ch
Feedback
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

前往频道在 Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም አስተያየት @Zimaredawitmessanger ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን። YouTube Page - https://bit.ly/2O1Z3d8 Facebook Page - https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

显示更多
2025 年数字统计snowflakes fon
card fon
166 284
订阅者
-1724 小时
-227
-430
帖子存档
ሐረገ ወይን ሐረገ ወይን /4/ እመብርኃን/2/ ሐረገ ወይን /4/ እመብዙኃን/2/
አዝ
የጸጋ ሁሉ ምንጭ የሕይወቴ ተስፋ እስኪ ላመስግንሽ ሳላፍር በይፋ ምርኩዜ ልበልሽ ጥላ ከለላዬ የእኔ መመከቻ ዕንቁዋ ጋሻዬ ሐረገ ወይን
አዝ
መልካሚቱ ሽቱ የሕሙማን ፈውስ የአብ ቃል እናቱ ድንቅ ዕፀ ጳጦስ መዓዛሽ ተስማሚ የሕይወት ምግብ የቅንነት መዝገብ የሰላም ርግብ ሐረገ ወይን
አዝ
የአቤል መሥዋዕት የዳዊት መዝሙር የአሮን ክህነት ነሽ ፀአዳ ፀምር የስደተኞች ቤት ማረፊያ ድንኳን የልባችን ደስታ እመቤታችን ሐረገ ወይን
አዝ
እንደ ወይን /2/ እንደዘለላ የጻድቃን እመቤት የጽድቃችን ጥላ ስምሽ የጣፈጠ ግሩም ነው ወለላ ማርያም ርግብየ ይቤላ/2/ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
4_5951610781354166038.mp311.12 MB
160😍 10🕊 7🔥 3
照片不可用在 Telegram 中显示
ኅዳር ፲፯ /17/
በዚች ቀን ታላቅና ክቡር የሆነ የዓለሙ ሁሉ መምህር የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት የዮሐንስ አፈወርቅ ሥጋው የፈለሰበት ነው። ይህም እንዲህ ነው መበለቲቱን ቦታዋን በግፍ ነጥቃታለችና እርሱም እንድትመልስላት ቢያዛት ስለ አልሰማችው ስለ መበለቲቱ ቦታ ቅዱስ ዮሐንስ ንግሥት አውዶክስያን በአወገዛት ጊዜ በእርሱ ላይ ተቆጣች ሰይጣንም በልቧ አደረና ስለ ክፉ ሥራቸውና ስለ በደላቸው አውግዞ የለያቸውን ኤጲስቆጶሳት በእርሱ ላይ ሰበሰበች። እነርሱም ስለ መሰደዱ ከእርሷ ጋር ተስማምተው አድራኮስ ወደምትባል ደሴት አጋዘችው በዚያም ጥቂት ዓመታት ኑሮ ወደ መንበረ ሲመቱ ተመለሰ። ከዚህም በኋላ ዳግመኛ መናፍቃን የሆኑ ኤጲስቆጶሳትን ሰበሰበችና ወደ አርማንያ አጋዙት ከዚያም በረሀ ወደ ሆነ ሩቅ አገር ሰደዱትና በዚያ አረፈ። የአርቃዴዎስም ልጅ ታናሹ ቴዎዶስዮስ በነገሠ ጊዜ መልክተኞችን ልኮ የቅዱስ ዮሐንስን ሥጋ ብዙ በመዘመርና በማመስገን በታላቅ ክብር ወደ ቊስጥንጥንያ አፍልሶ አስመጣው ይህም ከዕረፍቱ በኋላ በሠላሳ አምስት ዓመት ነው። በሌላ በቅብጢ መጽሐፍ በግንቦት ወር ሃያ ሁለት ቀን እንደ ደረሰ ይናገራል በሮማውያን መጽሐፍ ግን በየካቲት ወር ሃያ ሁለት ቀን ተባለ የዕንቊ ፈርጾች ባሉት የዕብነ በረድ ሣጥን ውስጥ አድርገው ወደ ቤተ መቅደስ አስገቡት ከሥጋውም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
251🕊 16🥰 8
ለነፍሴ ነፍሷ ነሽ ለነፍሴ ነፍሷ ነሽ ለመንገዴ ፋና እንዳልጠፋ አምናለሁ የአንቺ ልጅ ነኝና/2/
አዝ
የፃድቃን እናቶች እጅግ ብዙ ናቸው ከብሉይ ከሃዲስ ብንዘረዝራቸው አንቺ ግን አንዲት ነሽ የለሽም ጭማሪ ትኖሪያለሽ እንጂ ትውልድ ስታስምሪ
አዝ
ያንቺን ሥም ተማጽኖ ያንቺን ሥም ቀድሶ አንቺን አመስግኖ አንቺን አወድሶ የተጠቀመ እንጂ በረከት አግኝቶ አልታየም እስካሁን የተጎዳ ከቶ
አዝ
ጎርጎርዮስና ሊቁ ዮሐንስ አትናቴዎስና ሊቁ ባስልዮስ አባ ኤፍሬምና አባ ጊዮርጊስ ተጠቅመዋል በአንቺ በሥጋም በነፍስ
አዝ
አባትህን ጠይቅ ስለሚለን ቃሉ ብንጠይቃቸው ቅዱሳኑን ሁሉ ስላንቺ ነገሩን ክብር ተዓምራትሽን ለሰው ዘር በሙሉ አማላጅ መሆንሽን
አዝ
ገብርኤል ከሰማይ ኤልሳቤጥ ከምድር በአንድ መሠከሩ ስለ ድንግል ክብር ሰዓሊ ለነ ብሎ ተማጽኖ በአንቺ ስም የተጠቀመ እንጂ የተጎዳ የለም ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
Ethiopian-Orthodox-tewahedo-mezmur-by-dn-mindaye-birihanu-on.m4a5.48 MB
148🕊 10🥰 9
125 አዳዲስ አማንያን ሥርዓተ ጥምቀት ተፈጸመላቸው። ኅዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም የማኅበረ ቅዱሳን ስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት  በዳውሮ ሀገረ ስብከት ባለፉት ወራት ቅድመ ጥምቀት ትምህርት ሲስተምራቸው ከነበሩ ወገኖች  መካከል ሕዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም.  125 አዳዲስ አማንያን ሥርዓተ ጥምቀት ተፈጽሞላቸው የቅድስት ሥላሴን ልጅነትን እንዲያገኙ አደረገ፡፡ በአካባቢው ቤተ ክርስቲያን ባለመኖሩ ጥምቀቱን ለማስፈጸም ሥርዓተ ቅዳሴ በድንኳን ውስጥ የተከናወነ ሲሆን በዕለቱም የዳውሮ ሀገረ ስብክት ሥራ አስኪያጅ መልአከ ኃይል ቆሞስ አባ ክንፈ ገብርኤል በመገኘት ሥርዓተ ጥምቀቱን እና ቅዳሴውን በመምራት መርሐግብሩ እንዲከናወን አድርገዋል፡፡ አገልግሎቱ ለማስፋፋት  የብዙዎችን ድጋፍ የሚፈልግ ሲሆን ማገዝ የምትፈልጉ:- 1.  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000195489541 2.  አሐዱ ባንክ ፡- 0025342920301 3.  አቢሲኒያ ባንክ :-15376481 4.  አዋሽ ባንክ :-01304024224400 5.  ወጋገን ባንክ ፡-0837534110101 ስልክ ቁጥር፦ +251-9-60-676767
显示全部...
289🥰 12🕊 12
ላመስግነው ላመስግነው እግዚአብሔርን ከፍ ላድርገው ህይወት የሆነኝን ካልሰጠኸኝ ይልቅ የሰጠኸኝ ብዙ ነው አላጉረመርምም በኔ ላይ በሆነው
አዝ
ይሰማሉ ዐይኖቼ በጆሮዬ ፋንታ ያወራሉ እጆቼ በአንደበቴ ቦታ ጎደለኝ እያልኩኝ ጥቃቅኑ ነገር ምስጋና አላቆምም ውዳሴ እና ክብር/2/ 
አዝ
የሥጋ ጆሮዬ ድምፅህን ባይሰማ ዘውትር አንደበቴ መዘመር ቢጠማ ቃላት ሳላወጣ ቆሜ በትህትና በጣቴ ምልክት አቀረብኩ ምስጋና/2/
አዝ
ሰዎች ቢመስላቸው ብዙ የጎደለኝ የቀረብኝ የለም እኔ ሙሉ ሰው ነኝ ቅዱሱ ቃልህን በዓይኔ ሰምቼ የዝማሬ አንደበት ሆኑልኝ ጣቶቼ/2/
አዝ
የዝማሬ ሰልፍን ለጣቴ አስተማረ በምልክት ቋንቋ መዝሙር ተዘመረ ሙሉ አካልን ይዞ ማመስገን ያልቻለ ከእርሱ በላይ ከንቱ በምድር የታለ /2/ ዘማሪ አቤል መክብብ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
6082726593_1 (14).mp37.08 MB
227🥰 12🕊 10
‎ሕዳር ፲፮ /16/
‎ ‎በዚችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ ስምንተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሀገርሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት አባ ዮሐንስ አረፈ። ይህም ቅዱስ አባት የቆጵሮስ ሀገር ሰው ነው እጅግም ባለጸጋ ነው በእስክንድርያ አገርም የሚኖር ሆነ አባቱ አገረ ገዥ ነበርና ሚስትም አግብቶ ልጆችን ወለደ ከዚህም በኋላ ሚስቱም ልጆቹም ሞቱ። ‎ ‎በዚያንም ጊዜ ገንዘቡን ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጠ መጸወተ እርሱም መንኵሶ በታላቅ ገድል የተጠመደ ሁኖ በጎ ሥራዎችን ትሩፋትን ጨምሮ በመሥራት እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው። ‎ ‎ከበጎ ሥራዎቹና ከትሩፋቱም ከቀናች ሃይማኖቱ ከአገልግሎቱና ከደግነቱ ከጽድቁ ማማር የተነሣ በግብጽ አገር የሚኖሩ ኤጲስቆጶሳት ሁሉም ተሰማምተው ይዘው ወሰዱት ያለ ፈቃዱም በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙትና በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ላይ አስቀመጡት። ያን ጊዜ የከበረ ወንጌልን አነበበ በሹመቱና በክህነቱም ብርሃን ተገለጸ ብዙዎች ድንቆች የሆኑ ተአምራትንም አደረገ። ‎ ‎ለድኆችና ለችግረኞች ሁልጊዜ ያለማቋረጥ የሚሹትን የሚሰጣቸው ሆነ ስለዚህም የሚራራ ዮሐንስ ተብሎ ተጠራ። በአይሁድና በአረማውያን ዘንድ የሚአስፈራ ሆነ በመጸሐፈ ገድሉ እንደተጻፈ እጅግ ይፈሩትና ያከብሩት ነበርና መንጋዎቹንም በበጎ አጠባበቅ ጠበቃቸው እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ። ‎ ‎ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ‎ ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
213🕊 11
በጾም ትትፌወስ በጾም ትትፌወስ ቁስለ ነፍስ ወበጸሎት ትትሀሰይ መንፈስ /2/
አዝ
መአልትና ሌሊት በጾም ጸሎት ተግቶ አሳይቷል ጌታ ስርዓትን ሰርቶ አይቀርም ፈተናው ትጋት ከሌለበት ስጋ ካልደከመች በጾምና ጸሎት
አዝ
ሙሴ የተባለው ያ የእግዚአብሔር ሰው ፊቱን የበራለት አርባ ቀን ጾሞ ነው በሲና ተራራ ተቀብሎ ህግን እርሙን እንድንተው አሳየን መንገድን
አዝ
የጸሎት እናቷ ስለሆነች ጾም ትህትናን ይዘን ደግሞም አንድ ሆነን ብንተጋ በጸሎት ከንስሀ ጋራ ጾም ታደርሰናለች ከጽዮን ተራራ
አዝ
አንድበትም ይጹም ኃይልም ይረጋጋ ጆሮም ክፉ ሰምቶ ነፍሱን እንዳይወጋ ደኅን ከመበደል ልብም ተመልሶ መጾምስ እንዲህ ነው የበደለን ክሶ ዘማሪ ዲ/ን አቤል ተስፋዬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
ለአብይ_ፆም_የሚሆን_ልብን_የሚያረሰርስ_ድንቅ_የበገና_መዝሙር_በፆም_ትትፌወስ_ቁስለ_ነፍስ1.m4a5.72 MB
star reaction 1 183🥰 9🕊 9🔥 1
ሕዳር 15/፲፭/ በዚችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ አንደኛ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ሁለተኛው ሚናስ አረፈ ። ይህን ቅዱስ ሚናስንም በታናሽነቱ ያለ ፍላጎቱ ወላጆቹ ሚስት አጋቡት ትእዛዛቸውን መተላለፍ ስለአልፈለገ የጋብቻውን ሥርዓት ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ፈጸመ ። ለርሱ ይህ ሁሉ ሕልም ይመስለው ነበር ወደ ሙሽሪትም ወደ አዳራሽ በአስገቡት ጊዜ ተቀምጦ እንዲህ ብሎ ተናገራት እኅቴ ሆይ ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ካጠፋ ምን ይጠቅመዋል እንደ ተጻፈ ሁሉ ያልፋልና ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ለዘላለሙ ይኖራል አሁንም ድንግልናችንን እንድንጠብቅ ነይ ቃል ኪዳን እናድርግ እርሷም ቃሉን ተቀብላ ከእርሱ ጋር ተስማማች ። ከዚህም በኋላ ትቷት ወደ አስቄጥስ ገዳም ሒዶ በአባ መቃርስ ገዳም ውስጥ መነኰሰ ብዙ ዘመናትም በገድል ተጠምዶ ኖረ ። ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳትም በአረፈ ጊዜ ይህን ቅዱስ አባት ሚናስን ያለውዴታው ወስደው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በወንጌላዊ ማርቆስም ወንበር ላይ መንጋዎቹን በቅን ፍርድ እየጠበቃቸው እያስተማራቸውም ዐሥራ ስምንት ዓመት ኑሮ በሰላም አረፈ ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
267🕊 14🥰 7
​​​​ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) ኅዳር ፲፭ ቀን ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ‹‹ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ለአዳም የተነገረው የድኅነት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹ጾመ አዳም (የአዳም ጾም)›› ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹ጾመ ስብከት (የስብከት ጾም)››፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹ጾመ ልደት (የልደት ጾም)›› በመባል ይታወቃል፡፡ እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል። ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹ጾመ ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም)›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹ጾመ ማርያም›› በመባልም ይታወቃል፡፡ በአጠቃላይ በዚህ በገና ጾም ነቢያትም ሐዋርያትም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም እንደ እነርሱ በረከትን እናገኝ ዘንድ ይህንን ጾም መጾም እንደሚገባን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥርዐት ሠርተውልናል፡፡ በዚህም መሠረት የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡ ምንጭ፡- ፍት.ነገ ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭፡ ጾምና ምጽዋት፣ ዲያቆን ቃኘው ወልዴ፤ ገጽ ፵፯ -፶፡ ጾሙን የበረከት እና የምሕረት ያድርግልን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
381🕊 18🥰 17
አየኋት ባይኔ አሻግሬ አየኋት ባይኔ አሻግሬ የያሬድን ውብ ዝማሬ ተቀኘው እንደ አባቶቼ እጄን ለክብሯ ዘርገቼ/2/
አዝ
ድካም እና እንቅልፍ እንደምን ሊረታኝ ድንጋይ ብንተራስ ፍቅርሽ አያስተኛኝ አይኔ ቢከደን አለሽ በምናቤ አልተከለልሽም ነግሰሻል በልቤ/2/
አዝ
መረማመጃ የሎዛ መሠላል የዜማ ቤቴ የመቅደስ ጽናጽል የሰማይ ንጉስ በበላይሽ አለ ድንኳን አድርጎ አንቺን የተከለ/2/
አዝ
ስምሽ በሁሉ ስለተወደደ ድንግል ለክብርሽ ፍጥረት አረገደ ካላመኑት ዘንድ ቢሆንም ዝምታ ከገብርኤል ነው የስምሽ ሠላምታ/2/
አዝ
ሳደርስ ውዳሴ መፃፋን ገልጬ ተመለከትኩሽ አይኔ እምባ እየረጨ በገናን ዳዊት መሰንቆንም እዝራ ሰጡኝ ላነሳሽ በክብሩ ተራራ/2/ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
አየሗት_በአይኔ_አሻግሬ_የያሬድ_ውብ_ዝማሬ_++_Ayehwat_Be_Ayene_Ashagera_#የማርያም_መዝሙር.mp33.87 MB
179🥰 12🕊 7
ከፍታዬ በአምላኬ ነው ክብሬ በእግዚአብሔር ነው ከፍታዬም በአምላኬ ነው አይወስድብኝም ሰው ተጠላሁኝ ብዬ ለምን ልታጠብ በእንባዬ ሳይረሳኝ ጌታዬ
አዝ
እንደ ሰው ሰው የማይለየው በፍቅር ሁሉን የሚያየው አይጣለኝ ብቻ ጌታዬ አይሸሸኝ በሁኔታዬ።
አዝ
በሰማይ ሆኖ ሀገሬ አንዴ በደሙ ከብሬ ራሴን ዋጋ እንደሌለው ለምንስ አደርገዋለሁ።
አዝ
አልልም ብቻዬን ነኝ የአምላኬ ክብር ከቦኝ በእግዚአብሔር ሲሆን መወደድ ወረት የለውም በእርሱ ዘንድ።
አዝ
ዓይቶኛልና ስገፋ አንገቴን ከፍቶኝ ስደፋ አሰፋው አገልግሎቴን እስከሚደንቀው ጠላቴን።
አዝ
በሰማይ ሆኖ ሀገሬ አንዴ በደሙ ከብሬ ራሴን ዋጋ እንደሌለው ለምንስ አደርገዋለሁ በዘማሪት መስከረም ወልዴ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
6082726593_1 (13).mp34.89 MB
star reaction 2 178🕊 11🔥 4
‎ሕዳር ፲፫ /13/
‎ ‎በዚችም ቀን ዐሥራ ሦስት ወንበዴዎች ስለርሱ በእርሱ ሃይማኖት ከዓለም የተለዩ የከበረ ባለጸጋ አስከናፍር አረፈ። ይህም አስከናፍር ከሮሜ መኳንንት አንዱ ነው እርሱም ለድኆችና ለምስኪኖች ምጽዋትን የሚሰጥ እንግዶችንና መጻተኞችን የሚቀበል ነው። ‎ ‎በዚያም ወራት ያገኙትን ሰው ሁሉ የሚነጥቁና የሚያጠፉ ዐሥራ ሦስት ሽፍቶች ነበሩ እንግዳ እንደሚቀበል ይልቁንም መነኰሳትን እንደሚወድ የአስከናፍርን ዜና በሰሙ ጊዜ ወደርሱ ሒደው በተንኮል ይገድሉት ዘንድ ገንዘቡንም ሁሉ ሊወስዱ ተማከሩ። ከዚህም በኋላ የምንኲስና ልብስ ለብሰው ከደጁ ቆሙ በአያቸውም ጊዜ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት እንደሆኑ አንዱ ጌታ ክርስቶስ እንደሆነ አሰበ ሰገደላቸውም ወደ ቤቱም አስገብቶ ማዕድ አቀረበላቸው እግራቸውንም አጠበ ሠላሳ አምስት ዓመት ሽባ ሆኖ በኖረ ልጁ ላይ ያንን እግራቸውን የታጠቡበትን ውኃ ረጨ ወዲያውኑ ልጁ ዳነ። ‎ ‎እነዚያ ሽፍቶችም የሆነውን በአዩ ጊዜ እጅግ ደነገጡ እርሱ አስከናፍር ግን አባቶቼ ሆይ ጌታ ክርስቶስ ከእናንተ መካከል የቱ እንደሆነ ንገሩኝ እሰግድለት ዘንድ አላቸው የአገር ሰዎችም የመኰንኑ ልጅ እንደዳነ በሰሙ ጊዜ ወደርሳቸው መጥተው ሰገዱላቸው እንዲህም አሏቸው የእግዚአብሔር ቅዱሳኖች ሆይ ባርኩን በሽተኞቻችንን አድኑልን። ከዚህም በኋላ እሊያ ወንበዴዎች ሾተሎቻቸውን አውጥተው በእርሳቸው ልንገድልህ በወደድንበት እኛን ይገድሉን ዘንድ እሊህን ሾተሎች ውሰድ አሉት እግዚአብሔር በአንተ ጽድቅ የራራልን ባይሆን በአጠፋን ነበር። ‎ ‎ይህንንም ከአሉት በኋላ ተሰናበቱት ከእርሱም አንድ አንድ መስፈሪያ ምስርለየአንዳንዳቸው ተቀብለው ሃያ አምስት ቀን ያህል የሚያስጉዝ ጉዳና ወደ ምድረ በዳ ተጓዙ ያንንም ምስር ከአሸዋ ውስጥ በተኑት ፀሐይ በሚገባም ጊዜ ከአሸዋው ውስጥ ሦስት ሦስት ምስር ፈልገው ይቀምሳሉ እንደዚህም ሠላሳ ዓመት ኖሩ። ከዚህም በኋላ ከሀዲ መኰንን በመጣ ጊዜ እርሱ ወዳለበት ሒደው በጌታችን ታመኑ እርሱም ገደላቸውና የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ። ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
189🕊 17🥰 10😍 1
ያሻግራል ያሻግራል ያድናል አንተን ማመን እግዚብሔር አንተን ማመን ያሻግራል ያድናል አንተን ማመን አምላኬ አንተን  ማመን በወጀቡም አለን ዜማ ክርስቶስ ስለ አንተማ
አዝ
ደመናውን እያየነው አይደክምም ልቦናችን በበረሀ መና አዝንበህ አይተንሀል በአይናችን በሚለወጥ በሁኔታ ዜማችንን አንቀይር ሁሉም አልፎ ሁሉም ሄዶ ቀሪያችን ነህ እግዚብሔር
አዝ
ቀስቱን አልፎ ይታየናል የተዘረጋው ክንድህ ከሞት አይኖች በፍላጻ ከልሎናል ሞገስህ የሸለቆ ፈሳሽ ሆነን ተራምደናል በግርማ ሳይፈፀም አንወሰድ በእኛ ያለው አላማ
አዝ
ጥልቁ ባህር መድረካችን ውሀው ሰገነት ሆኖ ዘምረናል በእንባ መሀል ልባችን ባንተ ታምኖ እስከ መምጫህ ይቀጥላል አያቆምም ግፍያ ሰልፉ ስትገለጥ ይፈፀማል የእኛ ነው ማሸነፋ
አዝ
ህይወት አልባ ክርስትና አልሰጠኸንም እና በዝቅተም በከፍታም ዘመርን በፈተና ከሸለቆው ጥልቀት በላይ ስላለህ አለታችን በትከሻህ ተሻግረናል ገብተናል ከእርስታችን ሊቀ ዲያቆናት ነቢዩ ሳሙኤል 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
_ያሻግራል_Yashagral_በዘማሪ_ሊቀ_ዲያቆናት_ነቢዩ_ሣሙኤል_nebiyu_tubeM4A_128K.m4a7.89 MB
158😍 7🔥 4🕊 3
Repost from TgId: 2150339683
照片不可用在 Telegram 中显示
🏵 ሰላም፡ለኵልክሙ። እነሆ ግእዝን በአንድ ወር ልዩ ግእዝን የምንማርበት ዝግጅታችን ተመልሰናል። በግእዝ ቋንቋን ትውልዱ በሚቀለውና ዘመኑን በዋጀ መልኩ በርቀት ትምህርት ለመስጠት ቅድመ ዝግጅታችንን አጠናቀናል። ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመመዝገብ ጥንታዊና ውዱ ቋንቋችንን ዕንወቅ። 📖 ትምህርቱን ከ10 ዓመት ዕድሜ በላይ ለሆኑ ፤  ስልክ ወይም ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ በመጠቀም ሁሉም ሰው መማር ይቻላል
✅ ምዝገባውን ለማካሄድ ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር በዚህ በመላክ ነው ✅ @Geez180 @Geez180 @Geez180 👈
                 ⛳️ ለበለጠ መረጃ በምዝገባ ቦታ ወይም በአድራሻዎቻችን አግኙን። መማር ለሚፈልጉ ሌሎችም ኦርቶዶክሳውያን ሼር በማድረግ እንጋብዛቸው። ሠናይ፡ጊዜ። @MerfaqeGeez 🏵 ም ር ፋ ቀ ፡ ግ እ ዝ 🏵 0975760575
显示全部...
71
ይለይብኛል ጠብቆ አሳድጎ ከልጅነቴ አባት እየሆነኝ ሚካኤል አባቴ ይለይብኛል ሚካኤል ይለይብኛል በክንፉ ሸፍኖ በቤቱ አሳድጎኛል /2/
አዝ
አያምርብኝ ብዘነጋው ታሪኬን ሚካኤል ነው ያስጌጠልኝ ህይወቴን አልረሳብኝ እርሱ አትርሳብኝ ያልኩትን ለካስ ሰምቶኝ ኖሯል የልጅነት ጸሎቴን ሚካኤል  ያን ሁሉ ዘመን የታገሰኝ ሚካኤል   ፍሬ ጠብቆ ያልቆረጠኝ ሚካኤል የከፍታዬ መሰላል ሚካኤል መነሻዬ ሆነሀል
አዝ
እንዳይከፋኝ አንዳልደፋ አንገቴን እንዳላለቅስ እንዳላፈስ እንባዬን እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል ካጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል ሚካኤል  ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ ሚካኤል   ና ድረስልኝ ሳልልህ ሚካኤል እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን ሚካኤል አሳምረው ፍፃሜዬን
አዝ
ውድቅ አረገው የጠላቴ ክፉ እቅድ አራመደኝ በከፍታዬ መንገድ ሊያስቀረኝ አልቻለም ሊጎትተኝ ባላጋራ ተጥሎ ስላለ በእግዚአብሔር ድንቅ ስራ ሚካኤል   እሳታዊ ነው ነበልባል ሚካኤል ጠላቴ ፊትህ ይቀልጣል ሚካኤል  ለኔ ኃይሌ ነው መከታዬ ሚካኤል   የዘለዓለም ጠባቂዬ ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
4_5773691443289789286.mp36.36 MB
star reaction 1 252🥰 3🕊 3😍 3
ይበራል በክንፉ ይበራል በክንፉ ምልጃውም ፈጣን ነው የአምላክ ስም አለበት ስሙ ሚካኤል ነው ያሳደገኝ መልአክ ዛሬም ከኔ ጋር ነው/2/
አዘ
ከፊቴ ቀደመ ደመናን ዘርግቶ እንዳልደናቀፍ ጉድባዎቼን ሞልቶ ዛሬ ላለሁበት ብሩቱ ጉልበት ሆነኝ ሰው ለመባል በቃሁ ሚካኤል ደገፈኝ
አዝ
በእናቴ እቅፍ ገብቼ መቅደሱ አለሁ እስከዛሬ አጥሮኝ በመንፈሱ የህይወቴን ሰልፎች አለፍኩ ከእርሱ ጋራ ተፅፏል በልቤ የሚካኤል ስራ
አዝ
በዙሪያዬ ተክሎ የእሳት ምሰሶውን ፅድቅ እየመገበ ኣሳደገኝ ልጁን የአምላኬን ምስጋና ዘውትር እያስጠናኝ እርሱ ነው ሚካኤል በመዝሙር የሞላኝ
አዝ
ፊት ለፊት ተተክሎ ከታናሿ መንደር ይሰማኝ ነበረ ቅኔው ሲደረደር ይወስደኛል ደጁ እየቀሰቀሰ ታላቁን በረከት በውስጤ አፈሰሰ
አዝ
ሴኬምን እንዳላይ ክንፎቹን ጋረደ መራኝ ወደ ህይወት መዳኔን ወደደ የሞአብን ቋንቋ ከአፌ ላይ አጥፍቶ በፀጋው ቃል ቃኘኝ በበረከት ሞልቶ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ_መዝሙር_ይበራል_በክንፉ_yiberal_bekinfu_by_Tewodro.m4a5.65 MB
230🕊 7🔥 1
ማር ሚካኤል ማር ሚካኤል ልበል ማር ሚካኤል ልበልህ/2/  ባርከህ አሳደከኝ በቅኔ በዜማ መዝሙር አልሰስትም አባቴ ለአንተማ
አዝ
ጅማሬዬ ታናሽ ያልበቃሁ ብሆንም እንድፀና አውቃለሁ ከፊቴ ስትቀድም  ፍፄሜዬ እንዲያምር እንዲዋብ በቤትህ አበርታኝ ልበርታ አፅናኝ ልፅና ልጅህ ባህሩን ክፈለው በደረቅ እንዳልፈው እንዳልፈራ አበርታኝ እጄን በእጅህ ያዘው
አዝ
ከእንቅልፍ ያነቃኛል የደጅህ ደወል በሌሊት መጥቼ ቤትህ እንድውል በሄድኩበት ሁሉ ካፌ አትነጠልም የማር ወለላ ነው ሚካኤል ያንተ ስም ማር ሚካኤል ስልህ ማር ማር አለ አፌ መውደዴ እወነት ነው በምልጃህ ተርፌ
አዝ
በሞቱ ቀጠሮ ሰርግ የደገስክለት ምን አለ ባህራን ስታተርፈው ከሞት ዛሬም ተዐምርህን ትድግናህን አይተው ብዙዎች ይሉሀል ሚካኤል ሙት አንሳው ረዳኤ ምንዱባን በስደት ደጋፊ ከክፉ ከልለህ በድል አሳላፊ
አዝ
አለቱን ከፍለኸው በበትረ መስቀል ከጭንጫው ሰጠኸኝ ማርና ፀበል ቀድሞ ለእስራኤል ያኔ እንዳደረከው የሰማነውን ዛሬ ሆኖ አየነው የብርሀኑን አምድ ፋና ተከትለን ከቅዱሳን ስፍራ ዛጅርማኤል ደርሰን
አዝ
ከእንቅልፍ ያነቃኛል የደጅህ ደወል በሌሊት መጥቼ ቤትህ እንድውል በሄድኩበት ሁሉ ካፌ አትነጠልም የማር ወለላ ነው ሚካኤል ያንተ ስም ማር ሚካኤል ስልህ ማር ማር አለ አፌ መውደዴ እወነት ነው በምልጃህ ተርፌ ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
NEW_አዲስ_ዝማሬ_ማር_ሚካኤል_Mar_Michael_ዘማሪ_ዲያቆን_አቤል_መክብብ_mahtot.m4a8.18 MB
216🕊 14
Repost from TgId: 2150339683
照片不可用在 Telegram 中显示
🏵 ሰላም፡ለኵልክሙ። እነሆ ግእዝን በአንድ ወር ልዩ ግእዝን የምንማርበት ዝግጅታችን ተመልሰናል። በግእዝ ቋንቋን ትውልዱ በሚቀለውና ዘመኑን በዋጀ መልኩ በርቀት ትምህርት ለመስጠት ቅድመ ዝግጅታችንን አጠናቀናል። ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመመዝገብ ጥንታዊና ውዱ ቋንቋችንን ዕንወቅ። 📖 ትምህርቱን ከ10 ዓመት ዕድሜ በላይ ለሆኑ ፤  ስልክ ወይም ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ በመጠቀም ሁሉም ሰው መማር ይቻላል
✅ ምዝገባውን ለማካሄድ ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር በዚህ በመላክ ነው ✅ @Geez180 @Geez180 @Geez180 👈
                 ⛳️ ለበለጠ መረጃ በምዝገባ ቦታ ወይም በአድራሻዎቻችን አግኙን። መማር ለሚፈልጉ ሌሎችም ኦርቶዶክሳውያን ሼር በማድረግ እንጋብዛቸው። ሠናይ፡ጊዜ። @MerfaqeGeez 🏵 ም ር ፋ ቀ ፡ ግ እ ዝ 🏵 0975760575
显示全部...
37
​​​​​​​​👆 የቀጠለ የቅዱስ ሚካኤል አለቅነት በሐዲስ ኪዳንም አንደሚቀጥል ይህ ነቢይ በትንቢቱ “በዚያ ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ ሚካኤል ይነሣል..” (ዳን.12፡1) በማለት ተናግሮለታል ፡፡ ስለዚህም ቅዱስ ሚካኤል እኛን ከሰይጣን አሽክላና ወጥመድ ይጠብቀንና በጸሎቱ በእግዚአብሔር ፊት ይቆምልን ዘንድ በእኛም ላይ ሹም ነው። ምክንያቱም እኛ የእግዚአብሔር ሕዝቦችና የርስቱ ወራሾች ነንና፡፡ እግዚአብሔር ነቢዩ ሙሴን የሕዝቡ መሪ አድርጎ መሾሙ እጅግ ትሑትና ስለመንጎቹ ነፍሱን እንኳ አሳልፎ እስከመስጠት ደርሶ ስለሚወዳቸው ነበር፡፡ (ዘኁል.12፡3፤ዘጸአ.32፡32)በሕዝቡም ላይ እርሱን መሾሙ እንዲሠለጥንባቸው ወይም እንዲገዛቸው ሳይሆን በትምህርቱና በጸሎቱ እነርሱን እንዲያግዛቸው ነው፡፡ እንዲህም ስለሆነ ቅዱስ እስጢፋኖስ ስለሙሴ ሲመሰክር “እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው”አለ፡፡ (የሐዋ.7፡35) እንዲሁ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እጅግ ትሑትና ለሠራዊቱ ተቆርቋሪ የሆነ መልአክ በመሆኑ በመላእክትና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ተሾመ፡፡ በመላእክትና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙ ልክ እንደ ሙሴ በእነርሱ ላይ ሊሠለጥንባቸው ወይም ሊገዛቸው ሳይሆን መላእክትን ሊመራ ፣ እኛን ደግሞ ከሰይጣን ጥቃት ሊጠብቀንና በጸሎቱ ሊራዳን ነው (ይሁዳ.12)፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን መላእክት እኛን እንደሚጠብቁና እንደሚራዱ እንዲሁም ስለእኛ በፊቱ አንደሚቆሙ ሲያስተምረን “ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ስንኳ እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ሁል ጊዜ በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁ” (ማቴ.18፡10) ብሎናል፡፡ እኛን ይጠብቁ ዘንድ የተሰጡን ቅዱሳን መላእክት ስለእኛ እንዲህ የሚቆረቆሩና ስለመዳናችን የሚተጉ ከሆነ በቅድስናው ልቆ የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመው ቅዱስ ሚካኤል እንዴት ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ይበልጥ አይቆም? (ሉቃ.13፡6-9) እንዴትስ በተሰጠው ሥልጣንና ኃይል አይረዳን? (መዝ.33፡7) እርሱ “ስለሕዝብህ ልጆች የሚቆመው” መባሉም እኛን በጸሎቱና በተራዳኢነቱ የጽድቅ ሕይወታችንን በሚገባ እንድናከናውን እንደሚራዳን የሚያሳይ ኃይለ ቃል ነው፡፡ የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ጸሎቱና በረከቱ በእኛ ላይ ለዘለዓለሙ ይደርብን አሜን፡፡ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
314🥰 25🕊 13
​​​ሕዳር ሚካኤል ! እንኳን ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሲመት በሠላም አደረሰን ! በዓለ ሲመቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል (አንብባችሁ ስትጨርሱ ለሌሎችም ታሪኩን እንዲያዉቁ #SHARE ብታደርጉ ብዙ አተረፋችሁ፡፡) ቤተ ክርስቲያን ልጆቹዋ የመላእክትን ተራዳኢነት አውቀው እንዲጠቀሙና የመንግሥቱ ወራሾች ለመሆን እንዲበቁ ስትል ለቅዱሳን መላእክት የመታሰቢያ ቀን በመስጠት በእነርሱ የምናገኛቸውን እርዳታዎች እንዲታወሱ ታደርጋለች፡፡ በዚህም መሠረት በህዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡ እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል። ይህን ሁለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በተሰኘው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው ፡፡ ይህም እንደሆነ እንድንረዳ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለውን እስራኤል ዘሥጋን ሲራዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት “… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ የያዘ ሰው በፊቱ ቆመ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ” (ኢያ.5፡13) ይለናል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነፃ ሲያወጣቸው ይመራቸው የነበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ሹመቱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይም በመሆኑ ስለ እነርሱ ዲያብሎስ ይዋጋው፣ በጸሎትም ይራዳቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ኃጢአት ሠርተው ሲያገኛቸው ለእግዚአብሔር አድልቶ ኃጢአተኞችን ስለሚቀጣ እግዚአብሔር ሕዝቡን “በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት” (ዘጸ.23፡21) ብሎ አስጠንቅቋቸው ነበር፡፡ ይህም ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙን ያስረዳናል፡፡ ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱት ጥቅሶች ሕዝበ እስራኤልን ይራዳቸው የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ አያረጋግጥም የሚል ካለ “መልአክ” የተባለው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ነቢዩ ዳንኤል በተላከ ጊዜ ገልጦልን እናገኛለን፡- ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ቅዱስ ሚካኤል ስለመሾሙ ሲመሰክር “በእውነት በመጽሐፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ ማንም የለም”(ዳን.10፡21) ብሎአል፡፡ ስለዚህም ለኢያሱ የተገለጠውና እስራኤላውያንንም የመራው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን እንረዳለን፡፡ #ይቀጥላል ....... 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
224🕊 14