ግጥም ብቻ 📘
前往频道在 Telegram
✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13 ✔ @wegoch @Words19 ✔ @seiloch @shiyach_bicha ✔ @zefenbicha @leul_mekonnen1
显示更多2025 年数字统计

65 765
订阅者
-324 小时
-397 天
-30130 天
帖子存档
ግጥም ነው ምትመስዪው!
---------------------------------------
ከፊደል ማሳ ላይ ቃላት ለሚቃርም
ካገኘም ከትቦ እያደር ሚያርም÷
በአርኬው መባቻ በመድፋት አባዜ
ከሃሳብ ባህር ላይ ሰጥሞ በትካዜ÷
በብዕሩ እንባ ስንኞች ሲቋጥር
ቤቱን በመዘንጋት ቤት ለመምታት ሚጥር÷
እቴ አትሞኚ ከቁብ ለማይቆጥርሽ
በፍቅር አጊጠሽ አምሮብሽ ቢያይሽ÷
በቃላት ስደራ የተሽቀረቀረ
በታሪክ ፍሰቱ ጎልቶ የዳበረ÷
ግጥም ነው ምትመስዪው
መምቻና መድፊያው ፍፃሜው ያማረ::
By @Abuugida
@getem
@getem
@getem
❤ 31👍 4😁 1
ቆርጦልኝ ነበረ ነግሬሽ የልቤን ወድሻለሁ ብዬ
የምትወጂኝ መስሎኝ ስጠብቅሽ ቀረሁ ካደርኩበት ውዬ
ነካክተሽ ነካክሽ ልቤን አደረግሽው የፍቅርሽ ምርኮኛ
የማትወጂኝ ከሆን ለምን ቀሰቀስሽው ይቅር እንደተኛ
አይቀርም አንድ ቀን ያፈቀረሽ ልቤ የጎኑን ማግኘቱ
ህይወት ይቀጥላል ምን ልቤ ቢደክም አንቺን በማጣቱ
አገኘሽኝ እንጂ ሆኜ ያንቺ ወዳጅ
ከፍቅርሽ አለም ውስጥ
ሳላውቀው ገብቼ እንደ ባህር ሰርጓጅ
ግን ...
ያሳሰበኝ ፍቅር
ካንቺ ስር ያዋለኝ እንዲህ እንደከረረ
ሌላ ሲያይሽ ጊዜ ቀንቼ ነበረ
አፈቀርኩሽ ያልኩት
የኔ ያልኩትን ሰው በሌላ ሲታቀፍ
እንዴት ብዬ ልለፍ
የመነጠቅ መንፈስ
ውስጤን እንገብግቦት አላመጣሁሽም
እውነቱን ስነግርሽ
ቀንቼ ነው እንጂ አላፈቀርኩሽም
አልልሽም ይህን ቃሌን ድፍረት የለኝ የምልበት
ያጠፋዋልና የወንድነት ልኩን ይህን ያልኩሽ እለት
እንደገባኝ ቢሆን ከዚህ ሁሉ ነገር
ቅናት መንፈስ እንጂ አልነበረም ማፍቀር
ዮርዳኖስ @JorDanos7
@getem
@getem
@getem
👍 35❤ 26🤩 6🔥 3
የማመንታት ፍቅር
ልሂድ ወይስ ልቅር
(ያለበት)
ጓዝሽን ጠቅልለሽ በስንብትሽ እለት
ደግሞ ተመልሶ
ከበቃኸኝ በኃላ ካልበላሁ ማለት
(ምን ይሉታል አሁን)
ተፍተሺኝ አንቅረሽ
ጥላቻን አፍቅረሽ
ባፍንጫሽ ወጥቼ
ለፍቺያችን ድግስ የወይን ጠጅ ጠጥቼ
(ችርስ ተባብለን)
ወይ መተሽ አትመጪ ወይ ቀርተሽ አትቀሪ
ድንገት ትገኛለሽ ለፍቅር ከፊቴ ስትደነቀሪ
By @Absari_seven
@getem
@getem
❤ 33👍 11🔥 4
ዛሬ ሌላ ሰው ነኝ።
ያኔ ትንሽ ሆኜ-
በእድሜዬ ለጋ - በበሓሪ ችኩል፣
አፍንጫ አሽትቻለሁ፣
ቀድሞኝ ከበሰለው - ለመታየት እኩል።
ልጅነትን ሳልፈው-
ሌላን ማየት ትቼ - ራሴን ዐየሁ እና፣
ገደብ ሰራሁለት፣
ጉጉቴ ልክ አልፎ -ስጎድል እንዳይቀና።
ልልሽ የፈለግሁት-
አንቺ ላታስቢኝ አትበይ “ረስተኸኛል”፣
የሰርግሽን ፎቶ-
ከልቤ ሳደንቀው እራሴም ገርሞኛል።
ምክንያት፣...
ያኔ ወጣትነት - ኩራት የኮፈሰኝ፣
ትእቢት ላንዳፍታ - ወስዶ የመለሰኝ፤
እልህ እየጋተ - ምላጭ የሚያስውጠኝ፣
“ዛሬ ብቻ” ባይ ኅዝብ - አስሶ እሚመርጠኝ፤
ዛሬ...
አንቺ የኖርሽውን - ዘመን የኖርኩ እኔ፣
እራሴን ያስተማርኩ - በሕይወት ጠመኔ፤
አንቺ “ፈልጉኝ” ባይ - እኔ ራሴን መሪ፣
አንቺ ላይሽ ፋኖስ - እኔ ውስጤ በሪ፤
ከመንገድሽ እሩቅ - መንገዴ ወስዶኛል፣
ሺህ ግዜ አግብተሽ - ሺህ ግዜ ብትፈቺ ምን ያናድደኛል?
በርቺ 😐
@eyadermoges
@getem
@getem
@getem
❤ 26👍 20🔥 1😁 1
ራሱ’ንደማይጠጣ - የውሃ ማሰሮ፣
መሆን ላልተቻለው - ክው ያለ ጉሮሮ፤
አስመሳይ ደጋጎች - ውሃ ሰጡት’ና፣
የሞት ሞቱን ሲኖር - ችግሩ እንደጠና፤
ጉሮሮ ማሰሮ - ተመሳስሎባቸው፣
ያጠጡትን ቀድተው - መውሰድ ላቃታቸው፤
ረሃብ አንጎራጉሮ - ለለመደው ውሃ፣
ሰጥቶ ተቀባዮች አስቀየመልሃ!
(የሞገሴ ልጅ)
@eyadermoges
@getem
@getem
@getem
❤ 19👍 14🔥 1
ቃል ከአፋቸው ሳይወጣ
ፍቅር ተሰናብቶ መለያየት መጣ
ቻው እንኳን ሳይሉኝ
ሁሉም አገለሉኝ
እኔ ብቻ ሆነ እኔን የወደደው
እሱስ ተራው ደርሶ መች ይሆን ሚሄደው
By @Absari_seven
@getem
@getem
❤ 37🤩 9🔥 5
ቢታነፅ ቢወቀር!
(በእውቀቱ ስዩም)
እኔም አንድ ሰሞን
ልክ እንደ ሰለሞን
"ሁሉም ከንቱ ከንቱ ንፋስን መከተል
ላይጥሉ መታገል: ላይከብሩ መባተል"
እያልሁ አጨልሜ
በራሴ ለግሜ: እፈላሰፍ ነበር!
ከዚያ አንቺን አገኘሁ
በጓሮ በር በኩል: ሰለሞኔን ሸኘሁ
መፈጠሬን ወደድሁ
ንፋስ አሳድጄ እንደ ቆቅ አጠመድሁ
ከፀሀይዋ በታች: ግልገል ፀሀይ ፈጠርሁ
ለኦናው አምፖሌ: ብርሀን አበደርሁ
ማቅ የነበረው ጨርቅ: ሸማ ሆኖ ቆየኝ
"ከንቱ የነበረው: "አንቱ" ሆኖ ታየኝ!
ለካስ...
ጠቢብ ቢያስተምረው
መከራ ቢመክረው
አካሉና ልቡ: ቢታነፅ ቢወቀር
ሰው አቅሙን አያውቅም: ካልወደደ በቀር!
@getem
@getem
@paappii
❤ 63🔥 19👍 6🎉 1
显示全部...
❤ 43🔥 11😢 8😱 5👍 1
ወደግራ ወድቆ
ፍቅራችን ዳመራው
የትዝታሽ ጭሱን ናፍቆት ሰማይ ጠራው
እሄዳለሁ ብዬ ሶዶ ወይ ጉራጌ
አንቺ የሌለሽበት
መስቀል እንዴት ላክብር እንደምን አድርጌ
By @Absari_seven
@getem
@getem
❤ 46😁 13👎 2
ላንቺ ብፅፍ ግጥም
ቆረጥኩኝ የሴት ጥም
እንደው ባየሺልኝ
1 አንቺ ስትሄጂ ናፍቀሺኛል ብልሽ
በስንኜ በኩል
የእንስት ጋጋታ ህይወቴን ሞላልሽ
የምን በትዝታ ሰክሮ መንገዳገድ
ሀሳብ ውሎ ይግባ በብዕሬ መንገድ
(ይህንን አትርሺ)
ሰው በቃል ይረሳል
ሰው በቃል ይፈርሳል ሰው በቃል ይሰራል
ባለቀሰበትም ድንኳን ይሞሸራል
By @Absari_seven
@getem
@getem
❤ 59🔥 12👍 5😱 2
