2025 年数字统计

194 457
订阅者
-2724 小时
-1037 天
-80330 天
帖子存档
照片不可用在 Telegram 中显示
🚨በመሀል ፒያሳ ከአራዳ ፓርክ ትይዩ ከወዳጅነት ፓርክ እንዲሁም አብርሆት ቤተ መፅሀፍት በቅርብ ርቀት ላይ
🎄መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለውስን ቤቶች ብቻ 🎄35%🎄ቅናሽ እንዳደረግን ስንገልፅልዎ በታላቅ ደስታ ነው እርሶም ይሄን ቅናሽ በመጠቀም መሀል ፒያሳ ላይ የቤት ባለቤት የመሆን ሀሳብ ካሎት ፈጥነው ይመዝገቡ🎄
🏡ከባለ አንድ እስከ ባለ ሶስት መኝታ በ 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቀሪውን ዘና ብለው የሚከፍሉት
💎ባለ 1 መኝታ በ 514,500 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 840,000 ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 1,207,500 ብር ቅድመ ክፍያ
🔥እንዲሁም የቤቱን 65% ሲከፍሉ 35% በድርጅቱ የሚሸፈን ይሆናል (35% ቅናሽ)
💎ባለ አንድ መኝታ ሙሉ ክፍያ 3,344,250 ብር
💎 ባለ ሁለት መኝታ ሙሉ ክፍያ 5,460,000 ብር
💎 ባለ ሶስት መኝታ ሙሉ ክፍያ 7,848,750 ብር
-በግንባታ ላይ የሚገኙ
ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelMERITRealtor)
https://t.me/addisapartmentforu
❤ 9👍 1
በሀረሪ ክልል ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ቀርቦ የነበረው ዋጋ ማሻሻያ ተደረገበት።
የሀረሪ ክልል ቤቶች ልማት እና ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ቀደም ሲል ያወጣወን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዋጋ ማሻሻሉን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል ።
የኤጀንሲው ኃላፊ ኢ/ር ሃናን አብዱልፈታህ በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት ቀደም ሲል ይፋ የተደረገው የአፓርታማ ቤቶች ግንባታ እቅድ በአንዳንድ ችግሮች ምክንያት ምዝገባ ማስጀመር አለመቻሉን አንስተዋል።
በዚህም መሰረት ቀደም ሲል ለቅድመ ክፍያ 30 በመቶ የነበረው ወደ 20 በመቶ ማሻሻያ መደረጉን እና በካሬ ክፍያ ላይ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን ሀላፊዋ ተናግረዋል።
ቤቶቹ በገልመሺራ እና ደከር አካባቢ ባለ 4 ወለል የሆኑ 12 ሕንፃዎች እንደሚገነቡና እያንዳንዱ ሕንፃ 21 አባወራ መያዝ የሚችል ተደርጎ እንደሚገነባ አስታውቀዋል።
በክልሉ ዲያስፖራ መንደር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዘመናዊ ቤቶች ግንባታን ለማስቀጠል መታቀዱን ኃላፊዋ አንስተዋል።
- በዲያስፖራ መንደር ለባለ 4ፎቅ አማራጭ በአንድ ካሬ ሜትር 33,929ብር
- በደከር እና በገልማሺራ አካባቢ ደግሞ በአንድ ካሬ 30,000 ብር ዋጋ ተቆርጦለታል።
ህብረተሰቡ 20% የቅድመ ክፍያን በመክፈል ቀሪ ሙሉ ክፍያውን ከሶስት - አምስት ዓመታት በመክፈል መጠቀም ይችላል ተብሏል።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 53🕊 2
照片不可用在 Telegram 中显示
ናይጄሪያ እና አሜሪካ ለአምስት አመት የሚቆይ የ5.1 ቢሊየን ዶላር የጤና ዘርፍ ስምምነት ፈፀሙ።
አሜሪካ የክርስትና እምነት ላይ መሰረት ያደረጉ የጤና አገልግሎት ሰጪዎችን በደንብ ያበረታታል ያለችውን የጤና ስምምነት ከናይጄሪያ ጋር መፈራረሟን ገልፃለች።
አሜሪካ በስምምነቱ መሰረት እንደ ኤችአይቪ፣ ቲቢ፣ ወባ እና ፖሊዮ ያሉ በሽታዎችን ህክምና ለመደገፍ 2.1 ቢሊየን ዶላር ስትሰጥ ናይጄሪያ የጤና ዘርፍ በጀቷን በ3 ቢሊየን ዶላር ትጨምራለች።
አሜሪካ ስምምነቱ ክርስትያኖችን ከጥቃት መጠበቅን ቅድሚያ ይሰጣል ሰትል በልዩነት ድጋፉ የክርስቲያን ጤና ተቋማትን ይመለከታል ብላለች።
አሜሪካ 900 የሚሆኑ የእምነት መሰረት ያላቸው ክሊኒኮችና ሆስፒታሎች ከ30 በመቶ በላይ የሚሆነውን የናይጄሪያ ህዝብ እያገለገሉ ነው ስትል እነዚህን መደገፍ አስፈላጊ ነው ብላለች።
አሜሪካ ስምምነቶቹን በፈለገችው ጊዜ ማቋረጥ እንደምትችል ገልፃ ናይጄሪያ ክርስቲያኖችን ኢላማ ያደረገ የኃይማኖት ጥቃትን በመዋጋት ለውጥ ማምጣት ይኖርባታል ብላለች።
አሜሪካ ተመሳሳይ የጤና ዘርፍ ስምምነቶችን ከዚህ በፊት ከኬንያ ጋር ተፈራርማ ፍርድ ቤት ማገዱ ሲታወስ ከሩዋንዳ እና ኡጋንዳ ጋር ተመሳሳይ ስምምነቶችን ፈፅማለች።
አሜሪካን ቀዳሚ ያደረገውን የጤና ስምምነት በቀጣይ ሳምንትም ከብዙ ሃገራት ጋር እንደሚፈፀም አሜሪካ አስታውቃለች።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 34👎 10🤔 4
照片不可用在 Telegram 中显示
"ባንኮች ከጡረታ መዋጮ የአገልግሎት ክፍያ በሚል መቁረጥ አይችሉም" - የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
አንዳንድ ባንኮች የጡረታ ክፍያ ለተጠቃሚዎች ሲክፍሉ የአገልግሎት ክፍያ በሚል እንደሚቆርጡ ተነግሯል።
የአገልግሎት ክፍያውን እየቆረጡ ያሉት ብሄራዊ ባንክ መመሪያ አውጥቷል በሚል እንደሆነ ተጠቅሷል።
በ2014 የወጣው የጡረታ አዋጅ ግን ከጡረታ መዋጮ ገንዘብ ላይ ቀንሶ ለአገልግሎት ክፍያ፣ ለገንዘብ ማስተላለፊያ እያሉ መጠቀም እንደማይቻል ይደነግጋል ተብሏል።
ብሄራዊ ባንክ አወጣው የተባለው መመሪያ ከአዋጁ በላይ ሊሆን ስለማይችል ግን ተግባሩ ሊቆም ይገባል ሲሉ የአስተዳደሩ የህግ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ግርማ ሢሣይ አሳስበዋል።
ዘገባው የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 51👍 9
照片不可用在 Telegram 中显示
#ሰኞ
በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ባለሙያዎች በየሳምንቱ ሰኞ ጠዋት ወደ የሥራ ገበታቸው ሲመለሱ፣ በተመሳሳይ ሰዓት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደግሞ አዲስ የሥራ ዕድል ፍለጋ ወደ ኢንተርኔት እንደሚተሙ የLinkedIn መረጃዎች ያመለክታሉ።
የሥራ ማመልከቻዎች በከፍተኛ ሁኔታ የሚጨምሩት ሰዎች ከዕረፍት መልስ አዲስ ሕይወት ሲያልሙ እንደሚሆን ይታመናል።
ይሄንን በስነ-ባህሪ ባለሞያዎች "ዘ ፍሬሽ ስታርት ኢፌክት" እየተባለ ይጠራል። እንደ ሰኞ ያሉ ቀናት ያለፈውን ድክመታችንን ረስተን አዲስ ማንነት እንድንላበስ ይረዱናል።
ሰኞ ቀን "ስፖርት እጀምራለሁ" ወይም "አመጋገቤን እቀይራለሁ" የምንለውም ለዚህ ነው፤ አዕምሯችን አሮጌውን በር ዘግቶ አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት የሚዘጋጅበት ነው።
አዕምሯችን እንደ አዲስ ዓመት፣ ልደት ወይም የሳምንቱ መጀመሪያ ያሉ ቀናትን እንደ ጊዜያዊ መሸጋገሪያ ምልክቶች ይጠቀማቸዋል።
አዲስ ሥራ ፍለጋ ሰዎች ወደ ሊንኪዲን ጎራ ከማለታቸው በተጨማሪ በጎግል ፍለጋ ላይም የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ አጻጻፍን የሚፈልጉና ለቃለ-መጠይቅ ለመዘጋጀት የሚጣጣሩ ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል።
በተጨማሪም ሰዎች የሰኞን የሥራ ጫና ለመቋቋም ወይም ለማምለጥ ሲሉ፣ በሥራ ሰዓት ውስጥ ሶሻል ሚዲያ ላይ የማሳለፍና የመገበያየት (Online Shopping) ዝንባሌያቸው ይጨምራል።
በእርግጥ ይሄ ከሀገራት ሀገራት ይለያያል፥ ለምሳሌ ጃፓኖች ለሥራ ባላቸው ዲሲፕሊን ምክንያት ለእነሱ ሰኞ ማለት "የተስፋ ቀን" ነው።
ሩሲያውያን "ሰኞ ከባድ ቀን ነው" የሚል ጥንታዊ አባባል አላቸው። በዚህም ምክንያት ሰኞ ቀን አዲስ ረጅም ጉዞ መጀመር ወይም ትልቅ የቤት ውስጥ ስራ መጀመር እንደማይመከር በባህላዊ ደረጃ ያስባሉ። ቀኑን "በጥንቃቄ" ማሳለፍን ይመርጣሉ።
ለማንኛውም የተጋመሰው ሰኞ እንዴት እያለፈ ነው ?
መልካም ሳምንት !
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 47🕊 6🤬 3💔 2🤔 1
照片不可用在 Telegram 中显示
✨ከእኛ አንድ ቤት ሲገዙ ከኢትዮዽያ አየርመንገድ ET🇪🇹 Sheba Miles ደረጃዎን በእጥፍ ያሳድጉ ✈️🤝
በተጨማሪም በተመጣጣኝ ዋጋ የቤት ባለቤት ልናረጎ ሲሆን:-
እስከ 25% ቅናሽ ያላቸው በነፋሻማዋ ሰሜን ማዘጋጃ ላይ ግንባታቸው እየተካሄደ ያለ በካ.ሜ ከ65,000 ብር ጀምሮ ይዘንላቹ መተናል!
👉በ 25% ቅናሽ (100% ለሚከፍሉ ደምበኞች)
ባለ 1 መኝታ(81 ካ.ሜ)=5,300,000ብር
ባለ 2መኝታ(110ካ.ሜ)=7,200,000ብር
ባለ3መኝታ(130ካ.ሜ)=8,500,000ብር
👉በ 10% ቅድመ ክፍያ ቀሪው በግንባታ ሂደት የሚከፍሉት!
ባለ 1 መኝታ(81 ካ.ሜ) = 700,000 ብር
ባለ 2 መኝታ(110ካ.ሜ) =957,000 ብር
ባለ 3 መኝታ(130ካ.ሜ)=1,131,000ብር
✨በተጨማሪም እንደ ቅድመ ክፍያዎ ቀድመዉ ለሚመጡ 15 ደምበኞች ብቻ ከ3% እስከ 25% ቅናሽ ያለን ሲሆን ይህንን እድል ተጠቃሚ ለመሆን በ0913599755 ወይም 0912915147 ይደውሉ!
#Akoyaproperties #EthiopianAirlines #ShebaMiles #Partnership
❤ 15👍 1
照片不可用在 Telegram 中显示
አሜሪካ በቬኔዙዌላ ምን እያደረገች ነው?
አሜሪካ የኒኮላስ ማዱሮ አስተዳደር እፅ ማዘዋወርን እና ህገወጥ የሰዎችን ዝውውር ይደግፋል ካለች በኋላ መጠነ ሰፊ እርምጃዎችን በቬኔዙዌላ ላይ እየወሰደች ነው።
አሜሪካ እፅ ለማዘዋወር ይውላሉ ያለቻቸውን በርካታ የቬኔዙዌላ መርከቦች ላይ ጥቃት አድርሳ ከ100 በላይ ሰዎችን ስትገድል የማዱሮን አስተዳደርም የውጪ አሸባሪ በሚል ፈርጃለች።
አሜሪካ በቬኔዙዌላ የነዳጅ ጫኝ መርከቦችና ነዳጅ ላይ ማዕቀብ ከጣለች በኋላም ወደ ቬኔዙዌላ የሚገቡ እና ከቬኔዙዌላ የሚወጡ ታንከሮችን መያዝ ጀምራለች።
የአሜሪካ የሃገር ውስጥ ደህንነት ኃላፊ ክርስቲ ኖዬም አሜሪካ ሁለተኛውን የቬኔዙዌላ ነዳጅ ጫኝ መርከብ በሳምንት ልዩነት መያዟን ገልፀዋል።
ኃላፊዋ አሜሪካ በአካባቢው የናርኮ( የእፅ) ሽብርተኝነትን ፈንድ ለማድረግ በሚያግዘውና ማዕቀብ የተጣለበት ነዳጅ ላይ የምታደርገውን ቁጥጥር ትቀጥላለች ብለዋል።
ቬኔዙዌላ የአሜሪካ ተግባር አለም አቀፍ የባህር ውንብድና ነው ያለች ሲሆን በአለም አቀፍ የውሃ አካላት ላይ በአሜሪካ ጦር የሚፈፀምን ስርቆትም እንደምትቃወም እና ሁሉንም አይነት እርምጃ እንደምትወስድ ገልፃለች።
በአሁኑ አሜሪካ በያዘችው ታንከር ወደ ቻይና እየተጓጓዘ የነበረው 1.8 ሚሊየን በርሜል ነዳጅ ነበር ሲባል የፓናማ ሰንደቅ እንደያዘና በቬኔዙዌላ ባህር መታየቱ ለመያዙ ምክንያት እንደሆነ ተጠቁሟል።
ኋይት ሃውስ መርከቡ ሃሰተኛ ሰንደቅ መያዙን ገልፆ የታገደውን ነዳጅ ለማጓጓዝ ሲሞክር ነበር ብሏል።
ኒኮላስ ማዱሮ የአሜሪካ ተግባር እኔን ከስልጣን ለማስወገድና የቬኔዙዌላን ሃብት ለመቀራመት ነው ብለዋል።
ትራምፕ ቬኔዙዌላ የወሰደችብንን ሃብት ትመልስ ያሉ ሲሆን ፣ የወሰዱብንን ኢነርጂና ነዳጅ እንዲመልሱ እንፈልጋለን ብለዋል።
ከ1970ዎቹ በፊት አሜሪካ አብዛኛውን የቬኔዙዌላ የነዳጅ ንግድ ተቆጣጥራ የነበረ ቢሆንም ከሁጎ ቻቬዝና ማዱሮ መምጣት በኋላ መንግስት እንዲይዛቸው በመደረጉ አሜሪካ ከጨዋታ ውጪ ሆናለች።
ትራምፕ ከሃብታቻንን መልሱ በተጨማሪ ማዱሮ ህገወጥ እፆች ወደ አሜሪካ እንዲገባ እያደረጉ ነው በሚል እነዚህን እፆች ያጓግዛሉ ባሏቸው መርከቦች ላይ ጥቃት እንዲፈፀም አዘዋል።
ከባለፈው መስከረም ወር ጀምሮም አሜሪካ 28 ጥቃቶችን የፈፀመች ሲሆን 104 ሰዎችንም ገድላለች።
አሜሪካ በርከት ያለ ጦሯንና የባህር ተዋጊዎችን በካሪቢያን ያሰማራች ሲሆን አየር መንገዶችም ወደ ቬኔዙዌላ ከመብረር እንዲቆጠቡ አሳስባለች።
ትራምፕ በቅርቡ በቬኔዙዌላ የመሬት ውጊያ ይጀመራል ብለው ማስጠንቀቃቸው ደግሞ በአካባቢው እና በመላው አለም ውጥረት እንዲነግስ አድርጓል።
መረጃው የአሶሽየትድ ፕሬስና እና አልጄዚራ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 84👎 41😢 17👍 7🤬 5🤔 2
#Update
የሳምንቱን መረጃዎች በጥያቄ መልክ አቅርበን ከመቶ በላይ ተሳታፊዎች ተሳትፈዋል።
በዚህ ሳምንት ጥያቄ መልስ (10/10) 🎉 ያመጡ ቤተሰቦቻችን ዝርዝር ከላይ ተያይዟል፤ ስለተሳትፏችሁ ሁላችሁንም እናመሰግናለን 👏
#WeeklyNewsQuiz_002 #Leaderboard
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 31🙏 3👏 1
照片不可用在 Telegram 中显示
የዲጂታል ፕሮፓጋንዳ አዲስ ምዕራፍ
ከጥቂት ወራት በፊት እስራኤል በዓለም አቀፍ ደረጃ ያጋጠማትን የተቃውሞ ማዕበል ለመመከት፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) እንደ ዋነኛ የዲጂታል ዲፕሎማሲ መሣሪያ መጠቀም የሚያስችላትን ስምምነት አድርጋለች።
ስምምነቱ የእስራኤል መንግስት ከአሜሪካው Clock Tower X ኩባንያ ጋር የተፈጸመ ሲሆን የ6 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ነው።
ስምምነቱ ምንድን ነው ?
የስምምነቱ ዋነኛ ዓላማው እንደ ChatGPT ያሉ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሥርዓቶች ስለ እስራኤል እና ፍልስጤም ጉዳይ የሚሰጡትን መረጃ አስቀድሞ ለመቅረጽ ያለመ ነው።
ይህም የሚከናወነው ለዚህ ተብሎ የተዘጋጁ ልዩ የመረጃ መረቦችን በማደራጀት፣ የAI ሥርዓቶች መረጃ ሲፈልጉ የእስራኤልን መንግሥት ትረካዎች እንደ ዋነኛ ምንጭ እንዲጠቀሙ በማስቻል ነው።
በተጨማሪም የዘመቻው 80 በመቶ ትኩረት በቲክቶክ፣ ኢንስታግራም እና ዩቲዩብ ላይ የሚገኙ ወጣቶችን ኢላማ አድርጎ፤ በAI የታገዙ ቪዲዮዎች እና ፖድካስቶች ተፅዕኖ ፈጣሪ በሆነ መልኩ ለተጠቃሚዎች እንዲደርሱ ጭምር ታቅዷል።
ስምምነቱ ዩኒቨርሲቲዎችን፣ አብያተ ክርስቲያናትን እና የተወሰኑ ቋንቋ ተናጋሪ ማኅበረሰቦችን በማጥናት፣ ለእያንዳንዳቸው የሚስማማ መረጃ በማቅረብ ዓለም አቀፍ ተቃውሞን ለማርገብ አልሟል።
ዘመቻው ቢያንስ በወር 50 ሚሊዮን እይታዎችን እንዲያገኝ ታቅዶ ነው ወደ ተግባር የተገባው። Clock Tower X በተጨማሪም ሌሎች የቴክኖሎጂ ተቋማት እስራኤል በሚሊዮን ዶላሮች ታወጣለች።
ስጋቱ ምንድን ነው ?
የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ይህ ተግባር ዲጂታል መድረኮችን የመረጃ ማዛቢያ መሣሪያ ያደርጋቸዋል ሲሉ ተችተውታል።
ይህ እርምጃ የመረጃ ነፃነትን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ከማለታቸውም በላይ ወደፊት "እውነት" የሚባለው ነገር በትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና ገንዘብ ባላቸው መንግሥታት ፍላጎት ሊበላሽ እንደሚችል ትልቅ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።
እስራኤል ይህ ዘመቻ መረጃን ለማዛባት ሳይሆን፣ በኢንተርኔት ላይ ስለ እስራኤል የሚሰራጩ "ፀረ-ሴማዊ" እና የተሳሳቱ መረጃዎችን (Misinformation) ለመመከት የታለመ "ህጋዊ ዲፕሎማሲያዊ ስራ" ነው ስትል ትከላከላለች።
በመሰል ጉዳዮች ላይ ምን አስተያየት አሎት DM (💬) በማድረግ መልዕክቶን ማድረስ ይችላሉ
Source : TRT World , The Cradle , RS
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 77🤣 21👎 20👍 7🤬 6🕊 3😢 2
ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ለእሁድ አጥቢያ በተፈፀመ ጥቃት ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች ተገለዋል።
ይህ አሳዛኝ ክስተት በደቡብ አፍሪካ ከጆሃንስበርግ 48 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ቤከርስዳል ከተማ ከለሊቱ ሰባት ሰዓት አካባቢ ላይ ሲሆን 9 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ በ10 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።
እንደ ፖሊስ መረጃ ከሆነ 12 የሚሆኑ ታጣቂዎች ከሁለት መኪኖች ሆነው ወደ አንድ ቡና ቤት ደንበኞች ላይ ተኩስ በመክፈት ነው ጥቃቱን የፈጸሙት።
ቡና ቤቱ ህጋዊ ፈቃድ ያለው እንደሆነ እና የጥቃቱ ምክንያት ለጊዜው እንዳልታወቀ ፖሊስ አስታውቋል። እንደ የጋውቴንግ አውራጃ የምርመራ ባለስልጣን ገለፃ ወንጀለኞቹ ያመለጡ ሲሆን እነሱን ለመያዝ ሰፊ ዘመቻ ተጀምሯል።
በደቡብ አፍሪቃ የጅምላ ተኩስ በሰዎች ላይ ሲፈፀም ይህ ከሶስት ሳምንታት በኋላ ሁለተኛው መሆኑ ነው። ደቡብ አፍሪቃ በዓለም ላይ ከፍተኛ የግድያ ወንጀል ከሚፈፀሙባቸው ሀገራት አንዷ ናት።
እንደ አሶሺየትድ ፕረስ ዘገባ ባለፈው በጎርጎሮሲያዊው ዓመት 2024 ወደ 26,000 የሚጠጉ ግድያዎች ወይም በአማካይ በቀን ከ70 በላይ ግድያዎች በደቡብ አፍሪቃ ተፈፅመዋል።
ዘገባው የ DW ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 52😢 14👍 1🤝 1
照片不可用在 Telegram 中显示
🏠 ከኪራይ ቤት ለመውጣት አስበው ግን ያጠራቀሙት ገንዘብ አነስተኛ መስሎ ከታዮት እኛን ሳያማክሩ አይወስኑ!
👉 በ 3 አመት ጊዜ ውስጥ ቀስ እያላቹ ያለ ወለድ ከፍላቹ መሀል ከተማ ሳር ቤት እና አዋሬ ላይ የቤት ባለቤት መሆን ትችላላቹ.
🌅 ቴምር ሪል እስቴት በ8.3 ሚሊየን ብር ጠቅላላ ዋጋ በ 1.7 ሚሊየን ብር 20% ቅድመ ክፍያ ቤት የባለቤት ላርጋቹ እያለ ነው ቀሪውን 80% በ 3 አመት ጊዜ ውስጥ በግንባታ ሂደት ቀስ ብላቹ መክፈል ትችላላቹ .
👉 100% አሁን ላይ ከፍላለው ካላቹ ደግሞ 35 % ቅናሽ ተደርጎላቹ ከ5.4 ሚሊየን ብር ጠቅላላ ዋጋ ጀምሮ መግዛት ትችላላቹ .
💥ብዙ ቤቶች ተሸጠው አልቀዋል ቀሪዎቹም ተሸጠው ሳያልቅባችሁ በቢሮ ቁጥራቸው 0980782850 ደውሉ.
❤ 10👎 3👍 1😢 1
照片不可用在 Telegram 中显示
የሚዲያ ተቋሙ አልጄዚራ "The core" የተሰኘ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴል አስተዋውቋል።
መቀመጫውን ኳታር ያደረገው አልጄዚራ ከጎግል ክላውድ ጋር በመሆን "The core" ሲል የሰየመውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ይፋ ማድረጉን አስታውቋል።
አልጄዚራ ሞዴሉ AI በጋዜጠኝነት ያለውን ለዘብተኛ ሚና ወደ ንቁ ሚና ያመጣዋል ያለ ሲሆን ሞዴሉ የአልጄዚራ ጋዜጠኞች ትላልቅ መረጃዎችን እንዲያደረጁ በመርዳት ጥሩ ይዘቶችን እንዲፈጥሩና ስራቸውን እንደሚያቀላጥፍ ገልጿል።
የአልጄዚራ ዳይሬክተር ሼህ ናስር አልታኒ አልጄዚራ አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ምህዳርን ለመፍጠር ቁርጠኛ ነው ብለዋል።
የአልጄዚራ አዲሱ የAI ሞዴል ጋዜጠኞች ዜና የሚፅፉበትንና የሚያቀርቡበትን መንገድ በመቀየር ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ታምኖበታል።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 27👎 8
照片不可用在 Telegram 中显示
በአሜሪካ በ2025 ከመሳሪያ ተኩስ ጋር በተያያዘ ከ13 ሺህ ሰዎች በላይ ሞተዋል ተባለ።
ሊጠናቀቅ በተቃረበው 2025 የጅምላ ግድያ መስፈርትን ያሟሉ 17 አጋጣሚዎች ነበሩ ሲባል ከ2006 በኋላ ዝቅተኛው ስለመሆኑ ተነግሯል። ለአብነትም በ2023 42 የጅምላ ግድያ ሁነቶች ተመዝግበው ነበር።
መረጃ ሲሰበሰብ በጅምላ ግድያ የሚካተተው በ24 ሰዓት ጊዜ ውስጥ አራትና ከዛ በላይ ሰዎች የተገደሉ እንደሆነ ነው። ይህም ከመሳሪያ ግድያ ውጪ የእሳት እና የመኪናን አደጋዎችን ይጨምራል።
ለምሳሌ ባለፈው ነሐሴ በሚኒያፖሊስ ትምህርት ቤት በተፈፀመ ተኩስ 20 ሰዎች ቆስለው ሁለቱ ቢሞቱም ጉዳዩ በጅምላ ግድያ አልተመዘገበም።
በ2025 እንዲሁ በትምህርት ቤቶቸ የተፈፀመ የጅምላ ግድያም አልተመዘገበም።
በ2025 ከተፈጠሩ 17 የጅምላ ግድያ ጉዳዮች መካከል ግማሽ ያህሉ በቤተሰብ መካከል የተፈጠረ ነው ሲባል አራቱ በህዝብ ቦታዎች መፈፀማቸው ተነግሯል።
ለቁጥሩ መቀነስ የተሰሩ የባህሪ ግምገማዎችና ሰዎች የአዕምሮ መታወክ ከገጠማቸው በኋላ ሞላሽ የሚሰጡበት መንገድ መሻሻሉ በዋናነት ተጠቅሰዋል።
በአጠቃላይ በ2025 በአሜሪካ ከጥይት ተኩስ ጋር ተያይዞም 13,821 ሰዎች መሞታቸውና 24,968 ጉዳቶች መድረሳቸው ነው የተነገረው። ይህም የፖሊሶችን ተኩስ እና ራስን መከላከልን ይጨምራል።
በ2025 እድሜያቸው ከ11 አመት በታች የሆኑ 216 ህፃናት በተኩስ ምክንያት ሲሞቱ ከ12-17 ካሉት ደግሞ 962 ህፃናት ህይወታቸው አልፏል።
የሚፈፀሙ የጅምላ ተኩሶች መቀነስ ቢያሳዩም የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር አሳሳቢ መሆኑን የሚያነሱት ተመራማሪዎች የመሳሪያ ቁጥጥር ላይ ሰፊ ስራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
ዘገባው የኒውስዊክ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 33🤯 14🕊 6
በባንግላዴሽ መገደሉ ትልቅ ተቃውሞ ያስነሳው ሸሪፍ ኦስማን ማነው?
በባንግላዴሽ የወጣቶች መሪ የሆነው ሸሪፍ ኦስማን በሲንጋፖር ሆስፒታል ውስጥ ህይወቱ ማለፉ ከተሰማ በኋላ በባንግላዴሽ ተቃውሞ ተነስቷል።
ሸሪፍ ሆስፒታል እንዲገባ ያደረገውና ለህልፈት የዳረገው ደግሞ በባንግላዴሽ ዋና ከተማ ዳህካ ባለፈው ሳምንት የተተኮሰበት ጥይት ነው።
ወጣቱ ሸሪፍ ባለፈው ሳምንት ሞተር ሳይክል ላይ የነበሩ ሁለት ገዳዮች ግንባሩ ላይ ከተኮሱበት በኋላ በሲንጋፖር በሚገኝ ሆስፒታል እየታከመ የነበረ ቢሆንም ህይወቱ አልፋለች።
ሸሪፍ ኦስማን ማነው?
ሸሪፍ ኦስማን የ32 አመት ወጣት ሲሆን ባለፈው አመት በባንግላዴሽ የስርዓት ለውጥ ያስከተለውን የተማሪዎች አመጽ የመራ ወጣት ነበር።
በዳህካ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ትምህርቱን የተከታተለው ሸሪፍ የቀድሞዋን ጠቅላይ ሚኒስትርም ፋሽስት ብለ ይጠራቸው ነበር።
ሸሪፍ በቀጣይ የካቲት ወር ለሚካሄደው ምርጫ በፓርላማ አባልነት ለመወዳደር እየተዘጋጀ የነበረ ሲሆን በተማሪዎች አመፅ ከስልጣናቸው የተነሱት የቀድሞዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህ ሃሲና የተሰደደችባትን ህንድንም በመተቸት ይታወቃል።
ከግድያው በኋላ ምን ተፈጠረ?
የባንግላዴሽ ፖሊስ ሸሪፍ ላይ የተኮሱትን ለመያዝ እየጣረ መሆኑን ሲገልፅ የገዳዮቹን የምስል ቅጂ በመልቀቅም መረጃ ለሚሰጡት ሰዎች የ5 ሚሊየን ታካ(42,000 ዶላር) ሽልማት እንደሚሰጥ ገልጿል።
ገዳዮቹ ጥቁር ልብስና መነጽር የለበሱ ሲሆን እስካሁን ከግድያ ሙከራው ጋር በተያያዘ ከ20 በላይ ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል።
የሃገሪቱ ጊዜያዊ መንግስት መሪ ሙሐመድ ዩኑስ የሸሪፍ ሞት ለሃገሪቱ ትልቅ ኪሳራ መሆኑን ገልጸው ሃገሪቱ ወደ ዲሞክራሲ የምታደርገው ጉዞ በደም ማፍሰስ አይገታም ብለዋል።
የተቀሰቀሰው ተቃውሞ
የሸሪፍ ህልፈት ከተሰማ በኋላ በዋና ከተማዋ ዳህካና በመላው ባንግላዴሽ ተቃውሞ ተነስቷል።
ተቃዋሚዎች በተቃውሟቸው የሸሪፍን ደህንነት ማስጠበቅ አልቻሉም ያሏቸው የሃገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር እና የህግ ሚኒስትር ከኃላፊነት እንዲለቁ ጠይቀዋል።
ተቃዋሚዎች ሸሪፍ ላይ የተኮሱት ታጣቂዎች ወደ ህንድ ሸሽተዋል ያሉ ሲሆን፣ ተይዘው ለህግ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።
በተጨማሪ ተቃዋሚዎች ህንድ በሃገራቸው የውስጥ ጉዳይ በተለይ ምርጫ ሲደርስ ጣልቃ ትገባለች ሲሉ ለቀድሞዋ ጠቅላይ ሚኒስትርም ከለላ ሰጥታለች በሚል በባንግላዴሽ በሚገኙት የህንድ ከፍተኛው ኮሚሽን ረዳት ላይ ድንጋይ ወርውረዋል።
ተቃዋሚዎች የህንድ ደጋፊ ናቸው ያሏቸውን የሁለት ጋዜጦች ህንፃንም በእሳት አያይዘዋል።
አንዱ ጋዜጣ ለ4 ሰዓት በተፈጠረው እሳት የተነሳ 28 ጋዜጠኞቹና ሰራተኞቹ ውስጥ እንደቆዩ ገልፆ ስለደረሰ ጉዳት ምንም ሳይል ቀርቷል።
ህንድ እና ባንግላዴሽ በአለማችን ላይ ትልቁን ስድስተኛ ረጅም ድንበር ሲጋሩ ድንበራቸው 4096 ኪሎሜትር ነው።
በ1971 ባንግላዴሽ ከፓኪስታን ነፃ ስትወጣም ህንድ ለባንግላዴሽ ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ታደርግ የነበረ ሲሆን በኋላም ቀጥታ ወደ ጦርነቱ በቀጥታ ገብታ ተሳትፋለች።
እንደ ሸሪፍ ኦስማን ያሉ ወጣቶች ህንድ ከ1971 ጀምሮ በባንግላዴሽ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ትገባለች ብለው ሲተቹ፣ በተለይም አምባገነን ለሚሏት ሼህ ሃሲና ድጋፍ በማድረግ ይወቅሷታል።
ተቃዋሚዎች ለተገደለው ወጣት መሪያቸው ፍትህ እንፈልጋለን የሚል መፈክርን ይዘው አደባባይም ወጥተዋል።
ዘገባው የአልጄዚራና የፋይናንሺያል ኤክስፕረስ ነው።
ፎቶ 2: በቀብር ስርዓቱን የሚያሳይ
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 75👍 2👏 2🙏 2👎 1
照片不可用在 Telegram 中显示
✨ከእኛ አንድ ቤት ሲገዙ ከኢትዮዽያ አየርመንገድ ET🇪🇹 Sheba Miles ደረጃዎን በእጥፍ ያሳድጉ ✈️🤝
በተጨማሪም በተመጣጣኝ ዋጋ የቤት ባለቤት ልናረጎ ሲሆን:-
እስከ 25% ቅናሽ ያላቸው በነፋሻማዋ ሰሜን ማዘጋጃ ላይ ግንባታቸው እየተካሄደ ያለ በካ.ሜ ከ65,000 ብር ጀምሮ ይዘንላቹ መተናል!
👉በ 25% ቅናሽ (100% ለሚከፍሉ ደምበኞች)
ባለ 1 መኝታ(81 ካ.ሜ)=5,300,000ብር
ባለ 2መኝታ(110ካ.ሜ)=7,200,000ብር
ባለ3መኝታ(130ካ.ሜ)=8,500,000ብር
👉በ 10% ቅድመ ክፍያ ቀሪው በግንባታ ሂደት የሚከፍሉት!
ባለ 1 መኝታ(81 ካ.ሜ) = 700,000 ብር
ባለ 2 መኝታ(110ካ.ሜ) =957,000 ብር
ባለ 3 መኝታ(130ካ.ሜ)=1,131,000ብር
✨በተጨማሪም እንደ ቅድመ ክፍያዎ ቀድመዉ ለሚመጡ 15 ደምበኞች ብቻ ከ3% እስከ 25% ቅናሽ ያለን ሲሆን ይህንን እድል ተጠቃሚ ለመሆን በ0913599755 ወይም 0912915147 ይደውሉ!
#Akoyaproperties #EthiopianAirlines #ShebaMiles #Partnership
❤ 10
照片不可用在 Telegram 中显示
የራሳችንን ድምፅ በሪከርድ መስማት ለምን ያሸማቅቀናል ?
ብዙዎቻችን የራሳችንን ድምፅ ተቀድቶ በድምጽ ወይም በቪዲዮ ስንሰማው "ይህ የእኔ ድምፅ አይደለም" ከማለት አልፈን፣ በድምጻችን እንሸማቀቃለን። በሥነ-ልቦና ባለሙያዎች ይህንን ክስተት "Voice Confrontation" ይሉታል።
ይሄ ችግር የኔ ወይም የጥቂት ሰዎች ብቻ ነው ብለው ካሰቡ ተሳስተዋል፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚያደንቋቸው ታዋቂ የሚዲያ ሰዎችና ተዋናዮች እንኳ ሳይቀር የራሳቸውን ድምፅና ምስል መስማት እንደማይወዱ በግልጽ መስክረዋል።
ለምን ድምፁ ተለወጠ?
ሌሎች ሰዎች ድምፃችንን የሚሰሙበት መንገድ እና እኛ ድምፃችንን ከምንሰማበት መንገድ ይለያያል።
ለሌሎች ሰዎች ድምፃችን በአየር ሞገድ አልፎ ጆሯቸው ውስጥ ይገባል ይህንን "Air Conduction" ብለን ስንጠራው፤ እኛ የራሳችንን ድምፅ የምንሰማው ግን በሁለት መንገድ ተቀላቅሎ ነው።
አንደኛው በአየር ሲሆን፣ ሁለተኛውና ዋናው ግን በጭንቅላታችን አጥንት ውስጥ በሚያልፍ ንዝረት ወይም Bone Conduction ብለን በምንጠራው አማካኝነት ነው። ይህም ድምፅ በአጥንት ውስጥ ሲያልፍ ድምፁን ጎርናና ወይም ወፍራም አድርጎ ያሰማናል።
ስለዚህ እኛ ሁልጊዜ የምናውቀው ድምፃችንን በዚህ መልኩ ነው። ነገር ግን በሪከርድ ስንሰማው የአጥንቱ ንዝረት ስለሚቀር እና በአየር የመጣውን ብቻ ስለምንሰማው ድምፃችን ባለመድነው መልኩ እጅግ "ቀጭን" ሆኖ ይሰማናል።
ለምን እንሸማቀቃለን?
ድምፃችን ከምናስበው በላይ የማንነታችን መገለጫ ነው። በሪከርድ ስንሰማው ግን እኛ ከምናውቀው ማንነት ጋር የማይጣጣም "እንግዳ ድምፅ" ስለሚሆን አእምሯችን እንደ ስጋት ይቆጥረዋል።
ይህ ግን የሁላችንም የጋራ ችግር መሆኑን ማወቁ ለራሳችን ያለንን ግምት አሳንሰን እንዳንመለከት ይረዳናል። ሳይንሱ እንደሚለው አብላጫው ሰው የራሱን ድምፅ በሪከርድ መስማት አይወድም።
ስለዚህ ድምፅዎ በሪከርድ ሲሰሙት ቀጭን ቢመስልዎትም፣ ሌሎች ሰዎች ግን ሁልጊዜ የሚሰሙት ያንኑ ድምፅ ስለሆነ ለእነሱ ምንም ዓይነት ልዩነት የለውም። ስለዚህ በድምፅዎ ሳይሸማቀቁ መሞከር የፈለጉትን ነገር መሞከር ይችላሉ።
ዋቢ: CNN , Live Science , The Conversation
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 169🤣 66🤔 13👍 5👏 3
照片不可用在 Telegram 中显示
የሳምንቱን መረጃዎች በጥያቄ ይሞክሩ
❓ https://forms.gle/HN8knbrPEbhLo7T97
#WeeklyNewsQuiz #002
ውጤት ምሽት 3:00 ሰዓት ላይ ይለቀቃል።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 14
照片不可用在 Telegram 中显示
#Kazakhstan 🇰🇿
የካዛኪስታን ሴኔት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን የተመለከተ የመረጃ ስርጭትን #የሚያግድ ረቂቅ አፅድቋል።
ረቂቁ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን የተመለከቱ መረጃዎችን ኢንተርኔትን ጨምሮ ለሰዎች ማሰራጨትን የሚከለክል ሲሆን ተላልፈው በተገኙት ላይም ቅጣት ይጥላል።
የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን በህግ ደረጃ ባላገደችው ካዛኪስታን ከዓመት በፊት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን በተመለከተ የሚተላለፉ መረጃዎች ላይ እግድ እንዲቀመጥ ዜጎቿ ሲጠይቁ ቆይተዋል።
በፕሬዚዳንቱ ሲፀድቅ ወደ ስራ ይገባል ተብሎ በሚጠበቀው ህግ መሰረት ህጉን የተላለፈ ሰው የ144,500 Tenge(280 ዶላር ቅጣትና የ10 ቀን እስር ይጠብቀዋል ተብሏል።
ዘገባው የአናዶሉ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
👍 105❤ 42👏 26🤣 5👎 3🕊 2
照片不可用在 Telegram 中显示
የአለማችን የመጀመሪያው ትሪሊየነር ለመሆን የቀረበው ኢሎን መስክ
ከቀናት በፊት የተጣራ ሃብቱ ከ600 ቢሊየን ዶላር በመሻገር አለምን ያስደነቀው ኢሎን መስክ ከቀናት ቆይታ በኋላ ሃብቱ 700 ቢሊየን ዶላርን በመሻገር ይግረማችሁ ብሏል።
ኢሎን መስክ የዴላዌር ጠቅላይ ፍርድ ቤት 139 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ የቴስላ አክሲዮኖች ለመስክ እንዲሰጡ ከወሰነ በኋላ የቱጃሩ ሃብት 749 ቢሊየን ዶላር ደርሷል።
ኢሎን መስክ በ2018 ለቴስላ ለሰራው ስራ በወቅቱ 56 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ የክፍያ ጥቅል ከቴስላ ቢሰጠውም ፍርድ ቤት ክፍያውን አግዶበት ነበር።
የዚህን የአክሲዮን ክፍያ ፍርድ ቤቱ መስክ ለሰራው ስራ ተገቢ ነው ብሎ እንዲከፈለው እገዳውን ሲያነሳ ዋጋው 139 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ የመስክ አጠቃላይ ሃብትም ከ700 ቢሊየን ዶላር እንዲሻገር አድርጎታል።
ቢሊየነሩ መስክ ከየትኛውም ጊዜ በላይ ለትሪሊየነርነት ሲቀርብ በቅርቡ የቴስላን የአክሲዮን ገበያ ማሳደግ ከቻለና ጥሩ ስራ ከሰራ የ1 ትሪሊየን ዶላር የተመሳሳይ የአክሲዮን ክፍያ እንዲሰጠው መወሰኑ ደግሞ ለትሪሊየነርነት ጉዞው መሰላል ይሆናል።
ዘገባው የሮይተርስና ሲኤንኤን ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 70🤔 24🤷♀ 4👎 4👏 3🤣 3🔥 1
照片不可用在 Telegram 中显示
የ16 ሚሊየን ዶላሩ የክሪፕቶከረንሲ ማጭበርበር
ሮናልድ ስፔክተር የ23 ዓመት ወጣት ሲሆን ከ2023-2024 ድረስ 100 የሚሆኑ የኮይንቤዝ ዋሌት ተጠቃሚዎችን ከ16 ሚሊየን ዶላር በላይ አጭበርብሯል።
ሮናልድ እራሱን የኮይንቤዝ ተወካይ በማድረግ ተጠቂዎችን በስልክ ወይም በመልዕክት የሚያናግር ሲሆን ዋሌታቸው በመረጃ መዝባሪዎች የተነሳ ስጋት ውስጥ እንደሆነ በመግለፅ ገንዘባቸውን እሱ ወደሚቆጣጠረው ዋሌት እንዲልኩ ይጠይቃቸዋል።
በዚህ መልኩ ከ100 በላይ ሰዎችን ያጭበረበረው ሮናልድ የሚጭበረበረውን ገንዘብም ቁማር በመጫወት አጥፍቷል። ይህንንም የቴሌግራም ቻናል በመክፈት አንድ ጊዜ 6 ሚሊየን ዶላር ቁማር እንደተበላና ስለ ማጭበርበሮቹ በኩራት እንደሚናገር ተነግሯል።
ሮናልድ ይህንን ሁሉ ገንዘብ ሲያጭበረብር ምንም አይነት የክሪፕቶ ልምድ የለውም ሲባል አንድ በካሊፎርንያ የሚገኝ ሰው 6 ሚሊየን ዶላር በዚህ መንገድ ማጣቱን ይገልፃል
ይህ ነገር በክሪፕቶከረንሲ ይፈፀም እንጂ ከዘመኑ መለዋወጥ ጋር ተያይዞ አጭበርባሪዎች በተለያዩ መንገዶች ለማጭበርበር ደፋ ቀና ይላሉ።
ያልለፉበትን ለመውሰድ ከሚታትሩት ሰዎች ራሳችንን ለመጠበቅ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ ማድረግ ይገባል። አጭበርባሪዎች የሚሰሩባቸውን መንገዶች መረዳት ደግሞ ተገቢ ይሆናል።
በተለያያ መንገድ አጭበርባሪዎች ወደ እኛ ሊመጡ ስለሚችሉ አለመዘናጋት እና የትኛውንም እርምጃ ከመውሰዳችን በፊት ቆም ብለን ሁለት ጊዜ ደግመን ማሰብ ይኖርብናል።
መረጃው ከዋን ሴፍ የተወሰደ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 48🤷♂ 3🤯 2🤔 1
