2025 年数字统计

194 451
订阅者
-5824 小时
-1527 天
-79430 天
帖子存档
照片不可用在 Telegram 中显示
🌟🌟ታላቅ የበዓል ቅናሽ በካሬ 78,000 ብር
✅እንዲሁም ሙሉ ክፍያ ለሚከፊል በካሬ 54,800
🔷 በ10 % ቅድመ ክፍያ
🔷 50 % የባንክ ብድር የተመቻቸለት
📍Location እንግሊዝ ኢንባሲ አጠገብ ውብ እይታ (Top View) ያላቸው ቤቶች በሽያጭ ላይ እንገኛለን
👉ከባለ 2 መኝታ- ባለ4 መኝታ
✅ ህንፃው ላይ ያሉ ተጨማሪ አገልግሎትች
👉5 ሰፋፊ ሊፍት /elevator
👉የቆሻሻ መጣያ/garbage chute
👉አውቶማቲክ ጀኔረተር/ automatic generator
👉ሰገነት/terrace
👉የመኪና ማቆምያ/car parking
👉 ጂም , እስፖ
👉 የዋና ገንዳ
👉 የልጆች መጫወታ
✨ባለ 2 መኝታ ✨ባለ 3 መኝታ ✨ ባለ 4 መኝታ
138 ካሬ 152.4 ካሬ 240.7 ካሬ
157.3 ካሬ 158.1 ካሬ 258.4 ካሬ
163.6 ካሬ 187.6 ካሬ 211.5 ካሬ
📞 ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
0973559591
Telegram -@Homef17
❤ 17
照片不可用在 Telegram 中显示
ስልኮ መልክዎን እያበላሸው ይሆን?
ቆዳችንን ከፀሐይ ጨረር ለመጠበቅ እንጠነቀቃለን፤ ነገር ግን በቀን ለሰዓታት ከምንመለከተው ስልክና ኮምፒውተር የሚወጣው "ሰማያዊ ብርሃን" (Blue Light) ተመሳሳይ ወይም የከፋ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ጥናቶች እያመለከቱ ነው።
እንደ "Journal of Investigative Dermatology" ያሉ የቆዳ ጤና ጥናት ተቋማት ላይ የወጡ ጥናቶች፤ ለረጅም ሰዓታት ለዲጂታል ስክሪኖች መጋለጥ የቆዳን ጥንካሬ በማዳከም ቆዳችን ያለዕድሜው እንዲሸበሸብ ያደርጋል ይላሉ።
ከስክሪን የሚወጣው ሰማያዊ ብርሃን ወደ ቆዳችን ጥልቅ ክፍል (Dermis) ዘልቆ በመግባት የቆዳን ወጣትነት የሚጠብቀውን ኮላጅን (Collagen) እና ኤላስቲን (Elastin) ይሰብራል። ይህም ቆዳ እንዲላላ፣ እንዲዝልና ጥቁር ነጠብጣቦች እንዲፈጠሩ ያደርጋል።
የቆዳ ሐኪሞች እንደሚመክሩት፤ በስልካችን ላይ "Blue Light Filter" ወይም "Night Mode" ማብራት የብርሃኑን ኃይል ለመቀነስ ይረዳል።
በተጨማሪም፣ የቆዳን መከላከያ አቅም የሚጨምሩ በ"አንቲ-ኦክሲዳንት" የበለጸጉ የቆዳ ቅባቶችን መጠቀምና ከስክሪን ራቅ ያለ ጊዜን ማዘውተር ለቆዳ ጤና ወሳኝ እንደሆነም ያስቀምጣሉ።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 64🙏 8🤣 3🤔 2👎 1
照片不可用在 Telegram 中显示
ቲክቶክ የአሜሪካ ተቋሙን ለመሸጥ የሚያስችለውን የመጨረሻ ፊርማ ፈርሟል።
ቲክቶክ የአሜሪካ ተቋሙን ኦራክልና ሲልቨር ሌክ እና በአቡዳቢው MGX ለተመሰረተው ጥምረት ለመሸጥ የቀረበውን ስምምነት ፈርሟል።
ስምምነቱ የመጣው ቲክቶክ የአሜሪካ ተቋሙን ለአሜሪካ ተቋማት ካልሸጠ አሜሪካ ቲክቶክን በሃገሯ እንደምትዘጋ መግለጿን ተከትሎ ነው።
ሶስቱ ድርጅቶች የቲክቶክ አሜሪካን የ45 በመቶ ድርሻ ሲይዙ 20 በመቶው በቲክቶክ ባለቤት ባይትዳንስ ሲያዝ ቀሪው በሌሎች ኢንቨስተሮች ይያዛል።
በተጨማሪ ተቋሙ አሜሪካውያን የበላይ በሆኑበት 7 የዳይሬክተሮች ቦርድም ሲመራ አንዱ ቀጥታ የአሜሪካ መንግሰት ተወካይ እንደሚሆን ተገልጿል።
ቲክቶክ ለአሜሪካ ተጠቃሚዎች ብቻ የሚሆን መተግበሪያ እየሰራ ነበር ሲባል አሁን ያሉት ተጠቃሚዎች ወደዚህ አዲስ መተግበሪያ ለመዞር ፈቃደኝነታቸውን ይጠየቃሉ።
ቲክቶክ ከ170 ሚሊየን በላይ የአሜሪካ ተጠቃሚዎች እንዳሉት ሲታወቅ የአሜሪካ ተቋማቱ የአሜሪካ ተጠቃሚዎችን መረጃ የማስጠበቅ ኃላፊነት አለባቸው ተብሏል።
የስምምነቱ መፈረም ለአሜሪካ እና ፕሬዚዳንት ትራምፕ ትልቅ ድል ተደርጎም ተወስዷል።
ቲክቶክ የአሜሪካን መረጃ በመሰብሰብ በሚል ተዘግቶ መቆየቱና ከትራምፕ መምጣት በኋላ እገዳው ተነስቶ ድርድር መደረግ መጀመሩ የሚታወስ ነው።
ዘገባው የኢንዲፔንደንት ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 40👍 6
照片不可用在 Telegram 中显示
ቡርኪናፋሶ፣ ማሊና ኒጀር የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ የሚያስችል የኢንቨስትመንት ባንክ መሰረቱ።
ሶስቱ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ስልጣን በያዙ መሪዎች የሚመሩ ሃገራትና ከኢኮዋስ በመውጣት የራሳቸውን ጥምረት የመሰረቱት ሃገራት በሶስቱ ሃገራት ልማትን ሊያመጣ ይችላል ያሉትን የልማትና የኢንቨስትመንት ባንክን መስርተዋል።
የባንኩ መነሻ ካፒታል 895 ሚሊየን ዶላር መሆኑ ተገልጿል።
ሶስቱ ሃገራት የኢንቨስትመንት ባንኩን ባለፈው ግንቦት ወር ለመመስረት እንዳቀዱ ሲነገር በሶስቱ ሃገራት የኢኮኖሚ ትስስርን በማሳደግና የመሰረተ ልማት ግንባታን በመደገፍ የኢኮኖሚ ልማት ያመጣል ተብሎ ተገምቷል።
ዘገባው የአናዶሉ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 85👏 15🔥 4👍 3🤬 2😢 2👎 1
照片不可用在 Telegram 中显示
#በእጅዎ
ቤት ወይም አፓርትመንት ገዢ ፣ ሻጭ ፣ አከራይ ፣ ተከራይ ፣ ወይም አብሮ አልሚ ወደ አፕሊኬሽናችን በመቀላቀልዎ ብቻ ግብይቱ ሲጠናቀቅ ለሽያጭ እና አብሮ ማልማት እስከ 0.8% ለኪራይ እስከ 4% የ ሪፈራል ክፍያ ይቀበሉ።
የሞባይል መተግበሪያውን ያውርዱና ይቀላቀሉን 👉https://beijoholding.com/
❤ 8
照片不可用在 Telegram 中显示
✨ከእኛ አንድ ቤት ሲገዙ ከኢትዮዽያ አየርመንገድ ET🇪🇹 Sheba Miles ደረጃዎን በእጥፍ ያሳድጉ ✈️🤝
በተጨማሪም በተመጣጣኝ ዋጋ የቤት ባለቤት ልናረጎ ሲሆን:-
እስከ 25% ቅናሽ ያላቸው በነፋሻማዋ ሰሜን ማዘጋጃ ላይ ግንባታቸው እየተካሄደ ያለ በካ.ሜ ከ65,000 ብር ጀምሮ ይዘንላቹ መተናል!
👉በ 25% ቅናሽ (100% ለሚከፍሉ ደምበኞች)
ባለ 1 መኝታ(81 ካ.ሜ)=5,300,000ብር
ባለ 2መኝታ(110ካ.ሜ)=7,200,000ብር
ባለ3መኝታ(130ካ.ሜ)=8,500,000ብር
👉በ 10% ቅድመ ክፍያ ቀሪው በግንባታ ሂደት የሚከፍሉት!
ባለ 1 መኝታ(81 ካ.ሜ) = 700,000 ብር
ባለ 2 መኝታ(110ካ.ሜ) =957,000 ብር
ባለ 3 መኝታ(130ካ.ሜ)=1,131,000ብር
✨በተጨማሪም እንደ ቅድመ ክፍያዎ ቀድመዉ ለሚመጡ 15 ደምበኞች ብቻ ከ3% እስከ 25% ቅናሽ ያለን ሲሆን ይህንን እድል ተጠቃሚ ለመሆን በ0913599755 ወይም 0912915147 ይደውሉ!
#Akoyaproperties #EthiopianAirlines #ShebaMiles #Partnership
❤ 10
照片不可用在 Telegram 中显示
ናይጄሪያ የማይክሮሶፍት ተጠቃሚዎችን ኢላማ ያደረገ የማጭበርበር ተግባር ሲፈፅም የነበረ ግለሰብ ማሰሯን ገለፀች።
ናይጄሪያ ኦኪቲፒ ሳሙኤል የተባለና "Raccoon0365" በመባል የሚታወቀው ግለሰብ በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ የማይክሮሶፍት ተጠቃሚዎችን ኢላማ ያደረገ የማጭበርበር ስራዎችን ሲሰራ ነበር ብላለች።
ሳሙኤል የቴሌግራም ቻናል በመጠቀም ሃሰተኛ የመግቢያ ማስፈንጠሪያዎችን ይሸጥ እንደነበርና ክሪፕቶከረንሲ ለመዝረፍ የሚያገለግሉ ገፆችን ያዘጋጅ እንደነበር ተገልጿል።
የሳሙኤል እስር የመጣው ኤፍቢአይ እና ማይክሮሶፍት "Raccoon0365" የተባለው አገልግሎት ከአጭበርባሪ ድህረገፆች ጋር መተሳሰሩን እና የበርካቶች መረጃ መሰረቁን ካስታወቁ በኋላ ነው።
የዲጂታል ፎረንሲክ ምርመራዎች ከማጭበርበሩ ብቸኛው ተጠቃሚ እራሱ ሳሙኤል ብቻ መሆኑን ሲያመላክቱ ተጨማሪ ምርመራዎች ይቀጥላሉ ተብሏል።
ማይክሮሶፍት ባለፈው መስከረም ወር በዚሁ "Raccoon0365" በተባለ አገልግሎት ስር ከ94 ሃገራት የ5000 የማይክሮሶፍት ተጠቃሚዎች መረጃ መሰረቁን እና ለዚሁ አገልግሎት የሚውሉ 338 ድህረገፆችን መዝጋቱን መግለፁ ይታወሳል።
ዘገባው የDW ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 31👎 4🤔 3👍 2
照片不可用在 Telegram 中显示
ጭንቀትን ለማሸነፍ ለ20 ደቂቃ ከተፈጥሮ ጋር ማሳለፍ የተሻለ መፍትሔ ነው ተብሏል።
በዘመናዊው የከተማ ኑሮና በስራ ጫና ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች "ተፈጥሮ" ከማንኛውም መድኃኒት በላይ አዳሽና ለጭንቀት መፍትሔ መሆኑን ጥናቶች ይጠቁማሉ።
በሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ (University of Michigan) የተካሄደውና በ "Frontiers in Psychology" መጽሔት ላይ የታተመው አንድ ጥናት፤ በቀን ውስጥ ለ20 ደቂቃ ብቻ ከተፈጥሮ ጋር ጊዜ ማሳለፍ በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የጭንቀት ሆርሞን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ አረጋግጧል።
የጥናቱ ግኝት ምን ይላል?
ተመራማሪዎቹ "የተፈጥሮ ክኒን" (Nature Pill) ብለው በሰየሙት በዚህ ጥናት፤ ሰዎች ስልክ ሳይጠቀሙ፣ ኢንተርኔት ሳይመለከቱ ወይም መጽሐፍ እንኳ ሳያነቡ ለ20 ደቂቃ ብቻ አረንጓዴ ስፍራዎች ውስጥ መቀመጥ ወይም በእግር መጓዝ የጭንቀት መጠናቸውን በ21% እንደሚቀንስላቸው ደርሰውበታል።
ይህ ውጤታማ እንዲሆን ግዴታ ወደ ሩቅ ቦታ መሄድ አይጠበቅብዎትም፤ በአቅራቢያዎ ባለ ፓርክ፣ በጓሮዎ ውስጥ አልፎ ተርፎም ዛፎች ባሉበት መንገድ ላይ በእርጋታ መቆየት በቂ ነው ተብሏል።
ዋናው ነጥብ ግን በእነዚህ 20 ደቂቃዎች ውስጥ ከቴክኖሎጂ መራቅና አእምሮን ከተፈጥሮ ድምፅና ቀለም ጋር ማገናኘት ግድ ይላል።
ጥናቱ ሳይንሳዊ መንገድን ተጠቅሞ ይፋ ቢያደርገውም በርካቶች ዘንድ የተለመደ ተግባር ነው። እርሶ ሞክረውት ያውቁ ይሆን ?
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 114👍 31
照片不可用在 Telegram 中显示
ሞዛምቢክ አንዳንድ እቃዎች ወደ ሃገር ውስጥ እንዳይገቡ እገዳ ጥላለች።
ሞዛምቢክ እገዳውን የጣለችው የሃገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎችን ለማበረታታት እና የውጪ ምንዛሬን ለመቆጠብ ነው ብላለች።
የሞዛምቢክ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በውሳኔው የውጪ ምንዛሬ በጣም አስፈላጊ ለሆኑ እቃዎች ብቻ እንዲውል በማሰብ እንደተወሰነ ገልጿል።
እገዳው ጊዜያዊ ሲሆን እገዳው ከተጣለባቸው መካከል የታሸገ ውሃ፣ ፓስታ፣ ዱቄት እና ጨው ይገኙበታል።
እገዳው ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ የእነዚህ ምርቶቸ መጠን ላይ ገደብ ማስቀመጥ ሲሆን ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ እና ስለመጠኑ የተባለ ነገር የለም።
ዘገባው የሜድአፍሪካ ታይምስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 31👍 14
照片不可用在 Telegram 中显示
ሴቶችን የሚያበቃ ሕይወትን የሚቀይር ስምምነት ተፈፀፈ!
ድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ እና ጆርዳን ቢዩቲ አካዳሚ ሴቶችን በሙያና በፋይናንስ ለማብቃት የሚያግዝ የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ሥነ-ሥርዓት በመፈጸም አዲስ ምዕራፍ ከፍተዋል.
ይህ የስራ ስምምነት "ዛሬ ይማሩ ነገ ይክፈሉ!” በሚል መርህ ያለ ምንም ዋስትና ብድር በማቅረብ ብዙ ሴቶች የውበት ሙያ ስልጠና በመውሰድ ራሳቸውን የሚችሉበት ገቢ ማምጣት የሚያስችላቸውን ዕድል ይፈጥራል።
ይህ ከንግድ ባሻገር ማህበራዊ ለውጥን የሚያመጣ፣ ለሴቶች ተስፋን የሚያበራ እና ለሌሎች ተቋማት አርአያ የሚሆን ትብብር ነው። በዚህ የመግባቢያ ስምምነት ላይ የተለያዩ የሚድያ አካላት ተገኝተዋል።
ለበለጠ መረጃ ደሞ 6575 ላይ ይደውሉ!
ድጋፍ አነስተኛ ብድር አቅራቢ አ/ማ
❤ 27🤔 6
照片不可用在 Telegram 中显示
🚨በመሀል ፒያሳ ከአራዳ ፓርክ ትይዩ ከወዳጅነት ፓርክ እንዲሁም አብርሆት ቤተ መፅሀፍት በቅርብ ርቀት ላይ
🎄መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለውስን ቤቶች ብቻ 🎄35%🎄ቅናሽ እንዳደረግን ስንገልፅልዎ በታላቅ ደስታ ነው እርሶም ይሄን ቅናሽ በመጠቀም መሀል ፒያሳ ላይ የቤት ባለቤት የመሆን ሀሳብ ካሎት ፈጥነው ይመዝገቡ🎄
🏡ከባለ አንድ እስከ ባለ ሶስት መኝታ በ 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቀሪውን ዘና ብለው የሚከፍሉት
💎ባለ 1 መኝታ በ 514,500 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 840,000 ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 1,207,500 ብር ቅድመ ክፍያ
🔥እንዲሁም የቤቱን 65% ሲከፍሉ 35% በድርጅቱ የሚሸፈን ይሆናል (35% ቅናሽ)
💎ባለ አንድ መኝታ ሙሉ ክፍያ 3,344,250 ብር
💎 ባለ ሁለት መኝታ ሙሉ ክፍያ 5,460,000 ብር
💎 ባለ ሶስት መኝታ ሙሉ ክፍያ 7,848,750 ብር
-በግንባታ ላይ የሚገኙ
ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelMERITRealtor)
https://t.me/addisapartmentforu
❤ 16👎 2😢 2👍 1
照片不可用在 Telegram 中显示
"ባህላዊ ሕክምና ያለፈ ታሪክ አይደለም" ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም
የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በሕንድ ኒው ዴሊ ባካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ፣ ባህላዊ ሕክምናን ከዘመናዊው ሳይንስ ጋር ለማገናኘት "ሰው ሰራሽ አስተውሎት" (AI) ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት አስታውቋል።
ይህ ስትራቴጂ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የሚታደገውን የባህላዊ መድኃኒት ዘርፍ፣ በሳይንሳዊ ምዘና እና በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ ያለመ ነው።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር፣ "ባህላዊ ሕክምና ያለፈ ነገር አይደለም፤ ይልቁንም በየሀገራቱ ያለው ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል" ሲሉ ገልጸዋል።
በጉባኤው ላይ የተገኙት የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በበኩላቸው፣ ዘርፉ ያለውን እምቅ አቅም ወደ ሳይንሳዊ ምርምር ለመቀየር ቴክኖሎጂ ወሳኝ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው፣ በ90 በመቶ ከሚሆኑት አባል ሀገራት ውስጥ ከ40 እስከ 90 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ባህላዊ ሕክምናን ይጠቀማል።
ከዚህም በላይ፣ ግማሽ ያህሉ የዓለም ህዝብ ዘመናዊ የጤና አማራጮችን ባለማግኘቱ ሙሉ በሙሉ ጥገኛ የሆነው በባህላዊ መድኃኒቶች ላይ ነው።
ይሁን እንጂ መድኃኒቶቹ በቂ ሳይንሳዊ ምዘና ስር ባለማለፋቸው ለአጠቃቀም አዳጋች ሆነው ቆይተዋል ተብሏል።
ይህንን ለመቅረፍም የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እጅግ ውስብስብ የሆኑ የእፅዋት ሥርዓቶችን እና በውስጣቸው ያሉ የፈውስ ኬሚካሎችን በፍጥነት ለመለየት ያስችላል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።
በዚህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይም በየሀገራቱ የተበታተኑ እና ያልተደራጁ የባህላዊ መድኃኒት መረጃዎችን AI በመጠቀም ወደ አንድ ወጥ ሳይንሳዊ ቋንቋ መቀየር እንደሚቻል ተመልክቷል።
ከእፅዋት የሚገኙ ዘመናዊ መድኃኒቶችን ለማግኘት የሚፈጀውን ከ10 እስከ 15 ዓመታት እድሜም፣ AI በመጠቀም ወደ ጥቂት ዓመታት ማሳጠር እንደሚቻል የዘርፉ ተመራማሪዎች በጉባኤው አስረድተዋል።
ሆኖም ግን በጉባዔው ስጋቶች የተንጸባረቁ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አንዱ የባለቤትነት መብትን ማስጠበቅ (Intellectual Property) ላይ ያተኮረ ነው።
AI መረጃዎችን በሚሰበስብበት ወቅት፣ የባህላዊ እውቀት ባለቤት የሆኑ ማኅበረሰቦችን እና የሀገር በቀል እውቀቶችን መብት ማስጠበቅ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት እንደሚገባው በስፋት ተመክሮበታል ተብሏል።
የዓለም ጤና ድርጅት በዘርፉ ያለውን እውቀት ለማሳደግ 1.6 ሚሊዮን ሳይንሳዊ ሪከርዶች ያሉት ዲጂታል የምርምር ክምችት መፍጠሩን ይፋ አድርጓል።
ይህ ግዙፍ መረጃ በAI በመታገዝ ለተመራማሪዎች እና ለጤና ባለሙያዎች ክፍት የሚሆን ሲሆን፣ ባህላዊ መድኃኒቶች ደኅንነታቸው የተጠበቀ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የሚደረገውን ጥረት ይደግፋል ተብሎ ታምኗል።
Source: RTE , WHO
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 101👍 15🔥 4👎 3👏 2🕊 2
ኦፓልን ጨምሮ ሌሎች የማዕድን ምርቶችን በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኩል ማገበያየት ሊጀመር ነው።
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የኦፓል ማዕድንን ጨምሮ ሌሎች የማዕድን ምርቶችን ማገበያየት ለመጀመር የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለጸ።
የምርት ገቢያው በአሁኑ ወቅት ቡና፣ ሰሊጥ፣ ጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎች እና ቅመማ ቅመሞችን ጨምሮ ወደ 28 የግብርና ምርቶችን በማገበያየት ላይ ይገኛል።
ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መርጊያ ባይሳ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አዋጅ ከተሻሻለ በኋላ ተቋሙ ከግብርና ውጭ የሆኑ ማዕድንና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ማገበያየት የሚችልበት ኃላፊነት እንደተሰጠው ገልጸዋል።
ይህንኑ ተከትሎ የኦፓል ማዕድንን ወደ ገበያ ለማስገባት ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።
ከኦፓል በተጨማሪ ሌሎች ማዕድናትን ለማገበያየት የሚያስችል ራሱን የቻለ የግብይት ሥርዓት ለመዘርጋት በምርት ገበያው በኩል ሲደረጉ የነበሩ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን አስታውቀዋል።
በማዕድን ሚኒስቴር በኩል መጠናቀቅ ያለባቸው ጉዳዮች ሲፈጸሙ የማገበያየት ስራው እንደሚጀመር ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።
ዘገባው የኢዜአ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 64🤔 3🔥 2🤬 2
照片不可用在 Telegram 中显示
የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር የ2018 የሰላም ስምምነት ቁልፍ አንቀፆች ላይ ማሻሻያ ማድረጋቸው ተሰማ።
በ2018 የተፈረመው ስምምነት የደቡብ ሱዳንን ግጭት ለማስቆም የነበረ ሲሆን ምርጫ ለማካሄድ ቋሚ የሆነ ህገመንግስት እንደሚያስፈልግ ያስቀምጣል።
ደቡብ ሱዳን ስምምነቱ ከተፈረመ 7 ዓመታት ቢያስቆጥርም ቋሚ የሆነ ህገመንግስት የላትም።
ሳልቫኪር አሻሻሉት በተባለው ስምምነት ምርጫ ለማድረግ ቋሚ ህገመንግስት ያስፈልጋል የሚለውን በማስቀረት ደቡብ ሱዳን አሁን ባላት የሽግግር ህገመንግስት ስር ምርጫ እንዲደረግ ያዛል።
ሌላኛው የተሻሻለው የብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን የሽግግር ጊዜ ከመጠናቀቁ ከ60 ቀናት በፊት ምርጫ እንዲያደርግ የሚለው ሲሆን የህዝብ ቆጠራም ከምርጫው በፊት ይልቅ ከምርጫው በኋላ እንዲደረግ የሚለው ይገኝበታል።
ማሻሻያዎቹ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ በብሔራዊ ህግ አውጪ ሲፀድቅ ተግባራዊ ይሆናል።
የፕሬዚዳንቱ ፅህፈት ቤት ማሻሻያዎቹ ያስፈለጉት ህዝቡ በታህሳስ 2026 ምርጫ ለማድረግ ካለው ፍላጎት እና መሪዎቹ ለሰላምና ለዲሞክራሲ ያላቸውን ቁርጠኝነት ለማሳየት ነው ብሏል።
በእስር ላይ የሚገኙት የሪክ ማቻር ፓርቲ የፖለቲካ ቢሮ ማሻሻያው የሰላም ስምምቱን ፈራሚዎች ያላካተተ እና ህገወጥ እንደሆነ ገልጿል።
ማሻሻያው በፓርላማ ከፀደቀ ደቡብ ሱዳን ከሱዳን ነፃነቷን ካወጀችበት 2011 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ምርጫ እንድታደርግ ያስችላታል።
ዘገባው የRadio Tamazuj ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 36👎 7
照片不可用在 Telegram 中显示
✨ከእኛ አንድ ቤት ሲገዙ ከኢትዮዽያ አየርመንገድ ET🇪🇹 Sheba Miles ደረጃዎን በእጥፍ ያሳድጉ ✈️🤝
በተጨማሪም በተመጣጣኝ ዋጋ የቤት ባለቤት ልናረጎ ሲሆን:-
እስከ 25% ቅናሽ ያላቸው በነፋሻማዋ ሰሜን ማዘጋጃ ላይ ግንባታቸው እየተካሄደ ያለ በካ.ሜ ከ65,000 ብር ጀምሮ ይዘንላቹ መተናል!
👉በ 25% ቅናሽ (100% ለሚከፍሉ ደምበኞች)
ባለ 1 መኝታ(81 ካ.ሜ)=5,300,000ብር
ባለ 2መኝታ(110ካ.ሜ)=7,200,000ብር
ባለ3መኝታ(130ካ.ሜ)=8,500,000ብር
👉በ 10% ቅድመ ክፍያ ቀሪው በግንባታ ሂደት የሚከፍሉት!
ባለ 1 መኝታ(81 ካ.ሜ) = 700,000 ብር
ባለ 2 መኝታ(110ካ.ሜ) =957,000 ብር
ባለ 3 መኝታ(130ካ.ሜ)=1,131,000ብር
✨በተጨማሪም እንደ ቅድመ ክፍያዎ ቀድመዉ ለሚመጡ 15 ደምበኞች ብቻ ከ3% እስከ 25% ቅናሽ ያለን ሲሆን ይህንን እድል ተጠቃሚ ለመሆን በ0913599755 ወይም 0912915147 ይደውሉ!
#Akoyaproperties #EthiopianAirlines #ShebaMiles #Partnership
❤ 20🤣 3🤔 2
ስለ ዘይጋርኒክ ውጤት (The Zeigarnik Effect) ያውቃሉ ?
የጀመርነውን ሥራ ሳንጨርሰው ስንቀር፣ ሥራው ከአዕምሯችን አልወጣ ብሎ ሲያስጨንቀን የሚውለው ወይም ደግሞ በቲቪ የምናየው ተከታታይ ድራማ (Series) በጣም ወሳኝ ቦታ ላይ ሲቋረጥ፣ ቀጣዩ ክፍል እስኪመጣ ድረስ ስለዛ ታሪክ ደጋግመን የምናስበው ለምን ይመስላችኋል ?
የሥነ-ልቦና ባለሞያዎች ይህ የሚሆንበትን ምክንያት "የዘይጋርኒክ ውጤት/ The Zeigarnik Effect " ብለው ይጠሩታል።
የዘይጋርኒክ ውጤት መነሻው ምንድን ነው ?
ይህ ጥናት ስያሜውን ያገኘው ብሉማ ዘይጋርኒክ ከተባለች ሩሲያዊት የሥነ-ልቦና ባለሙያ ነው።
ብሉማ በ1920ዎቹ አጋማሽ ላይ በአንድ ምግብ ቤት ውስጥ ተቀምጣ ሳለች አንድ የሚገርም ነገር ትታዘባለች።
የታዘበችውም፥ አስተናጋጆቹ ገና ክፍያ ያልፈጸሙ ደንበኞችን ትዕዛዝ በዝርዝር ማስታወስ መቻላቸውንና ነገር ግን ደንበኞቹ ክፍያ ፈጽመው እንደጨረሱ፣ አስተናጋጆቹ ያዘዙትን ምግብ ወዲያውኑ ሲረሱት ነው።
ብሉማ፥ በዚህ ተገርማ ባደረገችው ምርምርም፤ አዕምሯችን ያልተጠናቀቁ ሥራዎችን ከተጠናቀቁት ሥራዎች ይልቅ በ90% በበለጠ ሁኔታ እንደሚያስታውሳቸው አረጋግጣለች
አንድን ሥራ ስንጀምር አዕምሯችን ውጥረት (Cognitive Tension) ውስጥ ይገባል። ይህ ውጥረት ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ አይለቀንም። ሥራው ሲጠናቀቅ ግን አዕምሯችን ፋይሉን "እንደተዘጋ" ይቆጥረውና መረጃውን ለማስታወስ የሚጠቀመውን ጉልበት ያቆማል።
ያልተጠናቀቀ ሥራ ግን በአዕምሯችን ውስጥ እንደ "ክፍት ፋይል" ሆኖ ስለሚቀመጥ፣ አዕምሯችን ሥራውን እንድንጨርስ ደጋግሞ ያስታውሰናል። ይህ ክስተት ነው ጭንቀት (Stress) እና "ይህ ሥራ አልተሰራም" የሚል ስሜት የሚፈጥርብን።
በዚህ ሳይንስ ምክንያት የፊልም አዘጋጆች አንድን ክፍል መጨረሻ ላይ "Cliffhanger" (በጉጉት ላይ ባለበት) ይቆርጡታል፤ ይህም አዕምሯችን ታሪኩ ስላልተጠናቀቀ ቀጣዩን ክፍል ለማየት በከፍተኛ ጉጉት እንዲጠብቅ ይገፋፋናል።
በዚህ ምክንያት ተማሪዎች አንድን ትምህርት ለረጅም ሰዓት አከታትለው ከማጥናት ይልቅ፣ በመሀል አጫጭር እረፍት ቢወስዱ ያጠኑትን ነገር በተሻለ መንገድ ማስታወስ ያስችላቸዋል።
ምክንያቱም እረፍት ሲወስዱ አዕምሯቸው ሥራው ገና እንዳልተጠናቀቀ ስለሚያውቅ መረጃውን በንቃት (Active Memory) ይይዘዋል።
ብዙ ያልተጠናቀቁ ሥራዎች ካሉባችሁም አዕምሯችሁ ስለሚወጠር እነዚህን ስራዎች በወረቀት ላይ በመጽሐፍ፣ አዕምሯችሁ ሥራዎቹ "ተመዝግበዋል" ብሎ እንዲያስብና ውጥረቱን እንዲቀንስ መርዳት ይቻላል።
አዕምሯችሁ አንድን ነገር እንዲያስታውስ ከፈለጋችሁ፣ ስራውን ሳትጨርሱ በመሀል አጭር እረፍት ማድረግ በባለሞያዎች ዘንድ ይመከራል።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 108👍 10
ስለ ዘይጋርኒክ ውጤት (The Zeigarnik Effect) ያውቃሉ ?
የጀመርነውን ሥራ ሳንጨርሰው ስንቀር፣ ሥራው ከአዕምሯችን አልወጣ ብሎ ሲያስጨንቀን የሚውለው ወይም ደግሞ በቲቪ የምናየው ተከታታይ ድራማ (Series) በጣም ወሳኝ ቦታ ላይ ሲቋረጥ፣ ቀጣዩ ክፍል እስኪመጣ ድረስ ስለዛ ታሪክ ደጋግመን የምናስበው ለምን ይመስላችኋል ?
የሥነ-ልቦና ባለሞያዎች ይህ የሚሆንበትን ምክንያት "የዘይጋርኒክ ውጤት/ The Zeigarnik Effect " ብለው ይጠሩታል።
የዘይጋርኒክ ውጤት መነሻው ምንድን ነው ?
ይህ ጥናት ስያሜውን ያገኘው ብሉማ ዘይጋርኒክ ከተባለች ሩሲያዊት የሥነ-ልቦና ባለሙያ ነው።
ብሉማ በ1920ዎቹ አጋማሽ ላይ በአንድ ምግብ ቤት ውስጥ ተቀምጣ ሳለች አንድ የሚገርም ነገር ትታዘባለች።
የታዘበችውም፥ አስተናጋጆቹ ገና ክፍያ ያልፈጸሙ ደንበኞችን ትዕዛዝ በዝርዝር ማስታወስ መቻላቸውንና ነገር ግን ደንበኞቹ ክፍያ ፈጽመው እንደጨረሱ፣ አስተናጋጆቹ ያዘዙትን ምግብ ወዲያውኑ ሲረሱት ነው።
ብሉማ፥ በዚህ ተገርማ ባደረገችው ምርምርም፤ አዕምሯችን ያልተጠናቀቁ ሥራዎችን ከተጠናቀቁት ሥራዎች ይልቅ በ90% በበለጠ ሁኔታ እንደሚያስታውሳቸው አረጋግጣለች
አንድን ሥራ ስንጀምር አዕምሯችን ውጥረት (Cognitive Tension) ውስጥ ይገባል። ይህ ውጥረት ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ አይለቀንም። ሥራው ሲጠናቀቅ ግን አዕምሯችን ፋይሉን "እንደተዘጋ" ይቆጥረውና መረጃውን ለማስታወስ የሚጠቀመውን ጉልበት ያቆማል።
ያልተጠናቀቀ ሥራ ግን በአዕምሯችን ውስጥ እንደ "ክፍት ፋይል" ሆኖ ስለሚቀመጥ፣ አዕምሯችን ሥራውን እንድንጨርስ ደጋግሞ ያስታውሰናል። ይህ ክስተት ነው ጭንቀት (Stress) እና "ይህ ሥራ አልተሰራም" የሚል ስሜት የሚፈጥርብን።
በዚህ ሳይንስ ምክንያት የፊልም አዘጋጆች አንድን ክፍል መጨረሻ ላይ "Cliffhanger" (በጉጉት ላይ ባለበት) ይቆርጡታል፤ ይህም አዕምሯችን ታሪኩ ስላልተጠናቀቀ ቀጣዩን ክፍል ለማየት በከፍተኛ ጉጉት እንዲጠብቅ ይገፋፋናል።
በዚህ ምክንያት ተማሪዎች አንድን ትምህርት ለረጅም ሰዓት አከታትለው ከማጥናት ይልቅ፣ በመሀል አጫጭር እረፍት ቢወስዱ ያጠኑትን ነገር በተሻለ መንገድ ማስታወስ ያስችላቸዋል።
ምክንያቱም እረፍት ሲወስዱ አዕምሯቸው ሥራው ገና እንዳልተጠናቀቀ ስለሚያውቅ መረጃውን በንቃት (Active Memory) ይይዘዋል።
ብዙ ያልተጠናቀቁ ሥራዎች ካሉባችሁም አዕምሯችሁ ስለሚወጠር እነዚህን ስራዎች በወረቀት ላይ በመጽሐፍ፣ አዕምሯችሁ ሥራዎቹ "ተመዝግበዋል" ብሎ እንዲያስብና ውጥረቱን እንዲቀንስ መርዳት ይቻላል።
አዕምሯችሁ አንድን ነገር እንዲያስታውስ ከፈለጋችሁ፣ ስራውን ሳትጨርሱ በመሀል አጭር እረፍት ማድረግ በባለሞያዎች ዘንድ ይመከራል።
😀 | @tikvahethmagazine
照片不可用在 Telegram 中显示
የናይሮቢ ግዛት ለሴት ሰራተኞች በወር የሁለት ቀናት እረፍት እንዲሰጥ ወስኗል።
የኬንያዋ ናይሮቢ ግዛት ሴቶች ከወር አበባ ጋር በተያያዘ በወር የሁለት ቀን እረፍት እንዲሰጣቸው ወስናለች።
የግዛቲቱ ግማሽ ያህል ሰራተኞች ሴቶች ናቸው ሲባሉ ከወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚገጥማቸው ህመም ስራቸው ላይ ተፅዕኖ ይፈጥራል።
ግዛቲቱ ከ65-80 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች የወር አበባ ህመም እንደሚያጋጥማቸው ጥናቶች ያሳያሉ ስትል ይህም በሰራተኞቹ እና በስራ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳለው ተገልጿል።
በአለም አቀፍ ደረጃ እንደ ዛምቢያ፣ ጃፓን፣ ስፔንና ደቡብ ኮሪያ ያሉ ሃገራት ከወር አበባ ጋር ተያይዞ ለሴት ሰራተኞች በወር የአንድ ቀን እረፍት ይሰጣሉ።
ዘገባው የኬንያንስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 210👏 56👍 20🤷♀ 4🤷♂ 3🔥 1
照片不可用在 Telegram 中显示
ደቡብ አፍሪካ በዩክሬን እየተዋጉ ያሉ 17 ዜጎቿን ለማስመለስ ከሩሲያ ጋር ድርድር መጀመሯን ገለፀች።
እነዚህ ወጣቶች በጃኮብ ዙማ ልጅ ተታለው ለሩሲያ ጦር የተመለመሉ ሲሆን ከ17ቱ የደቡብ አፍሪካ ዜጎች በተጨማሪ 2 የቦትስዋና ዜጎችም በጃኮብ ዙማ ልጅ መመልመላቸው ተነግሯል።
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ቃለ አቀባይ ቪንሰንት ማግዌንያ ወጣቶቹን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ከሩሲያና ዩክሬን ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ተናግረዋል።
ቃለ አቀባዩ በዋነኝነት ንግግሩ እየተደረገ ያለው ለጦር ከተመለመሉላት ሩሲያ ጋር እንደሆነ አንስተዋል።
ወጣቶቹ በተሳሳተ መንገድ ለሩሲያ ከተመለመሉ በኋላ የማይገባቸውን ኮንትራት እንዲፈርሙ መደረጋቸው መገለፁ ሲታውስ የጃኮብ ዙማ ልጅም በዚሁ ምክንያት ከፓርላማ አባልነቷ በገዛ ፈቃዷ መልቀቋ መዘገቡ ይታወሳል።
ዘገባው የአፍሪካ ኒውስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 15👎 5
