ch
Feedback
የስብዕና ልህቀት

የስብዕና ልህቀት

前往频道在 Telegram
2025 年数字统计snowflakes fon
card fon
68 961
订阅者
无数据24 小时
-137
-96730
帖子存档
❤እኔ_ደግሞ …." ምንድነው እንደዚህ - ፊቴን በብረሃን ከንፈሬን በውብ ሳቅ - የሚያጥለቀልቀው፣ ምንድነው ከልቤ - ኮለል ያለ ሰላም - በጧት የሚፈልቀው?። እያልኩ አስባለሁ ……                          ፡ #እኔ_ደግሞ ….. ምንድነው ሰው ሁሉ- ነጫጭ ክንፍ አብቅሎ - መላክ የመሰለው፣ ምንስ ነው ሰማዩ - እንዲህ ተጠቅልሎ - በጀ የምይዘው - መሃረም ያከለው።                        ፡ ኧረ ምን ታምር ነው - መሬት መዞር ትታ - በፎይታ ያቆማት፣ ምንድነው ጨረቃን - ከሰማይ አወርዶ - ምድር -ያሳረፋት?። እያልኩ አስባለሁ                         ፡ #እኔ_ደግሞ ….. የጠሉኝን ሁሉ - ድንገት የመውደዴ፣ መሬቱን ለቅቄ - ባየር ላይ መንጎዴ።                         ፡ ምንድነው ሚስጥሩ-ቆይ ውስጤን ምን ነካው፣ አለም እንዲህ ጠቦ - በርምጃ ሚለካው።                             ፡ ውቂያኖስ በፍኜ - ተጨልፎ የሚደርቅ፣ ተራራው በክንዴ - ተጎሽሞ የሚደቅ።                            ፡ ማነው በመንገዴ - ሳልፍ እልል የሚለው አበባ ነስንሶ፣ ማነው ግማሽ ልቤን - ሸርፎ የወሰደው -በትልቁ ቆርሶ?። ኧረ ምን ታምር ነው ? እያልኩ አስባለሁ                            ፡ #እኔ_ደግሞ ….. መንገዳኛው ሁሉ - የተከፋ ፊቱን - በማን ተነጠቀ፣ ከጨፍጋጋ ፊቶች - የዚህ አይነት ብርሃን - እንዴት ፈነጠቀ።                            ፡ ሚሊየን ህፃናት - ቀልብ በሚነሳ - ስርቅርቅ ድምፃቸው፣ የት ቢዘምሩ ነው - ልቤ ሚሰማቸው።                          ፡ በምን ተአምር ነው - ዛፎች የሚያረግዱት፣ በምን ጉድ አስማት ነው - የሰማይ ከዋክብት ቁልቁል የሚበሩት። እያልኩ አስባለሁ ….                               ፡ #እኔ_ደግሞ …. ቤሳ ቤስቲን ፍራንክ - ኪሴ ሳይጨመር፣ አመት የለበስኩት - ልብሴ ሳይቀየር።                           ፡ የዘወትር ጉርሴ - ጣሙ ሳይነካ፣ እኔነት እኔ ውስጥ - ተቀይሯል ለካ።                            ፡ እኮ በምን ምክንያት - እኔ ተቀየርኩኝ፣ እንዴት እኔ ነኝ ስል - እኔ ሌላ ሆንኩኝ። እያልኩ አስባለሁ …….. ለ ካ ስ ……………………..አፍቅሬሽ ነው!!! 🔘አሌክስ አብርሃም 🔘 #share Join: @Human_Intelligence Join: @Human_Intelligence
显示全部...
👍 47 16
ከ400 ዓመት በፊት የተነገሩ አምስት ጠቃሚ የሕይወት ምክሮች ራስን ለመለወጥ የሚረዱ ምክሮችን ስናስብ ምናልባት ገበያውን የሞሉት አዳዲሶቹ መጽሐፍት ጠቃሚ ሊመስሉን ይችላሉ። ሁሌም ቢሆን ማንም ሰው ዘመናዊና አዲስ የሆኑ ነገሮችን በመጠቀም ራሱን መቀየር ይፈልጋል። ነገር ግን ከብዙ ዘመናት በፊት የተጻፉ መጻሕፍት አሁን ላለንበት ዓለም ተግባራዊ መሆን ይችላሉ። 'ዘ አናቶሚ ኦፈ ሜላንኮሊ' የተባለው መጽሐፍ በአውሮፓውያኑ 1621 እንደተጻፈ ይነገራል። የዘመናዊውን ሰው አኗኗርና አስተሳሰብ ከዚህ መጽሀፍ በላይ የሚገልጽ ግን አልተገኝም። በርተን እንግሊዛዊ ቄስና ምሁር ሲሆን ከ2 ሺ ዓመታት በላይ ግሪክ ውስጥ ጥቅም ላይ ይውሉ የነበሩ ሕክምናዎችና እና ፍልስፍናዎችን አጠናቅሯል። ይህ እንግሊዛዊ ምሁርና ቄስ ከፍተኛ ድብርትን ያውቀዋል። በዚህ ጉዳይ ዙሪያም በርካታ ሃሳቦችን አስቀምጧል። ነገር ግን የበርተን የሕይወት ስራዎች በዘመናዊው ሰው ሕይወት ውስጥ ድብርትና ሀዘንን እንዴት ይረዱታል? ስኮትላንዳዊቷ ጋዜጠኛ ኤሚ ሎፕትሮት የበርተንን ስራዎች አጠናቅራ በድጋሚ በማዘጋጀት ለ21ኛው ክፍለዘመን ሰው በሚመች መልኩ አቅርባዋለች። እሷ እንደምትለው በ1620ዎቹ ሰዎች ከድብርትና ሀዘን ለመላቀቅ ይወስዷቸው የነበሩ የመፍትሄ እርምጃዎች አሁንም ድረስ ጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ ናቸው። 1. የራሳችንን የስሜት መለዋወጥ በአንክሮ መከታተል በድብርት አልያም በሀዘን ለሚሰቃይ ሰው የሚሰሙት ስሜቶች ምናልባት ያለምንም ምክንያት የሚሆኑ መስለው ሊታዩ ይችላሉ። ነገር ግን የሚሰሙን ስሜቶች የራሳቸው አካሄድ አላቸው። ድብርት ተላላፊ በሽታ እንደሆነና ምልክቶቹም ሆነ የሚያሳርፉት ጫና ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተወረስ እንደሚሄድ በርተን ያስብ ነበር። ምናልባት ነገሮችን የተመለከተበት መንገድ የተለየ ሊመስል ቢችልም በዘመናዊው ህክምናም ብቸኛው ምክንያት ባይሆንም ድብርት ከቤተሰብ የሚተላለፍ እንደሆነ ተረጋግጧል። "አንድ የቤተሰብ አባል በከባድ የድብርት በሽታ የሚሰቃይ ከሆነ መላው ቤተሰብ አብሮት ህክምናውን አብረውት እንዲከታተሉና ለራሳቸውም ነገሮችን እንዲያስተውሉ እፈልጋለሁ'' ይላሉ በቤተሰብ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩት ዶክተር ፍራንሲስ ራይስ። ነገር ግን ድብርት ከቤተሰብ ብቻ የሚመጣ ጉዳይ አይደለም። የተለያዩ ውጪያዊ ምክንያቶችም የራሳቸው አስተወዋጽኦ አላቸው። በርተን መጽሐፉን በሚያዘጋጅበት ወቅት ራሱ ላይ ያስተዋላቸውን ነገሮች ከግምት ውስጥ አስገብቷል። በየጊዜው የሚቀያየር የደስታና ሀዘን ስሜቶች በዘመናዊው የህክምና ዓለም 'ባይፖላር ዲስኦርደር' የሚባል ሲሆን በርካቶችን የሚያጠቃ ነው። በአሁኑ ጊዜ ሰዎች የሚሰሟቸውን ስሜቶች በአግባቡ መከታተልና ለምን እንደሚለዋወጡ ማወቅ ለድብርት ፍቱን መድሀኒት ተደርጎ ይወሰዳል። ምን ሲገጥመን የስሜት መለዋወጥ ውስጥ እንደምንገባ ማወቅ ከቻልን እነዚያን ነገሮች ማስወገድ ቀላል ነው። 2. የቀዝቃዛ ውሃ ጥቅም በርተን በመጽሐፉ ላይ ከብዙ ዓመታት በፊት በሌሎች ሰዎች የተጻፉ የተለያዩ ሀሳቦችን አስፍሯል። ንጹህ በሆነ ቀዝቃዛ ወንዝ ውስጥ ገላችንን መታጠብ ደግሞ በርተን ካስቀመጣቸው መፍትሄዎች መካከል አንደኛው ነው። ማንኛውም ሰው ረጅም ህይወት መኖር ከፈለገ በጣም በሚያምር ተፈጥሮአዊ ቦታ ላይ ገላን መታጠብ አንደኛው መንገድ ነው ይላል። '' በቀዝቃዛ ውሀ ምክንያት ሰውነታችን የሚሰማውን ጭንቀት መቋቋም ካስለመድነው ሌሎች አስጨናቂ ነገሮችንም መቋቋም ይማራል'' ይላሉ በዩናይትድ ኪንግደም በሚገኘው ፖርትስማውዝ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ማይክ ቲፕተን። 3. ከተፈጥሮ አለመራቅ ተፈጥሮ ለበርተን ከፍተኛ ድብርትን ለማባረር ቁልፍ ሚና የሚጫወት ነገር ነበር። በተለይ ደግሞ በተፈጥሮአዊ ጫካ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ አይነት እጽዋት ጭንቅላታችን ዘና እንዲል እና የሚያስጨንቁትን ነገሮች እንዲረሳ የማድረግ ከፍተኛ አቅም አላቸው። በኦክስፎርድ ቦታኒክ ጋርደን ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ሳይመን ሂሰኮክ እንደሚሉ አንዳንድ ተክሎች ድብርትን ለማከም ጭምር ጥቅም ላይ ይውላሉ። በርተን ደግሞ አንዳንድ ተክሎች ስንመገባቸው ጭምር ድብርትና የማባረር አቅም ያላቸው ቢሆንም ተክሎቹን መመልከት በራሱ ድብርትን እና ጭንቀትን የማባረር አቅም አለው ይላል። እንግሊዛዊው የእጽዋት ተንከባካቢ ሞንቲ ዶን እንደሚለው በከፍተኛ ሁኔታ በድብርትና ጭንቀት ተሰቃይቶ ነበር። ነገር ግን እጽዋትን መትከልና መንከባከብ ከጀመረ በኋላ ግን ነገሮች እየቀለሉ መምጣታቸውን ያስታውሳል። ''አንድ ተክል ከተተከለበት ጊዜ ጀምሮ እድገቱን መመልከትና መንከባከብ ለጭንቅላት የሚሰጠው ትልቅ እረፍት አለ'' ይላል። 4. ችግራችንን ለሌሎች ማጋራት ''በውስጣችን የሚሰማንን ጭንቀትና ድብርት ለራሳችን ብቻ ይዘነውና ተሸክመነው ከመቆየት ይልቅ ለሌሎች ማጋራትና አብሮ መፍትሄ መፈለግን የመሰለ ነገር የለም'' ብሎ ነበር በርተን ከ400 ዓመታት በፊት። ጭንቀትና ድብርት የሚያጋጥማቸው ሰዎች ሁሌም ቢሆን ራሳቸውን ከሰዎች ለይተው መቀመጥ ይመርጣሉ። ነገር ግን መሰል ነገሮች እንደውም ጭራሽ ስቃዩን ያበዙታል። በቤተሰብ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩት ዶክተር ፍራንሲስ ራይስ እንደሚሉት ጭንቀት ሲገባን ከምንወዳቸውና ከሚወዱን ሰዎች ጋር ዘና የሚያደርግ ነገር ማድረግና ችግራችን በዚያው ለእነርሱ ማጋራት በጣም ወሳኝ ነው። ''ምናልባት ከሰዎች ጋር ብዙም ማውራት የማንወድ እንኳን ቢሆን ከሰዎች ጋር ለየት ያለ ነገር ማድረግ ጭንቅላታችን ትኩረቱን ወደ ሌሎች ነገሮች እንዲያደርግ ያግዘዋል'' ጭንቀትና ድብርት አሰቃየኝ ብሎ አንድ ሰው ሐኪም ጋር ቢሄድ ምናልባት ድብርትን የሚያስወግዱ በርካታ አይነት መድሀኒቶች ሊታዘዙ ይችል ይሆናል። ነገር ግን በአሁኑ ሰአት እንደ ዴንማርክ፣ ካናዳ እና ዩኬ ባሉ አገራት መሰል ችግር የሚያጋጥማቸው ሰዎች ከመድሀኒት ይልቅ ከሰዎች ጋር እንዲገናኙ፣ አዲስ ክህሎቶችን እንዲማሩ አልያም ተፈጥሮአዊ ቦታዎችን እንዲጎበኙ ነው የሚታዘዝላቸው። 5. ስራችንን እና ሕይወታችንን ማጣጣም ምናልባት በርተን ቃል በቃል ስራችንን እና ሕይወታችንን ማጣጣም ብሎ ላይሆን ይችላል። ነገር ግን አዲስ ነገር የመማር ፍቅር በሚል ገልጾታል። እንደውም ይህ የመማር ፍቅር በራሱ ከበዛ ችግር ሊሆን እንደሚችልም አስቀምጧል። በርተን እንደሚለው ሕይወታችንን የምንመራበት ስራን ለማሳካት አልያም ምርምር ለማድረግ ይሁን ሙሉ ትኩረታችንን እና ጭንቅላታችንን በሙሉ እዛ ላይ ባደረግን ቁጥር ራሳችን ላይ ተጨማሪ ጭንቀትና ድብርት እንጨምራለን። ሰዎች ስለስራቸው አብዝተው ሲጨነቁ እና ነገሮችን ለማስተካከል ሙሉ ጊዜያቸውን እዚያ ጉዳይ ላይ ባዋሉ ቁጥር ከሰዎች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት እየቀነሰ ይመጣል። የሚያስደስታቸውን ነገር ማድረግም ቢሆን ያቆማሉ። ምናልባት በርተን የሰዎችን አስተሳሰብ የተመለከተበትና ያጠናበት መንገድ ያረጀ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን እርሱ ተውሶ ያመጣቸው የግሪክ ፈላስፋዎች አስተሳሰብና ህክምናዎች አሁንም ድረስ ጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ ናቸው። ራስን ማወቅ፣ መዋኘት፣ ተፈጥሮ፣ ማህበረሰብ እና ማንበብ ከዛሬ 400 ዓመት በፊት ከሰሩ አሁን ላይ ለእኛስ የማይሰሩበት ምክንያት አለ? source -BBC News የስብዕና ልህቀት Join: @Human_Intelligence
显示全部...
👍 52 19🔥 3
አእምሮአችን እየተጠቀመብን ነው ወይስ እየተጠቀምንበት? አእምሮ መሳሪያ ነው። የምትጠቀምበት የሆነ አንድ የተለየ ተግባርን ትከውንበት ዘንድ ለአንተ የተዘጋጀ መሳሪያ፡፡ እናም ተግባሩ ተከውኖ ሲያልቅ የምታሳርፈው ድንቅ መሳሪያ (ማሽን) ነው። ከ80 እስከ 90 በመቶ ያህሉ የአብዛኛዎቹ ሰዎች ሀሳብ ተደጋጋሚ እንዲሁም የማይጠቅም እንቶ ፈንቶ ነው፡፡ ይህም ብቻም አይደለም አዕምሮ በተፈጥሮው ፈሩን የመልቀቅና አሉታዊ ነገሮች ጋር የመጠናወት አባዜ አለበት። እናም አዕምሮ ይህ አይነቱ ባህሪ ስላለበት የጥቅሙን ያህልም ጎጅነቱም የዚያኑ ያህል ነው። አዕምሮህን ልብ ብለህ አስተውለው እናም ይህ እውነት መሆኑን እራስህ ትደርስበታለህ። እንደ እውነቱ ከሆነ አዕምሮ የዚህ አይነቱ በሀሳብ የመጠመድ አባዜ ሱስ ይሆንበታል፡፡ ልክ እንደማንኛውም ሱስ አስያዥ ነገር አዕምሮም የማሰብና በሀሳብ የመባዘን ሱስ ይይዘዋል። ለመሆኑ የሱስ መገለጫዎች ምንድን ናቸው። እጅ ሰጥተሀል፣ ለመተውም አቅቶሀል፣ ለመተው አማራጭ እንዳለህ እንኳ አልታይህ ብሎሀል። ሱሡ ከአንተ የበለጠ ብርቱ የመሰለብህ ሆኗል። በተጨማሪም ሱሡ የውሽት የሆነ የደስታ ስሜትን ሰጥቶሀል፣ ውሎ አድሮ በስተመጨረሻ ስቃይ የሆነ ደስታ፡፡ ለመሆኑ ማሰብ ምን ሊፈይድልን ነው ከማሰብ ጋር ሱስየሚይዘን? ምክንያቱም አንተ ከአዕምሮህ ጋር እንዲሁም ከሀሳብ ጋር ተቆራኝተሀልና ነው። ማለትም አንተ ማንነትህን የምትረዳውና የምትመዘዉ ከአእምሮህ ውስጥ ከታጨቀ ፍሬ ሀሳብና ድርጊት ስለሆነ ነው፡፡ ምክንያቱም ማሰብ ካቆምኩ አከተመልኝ ብለህ ስለምታምን ነው፣ አስተዳደግህን ተከትሎ በተገራህበት ግለሰባዊና ባህላዊ አተያይ መሰረት በአዕምሮህ ውስጥ የማንነት ምስል ትፈጥራለህ፡፡ ይህንን ምስልም የእራስ ወዳዱ እኔነት የገዛ ራሱ መንፈስ ብለን ልንጠራው እንችላለን፡፡ ይህ የአዕምሮ ተግባራቱንም ያካትታል፡፡ እናም አዕምሮ ህልውናውን የሚያስቀጥለውም ያለማቋረጥ በማሰብ ነው። እራስ ወዳዱ እኔነት (Ego) የሚለው ቃል ትርጉም ከሰው ሰው ይለያያል፣ እኔ ግን ቃሉን እዚህ ላይ የምጠቀምበት እንዲህ በሚል አንድምታ ነው፤ በንቃተ ህሊና አልባነት ምክንያት ከአዕምሮ ጋር በተደረገ ፅኑ ቁርኝት የተፈጠረ የውሸት ማንነት። ለእራስ ወዳዱ እኔነት፣ ለእርሡ የአሁን ገዜ የሚባል ነገር የለም፤ ለእራስ ወዳዱ እኔነት አስፈላጊውና እግምት የሚገባው የባለፈውና የወደፊቱ ብቻ ነው። ሀቁ ግን ፈፅሞ የተገላቢጦሽ ሁኖ ሳለ፣ ይህንን የአሁን ግዜ አላስፈላጊ፤ የባለፈውና የወደፊቱ ግን አስፈላጊ እንዲሆን ያደረገው በእራስ ወዳዱ እኔነት ስልተ ዘዬ አዕምሮ ፈፅሞ ፈሩን እንዲስት ስለተደረገ ብቻ ነው። እራስ ወዳዱ እኔነት ሁልግዜም ቢሆን ግድ የሚለው የባለፈው ነው የባለፈውን ነፍስ ይዘራበታል፣ ምክንያቱም የባለፈው ከሌለማ አንተ ማን ቢሉህ ማነኝ ትላለህ? እራስ ወዳዱ እኔነት ህልውናውን ለማስጠቀጠል እራሡን ያለማሰለስ ከወደፊቱ ጋር ይተልማል እራሱንም ከወደፊቱ ትልም ውስጥ ያስገባል። እንዲሁም ደግሞ ስኬትን ወይም እፎይታን ከወደፊቱ ይሻል። ወይም ደግሞ አዕምሮ፣ እርሡው እራሡ ለወደፊቱ ለተለመው ትልም ውጤት ሲል የአሁን ግዜን ከቁብም የማይቆጠር ያደርገዋል። እስቲ አዕምሮህን ልብ ብለህ አስተውለው፣ እናም ይህ እንዴት እንደሚሠራ እራስህ ታየዋለህ፡፡ የአርነት መውጫን ቁልፍ የያዘው የአሁን ግዜ (የአሁን ቅፅበት) ነው፣ ነገር ግን አንተ አዕምሮህን እስከ ሆንክ ድረስ፣ ማለትም አዕምሮህ ማለት አንተ፣ አንተ ማለት አዕምሮህን እስከሆንክና ከአዕምሮህ ጋር እስካልተፋታህ ድረስ ይህን ቁልፍ አታገኘውም፡፡ እዚህ ላይ አንድ ማስተዋል ያለብን ነገር አለ፤ ይኸውም ማሰብና ንቃተ ህሊና አቻ ትርጉም የላቸውም ፤ አቻም አይደሉም፡፡ ማሰብ የንቃተ ህሊና ቁንፅል መገለጫው ነው፡፡ ማሰብ ያለ ንቃተ ህሊና ህልውና ሊኖረው አይችልም፤ ንቃተ ህሊና ግን ያለ ሀሳብ እራሱን ችሎ መቆም ይችላል። መገለጥ (የበራ ህይወት) ማለት ከሀሳብ ልቆ መገኘት ማለት ነው። መገለጥ ማለት ወደ ሀሳብ ደረጃ አለመቀልበስ ማለት ነው፡፡ ሁኖም ግን የእንስሳትና የእፅዋት ደረጃ ወደ ሆነው ከማሰብ በታች መውረድ ማለት አይደለም፡፡ የመገለጥ ሁናቴ ውስጥ መሆን ማለት አስፈላጊ በሆነ ጊዜ፣ የሚያስበውን አዕምሮህን መጠቀም ትችላለህ፡፡ እናም ደግሞ ስትጠቀምበትም ከበፊቱ ይልቅ በበለጠ አትኩሮትና ብቃት ትጠቀምበታለህ፡፡ ሁኖም ግን ከአንተ እውቅና ውጭ ለሚደረግ የአዕምሮ በሀሳብ መባዘንና ከአዕምሮ ውስጥ ውስጡን ማብሰልሰል ነፃ ነህ፡፡ እናም ደግሞ አንተ አዕምሮህንም ስትጠቀምም፣ ውስጣዊ መረጋጋትህም እንደተጠበቀ ሲሆን፣ በተለይ ደግሞ የሆነ አይነት የፈጠራ መፍትሔ በሚፈለግበት ወቅት በየጥቂት ደቂቃዎቹ አንድ ግዜ ወደ ማሰብ ሌላ ግዜ ደግሞ አዕምሮን ከሚላጋበትና በሀሳብ ከሚቆዝምበት ሁናቴው አውጥተህ እንዲሰክን እያደረግክ ስራህን ትከውናለህ፡፡ ማለትም አዕምሮ አለ፣ አዕምሮ የለም አይነት በነዚህ በሁለቱ መካከል አዕምሮህን በተገቢው መንገድ ትጠቀምበታለህ። አዕምሮ ሳይኖር ማለት ከሀሳብ ነፃ ሁኖ በንቃተ ህሊና ውስጥ መሆን ማለት ነው። በተጨማሪም አሪፍ የሆነ የፈጠራ ሀሳብ የሚፈልቅልህ በዚህ ሁናቴ ስታስብ ብቻ ነው፤ ምክንያቱም ሀሳብ የነጠረ አቅም የሚኖረው በዚህ መንገድ ብቻ ስለሆነ ነው፡፡ ሀሳብ ህልቆ መሳፍርት ከሌለው ንቃተ ህሊና ጋር ካልተሳሰረ ግን ብዙም ሳይቆይ ባድማ፣ የተቃወስ እንዲሁም አጥፊ ይሆናል፡፡ የመኖር ዋስትና አቢይ ማሽኑ አዕምሮ ነው። አዕምሮ ከሌሎት አዕምሮዎች ጋር በመፋለም፣ በመከላከል መረጃን ማግኘትና መተንተን የሚችለው አዕምሮ ነው። ሁሉም እውነተኛ አርቲስቶች አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት ፈጠራቸው የፈለቀው እንበለ አዕምሮ (አዕምሮ ሳይኖር) ውስጣዊ ርጋታና ስክነት ካለበት ከውስጥ ነው። ታላላቅ ሳይንቲቶች የሚባሉትም እንኳ የፈጠራ ስራቸው ከች ያለላቸው በአርምሞ ውስጥ ሁነው እንደሆነ ተናግረዋል። ምንጭ ፦ የአሁን ሀያልነት ደራሲ ፦ ኤክሀርት ቶሌ ትርጉም ፦ብስራት እውነቱ @Zephilosophy @Zephilosophy
显示全部...
👍 38 19
ፍቅርና ተቀባይነት! አንድ ሰው እንዲህ ሲል የተናገረው ትዝ አለኝ፣ “በሕይወታችን የምናደርጋቸው አብዛኛዎቹ ነገሮች ፍቅርንና ተቀባይነትን ለማግኘት ነው ወይም ላጣነው ፍቅርና ተቀባይነት ማካካሻ ፍለጋ ነው”፡፡ የሚገርም ምልከታ! ከዚህ በፊት በጣም የተጎዳችሁበትን ሁኔታ አስታውሱት፡፡ ከዚህ በፊት ከእናነት በራቁ ቁጥር የተከታተላችኋቸው ሰዎች አስቧቸው፡፡ በአሁን ወቅት ስሜታችሁን የረበሸውን ነገር አስቡት፡፡ በአሁን ወቅት ከአእምሯችሁ አልወጣ ስላለው ሰው አስቡት፡፡ በአሁን ወቅት የተነሳሳችሁለትን ድንገተኛ ውሳኔ አስቡት፡፡ አብዛኛውን ነገር ከፍቅርና ከተቀባይነት ፍለጋ ጋር ተያይዞ ታገኙታላችሁ፡፡ ሰው የሚረጋጋው ፍቅርንና ተቀባይነትን የመሆኑን ያህል፣ ሰው መረጋጋትን የሚያጣው ፍቅርና ተቀባይነትን ማግኘት ከማይችልበት ሰውና ስፍራ ያንን በመፈለግ ሲንገላታ ነው፡፡ ሰው የሚረጋጋው መወደድንና ተቀባይነትን የሚያስገኝ ባህሪይ ካዳበረ በኋላ ሰዎች የራሳቸው ምርጫ እንዳላቸው አምኖ ሲቀበል የመሆኑን ያህል፣ ሰው መረጋጋትን የሚያጣው ከሰዎች የሚጠባበቀውን ሁኔታ ሚዛናዊ አድርጎ ካልያዘው ነው፡፡   ሰው የሚረጋጋው ከማንም ሰውና ሁኔታ ውጪ መኖር እንደሚችል ውስጡን ሲያሳምነው የመሆኑን ያህል፣ ሰው መረጋጋት የሚያጣው የሸሸውንና ተቀባይነት የነፈገውን ሰው ሁሉ ሲከታተል ውሎ ሲያድር ነው፡፡ ሰው የሚረጋጋው ከምን አይነት ሰው ምን አይነት ፍቅርና ተቀባይነት እንደሚያገኝ ለይቶ ሲያውቅ የመሆኑን ያህል፣ ሰው መረጋጋትን የሚያጣው ከአንዱ ያጣውን ፍቅርና ተቀባይነት ከሌላ ሰው ለማግኘት ሲጦዝና ደረጃውን ዝቅ ሲያደርግ ነው፡፡ መልካም ቀን! ዶ/ር እዮብ ማሞ @Human_intelligence
显示全部...
👍 89 22🙏 6🤔 4
照片不可用在 Telegram 中显示
59👍 29👏 4🥰 1
የራእይ ጉልበት! ታዋቂው ጸሐፊ ስቲቨን (Stephen Covey)  First Things First በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ ስለአንድ ቪክቶር (Viktor Frankl) ስለሚባል የአውስትራያዊ የስነ-ልቦና ባለሞያ ታሪክ ይናገራል፡፡ ይህ የስነ-ልቦና ባለሞያ ከናዚ (ጀርመን) የሞት ካምፕ የተረፈ ሰው ነው፡፡ ቪክቶር በናዚ የሞት ካምፕ ውስጥ ታሽገው ከነበሩ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ በሞት ሲያልፉ አንዳንዶቹ ግን እንዴት ያንን ለሞት የሚዳርግ ሁኔታ አሸንፈው ሊወጡ እንደቻሉ በምርምር ደረሰበት፡፡ በጥናቱ ብዙ ነገሮችን ተመልክቷል - የጤንነታቸው ሁኔታ፣ የቤተሰባቸው ሁኔታ፣ ብልህነታቸው፣ ችግርን የመቋቋም ብቃት እና የመሳሰሉት፡፡ በመጨረሻ የደመደመው፣ ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዱም እንኳን ለእነዚህ ሰዎች በሕይወት መኖር ምክንያት እንደልሆነ ነበር፡፡ በዚያ ከባድ ሁኔታ ውስጥ በሕይወት የቆዩት ሰዎች አንድ የጋራ ነገር ነበራቸው፡፡ ይህ ነገር የወደፊት ራእይ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች በሕይወት የመኖርን ነገር ጠንክረው እንዲይዙ ያደረጋቸው ብቸኛውና ጉልህ የሆነው ምክንያት በፊታቸው ገና ያላከናወኑት ራእይ እንዳላቸው የማመናቸው ሁኔታ ነበር፡፡ ጸሐፊው እንደ ቬትናም እና የመሳሰሉት ብዙ የጦር ምርኮኞች በስቃይ በሚታጎሩባቸው ካምፖችም ውስጥም ተመሳሳይ ሁኔታ እንደታየ ይናራል፡፡ አሳማኝ እና ወደፊት ላይ ያተኮረ ራዕይ ብዙዎቹን በህይወት እንዲኖሩ ያደረጋቸው ዋና ሃይል ነበር (ምንጭ፡- Stephen Covey, First Things First, p 103)፡፡ •  አንድ ሰው የሚሞተው ጤናው ሲጠፋ ብቻ አይደለም … ራእይ ሲጠፋም ጭምር ነው! •  አንድ ሰው የሚከስረው ስራ ሲበላሽ ብቻ አይደለም … የራእዩ ሁኔታ ሲበላሽም ጭምር ነው! •  አንድ ሰው ብቸኝነት የሚሰማው ሰው ሲርቀው ብቻ አይደለም … ራእይ ሲርቀውም ጭምር ነው! •  አንድ ሰው ተስፋ የሚቆርጠው ሁኔታዎች አልታይ ሲሉት ብቻ አይደለም … ራእይ አልታይ ሲለውም ጭምር ነው! •  አንድ ሰው ውዳቂ የሚሆነው ስለወደቀ ብቻ አይደለም … ራእዩን ሲጥል ጭምር ነው! . . . እያለ እውነታው ይቀጥላል፡፡ ይህ እውነታ እንደሚያሳየን አንድ ሰው ምንም እንኳን በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ሲያልፍ የዚያን ሁኔታ ውጤት መቅመሱ ባይቀርም፣ የመጨረሻውን ውሳኔ ከሚያስተላልፉትና በብርታትና በደካማነት መካከል ከሚወስኑት ሁኔታዎች መካከል አንጋፋው ራእይ የመኖሩና ያለመኖሩ ጉዳይ ነው፡፡ አሁን ከምታልፉበት አስቸጋሪና ተስ አስቆራጭ ነገር ባሻገር እንድትሄዱ ሊያደርጋችሁ የሚችል ዋነኛው የፈጣሪ ስጦታ ራእይ ይባላል፡፡  ራእያችሁን አግኙና እሱን በመኖር አሁን ያለውን ከባድ ዘመን አሳልፉት! @Human_intelligence @Human_intelligence
显示全部...
👍 57 9😢 1
ቢራቢሮዎቹ ለምን ይሸሹኛል ??? !!! “ቢራቢሮዎችን በተከታተላችኋቸው ቁጥር ከእናንተ እየሸሹ ይሄዳሉ፡፡ እነሱን መከታተል ትታችሁ ግሩም የሆነና የሚያምር የአትክልት ቦታ ብትሰሩ ግን ራሳቸው ወደ እናንተ ይመጣሉ” ይባላል፡፡ ይህ አባባል እኛ በጥብቅ ከምናሳድደውና ከምንከታተለው ይልቅ በበለጠ ሁኔታ ማንነታችን ሰዎችንና ሁኔታዎችን ወደ እኛ የመሳብ ኃይል እንዳለው ጠቋሚ ነው፡፡ ምናልባት በውስጣችን ያለውን፣ ምልከታ፣ ዝንባሌና የአጠያየቅ ሂደት ብንለውጥ በተከታተልናቸው ቁጥር እየራቁን ከሚሄዱ ሁኔታዎች እንተርፍና በተለወጠው ማንነታችን ለእኛ የሚመጥኑ ነገሮችን መሳብ እንጀምራለን፡፡ “ቢራቢዎሮዎቹ በተከታተልኳቸው ቁጥር ለምን ይርቁኛል?” የሚለው ጥያቄ፣ “እኔ ለቢራቢሮዎቹ አመቺ ሁኔታን ለምን አልፈጠርኩላቸውም?” በሚለው መቀየር የግድ ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ . . .  “ሰዎች ለምን ሁል ጊዜ ይህንና ያንን ነገር ያደርጉብኛል?” የሚለው ጥያቄ፣ “እኔው ራሴው ለምን ሰዎቹ ደጋግመው ያንን ነገር እንዲያደርጉብኝ እፈቅድላእለሁ?” ወደሚለው ይቀየርልን፡፡ “ሁል ጊዜ ለምን ጥሩ እድል አይገጥመኝም?” የሚለው ጥያቄ፣ “ማግኘት የምፈልገውን ነገር ለምን በርትቼ በመስራት አላመጣውም?” ወደሚለው ይቀየርልን፡፡ “ሁኔታዎቼ ለምን አይለወጡም?” የሚለው ጥያቄ፣ “ለምን እኔ በሁኔታዎቼ ላይ ያለኝን አመለካከት አልለውጥም?” ወደሚለው ይቀየርልን፡፡ “ሰዎች ለምን አይወዱኝም፣ ለምንስ አይፈልጉኝም?” የሚለው ጥያቄ፣ “ለምን እኔ የሚወደድና የሚፈለግ ማንነትና ባህሪይ አላዳብርም?” ወደሚለው ይቀየርልን፡፡ የቀረውን ራሳችሁን በመቀየር ሁኔታችሁን መቀየር የምትችሉባቸውን ሌሎች ሃሳቦች ጨምሩበትና ወደለውጥ!!! ዶ/ር እዮብ ማሞ
显示全部...
👍 72 29🔥 3🤣 3
照片不可用在 Telegram 中显示
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለ2016 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል  በሰላም አደረሳችሁ። አዲሱ አመት የሰላም፤የፍቅር፤ የሰኬት አመት እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን !!
显示全部...
👍 44 21
እንኳን አደረሰሽ (ለኢትዮጵያ ) ከፀሀይ በታች፥  አዲስ ነገር ባይኖርም መልካም አዲስ አመት፥ ማለት  አናቆምም። ዘመን ባይለወጥ፥ አዲስ ቀን ባይወጣ ከድጥ ወደ ማጡ፥  ቢሆንም የኛ እጣ ። እንኳን አደረሰሽ ማለት አላቆምም በሚመሩሽ እንጂ፥ እኔ ባንቺ አላዝንም ። እንኳን አደረሰሽ እንደ አምና ፥ ካች አምና ፀሀይም ባትኖር፥ ሌሊትሽ ባይነጋ መላው መሬትሽም፥ ቢርስ በሰው እንባ ዘመን ቢተካካም፥   አዲስ ቀን ባይወጣ ። በእንጥፍጣፊ ተስፋ፥  ከልቤ በቀረው እንኳን አደረሰሽ ፥ ዛሬም እልሻለው። ኬቲኤል @Human_intelligence
显示全部...
🔥 44👍 41 21🙏 14😢 6🤔 4🤣 2👏 1
ሕይወት ሁለንተናዊ ነች! (ክፍል አንድ) በያዝነው የአመቱ የመጨረሻ ሳምንት ውስጥ ባሉት ቀናት በሕይወታችሁ ሁለንተናዊ ልህቀት ውስጥ ለመግባት የሚያስችላችሁን ሃሳቦች ስለማጋራች አብረን እንቆይ፡፡  በሕይወታችን ከምንሰራቸው ስህተቶች አንዱ፣ በአንድ ወይም በሁለት ነገር ከተሳካልን ሁሉም የሕይወታችን ሁኔታ መስመር እንደሚይዝ የማሰብ ስህተት ይገኝበታል፡፡ ይህ እሳቤ ባለንበት ዘመን ሰዎች እጅግ የተዛባ ሕይወት ውስጥ እንዲገቡ የዳረጋቸው አደገኛ እሳቤ ነው፡፡ ይህንን እውነት-መሰል፣ ነገር ግን ጎዶሎ እውነትን ያቀፈ እሳቤ ደግሞ በሕረተሰቡ መካከል ከምናየው የኑሮ እና የአነጋገር ዘይቤ፣ በማሕራዊ ሚዲያ ከሚራገበው ሃሳብ፣ እና እነሱ በሚገባ ሳይበስሉና ነገሩ በሚገባ ሳይገባቸው ሌላውን ለማነቃቃት ከሚሞክሩ አንዳንድ ሰዎች ልንቀዳው እንችላለን፡፡ ሕይወታችንን ዘርፈ-ብዙ በሆነ እድገት ደግፈን ሁለንተናዊ ልህቀት ውስጥ ለመግባት ከፈለግን ሁሉን የሕይወት ገጽታ መመልከትና በእያንዳንዳቸው ላይ መስራት የግድ ነው፡፡ ከዚህ በታች አነዚህን ዘርፎች ከመዘርዘሬ በፊት በቅድሚያ በአንድ ነገር እንስማማ፡፡ ከሁሉም በፊት ሊቀድም የሚገባው ከፈጣሪያችን ጋር ያለን ግንኙነት ጤናማ የመሆኑ ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ፈጣሪ የሰጠንን የዚህችን ምድር ሕይወት በምን ዓላማ ላይ እንደምታሳልፉት ራእያችንን የማግኘታችን ጉዳይ ነው፡፡ እሱን ካላገኛችሁ እሱ ላይ መስራታችሁን እርገጠኛ ሁኑ፡፡ ራእያችሁን ካገኛችሁት በኋላ ያንን በመያዝ ወደ ሁለንተናዊ ልህቀት ለመግባት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የሕይወት ዘርፎች ላይ መስራትና መጠናከር የግድ ነው፡፡ ከእነዚህ የአንዱ መጉደል ሌላውን ይዞት እንደሚወርድና አልፎም ራእያችንን ለማሳካት እንቅፋት እንደሚሆን ማስታወስ ጠቃሚ ነው፡፡  1.  የስሜት ገጽታ ይህ ሃሳብ የሚጠቁመኝ በስሜት ብልህነት የመብሰሌና ስሜቴን በትክክለኛው ቦታ፣ ጊዜና መጠን የመጠቀሜ ጉዳይ፡፡ ራእይን በማወቅም ሆነ በሌሎች ዘርፎች ልቀን ብንገኝም እንኳን ያልተረጋጋና የተቃወሰ ስሜት ካለን ገዞው አዳጋች ይሆንብናል፡፡ 2.  አካላዊው ገጽታ ይህ ሃሳብ የሚጠቁመኝ ስጋዊ አካሌ እድሜዬን በሚመጥን ጤንነት እንዲቆይ በአካላዊ እንቅስቃሴ፣ አመጋገብና በመሳሰሉት ነገሮች የመጠበቁ ጉዳይ፡፡ የተሸከምነውንና የምንከተለው ራእይ ይዘን ወደፊት ለመቀጠል አካላዊ ጤንነታችን ከሁሉም ዘርፎች እኩል አስፈላጊ ነው፡፡  3.  ማሕበራዊው ገጽታ ይህ ሃሳብ የሚጠቁመኝ በቤተሰብና በማሕበረሰብ ግንኙነት ዙሪያ ጤናማ፣ ሰላማዊና ሚዛናዊ ሕይወት የመመስረቴ ጉዳይ፡፡ ማንኛውም ራእይና ሌሎችም አጋዥ ዘርፎች ሙሉ ሆነው ሳለ ማሕበራዊ ብልህነት ከጎደለን ከቀውስ አናመልጠም፡፡ 4.  የአእምሮው ገጽታ ይህ ሃሳብ የሚጠቁመኝ በአንድ ጎኑ በመደበኛ ትምህርት ወይም መደበኛ ባልሆነ መልኩ አእምሮዬን ካለማቋረጥ በእውቀት የማሳደጌን ጉዳይ ሲሆን፣ በሌላ ጎኑ ደግሞ የአመለካከቴን (Mindset) ጤናማነት ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የሚጎዱንና ወደኋላ ሚጎትቱን ነገሮች መስካችን የሚፈልገውን ነገር በሚገባ ካለማወቅ የተነሳ እና የምልከታችን መዛባት ነው፡፡ 5.  የፍቅር ሕይወት ገጽታ ይህ ሃሳብ የሚጠቁመኝ በፍቅር ግንኙነት፣ በትዳር ሕይወት ወይም ደግሞ ከሁለቱም ውጪ ለብቻ በመኖር ሕይወት ጤናማ ሂደት ውስጥ የመግባቴን ጉዳይና ሚዛናዊ ምልከታ የማዳበሬን ጉዳይ ነው፡፡ በማፍቀርና በመፈቀር፣ በትዳርም ሆነ ከእነዚህ ልምምዶች ውጪ “ለብቻ” በመኖር ሂደት ውስጥ ያለኝ እርካታና ብስለት ለጉዞዬ ወሳኝ ነው፡፡ 6.  የገንዘብ ገጽታ ይህ ሃሳብ የሚጠቁመኝ ገንዘብን በትክክለኛው መንገድ በማግኘት፣ በማባዛት፣ በመጠቀም፣ በማጠራቀምና በመሳሰሉት ዘርፎች የመብሰሌን ጉዳይ ነው፡፡ ማንኛውንም የላቀ ነገር ለማከናወን ገንዘብ ትልቅና ወሳኝ ድርሻ እንዳለው በማስታወስ በዚህ ዘርፍ ለማደግ መስራት አስፈላጊ ነው፡፡ ፈጣሪ እንኳን ለአመቱ የመጨረሻ ቀናት አደረሳችሁ! ዶ/ር እዮብ ማሞ @Human_intelligence @Human_intelligence
显示全部...
👍 44 11
Repost from TgId: 1163708603
በስቃይ ውስጥ ትርጉም መፈለግ - ፍራንክሊ ስቃይ አይቀሬ የሆነ የሕይወት ክፍል ነው፡፡ ምናልባትም እድለኛ ከሆንክ የፍቅረኛህ ጥላህ መሄድ፣ ለሁለት ወራት ታሞ መተኛት አልያም ሌላ ቀላል መሰቃየቶችን ታሳልፋለህ፡፡ ከዚህም ሲከፋ የምትወደውን የቅርብ ሰው በሞት ታጣለህ። ዶስቶየቭስኪ “ሰው በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ቢሆንም ከሁኔታው ጋር ተላምዶ የሚኖር ፍጡር ነው” ሲል ጽፏል። ኦስትሪያዊው ሳይኮሎጂስት ቪክተር ፍራንክል፤ በኦሽዊትዝ ማጎርያ ውስጥ በናዚዎች ከመገደል የተረፈ ነው፡፡ በ1946 Man's search for meaning የተሰኘውን እና አሁንም ድረስ በስፋት የሚነበበውን መጽሐፍ አሳትሟል፡፡ ፍራንክል ሰዎች ለስቃያቸው ትርጉም ከሰጡት፣ ስቃዩን የመሸከም አቅም ያገኛሉ ይለናል፡፡ ከዚህ በላይ ይህንን ስቃይ መሸከም አልፈልግም የምንለውም... በውስጡ ትርጉምን ስናጣበት ነው። ኒቼም፤ “ለምን እንደሚኖር ያወቀ፣ በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥም ቢሆን ይኖራል” ሲል ጽፏል። ብዙዎቻችን በስቃያችን ላይ ትርጉምን እንፈልጋለን፡፡ “ምን አሰቃየኝ? ምን አንገላታኝ?” እያልንም እንጠይቃለን፡፡ ለራሳችን ብቻ ትርጉም የሚሰጡን ምክንያቶችንም እንፈልጋለን፡፡ ፍራንክል ሕይወት ለእያንዳንዳችን የምትጠይቀን ጥያቄዎች አሏት፤ እኛም የእኛ ብቻ የሆነ መልስን እንሰጣታለን ሲል ጽፏል፡፡ የሕይወት መንገድህ ምን መሆን እንዳለበት የተጻፈ መመሪያ የለም፤ እናም ሁላችንም የሕይወት ነበልባል እየለበለበንም ቢሆን መኖራችንን ለምን እንደምንቀጥል የሚገልጽ የራሳችን የሆነ መልስ ይኖረናል። ፍራንክል ምሳሌ ይሰጣል፡፡ አንድ ሚስቱ የሞተችበት ባል፣ ስቃዩ ሲበረታበት እራሱን እንዲህ ይጠይቀዋል፤ “እኔ ሞቼ እርሷ በሕይወት ኖራ ቢሆንስ?” ወዲያውም ለስቃዩ ትርጓሜን ያገኛል፡፡ እርሱም አሁን እየተሰቃየ ያለው በሞተችው ሚስቱ ምትክ እንደሆነ ያስባል። እኔ ብሞት እና እርሷ በሕይወት ቆይታ ቢሆን ሃዘኑን አትችለውም ነበር ሲል ያስባል፡፡ የእርሱን ስቃይ አላስወገደውም፤ ሆኖም በስቃዩ ውስጥ የሚያኖረውን ትርጉም አገኘ፡፡ ብዙዎቻችን ስቃይን ከሕይወታችን ጠርገን ለማስወጣት እንሞክራለን፤ ሆኖም ይህ በስቃይ ውስጥ ትርጉም መፈለግ አይደለም። ስቃይ የእኛን ማንነት ቀጥቅጦ ይሰራዋል። ልክ እንደ አንጥረኛ የእኛን ነፍስም ቀጥቅጦ ይሰራታል፡፡ ፍራንክል ዘመናዊው ዓለም በስቃይ ውስጥ ትርጉምን ስለ ማግኘት ግድ የለውም ይለናል፤ የብዙዎቻችንም አርዓያዎች በስቃይ ውስጥ ያለፉ ሰዎች እንጂ በስቃይ ውስጥ ደስታቸውን የሚያገኙት አይደሉም። ከጎርፉ የተረፉት እንጂ በጎርፉ ውስጥ ደስታን የሚያገኙትን አናያቸውም፡፡ ስቃይን ከላይ ሆነን ስናየው የሕይወታችንን ደስታ የሚቀማን ሆኖ ይሰማናል፤  ‌ ሆኖም ያለ ስቃይ እና ሞት ሕይወት ሙሉ አይሆንም፡፡ ስቃዮቻችን ሕይወታችን ትርጉም እንዲኖረው ያስችሉታል፡፡ ስቃይ አልባ ሕይወትም ጣዕም የለውም፡፡ እናም በስቃይ ውስጥ በኩራት ልንራመድ የተገባ ነው፡፡ ምንጭ ፦ ፍልስፍና (ከዘርዐያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ) ዝግጅት ፦ ፍሉይ አለም @Zephilosophy @Zephilosophy
显示全部...
👍 40 4🔥 2
በቀለኛ አስተሳሰብ ያላቸው ፥ ይቅር ባይ መሆን የማይፈልጉ ሰዎች ቢያንስ በአደባባይ ስለሃይማኖት ባያወሩ ደስ ይለኛል። ቂመኛ ሆኖ ስለፈጣሪ የሚያወራ ሰው ግብዝ ነው! ከብሔራቸው አጥር የማይወጡ ጭፍኖች ፥ ለሌላው ወገን ጥላቻ ያላቸው ፥ እያንዱንዱን ጉዳይ በዘር መነፅር የሚመዝኑ፥ ለሌላው ሃጢያት ያሉትን ለነሱ ነገድ ሲሆን እንደ ፅድቅ የሚመለከቱ ዘረኞች በአደባባይ ስለሃይማኖት ባይወሩ ሸጋ ይመስለኛል። ጭፍን ብሔርተኛ ሆኖ ስለፈጣሪ የሚያወራ ሰው ግብዝ ነው ! ሁሉም ሃይማኖት መሰረታዊ አስተምህሮ አለው። አማኝ በተቻለ መጠን ለእምነቱ እሴት የሚታመን ቢሆን መልካም ነው። በግልፅ የሃይማኖትን እሴት የሚፃረር ፥ ከእምነቱ ትምህርት ተቃራኒ የሆነ ሰው እንደ ሃይማኖተኛ ሆኖ ድራማ የሚሰራው ማንን ለማታለል ነው? ራሱን ይሸውዳል ወይስ ተመካቹን ይሸውዳል? ወይስ 'አምነዋለሁ' የሚለውን ፈጣሪ ለማታለል እየሞከረ ነው ? ተስፋበአብ ተሾመ @Human_intelligence
显示全部...
👍 47👏 6 5
🌿#አንጀት_አርስ_እውነታ! ከ150 አመት በኋላ ዛሬ በህይወት ካለነው ሰዎች አንዳንችም በህይወት አንገኝም፡፡ዛሬ ላይ ከምንታገልላቸው ነገሮች 70 በመቶ የሚሆኑት ከ150 አመት በኋላ አንዳቸውም ለምልክት እንኳ አይገኙም፡፡ፈጽመው ይጠፋሉ ይረሳሉ፡፡ እስኪ ወደ ኋላ 150 አመት እንሂድ፡፡ወቅቱ 1872 ገደማ ነው የሚሆነው፡፡ያኔ የሰው ልጅ እንደ እቃ በአደባባይ ተደርድሮ የሚሸጥበት ወቅት ነበር፡፡በወቅቱ ብርቅ የነበረውን የፊት መስታወት ለማግኘት ሲሉ የገዛ ዘመዶቻቸውን የሸጡ ሰዎች ዛሬ የታሉ? መስታወትንስ ዛሬ ላይ እንደ ሀብት የሚያስበው ማን ነው? ማንም፡፡ጨው ወይም ጌጥ ወይም ሌላ ነገር ለማግኘት ሲሉ የተሻሻጡ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡ዛሬ ላይ እነዚያ ሰዎች የሞቱላቸው የገደሉላቸው የተካካዱባቸው የተሻሻጡላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ይህ ነው የሚባል የረባ ዋጋ ያላቸው አይደሉም፡፡በጊዜው ግን ለሰው ልጅ የሞትና የህይወት ልዩነት ነበሩ፡፡የሰው ልጅ በየጊዜው የሚታገልላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ዛሬ ላይ ዞር ተብለው ሲታዩ በጣም የሚያስቁ ናቸው፡፡ አስታውሳለሁ ፥ የሀይስኩል ተማሪ እያለሁ የትምህርት ቤቱ ፌመስ ለመሆን ብዙ ነገር አደርግ ነበር፡፡ዛሬ ከጥቂት አመታት በኋላ እንኳን ያኔ የነበረኝ ዝና ፥ በትምህርት ቤቱ መማሬንም የሚያስታውስ ሰው የለም፡፡አስቡት የዛሬ 150 አመት ደግሞ … ጭራሽ ትምህርት ቤቱም ላይኖር ይችላል፡፡ አሁን አሁን ላይ ዘመኑ የኢንተርኔት በመሆኑ ኢንተርኔት ትዝታችንን ያስቀምጥልናል ብለን እናስብ ይሆናል፡፡ግን እስኪ በዚህ ዘመን እንኳ ዝነኛ የሆኑትን እናስታውስ፡፡ማይክል ጃክሰን በጊዜው ዝነኛ ነበር፡፡ነገር ግን ከሞተ ገና ሁለት አስርት አመታት እንኳ ሳይሞላው እየተረሳ ነው፡፡ዛሬ ላይ ካለው ትውልድ ማይክልን የሚያስታውሰው በጣም ጥቂቱ ነው፡፡እሱንም ገና ካወቁት ነው፡፡ ከ150 አመታት በኋላ ደግሞ ማይክል ጃክሰን የሚለው ስም ጨርሶ ለማንም የማይታወቅ ይሆናል፡፡ ማጠቃለያው፥ ህይወትን ቀለል አርገህ ኑር፡፡ምንም ሆነ ምንም ዘላለም የሚኖር የለም፥ ከዚህች ምድር በህይወት የሚወጣ ሰውም የለም፡፡ዛሬ ልትሞትለት እና ልትገድልለት የተዘጋጀኸው መሬት ከዚህ ቀደምም ብዙዎች ተጋድለውለት ሞተው ጭራሽ እንዳልነበሩ ሁሉ ተረስተዋል፡፡ከ150 አመታት በኋላ ዛሬ አንተ እንደ ትልቅ ሀብት የምታያቸው አብዛኞቹ ነገሮች ምንም ፋይዳ የሌላቸው ተራ ቁሶች ይሆናሉ፡፡ እና ምን ለማለት ነው ፥ ፍቅር ይግዛን ፥ መጠላለፍ ከጀርባ መወጋጋት መቀናናት መፎካከር ይቅርብን፡፡ህይወት ከማንም ጋር የምታደርገው ፉክክር አይደለችም፡፡ቀደምንም ዘገየንም መጨረሻችን መቃብር ነው፡፡ @Human_intelligence
显示全部...
65👍 44🔥 3
እንዳያይ ሳይሆን እንዳያተኩር - የትኩረት ቁልፍ (ክፍል ሁለት) (“25 የስኬት ቁልፎች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ) . . . ካለፈው የቀጠለ በትናንትናው “ፖስቴ” በሕይወታችን የትኩረትን አስፈላጊነት ተመልክተናል፡፡ የትኩረትን አስፈላጊነት ከተማመንን፣ የሚቀጥለው ጥያቄ፣ “ስኬታማ ለመሆን የሚያስችለኝን የትኩት ጥበብ እንዴት ላዳበር?” የሚለው ነው፡፡  የሚከተሉትን ሶስት ምክሮች እለግሳለሁ፡- 1.  በሚሳካልህ ነገር ላይ አተኩር ብዙ ሰዎች የሚሳካላቸው ነገር ላይ ከማተኮር ይልቅ የማይሳካላቸው ጉዳይ ላይ ማተኮር ይመርጣሉ፡፡ መሆን የሚገባው ግን የማይሳካልንን ነገር ተወት በማድረግ የሚሳካልን ላይ መገንባት ነው፡፡ ከልጅነታችን ጀምሮ ሰዎች ያልተሳካልንና ያታገለን ነገር ላይ ነው ሃሳብ ሲሰጡን ያደግነው፡፡ ቤተሰቦቻችን ጥሩ ውጤታችንን አይተው ከሚያመሰግኑን ይልቅ መጥፎ ውጤት ሲመጣ የሚቆጡን ይበዛል፡፡ ይህ ሁኔታ ትኩረታችን ያልተሳካው፣ የሚያታግለንና አልሆን ያለን ላይ እንዲሆን በውስጣችን ዝንባሌን ፈጥሮአል፡፡ ይህ ዝንባሌ መወገድ አለበት፡፡ ወፍ የሚቀናት በአየር ላይ ስትበር ነው፣ አሳ የሚሆንለት በውኃ ውስጥ ሲዋኝ ነው፣ ፈረስ የሚሳካለት በምድር ላይ ሲገሰግስ ነው፡፡ እነዚህ ፍጥረቶች በአንድም ሆነ በሌላ ጊዜ ያኛውን ሞክረውት ቢያውቁም ብዙ ጊዜአቸውን የሚያጠፉት ግን የሚችሉበትን ደጋግሞ በማድረግ ነው፡፡ የአንተም ሁኔታ ከዚህ አይለይም፡፡ የማትችለውን አልፎ አልፎ ሞክር፣ ትኩረትህን ግን በሚቀናህና ውስጥህን በሚያነሳሳው ላይ መጣል አለብህ፡፡ “በዚህ አለም ላይ የአንተን ችሎታ ሊጠቀም የሚችል አንድ ሰው ብቻ ነው፣ እሱም አንተው ነህ” - Zig Ziglar አንተ ጋር ያለውን ብቃት ልትጠቀምበትና ልታሳድገው የምትችለው አንተው ብቻ ነህ፡፡ ሌላው ሰው በተጋው ትጋት የአንተ ብቃትና ማንነት ሊዳብር አይችልምና፡፡ አንድ ሰው ሌላኛው ሰው በሰራው ስፖርት ተጠቅሞ ጡንቻውን ማዳበር እንደማይችል ሁሉ አንተም የራስህን ብቃት አንተው ነህ ማዳበር ያለብህ፡፡ ብቃትህን በሚገባ በማወቅ በዚያ ላይ እንድታተኩር ካስፈለገ ደግሞ ራስህን ማወቅ የግድ ነው፡፡ አንተነትህን ከራስህ በበለጠ ሁኔታ ሊያውቀው የሚችል ሌላ ሰው የለም፡፡ ይህንን ማንነትህን በሚገባ ወደማወቅ ስትመጣና የሚሳካልህን ከማይሳካልህ ስትለይ ትኩረትህ የጸና ይሆናል፡፡ ይህ ሁኔታ ትንሽ ጊዜ ልፋት የሚፈልግ ቢሆንም እንኳ ብዙ ሳትቆይ ትርፋማና ስኬታማ የሚያደርግህን ነገር ስታከናውን ራስህን ታገኘዋህ፡፡ 2.  በየቀኑ በሚሳካልህ አንጻር ገንባ በየእለቱ የምታስበው፣ የምትተገብረው፣ የምታነበውም ሆነ የምታቅደው ነገር ከሚሳካልህና ከአላማህ አንጻር ሊሆን ይገባዋል፡፡ አስተማሪ ከሆንክ በምታስተምረው ነገር ዙሪያ በየቀኑ እውቀትን መሰብሰብ አለብህ፡፡ ምናልባት ወደፊት መሆን የምትፈልገውና በልቦናህ እንደ እሳት የሚንበለበል ነገር ካለ፣ ትኩረትህን በዚያ ዙሪያ እንደማድረግ ለስኬት ቅርብ የሚያደርግህ ነገር የለም፡፡ ለምሳሌ፣ ለማወቅ በምትጓጓበት ነገር ላይ በቀን አንድ ምእራፍ ማንበብ ብትጀምር፣ በአንድ አመት ውስጥ የሚኖርህን እድገት መገመት አያስቸግርም፡፡ ይህ አይነቱ ትኩረት ነው ከአማካኙ ሕዝብ ቀደም እንድትል የሚያደርግህ፡፡ “ችሎታ ማድረግ የምትችለውን ብቃትህን ያሳያል፡፡ መነሳሳት ብቃትህን በተግባርየማዋልህን ሁኔታ ይወስናል፡፡ ዝንባሌ ግን የተግባርህን ጥራት ይወስናል” – Lou Holtz ችሎታ ብቻውን ምንም እንደማያደርግልህ እወቅ፡፡ ችሎታ አንድን ነገር የማድረግ ብቃቱ እንዳለህ ብቻ አመልካች ነው፡፡ አስገራሚ ችሎታ ያላቸው፣ ነገር ግን ለምንም ጥቅም የማይውሉ በርካታ ሰዎች እንዳሉ አትዘንጋ፡፡ በችሎታህ ላይ መነሳሳትንና ጽኑ የስሜት ግለትን ልትጨምርበት ይገባል፡፡ ያለህን መነሳሳት በማዳበርና በየቀኑ አንዲትን ነገር በማድረግ ከወራትና ከአመታት በኋላ የተጠራቀመንና የተገነባን ነገር ማግኘት ትችላለህ፡፡ መነሳሳት ችሎታህን በተግባር ላይ እንድታውለው ሲረዳህ፣ ዝንባሌህ ግን የምታደርገውን ነገር በምን አይነት “መንፈስ” እንደምታደርገው ይወስናል፡፡ ይህ እጅግ አስፈላጊና ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ ምንም አይነት ችሎታ ቢኖርህና ለመተግበርም ያለህ መነሳሳት የላቀ ቢሆንም እንኳ፣ ዝንባሌህ የደስታ፣ የመጓጓትና በይሆናል የተሞላ ካልሆነ መጨረሻው አያምርም፡፡ ስለዚህ፣ አዎንታዊ ዝንባሌ ይኑርህ፡፡ 3.  ከአላማህ በፍጹም አትላቀቅ በቀላሉ ሃሳብህንና አቋምህን የምትለዋውጥ ሰው አትሁን፡፡ ከማንነትህ አንጻር እንጂ “ከሚያበላው” አንጻር ለመገንባት አትነሳ፡፡ የአንተ የወደፊት ያለው ከማንነትህ ጋር እንጂ በአለም ላይ ከሚያበላው የጊዜው ገበያ ጋር አደለም፡፡ ባለህበት ዘመንና በምትኖርበት ሃገር “ያበላል” በሚባለው ነገር ውስጥ እንኳ ሳይቀር አንተነትህንና ዝንባሌህን የሚያስተናግድ ክፍተት አለ፡፡ የገንዘብ አያያዝ ብልሃት በውስጥህ እያለ፣ ንግድ ያበላል ስለተባለ ብቻ ነጋዴ ለመሆን መነሳት መሳሳት ነው፡፡ በምትኩ ገንዘባቸውን በቅጡ መያዝ ለማይችሉ ነጋዴዎች የገንዘብ አያያዝን መፍትሄ ልታቀርብ ትችላለህ፡፡ ይህ እውነት በጊዜው ያለህ የኑሮ ሸክም አንገብጋቢ ሲሆን የማይታሰብ ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም፣ ለጊዜው ያለብህን የኑሮ ውጥረት ለማስተንፈስ ከአንተነትህ ጋር የማይፈስስ ነገር ብታደርግም፣ ውስጥህ ግን በፍጹም ከዋናው አላማህ መለያየት የለበትም፡፡ “ታላላቅ ስራዎች የሚከናወኑት በታላቅ ጉልበት ሳይሆን ሳያቋርጡ በመስራት ነው” –Samuel Johnson ውጤት የምታገኘው በአንድ ጊዜ ባንጠባጠብከው የላብ ብዛት አይደለም፤ ካለማቋረጥና ውጤት እስከምታገኝ ድረስ በተገበርከው ተግባር እንጂ፡፡ አንድን ነገር ለማግኘት መመኘትም ስኬት አይሰጥህም፡፡ በቅድሚያ በልብህ የሞላውንና ያመንክበትን ነገር ለመጀመር የቆረጥክ የመሆንህ ጉዳይ አስፈላጊ ነው፡፡ በመቀጠልም ያንን የጀመርከውን ነገር እስክትጨርስ ድረስ በተግባርህ መጽናት አለብህ፡፡ ከዚያም የጀመርከውን ነገር ላለመጨረስ ምንም ምክንያት አትስጥ፡፡ የስኬት ነገር የሚወሰነው የሕይወት ተራራን በምን ያህል ጉልበት እንደገፋህ ብቻ አይደለም ለምን ያህል ጊዜ በጽንአት እንደገፋህ ነው፡፡
显示全部...
👍 46 4🔥 3🤔 1
የብቸኝነትንና ብቻ የመሆንን ልዩነት እወቅ (ክፍል ሁለት) (“ራስን ማሸነፍ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ) . . . ካለፈው የቀጠለ በትናንትናው “ፖስቴ” ለብቻ መሆን ማለት ብቸኝነት እንደሆነ የማሰብን ሁኔታ እና ስህተት ተመልክተናል፡፡ የዛሬው ሃሳብ የሚያተኩረው ይህንን አመለካከት እንድናዳብረ የሚያደርጉንን አመለካከቶች በመለየትና ሁኔታውን ካልቀረፍነው የሚያስከትለው መዘዝ ላይ ነው፡፡ መንስኤው 1.  ባህላዊ ተጽእኖ ከሃገራችን መልካም ባህሎች አንዱ ማሕበራዊ ግንኙነታችን መሆኑን ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡ ከሰው ጋር ወጥተን፣ ከሰው ጋር እንገባለን፡፡ ስንበላ ከሰው ጋር ነን፣ ስንዝናና ከሰው ጋር ነን፣ በስራ መስክ ከሰው ጋር ነን፣ ከስራ ወጥተን ወደቤት ስንሄድ ከብዙ ሰው ጋር ነን፡፡ እቤትም ቢሆን ብዙ ሰው ነው የሚጠብቀን፡፡ ይህንን መልካም ባህል ተቀብሎ ያደገው ማንነታችን ሁኔታውን ሚዛናዊ ካላደረገው ለብቻ መሆንን እንደ ማሕበራዊ ቀውስ የማሰብ ዝንባሌ ሊኖረው ይችላል፡፡ በግርግር ውስጥ ተወልዶ በዚያው አይነት ግርግር ውስጥ ያደገ ሰው ከዚያ ውጪ ሌላ አለም እንዳለ ላያውቀውም ይችላል፡፡ ከዚያም በተጨማሪ ለብቻው ሲታይ፣ “ምነው ብቻህን?” የሚል ሃሳብ በሰዎች ሲነገረው ይህ ሰው የሚያዳብረውን አመለካከት መገመት አያዳግትም፡፡ 2.  ከህሊና ወቀሳ የመዳን ሙከራ ማንኛውንም በሕይወታችን የማንፈልገውን አጉል ስሜት ለማስወገድ የተለያዩ መንገዶችን የመጠቀም ምርጫው አለን፡፡ የህሊና ወቀሳም ሲኖርብን ከዚያ ወቀሳ ለመዳን በትክክለኛው መንገድ ስህተታችንን አስበንና ትክክለኛውን እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ከአንዱ ግርግር ወደሌላኛው በማለፍ “በመንጫጫት” ለመርሳት እንሞክራለን፡፡ እውነተኛው ችግር በውስጠኛው ማንነታችን ተንሰራፍቶ እየጮኸ፣ ከውጪ ያለውን የድምጽ መጠን በመጨመር ለጊዜው የውስጠኛውን ጩኸት የማንሰማበትን ሁኔታ እንፈጥራለን፡፡ ይህ ሙከራ ለጊዜው ልክ እንደማደንዘዣ መድኃኒት ቢሰራልንም ዘላቂ መፍትሄ ግን አይሰጠንም፡፡  3.  የራእይ አለመኖር ባለራእዮች ካላቸው አስገራሚ ባህሪይ አንዱ ለብቻቸው በመሆን ስለራእያቸው ማሰብ፣ ማቀድና ከራሳቸው ጋር መወያየት ዋነኛው ነው ብንል አንሳሳትም፡፡ አንድ ሰው በቅጡ ለማሰብና ለማቀድ ለብቻመሆንን የሚጠይቅ ራእይ ከሌለው በየእለቱ ብቅ ስላለው ክስተት ለማውራት ከዚህና ከዚያ ሲራወጥ ራሱን ያገኘዋል፡፡ አአምሮው ላይ የከበደ የወደፊት እቅድ ስለሌለው ያንን በራእይ ሊሞላ የሚገባውን ባዶ ቦታ የሚሞላ ሚዛነ-ቢስ ማህበራዊ ትርምስ ውስጥ ራሱን ያገኘዋል፡፡ እውነታው አጭርና ግልጽ ነው - ራእይ ያላቸው ሰዎች ለብቻቸውመሆን የሚናፍቃቸው ሰዎች ሲሆኑ፣ በተቃራኒው ራእየ-ቢሶች ደግሞ ብቻ መሆንን እንደብቸንነት የመቁጠር ዝንባሌ አላቸው፡፡ በግርግር ውስጥ ተወልዶ በዚያው አይነት ግርግር ውስጥ ያደገ ሰው ከዚያ ውጪ ሌላ አለም እንዳለ ላያውቀውም ይችላል፡፡ መዘዙ 1.  ውጤታማ አለመሆን ለብቻው የማይሆን ሰው ለማሰብ ጊዜ ያጣ ሰው ነው፡፡ ለማሰብ ጊዜ ያጣ ሰው ደግሞ በመጀመሪያ የትናንትናውን ጉዞ የመገምገሚያ ጊዜ ያጣል፡፡ ይህ የግምገማ ጊዜ የሌለው ሰው ከስህተቱ የማይታረም ሰው ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ለነገው የሚረዳውን የፈጠራ ብቃቱን የተነጠቀ ሰው ነው፡፡ ከፈጠራ ብቃት ውጪ ደግሞ የወደፊት ውጤታማነት የሕልም ጉዳይ ነው፡፡ለብቻ በመሆን የማሰብ እድል ከየት እንደመጣን፣ የት እንዳለን፣ ወደ የት መሄድ እንደምንፈልግና በምን መልኩ ወደዚያ መድረስ እንደምንችል ለማሰላሰል ጊዜ ይሰጠናል፡፡ ይህንን የግል ጊዜ ማጣት ማለት ለስኬታማነት ያለንን እድል መነጠቅ ማለት ነው፡፡ ከዚህ መሰረታዊ ልማድ ውጪ ወደተሻለ ቦታ ያደገ ሰው አለ ብሎ ለማሰብ አስቸጋሪ ነው፡፡ 2.  የአእምሮ መታወክ ቀኑን በጫጫታና በግርግር ጀምሮ በዚያው ሁኔታ የጨረሰ ሰው የሌሊት ሕልሙም ከዚያው የተለየ እንደማይሆን መገመት አያስቸግርም፡፡ ይህ ለአእምሮ እረፍት የሚያሳጣ ሁኔታ የሚፈጥረውን መታወክ የምናውቀው አረፍ ብለን ለማሰብ ጊዜ ስናገኝ ነው፡፡ ተቃራኒውን የተረጋጋ የሕይወት ዘይቤ ቀምሰነው ካላወቅን ከለመድነው የሁከት ዘይቤ ውጪ ያለ አይመስለንም፡፡ አንድን ጣፋጭ ጣእም ከዚህ በፊት ቀምሶ የሚያውቅ ሰው ብቻ ያንን ጣእም በድጋሚ ይፈልገዋል፡፡በጸጥታ ውስጥም የሚገኘውን የአእምሮ መረጋጋትና የትኩረት ብቃት የቀመሰ ሰው ብቻ ደግሞ ደጋግሞ ይፈልገዋል፡፡ 3.  የትክክለኛ ውሳኔ ችግር ሕይወት በውሳኔ የተሞላች ጉዞ ስለሆነች በየእለቱ የተለያዩ ውሳኔዎችን ከመወሰን አናመልጥም፡፡ ከእነዚህ ውሳኔዎች መካከል አንዳንዶቹ የኑሮአችንን አቅጣጫ ሊለውጥ የሚችል ተጽእኖ አላቸው፡፡ ለእነዚህ ውሳኔዎች ትክክለኛነት መዋጮ ከሚያደርጉ ልምምዶች አንዱ ለብቻ የመሆንና ሁኔታዎችን በተረጋጋ ሁኔታ የማሰብ ልምድ ነው፡፡ በዙሪያችን ካለው ግርግርና ጫጫታ መለስ ብለን የምናስብበትና ግራና ቀኙን የምናይበት የእረፍትና የብቻጊዜ ያስፈልገናል፡፡ ይህ አስፈላጊ ልምምድ ሲጎድለን አጥርተን ለማሰብና ትክክለኛ ውሳኔዎች ላይ ለመድረስ ያለን ብቃት ይደክማል፡፡ በአጭሩ፣ ለብቻቸው በመሆን የማያስቡ ሰዎች የውሳኔዎቻቸው ጥራት አናሳና ለስህተት የተጋለጠ ነው፡፡  በዙሪያችን ካለው ግርግርና ጫጫታ መለስ ብለን የምናስብበትና ግራና ቀኙን የምናይበት የእረፍትና የብቻ ጊዜ ያስፈልገናል፡፡ ይቀጥላል . . . ዶ/ር እዮብ ማሞ @Human_intelligence
显示全部...
👍 61👏 6🙏 6 5😢 1
የብቸኝነትንና ብቻ የመሆንን ልዩነት እወቅ (ክፍል አንድ) (“ራስን ማሸነፍ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ) በስነ-ልቦናው አለም፣ መረጃ-ተኮር ማሕበራዊ ተጽእኖ ተብሎ ሊተረጎም የሚችል፣ በእንግሊዝኛው “ሶሽያል ፕሩፍ” (Social Proof) የተሰኘ ሃሳብ አለ፡፡ ይህ ሁኔታ የሌሎችን ሰዎች ተግባር ተመልክተን እኛም ያንኑ ሰዎቹ የሚያደርጉትን ተግባር ብናደርግ ትክክለኛ እንደሆንን እንደማስረጃ የመጠቀም ዝንባሌ ነው፡፡ ይህንን ዝንባሌ በሌላ ስነ-ልቦናዊ አባባል ሲገልጹት በብዙሃኑ (በመንጋው ጋጋታ) የመነዳት ዝንባሌ (Herd Instinct) ይሉታል፡፡ ወደ አንድ የሙዚቃ ትርዒት (Concert) በመሄድ ላይ ነህ፡፡ መስቀለኛ መንገድ ላይ ስትደርስ፣ አንገታቸውን ቀና አድርገው ወደ ሰማይ የሚመለከቱ በርካታ ሰዎችን ታገኛለህ፡፡ ምንም ሳታስብበትና ሳታንገራግር አንተም ወደላይ መመልከት ትጀምራለህ፡፡ ለምን? ማሕበራዊ ተጽእኖ (Social Proof)፡፡ በሙዚቃው ትርዒት መካከል አርቲስቱ አስገራሚ ችሎታውን ሲያሳይ አንድ ሰው ማጨብጨብ ይጀምራል፣ በድንገት ተመልካቾች በሙሉ ያንን ሰው በመከተል ማጨብጨብ ይጀምራሉ፡፡ አንተም እንደዚያው ማድረግ ትጀምራለህ፡፡ ለምን? ማሕበራዊ ተጽእኖ (Social Proof)፡፡ ከሙዚቃው ትዕይንት በኋላ ካፖርትህን ወደሰቀልክበት አካባቢ ካፖርትህን ለመውሰድ ሄድክ፡፡ በፊትህ የቀደሙህ ሰዎች ካፖርታቸውን ሲወስዱ በዚያ በተቀመጠው ሳህን ላይ ሳንቲም ጣል እያደረጉ ሲሄዱ አየህ፡፡ ካፖርት እዚያ ሰቅሎ ለመግባት ምንም ክፍያ እንደማይጠይቅ በሚገባ ታውቃለህ፡፡ ምን ታደርጋለህ? ምናልባት አንተም ሳንቲም ጣል ታደረግ ይሆናል”፡፡ ይህ ሁኔታ ለብቻችን በመሆን የግል አመለካከትን ለማዳበር ከምናደርገው ጥረት ይልቅ ምን ያህል በሰዎች ሃሳብ እንደምንነዳ፣ ወጣ ብለን እንደ አፈንጋጭ ላለመታየትና ሰዎችን ለማስደሰት ምን ያህል ርቀት እንደምንሄድ ጠቋሚ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ብቻ መሆንን እንደብቸኝነት መቁጠር፤ የግል አመለካከትን እንደ ስህተት ማየት - የብዙዎቻችን ችግር! በብቸኝነትና ለብቻ በመሆን መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፡፡ አንዳንድ ሰዎች እነዚህን ሁለት ሁኔታዎች ለያይተው አያስቧቸውም፡፡ ስለሆነም፣ ለብቻቸው መሆን ማለት ብቸኝነት ስለሚመስላቸው ካለማቋረጥ በዙሪያቸው ሰዎች ከሌሉ የስሜት ቀውስ ይጫጫናቸዋል፡፡ ለብቻቸው ሆነው በማሰብና በጸጥታ ሁኔታዎችን የመገምገም ጊዜ ስለሌላቸው ከአንዱ ግርግር ወደሌላኛው በመዘዋወር ቀናቶቻቸውን “እንደተንጫጩ” ያባክናሉ፡፡ ከብዙ ሁኔታዎችና ሰዎች ጋር አሳልፈህ፣ ከብዙ ሰዎች ጋር ተዋውቀህ፣ ብዙ ቦታዎች ተጉዘህና ባክነህ ለብቻህ በማሳለፍ ከራስህ ጋር ካልተነጋገርክና ካልተዋወክ ብዙ ሰርተህ ትንሽ የምታተርፍ ከመሆን አታመልጥም፡፡ በአለም ላይ ካሉ ሁሉ ወዳጆችህ ይልቅ የቅርብ የሆነው ወዳጅህ ማንነትህ ነው፡፡ ከዚህ ወዳጅ ጋር መተዋወቅ፣ መነጋገርና ማንም በሌለበት የብቻ ጊዜን ማሳለፍህ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ ይህንን እውነታ የተገነዘቡ ሰዎች ከመባከንና ከመድከም የተረፉ ሰዎች ናቸው፡፡ ይቀጥላል . . . ዶ/ር እዮብ ማም @Human_intelligence
显示全部...
👍 58 28
1.‹‹ከታሪክ ምንም አልተማርንም፡፡ ከታሪክ የተማርነው ከታሪክ ምንም መማር አለመቻላችንን ነው፡፡›› ሲስሮ 2.‹‹ደስታ ከምክንያታዊነት ጋር የሚስማማ ሳይሆን ከምናብ ጋር የሚዋሃድ ነው፡፡›› ኢማኑኤል ካንት 3.‹‹ሌላ ሠው ማፍቀር የፈጣሪን ሌላኛውን ፊቱን ማየት ነው፡፡›› ቪክቶር ሂጎ 4.‹በህግ አንድ ሠው የሌላን ሠው መብት ከተጋፋ ወንጀለኛ ነው፡፡ በስነምግባር ግን አንድ ሠው ሌላ ሠው ላይ ክፉ ማሠቡ ብቻ ወንጀለኛ ያደርገዋል፡፡›› ኢማኑኤል ካንት 5.‹ልምድ ንድፈሃሳብ ከሌለው እውር ነው፡፡ ነገር ግን ንድፈሃሣብ ራሱ ልምድ ከጎደለው እንደው ዝምብሎ የምሁር ጨዋታ ነው የሚሆነው፡፡›› ኢማኑኤል ካንት  6.‹‹ሠዎች ጥንካሬ አላጠራቸውም፡፡ ያጠራቸው ፈቃድ ወይም ፍላጎት ብቻ ነው፡፡›› ቪክቶር ሁጎ 7.‹‹ተፈጥሮ በአዕምሮአችን ውስጥ በቀላሉ የማይረካ እውነትን የሚናፍቅ ተክል ተክላለች፡፡›› ሲሴሮ 8.‹‹ዝናህን ለመገንባት ሃያ ዓመት ይወስድብሃል፡፡ ዝናህን ለማበላሸት ግን ሃያ ደቂቃ በቂህ ነው፡፡ ይሄን ጉዳይ ካሰብክ ነገሮችን በተለያየ መንገድ ታከናውናቸዋለህ፡፡›› ዋረን በፌት 9.‹‹ታሪክ የዘመን ምስክር፣ የእውነት ብርሃን፣ የኑሮ ማስታወሻ፣ የሕይወት አስተማሪ፣ እንዲሁም የጥንት ስራ መልዕክተኛ ነው፡፡›› ሲሴሮ 10.የጨረቃዋን ውበት የሚሻ ጨለማውን አይሸሽም .....ጽጌረዳዋን ብሎ የሄደ እሾሁን ፈርቶ አይመለስም......ፍቅርን ከልቡ የሚፈልግ ሰው ከራሱ አይደበቅም......እራሱን ፈጽሞ አይሸሽም ሩሚ @Human_intelligence
显示全部...
👍 44 7😢 2
Excerpt taken from Borrowing Freedom: Dictators and their retinue are four times removed from truth and reality. The first time they lie to themselves as individuals, the second time they lie to each other as partners, the third time they lie to the people as a group, and the fourth time they expect the people to lie to them by acquiescing their lies. Mindaryalew Zewde
显示全部...
👍 32 3
አገር ለናንተ ምንድን ናት? በተስፋሁን ከበደ ፍራሽ አዳሽ የትኛው ነው ትክክል በሀገር ውስጥ ራስን መፈለግ ወይስ በራስህ ውስጥ ሀገርን መፈለግ? @Human_intelligence
显示全部...
ተስፋሁን ከበደ.mp310.05 MB
👍 34 2
አርሶ መና ናቲ ማን
显示全部...
Nhatty_Man_ናቲ_ማን_አርሶ_መና_Arso_Mena_New_Ethiopian_Music_2023256k.mp33.96 MB
👍 20 7