ch
Feedback
TIKVAH-MAGAZINE

TIKVAH-MAGAZINE

前往频道在 Telegram

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524

显示更多
2025 年数字统计snowflakes fon
card fon
194 451
订阅者
-5824 小时
-1527
-79430
帖子存档
照片不可用在 Telegram 中显示
🚨በመሀል ፒያሳ ከአራዳ ፓርክ ትይዩ ከወዳጅነት ፓርክ እንዲሁም አብርሆት ቤተ መፅሀፍት በቅርብ ርቀት ላይ 🎄መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለውስን ቤቶች ብቻ 🎄35%🎄ቅናሽ እንዳደረግን ስንገልፅልዎ በታላቅ ደስታ ነው እርሶም ይሄን ቅናሽ በመጠቀም መሀል ፒያሳ ላይ የቤት ባለቤት የመሆን ሀሳብ ካሎት ፈጥነው ይመዝገቡ🎄 🏡ከባለ አንድ እስከ ባለ ሶስት መኝታ በ 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቀሪውን ዘና ብለው የሚከፍሉት 💎ባለ 1 መኝታ በ 514,500 ብር 💎ባለ 2 መኝታ በ 840,000 ብር 💎ባለ 3 መኝታ በ 1,207,500 ብር ቅድመ ክፍያ 🔥እንዲሁም የቤቱን 65% ሲከፍሉ 35% በድርጅቱ የሚሸፈን ይሆናል (35% ቅናሽ) 💎ባለ አንድ መኝታ ሙሉ ክፍያ 3,344,250 ብር 💎 ባለ ሁለት መኝታ ሙሉ ክፍያ 5,460,000 ብር 💎 ባለ ሶስት መኝታ ሙሉ ክፍያ 7,848,750 ብር -በግንባታ ላይ የሚገኙ ይደውሉልን የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ! ☎️0900025097 #telegram (@SamuelMERITRealtor) https://t.me/addisapartmentforu
显示全部...
10
እውቀታችንን/ ሀሳባችንን እንዳንገልጽ የገደበን የራሳችን አድሎአዊ ዝንባሌ ይሆን? አብዛኞቻችን ያለንን እውቀት ለማካፈል ከሚከለክሉን ነገሮች መካከል አንዱ ውስጣችን ያለው አድሎአዊ ዝንባሌ (Biase) ነው። ይህም ውስጣችን የሚነግረን "ሁሉም ሰው ያውቀዋል፤ ምን አዲስ ነገር አለው?" የሚል የተሳሳተ ድምዳሜ ነው። ይህም ስሜት ለራሳችን በጣም ቀላል እና ግልጽ የሆነልን ነገር ለሌላውም እንዲሁ ቀላል ይመስለናል። ነገር ግን ይህ እሳቤ ትክክል አይደለም፤ ሳይንሱም "Curse of Knowledge " ብሎ ይጠራዋል። በተግባራዊ ትርጉሙ "የእውቀት ወጥመድ" ብለን ልንሰይመው እንችላለን። ይህንን በምሳሌ ስናስረዳ፥ አንድን የምናውቀውን ዜማ በጣቶቻችን ጠረጴዛ እየመታን ብንሰማው ለእኛ ለአዕምሯችን ዜማው በሙሉ በትክክል ይሰማናል፤ ሌላውም ተመሳሳይ እንደሚሰማው እንገምታለን። ነገር ግን ሌላው ሰው የሚሰማው የጠረጴዛውን ጩኸት እንጂ ዜማውን አይደለም። በተመሳሳይ ለእርስዎ በጣም ቀላል የሆነውና የፎቶግራፍ አነሳስ፣ የምግብ አሰራር ወይም በአንድ ጉዳይ ላይ ያላችሁ እውቀት በተመሳሳይ ሌላውም የሚያውቀው ቢመስላችሁም እውነታው ግን ይህ ነገር ሌላው ሰው ለዓመታት ሲፈልገው የነበረ መፍትሄ ሊሆን ይችላል። ይህ ጉዳይ በሥራ ላይም ከፍተኛ ተጽዕኖ አለው። ብዙ የፈጠራ ሰዎችና ስራ ፈጣሪዎች ድንቅ ሀሳብ ኖሯቸው ሳይሳካላቸው የሚቀረው በገንዘብ እጥረት ብቻ ሳይሆን፣ በዚህ የአዕምሮ ወጥመድ ምክንያት ጭምር ሊሆን ይችላል። ለዚህ አስረጂ የሚሆነው፥ ብዙዎቻችን አንድ የሥራ ለመስራት አስበን "ይህማ ቀላል ነው" ብለን የተውነውን ነገር ከጊዜ በኋላ ሌሎች ሲሰሩት እና ውጤታማ ሲሆኑ ተመልክተን እናውቅ ይሆናል። ይህንን ነው Curse of Knowledge " ወይም በተግባራዊ ትርጉሙ "የእውቀት ወጥመድ" ብለን የምንጠራው። ይህ ስሜት፥ "ይህንንማ ሁሉም ያውቀዋል/ ለሁሉም ሰው ቀላል ነው" ብለን እውቀታችንን/ ሃሳባችንን እንድንደብቅ የሚያደርጉንን አድሎአዊ ዝንባሌዎች ለሌሎች ማካፈል "ለቀባሪው ማርዳት" እንደሆነ አድርጎ እንዲሰማን በማድረግ እንዳናጋራው ምክንያት ይፈጥራል። በተጨማሪም፥ "አሁን ብናገረው ይስቁብኛል/ይንቁኛል" በሚል ፍርሃት እንዲሁም "ለሰው ለማጋራት ገና ነኝ፤ እውቀቴ በቂ አይደለም" የሚሉ ስሜቶች በአዕምሯችን በመመላለስ እንድንሸማቀቅ ያደርገናል። ከዚህ ስሜት ለመውጣት ይህንን ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ ስሰማ ምን ይሰማኝ ነበር? የትኛው ክፍል ነበር ግራ ያጋባኝ?" ብሎ ራስን መጠይቅ ያሰፈልጋል። በሥራም ወቅት ምርታችንና ሀሳባችንን ለመሞከር በጉዳዩ ላይ የተሻለ እውቀት ያላቸውን ሳይሆን ዝቅተኛ እውቀት ያለውስ እንዴት አድርጎ ይጠቀመዋል ብሎ በዛ ልክ ቀሎ መሰራቱን ማረጋገጥ ይፈልጋል። በዚህ ወቅት ለእኛ በጣም ቀላል የመሰሉን ጉዳዮች የተጠቃሚዎች ችግር ሆነው ሊጠቀሱ ይችላሉ። መሰል ስሜት ውስጥ ገብተው ያውቃሉ ? ሀሳቦትን DM 💬 ማድረግ ይችላሉ። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
95👍 13🔥 4
照片不可用在 Telegram 中显示
የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት ባለፈው ጥቅምት ወር በመረጃ መዝባሪዎች ተጠልፎ እንደነበር አስታወቀ። የብሪታኒያ የንግድ ሚኒስተር ክሪስ ብሪያንት መንግስት ባለፈው ጥቅምት ወር ተጠልፎ እንደነበር ተናግረዋል። የእንግሊዝ ጋዜጦች ጥቃቱን የፈፀመው የቻይናው "Storm 1849" የሳይበር ቡድን ነው ቢሉም ሚኒስትሩ ጥቃቱ ከቻይና መንግስት ጋር የተገናኘ ነው ማለት አልችልም ብለዋል። የእንግሊዙ ዘ ሰን ጋዜጣ በቻይናው የመረጃ መንታፊ ቡድን በውጪ ጉዳይ ቢሮው ላይ ጥቃት መፈፀሙንና በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የቪዛ መረጃን ስለማግኘታቸው ዘግቦ ነበር። ሚኒስትሩ መንግስት ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገልፀው የግለሰቦች የመጋለጥ እድል ዝቅተኛ ነው ያሉ ሲሆን ችግሩ በቴክኒክ ችግር መፈጠሩና ቶሎ እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል። በዚህ አመት በብሪታኒያው ጃጉዋር ላንድሮቨር መኪና አምራች ላይ በተፈፀመ የሳይበር ጥቃት አምራቹ ለ5 ሳምንታት መኪና ማምረት ማቆሙ ሲታወስ ማርክ እና ስፔንሰር በተሰኘ መሸጫ ላይም በተፈፀመ ጥቃት ድርጅቱ ለ6 ሳምንታት የኦንላይን አገልግሎቱን ማቋረጡ ይታወሳል። ቻይና በተደጋጋሚ የምትደግፋቸው የሳይበር ቡድኖች ትላልቅ ድርጅቶችንና ፖለቲከኞችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት እንደሚፈፅሙ ሲዘገብ የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስር ኪር ስታርመርም ቻይና የብሪታኒያ ብሔራዊ የደህንነት ስጋት ነች ማለታቸው ይታወሳል። ዘገባው የሮይተርስ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
44👏 7👍 3🤔 1
照片不可用在 Telegram 中显示
🚨በመሀል ፒያሳ ከአራዳ ፓርክ ትይዩ ከወዳጅነት ፓርክ እንዲሁም አብርሆት ቤተ መፅሀፍት በቅርብ ርቀት ላይ 🎄መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለውስን ቤቶች ብቻ 🎄35%🎄ቅናሽ እንዳደረግን ስንገልፅልዎ በታላቅ ደስታ ነው እርሶም ይሄን ቅናሽ በመጠቀም መሀል ፒያሳ ላይ የቤት ባለቤት የመሆን ሀሳብ ካሎት ፈጥነው ይመዝገቡ🎄 🏡ከባለ አንድ እስከ ባለ ሶስት መኝታ በ 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቀሪውን ዘና ብለው የሚከፍሉት 💎ባለ 1 መኝታ በ 514,500 ብር 💎ባለ 2 መኝታ በ 840,000 ብር 💎ባለ 3 መኝታ በ 1,207,500 ብር ቅድመ ክፍያ 🔥እንዲሁም የቤቱን 65% ሲከፍሉ 35% በድርጅቱ የሚሸፈን ይሆናል (35% ቅናሽ) 💎ባለ አንድ መኝታ ሙሉ ክፍያ 3,344,250 ብር 💎 ባለ ሁለት መኝታ ሙሉ ክፍያ 5,460,000 ብር 💎 ባለ ሶስት መኝታ ሙሉ ክፍያ 7,848,750 ብር -በግንባታ ላይ የሚገኙ ይደውሉልን የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ! ☎️0900025097 #telegram (@SamuelMERITRealtor) https://t.me/addisapartmentforu
显示全部...
照片不可用在 Telegram 中显示
ከቀናት በፊት በአውስትራሊያ ጥቃት ሲፈፀም ጣልቃ የገባው ግለሰብ 1.6 ሚሊየን ዶላር ተበረከተለት። በቦንዲ ዳርቻ ጥቃት ወቅት ከተኳሹ ጋር ታግሎ መሳሪያውን የቀማው አህመድ አል አህመድ በልገሳ ድህረገፆች ላይ የተሰበሰበለት 1.65 ሚሊየን ዶላር ቼክ ተሰጥቶታል። አል አህመድ ከመላው አለም ከሚገኙ 43,000 ለጋሾች የተሰበሰበውን የገንዘብ ቼክ በተኛበት ሆስፒታል ተረክቧል። ከ20 አመት በፊት ሶሪያን ለቅቆ ለስራ አውስትራሊያ የከተመው አህመድ "ይህ ገንዘብ ይገባኛል? ያደረኩትን ሁሉ ያደረኩት ከልቤ ነው" ሲል ተናግሯል። አህመድ ከተኳሹ ጋር ሲታገል ተተኩሶበት ሆስፒታል የሚገኝ ሲሆን በሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርም ጉብኝት ተደርጎለታል። ዘገባው የሮይተርስ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
220👏 49🤝 4🕊 3
照片不可用在 Telegram 中显示
ሲንጋፖር አጭበርባሪዎችን በግርፋት ልትቀጣ ነው። ሲንጋፖር ከመጪው የፈረንጆቹ አዲስ አመት ጀምሮ አጭበርባሪዎችን በ24 ግርፋት እንደምትቀጣ አስታወቀች። ሲንጋፖር የማጭበርበር ተግባራት እየበዙ ነው ያለች ሲሆን አጭበርባሪዎች ከሚቀጡት የገንዘብ መቀጮ እና እስራት በተጨማሪ 1.2 ሴንቲሜትር ውፍረት ባለው መግረፊያ እርቃናቸውን ሆነው 24 ጊዜ እንደሚገረፉ አስታውቃለች። የግርፋት ቅጣት በሲንጋፖር የተለመደ ሲሆን ከ50 አመት በታች የሆኑ ወንዶች በስርቆትና ወሲባዊ ጥቃት ጥፋተኛ ሲባሉ ይቀጣሉ። ሲንጋፖር በማጭበርበር ተግባራት ወቅት ገንዘቡ እንዲሸሽ የሚተባበሩ በ12 ግርፋት ይቀጣሉ ብላለች። ሲንጋፖር ከ2020-2025 ከተፈፀሙ ወንጀሎች መካከል 60 በመቶው ከማጭበርበር ጋር የተያያዘ እንደሆነ ስትገልፅ በዚሁ ጊዜ 2.8 ቢሊየን ዶላር ኪሳራ ያደረሱ 190,000 የማጭበርበር ተግባራትም መፈፀማቸውን ገልፃለች። ከሚፈፀሙት የማጭበርበር ተግባራት መካከል ሃሰተኛ ሊንኮች፣ ሃሰተኛ ስራዎች ፣ ሃሰተኛ ኢንቨስትመንቶችና ሌሎች ሰዎችን መስሎ ማታለል ቀዳሚዎቹ ናቸው። ዘገባው የአልአረቢያ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
38🤣 35👍 13👏 6👎 1🤝 1
ከአለቃ የሚመጡ የዋትስአፕ መልእክቶች ያስጨነቁት ሰራተኛ የAI ረዳት ፈጠረ ከሥራ ሰዓት ውጭም ሆነ አብዛኛው ጊዜ ከአለቃዎ የሚመጣ ረጃጅም የዋትስአፕ መልእክት ያስጨንቆት ወይም የግል ሰዓቶን እየወሰደ ተቸግረው ይሆናል። መልእክቱን አንብበው ምላሽ ባይሰጡ ደግሞ "ሰማያዊ ምልክት" ስለሚታይ ያስጨንቃል። በዚህ የተማረረው አንድ ሕንዳዊ የሶፍትዌር ባለሙያ ለዚህ መፍትሄ ይዞ ብቅ ማለቱ አነጋጋሪ ሆኗል። የሕንዱ የቴክኖሎጂ ባለሙያ ፕራጁል ጉፕታ ከአለቃው የሚመጡ ተከታታይ የዋትስአፕ መልእክቶች እረፍት ስለነሱት ስልኩን ሳይነካ መልእክቶቹን በሙሉ ባበለጸገው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) አማካኝነት ጠቅለል አድርጎ ይሰማዋል። ይህ ባለሙያ የሠራው መሣሪያ የራሱ የሆነ አነስተኛ ስክሪን እና ድምፅ ማውጫ ያለው ሲሆን፣ ከዋትስአፕ ጋር እንዲገናኝ ተደርጓል። በዚህም ከአለቃው የሚመጡ ረጅም እና ብዙ መልእክቶችን ይሄው የኤ.አይ "ባልደረባው" መልእክቶቹን አንብቦ ዋናው ቁምነገር ይሄ ነው ብሎ በአጭሩ በድምጽ ይነግረዋል። ሌላው ትልቁ አስገራሚ ነገር መሣሪያው መልእክቱን ቢያነበውም፣ ላኪው ጋ ግን "አንብቦታል" የሚለው ሰማያዊ ምልክት አይታይም። ይህም ባለቤቱ መልእክቱን እንዳላየ ሆኖ እንዲቆይ እና በፈለገው ሰዓት ምላሽ እንዲሰጥ ዕድል ይሰጠዋል። ይህ ባለሙያ እንደገለጸው፣ ይህንን የሠራው "የሥራ እና የግል ሕይወት ሚዛንን (Work-Life Balance) ለመጠበቅ" ሲል በሬዲት ገጽ ላይ የገለጸ ሲሆን "ሁልጊዜ ስልኬ ላይ የሚመጡ መልእክቶችን እያነበብኩ ምላሽ ለመስጠት ስገደድ የግል ጊዜዬ ይባክን ነበር፤ አሁን ግን AIው አስፈላጊ የሆኑትን ብቻ ለይቶ ይነግረኛል" ብሏል። ይህ ፈጠራ ግን በግል ጥረት ለግል ችግር የቀረበ መላ እንጂ ለገቢያ የቀረበ አለመሆኑ ተገልጿል። ሆኖም ተመሳሳይነገር መሞከር ለሚፈልጉ ባለሞያው ኮዱን ጊት ሀብ ላይ አስቀምጦታል። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
3.98 MB
75👍 29🤣 14👏 11
照片不可用在 Telegram 中显示
በሶማሊያ በተከሰት ድርቅ ከ55,000 በላይ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸው ተነገረ። የተመድ የምግብና ግብርና ድርጅት ፋኦ በሶማሊያ ዝናብ ባለመዝነቡ ባጋጠመው ድርቅ የተነሳ ከ55,000 በላይ የሶማሊያ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ተሰደዋል ብሏል። የፋኦ የምስራቃዊ አፍሪካ መሪ ሲሪል ፌራንድ የኢትዮጵያ፣ የኬንያና የሶማሊያ በርካታ ቦታዎች የዝናብ እጥረት እንደገጠማቸው ተናግረዋል። ፋኦ በሶማሊያ ብቻ ከድርቁ የተነሳ ከ185,000 በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል ያለ ሲሆን የቀጣናውን ሰብዓዊ ቀውስ ያባባሰ ሆኗል ብሏል። ፌራንድ አንዳንድ ቦታዎች ከ1981 ወዲህ በዝናባማ ወቅታቸው ሪከርድ የሆነ ደረቃማ ሁኔታ ውስጥ ናቸው ሲሉ በጊዜ እርምጃ ካልተወሰደ ችግሩ ይበልጥ አስከፊ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ዘገባው የዳዋን አፍሪካ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
19😢 14🙏 2👎 1
照片不可用在 Telegram 中显示
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉 እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
显示全部...
🤣 10 6👎 6
照片不可用在 Telegram 中显示
በሶማሊያ በተከሰት ድርቅ ከ55,000 በላይ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸው ተነገረ። የተመድ የምግብና ግብርና ድርጅት ፋኦ በሶማሊያ ዝናብ ባለመዝነቡ ባጋጠመው ድርቅ የተነሳ ከ55,000 በላይ የሶማሊያ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ተሰደዋል ብሏል። የፋኦ የምስራቃዊ አፍሪካ መሪ ሲሪል ፌራንድ የኢትዮጵያ፣ የኬንያና የሶማሊያ በርካታ ቦታዎች የዝናብ እጥረት እንደገጠማቸው ተናግረዋል። ፋኦ በሶማሊያ ብቻ ከድርቁ የተነሳ ከ185,000 በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል ያለ ሲሆን የቀጣናውን ሰብዓዊ ቀውስ ያባባሰ ሆኗል ብሏል። ፌራንድ አንዳንድ ቦታዎች ከ1981 ወዲህ በዝናባማ ወቅታቸው ሪከርድ የሆነ ደረቃማ ሁኔታ ውስጥ ናቸው ሲሉ በጊዜ እርምጃ ካልተወሰደ ችግሩ ይበልጥ አስከፊ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ዘገባው የዳዋን አፍሪካ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
1
照片不可用在 Telegram 中显示
#ቴምርሪልስቴት፡ ከቃል በላይ ያስረከብናቸው ከ 8 በላይ ሳይቶች ማሳያ ናቸው። ሳር ቤት ቫቲካን 🎯65/35 አከፍፈል 👉2መኝታ 106ካሬ ሙሉ ክፍያ 7.9ሚሊዮን 👉3መኝታ 139ካሬሙሉ ክፍያ 10.3ሚሊዮን 🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል 👉2መኝታ 106ካሬ 20% ቅድመ ክፍያ 2.4ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 12.1ሚሊዮን 👉3መኝታ 139ካሬ 20%ቅድመ ክፍያ 3.1ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 15.9ሚሊዮን አዋሬ 🎯65/35 አከፍፈል 👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን 🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል 👉 1መኝታ 78ካሬ = 20%ቅድመ ክፍያ 1.7ሚሊዮን ፤ ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን 👉 3 መኝታ 117ካሬ = 20%ቅድመ ክፍያ  2.6 ሚሊዮን ፤ ሙሉ ክፍያ 12.9ሚሊዮን 👉 157 ካሬ = 20% ቅድመ ክፍያ 3.4ሚሊዮን ፤ ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን ቀሪውን 80% በ 15ዙር  ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ  ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት፤ * 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇👇👇 0980782850
显示全部...
10
照片不可用在 Telegram 中显示
በሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጠራ ከስልጣን የወረዱት ማክሮን ከሰሞኑ በፌስቡክ ተሰራጭቶ ከ12 ሚሊየን በላይ እይታዎችን ያገኘው ቪዲዮ የብዙዎች መነጋገሪያ ነበር። በዚሁ ቪዲዮ ምክንያት የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን " ከአፍሪካ መሪዎች መካከል አንዱ፣ ውድ ፕሬዚዳንት ምን ተፈጥሮብህ ነው? ተጨንቄያለሁ" የሚል መልዕክት እንደደረሳቸው በቅርቡ ለሀገር ውስጥ ጋዜጣ መናገራቸውም ተገልጿል። በውል ያልተጠቀሱት የአፍሪካው መሪ ለፕረዚዳንቱ ከላኩት መልዕክት ጋር ወታደራዊ ልብስ የለበሱ ሰዎችን የሚያሳይ ቪዲዮና በማክሮን ላይ ማንነቱ ባልታወቀ ኮሎኔል መፈንቅለ መንግስት መፈፀሙን የሚናገር ድምፅ አክለው እንደላኩላቸው ማክሮን ገልፀዋል። ይህ ቪዲዮ ግን እውነተኛ ሳይሆን በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተፈጠረ ነበረ። ቪዲዮውም በኋላ ከሜታ ጋር ንግግር ተደርጎ እንዲወገድ ለመደረግ ጥረት ቢደረግም ሜታ ህጌን አይጥስም በሚል አላወርድም ብሎ ለሳምንት ቆይቷል። በኋላ ላይ ማክሮን ቪዲዮው እንዲወርድ እራሳቸው ጣልቃ ገብተው እንደነበር በቃለ-ምልልሱ ወቅት ገልፀዋል። "Islam" በተሰኘ የፌስቡክ አካውንት ተጋራ የተባለው ቪዲዮ ከ12 ሚሊየን በላይ እይታዎች ሲኖሩት የአካውንቱ ባለቤት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ይዘቶችን በመስራት እንዴት ገንዘብ ማግኘት እንደሚቻል የሚያስተምር በቡርኪናፋሶ የሚገኝ #ታዳጊ ነበር። ልጁ ቪዲዮው ውዝግብ ከፈጠረ ከአንድ ሳምንት በኋላ ቪዲዮውን ማጥፋቱ ተገልጿል። በአብዛኞቹ ቪዲዮዎች ላይ የኦፕን ኤአዩ የቪዲዮ መስሪያ የሶራ ምስል የሚታይ ሲሆን በመተግበሪያው ተሰርቶ ሊሆን ይችላል ተብሏል። ሶራ ባለፈው ጥቅምት ወር ይፋ ከሆነ በኋላ ሰዎች በፅሁፍ ትክክለኛ የሚመስሉ የ10 ሰከንድ ቪዲዮዎችን በነፃ እንዲሰሩ ሲፈቅድ ሌሎች ውዝግቦችም ገጥመውት እንደነበር ይታወሳል። ዘገባው የዩሮ ኒውስ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
75🤣 40😢 5
照片不可用在 Telegram 中显示
ብራዚል ከእናት ወደ ልጅ የሚተላለፍን ኤችአይቪ በመግታቷ ከአለም ጤና ድርጅት እውቅና ተሰጥቷታል። ብራዚል ከእናት ወደ ልጅ የሚተላለፍን ኤችአይቪ የገታች በሁለቱ የአሜሪካ አህጉራት ብዙ ህዝብ ያላት ሃገርም ሆናለች። የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም(ዶ/ር) ከእናት ወደ ልጅ የሚተላለፍን ኤችአይቪ መግታት መቻል ለየትኛውም ሃገር ትልቅ ስኬት ነው ያሉ ሲሆን በተለይም እንደ ብራዚል ትልቅና ውስብስብ ለሆነ ሃገር ትልቅ የህብረተሰብ የጤና ስኬት ነው ብለዋል። ብራዚል በፖለቲካ ቁርጠኝነትና የጤና አገልግሎትን በማስፋፋት ማሳካት እንደሚቻል አሳይታለች ያሉት ዳይሬክተሩ ሁሉም ህፃን ያለ ኤችአይቪ እንዲወለድ ሁሉም ሃገር ማድረግ ይችላል ብለዋል። ኩባ ከእናት ወደ ልጅ የሚተላለፍን ኤችአይቪ በ2015 በመግታት ቀዳሚዋ ሃገር ስትሆን ከብራዚል ጋር 19 ሃገራት እስካሁን ይህንን ስኬት ማሳካት ችለዋል። ከእነዚህ ሃገራት 12ቱ በካሪቢያን የሚገኙ ሲሆን የተቀሩት በአውሮፓ እና እስያ ይገኛሉ። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
61👍 9
በለንደን አደባባዮች የታየው አነጋጋሪው መልዕክት በሱዳን እየተካሄደ ባለው ደም አፋሳሽ ጦርነት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) ሚና ያሳያል የተባለና የብዙዎችን ትኩረት የሳበ አንድ ግዙፍ የቢልቦርድ ማስታወቂያ በለንደን ከተማ እምብርት ላይ ተሰቅሎ ውሏል በየ80 ሰከንዱ እየተቀያየረ የሚታየው ይህ ማስታወቂያ፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተፈጠረ አንድን ምስል በመጠቀም ነው መልዕክቱ የተላለፈው። የቢልቦርዱ ይዘት እንደሚያሳየው አንዲት ወጣት ሴት በዱባይ የቅንጦት መዋኛ ገንዳ (Infinity Pool) ውስጥ ሆና፣ ከበስተጀርባ የዱባይ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች እየታዩ ሴልፊ ስትነሳ የሚያሳይ ነው። ሆኖም በዛው ምስል ጎን ደግሞ በሴቷ ስልክ ላይ የታየው ሴልፊ በዱባይ ፎቆች ፋንታ፣ በጦርነት የፈራረሰችውን ሱዳን ገጽታ ከጀርባ በማድረግ "በሱዳን ምን እየፈጸሙ እንደሆነ ካላወቅህ በስተቀር የምትነሳውው ሰልፊ ያን ያህል አያምርም" የሚል በጹሑፍ ሰፍሮበታል። ይህ ምስል በቢልቦርድ ላይ ብቻ ሳይወሰን፣ በለንደን ከተማ በሚዘዋወሩ ተሽከርካሪዎች ጎን ላይም ተለጥፎ የሰዎችን ሕሊና እንዲሞግት እየተደረገ ይገኛል። ከዚህም በተጨማሪ በምስሉ ላይ የሚገኘው QR ኮድ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) በጦርነቱ ሚና ነበራት የሚሉ የተለያዩ ሚዲያዎችን ዘገባ ዝርዝር የሚያወጣ ነው። ይህ ዘመቻ "አቫዝ" በተሰኘው ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት የሚመራ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሱዳን ጦርነት ውስጥ እያደረገች ያለውን ተሳትፎ ለዓለም ለማሳየት ያለመ ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለሙያዎች እና የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ ኤምሬትስ ለሱዳኑ ፈጣን ደጋፊ ኃይሎች (RSF) ወታደራዊ ድጋፍ ታደርጋለች ሲሉ ደጋግመው ክስ ቢያቀርቡም ኤምሬትስ ግን ይህንን ክስ "መሠረተ ቢስ ነው" ስትል ስታስተባብል ቆይታለች። ዘገባው የሚድል ኢስት ሞኒተር ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
103👍 21👏 4🤔 4🤣 2
照片不可用在 Telegram 中显示
✨ከእኛ አንድ ቤት ሲገዙ ከኢትዮዽያ አየርመንገድ ET🇪🇹 Sheba Miles ደረጃዎን በእጥፍ ያሳድጉ ✈️🤝 በተጨማሪም በተመጣጣኝ ዋጋ የቤት ባለቤት ልናረጎ ሲሆን:- እስከ 25% ቅናሽ ያላቸው በነፋሻማዋ ሰሜን ማዘጋጃ ላይ ግንባታቸው እየተካሄደ ያለ በካ.ሜ ከ65,000 ብር ጀምሮ ይዘንላቹ መተናል! 👉በ 25% ቅናሽ (100% ለሚከፍሉ ደምበኞች) ባለ 1 መኝታ(81 ካ.ሜ)=5,300,000ብር ባለ 2መኝታ(110ካ.ሜ)=7,200,000ብር ባለ3መኝታ(130ካ.ሜ)=8,500,000ብር 👉በ 10% ቅድመ ክፍያ ቀሪው በግንባታ ሂደት የሚከፍሉት! ባለ 1 መኝታ(81 ካ.ሜ) = 700,000 ብር ባለ 2 መኝታ(110ካ.ሜ) =957,000 ብር ባለ 3 መኝታ(130ካ.ሜ)=1,131,000ብር ✨በተጨማሪም እንደ ቅድመ ክፍያዎ ቀድመዉ ለሚመጡ 15 ደምበኞች ብቻ ከ3% እስከ 25% ቅናሽ ያለን ሲሆን ይህንን እድል ተጠቃሚ ለመሆን በ0913599755 ወይም 0912915147 ይደውሉ! #Akoyaproperties #EthiopianAirlines #ShebaMiles #Partnership
显示全部...
2
照片不可用在 Telegram 中显示
ኢትዮጵያ በጋዛ የሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ እንድትሳተፍ ከአሜሪካ ጥሪ እንደቀረበላት ተገለጸ። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከቀናት በፊት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ጋር በስልክ መነጋገራቸው መገለጹ ይታወሳል። በወቅቱ በውይይቱ ሁለቱ ሀገራት ለቀጠናዊ መረጋጋት እና በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን ለመገንባት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት የገለጹበት እንደነበር ስቴት ዲፖርትምንት በወቅቱ ገልጾ ነበር። ዛሬ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ይዞ በወጣው ዘገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በዚህ ውይይት ወቅት ኢትዮጵያ በጋዛ ሰርጥ በሚቋቋመው ዓለም አቀፍ የሰላም አስከባሪ ኃይል ተሳታፊ እንድትሆን መጠየቃቸውን አንስቷል። ይሁን እንጂ ዘገባው የኢትዮጵያን ምላሽም ሆነ ዝርዝር ጉዳዮችን አላካተተም። ማርኮ ሩቢዮ በአንድ ጋዜጣዊ መግለጫቸው "ያነጋገርናቸው ሀገራት ሁሉም በሚባል ደረጃ ወታደሮቻቸውን ለመላክ ምን ዓይነት ግዳጅ ውስጥ እንደሚገቡ እና የፋይናንስ አቅርቦቱ ምን እንደሚመስል ማወቅ እንደሚፈልጉ ጠቁመዋል። ማርክ ሮቢዮ ይህንን የተናገሩት ፓኪስታን ወታደሮቿን ለማሰማራት ፈቃደኝነቷን መግለጿን ተከትሎ በቀረበላቸው ጥያቄ ውቅት ሲሆን የፓኪስታንን ጥያቄ "እያጤነው ነው" ሲሉም መልሰዋል። አብዛኞቹ የአረብ ሀገራት ወታደሮቻቸውን ለመላክ "የፍልስጤም መንግስት ምስረታ የጊዜ ሰሌዳ በግልጽ እንዲቀመጥ" የሚል ጥብቅ ቅድመ ሁኔታ ሲያስቀምጡ አንዳንዶቹ የሰላም አስከባሪ ኃይሉ የእስራኤልን ወታደራዊ ፍላጎት ብቻ የሚያስፈጽም እንዳይሆን እና በሕዝባቸው ዘንድ "ተቃውሞ" እንዳያስነሳ ስጋት ገብቷቸዋል። ማርኮ ሩቢዮ ሀገራት ወታደሮቻቸው ምን ዓይነት ግዳጅ ውስጥ እንደሚገቡ ሳያውቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ አንጠብቅም ሲሉ ተናግረዋል። ይህ የጋዛ ዓለም አቀፍ የሰላም አስከባሪ ኃይል (ISF) በዋናነት ሰብዓዊ እርዳታዎች ለተጎጂዎች እንዲደርሱ ጥበቃ ማድረግን፣ የሲቪል አስተዳደሩን መደገፍ እና አካባቢው ዳግም ለሽብር ጥቃት እንዳይውል ቁጥጥር ማድረግን ዓላማ ያደረገ ተብሏል። ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ስር በኮሪያ፣ በኮንጎ፣ በሩዋንዳ፣ በቡሩንዲ፣ በላይቤሪያ፣ በሱዳን እና በቅርቡ ደግሞ በሶማሊያ ባካሄደቻቸው ስኬታማ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተቀባይነትን አስገኝቶላታል። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
🤣 189 125👏 30👎 19😢 5👍 3🤔 3🤬 3
照片不可用在 Telegram 中显示
ገቢና ወጪ በማይገናኙበት ዘመን ማወቅ ያለብን የኪስ ጥበብ ዛሬ ላይ ሱቅ ሄዶ የሚፈልጉትን ገዝቶ በደስታ መመለስ ብርቅ እየሆነ መጥቷል። የዋጋ ግሽበቱ እና የኑሮ ውድነቱ "ገቢ እና ወጪን" እንደ ሰማይ እና ምድር አራርቋቸዋል። በኪሳችን ያለው ገንዘብ ገና ሳይነካ እንደ በረዶ የሚቀልጥበት፣ "የቀረውስ የት ገባ?" ብለን የምንጨነቅበት ወቅት ላይ ነን። ዛሬ ላይ ቁጠባን ማሰብ "የቅንጦት" ሊመስል ይችላል። ገቢው ለምግብ፣ ለቤት ኪራይ እና ለትራንስፖርት እንኳ በማይበቃበት ሁኔታ ስለ የፋይናንስ አስተዳደር ማውራት ለብዙዎች የሚመለከተን አይደለም የሚል ስሜት ቢፈጥርም ለሁሉም ግን "የኪስ ጥበብ" ን ማወቅ ግድ የሚል ነው። "የኪስ ጥበብ" ማለት ባለን ጥቂት ገቢ ውስጥ የሚሾልኩ ስውር ቀዳዳዎችን መዝጋት እና በገንዘባችን ላይ ስልጣን ማግኘት ማለት ነው። በኑሮ ውድነት ወቅት የምናደርጋቸው የገንዘብ ውሳኔዎች ከቀላል ስሌት ይልቅ ከአእምሮአችን የባህሪ ሳይንስ ጋር የተያያዙ ናቸው። በኢኮኖሚ ባለሙያዎች ዘንድም የሰዎችን ኢኮኖሚያዊ ውሳኔዎች ምክንያታዊነት የሚያጠይቅ የጥናት ዘርፍ፥ "ባህሪያዊ ኢኮኖሚክስ" ይባላል። ታዲያ ሳይንሱና የዘርፉ ባለሞያዎች ምን ይመክሩን ይሆን ? ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ አንድ ሰው በገንዘብ እጥረት ውስጥ ሲሆን አዕምሮው "Scarcity Mindset" በሚባል ሁኔታ ውስጥ ይገባል። ይህ ሁኔታ የአንድን ሰው የማሰብ አቅም (Cognitive Bandwidth) ይቀንሳል። በዚህ ጊዜ አዕምሯችን ለዛሬው ጭንቀት ጊዜያዊ መፍትሄ መስጠት ላይ ያተኩርና የፋይናንስ ውሳኔያችን ላይ ደካማ ይሆናል። ለዚህ መፍትሔው ወሳኝ ለሆኑ ወጪዎች አስቀድሞ ውሳኔዎችን መወሰንና ቅደም ተከተል መስጠት ይሆናል። ሌላው፥ ለገቢዎቻችን የምንሰጠው የተለያየ ዋጋ ( Mental Accounting) ነው። የኖቤል ተሸላሚው ሪቻርድ ታለር፥ ሰዎች ገንዘብን እንደ ምንጩ ይለያዩታል፤ ከደሞዝ የተገኘን እና በስጦታ የተገኘን እኩል ዋጋ አንሰጣቸውም ይላሉ። "ይህችማ ድንገት የመጣች ናት" በሚል ስሜት ከደሞዝ ውጭ የሚገኙ ገቢዎችን ያለምንም እቅድ የማባከን ዝንባሌ በብዙዎች ዘንድ ይስተዋላል። ሆኖም ገንዘቡ የመጣበት መንገድ ሳይሆን፣ ያለው የመግዛት አቅም ላይ ማተኮር ይመከራል። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት ማኅበራዊ ኑሮ ጎልቶ በሚታይበት፤ ሰዎች "ተቀባይነት" ለማግኘት ወይም ለይሉኝታ ብለው ተጽዕኖ ውስጥ ይወድቃሉ። በዚህም ባልታቀደ ወጪ ላይ ይወድቃሉ። ለዚህም የሚመከረው ለወጪዎች አስቀድሞ እቅድ ማስቀመጥ፤ ለምናወጣው ወጪ ጣራ (Limit) መወሰንና ለቅርብ ሰዎች ማሳወቅን ነው። ይህንን ማድረጋችን በአዕምሯችን ውስጥ "ማኅበራዊ ውል" ስለሚፈጥር በወቅቱ ለሚመጣ ስሜታዊ ግፊት የመሸነፍ እድላችንን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል። በሌላ በኩል አንድ አስፈላጊ ያልሆነ ዕቃ ለመግዛት ስታስቡ፣ ውሳኔውን ለ24 ሰዓት ማዘግየት አዕምሮ ከስሜታዊነት ወጥቶ ወደ ምክንያታዊነት እንዲመለስ ዕድል ይሰጠዋል ተብሎ ይጠበቃል። በተለያየ ጊዜ የወጡ ጥናቶችና የባለሞያዎች አስተያየት ለጹሑፉ በግብዓት ተጠቅመናል። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
125🙏 21👍 9💯 4
照片不可用在 Telegram 中显示
ገቢና ወጪ በማይገናኙበት ዘመን ማወቅ ያለብን የኪስ ጥበብ ዛሬ ላይ ሱቅ ሄዶ የሚፈልጉትን ገዝቶ በደስታ መመለስ ብርቅ እየሆነ መጥቷል። የዋጋ ግሽበቱ እና የኑሮ ውድነቱ "ገቢ እና ወጪን" እንደ ሰማይ እና ምድር አራርቋቸዋል። በኪሳችን ያለው ገንዘብ ገና ሳይነካ እንደ በረዶ የሚቀልጥበት፣ "የሄደው ይሂድ እንጂ የቀረው የት ገባ?" ብለን የምንጨነቅበት ወቅት ላይ ነን። ዛሬ ላይ ቁጠባን ማሰብ "የቅንጦት" ሊመስል ይችላል። ገቢው ለምግብ፣ ለቤት ኪራይ እና ለትራንስፖርት እንኳ በማይበቃበት ሁኔታ ስለ ፋይናንስ ማውራት ከባድ ነው። ነገር ግን፣ ሁኔታው በከፋ ቁጥር ይበልጥ የሚያስፈልገን "ገንዘብ" ሳይሆን "የኪስ ጥበብ" ነው። "የኪስ ጥበብ" ማለት ባለን ጥቂት ገቢ ውስጥ የሚሾልኩ ስውር ቀዳዳዎችን መዝጋት እና በገንዘባችን ላይ ስልጣን ማግኘት ማለት ነው። በኑሮ ውድነት ወቅት የምናደርጋቸው የገንዘብ ውሳኔዎች ከቀላል ስሌት ይልቅ ከአእምሮአችን የባህሪ ሳይንስ ጋር የተያያዙ ናቸው። በኢኮኖሚ ባለሙያዎች ዘንድም የሰዎችን ኢኮኖሚያዊ ውሳኔዎች ምክንያታዊነት የሚያጠይቅ የጥናት  ዘርፍ ባህሪያዊ ኢኮኖሚክስ ይባላል። ሳይንሱ ምን ይመክረን ይሆን ? ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ አንድ ሰው በገንዘብ እጥረት ውስጥ ሲሆን አእምሮው "Scarcity Mindset" በሚባል ሁኔታ ውስጥ ይገባል። ይህ ሁኔታ የአንድን ሰው የማሰብ አቅም (Cognitive Bandwidth) ይቀንሳል። በዚህ ጊዜ አዕምሯችን ለዛሬው ጭንቀት ጊዜያዊ መፍትሄ መስጠት ላይ ያተኩርና የፋይናንስ ውሳኔያችን ላይ ደካማ እንሆናለን። ለዚህ መፍትሔው ወሳኝ ለሆኑ ወጪዎች አስቀድሞ ውሳኔዎችን መወሰንና ቅደም ተከተል መስጠት ይሆናል። ሌላው ለገቢዎቻችን የምንሰጠው የተለያየ ዋጋ ( Mental Accounting) ነው። የኖቤል ተሸላሚው ሪቻርድ ታለር (Richard Thaler) ሰዎች ገንዘብን እንደ ምንጩ ይለያዩታል፤ ከደሞዝ የተገኘን እና በስጦታ የተገኘን እኩል ዋጋ አንሰጣቸውም ይላሉ። "ይህችማ ድንገት የመጣች ናት" በሚል ስሜት ከደሞዝ ውጭ የሚገኙ ገቢዎችን ያለምንም እቅድ የማባከን ዝንባሌ በብዙዎች ዘንድ ይስተዋላል። ሆኖም ገንዘቡ የመጣበት መንገድ ሳይሆን፣ ያለው የመግዛት አቅም ላይ ማተኮር ይመከራል። እንደ ኢትዮጵያ አይነት የማኅበራዊ ኑሮ በስፋት ባለበት ማኅበረሰብ ውስጥ ሰዎች "ተቀባይነት" ለማግኘት ወይም ለይሉኝታ ብለው ተጽዕኖ ውስጥ ይወድቃሉ። ለዚህም ለወጪዎች አስቀድሞ እቅድ ማስቀመጥ፤ ለምናወጣው ወጪ ጣራ (Limit) መወሰንና ለቅርብ ሰዎች ማሳወቅ። ይህ በአእምሯችን ውስጥ "ማህበራዊ ውል" ስለሚፈጥር በወቅቱ ለሚመጣ ስሜታዊ ግፊት የመሸነፍ እድላችንን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል። በሌላ በኩል አንድ አስፈላጊ ያልሆነ ዕቃ ለመግዛት ስታስቡ፣ ውሳኔውን ለ24 ሰዓት ማዘግየት አዕምሮ ከስሜታዊነት ወጥቶ ወደ ምክንያታዊነት እንዲመለስ ዕድል ይሰጠዋል ተብሎ ይጠበቃል። በተለያየ ጊዜ የወጡ ጥናቶችና የባለሞያዎች አስተያየት ለጹሑፉ በግብዓት ተጠቅመናል። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
1
照片不可用在 Telegram 中显示
የሳን ፍራንሲስኮ ከተማ በከተማዋ ለሚኖሩ ጥቁር ማህበረሰቦች የካሳ ፈንድ እንዲመሰረት ወስናለች። የሳን ፍራንሲስኮ ከተማ በከተማዋ ፖሊሲ የተነሳ መገለል ለደረሰባች ጥቁር ነዋሪዎችን የሚጠቅም ፈንድ እንዲመሰረት ወስናለች። ካሳው ጥቁር ለሆኑ ወይም በባሪያ ንግድ የመጡ ሰዎች ዘር ለሆኑና በከተማዋ ተጨባጭ ጉዳትና መበደል ለደረሰባቸው ጥቁሮች እንደሚሰጥና እስከ 5 ሚሊየን ዶላር የሚደርስ ክፍያ ሊሰጥ እንደሚችልም ተነግሯል። ከገንዘብ ክፍያው በተጨማሪ የመኖሪያ ቤትና የታክስ ቅነሳ ሊደረግ እንደሚችልም ተጠቁሟል። ከተማዋ ባደረገችው መልሶ ግንባታ ወቅት የከተማዋን 5 በመቶ የሚሸፍነው የጥቁር ማህበረሰብ መኖሪያውን በብዛት ያጣ ሲሆን ከፍተኛ በደልም ደርሶበታል። በካሊፎርኒያ ግዛት የምትገኘውና ከ827,000 በላይ ነዋሪዎች ያሏት የሳን ፍራንሲስኮ ከተማ የመሰረተችው ፈንድም በከተማዋ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ይመራል ተብሏል። ዘገባው የኒውዮርክ ፖስት ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
100👎 13👍 6👏 4
照片不可用在 Telegram 中显示
በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በጣለው ከባድ ዝናብ የተነሳ በረራዎች ተሰረዙ። በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ የተነሳ ዋና ዋና ከተሞች በጎርፍ ሲጥለቀለቁ ኤርፖቶች በረራቸውን እየሰረዙ ነው። የዱባዩ ኤምሬትስ አየር መንገድ ዛሬ 13 በረራዎቹን ሲሰርዝ በሻርጃህም በረራዎች ተሰርዘዋል። የሻርጃህ ዋናው አውራ ጎዳና በጎርፍ ሲጥለቀለቅ የዱባይ ፖሊስ የከተማው ነዋሪዎች ቤታቸው እንዲቆዩ አስጠንቅቋል። በ2024 በነበረው ከባድ ዝናብ በዱባይ ብቻ ከ2000 በላይ በረራዎች መሰረዛቸው ሲታወስ በሌላኛዋ የባህረ ሰላጤ ሃገር ኳታርም ባለው ከባድ ዝናብ የተነሳ የፊፋ የአረብ ዋንጫ የደረጃ ጨዋታ ተሰርዟል። ባለፈው አመት በኤምሬቶች ሪከርዶች መመዝገብ ከጀመሩበት ከ76 አመታት በኋላ የታየ ከባድ ዝናብ መዝነቡ ሲታወስ 4 ሰዎችም ሞተው ነበር። ዘገባው የAFP ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
显示全部...
37🤔 2