ch
Feedback
️ ንስር አማራ🦅

️ ንስር አማራ🦅

前往频道在 Telegram

የተቀደሰን ነገር በእግሩ ለሚረግጥ ፥ተመልሶም ያጎረሰውን እጅ ለሚናከስ ርኩስ መጫወቻ የማይሆን የነቃ ማህበረሰብ እስክንፈጥር ድረስ ብዕራችን አይነጥፍም። አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፥ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ። 💚💛❤️ እኛን በውስጥ ለማናገር @NISIREamhra2 @NISIREamhraa_bot 👈 ይችን አድራሻ ይጠቀሙ🦅 ንስር ዐማራ🦅 #የግፉአን_ድምፅ t.me/NISIREamhra

显示更多
2025 年数字统计snowflakes fon
card fon
63 160
订阅者
-2124 小时
-2237
-78730
帖子存档
🔥ዞብል አምባ ክፍለጦር 4ኛ (በረኸኛው) ሻለቃ ቆቦ ከተማ ዙሪያ ድል ተጎናፀፉ‼️ ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር 4ኛ (በረኸኛው) ሻለቃ ቆቦ ከተማ ዙሪያ ልዩ ስሙ ካራኤላ እና አጣዋ ጋሪያ ላይ ጠላት #ኮንክሪት_ምሽግ ሰርቶ ከመሸገበት ድረስ ትናትና ህዳር 25/2018 ዓ.ም ምሽት በመግባት በርካታ ሃይሉን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል:: ጠላት ወደሚመታበትና በጅምላ ወደሚማረክበት ቦታ ተስቦ የገባ ሲሆን በተደጋጋሚ የደፈጣ ጥቃት እየተመታ ሲሆን መካናይዝዱንም ማሸሽ ጀምሯል:: በቀጣይም በደፈጣ እና በሽምቅ ውጊያ የማሰላቸት የማሸማቀቅና የማፍረስ ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥልና ባመች ጊዜ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ወደሚደመሰስበትና ወደሚማረክበት መደበኛ ተጋድሎ በማስገባት ድል እናደርገዋለን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምኒልክ ዕዝ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 26/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
显示全部...
55👍 18
00:36
视频不可用在 Telegram 中显示
⚫️#የወጣቶች_አፈሳና_የወላጆች_ልቅሶ💔     #ደቡብ_ጎንደር_እብናት‼️ የአብይ አህመድ አስተዳድር ወንበሩን ለማፅናት በመላ ሀገሪቱ ወታደራዊ አፈሳ እያካሄደ በለብ ለብ ስልጠና በመስጠት ወጣቶችን ( የድሀ ልጆችን) ወደ ጦርነት እየማገደ ይገኛል።   ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ደቡብ ጎንደር ዞን እብናት ከተማ ለገቢያ የሚመጡ የአርሶ አደሩ ልጆች እና የከተማዋ ወጣቶች (በብዛት ከ15 አመት እድሜ በታች ህፃናቶች) የአብይ አህምድ ወንበር ለማፅናት በግዳጅ እየተደበደቡ ለውትድርና ታፍሰዋል። የታጋች ወላጆች ልጆቻችን ልቀቁ ብለዉ ቢወጡም ምላሽ የሚሰጥ ሳይሆን በመሳሪያ ሰደፍ የሚደበድብ ሚኒሻ ተመድቦላቸው በርካታ እናቶች ለጉዳት ተዳርገዋል።   ይህ አረመኔ ስርዓት በዛሬው ዕለት ወላጆችን እያስለቀሰ ህፃናቶችን ወደ ደብረታቦር ጭነዋቸው ሄደዋል ሲሉ የአይን እማኞች ይህንን አሳዛኝ ድርጊት ለንስር አማራ ገልፀዋል። የታፈሱ ወጣቶች ሲጫኑ ወላጆች ከተማ አስተዳደር ላይ በእንባ ሲራጩ የነበረውን ሁነት ሁሉም ያየው ዘንድ ምንጮቻችን በከፊል ምስሉን አድርሰውናል‼️ #ማስታወሻ!! የነገ ታጋች ፣ የዛሬ ታጋቾች በግዳጅ ወደ ጦርነት ሊማገዱ ሰወሰዱ ቁሞ ሲያይ ከምስሉ ተመልክተናል።ይህ ስርዓት ጭራቅ ነው ሁሉንም ይበላል። ተነጣጥሎ ከማለቅ በአንድነት ልንታገለው ይገባል‼️
显示全部...
4.26 MB
85👍 29😢 13💔 4
照片不可用在 Telegram 中显示
🔥#የፖለቲካ_ሞት‼️ አርበኛ ዘመነ ካሴ ሲታሰር ያኔ በጥዋቱ የህዝባዊ ኃይል ም/ል ሰብሳቢ የነበረው ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ መሪያዎቻችን፣ ድርጅቱን እና በህዕቡ የተደራጀውን ኃይል በትኖ ከስርዓቱ በተሰጠው መኪና ደብረ ማርቆስ ዮኒቨርስቲ ትምህርት ሲጀምር ነበር ከአዲሱ ትውልድ አዕምሮ የወጣው። የፖለቲካ ሞትን የተለማመደው ያኔ ነበር ። በቅርቡ ሁሉም የአማራ ህዝብ አንድነቱን እየናፈቀ ባለበት እና የቤተ-አማራዎች ከአብይ ወንበር አስጠባቂ ኃይል መሣሪያ ፣ተተኳሽ ፣አልባሳቱን እና ቁሳቁሱን እየማረኩ እና ነፃ ቀጠናዎች እያሰፉ ባለበት ወቅት፤ በዚህ ድልም መላው አማራ ያለምንም ልዩነት ደስታውን በሚገልፅበት ወቅት ካፒቴን ማስረሻ ግን በጣም የተናደድክ ነበር የምትመስለው። ለዚህም ይመስለኛል ድርጅትህ እና ጓዶችህ ሳይፈቅዱ እና እውቅና ሳይኖራቸው  በአጃቢህ ሞባይል የሚልኩህን ሰዎች ልብስ በመልበስ ደርዝ የሌለው ህዝባችንም ሰራዊታችንም የማይፈልገውን፣ ጠላት ግን የሚጠቀበትን ሐሳብ ማንፀባረቁ የአንተን ካህዲነት ለማያውቁህ በደንብ የተገለጥክበት ጊዜ ነው። በአንተ መግላጭ የሚቀር ድልም ሆነ አንድነት ግን የለም ። ቤትህን ጠርገህ ቆሻሻውን ሳታቃጥል ወይ ሳትቀብር ከግቢ ውጭ ከጣልከው ምግብ ስትበላ ወይም በሰርክ ስራህ የቆሻሻው በሽታ አመጪ ባክቴሪያዎች ተመልሰው በ ዝንብ አማካኝነት እየመጡ ቤተሰቡን በሙሉ በሽታ ለማስያዝ ይሰራሉ። እኛ ግን በመርህ ላይ የተመሠረተ የአማራን ህዝብ መብት እና ጥቅም በአከበረ መንገድ ጉዟችን እንቀጥላለን ። ካፒቴን መጀመሪያ ጫካ የወጣው የአማራ ህዝብ ምን ጎደለበት ብሎ ነው ? ለአማራ ህዝብ ምን አሳክቶ ተመለሰ ? ....? ዝና እና ነጭ ሻሽ በስሕትት ይጎድፋል ፣ ጋን ሙሉ ወተትም በአንድ ዝንብ ይደፋል ። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ ! ©አርበኛ ግሩም ምሳሌ የአፋብኃ ቴወድሮስ እዝ ም/የፓ/መምሪያ ኃላፊ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 25/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
显示全部...
172🙏 35👍 23👏 9😢 3🎉 2😡 1
🔥ሐውጃኖ ክፍለጦር የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሪፐብሊካን ጋርድ ላይ ታላቅ ድል ተቀዳጁ‼️ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ሐውጃኖ ክፍለጦር ዛሬ ህዳር 25/2018 ዓ.ም ማለዳ ጀምሮ እስከ ምሽት 12:00 ከሪፐብሊካን ጋርድ ጋር በመፋለም ከ50 በላይ ሃይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል:: በተጋድሎው ጠላት ከራያ አላማጣ ጥሙጋ ከተማ ተነስቶ በዙ23 እና ሞርተሮች ታግዞ ወደ ሐውጃኖ ክፍለጦር ቀጠና ማጥቃት ያደረገ ሲሆን ክፍለጦሯ ሁለት ሻለዎችን ተጠቅማ መልሶ ማጥቃት በማድረግ ከ50 በላይ ሪፐብሊካን ጋርድ ሙትና ቁስለኛ በማድረግና ቀጠናቸውን በማስከበር ጭምር ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል:: በርካታ ሃይሉ የተመታበት የፋሽስቱ አብይ አህመድ የመጨረሻ ምሽግ ሪፐብሊካን ጋርድ ከግራም ከቀኝም ተጨማሪ ሃይል በማያገኝበት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ራያ አላማጣ ጥሙጋ ከተማ ት/ቤት ውስጥ በከፍተኛ ድንጋጤና ፍርሃት ውስጥ ሆኖ ይገኛል:: በሌላ በኩል ለሪፐብሊካን ጋርዱ ተጨማሪ ሃይል ማስገባት ያልቻለው አገዛዙ ሰራዊት ከራያ ቆቦ ጮቢ በር ሆኖ ኦራል ላይ የተጠመዱ ሁለት ቻይና ሰራሽ 155 Mm መድፍ ወደ ራያ ቆቦ ባይባወ እና ኩቢ ቀረንሳ እያስወነጨፈ ንፁሃን ላይ ጉዳት እያደረሰ አምሽቷል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 25/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
显示全部...
👍 50 44🙏 3
照片不可用在 Telegram 中显示
🔥#የ4ኛ_ደጃዝማች_ኮር_ተጋድሎ‼️                                        አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ 4ኛ ደጃዝማች ኮር በዛሬዉ ቀን 25/3/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ሽመለ ጋራ ቀበሌ በ2 አቅጣጫ የመጣዉን ጠላት ኃይል ከቦ እርምጃ በመውሰድ  ሙትና ቁስለኛዉን እያንጠባጠበ ወደ ኃላ እንዲፈረጥጥ ተገዷል።ከኮሩ ስር የሚገኙ 6ክፍለ ጦር የተዉጣጣ ኃይል በውጊያው ተሳትፏል 1/አርበኞች ክፍለ ጦር 2/ጎቤ ክፍለ ጦር 3/ረመጡ ደጀን ክፍለ ጦር 4/ዘርዓይ ክፍለ ጦር 5/ተከዜ ክፍለ ጦር 6/አጣናዉ ዋሴ ክፍለ ጦር    ሙሉ መረጃዉን በቀጣይ እናደርሳለን። ©አርበኛ ባንዴራው ግርማይ የ4ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 25/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
显示全部...
77👍 19🙏 10👏 2❤‍🔥 1
照片不可用在 Telegram 中显示
🔥#የሰላም_ስምምነት_ተደረገ😂 #የጫካው_ብአዴን መሪ አቶ ማስረሻ ሰጤና  የከተማው ብአዴን መሪ አቶ አረጋ ከበደ (ቀንድ አውጣ (#ቀንዴክስ)) መካከል የውል እደሳ (የሰላም ስምምነት) ተፈረመ‼️ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 25/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
显示全部...
👍 83 46😡 13😢 5😍 4👏 3
🔥#የአደረጃጀት_ዜና‼️ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር የአመራር ሪፎርም አደረገ:: ቀናትን የፈጀ ውይይት እና ግምገማ ከተደረገ በኋላ አዳዲስ አመራሮች የተሰየሙ ሲሆን ከነባሮች የኃላፊነት ርክክብ አድርገዋል:: የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ አብነው ታደሰ በተገኘበት የተካሄደው የውውይት እና ግምገማ መድረክ በስኬት መጠናቀቁ የተገለፀ ሲሆን ጉባኤተኞች ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩትን አርበኞች የክፍለ ጦሩ አመራሮች አድርገው መምረጣቸውን ነው ከስፍራው የደረሰን መረጃ የሚያመላክተው:: በዚህም፦ 1ኛ. አርበኛ ስንደው ገዜ - የክፍለ ጦሩ አዛዥ 2ኛ. አርበኛ ዱቤ አሻግሬ- የክፍለ ጦሩ ምዕ/ አዛዥ 3ኛ. አርበኛ ንጉሥ ጌታቸው - ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ 3.1. አርበኛ መብሬ ጫብሲ - ዘመቻ መምሪያ ምዕ/ ኃላፊ 4ኛ. አርበኛ መብሬ ምስጌ - ወታደራዊ አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ 5ኛ. አርበኛ ደምሰው ጎቼ - ሎጀስቲክ ሃላፊ 6ኛ. አርበኛ ደመቀ አረጋ - የፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ 7ኛ. አርበኛ አስማማው ፈንታው - የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ 8ኛ. አርበኛ ጀንበሩ ጌታቸው - ስልጠና መምሪያ ኃላፊ መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 25/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
显示全部...
81👍 19🙏 9
🔥#ሰበር_ዜና_ግሽ_አባይ_ሰከላ#የብልፅግና_ባንዳ_ስሩ_ተቆረጠ_በሰከላ‼ በአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ሰከላ ላይ በወሰደዉ እርምጃ የሰከላ ወረዳ አስተዳድር ዋና ባንዳ #ይልማ_ጥላሁን ጨምሮ ከሁለት ደርዘን በላይ የሚነሻና የመከላከያ አባላት ተወግዷል። የስቦ መምታት ጥበበኞች 44ኛ ክፍለ ጦር  ጠላትን #ከሰከላ #ከማንኩሳና #ከቡሬ በመተንኮስ ወደ ቀጠናቸዉ  ድረስ ሰተት አድርገዉ በማስገባት #ሰከላ ላይ የቀረዉን ሰፈር ጠባቂ፣ ዘራፊ ሚኒሻና ሆድ አደሩን የብልፅግና አመራር መሃል ሰከላ ላይ አራምጠዉታል። "ፋኖን ባለበት አሳድጄ አጠፋዋልሁ" እያለ ሲፎክር የነበረዉ ዋና አስተዳድር እና አምስት ሚኒሻ ሲማረክ ብዛት ያለዉ ሰራዊት ደግሞ እስከ ወዲያኛው ተሸኝቷል። አረመኔው ቡድን በአጉትና ባሽፋ ከማንኩሳ ፔንፔ፣ዘ_23 ከሰከላ ግትልትል ሰራዊቱን በማስከተል #ምላስና #ብልት በመቁረጥ የስድስት ንፁሃንን ህይወት በቀጠፈበት ቀጠና እየተልከሰከሰ የባህር ኩበት በሆነበት ሰሃት ጀግኖቹ የ44ኛ ክፍለ ጦር ነበልባሎች ሰከላ ከተማ የሚገኘውን የብልፅግና ጦር በመቀጥቀጥ #12 ክላሽንኮፍና በሺዎች የሚቆጠር ተተኳሽ ማርኳል። ከዚህ በተጨማሪ መንግስታዊ ስርዓት አስቀጥላለሁ በሚል ሃሳዊ ህልም ሲገለገልባቸዉ የነበሩ  ኮምፒወተሮችና ላብቶቦች ማተሚያ ማሽኖች ሲማረኩ፤ የወረዳዉ መገልገያ ተቋም በሙሉ ፓትሮሎችን ጨምሮ ከጥቅም ውጭ ሁኗል። ከተማዋ ላይ የተሰገሰጉ በመረጃነት የሚያገለግሉ እንቁላል ቀቃይ ባንዳዎች መዉጫ መግቢያ ጠፍቷቸዉ ብዙዎቹ ተሸኝተዋል። ቁሞ መግጠም ያልቻለዉ አረመኔ ቡድን ከተለያ የቦታ እያፈነ እስረኛ ያደረጋቸዉን የሰከላ ወረዳ 25 ንፁሃን እስረኞችን ጭምር ከአረመኔዉ መንጋጋ ማስለለቅ ተችሏል። በተደጋጋሚ ቀጠናዉን እየረገጠ የጣለዉን እየጣለ ቁስለኛዉን ጭምር ሳያነሳ ወደ ቆፈረው ጉድጓድ የሚሮጠዉ አረመኔው ቡድን ዛሬም እንደልማዱ ከግሽ አደባባይ ጀምሮ እስከ ድንጋይ ገበጣ ሩጦ በመግባት ህይወቱን ሊተርፍ ችሏል። ዛሬ ህዳር 25/2018 ዓ.ም 44ኛ ክፍለ ጦር ባደረገዉ ትንቅን በተደጋጋሚ ጀብደኝነቱን ያስመሰከረ፣ የጠላትን ቅስም የሰበረ፣ ብዙ ባንዳዎችን ቀልብ የቀየረበት፣ የድል ቀን ሆኖ  ተመዝግቧል። #በተደጋጋሚ_ተናግረናል_ጀምረናል_እንጅ_አልጨረስነዉ#ላናሸንፍ_የጀመርነዉ_ትግል_የለም_ድልችን_ቅርብ_ነዉ‼ ©የ44ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ አለበል አወቀ። #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 25/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
显示全部...
127👍 29🙏 4
照片不可用在 Telegram 中显示
🔥#ፀዳሉ_ደሴና_ጓዶቹ_በአገዛዙ_እይታ‼️ በሰሜን ምዕራብ ዕዝ ግቢ ውስጥ የጸዳሉን ፎቶ አንድ የመከላከያ ከፍተኛ አመራር ሲልክልኝ እንዲህ አለኝ,,,,,,,"ዕጅ የሚሰጡትን በጣም ነው የምንስቅባቸው፣በጣም ነው የምንንቃቸው፣ለእኛ ዕጅ ሲሰጡ የምንፈልጋቸው ለዜና ብቻ ነው፣ዜና ከተሰራባቸው በኋላ የሚፈልጋቸው ባለመኖሩ የትም ቢሄዱ አይመለከተንም። የፖለቲካ አመራሮችም ዜናው ከተሰራ በኋላ ዞር ብለው አይጠይቁንም። ጸዳሉ የሚባለው ደህንነት መሆን እፈልጋለሁ ብሎ ግቢ ውስጥ እንደ ስደተኛ ሲንከባለል ይውላል። ወደ እኛ ሲመጣ መጠቋቆሚያ ነው የምናደርገው። እኛ ቤተሰብ አፍርተን ልጆች ወልደን ለእነሱ መኖሪያ ስንል ደሞዝ እየበላን ከውስጥ እንታገላለን፣ወጣቱ ታግሎ እኛንም ነጻ ያወጡናል ብለን ስንጠብቅ ዕጅ ሲሰጡ ያሳቅቁናል። መከላከያ በቅርቡ አይኖርም። እውነቱን ልንገርህ መንግስት ደክሞታል። ደሞዝ በቅርብ ቀን ይቋረጣል እየተባለ ነው" በማለት አጫውቶኛል። ዕጅ የሚሰጡት በእነሱ ዘንድ እንደዚህ ከተናቁ በሌላው ማህበረሰብ ዘንድማ አስቡት! አስፈላጊ ከሆነ ቪዲዮም አለኝ። ነገር ግን ዕጅ ለሰጠ ሰው ጊዜ ማቃጠሉ ተገቢ ነው ብየ አላምንም። ሰሞኑን ማስረሻ ሰጤም በአንዱ የዕዝ መመሪያ ግቢ ውስጥ ሆኖ እናየው ይሆናል። ክብርን የሚያውቀው በክብር ያደገ ሰው ነው። ለጁላ ዕጅ የሚሰጥ ከእሱ ያነሰ ማንነት በመያዙ ነው። ©ከፍያለው ጌጡ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 25/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
显示全部...
👍 117 68🙏 3🎉 1😍 1
03:43
视频不可用在 Telegram 中显示
39.53 MB
66👍 28🏆 10🙏 8👏 4💔 1
🔥በደፈጣ ጥቃት ተፈፀመ ሁለት ፓሊሶች ላይ እርምጃ ተወሰደ‼️      ህዳር 25/2018 ዓ.ም የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ እና74ኛ ክፍለ ጦር በሸበል በረንታ ወረዳ ሊዲ ቀበሌ፣ ገዳያሱ ቀበሌ እና መርጦ ለማራይም ከባድ ተጋሃድሎ ሲያካሂድ አድሯል። በሸበል በረንታ ወረዳ ወፍትማ ጎጥ ህዳር 24/2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት በነበረው የጨለማ የጨበጣ ውጊያ በረካታ የአረመኔዊ ሰራዊት አባላት ሲደመሰስ  በረከት ታደሰ የሚባል1 የአገዛዙ ሰራዊት አባል በንስሮች የበላይ ዘለቀ ልጆች እና የሽፈራው ገርባው ልጅች የተማረከ ሲሆን መርጦለማርያም ላይ  ሁለት ፓሊሶችላይ እርምጃ በመውሰድ ጀብድ ሰርቶ መውጣት ተችሏል። በሸበል በረንታ በነበረው ውጊያ የ64ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች እና ጥምር ጦሩ እና1ኛ እሪጅመንት እና የሸበል በረንታ ደጀኑ ህዝባችን ተሳትፈዋል።    ህዳር 25/2018 ዓ.ም አዲስ ትውልድ ፣ዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ    ©የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 25/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
显示全部...
76👍 16🙏 3
照片不可用在 Telegram 中显示
🔥#ሰበር‼️ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር የወረዳ አስተዳድሩን ጨምሮ ብዛት ያለው ሚኒሻን ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ፣ እንዲሁም በርከት ያለ አጥቦ አይለብሴ ተሸኝቷል‼ ዝርዝር ይዘን የምንመለስ ይሆናል!! #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 25/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
显示全部...
109👍 47🏆 2🙏 1
🔥#አፋብኃና_አፋሕድ_ጥምር_ተጋድሎ‼️ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር እና ከአፋሕድ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ዓፄ ዐምደፂዮን ኮር የተውጣጣ የፋኖ ኃይል በምዕራብ ወሎ ግንባር ከላላ ወረዳ ውስጥ ታላቅ የጦር ሜዳ ጀብዱ ፈፀመ:: በቅንጅት በተሰራው ኦፕሬሽን ከ20 በላይ ጠላት የተማረከ ሲሆን ጠላት 3 መኪና የሚሆን ሙት እና ቁስለኛ ጭኖ ፈርጥጧል:: በትናንትናው እለት #በደገር ግንባር የተጀመረው ጦርነት ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን በስተመጨረሻ ፋኖ ከተማይቱን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አውሏታል:: ከዚህ በተጨማሪ ከደገር ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኙት ቲርቲራ እና ቆርኬ ታዳጊ ከተሞችም በፋኖ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል:: ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ ትንቅንቅ በቲርቲራ በኩል የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር 1ኛ ሸዋንግዛው ካሳ ተሾመ ሻለቃ ጠላትን ሲያስፈረጥጠው ቆርኬ ላይ ደግሞ የዚሁ ክፍለ ጦር አካል የሆነችው 2ተኛ እንድሪስ ተሾመ ሻለቃ ታሪክ ሰርታለች:: የፋኖዎችን ምት መቋቋም ያቃተው ጠላት ከቲርቲራ ጎራ ወርዶ እየፈረጠጠ ተጉዞ ቀነሶ መንደር ሲደርስ አቶ ሁሴን ከማል የተባለ ገበሬን በአጨዳ ላይ ሳለ እረሽኖታል:: በቆርኬ ግንባር 17 የጠላት ኃይል የተመታ ሲሆን 5ቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ 12ቱ ቁስለኛ ሆነዋል:: ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ዋሲል ክፍለ ጦር በጃማ ግንባር በተለይም በአቦልድ፣ ዘርቃሚ እና ደጎሎ በኩል የጠላትን አከርካሪ መስበሩ ተረጋግጧል:: የወረዳው መቀመጫ የሆነችው ደጎሎ ከተማ እስከ ዛሬ ጧት ድረስ በተኩስ ስትናጥ እንደነበረ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመላክታል:: ከቅዳሜ ዕለት ጀምሮ የዋሲል ክፍለ ጦር 2ተኛ መብረቅ ሻለቃ አባላት ጠላትን እረፍት ነስተውት ሰንብተዋል:: በዚህ የተበሳጨው ጠላት ከአረብ ሀገር ከመጣች 1 ወር በትክክል ያልሞላትን እህታችንን መረሸኑም ታውቋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 24/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
显示全部...
120👍 42🙏 9💔 8💯 4😢 3
🔥የፋሽስቱ አገዛዝ ቁልፍ የመረጃና ደህንነት እንዲሁም የመከላከያ መንገድ መሪ የሆኑ ባንዳዎች ራያ ቆቦ አራዱም ወታደራዊ ካምፕ ላይ እርምጃ ተወሰደባቸው‼️ የራያ ቆቦ ወረዳ መረጃ እና ደህንነት፣ የመከላከያ መንገድ መሪ፣ እንዲሁም ንፁሃን አማራዎችን በማሳፈንና በማስረሸን ብሎም ወጣቱን በሃይል በማስገደድ ወደ መከላከያ በማስገባት የባንዳነት ተግባር ሲፈፅሙ የኖሩት የፋሽስቱ አገዛዝ ቁልፍ ሰዎችና ሆድ አደር የራያ ቆቦ ወረዳ ካድሬና ሚሊሻዎች በሰማዕቶቹ ጀግኖች በነ አርበኛ አለሙ ገብሩ በነ አርበኛ ዋሴ ከበደ በነ አርበኛ ፍሬው አለና እና ሌሎች አርበኞች ልጆች በምስራቅ አማራ ኮር 2 ቃኝ አባሎች እርምጃ ተወስዶባቸዋል:: ከአማራ ህዝብ ተፈጥረው ከፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ጋር በመተባበር የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀሙ የኖሩት ሆድ አደሮች አቶ ጉሽሽ ደረስን ጨምሮ አራት ባንዳዎች ህዳር 24/2018 ዓ.ም ራያ ቆቦ አራዱም ወታደራዊ ካምፕ ላይ በምስራቅ አማራ ኮር 2 ቃኝ አባሎች እርምጃ ተውስዶበታል:: በቀጣይም እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 24/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
显示全部...
106👍 23🏆 10🙏 3❤‍🔥 1🎉 1
🔥#አገዛዙ_ሰራዊቶች_እየተቀላቀሉን_ነው‼️ የዓብይ 57ኛ ክ/ጦር ዓባል ወታደር ነው።አገዛዙ አማራን ጨቋኝና አማራን ጨፍጫፊ ስለሆነ የአማራ ፋኖን ለመቀላቀል መወሰኑን እያስረዳ ነው። ከ1:00 ሰዓት በፊት የብርሃኑ ጁላን ጦር እስከ ሙሉ ትጥቁ በመክዳት ሰራዊታችን የተቀላቀለው ወታደር በላይ ይበልጤ መኮነን የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦርን በመቀላቀል ለመታገል መወሰኑን አስረድቷል። የአማራና የኢት/ያ ሀገራችን ቀንደኛ ጠላት ዓብይ አህመድና ቡድኑ አፓርታይዳዊ አደገኛ "ዘረኛ" አገዛዝ መሆኑን ከጦር ሰራዊቱ በተደጋጋሚ እየተመሰከረም ይገኛል።ወታደር በላይ ይበልጤም ይህንኑ በንግግሩ አስረድቷል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! ©ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 24/ዐ3/2018 ዓ.ም @hageremedianews
显示全部...
5.17 MB
20.29 MB
108👍 34💔 5😍 3
01:17
视频不可用在 Telegram 中显示
🔥#የምረቃው_ትርዒት_በከፊል‼️ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ለተከታታይ 6(ስድስት) ወራት ያሰለጠናቸውን የእግረኛ ሰራዊት በትናትናው ዕለት ህዳር 23/2018 ዓ.ም በሸበል በረንታ ወረዳ የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ የሽፈራው ገርባው ልጆች ለ5ኛ ዙር በደማቅ ሁኔታ አስመረቀዋል‼️ #መሰልጠን_መግጠም_ማሸነፍ_መንግስት መሆን💪 #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 24/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
显示全部...
11.75 MB
88👍 22
🔥#ሰበር_ዜና‼️ ዞብል አምባ ክፍለጦር 4ኛ (በረኸኛው) ሻለቃ ራያ ቆቦ ተኩለሽ ዙሪያ ያለውን የፋሽስቱ ሰራዊት አንዱን ምሽግ ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ:: ዞብል አምባ ክፍለጦር 4ኛ (በረኸኛው) ሻለቃ ዛሬ ህዳር 23/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ላይ ራያ ቆቦ ተኩለሽ ዙሪያ ካሉት የፋሽስቱ ሰራዊት ምሽጎች አንዱ ላይ በሬ አርዶ ከሚበላበት ተስበው በመግባት ምሽጉን ሙሉ ለሙሉ በመስበርና በርካታ ሃይሉን በመደምሰስ ብሎም በማቁሰል ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል:: የጠላት ሃይል ምንም አይነት ዋርድያ ባላስቀመጠበትና በሌለበት ሁኔታ ምሽጉ ላይ በሬ አርዶ በሚበላበት ቀን 10:00 ላይ ተስበው በመግባት እስከ ምሽት 12:00 ድረስ ሲረመርሙት አምሽተው ታላቅ ጀብድ በመፈፀም ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል:: ከዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ማግስት ፋሽስቱ አገዛዝ ቤተ-አማራ ከነበሩት ዕዞች በተጨማሪ ሁለት ዕዝ በማስገባት ወረራ ቢያደርግም ምኒልክ ዕዝ ጠላትን ወደሚመታበት ወረዳ በማስገባት ወደ ደፈጣ ውጊያ በመግባት ሲያመች ደግሞ መደበኛ ውጊያ በማድረግ በርካታ ሃይሉን ሙት ቁስለኛ እና ምርኮኛ እያደረገ በተጨማሪም እያስኮበለለ እያፈረሰው ይገኛል::  መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 23/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
显示全部...
137👏 19🏆 16👍 10🙏 9💔 9🎉 8
🔥ለተከታታይ 6(ስድስት) ወራቶች ሲሰለጥኑ የነበሩ የ64ኛ ክፍለ ጦር እግረኛ ሰራዊት በሸበል በረንታ በደማቅ ሁኔታ ተመረቁ‼️ ህዳር 23/2018 ዓ.ም የአፋብሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ለተከታታይ 6(ስድስት) ወራት ያሰለጠናቸውን የእግረኛ ሰራዊት ህዳር 23/2018 ዓ.ም በሸበል በረንታ ወረዳ የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ የሽፈራው ገርባው ልጆች ለ5ኛ ዙር በደማቅ ሁኔታ አስመረቀዋል። በቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ስር የሚገኘው 64ኛ ክፍለ  ጦር የእግረኛ ሰራዊት ለማስመረቅ በክብር የተገኙት የ64ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች፣ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የአካባቢው ማህበርሰብ በተገኙበት በሸበል በረንታ ወረዳ በደማቅ ሁኔታ ተመርቋል። የተከበራቹህ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች የተከበራቹህ የሸበል በረንታ ወረዳ ጊ/መንግስት አመራሮች የተከበራቹህ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት የተከበራቹህ የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም በዚህ ፕሮግራም የተገኛቹህ የከተመዋ ኖሪዎች እንዲሁም የክብር እንግዶች የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ ዙር የእግረኛ ሰራዊት የምረቃ ፕሮግራም እንኳን በሰላም አደረሳቹህ አደርሰን። በምረቃ ፕሮግራሙ የተገኛቹህ የክብር እንግዶች ክብራት እና ክብሯን እንዲሁም ተመራቄ የፋኖ አባላት እኛ እናተ እንዲህ የምንሰባሰበው፣ የምንደራጀው፣ የምንሰለጥነው ለሁላችንም የጋራ የሆነ ጉዳይ በየቤታችን ስላለን ነው? ሁላችንም እንድንደራጅ እና እንድንሰባሰብ ካደረጉን አንኳር ጉዳዩች ውስጥ ሰርቶ መብላትን ያስተማረው፣ ኢትዮጵያ ከውጭ ወራሪ እና ከውስጥ ሰላቶ እና ባንዳን በማፅዳት ሀገር የገነባው የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ በራሱ ሀገር፣ በእራሱ እርስት ሲያሻቸው በሀይማኖቱ፣ ሲያሻቸው በዕርስቱ፣ በማንነነቱ ጣልቃ እየገቡ የአማራን ህዝብ ከ50 ዓመት እና ከዛ በላይ እረፍት በመንሳት በገዛ ሀገሩ እንዳይኖር ተደርጓል። ሀገር መስራቹ፣ፊደል የቀረፀው፣የእራሱ እምነት፣ የእራሱ ባህል እና እሴት፣የእራሱ ወግ ያለው ለበርካታ ዘመናት የኢትዮጰያን ዳር ድንበር አስከብሮ የቆየው፣ በአራቱም መዓዘን ደሙን አፍሶ አጥንቶ የከሰከሰው ታላቁ የአማራ ህዝብ ዛሬ ላይ በገዛ ሀገሩ፣ በገዛ እርስቱ ባይተዋር ሆኖ በጅምላ ይገደላል፣ በጅምላ ይሰደዳል፣ በጅምላ ይፈናቀላል፣ ሀብት ንብርቱ በወራሪዎች እየተወረሰ ይገኛል። ኢትዩጰያን ያሻግራሉ፣ሀገር ይመራሉ በህዝብ ተወዳጅ የነበሩ የአማራ ሙህራን በጅምላ በጨለማ እስር ቤት እየተሰቃዩ ይገኛሉ። እንደ ምሳሌ ብንጠቅስ የመንጋው መድሀኒት የፖርላመው ንጉስ አቶ ክርስትያን ታደለ፣ አቶ ዩሀንስ ቦያለው እና መ/ር መስከረም አበራ እና ሌሎች ሙህራን በጅምላ በጨላማ እስር ቤት ታስረው እየተሰቃዩ ይገኛሉ። የአብይ አህመድ አረመኔዊ ስርዓት የአማራን ህዝብ ለማጥፋት የአጭር እና የረጅም ግዜ ዕቅድ በማውጣት በአለም ላይ ተደርጎ የማይታወቅ ለማየት የሚሰቀጥጡ ዘግናኝ እና አስነዋሪ ተግባር እየፈፀሙብን እና እያስፈፀሙብን ይገኛሉ። ይህ ሁሉ ድርጊት የሚፈፅሙት ከአማራነታቸው ይልቅ ሆዳቸው የግል ጥቅማቸው በልጦባቸው ባንዳ በሆኑ አመራሮች እና ሚሊሻዎች ጭምር ነው። ክቡራን እና ክቡራት እንዲሁም ተመራቂዎች ይህ ድርጊት የሚፈፀመው አማራ በመሆናችን ብቻ ነው። የአማራ ህዝብ በአማራነቱ ብቻ እንዲጠፋ የተፈረደበት ህዝብ ከሆነ ውሎ አድሯል። በመሆኑም የአማራ ህዝብ ህዝብ መዳኛ መንገድ አንድም በክንዱ አንድም በእግዚአብሄር ሀይል ብቻ ነው። የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ የመኖር መብቱን ማስከበር የሚችለው አማራ አንድ ሆኖ በጋራ መታጋል ስንችል ብቻ ነው። በመሆኑም ይህንን የአረመኔዊ አገዛዝን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ ነቅሎ ለመጣል የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ልጆች እና የሽፈራው ገርባው ልጆች በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር አደረጃጀት ስር ታቅፈው በተለያዩ ቦታዎች የውጊያ እቅዶችን በማቀድ እርሀቡ፣ የውሀ ጥሙ፣  ብርዱ፣ ሙቀቱ ሳይበግራቸው በረካታ ውጊያዎችን በማድርግ በርካታ ገድል ሲፈፅሙ  ቆይተዋል። በዚህ ሰዓት 64ኛ ክፍለ ጦር በድርጅቱ አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የሚሰጣቸውን የትኛውም አይነት ወታደራዊ ግዳጅ/ሚሽን በብቃት ከመፈፀም ጎን ለጎን በዚህ ፈታኝ ወቅት ህዝባችንን በመልሶ ማደራጄት፣ወታደሩን በመልሶ ማሰልጠን፣ ወጣቱን በልዩ ልዩ ስልጠና እና የውትድርና ሳይንስ በመስጠት ግዙፍ ሀይል እየገነባ ይገኛል። በዚህም ለጠላት ሀይል ቅስም መስበሪያ ለወዳጅ ደስታን ይዞ መጥቷል። በሸበል በረንታ እና በእነማይ ምድር ጀግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ሀገራችንን ከቀኝ ግዛትና ከባርነት ነፃ አድረገው ለትውልድ ያስረከቡበት የአረበኞች መሰባሰቢያ ከሆኑት ውስጥ ይህ አካባቢውን አንዱ ነው። በዛሬው እለት ህዳር 23/2018 ዓ.ም በሸበል በረንታ ለመሰባሰባችን ምክንያት የሆናቹህ የ5ኛ ዙር እግረኛ ተመራቂ አባላት እናተ የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ፣ የሽፈራው ገርባው፣ የእጅጉ ዘለቀ ልጆች ናቹህ። በዚህ ቅዱስ በሆነው የአማራ ህዝብ የትጥቅ ትግል በስም ዘርዝረን የማንጨረሳቸው ጀግኖች የትግል ጓዶች ከጠላት ጋር ተናንቀው ብዙ ዋጋ ከፈለው ተለይተውናል። በመሆኑም ድርጅታችንን እና መሪያችንን ከጥግል ጠላፊዎች እንድትጠብቁ አደራ እያልኩ እኛ ለእናተ አደራ የምንሰጣቹህ መሪዎቻችን በብዙ ስቃይ እና መከራ ውጣ ውርድ፣ ጀግኖች ውድ ህይወታቸውን የገበሩበት ትግል ተቀብላቹህ የድል ባለቤት እንድታደርጉት አደራ እንላለን። በመጨረሻም በመላው አማራ በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ያወጀውን የአማራን ህዝብ የአረመኔዊ ድርጊት በመስራት በረካታ ግፎች እና ወንጀሎችን እየሰራ የሚገኜው የአብይ አህመድ ጡት ቆራጭ አረመኔዊ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ስለሚጠበቅብን ሁላችንም በዚህ የምረቃ ፕሮግሬም የምትገኝ በሙሉ ራሳችሁን ዝግጁ እንድታደርጉ እያልኩ ለተመራቂ ፋኖዎች መልካም የምረቃ ጊዜ እንመኛለሁ። እንደራጃለን፣ እንሰለጥናለን፣ እንታጠቃለን፣ የአማራን ህዝብ ከአረመኔው ጡት ቆራጭ አራጅ ሰራዊት ነፃ እናወጣዋለን። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!         ህዳር 23/2018 ዓ.ም ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ ©አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64 ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 23/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
显示全部...
110👍 19👏 6🏆 3💔 3🙏 2
🔥የምኒልክ ዕዝ አሃዶች በጥምረት ዳውንት እና ፀሃይ መውጫ ላይ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ‼️ የምኒልክ ዕዝ አሃዶች በጥምረት ዳውንት እና ፀሃይ መውጫ ላይ ዛሬ ህዳር 23/2018 ዓ.ም ማለዳ 3:00 ጀምሮ እስከ ቀን 6:00 ከፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ጋር በመፋለም ታላቅ ድል አስመዝግበዋል:: ጠላት ዳውንት እና ፀሃይ መውጫ ከተማን ለመቆጣጠር ከኮንና ጋሼና አንድ ክፍለጦር ዙ23ን ጨምሮ እንዲሁም ከወገል ጤና አንድ ክፍለ ጦር ዙ 23 ጋር ወደ ዳውንትና ፀሃይ መውጫ ማጥቃት ያደረገ ሲሆን ከምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለ ጦር እና ከደጋው መብረቅ ኮር ከፅናት መክትና ሰንጥቅ ክፍለ ጦር የተውጣጡ ሻለቆች እንዲሁም ሌሎች በመደራጀት ላይ ያሉ አሃዶች በጥምረት የጠላትን ሰራዊት ለጊዜው በስም ያልታወቁ አመራሮችን ጨምሮ በመደምሰስና በማቁሰል ከባድ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ በማድረስ ብሎም ቀጠናውንና ከተሞቹን በማስከበር ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል:: በዚህ በድንቅ መናበብ በተመዘገበ ታላቅ ፍልሚያና ድል የጠላት ሰራዊት በሁሉም አቅጣጫ የተመታ ሲሆን አስከሬንና ቁስለኛውንም እያነሳ ወደመጣበት አቅጣጫ ሽሽቷል:: በተጋድሎው በመደራጀት ላይ ያለ የልዩ ዘመቻ አሃድም የተሳተፈ ሲሆን ከልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር አንድ ጓድ በውጊያ መሃል ደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ታላቅ ጀብድ ሰርተዋል:: በዚህ ታላቅ ተጋድሎ ከባድ ምት የተመታው አገዛዙ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገባ ሲሆን የደላንታና የወገል ጤና የብልፅግና ካድሬዎችና አመራሮች ተከበናል መላም የለን እያሉ ወደ ደሴ ከተማ መሸሽ ጀምረዋል:: ውጊያው አሁንም ሌሎች አሃዶች ተጨምረውበት ተጠናክሮ ቀጥሏል:: ዝርዝር መረጃ ይዘን እንመጣለን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 23/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
显示全部...
103👍 9👏 5💯 2
🔥#የዘጋርዲያን_ዘገባ‼️ ጓደኛዬ በወታደር (በመከላከያ) ስለተደፈረች ወደ ትግል ገባው ! ፋኖን ከተቀላቀሉ አንዷ! 👉የ83 አመት አዛውንት በድሮን ጥቃት ተገድለዋል 👉የ 5 አመት ህጻን ከመንግስት በተተኮሰ ከባድ መሳርያ በመገደሉ እናት ልቧ ተሰብሯል! በአማራ ክልል እየተፈጸሙ ስላሉ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች ፣ ስላለው ሰብአዊ ቀውስ እና የፋኖ ትግል ዙርያ ዘጋድርያን (theguardian) "Inside Ethiopia’s Fano insurgency – photo essay" በሚል ርዕስ ዛሬ ባቀረበው የፎቶ ዘገባ ጸሀፊው በወሎ አከባቢ የፋኖን የማሰልጠኛ ቦታዎች እንደጎበኘ እና ህዝብ ላይ ተፈጸመ የተባለውን ሰብአዊ መብት ጥሰት መረጃዎችን ማሰባሰቡን ገልጿል:: የአማራ ፋኖ አብዛኛውን (ወደ 80%) የሚሆነውን የአማራ ክልል በተለይም ገጠራማ አከባቢዎችን እያስተዳደርኩ እገኛለው ማለቱን ከመሪዎቹ መስማቱን ገልጿል:: ለምን የፋኖን ትግል እንደተቀላቀለች ከስልጠና ሜዳ ለዘጋቢው  የገለጸችው "ከዚህ ከ30 ኪ.ሜ በላይ ርቀት ላይ ካለ መንደር ነው የመጣሁት። እዚያም ከጓደኞቼ የ22 ዓመቷ ደርቤ በወታደሮች (በመከላከያ) አፍነው  እና ደፍረው ወደ ጎዳና ጥለዋታል። በዚያን ጊዜ መዋጋት እንዳለብኝ ወሰንኩኝ።" ማለቷን ዘግቦታል:: ሙሉ ዘገባውን ዘጋርዲያን ላይ ተመልከቱት። #Ethiopia: Widespread rights abuses in #Amhara region as federal forces move to battle Fano insurgency – the Guardian reveals Federal forces committed abuses in Amhara region, including kidnappings, massacres, sexual violence and attacks on humanitarian personnel, in an attempt to quell the Fano insurgency in Ethiopia’s Amhara region, the Guardian newspaper said in its photographic report. It added that the situation is out of control, with more than 2 million people in urgent need of humanitarian assistance in a region that is also hosting refugees from the war in Sudan. According to the Guardian newspaper in its photographic report, the Ethiopian federal army is regularly accused of massacres, arbitrary arrests, sexual violence and drone attacks targeting civilians in Amhara. Civilians interviewed described losing relatives to drone strikes and shelling, further fueling anger at the central government. The report notes that while the Fano militia initially enjoyed broad community support, worsening insecurity and economic collapse are gradually undermining this trust, with some Fano groups increasingly accused of extorting civilians, particularly at checkpoints. Once allies of the federal government during the Tigray war, the Fano turned against Addis Abeba after the Pretoria Agreement and the federal decision to dismantle regional special forces, which many Amhara fighters perceived as a direct threat to their security. Thousands of former special forces personnel subsequently joined the Fano, creating a fragmented armed movement estimated at nearly 20,000 fighters. The Guardian says the Fano now control large rural areas of Amhara, while federal forces are largely confined to major towns, and both sides hold alternating areas of control as fighting intensifies. https://www.theguardian.com/artanddesign/2025/dec/01/inside-ethiopia-fano-insurgency-photo-essay
显示全部...
176👍 31💔 12😢 4