TIKVAH-ETHIOPIA
前往频道在 Telegram
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። መረጃ እና መልዕክት ፦ 0998999899 ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም 0979333111 @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
显示更多2025 年数字统计

1 572 276
订阅者
-46024 小时
-1 9487 天
-3 00530 天
帖子存档
照片不可用在 Telegram 中显示
🌟 የአሜሪካ ደርሶ መልስ ትኬት መግዣን ጨምሮ የተለያዩ አጓጊ ሸልማቶችን ከ11% የገንዘብ ስጦታ ጋር ይሸለሙ!!
የገና እና የጥምቀት በዓልን በማስመልከት ከታህሣሥ 12 ጀምሮ በቴሌብር ሬሚት እና በአጋሮቻችን በኩል የተላከልዎን ገንዘብ በቴሌብር ሲቀበሉ 11% የገንዘብ ስጦታ ያገኛሉ።
በተጨማሪ 200 ዶላር እና ከዚያ በላይ ሲቀበሉ
✈️ 💰 300ሺህ ብር አሜሪካ ደርሶ መልስ የበረራ ትኬት
💻 ላፕቶፕ ኮምፒተሮች
📲 የስልክ ቀፎዎች
🐏🛍 የበዓል በግ እና አስቤዛ
🌐 የብሮድባንድ ኢንተርኔት የ6 ወር ክፍያዎች
📶 ከ25,000 በላይ 1GB የሞባይል ዳታ ስጦታዎችን ለሚያሸልመው የዕድል ጨዋታ ብቁ ይሆናሉ!
ዕጣዎቹ ቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/telebirr_SuperApp ላይ ክፍት ናቸው!
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
❤ 187😭 12🤔 9😡 8🕊 5😱 3😢 1
照片不可用在 Telegram 中显示
#CBE #EthiopianAirlines
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ27 ቢሊየን ብር በላይ የብድር ስምምነት ተፈራረሙ።
አየር መንገዱ ከዚህ በፊት ለሰራተኞቹ 1 ሺህ 200 ቤቶችን ገንብቶ ማስረከቡን አስታውሶ አሁን ላይ 5 ሺህ ቤቶችን በመገንባት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።
ይህ የቤት ግንባታ ለማሳካት በዛሬው ዕለት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ27 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የብድር ስምምነት መፈረሙን አሳውቋል።
@tikvahethiopia
❤ 1 211😡 179👏 149🤔 94😱 47🙏 45😭 36🕊 28🥰 24😢 20💔 15
照片不可用在 Telegram 中显示
#CBE #EthiopianAirlines
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ27 ቢሊየን ብር በላይ የብድር ስምምነት ተፈራረሙ።
አየር መንገዱ ከዚህ በፊት ለሰራተኞቹ 1 ሺህ 200 ቤቶችን ገንብቶ ማስረከቡን ገልጾ አሁን ላይ 5 ሺህ ቤቶችን በመገንባት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።
ይህ የቤት ግንባታ ለማሳካት በዛሬው ዕለት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ27 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የብድር ስምምነት መፈረሙን አሳውቋል።
@tikvahethiopia
❤ 1
የገቢዎች ሚኒስቴር በልብስ ስፌት አገልግሎት ላይ የሚጣለውን የኤክሳይዝ ታክስ አከፋፈል በተመለከተ አዲስ ማብራሪያ ሰጥቷል።
ሚኒስቴሩ፣ የልብስ ስፌት ፋብሪካዎች " የአገልግሎት ሰጪ ነን " በሚል ምክንያት ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ መሆን እንደማይችሉ ባወጣው ሰርኩላር ደብዳቤ ላይ አመልክቷል።
ከዚህ ቀደም የገንዘብ ሚኒስቴር በሰጠው ማብራሪያ፣ አምራቾች ከደንበኞች የሚቀርብላቸውን ጨርቅ የመስፋት አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት የኤክሳይዝ ታክስ እንዲከፍሉ አይጠየቁም ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ ይህ አሰራር የታክስ ገቢ እንዲታጣ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።
በመሆኑም በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 (እንደተሻሻለው) መሠረት፣ በHS Code 50.07 እስከ 63.04 የተመደቡ የጨርቃ ጨርቅና የተሰፉ ልብሶች ምርቶች የኤክሳይዝ ታክስ የሚጣልባቸው በመሆኑ፣ የልብስ ስፌት ፋብሪካዎች ግዴታቸውን እንዲወጡ መታዘዙን ካፒታል ጋዜጣ ዘገቧል።
የገንዘብ ሚኒስቴር በቁጥር ታ/ክ/4/5/952 በቀን 01/04/2018 በሰጠው አዲስ ማብራሪያ መሠረት፦ የኢንቨስትመንትና የንግድ ፈቃድ ያላቸው የልብስ ስፌት ፋብሪካዎች ለኤክሳይዝ ታክስ ዓላማ የመመዝገብ ግዴታ አለባቸው።
በተጨማሪም " የልብስ ስፌት አገልግሎት ሰጪ ነን" በሚል ሰበብ ከታክስ ነፃ መሆን አይችሉም የተባለ ሲሆን አምራች ፋብሪካዎችና የሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ይህንን አውቀው ተገቢውን ክትትል እንዲያደርጉ የገንዘብ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
በታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በገቢዎች ሚኒስትር የተላለፈዉ ይህ ውሳኔ በዘርፉ ሊሰበሰብ የሚገባውን የታክስ ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብና አሰራሩን ግልፅ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የካፒታል ጋዜጣ ነው።
@tikvahethiopia
❤ 646😡 334😭 39🕊 31🤔 16🙏 13😢 6💔 2
照片不可用在 Telegram 中显示
አቢሲንያ ባንክ
#የሁሉም_ምርጫ
እናንተን ለመሸለም ምክንያት ይበቃናል!
በፊት ገፅታዎ እና በጣት አሻራዎ የደንበኝነት ምዝገባ ሲያካሄዱ በየ15 ቀኑ የተለያዩ ሽልማቶች እና የመኪና ሽልማት የሚያስገኝ ዕድል ያገኛሉ።
ከአቢሲንያ ባንክ ጋር ይጀምሩ - ያድሱ - ይደጉ!
#StartRenewGrow #BOARewards #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
❤ 150😭 19😡 13🙏 12😢 10🕊 8
" ወረዳው የሚያቀርበው ሪፖርት እና መሬት ላይ ያለው ልዩነት አለው "-ትግራይ ክልል ጤና ቢሮ
በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን አስገደ ወረዳ ከእንዳስላሰ-ሽረ ከተማ አቅራቢያ የምትገኘው #ሕፃፅ የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ 16 ሺህ የሚሆኑ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የሆነ የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው መዘገባችን ይታወቃል።
በአካባቢው ስላጋጠመው የምግብ እጥረት ፣የጉዳቱ መጠን እና ስፋት ዙሪያ የተብራራ መረጃ እስካሁን ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የተባለ ነገር የለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከክልሉ ጤና ቢሮ ባገኘው መረጃ ጉዳዩን የሚያጣራ ቡድን ከሚመለከታቸው አካላት በማወጣጣት ዛሬ ከሰአት በኋላ ወደ አካባቢው መንቀሳቀሱን አረጋግጧል።
ቢሮው " የወረዳው ጤና ጽ/ቤት የምግብ እጥረት እይታ(Screening) አድርገው የነበረ ቢሆንም ወረዳው የሚያቀርበው ሪፖርት እና መሬት ላይ ያለው ልዩነት አለው " ነው ያለው።
የችግሩ ስፋት ምን ያህል ነው ? የሚለውን ለማረጋገጥ ዛሬ ከሰአት 10 ሰአት ወደ ቦታው አንድ ቡድን መንቀሳቀሱን ቢሮው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጸ ሲሆን የተረጋገጠ መረጃ እንደደረሰው የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጿል።
የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ምን አለ ?
" በማህበራዊ ሚዲያው ላይም እንደሚተላለፈው የወረዳው ጤና ጽ/ቤት የምግብ እጥረት እይታ (Screening) አድርገው ነበር።
ወረዳው የሚያቀርበው ሪፖርት እና መሬት ላይ ያለው ልዩነት አለው።
ስለዚህ እንደ ጤና ቢሮ ከሚመለከታቸው አካላት የተውጣጣ የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት ቲም (Emergency Preparedness Team) ተዋቅሮ ዛሬ ከሰአት ወደ ቦታው ተንቀሳቅሷል።
ያለው ሁኔታ ምንድነው የሚሉ የመረጃ ማጥራት ስራዎች ይደረጋሉ ፣ጤና ቢሮው የተረጋገጠ (Actual) የሆነ መረጃዎችን ለመግኘት እየጣረ ነው።
በማህበራዊ ሚዲያው ግልጽ የሆነ መቀንጨር እና የምግብ እጥረት ያጋጠማቸውን፣ በእድሜ ጠና ያሉ ሰዎችን ፎቶ አየተናል እንደ ጤና ቢሮ እንደዚህ አይነት ችግር ላጋጠማቸው ዜጎች የሚሰጥ 300 ካርቶን ሃይል ሰጪ ብስኩት (High energy Biscuits ዛሬ ጠዋት ወደ ቦታው ልከን ደርሷል።
ነገር ግን የችግሩ መጠን ምን ያህል ነው በሚለው ዙሪያ ወደ ቦታው የተንቀሳቀሰው ቡድን መረጃውን እንደላከ የምናሳውቅ ይሆናል " ብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በክልሉ ስላጋጠመው የምግብ እጥረት እየተከታተለ መረጃ የሚያቀርብ ይሆናል።
@tikvahethiopia
❤ 1 067😭 573💔 122🙏 53😡 36🕊 32😢 30🤔 18🥰 14👏 2😱 1
በተለይ በተለይ ምሽት እና ወደ ንጋት አካባቢ በሚደረጉ ጉዞዎች ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ አይለያችሁ።
" የምትመለከቱት ፎቶ ለሊት 10:45 ሰአት አካባቢ ከአርባምንጭ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዝ ዘመን ባስ እና ከአዲስ አበባ ወደ አርባምንጭ የሚጓዝ አይሱዙ ምእራብ አባያ አካባቢ ተጋጭተው የተፈጠረ አደጋ ነው።
በአደጋውም የአይሱዙ ሹፌር ሲሞት የባሱ ሹፌር እና ሌላ ሁለት ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በሰአቱ እኔም ባስ ውስጥ ተሳፋሪ ነበርኩኝ።
ሹፌሮች ሲያስሽከረክሩ ጥንቃቄ ያደርጉ። " - ቢንያም ዘለቀ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል
#TilvahEthiopiaFamily
@tikvahethiopia
😭 852❤ 472😢 67🙏 40🕊 29💔 28😱 15🥰 11
" የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ የከተማው ፀጥታ እንዲረጋጋ አድርገዋል " - ኢሰመኮ
በጋምቤላ ክልል ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የመከላከያ እና የፌደራል ፀጥታ አካላት መሰማራታቸውን ኢሰመኮ ለቢቢሲ ገልጿል።
ኢሰመኮ ለቢቢሲ በሰጠው ቃል "አሁን በከተማው እና በዙሪያው በቂ የፀጥታ አካላት አሉ። የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ የከተማው ፀጥታ እንዲረጋጋ አድርገዋል " ብሏል።
መንግሥታዊ፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ እንዲሁም የንግድ ተቋማት እንቅስቃሴ እንደጀመሩም አመልክቷል።
በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ አንድ የባንክ ሥራ አስኪያጅ በመቀጠልም የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር ኡመድ ኡጁሉ ተገድለዋል።
የፖሊስ አዛዡ የተገደሉት የባንክ ሥራ አስኪያጁ ከተገደሉ ከቀናት በኋላ ነው።
በሰሞነኛው ግጭት በርካታ ንጹሃን ሰዎች በወጡበት ቀርተዋል።
ፎቶ ፦ ፋይል
@tikvahethiopia
❤ 795😭 193👏 55😡 54🕊 50🙏 35💔 21🤔 20🥰 12😢 3
" የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ የከተማው ፀጥታ እንዲረጋጋ አድርገዋል " - ኢሰመኮ
በጋምቤላ ክልል ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የመከላከያ እና የፌደራል ፀጥታ አካላት መሰማራታቸውን ኢሰመኮ ለቢቢሲ ገልጿል።
ኢሰመኮ ለቢቢሲ በሰጠው ቃል "አሁን በከተማው እና በዙሪያው በቂ የፀጥታ አካላት አሉ። የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ የከተማው ፀጥታ እንዲረጋጋ አድርገዋል " ብሏል።
መንግሥታዊ፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ እንዲሁም የንግድ ተቋማት እንቅስቃሴ እንደጀመሩም አመልክቷል።
በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ አንድ የባንክ ሥራ አስኪያጅ በመቀጠልም የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር ኡመድ ኡጁሉ ተገድለዋል።
የፖሊስ አዛዡ የተገደሉት የባንክ ሥራ አስኪያጁ ከተገደሉ ከቀናት በኋላ ነው።
በሰሞነኛው ግጭት በርካታ ንጹሃን ሰዎች በወጡበት ቀርተዋል።
ፎቶ ፦ ፋይል
@tikvahethiopia
❤ 1
ህጻን ሀበን ካሱ ተገድሎ ተገኘ።
የ7 ዓመቱ ህፃን ሀበን ካሱ ከአዲስ አበባ፣ ሰሚት 30 ሜትር አካባቢ እሁድ ታህሳስ 5/2018 ዓም ከቤት እንደወጣ አለመመለሱን ተከትሎ ቤተሰቦቹ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የአፋልጉኝ ተማጽኖአቸውን ሲያቀርቡ እንደነበር ይታወቃል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጭንቀት ላይ የሚገኙ ቤተሰቦቹን በማናገር ሰኞ ታህሳስ ስድስት ህጻን ሀበንን ለማፋለግ የአፋልጉኝ ማስታወቂያ አውጥቶ ነበር።
ከቤት እንደወጣ ሳይመለስ የቀረው ህጻን ሀበን ካሱ ተገድሎ መገኘቱን ቲክቫህ ለቤተሰቦቹ ቅርብ ከሆነ ምንጭ አረጋግጧል።
ፖሊስ የህጻኑን መገደል ዛሬ ጠዋት ለቤተሰቦቹ ያረዳ ሲሆን ቤተሰቦቹም ለአስክሬን ምርመራ በሆስፒታል ይገኝ የነበረውን አስክሬን በመረከብ ስርአተ ቀብሩን ፈጽመዋል።
ስርአተ ቀብሩ በዛሬው ዕለት 8:30 ሰሚት በሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
ህጻን ሀበንን የገደለው ተጠርጣሪ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ የተገለጸ ሲሆን ህጻኑን በመግደል የቀበረበትን ስፍራ በመምራት አሳይቷል።
የህጻን ሀበን አስክሬን ተገድሎ የተገኘው በየካ ጫካ ውስጥ መሆኑን ተነግሯል።
ተጠርጣሪው ህጻኑን ቀደም ብሎ ገድሎት ለቤተሰቦቹ በመደወል በገንዘብ ሲደራደር ነበር ተብሏል።
ፖሊስ ወንጀሉን የፈጸመውን ግለሰብ በመያዝ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TilvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
😭 4 358❤ 728💔 353😡 142😢 87🕊 63😱 34🙏 31🥰 10👏 8🤔 6
ተራዝሟል !
የ2018 አጋማሽ ዓመት የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም የመውጫ ፈተና የምዝገባ ጊዜ ተራዝሟል።
የምዝገባ ጊዜው ከተቋማት በቀረበ ጥያቄ እና ሌሎች ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት እስከ አርብ ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ስዓት ድረስ የተራዘመ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
ሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞች እንዲሁም የግል ተፈታኞች ምዝገባችሁን በተራዘመው ጊዜ እንድታጠናቅቁ ተብሏል።
Via @tikvahuniversity
❤ 296👏 36🙏 32😭 11😡 9🕊 4
