2025 年数字统计

194 465
订阅者
-2724 小时
-1037 天
-80330 天
帖子存档
照片不可用在 Telegram 中显示
#Update:
የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ ድቤይቤህ የሊቢያ ጦር አዛዥ መሐመድ አሊ አህመድ አል-ሃዳድ እና ሌሎች አራት ሰዎች በቱርክ ዋና ከተማ አንካራ አቅራቢያ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ መሞታቸውን አረጋግጠዋል።
Source: TRT World
😀 | @tikvahethmagazine
😢 157🤔 41❤ 14🤯 13🔥 3👏 2
#NewsUpdate
የሊቢያ ጦር ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም የተሳፈሩበት አውሮፕላን የሬዲዮ ግንኙነቱ መቋረጡ ተገለጸ።
የሊቢያ ጦር ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም መሐመድ አሊ አህመድ አል-ሐዳድን እና ሌሎች አራት ሰዎችን አሳፍሮ ከአንካራ ቱርክዬ ተነስቶ ወደ ሊቢያ ሲያቀና የነበረ "Falcon 50" የተባለ የንግድ ጄት ግንኙነቱ መቋረጡን ቱርክዬ አስታወቀች
የቱርክዬ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አውሮፕላኑ ዛሬ ከምሽቱ 2፡10 ላይ የተነሳ ሲሆን፣ ከምሽቱ 2፡52 ላይ ከሬዲዮ ግንኙነት ውጪ ሆኗል ብሏል።
ግንኙነቱ ከመቋረጡ ጥቂት ቀደም ብሎ፣ አውሮፕላኑ በአንካራ "ሃይማና" (Haymana) በተባለ አካባቢ ላይ እያለ የድንገተኛ አደጋ ማረፊያ ጥያቄ አቅርቦ እንደነበር የቱርክ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ይርሊካያ ገልጸዋል።
ጄኔራል አል-ሐዳድ ወደ አንካራ የመጡት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ሲሆን ከቱርክ ወታደራዊ አቻዎቻቸው ጋር ለመወያየት ነበር ወደ ቱርክ ያቀኑት።
በአሁኑ ሰዓት ስለ አውሮፕላኑ ሁኔታም ሆነ በውስጡ ስለነበሩት ተጓዦች ደኅንነት የወጣ ተጨማሪ መረጃ የለም።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 56😢 25👎 2
በህገ-ወጥ መንገድ የቆዳ ህክምና መድኃኒት ሲያመርትና ሲያከፋፍል የነበረ ግለሰብ ተያዘ።
ለቆዳ በሽታ ፈውስነት ይውላል የተባለ እና ምንጩ ያልታወቀ መድኃኒት በህገ-ወጥ መንገድ ሲያመርትና ሲያከፋፍል የነበረ ግለሰብ ከነተባባሪው በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል።
ባለሥልጣኑ ከህብረተሰቡ ደረሰኝባለው ጥቆማ መሰረት ከልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጋር በጋራ በመሆን አደረኩት ባለው ክትትል ተጠርጣሪው እጅ ከፍንጅ ሊያዝ መቻሉን ገልጿል።
በኦፕሬሽኑ ወቅት እንደተረጋገጠው፣ ግለሰቡ ለመድኃኒት ቅመማ የሚውሉ (Pharmaceutical grade) ያልሆኑ 8 የተለያዩ ኬሚካሎችን እና 7 አይነት መድኃኒቶችን በመቀላቀል፣ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ያልተረጋገጠ ውህድ በማዘጋጀት ለገበያ ሲያቀርብ እንደነበር ተደርሶበታል።
ምርቱን ለደንበኞች ሲያደርስ (Delivery) የነበረ አንድ ሞተረኛም አብሮ በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሏል፡፡
ተጠርጣሪው በሚያመርተው ህገ-ወጥ መድኃኒት ላይ “ISRAELOHIM PHARMA MEG AND IMPORT” የሚል የድርጅት ስም በመለጠፍ ህብረተሰቡን ሲያታልል ቆይቷል።
በተጨማሪም፥ ከኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን የአምራችነት ፈቃድም ሆነ ከአዲስ አበባ ምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን የመድኃኒት ቅመማ ፈቃድ የሌለው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
በቁጥጥሩ ወቅት ምንጫቸው የማይታወቅ እና ለመድኃኒትነት የማይውሉ 53 ጠርሙስ የተዘጋጁ ኬሚካሎች መገኘታቸውን የባለሥልጣኑ መረጃ ያሳያል።
ግለሰቡ የቆዳ በሽታን የሚያድን ዋና ንጥረ ነገር (Active Ingredient) ሳይኖረው፣ በዘፈቀደ መድኃኒቶችን እየፈጨ ከኬሚካሎች ጋር በመቀላቀል ለህብረተሰቡ ጤና ጠንቅ የሆነ ምርት ሲያከፋፍል መቆየቱን ነው የገለጸው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 38👍 13👏 5👎 1🤣 1
照片不可用在 Telegram 中显示
"በጋምቤላ ክልል ያሉ ስደተኞችን በተመለከተ የሚሰራጨው ሐሰተኛ መረጃ አሳስቦኛል" የተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ
የተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በጋምቤላ ክልል የሚገኙ ስደተኞችን ኢላማ ያደረጉ የተሳሳቱ መረጃዎች መሰራጨታቸው እንዳሳሰበው ገልጿል።
ኤጀንሲው ስደተኞቹ በሃገራቸው ካጋጠማቸው ግጭት የተነሳ ደኅንነትና ጥበቃ ፈልገው መጥተዋል ያለ ሲሆን ሁሉም ሰው ስደተኞች እና ስደተኞቹን የተቀበሉ ማኅበረሰቦች ላይ የጥላቻ ንግግርን እንዳይደረግ ጠይቋል።
የተመድ ኤጀንሲ በክልሉ የተከሰተው ሁኔታ የምግብ እና ውሃ ሥርጭትን ጨምሮ አንዳንድ አገልግሎቶች በጊዜያዊነት እንዲቆሙ ማስገደዱን አንስቶ ሁኔታውን እየተከታተለ ስለመሆኑና ከአስተዳደር አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
እንደ የስደተኞች ኤጀንሲው ዘገባ ከ482 ሺህ በላይ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በኢትዮጵያ የሚገኙ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከ447 ሺህ በላዩ የሚገኙት በጋምቤላ ክልል ነው።
ከባለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ ደግሞ ከ50,000 በላይ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ወደ ጋምቤላ ክልል መግባታቸውም ተገልጿል።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 41
照片不可用在 Telegram 中显示
ሩዋንዳ ከ10ሺ በላይ የወንጌላውያን ቤተክርስቲያናትን ዘጋች።
ሩዋንዳ ከ10 ሺ በላይ ቤተክርስቲያኖችን ስትዘጋ ለዚህም የአምልኮ ስፍራን ለመቆጣጠር ከወጣው የ2018 ህግ ጋር አልተስማሙም የሚል ምክንያት አቅርባለች።
ህጉ የጤና፣ የደህንነትንና የፋይናንስ ሁኔታን ለኃይማኖት ተቋማት ሲያስተዋውቅ ሁሉም ሰባኪዎች የቲዎሎጂ ( የስነ-መለኮት) ስልጠና እንዲኖራቸው ያስገድዳል።
በተጨማሪ ህጉ ቤተክርስቲያናቱ አመታዊ የተግባር እቅድ እንዲያቀርቡ ሲያስገድድ፣ የገንዘብ እንቅስቃሴያቸውም በተመዘገቡ አካውንቶች ብቻ እንዲሆን ያስገድዳል።
ከሳምንታት በፊት ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ የኃይማኖት ተቋማቱን መተቸታቸው ይታወሳል።
ዘገባው የTRT ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 140👏 98👎 12👍 3🤔 3😢 3🤬 1
照片不可用在 Telegram 中显示
በሪልስቴት ግንባታ ዘርፍ ውስጥ አንጋፋ
* የሀገር ውስጥ እና የውጭ አልሚዎች
* ኮንትራክተሮች እንዲሁም
* በተለያየ መስሪያ ቤት ውስጥ በማህበር ተደራጅተው ቤት መገንባት የሚፈልጉ ቤት ሰሪዎች
እናንተን ውድ ባለንብረቶች በእጅዎ ፕሮፐርቲስ የሞባይል አፕሊኬሽን ሱፐር ፕላትፎርም ውስጥ እየጠበቋችሁ ይገኛሉ።
ይዞታችሁን በትክክለኛ መረጃ መዋቅር ውስጥ በማስገባት ከልዩ ልዩ አልሚዎች ጋር ልናገናኛችሁ ሙሉ ዝግጅታችን ያጠናቀቅን ሲሆን አሁንም በጋራ መገንባት ፍላጎት ያላችሁ ባለይዞታዎች ንብረቶቻችሁን ይዛችሁ ቅረቡ።በዚህ ትልቅ የ አብሮ ማልማት ግንባታ ፕሮግራም ውስጥ ተሳትፎ ማድረግ ብልህነት ነውና ይፍጠኑ።
ለበለጠ መረጃ ☎️
0990494984
0990464684
❤ 10👍 3
照片不可用在 Telegram 中显示
ህንድ እና ታንዛኒያ የባህላዊ መድሃኒቶችን ለማሳደግ እና ለመጠበቅ የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ ቴድሮስ አድሃኖም(ዶ/ር) በተገኙበት የተፈረመ ሲሆን ስምምነቱ ለባህላዊ መድሃኒቶች ህጋዊ እና የዲጂታል ማዕቀፎች ጥበቃ እንዲሰጥ ያስችላል ተብሏል።
የታንዛኒያ የጤና ሚኒስቴር 60 በመቶ ዜጎቹ ባህላዊ መድሃኒቶችን እንደሚጠቀሙ ገልፆ በአሁኑ ወቅት 27 የባህላዊ መድሃኒቶች እውቅና ተሰጥቷቸው በሆስፒታሎች ጥቅም ላይ መዋላቸውን አስታውቋል።
የታንዛኒያ የጤና ሚኒስቴር ባለፈው መስከረም ወር ከ30 በላይ ባህላዊ መድሃኒቶች በሃገሪቱ በሚገኙ 14 የክልል ሪፈራል ሆስፒታሎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ፈቅዷል።
ታካሚዎችም ወደነዚህ ሆስፒታሎች ሲያመሩ የባህላዊ ወይም የተለመደውን የህክምና ዘዴ አልያም ሁለቱንም በጣምራ የመጠቀም አማራጭ ይሰጣቸዋል።
ታንዛኒያ ከ42 በሚበልጡ የባህላዊ መድሃኒቶች ላይ በመንግስት ደረጃ ምርምር ከተደረገ በኋላ 30ዎቹ በጥቅም ላይ እንዲውሉ ፈቅዳለች።
ታንዛኒያ መድሃኒቶቹ ደረጃቸው በመሻሻላቸው ለውጪ ገበያ መላክ መጀመሯን ስትገልፅ በሂደቱ ዙሪያ ከአለም ጤና ድርጅት ጋር መረጃ እየተለዋወጠች መሆኗን ገልፃለች።
ታንዛኒያ ሌሎች መድሃኒቶችንም እውቅና ለመስጠት ተቋማቷና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቶቿ ምርመር እያደረጉ እንደሆነ ገልፃለች።
ዘገባው የሲቲዝን እና ዴይሊ ኒውስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 40👍 3👏 1
照片不可用在 Telegram 中显示
ደቡብ ሱዳን ጠቅላላ ምርጫዋን በቀጣይ አመት ታህሳስ፣ 2026 እንደምታደርግ ይፋ አደረገች።
የደቡብ ሱዳን የብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት የደቡብ ሱዳን የ2018 የሰላም ስምምነት ላይ ማሻሻያዎች ከተደረጉ በኋላ በመጪው አመት ታህሳስ ወር ምርጫ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
በማሻሻያው የህዝብ ቆጠራ ከምርጫው በኋላ እንዲደረግ በመወሰኑም የምርጫ ኮሚሽኑ በ2010 የሱዳን አካል ሳለች የነበረውን የምርጫ ክልል ይጠቀማል ተብሏል።
በዚህም መሰረት በ10 ግዛቶች እና 3 አስተዳደሮች 102 የምርጫ ክልሎች እንደሚኖሩ ተገልጿል።
በ2011 ከሱዳን ነፃነቷን ያገኘችው ወጣቷ ሃገር ደቡብ ሱዳን እስካሁን ምርጫ አላደረገችም። በዚህም የ2026 ቱ ምርጫ የመጀመሪያዋ ይሆናል ማለት ነው።
ዘገባው የRadio Tamazuj ነው
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 22👍 2
照片不可用在 Telegram 中显示
✨ከእኛ አንድ ቤት ሲገዙ ከኢትዮዽያ አየርመንገድ ET🇪🇹 Sheba Miles ደረጃዎን በእጥፍ ያሳድጉ ✈️🤝
በተጨማሪም በተመጣጣኝ ዋጋ የቤት ባለቤት ልናረጎ ሲሆን:-
እስከ 25% ቅናሽ ያላቸው በነፋሻማዋ ሰሜን ማዘጋጃ ላይ ግንባታቸው እየተካሄደ ያለ በካ.ሜ ከ65,000 ብር ጀምሮ ይዘንላቹ መተናል!
👉በ 25% ቅናሽ (100% ለሚከፍሉ ደምበኞች)
ባለ 1 መኝታ(81 ካ.ሜ)=5,300,000ብር
ባለ 2መኝታ(110ካ.ሜ)=7,200,000ብር
ባለ3መኝታ(130ካ.ሜ)=8,500,000ብር
👉በ 10% ቅድመ ክፍያ ቀሪው በግንባታ ሂደት የሚከፍሉት!
ባለ 1 መኝታ(81 ካ.ሜ) = 700,000 ብር
ባለ 2 መኝታ(110ካ.ሜ) =957,000 ብር
ባለ 3 መኝታ(130ካ.ሜ)=1,131,000ብር
✨በተጨማሪም እንደ ቅድመ ክፍያዎ ቀድመዉ ለሚመጡ 15 ደምበኞች ብቻ ከ3% እስከ 25% ቅናሽ ያለን ሲሆን ይህንን እድል ተጠቃሚ ለመሆን በ0913599755 ወይም 0912915147 ይደውሉ!
#Akoyaproperties #EthiopianAirlines #ShebaMiles #Partnership
❤ 13
照片不可用在 Telegram 中显示
ረጅም ሰዓት መቀመጥ ሲጋራ ከማጨስ አይተናነስም (Sitting is the new smoking) ሲባል ሰምተዋል ?
ይህ አገላለጽ ሳይንቀሳቀሱ ለረጅም ሰዓታት መቀመጥ በጤና ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከሲጋራ ማጨስ ጋር እኩል አደገኛ መሆኑ ስለተረጋገጠ ሰዎችን ለማንቃት እያገለገለ ይገኛል።
በሥራ ምክንያት ሆነ በሌላ በቀን ከ8 ሰዓት በላይ ተቀምጠው የሚያሳልፉ ከሆነ ይህ አገላለጽ በእውነትም ሊያስጨንቆት ይገባል።
በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች ረጅም ሰዓት መቀመጥን በዋናነት የሚያስከትሉትን የጤና አደጋዎች እንዲህ ይገልጹታል፦
- ለረጅም ሰዓት መቀመጥ የሰውነትን ስብ የማቃጠል አቅም በ90% ይቀንሳል።
- የደም ግፊትን ይጨምራል።
- ከመጠን ላለፈ ውፍረት በማጋለጥ ለስኳር፣ ለልብ ህመም እና ለተለያዩ የካንሰር ዓይነት በሽታዎች ያጋልጣል።
- በቀን ከ6 ሰዓት በላይ ተቀምጠው የሚያሳልፉ ሰዎች፣ ከ3 ሰዓት በታች ከሚቀመጡት ጋር ሲነፃፀሩ በ15 ዓመት ውስጥ የመሞት እድላቸው በ40% ከፍ ያለ ነው።
- ንቁ እንቅስቃሴ አለማድረግ ለጭንቀትና ለድብርት (Depression) ተጋላጭነትን ይጨምራል።
ይህን ያህል ረጅም ሰዓት መቀመጥ አደጋ ከሆነ ምን እናድርግ ?
ልክ ሲጋራን ማቆም ለጤና ወሳኝ እንደሆነ ሁሉ፣ ለረጅም ሰዓት ያለ እንቅስቃሴ የመቀመጥ ዝንባሌያችንን ማስቀረት የህልውና ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን።
ለዚህም የሚከተሉት እርምጃዎች እንደ መፍትሄ መቀመጥ ይችላሉ፦
- ከተቻለ በ30 ደቂቃው ከወንበር ተነስቶ ለጥቂት ደቂቃዎች እንቅስቃሴ ማድረግ፤
- በቀን ውስጥ ቢያንስ ለ30 ደቂቃ ፈጣን እርምጃ ወይም ስፖርት ማዘውተር፤
- ስልክ ሲደወልልዎት ወንበርዎ ላይ ከመቀመጥ ይልቅ እየተንቀሳቀሱ ማውራት፤
- በሊፍት ፋንታ ደረጃን መጠቀም የደም ዝውውርን ማሻሻል፤
በአጠቃላይ ወንበር ላይ ረጅም ጊዜን ማሳለፍ ልክ እንደ ሲጋራ ጢስ ቀስ በቀስ ጤናን የሚያውክ በመሆኑ፣ መንቀሳቀስ ለጤናችን ግድ መሆኑን አውቀን በጊዜ እንዘይድበት መልዕክታችን ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 119👍 35👎 8🤯 6🤣 2😢 1
照片不可用在 Telegram 中显示
ሳዑዲ አረቢያ ከመጪው ጥር 1፣ 2026 ጀምሮ የቤት ሰራተኞች ክፍያ መንግስት በዘረጋው ስርዓት እንዲከፈል ወስናለች።
በሳዑዲ አረቢያ የሚሰሩ የቤት ሰራተኞች ከመጪው ጥር 1፣ 2026 ጀምሮ ክፍያቸውን በተዘረጋው የኤሌክትሮኒክስ ስርዓት እንደሚከፈላቸው ይህም የደመወዝ ጥበቃ እንደሚሰጣቸው እና ግልፀኝነትን እና ጊዜውን የጠበቀ ክፍያ እንዲሰጣቸው እንደሚያደርግ የሃገሪቱ የሰው ሃብት ሚኒስትር አስታውቋል።
ሰራተኞቹ ወቅቱን ጠብቆ ደሞዛቸው በጥሬ ገንዘብ ሳይሆን "ሙሳነድ" በተባለው ሥርዓት የሚከፈላቸው ሲሆን ያገኙትን ገንዘብም በተፈቀዱ መንገዶች ውጪ ላሉ ቤተሰቦቻቸው ማስተላለፍ ይችላሉ።
ሳዑዲ ይህንን ስርዓት ከ2024 ጀምሮ ወደ ስራ ለገቡ አዳዲስ ሰራተኞች መጠቀም የጀመረች ሲሆን የተለያዩ ሂደቶችን ካለፈ በኋላ ከ2026 ጀምሮ ወደ ሙሉ ትግበራ ይገባል ተብሏል።
በአዲሱ ሥርዓትም ሰራተኞቹ የሂጂራ ወር መጨረሻ ላይ በኮንትራታቸው መሰረት ክፍያቸውን ያገኛሉ ተብሏል።
አዲሱ ሥርዓትም የቤት ሰራተኞች ጊዜውን የጠበቀ ክፍያ እንዲያገኙ በማስቻል ከሚጠብቃቸው መንገላታትና የክፍያ ማጣት ይጠብቃቸዋል።
ዘገባው የዘ ኢኮኖሚክ ታይምስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
👍 102❤ 48🙏 6🕊 2🤝 1
#Update
የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን መስማት ለተሳናቸው ዜጎች የማሽከርከር ሥልጠና ማስጀመሩን አስታውቋል።
መስማት የተሳናቸው ዜጎች የማሽከርከር ፈቃድ እንዲሰጣቸው ረጅም ዓመታት ሲጠይቁ ቢቆዩም ትኩረት ሳይሰጣቸው ቆይቷል።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 50👏 22🤔 5👍 3
照片不可用在 Telegram 中显示
የትራምፕ አስተዳደር በርከት ያሉ በውጪ ሃገራት እየሰሩ ያሉ አምባሳደሮችን ከኃላፊነት ሊያነሳ ነው።
ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በርካታ ለውጦችን እያደረጉ ሲሆን አሁን ደግሞ ትኩረታቸው ዲፕሎማሲው ሆኗል።
በዚህም መሰረት ለበርካታ አመታት በዲሞክራቶችም በሪፐብሊካኖቹም ስር በውጪ ጉዳይ ላይ የሰሩና በባይደን አስተዳደር በአምባሳደርነት የተመደቡ ከ24 የሚበልጡ አምባሳደሮች ከኃላፊነታቸው በቀጣይ ወር እንደሚነሱ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ተነግሯል።
ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ዲፕሎማቶች ፕሬዚዳንቱ አምባሳደሮቹ አሜሪካን ቀዳሚ ያደረገ አጀንዳ በተወከሉበት ሃገራት ማራመዳቸውን ማረጋገጥ አለባቸው ያሉ ሲሆን በየትኛውም አስተዳደር የተለመደ ተግባር ነው ብለዋል።
በየትኞቹ ሃገራት የተመደቡ ዲፕሎማቶች እንደተነሱ እና ስለ ትክክለኛ ቁጥር የታወቀ ነገር ባይኖርም አብዛኞቹ #ከአፍሪካ ስለመሆናቸው ምንጮች ተናግረዋል ተብሏል።
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲን የሚመራው ስቴት ዲፓርትመንት በዚህ አመት ከትራምፕ መምጣት በኋላ በዋና መስሪያ ቤቱ የሚሰሩ 1300 ባለሙያዎች አሰናብቷል።
ዘገባው የሲኤንኤን ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 34🤣 8👍 3🤔 2👎 1
照片不可用在 Telegram 中显示
ጃፓን የአለማችንን ትልቁን የኒውኪሊየር ጣቢያ ስራ ዳግም ልትጀምር ነው።
የሒሮሺማ እና ናጋሳኪ የአቶሚክ ቦንብ ውድመትን በታሪኳ ይዛ ያለችው ጃፓን ፉኩሺማ በተባለው የኒውኪሊየር ጣቢያዋ ላይ ከ15 አመታት በፊት ከባድ ውድመት ከደረሰ በኋላ የአለማችን ትልቁ የኒውኪሊየር ጣቢያ ዳግም ስራ እንዲቀጥል ወስናለች።
በወቅቱ በጣቢያው በደረሰ ውደመት ከ160 ሺህ በላይ ሰዎች ሲፈናቀሉ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ከጨረሩ የተነሳ በተለያየ የካንሰር አይነት ተይዘው አንድ ሰው በጨረሩ ምክንያት ህይወቱ አልፏል።
ፉኩሺማ ጣቢያ በ2011 በሃገሪቱ በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ እና ሱናሚ ከ33 ማብለያዎች የሚሰራው 14ቱ የነበረ ሲሆን ጃፓን የኃይል ምንጯንም ከድንጋይ ከሰል ለመሸፈን ተገዳ ነበር።
ውሳኔውን ተከትሎ 300 የሚሆኑ የኒውኪሊየር ጣቢያው የሚገኝበት አካባቢ ነዋሪዎች "No Nukes" የሚሉ ባነሮችን ይዘው ውሳኔውን ተቃውመዋል።
የኒውኪሊየር ጣቢያው የሚገኝበት የኒጋታ አካባቢ ነዋሪዎች በጣቢያው ላይ የሆነ አደጋ ቢደርስ የመጀመሪያ ተጎጂዎች እኛ ነን ቢሉም ባለስልጣናት የአካባቢውን ነዋሪዎች መጠበቅ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው ብለዋል።
አጠቃላይ 8.2 ጊጋዋት ኃይል የሚያመነጨው ጣቢያ ማብላያ ከመጪው ጥር 20 ጀምሮ ወደ ስራ ይገባል ሲባል የአንዱ ማብላያ ወደ ስራ መመለስ የቶኪዮ አካባቢን የኤሌክትሪክ አቅርቦት በ2% ያሳድጋል ተብሏል።
ጃፓን ባለፈው አመት ለኃይል ፍጆታ የሚውል የድንጋይ ከሰል ከውጪ ለማስገባት 10.7 ትሪሊየን የን ያወጣች ሲሆን ይህም ከአጠቃላይ ካስገባችው እቃ አንድ አስረኛ እንደማለት ነው።
በተጨማሪ ከፍተኛ የኃይል ፍጆታ የሚፈልጉት የAI የዳታ ማዕከላት ግንባታ የጃፓንን የኃይል ፍጆታ ይጨምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዘገባው የሮይተርስና አልጄዚራ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 36🤔 7👍 3👎 2
照片不可用在 Telegram 中显示
ፌስቡክ በመተግበሪያው ላይ የሚጋሩ ሊንኮችን ሊገድብ ነው።
ፌስቡክ እያደረገ ነው በተባለው ሙከራ ከ14.99 ዶላር የሚጀምረው የፌስቡክ ቬሪፋይድ ሰብስክሪፕሽን የሌላቸው ተጠቃሚዎች በሳምንት ሁለት ሊንኮችን ብቻ እንዲያጋሩ ይገድባል።
ሜታ ገደቡ የፕሮፌሽናል ሞድ የሚጠቀሙ ሰዎችንና የፌስቡክ ፔጆችን እንደሚመለከት ገልጿል።
የሜታ ቃል አቀባይ ሙከራው ከሊንኮች ጋር ተጨማሪ ልጥፎችን ማጋራት መቻል የሜታ ሰብስክሪፕሽንን እንደሚጨምር ለማየት ስለመሆኑ ገልጿል።
የሜታ ሙከራ ከሌሎች መተግበሪያዎቸ የሚደርሱትን አንባቢ ለመጨመር የሚሞክሩ ሰዎች ላይ ተፅዕኖ ሲኖረው ተጠቃሚዎች አሁንም በሃሳብ መስጫዎች ሊንኮችን ማጋራት ይችላሉ ብሏል።
ዘገባው የቴክ ክራንች ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 17😢 8👍 4👎 4
照片不可用在 Telegram 中显示
ገንዘብዎን ከሌቦች ይጠብቁ!
በኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያ ተጠቃሚዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ የሳይበር ስርቆቶች እየተበራከቱ ይገኛሉ።
• የእርስዎን የሚስጥር ቁጥር (PIN) ለማንም አይስጡ።
• "ሽልማት ደርሶዎታል" በሚሉ አጠራጣሪ ሊንኮች አይታለሉ።
• በስልክ የኦቲፒ (OTP) ቁጥር የሚጠይቁዎትን ግለሰቦች ፍጹም አይመኑ።
• በኢሜይልዎ እና በሶሻል ሚዲያ አካውንቶችዎ ላይ ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫን (2FA) በመጠቀም ደህንነትዎን ያጠናክሩ።
ዲጂታል ክፍያን በጥንቃቄ በመጠቀም ንብረትዎን ከዘራፊዎች ይከላከሉ!
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 29👍 5🕊 1
照片不可用在 Telegram 中显示
🏠 ከኪራይ ቤት ለመውጣት አስበው ግን ያጠራቀሙት ገንዘብ አነስተኛ መስሎ ከታዮት እኛን ሳያማክሩ አይወስኑ!
👉 በ 3 አመት ጊዜ ውስጥ ቀስ እያላቹ ያለ ወለድ ከፍላቹ መሀል ከተማ ሳር ቤት እና አዋሬ ላይ የቤት ባለቤት መሆን ትችላላቹ.
🌅 ቴምር ሪል እስቴት በ8.3 ሚሊየን ብር ጠቅላላ ዋጋ በ 1.7 ሚሊየን ብር 20% ቅድመ ክፍያ ቤት የባለቤት ላርጋቹ እያለ ነው ቀሪውን 80% በ 3 አመት ጊዜ ውስጥ በግንባታ ሂደት ቀስ ብላቹ መክፈል ትችላላቹ .
👉 100% አሁን ላይ ከፍላለው ካላቹ ደግሞ 35 % ቅናሽ ተደርጎላቹ ከ5.4 ሚሊየን ብር ጠቅላላ ዋጋ ጀምሮ መግዛት ትችላላቹ .
💥ብዙ ቤቶች ተሸጠው አልቀዋል ቀሪዎቹም ተሸጠው ሳያልቅባችሁ በቢሮ ቁጥራቸው 0980782850 ደውሉ.
❤ 12👎 3
照片不可用在 Telegram 中显示
AI እና ሽብርተኝነት
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ከመጣ በኋላ እራሱን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያዘመነ የመጣ ሲሆን አንዱ ይዞት የመጣው ገጽታ ድምፅ የመስራትን ገፅታ ነው።
ታዲያ በአለም ላይ ያሉ አሻባሪዎችና ፅንፈኛ ቡድኖች ይህንን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሃሳባቸውን እያሰራጩ ነው።
ለአብነትም የናዚ ደጋፊዎች የAI ቴክኖሎጂን በመጠቀም የአዶልፍ ሂትለር ንግግሮችን በእንግሊዝኛ አድርገው በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በመልቀቅ በርከት ያለ ሚሊየን እይታን እያገኙ ነው።
በተለይ ቡድኖቹ "elevenlabs" የተሰኘውን መተግበሪያ በመጠቀም የድሮ ንግግሮችን እየሰጡ አንግሊዝኛውን ድምፅ እንደሚሰሩ ተነግሯል።
በተመሳሳይ እነዚህ ቡድኖች የራሳቸውን ሃሳብ የሚገልፁ ፅሁፎችንም AIን በመጠቀም ወደ ድምፅ መፅሐፍ(Audio Book) እየቀየሩና እያከፋፈሉ ነው።
ቡድኖቹ በፅሁፍ ያሉ ሃሳቦቻቸውን በቀላሉ ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ማራኪ ወደሆነ ንግግር በመቀየር መልእክታቸውን ያዳርሳሉ።
በተመሳሳይ የእስላሚክ ስቴትም እንደ ናዚ ደጋፊዎች ሁሉ ፅሁፉን ወደ ድምፅ በመቀየር አስተምህሮውን እያስፋፋ ሲገኝ በጃፓንኛ ሳይቀር እየተረጎመ ያቀርባል።
የአሸባሪ ቡድኖቹና የፅንፈኛ ቡድኖቹ ከሚመጣው ቴክኖሎጂ ጋር እራሳቸውን እያስማሙ የቀጠሉ ሲሆን የብሎክቼይን ቴክኖሎጂ በመጣ ጊዜም ገንዘብ በክሪፕቶከረንሲ ለማግኘትና ፋይሎችን ለመላላክ እንደተጠቀሙበት ይታወቃል።
ፅሁፉ የዘ ጋርዲያን ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 80👎 10😢 9🤔 5🔥 1🤯 1
01:07
视频不可用在 Telegram 中显示
በህንድ 187 ሰዎች ለሚፈለጉበት የስራ ዘርፍ 8000 ሰዎች ለስራ ፈተና መቀመጣቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
በህንድ ኦዲሻ ግዛት ለፖሊስ ድጋፍ ለሚሰጡ የፀጥታ ኃይሎች 187 ሰዎች ብቻ ቢፈለጉም 8000 ያህል ሰዎች ለፈተና ተቀምጠዋል።
ፈተናው በአውሮፕላን መንደርደሪያ አስፋልት ላይ የተሰጠ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ተፈታኞች በጣም መብዛታቸው ነው ተብሏል።
ፈተናው በክፍት ቦታው ላይ ሲሰጥም ተፈታኞችን ለመቆጣጠር ድሮን ጥቅም ላይ ውሏል።
ለፈተናው ከ10,000 በላይ ሰዎች መመዝገባቸው ሲነገር በፈተናው እለት የተገኙት 8000 ያህሉ ናቸው ተብሏል።
ምንም እንኳን ለስራው ብቁ ለመሆን አምስተኛ ክፍልን መጨረስ በቂ ነው ቢባልም በርከት ያሉ የመጀመሪያ እና ከዛ በኋላ ያሉ ድግሪዎች ያሏቸው ሰዎች መመዝገብ እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ሆነው 18 በመቶ ያህሉ ስራ አጥ በሆነባት ህንድ ስራ ማግኘት ቀላል እንዳልሆነ ማሳያ ነው ተብሏል።
😀 | @tikvahethmagazine
amit_mehra_unbelievable_scene_in_india_8_000_youth_running_on_.mp42.21 MB
🤔 57❤ 51😢 30🤣 20💔 1
照片不可用在 Telegram 中显示
የሳህል ሃገራት ጥምረት የጋራ የደህንነት ኃይል መሰረቱ።
ከቀናት በፊት የጋራ የኢንቨስትመንት ባንክ የመሰረቱት ማሊ፣ ቡርኪናፋሶ እና ኒጀር የጋራ ጦር መስርተዋል።
የፀጥታ ኃይሉ የሳህል ሃገራት ጥምረት የጋራ ኃይል ሲባል የፀጥታ ኃይሉ አባላት ከሶስቱም ሃገራት ጦሮች የተውጣጣ ይሆናል ተብሏል።
ሶስቱ ሃገራት ከኢኮዋስ ወጥተው የመሰረቱትን ጥምረት በማሊ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ስልጣን የያዙት ጀነራል ጎይታ በአሁኑ ጊዜ በሊቀመንበርነት ሲመሩት ጀነራሉ ሽብርተኝነትን በሳህል ቀጣና ለማሸነፍ የተመሰረተ ስትራቴጂካዊ ጥምረት ብለውታል።
ሶስቱ ሃገራት ያሉበት የሳህል ቀጣና በተደጋጋሚ ለሽብርተኝነት ተጋላጭ የሆነ አካባቢ እንደሆነ ሲታወቅ የጋራ ጦሩን የቡርኪናፋሶው ጀነራል ዳውዳ ትራኦሬ ይመሩታል ተብሏል።
ዘገባው የTRT ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
👍 50❤ 21👏 8👎 3
