ch
Feedback
YeneTube

YeneTube

前往频道在 Telegram

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

显示更多
2025 年数字统计snowflakes fon
card fon
107 389
订阅者
-5724 小时
-4017
-2 12730
帖子存档
照片不可用在 Telegram 中显示
"በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚተገበር የ30 በመቶ ግብር የለም!" ከታኅሳስ ወር 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚተገበር የ30 በመቶ ግብር እንደማይኖር፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኳንንት (ዶ/ር)፣ ከታኅሳስ ወር 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች ላይየ30 በመቶ ግብር ይጣላል የሚል መረጃ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲዘዋወር መቆየቱን፣ ነገር ግን ይህ መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን ለሪፖርተር ገልጸዋል። ገንዘብ ሚኒስቴርን ጨምሮ በጉዳዩ ላይ በየትኛውም የመንግሥት አካል የተሰጠ መግለጫ እንደሌለ ማረጋገጣቸውን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ይጣላል የተባለው ግብር በማኅበራዊ ሚዲያው ላይየተፈጠረ እንጂ፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣንም የሚያውቀው ከዚህ ወር ጀምሮ የሚጣል ምንም ዓይነት የግብር ጭማሪ እንደማይደረግና መንግሥትም ይህን የማድረግ ዕሳቤ እንደሌለው መሆኑን ተናግረዋል። ‹‹በሐሰተኛ መረጃ የተነሳ ኅብረተሰቡ ላልተገባ ሠልፍና እንግልት እየተዳረገ ይገኛል፤›› ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ያለ ምንም ይፋዊ የመንግሥት ውሳኔ ከወጣው የነዳጅ ዋጋ ውጪ ያለ አግባብ ጭማሪ የሚያደርጉ የነዳጅ አከፋፍይ ኩባንያዎችና ማደያዎች ተጠያቂ እንደሚደረጉም አሳስበዋል። በአዲስ አበባ ከተማ በመደበኛ ሁኔታ ነዳጅ እየቀረበ መሆኑን፣ ነገር ግን በዚህ ሐሰተኛ መረጃ ምክንያት ፍጆታ ላይ ጭማሪ መፍጠሩን ገልጸዋል። የተናፈሰው መረጃ ስህተት መሆኑን ለነዳጅ ኩባንያዎችና ማደያዎች በተደጋጋሚ እያሳወቁ መሆናቸውን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ኩባንያዎች ባልተፈለገ መንገድ ተታለው ከጂቡቲ የተረከቡትን ነዳጅ ላልተገባ ጥቅም የማዋል ዕሳቤ እንዳይፈጠርባቸው በድጋሚ አሳስበዋል። @YeneTube @FikerAssefa
显示全部...
49😁 11
照片不可用在 Telegram 中显示
የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ፡፡ በሕንድ፣ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 20ኛው የዩኔስኮ የማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶች ጥበቃ ኮሚቴ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ያቀረበችው የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በሰው ልጅ የማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶች ዝርዝር ስር ተመዝግቧል። "ጊፋታ" በወላይታ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ታላቅ በዓል ሲሆን፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የሕዝቡ የማንነት መገለጫ የሆነ የአሮጌው ዓመት ማብቂያና የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ የመሸጋገሪያ በዓል ነው፡፡ ጊፋታ እድሜ፣ ጾታ፣ ሃይማኖት ወይም ሌላ ማኅበራዊ ደረጃ ሳይለይ ለሁሉም ሠላም እና ማኅበራዊ ትሥሥር አስተዋጽኦ በማድረግ በዩኔስኮ የተለዩትን ዘርፎች ያካተተ ሁሉን አቀፍ ተግባራትን በማበረታታት የሚከበር በዓል መሆኑ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ አስችሎታል። @YeneTube @FikerAssefa
显示全部...
👍 24 12😁 8👎 1
照片不可用在 Telegram 中显示
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ - ዳይናሚክ አክሲዮን ማህበር የስራ ቦታ፡ የሽያጭ እና የግብይት ኃላፊዎች (ብዛት 20 ) ‎አካባቢ፡ አዲስ አበባ ‎🔹 ቁልፍ ኃላፊነቶች ‎የኩባንያ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ማስተዋውቁ እና መሽምጥ። ‎የመስክ ግብይት እና የደንበኛ ክትትል ማካሄድ። ‎ሳምንታዊ እና ወርሃዊ የሽያጭ ግቦችን ማሳካት። ‎የዕለታዊ እንቅስቃሴ እና የገበያ ግብረመልስ ሪፖርቶችን ማቅረብ። ‎🔹 መስፈርቶች ‎በማርኬቲንግ፣ በቢዝነስ፣ በኢኮኖሚክስ ወይም ተዛማጅ መስኮች ዲፕሎማ ወይም ዲግሪ። ‎እጅግ በጣም ጥሩ የመግባቢያ እና የማሳመን ክህሎቶች። ‎በጫና ስር የመስራት እና የሽያጭ ግቦችን የማሳካት ችሎታ። ‎በሽያጭ ወይም በማርኬቲንግ ልምድ መኖሩ ተጨማሪ ነው (ግዴታ አይደለም።) ‎ሐቀኛ፣ ታታሪ እና የመስክ ስራ ለመስራት ፈቃደኛ። ‎🔹 የምናቀርበው ነገር ‎ወርሃዊ ደሞዝ + ማራኪ ኮሚሽን ‎የአፈጻጸም ጉርሻዎች ‎የስልጠና እና የሙያ እድገት እድሎች ‎📩 እንዴት ማመልከት እንደሚቻል (የTalentHub ብቻ) ‎ሁሉም አመልካቾች በTalentHub በኩል ብቻ ማመልከት አለባቸው። https://talenthubethiopia.com/ ‎📍 የቢሮ አድራሻ ‎Megenagna፣ Hibire ህንፃ፣ 3ኛ ፎቅ፣ የቢሮ ቁጥር 312፣ አዲስ አበባ‎ ‎📅 የማመልከቻ ቀነ-ገደብ፡ ‎ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ።
显示全部...
20👍 1😭 1
"ዘለንስኪ ከአሜሪካ 350 ቢሊዮን ዶላር ወስዶ ከአገሩ መሬት 25 ፐርሰንቱን ያጣ ሰው ነው" ሲሉ ትራፕም ተናገሩ፡፡ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ከፖለቲኮ ጋር ሰፋ ያለ ቃለምልልስ አድርገዋል፡፡ በዚህ ቃለምልልስ ከተነሱላቸው ጥያቄዎች መካከል ፕሬዝደንት ዘለንስኪን የሚመለከተው ይገኝበታል፡፡ ትራምፕ በቃለምልልሳቸው ዘለንስኪን ከታዋቂው አሜሪካዊው ትርኢት አቅራቢና ነጋዴ ፒቲ ባርኑም ጋር አመሳስለዋቸዋል፡፡ ሲናገሩም ‹‹ዩክሬይን ኔቶ ውስጥ እንደማትገባ ከፑቲን በፊት መግባባት ላይ የተደረሰበት ጉዳይ ነው፡፡ እናም ዘለንስኪ መጀመሪያ ፑቲንን እንዳገኘው ሁለት ጥያቄዎችን አቀረበ፡፡ እነዚህም ክሬሚያ ይመለስልኝና ኔቶ ውስጥ መግባት እፈልጋለሁ የሚሉ ናቸው›› ብለዋል፡፡ ሲቀጥሉም ‹‹ነገር ግን ሁለቱንም ጥያቄዎቹን አግባብ ባለው መንገድ አልጠየቀም›› ያሉት ትራምፕ በዚህም ከአሜሪካዊው ትርኢት አቅራቢና ስራ ፈጣሪ ፒቲ ባርኑም ጋር እንደሚያመሳስላቸው አስታውቀዋል፡፡ አባባላቸውን ሲያብራሩም ‹‹ፒቲ ባርኑም የአለማችን እጅግ ምርጥ ሰው ነበረ፡፡ ምርቱን በማንኛውም ጊዜ የትም ቦታ መሸጥ የሚችል ሰው ነበር፡፡ ምንም ሆነ ምን በእጁ ላይ ያለውን እቃ እንደፈለገው አድርጎ የሚሸጥ ነበር፡፡ ያ ሁኔታ አሁን ያለፈ ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን ዘለንስኪ ከፕሬዝደንት ጆ ባይደን 350 ቢሊዮን ዶላር ቢወስድም ከአገሩ ግዛት ውስጥ ግን 25 ፐርሰንቱን አጥቷል፡፡ እውነታው ይህ ነው›› በማለት ገልፀዋል፡፡ @Yenetube @Fikerassefa
显示全部...
28😁 12
ከአሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ ድርጅታችን አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ጋዜጠኛ ሶፎንያስ ዋሲሁን በኮንትራት ውል በዜና አቅራቢነት እንዲሁም በቅርቡ በጣቢያችን ‹‹ሶፊ ሾው›› ሲል በሰየመው የመዝናኛ ዝግጅቱ በአሻም የቴሌቪዥን እና በዩትዩብ ገፅ እያዘጋጀ ሲያቀርብ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ይህ በሆነበት ከትላንት ሕዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ አማራጮች ስለ ጋዜጠኛው ከኢትዮጵያዊነት ባሕል፣ ወግ እንዲሁም ሃይማኖት ያፈነገጠ ተግባር ሲፈጽም የሚያሣይ መረጃ በድምጽ፣ በጽሁፍና በተንቀሳቃሽ ምስል ጭምር ሲዘዋወር ተመልክተናል፡፡ አሻም ይህንኑ በማህበራዊ ሚዲያ ስለ ጋዜጠኛው የተሰራጨውን መረጃ ተከትላ ስለ ተሰራጨበት መረጃ ሶፎኒያስን ማብራሪያ እንዲሰጥበት ጠይቃለች፡፡ በዚህም ሶፎኒያስ <<አሁን ራሴን ለማስተካከል፤ለማከም ፀበል ገብቻለሁ>> የሚል አጭር ምላሽ ከመስጠት ውጭ ተጨማሪ ያለው ነገር የለም። ስለሆነም አሻም ሚድያ ትሬዲንግ አ.ማ. የኢትዮጵያን ባህል እና ወግ እንዲሁም የህብረተሰቡን እሴት እና ሃይማኖት ያከበረ የምትመራበት ኤዲቶሪያል አላት፡፡ ይሁን እንጂ ጋዜጠኛው የሚዲያውን ኤዲቶሪያልም ሆነ የማህበረሰቡን እምነት ፣ እሴት፣ ወግ፣ ባህልና ሃይማኖት የሚጻረር ተግባር ተሰራጭቶበት በመመልከቷ እጅጉን እያዘነች ድርጊቱ የሚዲያ ተቋሟን የማይወክል ይልቁንም በጽኑ የምታወግዘው መሆኑን ለውድ ተመልካቾቻችን እና ተከታታዮቻችን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አሻም ሚዲያ ትሬዲን አክሲዮን ማህበር ጋዜጠኛ ሶፎኒያስ ዋሲሁን በፈጸመው ከባድ የማህበረሰባዊ እሴት እና ኤዲቶሪያል ጥሰት ጭምር የነበራትን የስራ ውል ከዛሬ ሕዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ማቋረጡዋን ለመግለጽ ትወዳለች፡፡ @Yenetube @Fikerassefa
显示全部...
56👍 25👎 2
照片不可用在 Telegram 中显示
5
照片不可用在 Telegram 中显示
የዘንድሮው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ መስጫ ቀን ግንቦት 24 ቀን ሆኖ ፀደቀ! የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተያዘው ዓመት የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ መስጫ ቀን ግንቦት 24/2018 ዓ.ም እንዲሆን መወሰኑን አስታወቀ።ቦርዱ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል። የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ ባለፉት ወራት በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰው፣ የፓርቲዎች እንዲሁም በግል የሚወዳደሩ እጩዎች እና መራጮች የሚመዘገቡበትን የዲጂታል ስርዓት መዘርጋቱን አስታውቀዋል። ሰብሳቢዋ ለእጩዎች ምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ማስገባት እና የእጩዎች ምዝገባ ማካሄድ እንደሚለያይ ገልፀው ምርጫ ቦርድ ከህዳር 8- ህዳር 23/2018 ዓ.ም ድረስ የጠየቀው ፓርቲዎች የምዝገባ ሰነዶቻቸውን እንዲያቀርቡ እንደሆነ ጠቁመዋል።የእጩዎች ምዝገባን በተመለከተም የሚከናወነው ከታህሳስ 1- ጥር 1/2018 ዓ.ም መሆኑን ገልፀዋል። ከሰሞኑ የምርጫ ክልል ፅህፈት ቤት ሥራ አስፈፃሚዎችን የመመልመል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው፣ 131ሺህ አመልካቾች በአሁኑ ወቅት የፅሁፍ እና የቃል ፈተና እየወሰዱ መሆኑን ተናግረዋል። ምርጫውን ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታ መኖሩን በተመለከተ ማብራርያ የሰጡት ሰብሳቢዋ አስቻይ ሁኔታ በአንድ ቀን፣ በሶስት ቀን፣ በአምስት ቀን የሚሰራ አይደለም ቀጣይነት ያለው እና እስከ ምርጫው ዕለት ድረስ የሚከናወን ስራ ነው ብለዋል። አስቻይ ሁኔታ ሲባል የፀጥታ ሁኔታዎች ብቻ አለመሆናቸውን የገለፁት ሰብሳቢዋ መሬት ላይ ያለውን የፖለቲካ ምህዳርን እንደሚያካትት ገልፀዋል።በዚህም ፓርቲዎች እንደልባቸው ይንቀሳቀሳሉ ወይ የሚለውም ላይ ቦርዱ ዕለት ዕለት እየሰራበት መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል። [AS] @YeneTube @FikerAssefa
显示全部...
19😁 9🔥 1
በጎንደር የሰዓት እላፊ ገደብ ተነሳ "ያለምንም የፀጥታ ስጋት 24 ስዓት መንቀሳቀስ ይቻላል" የጎንደር ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ፣ በከተማዋ ተጥሎ የቆየው የስዓት እላፊ የእንቅስቃሴ ገደብ መነሳቱን አስታውቋል፡፡ በከተማው አስተማማኝ ሰላም መፈጠሩን ተከትሎ፣ የስዓት እላፊ ገደብ የተነሳ መሆኑን የጎንደር ከተማ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ አለልኝ ዓለም የገለጹ ሲሆን፤ ህብረተሰቡ ያለምንም የፀጥታ ስጋት 24 ስዓት መንቀሳቀስ እንደሚችል መናገራቸውን የከተማዋ ኮሚኒኬሽን ጠቁሟል። ህብረተሰቡም ሆነ ተሽከርካሪዎች 24 ስዓት መንቀሳቀስ እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን፤ የማታ አገልግሎት የሚሰጡ ባጃጆች ደግሞ እውቅና ይሰጣቸዋል ተብሏል፡፡ @Yenetube @Fikerassefa
显示全部...
32😁 12👍 2🔥 1👀 1
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በሚቀጥለው ሳምንት ኢትዮጵያን ሊጎበኙ እንደሚጠበቅ ተነገረ። ይህ ጉዞ የህንድ መሪ ለአፍሪካ ቀንድ አገር ከአሥር ዓመት በላይ በኋላ የሚያደርጉት የመጀመሪያው ሲሆን፣ ኒው ዴሊ ከአኅጉሪቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ያላትን አዲስ ቁርጠኝነት ያሳያል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከታኅሣሥ 7 እስከ 8፤ 2018 ዓ.ም. ድረስ በአዲስ አበባ ሊቆዩ እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም ዮርዳኖስን (ታኅሣሥ 6 እና 7) እና ኦማንን (ታኅሣሥ 8 እና 9) የሚያካትተው የሶስት አገራት ጉብኝት አካል ነው። ለመጨረሻ ጊዜ ኢትዮጵያን የጎበኙት የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማንሞሃን ሲንግ ሲሆኑ እሱም እ.ኤ.አ. በ2011 ዓ.ም. እንደነበር መረጃዎች ይጠቀማሉ። ህንድ እና ኢትዮጵያ በደቡብ-ደቡብ ትብብር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ የልማት አጋርነት አላቸው። አዲስ አበባ ከአኅጉሪቱ ከፍተኛ የህንድ የቅናሽ ብድር ተቀባዮች አንዷ ስትሆን፣ ፕሮጀክቶችም የባቡር መስመር፣ የሸንኮራ ፋብሪካዎችና የኃይል ማስተላለፊያን ያካትታሉ። ይህ ባለብዙ አገራት ጉዞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው G20 ስብሰባ እና በቅርቡ በቡታን ባደረጉት ይፋዊ ጉብኝት ከተሳተፉ በኋላ የሚደረግ ሲሆን፣ ህንድ በተለያዩ ክልሎች ያሉ ግንኙነቶቿን ለማጠናከር የምታደርገውን ጥረት ያመለክታል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጰያ በሚያደርጉት ጉዞ በዲጂታል የህዝብ መሠረተ ልማት፣ በግብርና ቴክኖሎጂ፣ በንጹህ ኃይል፣ በባቡር ዘመናዊነት፣ በማምረት፣ በመከላከያ ትብብር እና በትምህርት ዘርፎች ላይ አዳዲስ ስምምነቶችን ያስከትላል ተብሎ ይጠበቃል። በአሁኑ ጊዜ ከ650 በላይ የህንድ ኩባንያዎች ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሲሆን፣ ይህም የሕንድ ኢንተርፕራይዞች የአገሪቱ ትላልቅ የግል ቀጣሪዎች እንዲሆኑ አድርጓል።በተጨማሪም፣ በቴክኖሎጂ አጋርነት እና በዲጂታል ለውጥ ላይ አዲስ ተነሳሽነት መፍጠር የሞዲ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ቀደምት ውይይቶች ውጤት መሆኑ ተጠቁሟል። Via Capital @YeneTube @FikerAssefa
显示全部...
27🔥 4👍 1😭 1
照片不可用在 Telegram 中显示
4
00:05
视频不可用在 Telegram 中显示
Samsung A06 5G Memory: 128/6GB Condition: Brand New Battery: 5000mAh Price: 17500ETB Call: 0924769665 DM: @adagioandante
显示全部...
1.68 MB
14
በቅርቡ በአዲስ አበባ በተካሄደው 3ኛው የ«ጂ-ፓወር ቲክቶክ ሽልማት» (G-Power TikTok Creative Award) ሥነ-ሥርዓት ላይ፣ የኢትዮጵያን ባህልና የህዝብ ሞራል የሚጋፋ አለባበስ ለብሰው ቀርበዋል የተባሉ ታዋቂ የማህበራዊ ሚዲያ ፊቶች እና የዝግጅቱ አስተባባሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። ፖሊስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ በዝግጅቱ ላይ የተስተዋለው አለባበስ "ከኢትዮጵያ ህዝብ ባህል እና ሥነ-ምግባር ያፈነገጠ፣ እንዲሁም ሰውነትን በዝርዝር የሚያሳይ አስነዋሪ ድርጊት" ነው። ይህ ድርጊት በአደባባይ ብቻ ሳይሆን በቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ለሚሊዮኖች መሰራጨቱ ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ እንዳደረገው ተገልጿል። በቁጥጥር ስር የዋሉት እነማን ናቸው? ፖሊስ በጉዳዩ ላይ እያደረገ ባለው ምርመራ፣ አለባበሱ በቀጥታ ከሚመለከታቸው ግለሰቦች በተጨማሪ ዝግጅቱን በስፖንሰርነት የደገፉ እና ያቀነባበሩ አካላትንም አካቷል። በዚህም መሰረት፡- 1. ወንጌላዊት ገብረ እንድርያስ በርሄ፣ 2. በረከት ፀጋዬ ጅፋር፣ 3. መቅድም ደረጄ መንግስቱ፣ 4. ግሩም ገዛሀኝ ቀጭኔ፣ እና 5. ዮሃንስ መኮንን ሀ/ማርያም የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን ፖሊስ አረጋግጧል። የፖሊስ ቀጣይ እርምጃ እና ማስጠንቀቂያ ፌደራል ፖሊስ አክሎ እንደገለጸው፣ መሰል "መጤ ባህሎች እና ከእሴት ያፈነገጡ አለባበሶች" በሀገር ተረካቢው ትውልድ ላይ ስነ-ልቦናዊ እና ሞራላዊ ውድቀት እንዳያስከትሉ ስጋት አለ። በመሆኑም የህዝብን ሥነ-ምግባር ለመጠበቅና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ተጠያቂነትን እንደሚያሰፍን ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። @Yenetube @Fikerassefa
显示全部...
👍 103 35😁 13😭 5🔥 1
照片不可用在 Telegram 中显示
"የነዳጅ ዋጋ አልጨመረም"
የአቅርቦት ችግርም የለም።
የነዳጅ ሰልፍ የተከሰተው ከአቅርቦት እጥረት ሳይሆን በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን በሚሰራጭ የተሳሳተ መረጃ ነው ተብሏል። በአዲስ አበባ ከተማ ሰሞኑን የሚስተዋል የነዳጅ ሰልፍ በአቅርቦት ችግር ሳይሆን በተሳሳተ መረጃ ምክንያት መሆኑን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል። በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለውን የነዳጅ ሰልፍ ተከትሎ ባለስልጣኑ የማጥራት ስራ መስራቱን እና በዚህም የአቅርቦት እጥረት አለመኖሩን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ በቀለች ኩማ ተናግረዋል። በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን አማራጮች ከዋጋና አቅርቦት ጋር በተገናኘ የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎችን ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች የነዳጅ ሰልፎች እንደሚስተዋሉም ገልፀዋል። ባለስልጣኑ በከተማዋ በተለመደው መሰረት ነዳጅ  እያቀረበ እንደሚገኝ ያስታወቁት ሀላፊዋ በቀጣይ ቀናትም ምንም አይነት የአቅርቦት ችግር እንደማይፈጠር አስታውቀዋል፡፡ ተጠቃሚው ትክክለኛውን መረጃ በማረጋገጥ  አማራጭ የነዳጅ ማደያዎችን በመጠቀም አላስፈላጊ ሰልፎች እንዳያጋጥሙ ሊያደርግ እንደሚገባም ሃላፊዋ አመላክተዋል፡፡ አክለውም በከተማዋ በሁሉም የነዳጅ ማደያዎች በየእለቱ ከ1 ሚሊየን ሊትር በላይ የቤንዚን አቅርቦት መኖሩን ገልጸዋል። የከተማዋ ንግድ ቢሮ በበኩሉ የነዳጅ አቅርቦት ችግር ሳይኖር በህገ ወጥ አሰራር ተጠቃሚውን የሚያጉላሉ አካላት ላይ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል። @Yenetube @Fikerassefa
显示全部...
37😁 6
照片不可用在 Telegram 中显示
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የአክሲዮን ምዝገባ ቀነ ገደብ በህዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም. መጠናቀቁን ተከትሎ፣ ያልተመዘገቡ ሰነደ ሙአለ ንዋዮች (አክሲዮኖች) ላይ የሚካሄዱ ማናቸውም ግብይቶች ከባድ የወንጀል ተጠያቂነት እንደሚያስከትሉ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል። ባለስልጣኑ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በአዋጅ ቁጥር 1248/2013 አንቀጽ 75 መሰረት ለህዝብ የሚሸጥ ሰነደ ሙአለ ንዋይ ለገበያ ከመቅረቡ በፊት መመዝገብ ግዴታ ነው። ቀነ ገደቡ ካለፈ በኋላ ያልተመዘገቡ አክሲዮኖችን ለግብይት ማቅረብ ወይም መገበያየት በአዋጁ አንቀጽ 106 (5) መሰረት በወንጀል የሚያስቀጣ ተግባር ሲሆን፣ ቅጣቱም ከ7 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከ150 ሺህ እስከ 300 ሺህ ብር በሚደርስ መቀጮ ነው። ይሄን ተከትሎ፣ አክሲዮኖቻቸውን ያላስመዘገቡ አክሲዮን ማህበራት ከአዲስም ሆነ ነባር አክሲዮኖች ሽያጭና ግብይት ጋር የተያያዘ ማንኛውንም እንቅስቃሴ እና ማስተዋወቅ እንዲያቆሙ፣ እንዲሁም አክሲዮን የሚያገበያዩ ቢሮዎች ያሏቸው ኩባንያዎችም የማገበያየት ሥራ እንዲያቆሙ በጥብቅ አሳስቧል። Via Capital @YeneTube @FikerAssefa
显示全部...
7🔥 2
照片不可用在 Telegram 中显示
የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢብራሂም ትራኦሬ "ጥሩ መሪ አይደለም" አሉ የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የቡርኪናፋሶው ኢብራሂም ትራኦሬ ጥሩ መሪ አይደለም ሲሉ ትችት ሰንዝረዋል፡፡ የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሳሊያ ሙዳቫዲ፣ ስለ ቡርኪናፋሶ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ የሰነዘሩት የሰላ ትችት እያነጋገረ ነው፡፡ ሙዳቫዲ በንግግራቸው፤ አንድ ትክክለኛ መሪ በወገቡ ላይ ሽጉጥ መታጠቅ ወይም በጠረጴዛው ላይ የጦር መሳሪያዎችን ማሳየት የለበትም፤ ብለዋል፡፡ እንደ እሳቸው አባባል፤ አመራር በተቋማት፣ በዴሞክራሲና በተጠያቂነት ላይ መገንባት አለበት - በኃይል ሳይሆን። መሪዎችን መሪ የሚያደርጋቸው መሣሪያ ሳይሆን ርዕይ፣ ህግና ኃላፊነት ነው ሲሉም አክለዋል፤ የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፡፡ @Yenetube @Fikerassefa
显示全部...
👎 66 17👍 4👀 2
照片不可用在 Telegram 中显示
ቲክቶክ በናይጄሪያ የምሽት የቀጥታ ስርጭቶች እንዳይደረጉ አገደ። የቻይናው የማህበራዊ ሚዲያ ተቋም ቲክቶክ በናይጄሪያ በምሽት የሚደረጉ የቀጥታ ስርጭቶችን በጊዜያዊነት ማገዱን ገልጿል። ቲክቶክ በናይጀሪያ ከምሽቱ 5 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት የሚደረጉ የቀጥታ ስርጭቶችን ማቆሙን ይፋ ያደረገው ወሲባዊ ይዘት ያላቸው ስርጭቶች መብዛታቸውን ተከትሎ ነው። ይህ የወሲብ ይዘት በብዛት ይሰራጭበታል በተባለው በዚህ ሰዓትም በናይጄሪያ የቀጥታ ስርጭቶችን ማሰናዳት ወይም መመልከት አይቻልም። "የይዘት ደህንነትና ተጠቃሚዎቼን እጠብቃለሁ" ያለው ቲክቶክ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ምክንያት ከ49,000 በላይ የቀጥታ ውይይቶችን ከናይጄሪያ አጥፍቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቲክቶክ እውቅና እና ትኩረት ለማግኘት በሚል ወሲባዊ ይዘት ያላቸውን ነገሮች ማሰራጨት እየተለመደ ሲሆን ቲክቶክ በተደጋጋሚ ቁጥጥር እንዲያደርግ በተለያዩ አካላት ሲጠየቅ ቆይቷል። ቲክቶክ የቀጥታ ስርጭት እገዳው ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ያሳወቀው ነገር የለም። መረጃው የDW ነው። @Yenetube @Fikerassefa
显示全部...
26👍 4
照片不可用在 Telegram 中显示
QR code ወይም ነባሩ ደረሰኝ የሌለው  ከታህሳስ 30/2018 በኋላ የማያገለግል በመሆኑ ፤ እስካሁን QR code ያለውን የማንዋል ደረሰኝ ህትመት ያላቀረባችሁ ግብር ከፋዮች በ10 ቀናት ውስጥ የትዕዛዝ ደብዳቤ ውሰዱ ተብላችኋል፣ደብዳቤው ተያይዟል። Via:- አዩዘሀበሻ @Yenetube @Fikerassefa
显示全部...
1
ትራምፕ  የቅርብ ጊዜውን የሰላም እቅድ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ባለማንበባቸዉ መበሳጨታቸዉን ተናገሩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር የምታደርገውን ጦርነት እንዴት ማስቆም እንደሚቻል የሚያትተዉን የቅርብ ጊዜውን እቅድ የዩክሬን አቻቸዉ ቮልዲሚር ዜለንስኪ አላነበቡትም ሲሉ ተናግረዋል ።በኬኔዲ ማእከል ዋሽንግተን ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ትራምፕ እንደተናገሩት የዜለንስኪ ሰዎች በፍሎሪዳ ከዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ጋር ሲነጋገሩ የቆዩት እቅዱን ወደዉት ነበረ ሲሉ አጥብቀው ተናግረዋል ። ትራምፕ “ሩሲያ ጥሩ ናት” ብለዋል ። "ሩሲያ ዩክሬንን በሙሉ ብትይዝ እንደምትመርጥ እገምታለሁ። ነገር ግን፣ ጥሩ ነች፣ ዘሌንስኪ ጥሩ ስለመሆኑ ግን እርግጠኛ አይደለሁም።" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ዘሌንስኪ ቀደም ሲል ዩክሬን ግዛትን ለሩሲያ አሳልፋ እንድትሰጥ እና የመከላከያ አቅሟን እንድትገድብ የቀረበውን ሀሳብ ተቃውመዋል።ሰኞ ማለዳ ለዩክሬን ህዝብ ባደረጉት ሳምንታዊ ንግግር ዘሌንስኪ ከትራምፕ ልዑካን ጋር "ጠቃሚ ውይይት" መደረጉን ተናግረዋል።አክለውም "የአሜሪካ ልዑካን የዩክሬንን ዋና አቋም ያውቃሉ እና ውይይቱ ቀላል ባይሆንም ገንቢ ነበር፤ ስራችንን እንቀጥላለን አንዳንድ ጉዳዮችን በአካል ብቻ መወያየት ይኖርብናል" ብለዋል፡፡ በቀጠለዉ ዉጊያ በሱሚ ክልል ሰሜን ምስራቅ በምትገኘው ኦክቲርካ ከተማ ሩሲያ በፈጸመችዉ ጥቃት ቢያንስ ሰባት ሰዎች በአንድ ሌሊት ቆስለዋል ሲሉ የክልሉ አስተዳዳሪ ኦሌግ ግሪጎሮቭ ተናግረዋል።ይህ የሆነው ሰው አልባ አውሮፕላኖች አፓርተማዎችን ከመተ በኋላ ነው። በተጨማሪም በቼርኒሂቭ እና ዲኒፕሮፔትሮቭስክ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል፡፡እሁድ እለት በሩሲያ ጥቃቶች አራት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸዉ ይታወሳል። ባለፈው ሳምንት ብቻ በ1,600 የሩስያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና 70 የሚጠጉ ሚሳኤሎች ጥቃት ዩክሬን ደርሶባታል ሲሉ ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ ተናግረዋል። @Yenetube @Fikerassefa
显示全部...
24😁 2🔥 1
照片不可用在 Telegram 中显示
2👍 1
የጠለፋ እና የእገታ ተግባር የፈፀሙ አምስት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ በምዕራብ ሸዋ እና  በሰሜን ሸዋ  ሁለት ዞኖች ውስጥ የጠለፋና የእገታ ተግባር የፈፀሙ አምስት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ።እንደ ምዕራብ ሸዋ ዞን የአደአ በርጋ ወረዳ አቃቢ ሕግ ፅህፈት መግለጫ 1ኛ ተከሳሽ ግርማ ሳሕሉ 2ኛ ተከሳሽ ፀጋ ሐይሉ 3ኛ ተከሳሽ  ቶሊ ደጉ የተባሉ ሶስት ተከሳሾች ጥቅምት 11 ቀን 2018ዓም ከቀኑ ዘጠኝ ሠዓት ላይ ለአንደኛው ተከሣሽ በግዳጅ የትዳር አጋሩ ለማድረግ የአስራ አራት ዓመቷን ታዳጊ ከወፍጮ ቤት ስትመለስ ጠብቀው የጠለፋ ተግባር ፈፅመው ለማምለጥ ሲሞክሩ ተጠላፊዋ ባሰማችው የድረሱልኝ ጩኸት ስልጠና ላይ የነበሩ የፀጥታ አካላት ሰምተው ተከታትለው በቁጥጥር ስር ዉለዋል። ሶስቱም ተከሳሾች በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኃላ በፖሊስ የምርመራ መዝገባቸው  በበቂ ማስረጃ ተጣርቶ ለአቃቤ ሕግ የተላከ ሲሆን አቃቤ ሕግም በወንጀል ሕግ ቁጥር 587 ንዑስ አንቀፅ 1 ሴትን በመጥለፍ ወንጀል ክስ መስርቷል፡፡ ክሱን ሲከታተል የቆየው የአደአ በርጋ ወረዳ ፍርድ ቤት ጥቅምት 24-2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሶስቱም ተከሣሾች ላይ በእያንዳዳቸው ላይ በሉለት አመት ከሶስት ወር እስራት እንደተወሰነባቸው የአቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት መግለጫው አመልክቷል። በተመሳሳይ በወረጃርሶ ወረዳ ሌንጮ ቦርሱ ቀበሌ የጦር መሣርያ በመታጠቅ የእገታ ተግባር ሲፈፅሙ የነበሩ ግለሰቦች በእስራት ተቀጠተዋል።እንደ ወረጃርሶ ወረዳ አቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት መግለጫ  ደሬሣ ተሾመ እና ጀማል ደምሴ የተባሉ ሑለት ተከሳሾች ለግዜው እጃቸው ካልተያዙ ሑለት ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን የጦር መሣርያ በመታጠቅ  መስከረም 25 ቀን 2018 ዓም ሁለት ግለሰቦችን አግተው አፍነው ለመውሠድ ሲሞክሩ በፀጥታ ስራ ላይ በተሠማሩ አካላት በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል። ፖሊስም በሁለቱ ተከሣሾች ላይ አስፈላጊውን ማስረጃ በማሠባሰብ አጠናክሮ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ሕግ የላከ ሲሆን አቃቤ ሕግም ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በጦር መሣርያ በመታገዝ የእገታ ተግባር መፈፀምን ጠቅሶ ክስ የመሠረተ ሲሆን ክሱን ሲከታተል የቆየው የወረጃርሶ ወረዳ ፍርድ ቤት ሕዳር 24 ቀን 2018ዓም በዋለው ችሎት አንደኛ ተከሣሽ ደሬሣ ተሾመ ስምንት አመት ከአራት ወር  እስራት ሁለተኛ ተከሳሽ ጀማል ደምሴ በስድስት አመት ከስድስት ወራት እስራት እንዲቀጡ የወሠነ መሆኑን የአቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት መግለጫ አመላክቷል። Via :- ዳጉ_ጆርናል @Yenetube @Fikerassefa
显示全部...
29👎 5👍 3🔥 2