ch
Feedback
TIKVAH-ETHIOPIA

TIKVAH-ETHIOPIA

前往频道在 Telegram

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። መረጃ እና መልዕክት ፦ 0998999899 ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም 0979333111 @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

显示更多
2025 年数字统计snowflakes fon
card fon
1 572 289
订阅者
-46024 小时
-1 9487
-3 00530
帖子存档
የዜጎች የመደራጀት እና የፖለቲካ ፖርቲ የመመሥረት ሕገ-መንግሥታዊ መብት ጥሠትን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ዛሬ አንድ መግለጫ አውጥቷል። በዚህም መግለጫ ይህን ሰርፎ ተመልክተናል ፦ 1. " ' የኮንቶማ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ' መሥራቾች ፓርቲ ለመመሥረት የሚያስፈልጉ ሁሉንም ሕጋዊ ሠነዶች አሟልተው የመሥራች ጠቅላላ ጉባዔያቸውን ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡታጅራ ከተማ እንደሚያደርጉ ለቦርዱ ማሳወቃቸውን ተከትሎ ቦርዱ፦ - ለክልሉ መንግሥት አስተዳደር፣ - ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፣ - ለምሥራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር፣ - ለቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፣ - ለማረቆ ልዩ ወረዳ ከማንድ ፖስት እና ለቡታጅራ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ለመሥራቾቹ የፀጥታ ድጋፍ ትብብር እንዲደረግላቸው በደብዳቤ አሳውቋል። የቦርዱ ባለሙያዎችም በሕጉ መሠረት በቦታው በመገኘት ታዝበው ሪፖርት እንዲያቀርቡ ተመድበው ነበር፡፡ ሆኖም ግን የክልሉ የፀጥታ አካላት፤ ጉባዔ መደረግ የማይችልበትን ሁኔታ በጽሑፍ ለቦርዱ ሳያሳውቁ #መሣሪያ_የታጠቁ የቡታጅራ ከተማ የፀጥታ አካላት በጉባዔው ዕለት ' ከተማው በኮማንድ ፖስት ሥር ስለሆነች መሰብሰብ አይቻልም ' በሚል ለስብሰባ የመጡ የፓርቲው መሥራች አባላቶችን ከአዳራሽ በማስወጣት በቁጥጥር ሥር እንዳዋሏቸው ቦርዱ በታዛቢነት ከላካቸው ባለሞያዎቹ ሪፖርት መረዳት ተችሏል። " 2. " ' የደንጣ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ' መሥራቾች ፓርቲ ለመመሥረት የሚያስፈልጉ ሁሉንም ሕጋዊ ሠነዶች አሟልተው የመሥራች ጠቅላላ ጉባዔ ታኅሣሥ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀድያ ዞን ቢጠና ታዳጊ ከተማ እንደሚያደርጉ ለቦርዱ ማሳወቃቸውን ተከትሎ፤ ቦርዱ ለክልሉ መንግሥት አስተዳደር፣ ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እና ለሀድያ ዞን አስተዳደር ለመሥራቾቹ የፀጥታ ድጋፍ እንዲደረግላቸው በደብዳቤ አሳውቋል፡፡ የቦርዱ ባለሙያዎችም በቦታው ተገኝተው በመታዘብ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ተመድበው ነበር። ሆኖም ግን መሥራቾቹ ተሟልተው ጉባዔው ሊጀመር ሲል የከተማዋ የፀጥታ አካላት ' ስብሰባውን ማድረግ አይቻልም፣ የፀጥታ ድጋፍ አናደርግላችሁም፣ አደጋ ቢደርስባችሁም ኃላፊነቱን አንወስድም እንዲሁም ስብሰባውን ለመረበሽ የተዘጋጁ አካላት አሉ ቦታውን ለቃችሁ ውጡ ' በማለት የቦርዱን ታዛቢዎች ከከተማዋ ለቀው እንዲወጡ አድርገዋቸዋል፡፡ " ቦርዱ ምን አለ ? በየደረጀው የሚገኙ የክልሉ የመንግሥት አካላት በሕገ መንግሥቱ እንዲሁም በዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሠረት ለዜጎች የተረጋገጠውን የመደራጀት እና የፖለቲካ ፓርቲ የመመሥረት መብት ማስተጓጎላቸው የፖለቲካ ምኅዳር የሚያጠብ ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ተግባር ነው ብሏል። በየደራጃው የሚገኙ የክልሉ የመንግሥት አካላት የዜጎች የመደራጀት እና የፖለቲካ ፖርቲ የመመሥረት ዲሞክራሲያዊ መብት ላይ የሚፈጸሙ የማስተጓጎል ተግባራት ላይ ተገቢው የዕርምት ዕርምጃ እንዲወስዱ በጥብቅ አሳስቧል። #NBE @tikvahethiopia
显示全部...
354👏 29😡 21🤔 10🙏 5😢 4😭 3
照片不可用在 Telegram 中显示
የወዳጅ ዘመዶችዎ ችሮታ + የዓባይ ባንክ ስጦታ = ታላቅ ደስታ! ከባሕር ማዶ በፈጣን እና አስተማማኝ የሐዋላ ወኪሎቻችን የሚላክልዎን ገንዘብ ከዓባይ ባንክ ሲቀበሉ እና ሲመንዝሩ 4 በመቶ ተጨማሪ ጉርሻ ከፈጣን አገልግሎት ጋር ስናበረክትልዎ በደስታ ነው፡፡ በዓባይ ባንክ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ 4% ጉርሻ ይሸለሙ! 🌐 ለበለጠ መረጃ ወደ 8834 ይደውሉ፤ ወይም በ customercare@Abaybanksc.com ኢሜል ይላኩልን፤ በታላቅ ትህትና እናስተናግድዎታለን፡፡ ለክፍት የሥራ መደቦችና ፈጣን የፋይናንስ መረጃዎች ከባንካችን የማኅበራዊ ሚዲያዎች ጋር ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook|Telegram |X|LinkedIn|YouTube|TikTok|Instagram| ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!
显示全部...
180🙏 8😡 3🥰 2👏 2🕊 1😭 1
" አጥሮቹን አንሱ ብዬ ማስጠንቀቂያ ብሰጥም ስላልተነሱ በግብረኃይል ማንሳት ጀምሬያለሁ " - የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በከተማዋ ተለያዩ አካባቢዎች በአጥር የተዘጉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በግብረ ኃይል የማንሳት ስራ በዛሬው ዕለት በይፋ መጀመሩን አሳውቋል። መ/ቤቱ " የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን የዘጋችሁ አንሱት ብዬ ባስጠንቅቃችሁም ስላላነሳችሁ በግብረ ኃይል ወደ ማንሳት ልገባ ተገድጀለሁ " ብሏል። ዛሬ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቃሊቲ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ጀርባ የውስጥ ለውስጥ መንገድ የዘጉ አጥሮችን የማንሳት ስራ መጀመሩን ገልጿል። " በቀጣይ ቀናት ይህንኑ ተግባር በሁሉም የከተማዋ ክፍሎች አጠናክረዋለሁ " ሲል አሳውቋል። የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በአጥር በመዘጋታቸው ነፍሰጡር እናቶች ሌሊት ላይ ወደ ህክምና ተቋም ለመሄድና የአደጋ መካከል ሥራዎችን በአግባቡ ለማከናወን አስቸጋሪ ሁኔታ መፍጠራቸው ተመላክቷል። የተበላሹ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ለመጠገንም ፈተና እንደሆኑ ተገልጿል። ፎቶ/ቪድዮ፦ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ @tikvahethiopia
显示全部...
5.05 MB
1 921👏 626😡 109😭 86🤔 59🙏 58🕊 31💔 14😢 12😱 1
" የተጠረጠሩ 21 ሰዎች አሉ። የኦሮሚያ ጸጥታ ዘርፍም አረጋግጦ አስቀምጧል፤ ደብዳቤም አለ " - የሆሮጉዱሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ➡️ " 12 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች ታስረዋል፤ ዲያቆናትም፤ ካህናትም አሉበት። የወልዳ ዱከ ማህበር ሰብሳቢም አሉበት " - ቤተክርስቲያኗ ከሳምንት በፊት በተገደሉት የሆሮጉድሩ ወለጋ ሀገረ ስብሰት ዋና ስራ አስኪያጅ በመላከኤዶም ቀሲስ ዱጉማ ግድያ 21 ሰዎች መጠርጠራቸውን፣ ከእነዚህም መካከል ወደ 12 የሚሆኑት መያዛቸውን ሀገረ ስብከቱና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። የሆሮጉድሩ ወለጋ ሀገረስብከት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ ? ስለጉዳዩ የጠየቅነው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሆሮጉድሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ " የተጠረጠሩ 21 ሰዎች አሉ። የኦሮሚያ ጸጥታ ዘርፍም አረጋግጦ አስቀምጧል፤ ደብዳቤም አለ " ብሏል። ለደኀንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁን አንድ የሀገረ ስብከቱ አመራር፣ " ሟቹ መጀመሪያ አመልክተዋል፤ በፊትም ሲጣሉ የነበረው 'በኦሮሚያ ሲኖዶስና በኢትዮጵያ' ተብሎ እንዲሞቱ ብዙ ትኩረት ሲያደርጉ የነበሩት እነኝህ ሰዎችን ነው " ያሉ ሲሆን፣ ሟቹ ይህን መናገራቸውን "መንግስትም ያውቃል" ሲሉ ገልጸዋል። "እሳቸው መጀመሪያም 'እኔ ከሞትኩ' ብለው ማመልከቻ አስገብተው 21 ሰዎችን ጠቅሰው 'የሀገሩ ጸር ስለሆኑ ክትትል እንድታደርጉ' ብለው ለጸጥታ ዘርፍም ለሀገረ ስብከቱም ደብዳቤ ተጽፏል። ደብዳቤው ያልገባበት ቦታ የለም በእጃችንም አለ" ነው ያሉት። ከተጠርጣሪዎቹ መካከል በቁጥጥር ስር የዋሉ አሉ? " ተጠጣርዎቹ የቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰሩ ካህናትና ዲያቆናት አሉበት " መባሉስ ትክክል ነው ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄም፣ "6 ሰዎች ተይዘዋል" የሚል ምላሽ ሰጥተው፣ "ከተጠርጣሪዎቹ መካከል የቤተክስርስቲያን አገልጋዮች አሉበት" መባሉን በተመለከተ ግን ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ቤተክርስቲያኗ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለች ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ማብራሪያ የጠየቃቸው አንድ የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አመራር፣ " በግድያው 12 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች ታስረዋል፤ ዲያቆናትም፤ ካህናትም አሉበት። ዞሮ ዞሮ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግሉ ናቸው። የወልዳ ዱከ ማህበር ሰብሳቢም አሉበት' የሚል መረጃ አጣርቻለሁ" ብለዋል። ታሰሩ የተባሉትም በሆሮጉድሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መላከ ኤዶም ቀሲስ ዱጉማ ግድያ ተጠርጥረው መሆኑን እኝሁ አካል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። የካህናቱን ግድያ በተመለከተም፣ "የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እጅ አለበት፤ ሟች ዋና ስራ አስኪያጁም ከሞትኩ ገዳዮቸ እነዚህ ናቸው ብለው ስም ዝርዝራቸውን ጭምር ተናግረው ነበር" የሚል መረጃ ሰሞኑን ማህበራዊ ሚዲያው በሰፊው ተሰራጭቷል። ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ የጠየቃት ቤተክርስቲያኗ፣ " በግድያው እጃቸው ያለበት ሰዎች አሉ " በሚል " ሚዲያው ላይ እየወጣ ያለው ነገር ትክክል ነው " ብለዋል። " ቤተክስርስቲያኗም ተጨማሪ ማጣራት አድርጋ የሆነ ማለቷ አይቀርም " ሲሉም ገልጸዋል። ከግድያው ጋር በተያያዘ ስሙ የተነሳው “በኢትየጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአፋር ኦሮሞ መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት በ2004 የተመሰረተው” ወልዳ ዱከ ቡኦታ ጠቅላላ ማህበር በበኩሉ፣ በማህበሩ አባል መላከኤዶም ቀሲስ ዱጉማ እንዲሁም በቀሲስ ደሳለኝ ነሞምሳ ግድያን ማውገዙን አስተውሶ፣ ይሁን እንጅ “የስም ማጥፋት ዘመቻ በሰፊው ተከፍቶብኛል” ሲል ባወጣው መግለጫ ወቅሷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል እና ሆሮጉዱሩ ወለጋ የጸጥታ አካላት ስለጉዳዩ ያላቸውን ሀሳብ ለማካተት ጥረት ቢያደርግም ለጊዜው ያልተሳካ ሲሆን፤ ፈቃደኞች ከሆኑ በሩ ክፍት ነው። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
显示全部...
733😭 226🙏 25🕊 22💔 18🤔 17😡 15👏 11🥰 5😢 5
አፋልጉን 🙏 " እናቴ ለመጨረሻ ጊዜ የታየችው መርካቶ አካባቢ ነበር ከዛ በኋላ የደረሰችበትን አላወቅኩም ! " - ፈላጊ ልጅ ወ/ሮ እማዋይ ብርሀኑ የተወለደችው ወሎ፣ ተንታ ሚካኤል ሲሆን ወላጅ አባቷ አቶ መኮንን ታየ ይባላሉ። ያደገችው አረጋሽ ታየ ከተባሉ አክስቷ ጋር በደብረ ታቦር ከተማ ነው። ፈላጊ ልጃቸው እንደገለጸችው ፤ ከዛሬ 22 አመት በፊት ከታናሽ እህቷን ይዛ ከደብረ ታቦር ወደ አዲስ አበባ ሄደዋል። ለመጨረሻ ጊዜ የታየችው አዲስ አበባ ወደ መርካቶ አካባቢ ዘመዶቿ ጋር ነበር። አሁን ላይ ያለችበት አይታወቅም። " የእናቴን ወይም የቤተሰቦቿን አድራሻ የሚያውቅ በዚህ ስልክ ቁጥር ፦ 0913352539 ወይም 0907353522 ይደውሉልኝ። " ስትል ፈላጊ ልጇ ቤዛዊት ይበልጣል ተማፅናለች።                                 ⚫️ " ህዳር 17 ከቤት እንደወጣ አልተመለሰም " - ፈላጊ ቤተሰቦች ወጣት ብሩክ ዘርፋ ይባላል። የ22 ዓመት ወጣት ነው። ከሚኖርበት የደቡብ ወሎ ወረዳ ከሆነችው አልብኮ ወረዳ ህዳር 17 ቀን 2018 ከቤት እንደወጣ እስካሁ  አልተመለሰም። " እስከ ዛሬዋ ቀን ከዛሬ ነገ ይመለሳል ስልክም ይደውላል ብንል በአካልም ይሁን በስልክ ያለበትን ማወቅ አልተቻለም " ብለዋል ቤተሰቦቹ። " በተለያየ መንገድ ያፈላለግን ቢሆንም ያለበትን ሁኔታ ማወቅ አልቻልንም። በአሁኑ ሰዓት መላዉ ቤተሰቡ በጣም ተጨንቆ ይገኛል " ብለዋል። ወጣት ብሩክ ዘርፉን ያየ ወይም ያለበትን የሚያዉቅ ኢትዮጵያዊ በነዚህ ስልክ ቁጥሮች ፦ አባት ዘረፉ ሰጥ አርጌ 0914604593 ወንድም ፀጋዓለም ዘርፉ 0905038483 ደውሎ እንዲያሳዉቀን ሲሉ በፈጣሪ ስም ጠይቀዋል።                                 ⚫️ " ልጃችን ከጠፋች ከአመት በላይ ሆኗታል " - ፈላጊ አሳዳጊዎቿ ሌሊሳ ጂሳ የምትባል ታዳጊ ከጠፋች አንድ አመት እንደሆናት ግን እስካሁን ያለችበትን ማወቅ እንዲሁም ስለሷ የሰሙት ነገር እንደሌለ አሳዳጊዋ ገልጸዋል። ከቤት ወጥታ የጠፋችው በቀን 29/9/2016 ዓ/ም ከለገጣፎ አካባቢ ነው። ያለችበትን የሚያውቅ ወይም ስለሷ የሰማ በስልክ ቁጥር ፦ 0976062116 0929908002 ላይ በመደወል እንዲያሳውቋቸው አሳዳጊዎቿ ተማፅነዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ #አፋላጊ @tikvahethiopia
显示全部...
605🙏 73😭 64💔 22🕊 20😢 15🥰 7😡 5
በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ስለ ሕፃፅ ምን አሉ ? ህወሓት ጨምሮ ትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ 6 የፓለቲካ ፓርታዎች በሕፃፅ የተከሰተው የረሀብ አደጋ የተመለከተ መግለጫ አውጥተዋል። ፓርቲዎቹ  ፦ - ህወሓት - ስምረት  - ሳልሳይ ወያነ ትግራይ - ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ - ዉድብ ናፅነት ትግራይ - ሹም ተምቤን ናቸው። ምን አሉ ? ህወሓት ፦ " ከ5 ዓመታት በላይ በተቀዳደደ ፕላስቲክ እየኖረ ያለው ህዝብ የአራዊት ሲሳይ ሆኗል ፤ የተቀረው ደግሞ እየቀነሰ በመሄዱ ባለው የእርዳታ አቅርቦት ምክንያት ለከፍተኛ ቀውስ ተዳርገዋል። በየቀኑ በረሀብና በሽታ ሰው እየሞተ ነው፤ ጊዜ እየሄደ ነው ፤ ትዕግስትም ልክ አለው። የትግራይ ህዝብ ከዚህ በላይ መከራ የሚሸከም ጫንቃ የለውም ስለሆነም ትግራይ ለማዳከም የተሸረበው ሴራ ተቋቁመን ህዝባችን እስኪያልቅ አንታገስም። "                            •••••••••• ስምረት ፓርቲ ፦ " ' የድርጅት ደህንነት ከህዝብ ድህንነት ይቅደም ' የሚል አቋም ባለው ኋላቀር ቡድንና ጀሌዎቹ ከማንኛውም ጊዜ በላይ በመሬትና ወርቅ ስርቆት ኪሳቸው በሚያደልቡበት ወቅት በምግብና መድሀኒት እጦት ተፈናቃዮች መሞታቸው አንገታችን እንድንደፋ አድርጎናል። የተፈናቃዮች ስቃይ ከሚድያ ተሰውሮ ለዓለም እንዳይታይና እንዳይሰማ ያደረገው ኋላቀሩ ቡድንና አሽከሮቹ ናቸው። ስለሆነም ሁሉም ትግራዋይ ለዚሁ የሁሉም ዓይነት ጥፋቶች መነሻ የሆነው ኋላቀር ቡድንና አሽከሮቹ ለአንዴና ለመጨረሻ ተመንግሎ እንዲወገድ በጋራ መታገል ይገባል። " ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ ፦ " የረሀቡ ዋና ምንጭ ፓለቲካዊ ስንፍና ነው ። ስለሆነም ህዝቡ የረሀብ አደጋውን የሚገታ አስቸኳይ ድጋፍ ከመለገስ ለጎን ለጎን የችግሩ መነሾ የሆነውን ስርዓት እንዲለወጥ አብሮን እንዲታገል ጥሪ እናቀርባለን። "                              •••••••••• ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ፦ " የተደቀነው የረሀብ አደጋ በዘላቂነት እንዲገታ ' ከህዝብ ህልውና ይልቅ ድርጅታዊ ህልውና ይቅደም ' በሚለው መፈክር የሚመራው ጊዚያዊ አስተዳደር ፈርሶ በአቃፊና አሳታፊ ጊዚያዊ አስተዳደር ሊተካ ይገባል። "                             •••••••••• ዉድብ ናፅነት ትግራይ ፦ " አሰቃቂ ረሀቡ ሆን ተብሎ ከዓለም አቀፍ ማህበረብ እንዲደበቅ በማድረግ በተፈናቃዮች ላይ ከፍተኛ ክህደት ተፈፅመዋል። ስለሆነም ይህንን አስነዋሪ ክህደት የፈፀሙ አመራሮች በህግና በሞራል ተጠያቂ ናቸው።                              •••••••••• ሹም ተምቤን ፓርቲ ፦ " አምባገነንና ፀረ-ህዝብ የሆነው የህወሓት ቡድን ዜጎቻችን ወደ ቄያቸው እንዳይመለሱ ለፓለቲካ ትርፍ ሲባል ለ5 ዓመታት ያህል ቁማር እየተጫወተና እንቅፋት ሆኖ ቀጥሏል። ተፈናቃዮች ለከባድ አደጋ ያጋለጠው ቡድን በህግ እንዲጠየቅና እንዲወገድ ሁሉም የትግራይ ወዳጅና ፍትህ ፈላጊ ተደራጅቶ ይታገል። " ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ #TilvahEthiopiaFamilyMekelle @tikvahethiopia
显示全部...
star reaction 3 1 577💔 149😭 86😡 61🕊 60🤔 52🙏 45👏 26😢 21🥰 10
የሳፋሪኮም እና ኢትዮ ቴሌኮም ውዝግብ እንዴት ሊፈታ ይችላል? ኤምፔሳ ኢትዮጵያ በቅርቡ ያስተዋወቀው ‘ኤምፔሳ ለሁሉም’ የተሰኘው መተግበሪያ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ኔትዎርክ (ሲም ካርድ - 09) ተጠቃሚዎች እንዳይገለገሉበት ተከልክሏል የሚል ቅሬታ አቅርቧል። መተግበሪያው በብሔራዊ ባንክ እና በኢንሳ (INSA) ፈቃድ የተሰጠው ቢሆንም፣ የ09 ቁጥር ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን እንዳያገኙ እገዳ ተጥሎባቸዋል ብሏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎችን አነጋግሮ ይህ በአጠቃላይ ምን ያሳያል ? ምንስ መደረግ አለበት ? የሚለውን ዳሷል። 09 ለምን 07 ን አገደ ? ኢትዮ ቴሌኮም ‘የኤምፔሳ ለሁሉም’ መተግበሪያን ያገደበትን ምክንያት ያብራራበት ይፋዊ መግለጫ እስካሁን አላወጣም። ሆኖም ያነጋገርናቸው የኢኮኖሚ ባለሙያዎች የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠቅሰዋል። የኢኮኖሚ ባለሙያው አብዱልመናን መሐመድ (ዶ/ር) ውሳኔው ውድድርን ለመግታት የሚደረግ ሙከራ ሊሆን እንደሚችል ይገልጻሉ። " ቴሌ ብር በተጀመረበት ወቅት ሌሎች ተቋማት ለአንድ ዓመት በፖሊሲ ታግደው ነበር፤ አሁንም ውድድር ሲመጣ ገበያ ይወሰድብኛል በሚል ስጋት እንቅፋት መፍጠር ለደንበኛው ፍትሐዊ አይደለም " ይላሉ። በተቃራኒው የቢዝነስና ኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ከፈለኝ ኃይሉ ግን እገዳው የደንበኞችን ደኅንነት ከመጠበቅ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ይሞግታሉ። " አፕሊኬሽኑ በቴሌ ኔትወርክ ላይ ሲጫን የደንበኞችን መረጃ አክሰስ ሊጠይቅ ስለሚችል፣ ተቋሙ ከዳታ ጥበቃና ከፋይናንስ ተገዢነት ጋር ያለውን ነገር የመመርመር ኃላፊነት ሊኖርበት ይችላል" ብለዋል። አብዱልመናን መሐመድ (ዶ/ር) ይህ ውሳኔ " ለደንበኛውም ፍትሐዊ አይደለም። እኔ እንደ ደንበኝነቴ የፈለኩትን አፕ እንዳልጠቅም ለምን ያግደኛል?  ይኼ ማለት የእከሌን ባንክ አፕ መጠቀም ትችላለህ የዚህን ደሞ አትችልም እንደማለት ነው " ሲሉ ሀሳባቸውን ያስረዳሉ። አቶ ከፈለኝ በአንጻሩ፥ እገዳው " የቴሌብርን መወዳደር አቅም ይፈታተንብኛል ብሎ ሳይሆን የሚከለክለው ኔትዎርክ አቅራቢ እስከሆነ ድረስ በሌሎች ድርጅቶች የቀረቡትን አፕሊኬሽኖች ከህግና ደንብ ተገዢነት ጋራ ያለውን ነገር መመርመር ያስፈልገው ይሆናል…ተወዳዳሪነተን ከመገደብ አንፃር ሊሆን እንደማይችል ግን ተስፋ አደርጋለሁ " ሲሉ አብራርተዋል። ዕገዳው ኤምፔሳ ላይ ምን ተፅህኖ አለው ? አብዱልመናን (ዶ/ር) እገዳው ኤምፔሳ ሰፊው የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኛ ዘንድ እንዳይደርስ እንቅፋት እንደሚሆንበት ጠቅሰው፣ " ይህ አሰራር ለውጭ ተቋማት ጥሩ አይደለም፤ ባንክ ሴክተር ውስጥ ብንገባ እንቅፋት ይግጠመናል የሚል ስጋት እንዲሰማቸው ያደርጋል" ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። አቶ ከፈለኝም ይህንን ስጋት ይጋራሉ። ኢትዮጵያ ለውጪ ኢንቨስትመንት በሯን እየከፈተች ባለችበት በዚህ ሰዓት ኤምፔሳ እየደረገ ባለው ነገር " ኢትዮጵያ የውጪ ኢንቨስትመንት ለመሳብ እያደረገች ያለችውን ጥረት እየተፈተሸ ነው ወይም ሙከራ ላይ ነው ብሎ መወሰድ ይቻላል " ሲሉ ይገልጻሉ። አክለውም፥ "ባንኮችም ሆኑ ሌሎች ኢንቨስተሮች ይኼ ተወዳዳሪነትን የሚገደብ ነገር አለ ብለው ካሰቡ፣ በኢንቨስትመንት መተማመን ላይ ጥያቄን ያጭራል" ሲሉ ተናግረዋል። የ09 እና 07ን ውዝግብ ማን ይፍታው ? አቶ ከፈለኝ ኃይሉ፥ በትብብር መስራት ላይ በማተኮር፤ "ጉዳዩ አንዱ አንዱን የመዋጥ ጉዳይ መሆን የለበትም፤ ሁለቱም አብረው ሊያድጉ ይችላሉ። የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን እና ብሔራዊ ባንክ የመጫወቻ ሜዳው የተደላደለ እንዲሆን ማስቻል አለባቸው" ብለዋል። አብዱልመናን (ዶ/ር) በበኩላቸው ኃላፊነቱን ለተቆጣጣሪዎች ይሰጣሉ። "ቴሌ ሲም ካርዱ እንዳይሰራ ስላደረገ የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን ነው መፍትሄ መስጠት ያለበት። የክፍያ ስርዓቱን ደግሞ ብሔራዊ ባንክ ይመለከተዋል። ሁለቱ ተቋማት ቶሎ ተነጋግረው መፍትሄ መስጠት ያስፈልጋል" ሲሉ አሳስበዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ @tikvahethiopia
显示全部...
882😭 58🤔 33😡 21👏 15🕊 9😱 8🙏 5😢 3💔 3
በአዲስ አበባ መኪና የተሰረቀባቸው ሁለት የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የጠፋባቸውን መኪና እንድታፋልጓቸው ጥሪ አቅርበዋል። የመጀመሪያዋ የተሰረቀችው መኪና ማክሰኞ ሕዳር 30 ቀን 2018 ዓ/ም ነው። የመኪናው አይነት ፦ ቶዮታ ላንድክሩዘር ታርጋ ፦ ኮድ5 - 00769  አሽከርካሪው ቤተሰባችን ኮዬ ፈጬ ወዴሳ ወረዳ ፕሮጀክት 16 ከቀኑ ለ7  20 ጉዳይ  መኪናውን አቁመው ግብር ለመገበር ወረዳ እንደገቡ ገልጸዋል። ልክ 9 ሰዓት ስራቸውን ጨርሰው ሲወጡ መኪናዋን ካቆሙበት አጥተዋታል፤ የለችም። ወዲያው ለፖሊስ ማመልከታቸውን ቢገልጹም እሰከአሁን መኪናው አልተገኘም። ያያችሁ ወይም ስለመኪናው የምታውቁት መረጃ ካለ ፦ በ 0911824413 ወይም 0983286645 ላይ በመደወል እንድታሳውቋቸው ተማጽነዋል። ሌላኛው የጠፋችው መኪና ትላንት 9:30 ላይ ሲሆን እዛው ኮዬ ፈጬ ፕሮጀክት 12 ብሎክ 411 አካባቢ እንደሆነ የጠፋባቸው አሽከርካሪ ገልጸዋል። የመኪና አይነት ፦ ቶዮታ ላንድክሩዘር ታርጋ ፦ ኮድ 35 - 3817 (ዕ.ድ) መኪናዋን ያያችሁ በ0920162695 ወይም 0911672735 ደውላችሁ አሳውቁ። #TilvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
显示全部...
538🤔 147😢 54😭 40🕊 16😡 15🥰 12👏 12🙏 10
‎" ድንገት በተከሰተ በሽታ ከ47 በላይ ከብቶች ሞተዉብናል " - የበና ፀማይ ወረዳ አስተዳዳሪ ‎ ➡ ‎" ከብቶቹ አረፋ እየደፈቁ የሚሞቱ ሲሆን አረፋዉ ላይ የሚያርፉ ዝምቦች ወዲያውኑ ይሞታሉ ! " ‎ ‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን በና ፀማይ ወረዳ ድንገት በተከሰተ የእንሰሳት በሽታ እስካሁን 47 ከብቶች መሞታቸውን የወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዮሐንስ ጋርሾ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ‎ ‎ትናንት ማምሻውን በወረዳዉ ጎልዲያ ቀበሌ በአንድ አከባቢ የተሰማሩ የ6 አርብቶ አደሮች የቤት እንስሳት ከመስክ ወደ ቤት በሚመለሱበት ወቅት አንድ በሬ በአፍና በአፍንጫው አረፋ ደፍቆ ወዲያዉ መሞቱን እና በአንድ ምሽት ሌሎች 42 ከብቶች ዛሬ ደግሞ 4 በድምሩ 47 ከብቶች መሞታቸውን አስረድተዋል። ‎ ‎የበሽታውን ትክክለኛ ምንነት እስካሁን መለየት እንዳልተቻለ የገለፁት ዋና አስተዳዳሪዉ ከሞቱት ከብቶች ናሙና ተወስዶ ለምርመራ ጂንካ ወደሚገኝ የምርምር ማዕከል መላኩንም አስታውቀዋል። ‎ ‎" ዝምቦች በሞቱት ከብቶች አረፋ ላይ ሲያርፉ መርዝ ላይ የተቀመጡ ይመስል ወዲያውኑ ይሞታሉ " ያሉት ዋና አስተዳዳሪዉ አቶ ዮሐንስ ከሞቱ ከብቶች ጋር ንኪኪ የነበራቸዉ ከብቶች ከሌሎች ጋር እንዳይቀላቀሉ እየተደረገ መሆኑንና ከዞኑና ከክልሉ ባለድርሻ አካላት ጋር ችግሩን የመቆጣጠር ስራ እየተሰራ ስለመሆኑ ገልፀዋል። ‎ ‎ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከበሽታው ጋር በተያያዘ የአከባቢዉን አርብቶአደሮች አነጋግሮ ተጨማሪ መረጃ የሚያደርስ ይሆናል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ #TikvahEthiopiaFamilyHawassa #TilvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
显示全部...
#PMOEthiopia ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጻፏቸው መጽሐፍት በመተግበሪያ አማካኝነት በድምጽ ተተርጉመው መቅረባቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ገለጸ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፉት “መደመር” ፣ “የመደመር መንገድ”፣ “የመደመር ትውልድ” እና “የመደመር መንግሥት” መጻሕፍት Medemer በተሰኘ መተግበሪያ በድምጽ ተተርጉመው እንደቀረቡ አመልክቷል። " መጽሓፍቱ ሰው ተኮር በሆነ የብዝሃ ኢኮኖሚ ጉዞ ኢትዮጵያን በአጠረ ጊዜ ውስጥ ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር አግዘዋል " ያለው የጠ/ሚ ጽ/ቤት " በእነዚህ መጻሕፍት የተነሱ እሳቤዎች ከንድፈ ሃሳብ ባሻገር በተግባር የተገለጡና ለትውልዱ ብሩህ ተስፋን ያጎናጸፉ ናቸው " ብሏል። መጻሕፍቱ አሁን ላይ ከሕትመት ባሻገር በድምጽ ተተርጉመው በመደመር መተግበሪያ ቀርበዋል ሲል አሳውቋል። መተግበሪያውን የአኦኤስ እንዲሁም የአድሮይድ ተጠቃሚዎች አውርደው መጠቀም ይችላሉ ተብሏል። ለአይኦኤስ ተጠቃሚዎች ፡ https://apps.apple.com/ae/app/medemer-books/id6756063015 ለአንድሮይድ ተጠቃሚዎች : For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.medemer.audiobook @tikvahethiopia
显示全部...
😡 925 505😭 59🤔 24🙏 17👏 14🥰 6🕊 5😱 3💔 1
የዩናይትድ ስቴትስ እና የኢትዮጵያ መንግስት ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የሚዘልቅ የጤና ትብብር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። የመግባቢያ ስምምነቱን የአሜሪካ መንግሥት ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ በማቅረብ የሚደግፈው ነው። በዛሬው ዕለት የተከናወነውን የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙት የገንዘብ ሚኒስትር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ፣የጤና ሚኒስትር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና የዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ናቸው። እ.ኤ.አ 2026 እስከ 2030 የሚቆየው የትብብር ማዕቀፍ ስምምነቱ በአጠቃላይ ከአሜሪካ መንግስት የሚለቀቀው የገንዘብ መጠን 1.016 ቢሊየን ዶላር ሲሆን ቀሪው 450 ሚሊየን ዶላር የሚሆነው ከኢትዮጵያ መንግሥት በትብብር ፋይናስ የሚቀርብ ነው። የአሜሪካ መንግሥት ባለፉት ሃያ አመታት 5 ቢሊየን ዶላር የጤና ፋይናንስ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ማድረጉን የገለጹት አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ለሚቀጥሉት አምስት አመታት ደግሞ 1.016 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ የአሜሪካ መንግሥት ለኢትዮጵያ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል። የገንዘብ ድጋፉ በአምስት አመታት ጊዜ ውስጥ በየበጀት አመቱ የሚለቀቅ ይሆናል ተብሏል። በተደረገው የትብብር ማዕቀፍ:- • በኤች አይ ቪ፣ • ቲቢ፣ • ወባ ፣ • የእናቶች እና ህጻናት ጤና፣ • በወረርሽኝ ዝግጅት እና በሌሎችም የጤና ዘርፎች ላይ ትኩረት በማድረግ የሚሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የገለጹ ሲሆን ድጋፉ የኢትዮጵያን የጤና ስርአት የበለጠ ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል። @tikvahethiopia
显示全部...
875🤔 133😡 105👏 31😭 20😢 10😱 7🙏 7🕊 4💔 2