ch
Feedback
TIKVAH-ETHIOPIA

TIKVAH-ETHIOPIA

前往频道在 Telegram

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። መረጃ እና መልዕክት ፦ 0998999899 ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም 0979333111 @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

显示更多
2025 年数字统计snowflakes fon
card fon
1 572 505
订阅者
-46024 小时
-1 9487
-3 00530
帖子存档
照片不可用在 Telegram 中显示
የትኛው ይሁንሎት? መኪናው? ፍሪጁ፥ TV፥ የልብስ ማጠብያው? በዲጅታል ባንኪንግ ወይም ቅርንጫፍ በመምጣት የአቢሲንያ ባንክ አገልግሎቶችን ያግኙ። ሽልማቱ የእርስዎ ሊሆን ይችላል። #StartRenewGrow #BOARewards #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
显示全部...
star reaction 1 97🙏 6💔 1
照片不可用在 Telegram 中显示
" ልክፈላችሁ ሂዱልኝ ! " " 3,000 ዶላር እሰጣችኋለሁ (ከ465,000 ብር በላይ) ፤ ነጻ በረራ ሁሉ አዘጋጃለሁ ብቻ እናተ በፍቃዳችሁ ምድሬን ለቃችሁ ውጡልኝ " ስትል አሜሪካ በሀገሯ ለሚገኙ ሰነድ አልባ ስደተኞች መልዕክት አስተላልፋለች። በ2026 መጨረሻ ላይ ከአሜሪካ በገዛ ፈቃዳቸው ለመውጣት ለሚፈልጉና በፈረንጆች እስከ ታህሳስ 31 ለሚመዘገቡ ስደተኞች ሀገሪቱ ነፃ በረራ እንዲሁም የ3000 ዶላር ክፍያም ይሰጣቸዋል። በገዛ ፈቃዱ አልወጣም ያለ ስደተኛ ግን ፦ - እስራት፣ - በግዳጅ መባረር - ዳግም ወደ አሜሪካ ምድር መግባት እንዳይችል እገዳ እንደሚጣልበት ሀገሪቱ አሳውቃለች። Via @tikvahethmagazine
显示全部...
1 319😭 663🤔 145😱 91💔 76👏 66😡 64🙏 57🕊 50😢 25🥰 24
" ግለሰብን እንደዛ ማላት ይችላል ሃገርን ግን እንደዛ ማለት አይችልም። ...  ከፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ ወጥቷል " - ኢንስፔክተር ታምሩ ባይሳ የሰሜን ሸዋ ዞን ሰላሌን ተሳድቧል ያላቸውን የሃይማኖት መምህር ሄኖክ ግርማን በቁጥጥር ስር ለማዋል እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጿል። የሰሜን ሸዋ ዞን አቃቤ ህግ ነብይ ሄኖክ ግርማ የ "JPS INTERNATIONAL CHURCH" መስራች ህዝብን በመሳደብ ብጥብጥ በመፍጠር በማሰብ ወንጀል ከሷቸዋል። ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሃይማኖት አስተማሪው አንዲት ሴት ከየት እንደመጣች ከጠየቁ በኋላ ሴትየዋ ከሰላሌ መሆኗን ስትናገር ነብይ ሄኖክ " ሃገሩ የጠንቋይ ነው " ብለው ሲናገሩ የሚያሳይ ቪዲዮ ተሰራጭቶ የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኗል። ቪዲዮው በማህበራዊ ሚዲያዎች ከተለያዩ አካላት ግብረመልስ ያገኘ ሲሆን ነብይ ሄኖክ ግርማም የወጣው ቪዲዮ ያለ አግባብ ተወስዶ ቅሬታን ፈጥሯል በማለት #ይቅርታ ጠይቀዋል። የፊቼ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ታምሩ ባይሳ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ በሰጡት ቃል፥ " ነብይ ሄኖክ ሰላሌን ' የጠንቋይና የሟርተኛ ሃገር ' " ብሏል ያሉ ሲሆን " ግለሰብን እንደዛ ማለት ይችላል፤ ሃገርን ግን ማለት አይቻልም " ሲሉ ተናግረዋል። ኢንስፔክተሩ በቪዲዮው ላይ የታየችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሏን ገልፀው ነብይ ሄኖክን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ ወጥቷል ብለዋል። " ነብይ ሄኖክ አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ ነዋሪ መሆኑን ሰምተናል " ያሉት ኢንስፔክተር ታምሩ የተያዘችው ግለሰብ ስለሁኔታው ማመኗን ገልፀዋል። " በቲክቶክ እና በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው ቪዲዮ በማስረጃነት ተይዟል በህግ አካሄድ ሰንሰለትን በመከተል በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተሰራ ነው " ሲሉ አክለዋል። @tikvahethiopia
显示全部...
👏 1 724 797😡 143🤔 64😭 47🙏 32💔 27🕊 15😢 7😱 4🥰 3
Repost from N/a

" ተጠርጣሪው በተለምዶአዊው ንግግር ሊገለፁ የማይችሉ አስፀያፊ ቃላትን በመጠቀም በትውልዱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር ነበር " - ፖሊስ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ። ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጩ ከነበሩ ግለሰቦች አንዱ የሆነው ነዋሪነቱ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የሚገኝ ናትናኤል ባደግ ገብሬ የተባለን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል። ግለሰቡ የማህበራዊ ሚዲያን (YouTube  እና TikTok) ን በመጠቀም በንግግር ልቅ ፆታዊ ግንኙነትን የሚያበረታታና የሚያስፋፋ አፀያፊ መልዕክቶችን ሲያሰራጭ በመቆየቱ በቁጥጥር ስር እንዳዋለው አስረድቷል። ተጠርጣሪው በተለምዶአዊው ንግግር ሊገለፁ የማይችሉ አስፀያፊ ቃላትን በመጠቀም በትውልዱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር እንደነበር እና መሰል ይዘቶችን በተደጋጋሚ ጊዜ በመስራት በማህበራዊ ሚዲያ (YouTube እና TikTok) በመጠቀም ሲያሰራጭ እንደነበር ፖሊስ አብራርቷል፡፡ ፖሊስ በቁጥጥር ስር በዋለው ናትናኤል ባደግ ወይም " የማህበራዊ ሚዲያ አንቂ ወይም ይዘት ፈጣሪ ነኝ " በሚለው ግለሰብ ላይ ምርመራ ጀምሯል። በአንዳንድ ኃላፊነት በማይሰማቸው ግለሰቦች በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከህብረተሰቡ ሞራል ባህልና እሴት ባፈነገጠ ሁኔታ አሉታዊ መረጃዎች እየተሰራጩ መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ በማህበረሰቡ በተለይም ታዳጊ በሆኑ ህፃናት ሥነ-ልቦናና ሞራል ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን ገልጿል። በቀጣይም ተመሳሳይ ድርጊት ውስጥ በሚገቡ ግለሰቦች ላይ ተገቢውን ህጋዊ ርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል። ከዚህ ቀደም ፖሊስ በቲክቶክና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያዎች ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን አሰራጭተዋል ፣ በአለባበስም አሳይተዋል ያላቸውን ወጣቶች በቁጥጥር ስር ውሎ ለቋቸዋል። #TilvahEthiopiaFamilyAA #AddisAbabaPolice @tikvahethiopia
显示全部...
star reaction 303👏 3 709 1 024😡 144🙏 109😭 58🤔 49😢 44🕊 35😱 19🥰 18💔 15
照片不可用在 Telegram 中显示
እድለኞቹ ከተሞች እነሆ! 💰 በመላው ሀገሪቱ በሽ እድለኞች ያፈራው ፕሮግራማችን እነዚህን ቦታዎች ነክቶ አልፏል! ስለተሳትፎአችሁ እጅግ እናመሰግናለን! #SafaricomEthiopia #furtheraheadtogether #besh
显示全部...
109😡 32🙏 11🤔 8🥰 6💔 2
" ተጠርጣሪው በተለምዶአዊው ንግግር ሊገለፁ የማይችሉ አስፀያፊ ቃላትን በመጠቀም በትውልዱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር ነበር " - ፖሊስ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ። ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጩ ከነበሩ ግለሰቦች አንዱ የሆነው ነዋሪነቱ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የሚገኝ ናትናኤል ባደግ ገብሬ የተባለን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል። ግለሰቡ የማህበራዊ ሚዲያን (YouTube  እና TikTok) ን በመጠቀም በንግግር ልቅ ፆታዊ ግንኙነትን የሚያበረታታና የሚያስፋፋ አፀያፊ መልዕክቶችን ሲያሰራጭ በመቆየቱ በቁጥጥር ስር እንዳዋለው አስረድቷል። ተጠርጣሪው በተለምዶአዊው ንግግር ሊገለፁ የማይችሉ አስፀያፊ ቃላትን በመጠቀም በትውልዱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር እንደነበር እና መሰል ይዘቶችን በተደጋጋሚ ጊዜ በመስራት በማህበራዊ ሚዲያ (YouTube እና TikTok) በመጠቀም ሲያሰራጭ እንደነበር ፖሊስ አብራርቷል፡፡ ፖሊስ በቁጥጥር ስር በዋለው ናትናኤል ባደግ ወይም " የማህበራዊ ሚዲያ አንቂ ወይም ይዘት ፈጣሪ ነኝ " በሚለው ግለሰብ ላይ ምርመራ ጀምሯል። በአንዳንድ ኃላፊነት በማይሰማቸው ግለሰቦች በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከህብረተሰቡ ሞራል ባህልና እሴት ባፈነገጠ ሁኔታ አሉታዊ መረጃዎች እየተሰራጩ መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ በማህበረሰቡ በተለይም ታዳጊ በሆኑ ህፃናት ሥነ-ልቦናና ሞራል ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን ገልጿል። በቀጣይም ተመሳሳይ ድርጊት ውስጥ በሚገቡ ግለሰቦች ላይ ተገቢውን ህጋዊ ርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል። ከዚህ ቀደም ፖሊስ በቲክቶክና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያዎች ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን አሰራጭተዋል ፣ በአለባበስም አሳይተዋል ያላቸውን ወጣቶች በቁጥጥር ስር ውሎ ለቋቸዋል። #TilvahEthiopiaFamilyAA #AddisAbabaPolice @tikvahethiopia
显示全部...
1
"በኢታንግ ልዩ ወረዳ ዛሬ ንጋት 11 ሰዓት በጀመረው ተኩስ ከ30 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። የሞቱት ህፃናትም በርካታ ናቸው። የአጎቴ ልጆች የት እንዳሉ አይታቅም። ቤታቸው ተቃጥሏል" - ነዋሪዎችና ቤተሰብ ➡️ "ሥራ እየሰራን ነው፤ ስንጨርስ እንነግራችኋለን"- የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ ተርፋም ቀበሌ ዛሬ ረቡዕ ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ/ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ በተከፈተ ተኩስ "ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸውን" ነዋሪዎችና የዓይን እማኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች ባለፉት ሳምንታት በጸጥታ ችግር የንጹሐን ህይወት መቀጠፉን፣ ተጎጅዎች የህክምና አገልግሎት እንዳላገኙ ነዋሪዎች፣ የተጎጂ ቤተሰቦች፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ዛሬ ደግሞ በኢታንግ ልዩ ወረዳ "በርካቶች ተገድለዋል" ተብሏል። የአካባቢው ነዋሪዎችና አንድ የዓይን እማኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ "በኢታንግ ልዩ ወረዳ ዛሬ ንጋት 11 ሰዓት በጀመረው ተኩስ ከ30 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። የሞቱት ህፃናትም በርካታ ናቸው" ብለዋል። በወረዳው ተርፋም ቀበሌ የተኩል ልውውጥ ሲደረግ መዋሉን በመግለጽ፣ "ሁኔታው ከበድ እያለብን ነው" የሚሉት ነዋሪዎቹ፣ በርካታ ሰዎች በጥይት ተመትነው እንደቆሰሉ፣ ንጋት ላይ ሰዎች በተኙበት ቤት የማቃጠል ድርጊት እንደተፈጸመ አስረድተዋል። ከቦታው ሆነው የተኩሱን ሁኔታ በቅርብ ርቀት ሲከታተሉ የነበሩ አንድ የዓይን እማኝ የክልሉ ነዋሪ፣ "የአንድ፣ የሁለት ዓመት ህፃናት" ጨምር ህይወታቸው ማለፉን ገልጸዋል። "የኔም የአጎቴ ልጆች የት እንዳሉ አይታቅም። ቤታቸው ተቃጥሏል። ልጆች፣ አረጋውያን፣ ወጣቶችም ተገድለዋል" ሲሉ ገልጸው፣ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ በአንክሮ አሳስበዋል። "ቤቶች ተቃጥለዋል፤ በቃጠሎና በጥይት ህይወታቸው ያረፈው በርካታ ናቸው። በቦንብ የተመቱ ነዋሪዎችም አሉ" የሚሉት የዓይን እማኝ፣ "ከደቡብ ሱዳን የገቡ ሰዎች በተኩሱ ሲሳተፉ ተስተውለዋል" ሲሉ አክለዋል። የጸጥታ ችግሩ በተመለከተ ምን ምላሽ እንዳላቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸው የክልሉ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ፣ " የጸጥታ አካላት ጋር ደውሉ ስብሰባ ላይ ነኝ" ያሉ ሲሆን፣ የጸጥታ ኃላፊው ስልክ እንዳላነሱ ስንነግራቸውም፣ "ሥራ እየሰራን ነው፤ ስንጨርስ እንነግራችኋለን " የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል። የክልሉ ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ለጊዜው ስልክ ያላነሱ ሲሆን፣ የክልሉ መንግስት በበኩሉ፣ የጋምቤላ ከተማን ጨምሮ "የጸጥታ  ችግር በሚስተዋልባቸው የክልሉ አካባቢዎች" "ከጸጥታ አካላት ውጭ የሰውና የተሽከርካሪ" የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን አስታውቋል። በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች "በአኘዋክና ኑዌር ብሔረሰቦች መካከል" በተለያዩ ጊዚያቶች "ግጭት" ሲነሳ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን፣ ከአመት በፊት ቆሞ እንደነበር አሁን ደግሞ ማገርሸቱን፣ ችግሩን ለማስቆምም እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሽኔ አስቲን ከሳምንት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል። የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ በበኩሉ፣ ችግሩን ለማስቆም እየተሰራ መሆኑን፣ 18 ተጠርጣሪዎች እንደተያዙ ከሳምንት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ የሚታወስ ሲሆን፣ ነዋሪዎቹ ደግሞ ዛሬ በኢታንግ ልዩ ወረዳ የተኩስ ልውውጥ እንደተደረገ ገልጸው፣ "በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ የአኙዋክና ኑዌር ብሔረሰቦች" እንዳሉ፣ በዛሬ ተኩስም "ከደቡብ ሱዳን የመጡ ታጣቂዎች" እንተሳተፉ እየተናገሩ ናቸው። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
显示全部...
490😭 265🕊 44😱 18😡 15💔 14🤔 13🙏 9😢 8
#NewsAlert🚨 #Gambella የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ ! የጋምቤላ ከተማን ጨምሮ የፀጥታ ችግር በሚስተዋልባቸው የክልሉ አካባቢዎች ከዛሬ ጀምሮ የሚተገበር የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ። የጋምቤላ ክልል መንግስት ከዛሬ ጀምሮ ከምሽት 2 :00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 :00 ሰዓት ከተፈቀደላቸው አካላት ውጪ ማንኛውም ሰው ሆነ ተሽከርካሪ እንዳይንቀሳቀስ የሰዓት እላፊ ገደብ ጥሏል። ሰሞኑን በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት የሰዓት እላፊ ገደቡ መጣሉን የገለጸው ክልሉ ይህም ላልተወሰነ ጊዜ ተግባራዊ ሆኖ የሚቀጥል ነው ብሏል። ከዛሬ ጀምሮ ከተመደቡ የጸጥታ ኃይል በስተቀር ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ማንኛውም ተሽከርካሪ ሆነ ሰው መንቀሳቀስ ተከልክሏል። ከተፈቀደላቸው የፀጥታ አካላት ውጪ የትኛውም ቦታ ጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻል ተገልጿል። ሁሉም ይህንን ትዕዛዝ እንዲፈጽም ማሳሰቢያ ተላልፏል። #TilvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
显示全部...
629🕊 63👏 61🙏 36😭 36🥰 15😡 15🤔 13
የአውሮፓ የፀረ ደን ምንጣሮ ደንብ (EUDR) መራዘሙ ለኢትዮጵያ ቡና ዘርፍ ምን ትርጉም አለው ? የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ ከሁለት ዓመት በፊት ያፀደቀውን የፀረ ደን ምንጣሮ ደንብ (EUDR) ትግበራ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ማራዘሙን አስታውቋል። ደንቡ ከቀጣዩ ታኅሣሥ 21/2018 ዓ.ም ጀምሮ ይተገበራል ተብሎ ቢጠበቅም፣ አሁን በተወሰነው መሠረት ለአነስተኛና ጥቃቅን አምራቾች የ1 ዓመት ከ6 ወር፣ ለከፍተኛ ኩባንያዎች ደግሞ የ1 ዓመት የዝግጅት ጊዜ ተሰጥቷል። የአውሮፓ ኅብረት ፀረ ደን ምንጣሮ ደንብ (EUDR) ምንድን ነው? ከኢትዮጵያ ጋር ምን አገናኘው? EUDR ወደ አውሮፓ የሚገቡ ምርቶች ለደን ጭፍጨፋ እና ለደን መመናመን አስተዋፆ አለማድረጋቸውን ለማረጋገጥ የወጣ ደንብ ነው። ይህ ደንብ የኢትዮጵያን ዋነኛ የውጪ ንግድ ምርት የሆነውን ቡናን ጨምሮ ሰባት ምርቶች (ከብት፣ ካካዋ፣ የፓልም ዘይት፣ አኩሪ አተር፣ እንጨትና ራበር) ላይ ያነጣጠረ ነው። በደንቡ መሠረት ከታኅሣሥ 22/2013 ዓ.ም ወዲህ በደን ምንጣሮ የተገኙ ምርቶች ወደ አውሮፓ መግባት አይችሉም፤ ጥሳቱ ከተገኘም ኩባንያዎቹ ከባድ ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ኢትዮጵያ ከጠቅላላ የቡና ምርቷ 40 በመቶ የሚሆነውን ወደ አውሮፓ የምትልክ በመሆኗ ደንቡ ቀጥተኛ ተፅዕኖ አለው። የኢትዮጵያ ቡና ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ግዛት ወርቁ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲያስረዱ፥ "ደንቡ በቀኑ ተፈፃሚ ቢሆን ኖሮ እነሱም ቡናውን ሊያጡት ይችላሉ፣ እኛም መስፈርቱን አሟልቶ ማቅረብ ይከብደን ነበር" ብለዋል። የማረጋገጫ ሂደቱ እና የቴክኖሎጂው ፈተና የቡና ምርቱ ከደን ምንጣሮ ነፃ መሆኑን ለማረጋገጥ Geolocation የተሰኘ በጂፒኤስ (GPS) እና በሳተላይት የታገዘ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ መዋል ይኖርበታል። ይህ ሂደት ግን ለኢትዮጵያ ከባድ እንደሆነ ባለሙያዎች ይስማማሉ። የአቶ ግዛት ወርቁ"6 ሚሊዮን አርሶ አደር ማሳ ላይ ቆመህ ጂኦሎኬት ማድረግ ብቻ እንኳ ከፍተኛ ወጪና ጊዜ የሚጠይቅ ሥራ ነው" በማለት የሥራውን ስፋት ያስረዳሉ። ሌላው የዘርፉ ባለሙያ አቶ ዳንኤል ዘረዓ ያዕቆብ በበኩላቸው "እንደ ብራዚልና ቬትናም በትልልቅ እርሻ ሳይሆን በየቦታው በተበጣጠሰ ማሳ ላይ ለሚመረት የኢትዮጵያ ቡና፣ እያንዳንዱን ማሳ ኦዲት አድርጎ ዳታ ቤዝ ውስጥ ማስገባት ከፍተኛ የቴክኒክ ሥራ፣ የሰው ኃይል እና የገንዘብ አቅም ይጠይቃል" ብለዋል። እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች እና የመራዘሙ ጥቅሞች ምንም እንኳ ፈተናው ከባድ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን መረጃ የሚተላለፍበት ሞባይል መተግበሪያ (App) ማዘጋጀቱንና ትልልቅ ማኅበራት (ዩኒየኖች) ጂኦሎኬት የማድረግ ሥራ መጀመራቸውን አቶ ግዛት ጠቅሰዋል። “መስፈርቱን ለማሟላት የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች በ2025 (በፈረንጆች አቆጣጠር) ሲለፉ ነው የቆዩት። ጂኦሎኬት ማድረግን ጨምሮ የቻሉትን ያህል ሄደዋል። ትላልቆቹ ኮሜርሻል ፋርሞችም እየሰሩ ነው።. . . ጂኦሎኬት ተደርጎ ለአውሮፓ ህብረት ገበያ ዝግጁ የሆኑ አሉ። የኦሮሚያ፣ የሲዳማና የይርጋጨፌ ዩኒየኖች የራሳቸወን ጥረት ሲያደርጉ ነው የቆዩት” ብለዋል። የደንቡ መራዘም የሚሰጠው ጥቅም ይኖር ይሆን ? አቶ ግዛት፥ "አሁን ቢጀመር ኖሮ ለአውሮፓ ቡና ለመሸጥ እንቸገር ነበር፤ መራዘሙ በትክክል ጠቅሞናል" ሲሉ ጥቅሙን አስረድተዋል። 40 በመቶ ትንሽ አይደለም አይደለም የሚሉት አቶ ግዛት  የአውሮፓን መስፈርት ለማሟላት ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን ሰሜን አፍሪካና መካከለኛው ምሥራቅ ያሉ አማራጭ ገበያዎችን ለማየት ጊዜ ይሰጣል ብለዋል። አቶ ዳንኤል በበኩላቸው፥ ልክ እንደ አረንጓዴ አሻራ ሁሉ መንግሥት በሀገር ደረጃ የቡና ማሳዎችን ዳታ ቤዝ በማደራጀት ረገድ ከፍተኛ እገዛ ሊያደርግ ይገባል የሚል ሀሳብ አንስተዋል። የአውሮፓ ኅብረት የወሰደው የመራዘም ውሳኔ ለኢትዮጵያ ቡና ኤክስፖርት ትልቅ "የትንፋሽ ጊዜ" የሰጠ ሲሆን፣ በቀጣዩ አንድ ዓመት ውስጥ ግን የተቀመጡትን የቴክኖሎጂ መስፈርቶች አሟልቶ መገኘት ለዘርፉ ህልውና ወሳኝ ሆኖ ቀጥሏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TilvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
显示全部...
498👏 27🤔 8😡 7😢 3🥰 2😭 2🕊 1
#Gambella🚨 በጋምቤላ ክልል ፤ ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ ፑልኮት / ተርፋም አካባቢ (ወደ ደቡብ ሱዳን ድንበር) ዛሬ ኃይለኛ ግጭት ሲካሄድ እንደዋለ፤ በዚህም የሰዎች ህይወት መጥፋቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጋምቤላ ቤተሰቦቹ ሰምቷል። ዛሬ በአካባቢው ያለው ሁኔታ እንደሚያስፈራ የገለጹልን ነዋሪዎች የፌዴራል መንግሥት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈልግ አሳስበዋል። በአንድ ቀበሌ ብቻ የበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋቱን አመልክተዋል። ቤቶችም ሲቃጠሉ እንደዋሉ ጠቁመዋል። ለስራ ጉዳይ ከጋምቤላ ከተማ 120 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ኚኛንግ እንዳለ የገለጸልን አንድ የቤተሰባችን አባልም የግጭቱን አሳሳቢነት ገልጾልናል። መሄጃም ይሁን መምጫ መንገድ መዘጋቱን በመጠቆም ስጋት ላይ መውደቃቸውን አስረድቷል። ግጭቱ እንዲበርድ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግ እንዲሁም ወደ ጋምቤላ ከተማ የሚወጡበት መንገድ እንዲመቻችላቸው ጠይቋል። በጋምቤላ ከተማ እና ዙሪያው በሌሎችም ቦታዎች ሰሞነኛው ግጭት በአገር መከላከያ እና ፌዴራል ፖሊስ እንዲረጋጋ ቢደረግም በኢታንግ ልዩ ወረዳ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑ ተገልጿል። #TilvahEthiopiaFamily @tikvahethiopia
显示全部...
😭 217 213🕊 32🙏 11😡 9😢 6🥰 3😱 2💔 2
#HopeOncology በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የካንሰር ህክምና ብቻ የሚሰጥ ማዕከል የሆነው Hope Oncology 2ተኛ አመት የአገልግሎት ዘመኑን እያከበረ ይገኛል። ይህም በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተስፋፋ ያለውን የህፃናት እና የአዋቂ የካንሰር ህመም የተለየ ትኩረት አጊኝቶ የተሻለ ህክምና እና እንክብካቤ ታካሚዎች እንዲያገኙ ያስቻለ ሲሆን ከሚሰጣቸውም አገልግሎቶች ውስጥ የኬምቴራፒን እና አስተኝቶ ማከምን ጨምሮ 7ቱንም ቀን 24 ሰአት የካንሰር ህክምና ላይ ልምድ ባላቸው ስመጥር ሀኪሞች አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል። በቅርቡ አለም አቀፍ የቀዶ ጥገና ሀኪሞችን በማካተት የካንሰር ቀዶ ጥገና ህክምናን በሀገር ውስጥ ለማስጀመር እየተዘጋጀ ሲሆን ይህም ታካሚዎች ወደ ውጪ ሀገር መጓዝ ሳያስፈልጋቸው የላቀ የካንሰር ቀዶ ህክምና አገልግሎት በሀገር ውስጥ ማግኘት እንዲችሉ ያደርጋል። አድራሻ:-  ጦር ሀይሎች ከሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን 200 ሜትር ዝቅ ብሎ ኢብራሂም ህንፃ ፊት ለፊት ☎️ ስልክ:- 0916363738 / 0973555566
显示全部...
371👏 73🙏 23😭 11🕊 5😡 4😢 2