በተለያዩ አካባቢዎች ወደሚገኙ እርሻ ጣቢያዎች ተወስደው  እንዲሠሩ እንደሚደረግ ለመገንዘብ ተችሏል። ይህም የነጻነት መብታቸውን ጨምሮ ሌሎች መሠረታዊ የሰብአዊ መብቶቻቸውን የሚጥስ ነው" በማለት ኢሰመኮ አስታውቋል። አሁን በደረሰኝ መረጃ መሰረት ከእነዚህ ዜጎች መሀል 3,700 የሚሆኑት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በአንድ የግል የቡና እርሻ ድርጅት ውስጥ በግዳጅ አምጥተው አስፈረዋቸዋል። ከእነዚህ የጎዳና ላይ ወጣቶች መሀል ህይወት ከብዷቸው አሁን ላይ እራሳቸውን ያጠፉ በርካቶች እንደሆኑ ታውቋል። በዚህ ቃሊቲ ማሰልጠኛ አካባቢ ባለው ስፍራ ታስረው የተለቀቁ ዜጎች "መኝታ እና ምግብ ብሎ ነገር የለም፣ ጤነኛ ሆኖ የገባው ህይወቱ አልፎ ሲወጣ አይተናል" በማለት ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል። የእኔ ጥያቄ: ህዝባዊ እና ሀይማኖታዊ በአላት ሲደርሱ፣ እንደ አፍሪካ ህብረት ያሉ ስብሰባዎች ሲካሄዱ፣ ከተሞች በልማት ሲፀዱ እንዲሁም ግጭቶች ሲከሰቱ ድሀውን ማህበረሰብን ለምን ይሰቃያል? ምን ያድርጉ? የሚያሳዝነው አንድ ግለሰብ በቅርቡ "ፒያሳን አይታችሁታል? ኮተት ሁሉ ተጠራርጎ ወጥቶ እብድ ራሱ ጠፋ" ብሎ ማህበራዊ ሚድያ ላይ በተሰራጨ ቪድዮ ላይ ሲሳለቅ ነበር። @EliasMeseret
إظهار الكل...
😢 823👍 324 52😱 17😁 7🙏 7
Photo unavailableShow in Telegram
👍 39 4😱 4
ከሰሞኑ አንድ፣ ሁለት ወይም ሶስት የሚሆኑ በመንግስት የተሰሩ ስራዎች ትክክል መስለው ስለታዩኝ 'መልካም ነው' ብዬ ከመፃፌ አንዳንዶች 'ምን ነክቶህ ነው?' እና 'ተቀላቀልካቸው እንዴ?' የሚል መልእክት አድርሰውኛል 😊 ድሮም ሆነ አሁን አስተያየት፣ ጥቆማ እና ትችት የማቀርበው ሊጠቅም ከቻለ በሚል ነው... ጥቅም ሲሰጥም ስላየሁበት። የማቀርባቸው መረጃዎች ደግሞ ለሀገር እንደ አንድ የሚድያ ባለሙያ ግዴታ ከመወጣት እና ለህዝብ ድምፅ ከመሆን አንፃር ነው። ከዛ ውጪ በትግራይ ይደርስ የነበረውን ግፍ ስፅፍ 'ጁንታ' የተባልኩት ግለሰብ ዛሬም በአማራ ክልል የሚደርሰውን ሰቆቃ ለህዝብ ሳቀርብ 'ጃዊሳ' እየተባልኩ ነው፣ አንድ ሰሞን በኦሮሚያ ሰላማዊ ዜጎች ተገደሉ የሚል ዜና ሰርቼ 'ሸኔ' የሚል ስም ተሰጥቶኝም ነበር። ስም ልጠፋው ስለለመድኩት እና ስለማይደንቀኝ አጠናክሮ መቀጠል ይቻላል።  ነገር ግን እኔ እዛው የድሮ አቋሜ ላይ እገኛለሁ፣ የማንም ደጋፊ ወይም ተቃዋሚ አይደለሁም። ያለሁበት ይህ ቦታ ስለተመቸኝ ወደፊትም መገኛዬ እዛው ነው 📍 መልካም ምሽት። @EliasMeseret
إظهار الكل...
1 378👍 706🙏 109😁 34🕊 30🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
#GoodNews ዛሬ በይፋ ስራ የጀመረው የኢትዮጵያ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (Ethiopian Securities Exchange) ትልቅ እምርታ ነው ሩቅ ሳንሄድ እዚሁ ጎረቤት ሀገሮች እንኳን ዜጎቻቸው ለስቶክ ገበያ ክፍት የሆኑ ድርጅቶችን በግልፅ ገበያ ሼር በመግዛት እና በመሸጥ ይነግዳሉ፣ ያተርፋሉ፣ ኑሯቸውን ይገፋሉ። የውጭም ሆነ የሀገር ውስጥ ኢንቨስተሮችን ለመሳብም ሁነኛ መንገድ እንደሆነ የሚታመንበት ይህ Securities Exchange በቅርብ ወራት 50 የሀገር ውስጥ ኩባንዎች ይካተቱበታል ተብሏል። በአሜሪካ ሀገር እንዳለው Securities and Exchange Commission (SEC) ያለ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ አካል ግን እንደሚያስፈልገው ግልፅ ነው። አለበለዛ ገበያው በቀላሉ ሊጭበረበር እንደሚችል በቅርብ በሌላ ሀገራት የተከሰቱ እንደ Insider Trading,  Pump and Dump እና Ponzi Scheme ያሉ ወንጀሎችን ማየት ይቻላል። በጅማሮው ተስፋ አድርገን መልካሙን ሁሉ ለተገበያዮች ተመኘን። @EliasMeseret
إظهار الكل...
👍 526 53🙏 15🤔 11😁 7😱 4🕊 4😢 3
Photo unavailableShow in Telegram
ትናንት ምሽት በደቡባዊ ኢትዮጵያ ስለታየው ክስተት መረጃ ለማግኘት እንደ ናሳ፣ የአውሮፓ ስፔስ ኤጀንሲ፣ የሩስያ ጠፈር ድርጅት እና የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ያሉ አካላትን ታግ በማድረግ እና ኢሜይል በመላክ ለማግኘት ሙከራ አድርጌ ነበር የአውሮፓ ስፔስ ኤጀንሲ ከደቂቃዎች በፊት ምላሹን ያሳወቀኝ ሲሆን ክስተቱ የሰው ሰራሽ ጠፈር ስብርባሪ ወደ ምድር ንፍቀ ክበብ ሲመለስ የተፈጠረ መሆኑን አስታውቋል፣ ስብርባሪውም የቻይና ሺጂያን-19 መንኩራኩር ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል። ሙሉ መረጃውን መሠረት ሚድያ ላይ ያገኙታል ⤵️ https://t.me/meseretmedia/765
إظهار الكل...
👍 507🙏 65 25😁 15🤔 14😢 7🕊 4
Photo unavailableShow in Telegram
አሜሪካንን ታላቅ ሀገር ካደረጋት አንዱ ይህ የፖለቲካ ልምምዳቸው ነው ምንም ያህል በፖለቲካው ቢጠላለፉ፣ ቢጠላሉ እና ቢጋጩ በሀገራዊ እና እንዲህ በግል ጉዳያቸው ላይ 'ለአሜሪካ ቅድሚያ' ብለው ይነሳሉ፣ የግል ፀባቸውን ያለዝባሉ እንዲሁም በህዝብ ዘንድ እንዲህ ይታያሉ። ይህ ምስል ትናንት በጂሚ ካርተር የሽኝት ፕሮግራም ላይ የተነሳ ነው። እኛ ጋር ቢሆንስ? በእውነት ያስቀናል። @EliasMeseret
إظهار الكل...
534👍 302😁 62😢 15🤔 9😱 4🙏 4
00:31
Video unavailableShow in Telegram
ዛሬ ከምሽቱ 1:30 ገደማ በደቡብ ኢትዮጵያ ባሉ በርካታ ዞኖች ይህ በቪድዮ ላይ የሚታየው ግዙፍ 'ነገር' ሰማይ ላይ መታየቱን በአካባቢ ያሉ ሰዎች መመልከታቸውን እያሳወቁኝ ይገኛሉ ምዕራብ ጉጂ ዲምቱ አካባቢ ያለ አንድ ነዋሪ "በጣም አስፈሪ የሆነ ግዙፍ ነገር ከሰማይ ሲወርድ ነበር፣ ግቢ ውስጥ ያለነው ሰራተኞች በግርምት ተሰባስበን ነው ያየነው። እየተቀጣጠለ ሚወርድ ነው ሚመስለው፣ ክስተቱ የሕዋ ከሆነም ብታጣሩልን" በማለት ገልፆታል። ቪድዮው ላይ የሚታየው ምን እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ብታሳውቁን በሚል አጋራሁት። በቅርብ ቀናት የጠፈር ስብርባሪ ኬንያ ውስጥ ባለ አንድ ገጠራማ ቦታ መውደቁ ይታወሳል። @EliasMeseret
إظهار الكل...
5.23 KB
😱 280👍 205😢 30 23😁 16🤔 16🙏 13🕊 8
Photo unavailableShow in Telegram
ምነው ጋሼ 😅 @EliasMeseret
إظهار الكل...
😁 1 896😢 182👍 76🤔 69😱 29 17🙏 7🕊 6
Photo unavailableShow in Telegram
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ያሉ መምህራን፣ የጤና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች በርካታ የመንግስት ተቀጣሪዎች ደሞዝ ለወራት ሳይከፈላቸው ቀርቶ ለመንገድ ዳር ልመና እና ለጉልበት ስራ ጭምር የተዳረጉ እንዳሉ የሚደርሱኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ እዚህ ጋር ደግሞ በ3.5 ቢልየን ብር (ሚልየን አይደለም) የጢያ ትክል ድንጋይን ለማልማት እቅድ ወጥቶ ወደ ስራ እየተገባ ነው ይለናል ይሄ ዘገባ። የቱሪዝም ሀብትን አልምቶ መጠቀም ይበል ያሰኛል፣ ግን ቅድሚያ የሚሰጠው የቱ ነው? ይሄ በመላው ሀገሪቱ የሚታየው ቅድሚያ የሚሰጠውን ነገር አለማወቅ ወይም ሆን ብሎ ማዛባት አይነተኛ ማሳያ ነው። Misplaced priorities! @EliasMeseret
إظهار الكل...
👍 563😢 187 58🤔 27😁 24😱 9🕊 5
Photo unavailableShow in Telegram
ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃባቸውን ለብሰው መማር መቻል አለባቸው በአክሱም የሚገኙት እነዚህ ተማሪዎቹ እየጠየቁ ያሉት መብታቸውን ነው፣ ያውም ሀይማኖታቸው የሚያዛቸውን ለመፈፀም። ያለን መንግስት አለማዊ (secular) ነው፣ የሁሉንም ሀይማኖቶች መብት ያከበረ መሆን አለበት። በዚህ ዙርያ የመሠረት ሚድያ ዘገባ ⬇️ "የአክሱም ከተማ ሙስሊም ነዋሪዎች ችግር እልባት ያልተሰጠበት እና ወደባሰ ሁኔታ እየሄደ ነው"--- የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መሠረት ሚድያ)- የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የአክሱም ከተማ ሙስሊም ነዋሪዎች ለዘመናት የነበረባቸውን የእምነት ነፃነት፣ የመስገጃ ቦታ ችግር እና የቀብር ቦታ ችግር እልባት ያልተሰጠበት እና ወደባሰ ሁኔታ እየሄደ ነው አለ። ምክር ቤቱ መግለጫውን ያወጣው በከተማው የሚገኙ ሴት ተማሪዎች ሂጃባቸውን አድርገው ትምህርት መከታተል እንዳልቻሉ ከሰሞኑ መሰማቱን ተከትሎ ነው። "በዚህ ዘመን በጋራ እምነቶች ተከባብረው በሚኖሩበት አገር እሴቱን የሚሸረሽር ተግባር መፈፀሙን በፅኑ እናወግዛለን" ያለው ምክር ቤቱ የሙስሊሙ ማህበረሰብ መብቶች ሳይሸራረፉ ተግባራዊ እንዲደረጉ እና መንግስትም ይህን እንዲያስፈፅም ጥያቄ አቅርቧል። መረጃን ከመሠረት! @EliasMeseret
إظهار الكل...
👍 407 88😁 59🙏 21🤔 14😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢቢሲ ዛሬ ባስነበበው አንድ ዘገባው "... ኢትዮጵያ ነዳጅን በዝቅተኛ ዋጋ በመሸጥ ከአፍሪካ ሀገራት በ8ኛ ደረጃ፣ ከዓለም በ28ኛ ደረጃ ላይ ነች" የሚል መረጃ የሆነ ድረ-ገፅን ዋቢ አድርጎ አጋርቷል። እውነታው ግን በእነዚህ ሀገራት ያሉ ዜጎች ከእኛ ጋር ለንፅፅር ሊቀርቡ አይችሉም፣ ምክንያቱም በብዙ እጥፍ የመግዛት አቅማቸው የተሻለ ነው። ዜናው በገራሚነት እንደምሳሌ አሜሪካንንም ጠቅሷል፣ በአሜሪካ አንድ ሌትር ነዳጅ 0.897 ዶላር ሲሸጥ በኢትዮጵያ ደግሞ 0.805 ዶላር (ተመሳሳይ ሊባል የሚችል ነው)። ታድያ ኢቢሲ በአሜሪካ ያለ ህዝብ ገቢው ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አንድ ነው እያለን ይሆን? እንደ IMF መረጃ በአሜሪካ የነፍስ ወከፍ ገቢ 89,600 ዶላር ሲሆን በኢትዮጵያ ደግሞ 1,100 ዶላር ነው። ለዛ ነው 'መንግስት' የሚባል አካል የህዝቡን የመግዛት አቅም አገናዝቦ ድጎማም ሆነ ሌላ ዋጋ መቀነሻ መፍትሄ የሚያበጀው። ለግዜው የተያዘው አካሄድ ግን 'በርካሽ እየሸጥን ነው' እያሉ ህዝቡን ማደንዘዣ መውጋት ነው። @EliasMeseret
إظهار الكل...
👍 1 509😢 253😁 143 93🙏 40🤔 38😱 8🕊 6
Photo unavailableShow in Telegram
#መልካምዜና መልካም እርምጃ! @EliasMeseret
إظهار الكل...
👍 372🙏 36 18🕊 16😁 13😢 4😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
በጣም ያምራል፣ እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ። #የአእላፋትዝማሬ @EliasMeseret
إظهار الكل...
2 002👍 276🙏 62🕊 45😁 25😢 10🤔 1