ch
Feedback
ግጥም ብቻ 📘

ግጥም ብቻ 📘

前往频道在 Telegram

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13@wegoch @Words19@seiloch @shiyach_bicha@zefenbicha @leul_mekonnen1

显示更多
2025 年数字统计snowflakes fon
card fon
65 745
订阅者
-924 小时
-597
-32030
帖子存档
ጥላና የሰው ልጅ ይመሳሰላሉ አለውልህ ብለው ሲመሽ ይጠፋሉ ጨለማ ሲወርስህ ብርሀንህ ሲጠፋ ቅን እኮ ነው ያልከው ታያለህ ሲ'ከፋ [ ጥሩቤል ] @ebuh_bhr @getem @getem @getem
显示全部...
68👍 33🔥 8👎 1
, ( ግዛትሽ ነኝ ) እንደ ሀይቅ ጠልቄ ከሃገር የሰፋሁ አለሜን ስፈልግ ከአለም የጠፋሁ በልብሽ መቅደስ ውስጥ አብሬ የተሰፋሁ ሰፊ ግዛትሽ ነኝ ወሰን ያልወጣልኝ ለክብሬ ዘብ ያጣሁ ወሰንሽን ደፍረው ግዛትሽን ሳይወርሱት በዳው መሬትሽን መንጥረው ሳያርሱት ነይና ግዛትሽን አንቺው ዘብ ሁኝለት መረቡን አስፊ እና ወሰን አብጂለት ዳግምም አታገኝው ብትባክኝ በስለት ችላ ያልሽው ግዛት ገዥ ሰው ያገኘ ዕለት ውቢቷን ቀለሜን ውዲቷን ህይዎቴን አለሜን ስፈልግ አለሜን ማጣቴን ላንቺ እንዲህ መሆኔን አንቺ ግን አታውቂም አንቺ ግን አንቺ ግን አንቺ ግን አታውቂም እውነት እልሽ አለሁ ያለ እኔም አትደምቂም By Habtish @getem @getem @getem
显示全部...
17👍 15
#አላት_መንገድ አላት መንገድ የቁንጅና አላት መንገድ ያንዳች ውበት ፈ ገ ግ     ምትልበት ዮኒ      ኣታን @yonatoz @getem @getem @getem
显示全部...
👍 21 14
ከጎኔ ርቀሽ ከሌላ ብትለምጂ ልሁን አልል ደባል ብናፍቅ ይሻላል የሚያፈቅሩትን ሰው አትናፍቅ አይባል ዮኒ      ኣታን  @yonatoz @getem @getem @getem
显示全部...
👍 24 8😢 5
照片不可用在 Telegram 中显示
ህልም እልም ሠዓሊ ስዩም አያሌው በፈንድቃ ከሚያዝያ 20 እስከ ግንቦት 4 @Seiloch
显示全部...
👍 24 4🔥 1
ተዘነጋሽ አይደል ገፍተው አናናቁሽ ከሳምንታት በፊት ንግሥቴ እንዳላሉሽ የኔማ ሽሮዬ ብለው እንዳልተቀኙ ጥለውሽ ነጎዱ ሚሽቱን ሲያገኙ . እኔን የኔ አበባ እኔን የኔ እመቤት 50 ቀን ቀርቶሻል ልትገቢ ዳግም ቤት . እኔ የኔ አበባ እኔን የኔ ንግስት ሰው ብቻ አይደለም ማግጧል ያም ብረት ድስት . ሁሉም ከድተውሻል ሁሉም ትተውሻል ትንሽ ብቻ ታገሽ 50 ቀን ቀርቶሻል . ያኔ ቀኑ ሲደርስ በእየንብርክካቸው ማሪኝ ማሪኝ ሽሮ አይቀር ማለታቸው . እኔን የኔ አበባ እኔን የኔ እመቤት 50 ቀን ቀርቶሻል ልትገቢ ዳግም ቤት አለፈልን ብለው ቢያናንቁሽም አትፍረጂባቸው! የድሃ ብረት ድስት መቼም አይለቅሽም #ስሜታዊ_ሆነው_ነው [ ጥሩቤል ] @ebuh_bhr @getem @getem @getem
显示全部...
👍 52😁 27 11🔥 6👎 1
(የአብስራ ሳሙኤል) ጥበብ ናት እሷ ሽንሽን ቀሚሷ የዘመን ቀለም ችቦ ናት ለአለም ሳቋ የድል ብስራት ኩርፊያው እስራት የአንገቷ ድሪ ሸማ ቀሚሷ ዜማ ናት እሷ የህይወት ቃና የመዳን ዜና ከጡት ወተቷ ከመቀነቷ እያጎረሰች ጎጆ የቀለሰች ጥበብ ናት እሷ ችቦ ነው ነፍሷ ቁጣዋ ማዕበል ዝም ጭጭ ደርሶ ክፋት ገርስሶ ፍቅር የዘራ ጥበብ ናት እሷ የአምላክ ስራ የእጅ የመዳፋ እስትንፈስ የአፋ የመዳን ድልድይ የተስፋ ነብይ መቀነት ፈታ ጡቷን አሟሽታ እያጎረሰች ቀን ያደረሰች ጥበብ ናት እሷ ሸማ ቀሚሷ የዘመን ቀለም ችቦ ናት የአለም የመዳን ዜና የመኖር ቃና መራራ ወዟ ድል ያስጎነጭን የእኔን እንባዋ ውስኪ ያራጨን ቅድ ጥለቷ ገመና ጋርዶ የመዳፍ ቁስሏ ትኩስ አብርዶ ትውልድ ያኖረ ችቦ ነው ሳቋ ድል ያበሰረ ጥበብ ናት እሷ ሽንሽን ቀሚሷ የዘመን ቀለም መርከብ የሆነች ለጠፋች አለም መቀነት ፈታ ቀን ያሻገረሰች ድል ያበሰረች ጥበብ ናት እሷ ዜማ ናት እሷ ሷቋ የድል ብስራት ኩርፊያዋ አሰስራት By @mad12titan @getem @getem @getem
显示全部...
👍 15 13
照片不可用在 Telegram 中显示
"በይው ተቀየረ እንጂ  ትሪው አልተነሳም" አሸናፊ ማስቲካ በአርታዊ ከ ሚያዝያ 18 -  ግንቦት 10 @seiloch
显示全部...
👍 10🎉 3🔥 2😁 1
አወቅሽኝ አወኩሽ . . . ተዋወቅን በፍቅር ነጠቅን ጨረቃን ዳሰስናት ኮኮቦችን ቆጠርን ቅዳሴ እና አዛንን አስቀደስን አፈጠርን አወኩሽ ወደድኩሽ ከልብ ተመኘሁሽ ለነብሴ ፈለኩሽ አጌጥን በፍቅራችን አስቀናን ላገሩ             ኮራን በመንደሩ ወጣቶች ተያይተው      "ሲያምሩ...ሲያምሩ" እየተባባሉ ወደድሽኝ ወደድኩሽ . . . ተዋደድን በፍቅር አበድን ነጎድን...ነጎድን...ነጎድን ከአፍ ባልወጣ ቃል መፋቀራችንን ሀገር ምድሩ ያውቃል መገረም መደነቅ ለኛ ምንም ነው          ተፋቅረን አየነው ደላኝ ባንቺ ፍቅር         ደላሽ በኔ ፍቅር እኔ ለንቺ አንቺ ለኔ ካለን ሁሉም ነገር ይቅር አፈቀርሽኝ አፈቀርኩሽ . . . ተፋቀርን የዛሬን ትዝታ ለነገ ወቀርን። ዮኒ      ኣታን  @yonatoz @getem @getem @getem
显示全部...
40👍 26👎 2😁 1
01:08
视频不可用在 Telegram 中显示
显示全部...
5.23 MB
👍 1
01:10
视频不可用在 Telegram 中显示
5.27 MB
👍 2
ቅጽርህ የእናት እቅፍ ሸክምን የሚያራግፍ አልተነፍስ ጸሎት አይወጣ ቃል ከአፌ ይተናል ጭንቀቴ ስመለስ አርፌ እመጣለሁ ደጅህ ሀሳብ አንጠልጥዬ እገባለሁ ቅጽርህ አንገቴን ደፍቼ መች ታዝንብኛለህ መች ትወቅሰኛለህ በሽቅጬ ከርፍቼ አይነድህ ድፍረቴ አይቆጨኝ ስንፈቴ አይበሽቅህ ስህተቴ አይገደኝ ዝለቴ በኦና ተግባሬ ውድቀት አንከርፍፌ ስቆም ከነእድፌ ምን አድርጌልህ ነው? አክመህ ምትልከኝ በምህረት መርፌ ከመቀመጥ በቀር ኢምንት ታህል ድርጊት ፈጽሜ የማላውቅ አንዲት ዘለላ እንባ በጉንጬ ሳልሰድ እንዴት ደመቅኩ በሳቅ? እንዴት ቻልኩ መፍገግ? እንዴት ቻልኩ ማማር? እሬት ህይወት ይዤ አጣፍጥልኝ ሳልል ሳልጠይቅ የሀሴት ማር ትዕቢት አይሉት ጥጋብ ፍርሃት አይሉት ስጋት ስም ያላገኘሁለት አንዳች አሳሪ ኃይል ወርሮኝ እንደ ውጋት አላልኩኝ እግዚኦታ አልቆምኩኝ ሰዓታት ፈውስ አሰኝቶኝ አላደረስኩ ኪዳን ስለረገጥኩ ብቻ ስላረፍኩ በቤትህ ይገባኝ ነበር መዳን? እንጃ! ብቻ እመጣለሁ ሀሳብ አንጠልጥዬ ደጅህ እገኛለሁ ማረኝ ቃልን ጥዬ አርፋለሁ ካንዱ ጥግ አንገቴን ደፍቼ መች ትቆጣኛለህ ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ከነእድፌ ተኝቼ ቆይቼ ቆይቼ . . . ቆይቼ ስነሳ ተጋድሞ አየዋለሁ ሸክሜ እንደ ሬሳ አልጸለየም ሳትል አልለመነም ሳትል አላነባም ሳትል ይገርመኛል እኮ ጊዮርጊስ አባቴ ጭንቀቴን ስትጥል ይገርመኛል ቅጽርህ... ልክ እንደ እናት እቅፍ ደስታን 'ሚያሳቅፍ! አባብሎ 'ሚያሳርፍ! ሸክምን 'ሚያራግፍ! . . . እርፍ! #ኤልዳን @marda129 @getem @getem @getem
显示全部...
37👍 17🔥 4👎 3
አልከነፍኩም ስላፈቀርኩ           ተሰባበርኩ እንጂ የትም መልስ የለሽም ለጥያቄ              ልብሽ እኔን አያካትም ያንቺ ፍቅር አሳነሰኝ            ደጅ አስጠናኝ በዳጃፉ ሰው እንደሆን ወሬ አያጣም            ይለቅመኛል ሁሌ ባፉ ህመም ብቻ ውስጤ እሳቱ        አይዳፈን እየነደድኩ መፈቀር ግን ህያው ሞት ነው       ስቃይ ብቻ ማፍቀር ልኩ አላመንሽም ያንደበቴን         የማፍቀሬን ስር ትርጉሙን አይወደኝም ሰርክ መልስሽ       አላወቅሽም ጥግ ህመሙን ተፈቃሪ ምን ግድ አለው        ምን ቢፈቅር እንደሀገሩ አፍቃሪ ነው ነገር ሚፈጅ         የሚማገድ ለወደሩ ትገርሚያለሽ አንቺ ብቻ       አላመንሽም የኔን ፍቅር አትወድህም ቢለኝም ሰው      ከደጃፍሽ ዛሬም አልቀር ዮኒ      ኣታን @yonatoz @getem @getem @getem
显示全部...
👍 16 7🔥 2
ደህና ዋልሽ አልኳትኝ የፈካውን ፊቷን በአይኖቼ እየካደምኩ "እግዛቤር ይመስገን" በጥፍጥ አንደበቷ በከንፈር ተማረኩ "አንተስ እንዴት ከረምክ....ተስማማህ አየሩ" ግርምታ እየያዛት ብመጣ በወሩ "..ኧኧ....ይመስገን ጀሊሉ.."      "ይመስገን ጀሊሉ" "ምነው ጠፋህሳ ከሄድክበት ግድም እንደው ቢቻል...ቢቻል            አይደወልም አንድም" "አፉ በይኝ አቦ.... ባይመቻችልኝ ነው መደወል መርሳቴ" ተጠጋሁ ከፊቷ አሳረፍኩ አንጀቴን "ይልቁንስ አንቺው ከዛ ከሩቅ ሀገር ያመጣሁት አለ ከተስማማሽ ላንቺ ብትለብሺው ምናለ"           "ማርያምን..?......የታለ.." "አለ ከሰነኩት...ከሻንጣዬ ግድም ቢሆን ለደብርሽ ለባዕልሽ ግልድም" "ደስ ይለኛል....ወላዲቷን" ደስ ብሏታል የእውነቷን "በል ና ቅመስ የቡና ቁርስ        አልወረደም ገና አቦሉ" "የለም ልሂድ.....ሌላ ጊዜ ሳይብስብኝ ይህ ቀትሩ" "ማይሆነውን.... እዚህ መተህ አትመለስ የባታ ነው ፀበል ቅመስ" "ወላሂ..ይቅርብኝ ሩቅ ነው መንገዴ ባየሆን ልዝገን ካለው ባዶ እንዳይሆን ሆዴ" ዘገንኩት ከቁርሱ ካፌ ላይ ወረወርኩ ያመጣሁላትን ለገላዋ አስረከብኩ "ባታ ትስጥልኝ አለሜ...." "አሜን....ሙሃመዴ" ዮኒ     ኣታን  @yonatoz @getem @getem @getem
显示全部...
👍 41 9🤩 5
( የወጉት ) ============= ያኔ .... አይሁድ በጭካኔ ክንድህን ወጥረው ለፍቅርህ ብድራት ለውለታህ ዋጋ አምስት ችንካር ቆጥረው ያለ ርህራሄ በመስቀሉ አግድም እጅህን ሲዘረጉት አላወቁት እንጂ ... ባንተ መዳፍ በኩል እልፍ ልቦችን ነው በምስማር የወጉት !! By @Kiyorna @getem @getem @getem
显示全部...
114👍 25
ፆመ እባላለሁ ፥ ፆሜን እየፈታሁ (ሳሙኤል አለሙ) እንቁላሉን፣ስጋውን እንዳልበላሁ ሰው ያውቃል፤ ወተቱን ፣ እርጎውን እንዳልጠጣሁ ሰው ያውቃል፤ ላግኘው ብየ ልያዘው ብየ እንዳልወጣኝ ፥ ክፉ ቃል ሰው ያውቃል፤ አውቃለሁ አያውቁም አያውቁም አውቃለሁ ፤ ስብሰለሰል ግዜ ስንገበገብ ግዜ የከንፈሬን ስሷን ቆዳ --ልጬው እየበላሁ ፆመ እባላለሁ ፥ ፆሜን እየፈታሁ። ሳሙኤል አለሙ @Samuelalemuu @Getem @Getem @Getem
显示全部...
🔥 24👍 19 17😁 9😢 1
መኖር በፍላጭ ሰከንዶች፤ በሽራፊ ሰዓት፤ በደቂቃ ቅንጣት፤ እለት እየገፉ፤ ወራት እያለፉ፤ እየጣሉ አመታት፤ በዘመን ምትሀት፤ በአንዲት የጊዜ ጋት፤ መኖር መሳብ አይደል፤ ወደሞት መጠጋት ?            By @poetkidus @getem @getem @paappii
显示全部...
30👍 8
መባቻ ነው ይህ ኑሯችን የኖህ ሆኗል ዝማሚያችን ግማድ ሆኗል ይህ ፍቅራችን በዚች አለም የታሰረ ቅን ልባችን ስማችን ነው እጣን ከርቤ ሙዳያችን ከመረጥሽው አንቺ ካልሽው ካህን ወጣንም ወረድን በደብተራ ምርኩዝ የተነከረብን እኔ አንቺ ወይ ድውያችን ታስሮ ኖሯል በደብተራ በመባቻ ፅኑ ኪዳናችን እኔ እና አንቺ ወይ ድውያችን መሞቻ ቀናችን በዘመን በታሪክ ስማችን ተመርጦ መደገሚያ ሆነ ለደብተራ ሸቶን By አለምሰገድ ወልዴ @getem @getem @getem
显示全部...
👍 36 11👎 4
照片不可用在 Telegram 中显示
ሥዕል ማሳል ለምትፈልጉ በሙሉ በ +251984740577 ወይም @gebriel_19 ላይ  ፎቶ  በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ  ማዘዝ ይችላሉ! #ሥዕል_ብቻ @seiloch @seiloch
显示全部...
👍 32 10👎 3🤩 3
. ነፍስ ምኞቷ መፈንጠዝ ወንጀልን ማትፈራ የፈለገችዉን ገፍታ ምታሰራ ከንቱ የሆነች ነፍስ ፍፁም የከሰረች ስጋዬን የምታዝ መረን የለቀቀች ደልቃ ደልቃ የደከመች ለታ እኔን ትወቅሳለች... የፈጣሪ ሎሌ የ ስሜቴ ጌታ። ረቡዕ ፣ መስከረም 25 ፣ 2015 ዓ.ም @getem @getem @getem
显示全部...
👍 27 15