TIKVAH-ETHIOPIA
前往频道在 Telegram
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። መረጃ እና መልዕክት ፦ 0998999899 ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም 0979333111 @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
显示更多2025 年数字统计

1 572 085
订阅者
-51224 小时
-2 3697 天
-3 44030 天
帖子存档
#ነዳጅ
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋን ይፋ ማድረጉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር የዓለም የነዳጅ ዋጋን መነሻ በማድረግ ከታህሳስ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀነ-6፡00 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋን ነው ይፋ ያደረገው።
የአውሮፕላን፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ አና የከባድ ጥቁር ናፍጣ መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ የሚቀጥል ሲሆን ፤ የቤንዚን፣ የነጭ ናፍጣ እና የኬሮሲን ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ግን ጭማሪ ተደርጎበታል።
በእዚህም መሰረት ፦
- ቤንዚን 129.12 ብር በሊትር
- ነጭ ናፍጣ 129.12 ብር በሊትር
- ኬሮሲን 129.12 ብር በሊትር እንዲሸጡ የተወሰነ መሆኑ ታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲሱ የነዳጅ ችርቻሮ ዋጋ ማሻሻያ የደረሳቸው መሆኑን ከነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ደስታው መኳንንት አረጋግጧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
የቤንዚን እና የነጭ ናፍጣ ዋጋ 129 ብር ከ12 ሳንቲም ገብቷል።
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ይፋ ያደረገበትን ደብዳቤ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመልክቷል።
በዚህም መሰረት ፦
➡️ አንድ ሊትር ቤንዚን 129 ብር ከ12 ሳንቲም
➡️ አንድ ሊትር ነጭ ናፍጣ 129 ብር ከ12 ሳንቲም
➡️ አንድ ሊትር ኬሮሲን 129 ብር ከ12 ሳንቲም ገብቷል።
የሌሎች የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
😭 632❤ 364😡 100🙏 35👏 20🕊 17😢 13🥰 12😱 10🤔 9💔 5
" የነዳጅ ዋጋ ይጨምራል " በሚል ልክ እንደ ሌላው ጊዜ ማደያዎች ያላቸውን የነዳጅ ክምችት በመያዛቸው አሽከርካሪዎች እንግልት ላይ ናቸው።
በሀገራችን መዲያ አዲስ አበባ ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ናፍጣ እና ቤንዚን ማግኘት ከባድ ሆኗል።
ስራ ያላቸው ሰዎች ፣ የእለት እንጀራቸውን በተሽከርካሪ ተንቀሳቅሰው በመስራት ይዘው የሚገቡ ዜጎች፣ ቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ነዳጅ ለመቅዳት ተሰልፈው ይውላሉ።
አንዳንድ ማደያዎች " የለም " ቢሉም ከጀርባ ግን በጄሪካን ይቀዳሉ።
በክልል ያለው ነገር ደግሞ እጅግ የከፋ ነው። ለቀናት ተሰልፎ ነዳጅ ማግኘት የማይታሰብ ነው።
#TikvahEthiopiaFamily
@tikvahethiopia
❤ 430😭 194🙏 37💔 15😡 13🥰 10🕊 9🤔 8
የቤንዚን እና የነጭ ናፍጣ ዋጋ 129 ብር ከ12 ሳንቲም ገብቷል።
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ይፋ ያደረገበትን ደብዳቤ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመልክቷል።
በዚህም መሰረት ፦
➡️ አንድ ሊትር ቤንዚን 129 ብር ከ12 ሳንቲም
➡️ አንድ ሊትር ነጭ ናፍጣ 129 ብር ከ12 ሳንቲም
➡️ አንድ ሊትር ኬሮሲን 129 ብር ከ12 ሳንቲም ገብቷል።
የሌሎች የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
13 ዓመት ተፈርዶባቸዋል !
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር የቀድሞ ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በተከሰሱበት ከባድ የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው በ13 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጥተዋል።
የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ምን አለ ?
በኮሚሽኑ የተረጂዎችን ቁጥር በማጋነን የተለያዩ የእርዳታ ዓይነቶችን ከመጋዘን ወጪ በማድረግ ለተረጂዎች ሳይደርስ ተሽጦ ለግል ጥቅም መዋሉን ገልጿል።
በዚህም በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረትን ምንጩን ደብቆ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ክስ በነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም ተመስርቶባቸው እንደነበር አመልክቷል።
የቀረበው የክስ ዝርዝር ምን ይዟል ?
ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ዴቭሎፕመንት አሶሴሸን ዳይሬክተር የማነ ወ/ማሪያምና ከሌሎች ሰራተኞች ጋር ያልተገባ የጥቅም ግንኙነት በመፍጠር በሺዎች በሚቆጠሩ ተረጂዎች ስም እንዲሁም የተረጂዎችን ቁጥር በማጋነን ለበርካታ ጊዜ የምግብ ቁሳቁሶች ከኮሚሽኑ መጋዘን በማውጣት ለዱቄት ፋብሪካዎችና ለሌሎች ግለሰቦች #በመሸጥ ሕገወጥ ጥቅም ሲያገኙ ነበር።
በአማራ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ክልል (የቀድሞ) ክልሎች ውስጥ በሚገኙ የግብረሰናይ ድርጅቱ (ኤልሻዳይ) ማዕከላት ለተረጂዎች ሳያደርስ በመሸጥ ለግል ጥቅም ማዋል፣ ብድርና ድጋፍ በሚል ሰበብ በሕገ ወጥ መንገድ ከኮሚሽኑ #በ100_ሚሊየን የሚገመት ለእርዳታ ድርጅቱ በገንዘብ መልክ ተሰጥቷል።
ለዚህም በአቶ ምትኩ ካሳ ቤተሰቦች ስም ከኤልሻዳይ ድርጅት በተለያዩ ጊዜ ክፍያ ተፍጽሟል።
በተለይም ፦
- ከ601 ሺህ ኩንታል በላይ ስንዴ፣
- ከ41 ሺህ ኩንታል በላይ በቆሎ፣
- ከ78 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት፣
- ከ3 ሺህ 999 ኩንታል በላይ ሩዝ ከተራድኦ ድርጅቱና ከኮሚሽኑ ጋር በመመሳጠር እርዳታውን አዳማ ለሚገኝ የዱቄት ፋብሪካ ተሽጧል።
በሌላ ክስ ደግሞ ከ472 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ በድጋፍ መልክ በ1ኛ ተከሳሽ አቶ ምትኩ ካሳ ፈቃጅነት በ2ኛ ተከሳሽ አማካኝነት ክፍያ እንደተፈጸመና በ3ኛ ተከሳሽ ወጪ አድራጊነት ለግል ጥቅም በመዋሉ በመንግስት ከፍተኛ ኪሳራ ደርሷል።
በአቶ ምትኩ ልጆችና ባለቤታቸው ስም ተገዝተው የተገኙ ተሽከርካሪዎችና መኖሪያ ቤቶች ተገኝተዋል።
ተከሳሾቹ አቶ ምትኩ ካሳ፣ ባለቤታቸው ወ/ሮ ሶፊያ ጀማል፣ ልጃቸው ወ/ሮ ሚልካ ምትኩ የወንጀል ድርጊት መፈፀማቸውን ተከትሎ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፏል፡፡
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ጉዳዮች ችሎት የዐቃቤ ሕግን የቅጣት ማክበጃና የተከሳሾችን የቅጣት ማቅለያ ካደመጠ በኋላ አቶ ምትኩ ካሳ በ13 ዓመት ጽኑ እስራትና በ50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል፡፡
በተጨማሪም በአቶ ምትኩ ካሳ ባለቤት ወ/ሮ ሶፊያ ጀማል ላይ የ8 ዓመት ከ4 ወር እስራትና 3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።
ልጃቸው ወ/ሮ ሚልካ ምትኩ 5 ዓመት እስራትና 3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል።
#ኤፍኤምሲ
@tikvahethiopia
❤ 1 297👏 275😡 61😭 39😢 37🤔 33🙏 29😱 24💔 23🕊 11🥰 5
" ጊፋታ " በሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት ተመዘገበ።
ጊፋታ የወላይታ ህዝብ የአዲስ ዓመት ፌስቲቫል በሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት በተባበሩት መንግስታት ትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) መመዝገቡ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን እንዳስታወቀው "ጊፋታ" በህንድ፣ በኒው ዴሊ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው 2ዐኛው የኢንታንጀብል ባህላዊ ቅርስ ጥበቃ የመንግስታት ኮሚቴ ስብሰባ ነው በሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት መመዝገቡ የተገለጸው።
ጊፋታ ዩኔስኮ ቅርስን በሰው ልጆች ወካይ ኢንታንጀብል ቅርስነት ለመመዝገብ ያስቀመጣቸውን መመዘኛዎች አሟልቶ ተገኝቷል ተብሏል።
- በዓሉ እድሜ፣ ፆታ፣ ሀይማኖትና ማህበራዊ ደረጃን ሳይለይ የሚያሳትፍ መሆኑ፣
- የቅርሱ ተስተላልፎ ጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኝ
፤ በትምህርት ቤቶችና በሚዲያዎች ለትውልድ በመሸጋገር ላይ የሚገኝ መሆኑ፤
- በዓሉ ሰላምን፣ አንድነትን እና አብሮነትን የሚያበረታታ መሆኑ፣
- ለዘላቂ ልማት፣ የምግብ ዋስትናን ከፍ በማድረግና አካባቢን ከመጠበቅ አንፃር ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያደርግ መሆኑ፤
- ኖሚኔሽን ፋይሉ በቅርሱ ባለቤቶች ነፃና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ተሳትፎ የተከናወነ መሆኑ እና
- ቅርሱ በሀገሪቱ ብሔራዊ ምዝገባ ውስጥ የተካተተ መሆኑ የሚሉት ይገኙበታል፡፡
Via @tikvahethmagazine
❤ 669👏 106🙏 25😭 18🥰 14😡 11😢 4🤔 1
#HawassaUniversity
" ከሥራ ሊበትኑን ነው። ስራው ሲቋረጥ የካሳ ይታሰብልን። ጉልበታችንን ጨርሰናል። ጡረታ የምናገኝበት እድሜ እንጂ ደመወዝ ጨምሩልኝ፤ ሥራ አስተካክሉልን ብለን የምንጠይቅበት አልነበረም " - ሠራተኞች
➡️ " እየታገልን ያለነው በሠራተኛ ማህበር እንዲታቀፉ ነው፤ ይሄን ለማድረግ ደግሞ መጀመሪያ ህጉ መሻሻል አለበት " - ኢሰማኮ
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በምገባና መሰል ስራዎች ተሰማርተው እስከ 20 ዓመት ድረስ የሰሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች " ያለምንም ካሳ ከሥራ ልንስናበት ነው " ሲሉ በማማረር መፍትሄ እንዲሰጣቸው ከወዲሁ ጠየቁ።
ሠራተኞቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?
አንድ ቅሬታ አቅራቢ ፦" 'ታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ/ም ስራ ትለቃላችሁ' አሉን። አንድ ወር ብቻ ናት የቀረችን። እስከ 20 አመት የሰራ ሠራተኛ አለ፤ በአጠቃላይ ወደ 800 ሠራተኛ ነው ያለው። ይህ ሁሉ ከሥራ ተባሮ የት እንደሚገባ አናውቅም። ከሥራ ሊበትኑን ነው። ደመወዛችንም 1,100 ብር ነው፤ ይሄም ሊቀር ነው።
ዩኒቨርሲቲውን ስንጠይቅ 'የማውቀው የለም' ይላል፤ ጭራሽ እያስፈራሩን ነው። ይሄ ሁሉ አመት አገልግለን መፍትሄ አጥተናል። 'መንግስት የት ያውቃችኋል' እስማለትም ደርሰዋል። ምን ሰርተን ልንበላ ነው ? ብለን ስንጠይቅ 'እኛ የምናውቀው ነገር የለም' ነው የሚሉን " ብለዋል።
ሌላኛዋ ስሞታ ያቀረቡ እናት ፦ " 14 ዓመት ሙሉ በእሳት ተንገብግበን ከዚህ በፊትም 'ሥራ አቁሙ' ተብለን ወጥተን ነበር፤ በኋላ ደግሞ 'ተመለሱ' አሉን፤ እንደገና አሁን ደግሞ 'የምትሰሩት እስከ ታህሳስ 30/2018 ነው' ተባልን።
እኔ የወጥ ቤት ሠራተኛ ነኝ። 1,500 ብር ነው የወር ደመወዜ። የደመወዝ ጭማሪ አልተደረገልንም። የምንሄድበት ቦታ አጥተናል። ስራው ሲቋረጥ የካሳ ይታሰብልን። ጉልበታችንን ጨርሰናል" በማለት ተናግረዋል።
ሌላኛዋ ሠራተኛ ፦ " ተቆጥሮ የማያልቅ ጉዳት ነው የደረሰብን። ከ2001 ዓ/ም ጀምረን የገባነው በማህበር ተጀራጅተን ነው። እኔ ወጥ ቤት ነው የምሰራው። ሥራው የምንተዳደርበት፤ ልጆች የምናስተምርበት፤ የቤት ኪራይ የምንከፍልበት፣ የእለት ጉርስ የምናደርገው ነው፤ ግን ሰው መሆናችን ተረስቷል። የተለዬ ሰውነት ኖሮን ነው? ለኛ የተለየ ገበያ አለን?
ከ2001 ዓ/ም ጀምሬ 17 ዓመት ነው የሰራሁት። ጡረታ የምናገኝበት እድሜ እንጂ ደመወዝ ጨምሩልኝ፤ ሥራ አስተካክሉልን ብለን የምንጠይቅበት አልነበረም። 'ነይ ከዚህ ተነሺ' ማለት ለአዕምሮ ራሱ አይከብድም? መንግስት ካለ ይሄ ታሳቢ ይደረግልን። ወዴት አቤት እንበል? " ሲሉ በምሬትና በሀዘን ስሜት ቅሬታ አሰምተዋል።
ለቅሬታው ምላሽ ለመጠየቅ ወደ ዩኒቨርሲቲው ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም ስልክ ያልተነሳና የሚመለከታቸው የከተማዋን አካላት፣ የፌደራሉን ሲቪል ሰርቪስ ባለስልጣን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ያልተሳካ ሲሆን፣ የሠራተኞቹ እጣ ፋንታቸው ምንድን ነው? ስንል ግን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ)ን ጠይቀናል።
የኢሰማኮ የውጭና ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አቶ አያሌው አህመድ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን መለሱ?
" ሠራተኞቹ የሚተዳደሩት በሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስለሆነ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለው የሲቪል ሰርቫንት ህግ መሰረት ነው የሚዳኙት። በኛ ስር ያሉት የግል ድርጅቶችን በተመለከተ የህብረት ስምምነት የአሰሪና ሠራተኛ ህግ መሰረት ሠራተኞቹ የመከፈል መብት አላቸው።
ይሄኛውን (የዩኒቨርሲቲውን) በተመለከተ ግን ሠራተኞች ከስራ ሲለቁ ምን መሆን አለበት የሚለው በሲቪል ሰርቫንት ደንብ መሰረት ነው መታየት ያለበት እንጂ በግል ተቋማት በሚወጡ ደንቦች ለጊዜው ሽፋን የላቸውም።
በኛ አሰሪና ሠራተኛ ህግ ሠራተኛ ከሥራ በሚለቅበት ወቅት እስከ አምስት አመት ሰርቶ ሠራተኛው በራሱ ፈቃድም ሆነ በአሰሪው ተነሳሽነት ሥራ ከለቀቀ የአገልግሎት ክፍያ ይከፈለዋል። ይሄ በአሰሪና ሠራተኛ ህጉ የሚሸፈኑትን ሠራተኞች ነው። ሠራተኞቹ በማህበር እስካልተደራጁ ድረስ ይሄኛው ህግ ያስተዳድራቸዋል ለማለት አስቸጋሪ ነው።
የተደራጁት በሠራተኛ ማኀበር ካልሆነ ወደኛ ሊመጡ አይችሉም። አሁን ተነሳስተው እንዳይደራጁ ደግሞ ህጉ አልፈቀደላቸውም፤ ህጉ ስላልፈቀ አሁን በሙያ ማህበር እንጂ በሠራተኛ ማህበር አይደለም የታቀፉት። እኛ እየታገልን ያለነው በሠራተኛ ማህበር እንዲታቀፉ ነው፤ ይሄን ለማድረግ ደግሞ መጀመሪያ ህጉ መሻሻል አለበት " ሲሉም አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#GSTS
የትግራይ ዓለም የሙሁራን ማህበር /Global Society of Tigrai Scholars - GSTS/ ባወጣው ፤ ህዳር 22/2018 ዓ.ም በመቐለ በሚገኘው ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ የማህተምና የባንኪ ሂሳብ ደብተር ቅምያ እንደተፈጸመበት ገለጸ።
ቅምያው በህወሓት የማእከላዊ ኮሚቴ አባልና የትግራይ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ኪሮስ ጉዑሽ ( ዶ/ር) ነው የተፈፀመው ብሏል።
" እንዲህ ዓይነት የሽፍትነት ተግባር ሁሉም ባለድርሻ አካላትና የትግራይ ወዳጆች ሊያውቁትና ሊያወግዙትና ይገባል " ሲል ጥሪ አቅርቧል።
ዋና ፅህፈት ቤቱ በውጭ አገር የሆነና በዓለም አቀፍ ደረጃና በአፍሪካ ቀንድ አገራት የትግራይ ሙሁራን ወክሎ እንዲንቀሳቀስ ምዝገባና እውቅና ያለው ለትርፍ ያልተቋቋመው ማህበሩ በትግራይ የተፈጠረው የፓለቲካ ቀውስ ሰለባ ከሆነ ቆይቷል።
ለዚሁ ማሳያ ባለፈው ሳምንት በምርጫ ቦርድ ከፓለቲካ እንቅስቃሴ የተሰረዘው ህወሓትን የሚደገፍ በGSTS ስም የወጣው መግለጫ ማህበሩ እንዳማያውቀውና እንደማይወክለው በመግለጫው ይፋ አድርጓል።
የፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት አድርጎ ጥር 2015 ዓ.ም የተቋቋመው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር መስራች አባል የሆነው GSTS በአስተዳደሩ ካቢኔ የኃላፊነት ቦታዎች አግኝቷል።
የቀድሞው ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ምክትል የነበሩት ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ( ሌ/ጀ) ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ከላሊ ኣድሃና (ዶ/ር) እስከ አሁን በኃላፊነት የሚገኙት የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አፅብሃ ገ/ሄር (ዶ/ር) በማህበሩ ከተወከሉ መካከል ናቸው።
GSTS በቅርንጫፍ ማህበሩ የተፈፀመው ቅምያና በአመራሩ ለሚደረሰው ጉዳት በህግ ለመከታተል መወሰኑን አሳውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
@tikvahethiopia
照片不可用在 Telegram 中显示
📚 Want to Learn Afaan Oromoo?
አፋን ኦሮሞን መማር ይፈልጋሉ?
🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽
📝 Register Now: https://ethiolanguage.com/customers/register/
🌞 Summer Registration is Open!
Join us in-person or online — enjoy 24/7 access, live interactive classes, and expert teachers.
📩 Don’t miss out — spots are filling fast! Contact : Telegram:https://t.me/learnafanoromoo3
Phone : 0995030326
Website: https://www.ethiolanguage.com
照片不可用在 Telegram 中显示
#ዓባይ_ባንክ
4% ጉርሻ ስናበረክትልዎ በደስታ ነው!
ከውጭ አገር የሚላክልዎን ገንዘብ ከዓባይ ባንክ ሲቀበሉ እና ሲመንዝሩ 4 በመቶ ተጨማሪ ጉርሻ ያገኛሉ።
ለክፍት የሥራ መደቦችና ፈጣን የፋይናንስ መረጃዎች ከባንካችን የማኅበራዊ ሚዲያዎች ጋር ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook (http://www.facebook.com/abaybanksharecompany)
Telegram (https://t.me/abaybanksharecompany)
X (https://twitter.com/AbayBank)
LinkedIn (https://www.linkedin.com/company/abaybank)
YouTube (https://www.youtube.com/@abaybank4665)
TikTok (https://www.tiktok.com/@abaybank)
Instagram (https://www.instagram.com/abay_bank/)
ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!
❤ 163🕊 6😱 3🙏 3😢 1😭 1
የገንዘብ ሚኒስቴር በወቅቱ ያልተሰበሰበ የማህበራዊ ልማት ቀረጥን በተመለከተ ውሳኔ አስተላልፏል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ለጉምሩክ ኮሚሽን በ 23/03/18 ዓም በጻፈው ደባዳቤ በወቅቱ ያልተሰበሰበ የማህበራዊ ልማት ቀረጥን በተመለከተ የታክስ ዕዳ ማቃለያ ውሳኔ መስጠቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከደብዳቤው ተመልክቷል።
የማህበራዊ ልማት ቀረጥ ለትምህርት፣ ለስልጠና፣ እና ለጤና ተቋማት መልሶ ማቋቋሚያ እና ግንባታ እንዲሁም ለሌሎችም የማህበራዊ አገልግሎቶች ማስፋፊያ የሚውል የፋይናንስ ምንጭ እንዲያስገኝ በሚል ተግባራዊ የተደረገው ከሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ነው።
ነገር ግን ደንቡ ተግባራዊ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ መሰብሰብ የነበረበት የማህበራዊ ልማት ቀረጥ በወቅቱ ባለመሰብሰቡ ኮሚሽኑ(የጉምሩክ) ውዝፍ የታክስ ዕዳ እንዲከፈለው ዕቃዎችን ወደ አገር ያስገቡ አካላትን እየጠየቀ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ተለዋጭ ውሳኔ እስኪሰጥ ዕዳውን የመሰብሰብ ሂደት ለጊዜው እንዲዘገይ በ17/4/2016 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ማሳወቁን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውሷል።
ገንዘብ ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ ጉዳዩ ውሳኔ ሳያገኝ ተንጠልጥሎ መቆየቱ በኮሚሽኑ እና በግብር ከፋዮች መካከል የታክስ አስተዳደር ችግር እየሆነ መማጣቱን የጠቀሰ ሲሆን "ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ በማየት የታክስ ዕዳ ማቃለያ ውሳኔ መስጠቱ ተገቢ መሆኑ ታምኖበታል" ብሏል።
በውሳኔው መሰረት ፍሬ ግብሩ መከፈሉ እንደተጠበቀ ሆኖ:-
• በፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 648/2001 (እንደተሻሻለ) አንቀፅ 13(3) መሠረት በፍሬ ግብሩ ላይ የተጠየቀው ወለድ ቀሪ እንዲሆን፣
• መቀጫው እንዲነሳ፣
• እንዲሁም ፍሬ ግብሩን በአንድ ጊዜ መክፈል የማይችሉ ግብር ከፋዮች የክፍያ ስምምነት ውስጥ በመግባት በመመሪያው መሠረት የታክስ ዕዳቸውን በተራዘመ ጊዜ እንዲከፍሉ ተወስኗል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔ የደረሰው መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጉምሩክ ኮሚሽን አረጋግጧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
❤ 1 006😭 66🙏 35🕊 29😡 29🤔 26😢 25💔 12😱 6🥰 5👏 1
#ምርጫ2018
" የአስቻይ፣ የሰላም ሁኔታ እስከ ምርጫው ቀን ድረስ የሚደረግ አሰስመንት ነው - ወ/ሮ ሜላትወርቅ ሀይሉ
➡️ " ችግር መሬት ላይ አለ፤ የቢሮ መዘጋት፤ የአባላት እስር አለ። ምርጫ ቦርድ ይሄንን እየተናገረ ነው! "
ለመካሄድ አስቻይ ሁኔታ አለው ወይ ? የሚል ስጋት አዘል ጥያቄ የገጠመውን ሰባተኛውን ዙር ምርጫ በተመለከተ ማብራሪያ የሰጠው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ “የአስቻይ ሁኔታ” እና “የሰላም ሁኔታ”፣ “እስከ ምርጫው ቀን ድረስ የሚደረግ አሰስመንት” ነው ሲል ተደምጧል።
በሌላ በኩል፣ " ችግር መሬት ላይ አለ፤ የቢሮ መዘጋት፤ የአባላት እስር አለ" ሲል የፓለቲካ ፓርቲዎች ስለሚደረግባቸው ጫና በግልጽ አረጋግጧል።
የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ሀይሉ ምን አሉ ?
“ሙሉ ለሙሉ ምርጫ ጣቢያዎችን ለይተን አልጨረስንም። በሂደት እየሰራነው የምንሄደው ነው” ያሉ ሲሆን “ ወደ 30 ሺሕ የሚጠጉ ምርጫ ጣቢያዎች ያሉበትን ቦታ፣ አደረጃጀቶቻቸውን ለማየት ሞክረናል" ብለዋል።
"ሙሉ ለሙሉ ስንጨርስና በምርጫ ሰሌዳው በግልጽ እንደተቀመጠው ምርጫ የሚካሄድባቸው ዝርዝር የምርጫ ጣቢያዎች ለይተን በምናወጣበት ጊዜ ለህዝብ ግልጽ ሆኖ የሚወጣ ይሆናል ” ሲሉ ገልጸዋል።
የተለያዩ ፓርቲዎች፣ ምሁራን፣ ማህበረሰቡ የዘንድሮውን “ ምርጫ ለማድረግ አስቻይ ሁኔታዎች አሉ ወይ? ” ሲሉ ተደጋጋሚ ስጋት አዘል ጥያቄ እያቀረቡ ናቸው። ለቦርዱ ሰብሳቢም " ለመሆኑ ምርጫ ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታ አለ? ምርጫው ይካሄዳል ? የሚል ጥያቄ ቀርቧል።
የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ፣ “አስቻይ ሁኔታ በአንድ ቀን፣ በሦስት ቀን፤ በአምስት ቀን የሚሰራ አይደለም። በጣም በቀጠይነት የሚሰራ ስራ ነው። ለዚህም መነሻ የሚሆነን ከክልል መንግስታት እና ከጸጥታ አካላት የምናገኛቸው መረጃዎች መሰረቶቻችን ናቸው” ሲሉ መልሰዋል።
“እነኝህን በምርጫ ክልል፣ በምርጫ ጣቢያ አደራጅተን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የምንወያይበት ዳታ እየሰበሰብን በአብዛኛው ተቀብለናል። ነገር ግን የፓለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ፕሮግራም አውጥተን መወያየትን ስለሚጠይቅ መረጃው ተደራጅቶ መጥቶ እርግጠኛ የሆነበትን ቀን በምናምንበት ጊዜ የሚታወቅ ይሆናል፤ ለባለድርሻ አካላትም የሚገለጽ ይሆናል” ነው ያሉት።
“በዚህኛው ወር እናደርጋለን፣ በሚቀጥለው ወር ሁለተኛ ይሄን እናደርጋለን የምንለው አይደለም። እንደተጨባጭ ሁኔታው በቀጣይነት የምናደርገው ነው” ያሉት ወ/ሮ ሜላትወርቅ፣ “የአስቻይ ሁኔታ፣ የሰላም ሁኔታ እስከ ምርጫው ቀን ድረስ የሚደረግ አሰስመንት ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።
“ከሚሰባሰበው መረጃ በኋላ ቡድን ተቋቁሞ የቦርዱ፣ የፓርቲ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች ባሉበት ችግር አለባቸው የሚባሉ ቦታዎችን እየተዘዋወሩ አስቻይ ሁኔታ አለመኖሩ በጋራ ነው አሰስ የሚደረገው” ነው ያሉት።
ምርጫው በሕገ መንግስቱ መሰረት በየአምስት አመቱ የሚደረግ ምርጫ መሆኑን የጠቀሱት ሰብሳቢዋ፣ “በተለያዬ ምክንያት 'ይደረጋል አይደረግም' የሚል ነገር በአየሩ ላይ እየወጣ እናያለን፤ ምርጫ ቦርድ ግን ያለማቋረጥ ምርጫው እንደሚደረግ ነው የሚናገረው፤ በተግባርም እያሳየ ያለው ይሄንኑ ነው። ፓርቲዎችም በሚኖረን ምክክር ያላቸው ጥያቄ 'አስቻይ ሁኔታ አለ?' የሚል እንጅ 'ምርጫ አይደረግም' የሚል ነገር አላቸው ብዬ አላምንም” ብለዋል።
ሰብሳቢዋ፣ “ለምሳሌ እጩዎችን ለመመዝገብ System Administrations ላኩልን ብለን ፓርቲዎችን ስንጠይቅ 64 ፓርቲዎች ልከውልናል፤ ይሄ የሚያሳየን ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን ለመመዝገብ ያላቸውን ዝግጁነት ነው” ባይም ናቸው።
ሕወሓት “ሳልሳተፍ ምርጫ አይደረግም” የሚል መግለጫ ከሳምንት በፊት ማውጣቱን በተመለከተ ቦርዱ እሰራው ያለ ስራ እንዳለ የተጠየቁት ወ/ሮ ሜላትወርቅ፣ “ምርጫ ቦርድ ሕወሓትን መሰረዙ የሚታወቅ ነው። ከዚህ ውጭ ምንም ግንኙነት የለንም። የፕሪቶሪያ ስምምነትን በተመለከተ ለሚነሳው የፓለቲካ ጉዳይ ከሆነ በፓለቲከኞች የሚፈታ ነው፤ ምርጫ ቦርድ የሚመለከተው ጉዳይ አይደለም። ከዚህ የተነሳ በኛ በኩል በየትኛውም አቅጣጫ እየተደረገ ያለ ውይይት የለም” ሲሉ መልሰዋል።
“ኦፌኮ ‘ስልታዊና ስትራቲጂካዊ በሆነ መንገድ በተወሰኑ አዲስ አበባ አካባቢዎች ምርጫ እካፈላለሁ፣ ሁኔታዎችን እየገመገምንና እያየን እንሳተፋለን’” የሚል መግለጫ ማውጣቱን አስታውሰው፣ “እኛም ግምገማ እናደርጋለን፤ በአረንጓዴ (ምርጫ የሚካሄድበት)፣ በቢጫ (ጥንቃቄ የሚጠይቅ)፣ በቀይ (ምርጫ የማይካሄድበት) በሚል። አስቻይ ሁኔታዎችን እየገመገምን እየሰፋ ሲሄድ፣ እነርሱም ከፓርቲዎች ጋር ተካፋዮች ስለሚሆኑ እያዩ ሲሄዱ በተሻለ በስፋት የመሳተፍ እድል ሊኖራቸው እንደሚችሉ ያዩታል” ብለዋል።
በተያያዘ፣ ኢሕአፓ የህዝብ ስብሰባ እንኳ ማድረግ እንዳልቻለ፣ የቁጫ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁዴፓ) አባላቱ እየታሰሩ እንደሆነ፣ ይሁን እንጅ ምርጫ ቦርድ ምላሽ እየሰጠ እንዳልሆነ እየገለጹ መሆኑን ተከትሎ ማብራሪያ እንዲሰጡ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።
እሳቸውም፣ “የቁጫ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በምርጫ ክልሉ የሚደረሱ ማስፈራራት እስር፣ የቢሮ መዘጋት፣ የአባሎች መንገላታት የሚል ጥያቄ ቦርዱ በየቀኑ የሚቀበለው ጥያቄ ነው። ይሄንንም ቦርዱ ሦስትዮሽ የሚባል ኮሚቴ አቋቁሞ (ቁዴፓ፣ ገዢው ፓርቲ፣ ምርጫ ቦርድ ያሉበት) ከሦስት ዓመት በፊት ጀምሮ እየሰራ ያለበት ሁኔታ አለ። አሁንም ሰሞኑን ስብሰባ ስላለ ሂደቱ የቀጠለ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
“ችግሩ መሬት ላይ አለ፤ የቢሮ መዘጋት፤ የአባላት እስር አለ። ምርጫ ቦርድ ይሄንን እየተናገረ ነው። እስሩን ፈጸሙ ለሚባሉ አካላት ደብዳቤ ይጠይቃል፤ የታሰሩ የፓርቲ ፍርድ ቤት ከቀረቡ፣ ካልቀረቡ” ያሉት ሰብሳቢዋ፣ “መልስ የሚሰጥ መዋቅር አለ፤ የማይሰጥ አለ። ፓርቲ አባሌ ታሰረ፣ ቢሮዬ ተዘጋ ብሎ አቅርቦ ምርጫ ቦርድ ዝም ያለበት ሁኔታ ካለ በዳታ መነጋገሩ ግልጽ ያደርገዋል” ነው ያሉት።
ዘንድሮስ ከ7ኛው ዙር ምርጫ ጋር አካባቢያዊ ምርጫ ይደረጋል ወይስ አይደርግም? ለሚለው ጥያቄ ደግሞ፣ “አካባቢያዊ ምርጫ በትክክል ከተካሄደ ረዘም ያለጊዜ ነው። ምርጫ ቦርድ አካባቢያዊ ምርጫ ለማድረግ ከአጠቃላይ ምርጫው በፊት ዝግጅት አድርጎ ነበር፤ በተለይም በ2017 በሁለት ከተሞችና በሁለት ክልሎች ለይቶ ነገር ግን መቀጠል አልተቻም” ሲሉ አስታውሰዋል።
“የአካባቢ ምርጫ በጣም ሰፊ ዝግጅት የሚጠይቅ ሥራ ነው። በየክልሉ ለምሳሌ ባለን አስመንት እንኳ ስንሰራ ወደ 3 ሚሊዮን እጩዎች የሚቀርቡበት ነው። ይህንን ሰፊ ስራ ከአጠቃላይ ምርጫ ጋር ማስኬድ ሥራውን ውስብስብና ከባድ ስለሚያደርገው አጠቃላይ ምርጫ እያደረግን ጎን በጎን አካባቢያዊ ምርጫ አናደርግም። ቦርዱ አካባቢያዊ ምርጫ ለማድረግ አቅዶ ነበር፤ ግን መፈጸም አልቻለም፤ አጠቃላይ ምርጫ ሲያልቅ ወደአካባቢ ምርጫ መገባቱ የግድ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiqFamilyAA
@tikvahethiopia
❤ 784😡 72😭 17😢 11🙏 8🤔 6🕊 4💔 3🥰 1
照片不可用在 Telegram 中显示
💭❓ይህን ያውቃሉ?
ከኢትዮ ቴሌኮም የDStv Stream ፓኬጅ ገዝተው ሁሉንም የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች በስልክዎ ወይም በስማርት ቲቪዎ አልያም በሁለቱም መመልከት ይችላሉ!
⚽️🤩 DStv Stream ሜዳ ፓኬጅ ከ10GB ጋር በ1240 ብር ወርኅዊ ክፍያ ብቻ!
አሁኑኑ ይግዙ፤ የሳምንቱን ምረጥ ጨዋታዎች ዘና ብለው ይመልከቱ!!
እንዴት በስልክ እና በቲቪ መጠቀም እንደምንችል ይመልከቱ: https://youtu.be/5u0r_t7_WGA?si
📍 የአገልግሎት ማዕከሎቻችንን ይጎብኙ!
#DSTV
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
❤ 211🥰 6😭 6😢 4🙏 1
照片不可用在 Telegram 中显示
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ያደረገ ሲሆን የድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም መሆኑን አመልክቷል።
(ሙሉ የጊዜ ሰሌዳው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
❤ 880😭 364😡 121🤔 102🕊 78👏 62💔 26😱 18😢 18🥰 16🙏 4
" ከሀገራችን ባህልና ሥነ-ምግባር ያፈነገጠ አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የታዩ ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ ጀምሬያለሁ " - ፌዴራል ፖሊስ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ " G-Power TikTok Creative Award " በሰተኘ ዝግጅት ላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህልና ሥነ-ምግባር ባፈነገጠ አኳሃን ሰውነታቸውን የገላለጠ አለባበስ ለብሰው በአደባባይና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የታዩ ተጠርጣሪዎችን ከነግብረ-አበሮቻቸው በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ ማጣራት መጀመሩን አስታውቋል።
ሰሞኑን በተካሄደው ዝግጅት ላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህል እና መልካም ሥነ-ምግባር በተቃራኒ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት የታዩ፣ ዝግጅቱን በስፖንሰርነት የደገፋ እና ፕሮግራሙን ያቀነባበሩ ተጠርጣሪዎች :-
1ኛ. ወንጌላዊት ገብረ እንድርያስ በርሄ፣
2ኛ. በርከት ፀጋዬ ጅፋር፣
3ኛ. መቅድም ደረጄ መንግስቱ፣
4ኛ. ግሩም ገዛሀኝ ቀጭኔ እና
5ኛ. ዮሃንስ መኮንን ሀ/ማርየም የተባሉ ግለሰቦችን በቀጥጥር ስር ያዋላቸው መሆኑን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ " ከህብረተሰቡ ባህልና እሴት ያፈነገጡ አለባበሶችና መጤ ባህሎች ተስፋፍተው በትዉልዱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳያስከትሉ ተጠርጣሪዎቹ ላይ የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የጀመርነውን ምርመራ አጠናክረን እንቀጥላለን " ብሏል።
#EthiopianFederalPolice
@tikvahethiopia
👏 6 343❤ 1 202🙏 356😡 274🤔 136😭 83💔 48🥰 37🕊 24😱 17😢 12
00:19
视频不可用在 Telegram 中显示
ዕድል እና አጋጣሚዎች ፈጣን ተጠቃሚን ይመርጣሉ!
እርስዎም ፈጠን ብለው ተሸላሚ እንዲሆኑ፣ አቢሲንያ ባንክ - ከ ኅዳር 22 እስከ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ “ከአቢሲንያ ባንክ ጋር ይጀምሩ - ያድሱ እና ይደጉ” የተሰኘ የሽልማት መርሀ-ግብር ለደንበኞቹ አዘጋጅቷል!
ከእርስዎ የሚጠበቀው የባንካችን ቤተሰብ በመሆን፣ በቅርንጫፍም ሆነ በዲጂታል አማራጮቻችን አዲስ ሂሳብ መክፈትና ተቀማጭ ማድረግ ፣ ነባር ሂሳብዎ ላይ ተጨማሪ ገቢ ማድረግ ፣ በፊት ገፅታዎ እና በጣት አሻራዎ የደንበኝነት ምዝገባ ማካሄድ፣ በባንካችን የውጭ ምንዛሬ መመንዘር ወይም ገቢ ማድረግ እንዲሁም ከባንካችን ጋር በአጋርነት ከሚሠሩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በአቢሲንያ ባንክ በኩል ክፍያ መፈጸም ብቻ ነው!
ያን ጊዜ የሚያስሸልሙ ኩፖኖችን ወዲያውኑ ያገኛሉ!
እነዚያ ኩፖኖች ደግሞ፦ አዲስ ሀዩንዳይ ኤሰንት መኪና፣ ቲቪና ላፕቶፕ፣ ጨምሮ ሌሎች በየ15 ቀኑ ፍሪጅ፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽን እና ሌሎችም አጓጊ ሽልማቶችን አሸናፊ ያደርግዎታል፡፡
ያስታውሱ—የብዙ ኩፖኖች መኖር የሽልማት ዕድልን ይጨምራል
ይበሉ ከአቢሲንያ ጋር ይጀምሩ – ያድሱ እና ይደጉ!
ለበለጠ መረጃ 8397
ደንብና ሁኔታዎች ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል
አቢሲንያ - የሁሉም ምርጫ!
IMG_5547.MP42.83 MB
❤ 307🙏 20😭 8🥰 2😱 1
በ2018/2025 ግብር ዓመት በየ3 ወሩ የሚከፈለዉ ቅድመ ግብር የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ተደርጓል።
በገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያ መሰረት ከተያዘዉ የግብር አመት በፊት በነበረዉ የግብር አመት የተከፈለዉን ግብር 25 በመቶ እንደሚከፈል መደንገጉ ይታወቃል።
በማሻሻያ አዋጁ መሰረት ገቢዎች ሚኒስቴር የ2018/2026 ግብር አመት ዓመታዊ የትርፍ ግብር በየሩብ አመቱ (በየሦስት ወሩ) በማሳወቅ የሚከፈልበት የጊዜ ሰሌዳ አሳውቋል፡፡
በእዚህም መሰረት በኢትዮጵያ የጊዜ ቀመር ለሚጠቀሙ (ሒሳባቸዉን ሰኔ 30 ለሚዘጉ) ግብር ከፋዮች:-
• የመጀመሪያዉ ሩብ አመት የመክፈያ ጊዜ ከየካቲት 1 እስከ የካቲት 30 ፣ ከሀምሌ 1- መስከረም 30 የተቀነሰ 3 % ቅድመ ግብር (withholding) በዚህ ወር ከሚከፈለዉ ክፍያ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል።
• የሁለተኛ ሩብ አመት የመክፈያ ጊዜ ከግንቦት 1 አስከ ግንቦት 30 ፣ከጥቅምት 1 እስከ ታህሳስ 30 የተቀነሰ 3 በመቶ ቅድመ ግብር (withholding) በዚህ ወር ከሚከፈለዉ ክፍያ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል
• የሦስተኛዉ ሩብ አመት የመክፈያ ጊዜ ከነሀሴ 1 እስከ ነሀሴ 30 ፣ከጥር 1 እስከ መጋቢት 30 የተቀነሰ 3 % ቅድመ ግብር (withholding) በዚህ ወር ከሚከፈለዉ ክፍያ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል።
በ2019 ከሀምሌ 1 እስከ ጥቅምት 30 አጠቃላይ የ2018 ግብር አመት የትርፍ ግብር ቀድመዉ የከፈሉትን በመቀነስ ቀሪዉን ይከፍላሉ፣ በትርፍ የተከፈለም ካለ ተመላሽ ይጠይቃሉ።
በግሪጎሪያን የጊዜ ቀመር ለሚጠቀሙ (ሒሳባቸዉን ዲሴንበር 30 ለሚዘጉ) ግብር ከፋዮች ፦
• የመጀመሪያዉን ሩብ አመት የመክፈያ ጊዜ August 1 እስከ August 30 ፣ January 1 እስከ March 30 የተቀነሰ 3 % ቅድመ ግብር (withholding) በዚህ ወር ከሚከፈለዉ ክፍያ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል።
• የሁለተኛ ሩብ አመት የመክፈያ ጊዜ November 1 እስከ November 30 ፣ከApril1 እስከ June 30 የተቀነሰ 3 % ቅድመ ግብር (withholding) በዚህ ወር ከሚከፈለዉ ክፍያ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል።
በ2026 January 1 እስከ April 30 አጠቃላይ የ2025 ግብር አመት የትርፍ ግብር ቀድመዉ የከፈሉትን በመቀነስ ቀሪዉን ይከፍላሉ፣በትርፍ የተከፈለም ካለ ተመላሽ የሚጠይቁ መሆኑን ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ያወጣው መርሃ ግብር ያመለክታል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
❤ 1 138😡 367😭 58🙏 25🕊 25😱 18👏 17💔 15🥰 12
#Update
" በቫይረሱ ስርጭት ምክንያት ተቋርጦ የነበረዉ ትምህርት ከ5ኛ ክፍል በላይ ብቻ እንዲቀጥል ተወስኗል " - አቶ አብረሃም አታ የአሪ ዞን አስተዳደር
" ከቅድመ መደበኛ እስከ 4ኛ ክፍል ደግሞ ለጊዜዉ ቤት ይቆያሉ ! "
በጂንካ ከተማ በተከሰተው የማርበርግ ቫይረስ ስርጭት ስጋት ምክንያት ትምህርቶች ተዘግተው ቆይተዋል።
አሁን ላይ ከተስተዋለው የቫይረሱ ስርጭት መቀነስና የቁጥጥር ስርዓት መጠናከር ጋር በተያያዘ ከዛሬ ሕዳር 29/2018 ዓ/ም ጀምሮ በሁሉም የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ትምህርት እንዲጀምሩ የዞኑ ቀዉራውስ አስወጋጅ ግብረሃይል ዉሳኔ ማስተላለፉን የአሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብረሃም አታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
" ትምህርት የሚጀምረው ከወትሮው በተለየ መልኩ በፕሮቶኮሉ መሰረት በልዩ ጥንቃቄና ክትትል ነው " ያሉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ " በተማሪዎች መካከል የአካል ንክኪ እንዳይኖር ከፍተኛ ጥንቃቄ እየተደረገና በየዕለቱ የጤና ባለሙያዎች ተማሪዎችን የሙቀት መለካት ሌሎች የክትትል ተግባራትን እያከናወኑ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
ከቅድመ መደበኛ እስከ 4ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የመከላከል አቅምና ከጤና ባለሙያዎች የሚነገራቸዉን የጥንቃቄ መልዕክት ሰምተዉ ከመተግበር ጋር በተያያዘ ለጊዜዉ በቤቶ እንዲቆዩና በአጭር ጊዜ ዉስጥ የዚህ ዉጤት ታይቶ ዉሳኔ እንደሚሰጥም ገልፀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
❤ 447👏 43🕊 25🤔 14😡 12🙏 10😭 10🥰 8💔 7
照片不可用在 Telegram 中显示
#SafaricomEthiopia
2 ሚሊየነሮች ብቻ ቀርተዋል! ማን ያውቃል
ቀጣዩ የ1 ሚሊየን ዕድለኛ እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ! የበሽ ጥቅል እየገዛን እንንበሽበሽ! 🥳🎉🎉
📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፡
https://onelink.to/ewsb22
የቴሌግራም ቦታችን 👉🏼 https://t.me/official_safaricomet_bot
ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!
#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#bes
❤ 134😡 7🙏 5🕊 4🥰 1😱 1😢 1
照片不可用在 Telegram 中显示
#SafaricomEthiopia
2 ሚሊየነሮች ብቻ ቀርተዋል! ማን ያውቃል
ቀጣዩ የ1 ሚሊየን ዕድለኛ እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ! የበሽ ጥቅል እየገዛን እንንበሽበሽ! 🥳🎉🎉
📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፡
https://onelink.to/ewsb22
የቴሌግራም ቦታችን 👉🏼 https://t.me/official_safaricomet_bot
ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!
#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#bes
