ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
الذهاب إلى القناة على Telegram
2025 عام في الأرقام

133 743
المشتركون
-4624 ساعات
-1437 أيام
-61730 أيام
أرشيف المشاركات
ኢትዮጵያውያን ቅጥር ሰራተኞች ግብር የማይከፍሉበት መነሻ ደመወዝ፣ ከስራ ለሚገኝ ገቢ የሚከፍሉት ግብር ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሲወዳደር ምን ይመስላል ? የነፍስ ወከፍ ገቢያችንስ?
(በአቶ ሙሼ ሰሙ የተፃፈ)
-ግብር የማይከፈልበት መነሻ ደመወዝ በጣም ዝቅተኛ የሆነባት
-በዝቅተኛ ደመወዝ ላይ ከፍተኛ ግብር የሚጣልባት
-የግብር ቅንፉ በጣም ጠባብ የሆነባት
-ትልቅ ግብር የሚከፈልበት የደመወዝ ጠገግ ዝቅተኛ የሆነባት
- ከፍተኛ የገቢ ግብር ተመን ያለባት
-የሀገር ውስጥ ምርት በነፍስ ወከፍ (GDP/capita/ PPP) ከጎረቤት ሀገራት ዝቅተኛ የሆነባት ኢትዮጵያ እንደሆነች ያውቃሉ?
================================
ኢትዮጵያ ውስጥ (1 ዶላር በ100 ብር) ተሰልቶ ከ6 ዶላር (600 ብር) በታች የሚከፈለው ሰራተኛ ከግብር ነጻ ነው። ከ109 ዶላር (በብር 10,900) በላይ የሚያገኝ ሰራተኛ ከፍተኛውን ጣራ 35% ግብር ይቀረጣል። የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ምርት በነፍስ ወከፍ (በተመጣጣኝ የመግዛት አቅም) በዶላር 2803 ( በብር 280,300) ።
ኡጋንዳ ውስጥ እስከ 63 ዶላር (በብር 6300) የሚከፈለው ሰራተኛ ከግብር ነጻ ነው። ከ2684 ዶላር (በብር 268,400) በላይ የሚያገኝ ሰራተኛ ከፍተኛውን የግብር ጣራ 30% ይቀረጣል። የኡጋንዳ የሀገር ውስጥ ምርት በነፍስ ወከፍ (በተመጣጣኝ የመግዛት አቅም) 3098 (በብር 309,800)
ኬንያ ውስጥ 186 ዶላር (በብር 18,600) የሚከፈለው ሰራተኛ ከግብር ነጻ ነው። ከ1613 ዶላር (በብር 161,300)በላይ የሚያገኝ ሰራተኛ ከፍተኛውን የግብር ጣራ 32.5 % ይቀረጣል። የኬንያ የሀገር ውስጥ ምርት በነፍስ ወከፍ (በተመጣጣኝ የመግዛት አቅም) በዶላር 5700 (በብር 570,000)
ታንዛንያ ውስጥ ከ99 ዶላር (በብር 9900) በታች የሚከፈለው ሰራተኛ ከግብር ነጻ ነው። ከ368 ዶላር (በብር 36,800) በላይ የሚያገኝ ሰራተኛ ከፍተኛውን የግብር ጣራ 30% ይቀረጣል። የታንዛንያ የሀገር ውስጥ ምርት በነፍስ ወከፍ (በተመጣጣኝ የመግዛት አቅም) በዶላር 3581( በብር 358,100)
ግብጽ ውስጥ 828 ዶላር በብር (82,800) ድረስ ደሞዝ የሚከፈለው ሰራተኛ ከግብር ነጻ ነው። 24,752 ዶላር (በብር 2,475,200) በላይ የሚያገኝ ሰራተኛ ከፍተኛውን የግብር ጣራ 27.5% ይቀረጣል። የግብጽ የሀገር ውስጥ ምርት በነፍስ ወከፍ (በተመጣጣኝ የመግዛት አቅም) 16,961 (1, 696,100 በብር)
ጅቡቲ ውስጥ እስከ 189 ዶላር (በብር 18,900) ድረስ የሚከፈለው ሰራተኛ ከግብር 11,236 ዶላር (በብር 112,3600) በላይ የሚያገኝ ሰራተኛ ከፍተኛውን የግብር ጣራ 45% ግብር ይቀረጣል። የጅቡቲ የሀገር ውስጥ ምርት በነፍስ ወከፍ (በተመጣጣኝ የመግዛት አቅም) በዶላር 6493 ( በብር 649,300)
@EliasMeseret
👍 487😢 199😱 45🤔 39❤ 28🙏 21🕊 2
Photo unavailableShow in Telegram
ግብፅ የህዳሴ ግድብ ላይ ጥቃት አደርሳለሁ ካለች የአጥፍቶ መጥፋት ውሳኔ እንደሚሆን ብዙ ያግባባል
ከዛ ውጪ ሰሞኑን እያየነው እንዳለው ከቀጠናው አኩራፊዎች ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ለማተራመስ ልትሰራ ትችላለች፣ ይህ ደግሞ እንዳይሆን የመንግስት ስራ ነው።
Story coming up.
#ItsMyDam
@EliasMeseret
👍 566😁 89❤ 37🕊 21🤔 13🙏 12
Photo unavailableShow in Telegram
ADVERTISEMENT
📍 ፒያሳ ከምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት የንግድ ሱቆችን መሸጥ ጀምረናል።
👉 2 ቤዝመንት ያለው
👉ከ 900,000 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
👉በ1 ዓመት ተኩል የምትረከቡት
👉ምድር ቤት
22 ካሬ= 7.5 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 3.5 ሚሊዮን ብር
👉1ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 5 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 2 ሚሊዮን ብር
👉2ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 4.5 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 1.5 ሚሊዮን ብር
👉3ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 4.2 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 1.2 ሚሊዮን ብር
👉4ኛ እና 5ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 3.9 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 900 ሺ ብር
👉ቀሪው በግንባታ ሂደት የሚከፈል።
ለበለጠ መረጃ
09-65-50-57-65 /09-42-17-90-98
ቴምር ሪል እስቴት
👍 83😁 14❤ 4🤔 3
#Update
"እናታችንን ትናንት ማታ ከመሸ ከሰሚት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ደውለውልን በሰላም አግኝተናታል።
ስለመልካም ትብብራችሀ እጅግ እናመሰግናለን"- ቤተሰብ
👍 732❤ 121🙏 78🤔 7😢 7
00:31
Video unavailableShow in Telegram
መሠረት ሚድያ በአዲስ አመት በዩትዩብ መረጃ ማሰራጨት ይጀምራል!
Bara haaraatti gama Yuutuubiin nu eegaa!
ኣብ ሓድሽ ዓመት ኣብ ዩትዩብ ተጸበዩና!
Join now ⤵️
https://youtube.com/@meseretmedia-em?si=SoNCcn3u0xZv7Jp7
4.03 MB
👍 438❤ 60😁 10🕊 4🙏 3
Photo unavailableShow in Telegram
'የታጋቾች ሞት' ብሎ ብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮችን ሄዶ ስለ እስራኤል ከማውራት እዚሁ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ እየተፈፀሙ ያሉ እገታዎች እና ግድያዎችን መዘገብ አይቀድምም?
ጎንደር ውስጥ ታግታ፣ ኋላም ትናንት ስለተገደለችው የ2 አመት ህፃን አልሰሙ ይሆን?
@EliasMeseret
👍 1 204😢 404❤ 65😱 54🙏 51🤔 25😁 16
Photo unavailableShow in Telegram
የአፋልጉኝ ማስታወቂያ!
ተፈላጊ እናታችን ወ/ሮ የንጉስነሽ ማሞ አስፋው ይባላሉ። ተፈላጊዋ ቱሉ ዲምቱ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በቀን 27/12/16 ከጠዋቱ 12፧00 ወደ ፃድቃኔ ማርያም ገዳም ለፀበል ብለውን ላምበረት መነሀሪያ መኪና ውስጥ አስገብተናቸው ነበር፣ ነገር ግን ወርደው ጠፍተውብናል፣ በወቅቱም ላምበረት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በአካል ቀርበን ሪፓርት አድርገናል። ተፈላጊዋ በወቅቱ ሰማያዊ ሽፎን ቀሚስ ከላይ የእጅ ስራ ሹራብ ፒንክ ጥለት ነጠላ ለብሰው ነበር። ተፈላጊዋን ያየ ያለችበትን የሚያውቅ ቢነግረን ወሮታውን ከፋይ ነን ፈላጊ ቤተሰቦቻቸው:
0913738580
0911809234
0954623141
👍 171😢 92❤ 16
"ሰላም እስኪሆን የአለም መንግስት ልጆቻችንን ይረከበን!"
ዛሬ እንዲህ ያሉኝ አንድ የጎንደር ከተማ ነዋሪ የሆኑ አባት ሲሆኑ በከተማው ክፉኛ በተንሰራፋው የእገታ ወንጀል ዙርያ ሳናግራቸው የተናገሩት ነው።
መቼም የማልረሳው አገላለፅ!
#Gondar
@EliasMeseret
😢 966👍 145😁 41❤ 24🤔 15
Photo unavailableShow in Telegram
ክቡርነትዎ፣
ሀገራችን ለም እና ቆንጆ ናት። ይሁንና:
- ህዝቡ ልጆቹን ሞፈር አሸክሞ 'ሰላም አውርዱልን' እያለ ከፈጣሪው አልፎ የሰው ልጅን እየለመነ ነው፣
- በትናትናው እለት ብቻ ሰሜን ሸዋ ላይ በርካታ ሰዎች ታግተው ተወስደዋል፣ በየቀኑ ለቁጥር የሚታክቱ ዜጎች በታጣቂዎች እንደ እንስሳ እየተነዱ ወደ ጫካ ይወሰዳሉ፣
- እርስዎ የወጡበት የአማራ ክልል ውስጥ እንኳን በየቀኑ ለቁጥር የሚታክት ህዝብ በጥይት እያለቀ ነው፣
- በጦርነት የተዳከመ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ በኑሮ ጫና እያለቀሰ ነው፣
- ዛሬ እንኳን ወደ ኦሞ ዞር ብንል ወንዝ ሞልቶ ህዝብ ከዛሬ ነገ ተዋጥኮ ብሎ የድረሱልኝ ጩኸት እያሰማ ነው።
እውነት አሁን ያለንበት ግዜ የምድር ገነት መሆናችንን እንድናስብ እና ውበቷን እንድናጣጥም የሚያረገን ነው ወይስ አንገት የሚያስደፋ ሁኔታ ውስጥ ነን?
We need some soul searching!
@EliasMeseret
😢 1 405👍 629❤ 116🙏 106😁 37🕊 34🤔 13
Photo unavailableShow in Telegram
ፐርፐዝ ብላክ በ1.5 ሚልየን ብር አፓርትመንት እየሸጥኩ ነው ሲል "ይሄን ነገር ቆም ብላችሁ አስቡበት፣ ሊሆን አይችልም" ያልን ሰዎች ነበርን
ተሰልፎ ሲገዛ የነበረው አንዳንዱ "በገንዘባችን የፈለግነውን መግዛት እንችላለን" እና "ምናገባህ? ለምን ትመቀኛለህ?" ሲለኝ ነበር
የሆነው ሆኖ ከእነዚህ የድርጅቱ ሀላፊዎች በተጨማሪ ይህን ያህል በቢልዮን የሚቆጠር ገንዘብ እጅግ አጠራጣሪ በሆነ መልኩ ከብዙ ሺህ ህዝብ ሲሰበሰብ ቆሞ የተመለከተ የመንግስት አካል እና ቢዝነሱን በተለያየ መልኩ ሲያሟሙቅ የነበረ ሁሉ ተጠያቂነት ሊያገኝ ይገባል።
@EliasMeseret
👍 596😁 77🙏 24❤ 21🤔 12
Photo unavailableShow in Telegram
ምንም አይነት የደሞዝ ጭማሪ ሳይደረግ የሸቀጦች እና የምግብ አይነቶች ዋጋ ላይ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ እስከ 50 ፐርሰንት ጭማሪ በተፈጠረበት ሁኔታ እንደገና ሌላ ታክስ በውሀ፣ ኤሌክትሪክ፣ ትራንስፖርት ወዘተ ላይ ማዥጎድጎድ ምንድን ነው?
ሰዉን ባትፈሩ ፈጣሪን...!
@EliasMeseret
👍 1 468😢 561❤ 74🙏 60🤔 42😁 21😱 9🕊 6
Photo unavailableShow in Telegram
በአሜሪካ አዲሱ የኢትዮጵያ አምባሳደር እንዲሆኑ የተመረጡት ሌንጮ ባቲ በአሜሪካ መንግስት ተቀባይነት አጡ
ለሙሉ ዘገባው ከመሠረት ሚድያ ⤵️
https://t.me/meseretmedia/229
😁 714👍 150🤔 28😱 27❤ 13😢 6🙏 2
Repost from TgId: 2155627280
Photo unavailableShow in Telegram
በአሜሪካ አዲሱ የኢትዮጵያ አምባሳደር እንዲሆኑ የተመረጡት ሌንጮ ባቲ በአሜሪካ መንግስት ተቀባይነት አጡ
- ሌላ ተተኪ አምባሳደር እንዲላክ አሜሪካ ለኢትዮጵያ እንዳሳወቀች የመሠረት ሚድያ ምንጮች ጠቁመዋል
(መሠረት ሚድያ)- ከጥቂት ሳምንታት በፊት ወደ አዲስ አበባ የተጠሩትን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ኢ/ር ስለሺ በቀለን እንዲተኩ የተመረጡት አምባሳደር ሌንጮ ባቲ በአሜሪካ መንግስት ተቀባይነት ማጣታቸውን ምንጮች ጠቁመውናል።
እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉትን አምባሳደር ሌንጮን አሜሪካ እንደማትቀበል ገልፃ ተተኪ ስም እንዲላክላት መጠየቋ ታውቋል።
ምክንያቱ ምን ይሆን በሚል መሠረት ሚድያ የጠየቃቸው እነዚህ ጉዳዩን የሚያውቁ ምንጮች አምባሳደር ሌንጮ ከአመታት በፊት በአሜሪካን ሀገር ሲኖሩ ከነበረባቸው አንዳንድ ክሶች ጋር የተያያዘ እንደሆነ ጠቁመው ዝርዝር ጉዳዩን ማንሳት ግን እንደማይፈልጉ ተናግረዋል።
"እነዚህ ክሶች በህዝብ ማህደር (public record) ውስጥ ስላሉ አሜሪካኖቹ አምባሳደሩ በሀገራቸው እንዲሾሙ አልፈለጉም። ይህንን ጉዳይ አሜሪካኖቹ ለኢትዮጵያ መንግስት አሳውቀዋል" ብለው ምንጮቹ ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።
በጉዳዩ ዙርያ እስካሁን በኢትዮጵያ መንግስት የተሰጠ ማረጋገጫም ይሁን ማብራርያ የለም።
አሜሪካ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በሀገሯ ሲሾሙ የራሷን መስፈርት በማስቀመጥ የምትመረምር ሲሆን በበርካታ አጋጣሚዎች የሌላ ሀገራት አምባሳደሮችን ሳትቀበል ቀርታለች።
የአሜሪካ ህገ-መንግስት የሀገሪቱ ፕሬዝደንት የሌሎች ሀገራትን አምባሳደሮች እንዲቀበል ወይም በተለያዩ ምክንያቶች እንዳይቀበል መብት ይሰጣል።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia
Photo unavailableShow in Telegram
የመሠረት ሚድያን የቴሌግራም ቻናል ተቀላቅለዋል?
በርካታ ወቅታዊ መረጃዎች በአማራጭነት እየተጋሩበት ነው ⤵️
https://t.me/meseretmedia
👍 176❤ 33
Photo unavailableShow in Telegram
ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማምሻውን ያወጣው ጠንከር ያለ መግለጫ በቀጠናው እየተከሰተ ያለውን ውጥረት የሚመጥን ነው
ትናንት የግብፅ ጦር ወታደራዊ አውሮፕላኖች በሞቃዲሾ ጭነት ማጓጓዛቸውን ተከትሎ እንዲህ አይነት መግለጫ ቢኖር ብዬ ተመኝቼ ነበር፣ ከምኞት በዘለለ ግን ቃሉን ወደ ተግባር የሚቀይር በቂ ዝግጅት እና በቅርብ ጊዜያት የተፈፀሙ ዲፕሎማሲያዊ መንገጫገጮችን ላለመድገም ጥረት ሊደረግ ይገባል።
#Ethiopia
@EliasMeseret
👍 392😁 77❤ 40🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
ይህ የፍትህ ስርዐቱን እና የፍትህ አስፈፃሚ አካላትን አፈፃፀም በወፍ በረር ያሳየ መረጃ ነው!
በሌላ በኩል ደግሞ ቶሎ ካልታሰሩ መረጃ ያወጣሉ ተብለው እስር ቤት የሚማቅቁት ጋዜጠኞች ታወሱኝ።
@EliasMeseret
👍 434😱 51😢 50😁 27❤ 21🤔 12🕊 3
#Update: የቤተሰብ መልዕክት
ጠፍቶብን የነበረው ምትኩ በላይ በሰላም ወደቤቱ ተመልሷል/ተገኝቷል... ድምጽ ስለሆናችሁን እናመሰግናለን ፣ክብር ይስጥልን 🙏
🙏 739👍 191❤ 99🕊 19🤔 17😁 16😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
በነዚህ ልጆች ድርጊት አፍሬ እና ስራቸውን አውግዤ ከአራት ቀን በፊት አስተያየት አቅርቤ ነበር። አሁን ይህን ክስ በተመለከተ እነዚህን ነጥቦች ላንሳ:
1ኛ: ማንም ሰው ከህግ በላይ አይደለም የሚለው መርህ በሀገራችን ይሰራል እንበል እና ጉዳዩን ወደ ሽብር ክስ መውሰዱ ለምን እንዳስፈለገ በሂደት እናየዋለን። ልጆቹ እንዲሁም ህብረተሰቡ ሊማርበት የሚችል ክስ አቅርቦ ማስኬድ እየተቻለ ከኢህአዴግ ግዜ ጀምሮ እንደለመድነው 'ከውጭ ሀይሎች ጋር ተባብረው' የሚል ታግ መለጠፍ ተመርጧል። 'ሽብር' የሚለውን ክስ ነገ ከነገ ወዲያ እንደሚተዉት መገመት ይቻላል፣ አካሄዱ ግን ምን ያህል ከድሮው እሳቤ እንዳልወጣን ማሳያ ነው። 'አየር መንገዱ ላይ ጥቃት ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ' የሚል ነገር ክስ ውስጥ ገብቷል፣ እውነት ያየነው ይህን ነበር? በቲክቶክ እውቅና የከነፉ እና ልጅነት ብዙም ያልለቀቃቸው ወጣቶች ድርጊት እንጂ እኔ ሌላ ለእኔ አልታየኝም።
2ኛ: አንዳንድ ሰው በሽብር ህግ መከሰሳቸውን ደግፎ አይቻለው፣ መብት ነው። ይህን በማድረግ ግን ወደፊት ረብሸሀል፣ ያልተፈቀደ ነገር አርገሀል ተብሎ ህዝቤ በሽብር ቢከሰስ ሊከፋው አይገባም። ምንም ያህል ልጆቹ የፈፀሙትን ድርጊት ብንጠላ አሁን ላይ 'ለምን በሽብር ህግ?' ብለን ካልጠየቅን ነገም እኔ ላይ ይፈፀምብኝ ብሎ ፈቃድ እንደመስጠት ነው።
3ኛ: ይህ አካሄድ በትክክል እንግልት የሚደርስባቸውን ዜጎች እና ካለ አግባብ ለሚንገላቱ ሰዎችን ድምፅ እንዳያፍን ያሰጋል። አየር መንገዱ አገልግሎት ሰጪ ተቋም እንደመሆኑ ሁሌ ተገልጋዮች ቅሬታ ወይም ነቀፋ ሊሰነዝሩ ይችላሉ፣ ግን የሽብር ህጉን ከህግ ፍሬው በተለየ መምዘዙ እነዚህን ድምፆች ዝም ለማስባል ከሆነ ይበልጥ ችግር ፈጣሪ እንጂ መፍትሄ አይሆንም።
መልካም ምሽት።
@EliasMeseret
👍 1 947❤ 171😁 42🙏 36🤔 31🕊 14😱 8😢 3
Photo unavailableShow in Telegram
ድምፅ በመስጠት እንሳተፍ!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው 'World Travel Awards' ሽልማት ላይ በስድስት ዘርፎች ዕጩ ሆኖ ቀርቧል። እርስዎም ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ድምፅዎን የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኩራት ለሆነው አየር መንገድዎ እንዲሰጡ ተጋብዘዋል።
https://www.worldtravelawards.com/vote-r3
የሌሎች ሀገራት አየር መንገዶች በብዛት በሶሻል ሚድያ አማካኝነት ድምፅ እያገኙ ነው፣ እኛም ድምፃችንን በመስጠት እንሳተፍ። ድምፅ መስጠት ጷጉሜ 3 ስለሚያበቃ አሁኑኑ ድምፅ ይስጡ።
@EliasMeseret
👍 520😁 102❤ 44🤔 22😱 9🕊 7😢 6🙏 5
