ch
Feedback
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

前往频道在 Telegram

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

显示更多
2025 年数字统计snowflakes fon
card fon
44 133
订阅者
无数据24 小时
无数据7
-21530
帖子存档
照片不可用在 Telegram 中显示
ሀኪሚ 👉 የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች አሸናፊ 🥇🇲🇦 #ዳጉ_ጆርናል
显示全部...
42👍 10
በድሬዳዋ ከተማ በሶስት ወራት ውስጥ 289.24 ቶን ፓልም ዘይትና ሩዝ ጥራቱ የተጓደለ በመሆኑ ወደ ሀገር እንዳይገባ ተደረገ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባለፉት 3 ወራት ባካሄደው የተቀናጀ የቁጥጥር ስራ ለሕዝብ ጤና ስጋት የሆኑ ምርቶችን ከገበያ ማስወገዱን ገልፃል።የቅርንጫፉ ኃላፊ አቶ ጌቱ ቦጋለ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት  በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 259 ቶን ጊዜያቸው ያለፈባቸው የምግብ ምርቶች እንዲወገዱ ሲደረግ በተጨማሪም 30 ቶን ሩዝና እና  የምግብ ዘይት የተበላሹ ምርቶች በህብረተሰብ ጤና ላይ ጉዳት እንዳያደርስ  ከገበያ ተሰብስቦ ጥቅም ላይ እንዳይውል ተደርጓል። በተለይም በገቢ ምርቶች ላይ በተደረገው ጥብቅ ቁጥጥር ምክንያት 289ነጥብ24 ቶን ፓልም ዘይትና ሩዝ ጥራቱ የተጓደለ በመሆኑ ወደ መጣበት አገር እንዲመለስ ተደርጓል። ባለሥልጣኑ በሩብ ዓመቱ ባካሄደው የቁጥጥር ስራ 65 የሕግ ጥሰት ጉዳዮች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን መውሰዱን የገለፁት አቶ ጌቱ አክለውም  ከ276ሺ489 ሜትሪክ ቶን በላይ ለሚሆን ገቢ ምግብ እንዲሁም 711 ሜትሪክ ቶን ለውጭ ገበያ የቀረበ ምግብ የጥራትና ደህንነት ቁጥጥር ተደርጓል። በመድኃኒት ዘርፍም ክትትሉ ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው በዚሁ ጊዜ ውስጥ 96 የመድኃኒት የጎንዮሽ ጉዳት እና 437 የክትባት የጎንዮሽ ጉዳት ሪፖርቶች ተሰብስበዋል። ህገ-ወጥ ምርት ዝውውርን ለመቆጣጠር ከፖሊስ ጋር በቅንጅት እየተሰራ ሲሆን ከህብረተሰቡ የተላኩ 30 የጥቆማ መልዕክቶች ለቁጥጥር ስራው ከፍተኛ ጥቅም ላይ መዋላቸውን ያሳወቁ ሲሆን በተጨማሪም ወደ ዘርፉ ለመግባት መስፈርት ላሟሉ 160 ድርጅቶችም የብቃት ማረጋገጫ እንደተሰጣቸው አሳውቀዋል። በትግስት ላቀዉ #ዳጉ_ጆርናል
显示全部...
15👍 5😁 3
照片不可用在 Telegram 中显示
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ያለ ረዳት አገልግሎት የሚሰጡ የህዝብ ማመለሽ ተሽከርካሪዎችን እቀጣለሁ አለ ቢሮው ያለ ረዳት አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች በከተማዋ እየበዙ ነው ያለ ሲሆን ከዚህ በኋላ በመመሪያው መሰረት ረዳት የሌላቸውን ታክሲዎች እቀጣለሁ ብሏል። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ክትትልና ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ታመነ ያለ ረዳት ማሽከርከር ገንዘብ በመቀበል፣ ገቢና ወራጅ በመቆጣጠር የሹፌሩን ትኩረት ስለሚሰርቅ ለአደጋ ያጋልጣል ብለውናል። ኃላፊው ከዚህ ቀደም ለሌሎች የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ብቻ ትኩረት በመስጠታችን ረዳት ያላቸውና የሌላቸውን ተሽከርካሬዎች የመለየት ውስንነት ታይቶብናል ብለዋል። ከዚህ በኋላ ግን የታክሲ ረዳት መኖር አንዱ የትራፊክ ደህንነት አካል በመሆኑ ሁሉም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ላይ ክትትል እናደርጋለን ብለዋል። Via ሸገር ኤፍኤም #ዳጉ_ጆርናል
显示全部...
29👍 11😁 7
በትምህርት ቤቶች ዉስጥ ሲከበሩ የሚታዩት እንደ Crazy Day፣ Gentle Day ፣ Olds Day፣  Valentine Day፣ Color Day፣ Pyjama Day ከዚህ በኋላ እንዳይከበሩ ተከለከለ ደንቡ የኢትዮጵያውያንን ባህልና ወግ የሚቃረኑ ተብለው በግልጽ የተዘረዘሩ አሉታዊ መጤ ድርጊቶችንና ክብረ በዓላትን በትምህርት ቤቶችና አካባቢ መፈጸም ሙሉ በሙሉ ይከለክላል። የሀገሪቷን ባህልና ወግ ይቃረናል ከተባሉት ድርጊቶች ዉስጥ Crazy Day፣ Gentle Day ፣ Olds Day፣  Valentine Day፣ Color Day፣ Pyjama Day የሚሉት ይገኙበታል መባሉን ዳጉ ጆርናል ከካፒታል ዘገባ ተመልክቷል። በተጨማሪም የትምህርት አዋኪ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ ግለሰቦች እና ተቋማት እስከ 150,000 ብር ቅጣት በአዲሱ ደንብ ይጠብቃቸዋል። ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ተቋማትና አካባቢያቸው የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያለመ አዲስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ ማውጣቱን አስታውቋል። ይህ ደንብ ከኢትዮጵያውያን ወግና ልማድ ጋር ይቃረናሉ ተብለው የተለዩ የውጭ ባህላዊ ልማዶችን ጨምሮ፣ እየጨመረ የመጣውን አዋኪ ጉዳዮች ለመግታት ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል። የደንቡ ዋና ዓላማ በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የሚስተዋሉ አዋኪ ጉዳዮችን በመከላከል፣ ሁለንተናዊ ስብዕናው የተሟላ፣ በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፀና ግብረ-ገብነትን የተላበሰ ብቁ ትውልድ እንዲፈጠር ማስቻል ነው። ትምባሆ (ሲጋራ፣ ሺሻ)፣ ጫት፣ አልኮል፣ የናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ ዝርያ ያላቸው አደገኛ ህገ ወጥ መድኃኒቶችና ሱስ አስያዥ ዕፆች በትምህርት ቤቶችና አካባቢ መገኘት፣ መጠቀም፣ መሸጥ፣ ማብቀል፣ ማምረት ወይም መለወጥ የተከለከለ መሆኑን አስታውቋል። የአልኮል መሸጫና ማከፋፈያ ቤቶች፣ የሲጋራ መሸጫ ሱቆች፣ ሺሻ ቤቶች፣ ጫት መሸጫና መቃሚያ ቤቶች፣ ጭፈራ ቤቶች፣ ቁማር ቤቶች፣ የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች እና የሰውነት መታሻ (ማሳጅ) ቤቶች በአዲሱ ደንብ  ተከለክለዋል። እንዲሁም ፊልም ማጫዎቻ ቤቶች፣ ፕሌይ ስቴሽን ቤቶች፣ ዲ.ኤስ.ቲቪ ቤቶች፣ ከረንቡላ ፑል፣ ጆተኒ፣ ቢንጎ እና የስፖርት ቁማር መጫወቻ ቤቶችም እገዳ ከተጣለባቸው ድርጊቶች መካከል ዉስጥ ተካተዋል። Via ካፒታል #ዳጉ_ጆርናል
显示全部...
👍 92 22👏 10👎 3😁 3🤔 1🤝 1
የሰባት ዓመቱን ታዳጊ በማገት አንድ ሚሊዮን ብር የጠየቀዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ በቡኖ በደሌ ዞን ገቺ ወረዳ የሰባት ዓመት ልጅ በማገት ወላጆቹን አንድ ሚሊዮን ብር የጠየቀዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጥቷል ። ብስራት ሬዲዮ ከቡኖ በደሌ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ባገኘዉ መረጃ መሠረት ጉተማ አቡበከር የተባለ የ27 ዓመት ወጣት የሰባት ዓመቱን ልጅ በማገት አንድ ሚሊዮን ብር ወላጆቹን የጠየቀ ሲሆን ቤተሰቦችም ብሩን መክፈል ስለማይችሉ ለፖሊስ ማሳወቃቸዉ ተገልጿል ። ፖሊስ ተከሳሹን በመከታተል በምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ እራሱን ሸሽጎ ሲንቀሳቀስ በፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል ። ተከሳሹ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኃላ ፖሊስ ልጅን ለቤተሰቦቹ ያስረከበ ሲሆን በተከሳሹ ላይ አስፈላጊዉን ማስረጃ አሰባስቦ ለአቃቤ ህግ ልኳል ። አቃቤ ህግ በወንጀል ህግ ቁጥር 589 ንዑስ አንቀፅ መሠረት ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅን በሀይል አፎኖ በመዉሰድ ወንጀል ክስ መስርቶበታል ። ክሱን የተመለከተው የቡኖ በደሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት ተከሳሹ በፈፀመዉ የወንጀል ድርጊት በ14 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ። በመባ ወርቅነህ #ዳጉ_ጆርናል
显示全部...
18👍 4
በደብረ ማርቆስ ከተማ ወላጅ አባቱን እና የእንጀራ እናቱን በጥይት የገደለው ተከሳሽ በእድሜ ልክ  እስራት ተቀጣ በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በተድላ ጓሉ ክፍለከተማ ቀበሌ 18 ልዩ ቦታው ታቦር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ተከሳሽ ትዕዛዙ ዋለልኝ ፈንታ የተባለው ግለሰብ  ጥቅምት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 3:00 ሰዓት የወንጀል ድርጊቱን ፈፅሟል። ለቤት መስሪያ ድጋፍ ካልሰጣችሁኝ በሚል ምክንያት ወላጅ አባቱን እና የእንጀራ እናቱን ለስራ በተሰጠው የጦር መሣሪያ የተለያዩ የሰውነት ክፍላቸው ላይ በጥይት ደጋግሞ በመምታት ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጓል ። ወንጀሉ ከተፈጸመ በኋላ ህብረተሰቡ ለጸጥታ ኃይሉ በሰጠው ጥቆማ መሠረት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል ፖሊስ የምርመራ ሂደቱን በእጅ ከፈንጅ በማጣራት እና መዝገቡን በተገቢው ሁኔታ በማደራጀት ለምስራቅ ጎጃም ዞን አቃቢ ህግ መምሪያ ልኳል ። የምስራቅ ጎጃም ዞን አቃቢህግ ከፖሊስ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ በማደራጀት በማስረጃ አስደግፎ ክስ በመመስረት  ተገቢው የህግ ሂደት እንዲታይ አድርጓል ። የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር 9 ቀን  2018 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ መሠረት ተከሳሽ ትዕዛዙ ዋለልኝ ፈንታ ጥፋተኛ መሆኑን በሰው ማስረጃ በመረጋገጡ በእድሜ ልክ  እስራት መቀጣቱን የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የህዝብ ግንኙነት  እና ኮሙኒኬሽን  ባለሙያ የሆኑት አቶ መስፍን ትዕዛዙ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። የሰው ልጅ ችግሮች እና አለመግባባቶች በሚከሰቱበት ግዜ ሰከን ብሎ ተወያይቶ መፍታት እየተቻለ በቂ ባልሆነ ምክኒያት ክቡር የሆነውን የሰው ህይወት መቅጠፍ ተገቢ ያልሆነ እና ያውም ተንከባክበው ያሳደጉትን ወላጆችን በጥይት መግደል ሰብአዊ ባህሪ ያልሆነ አረመኔያዊ ተግባር መሆኑን መምሪያው ገልጿል። ጊዜያዊ ያልሆኑ አለመግባባት እና የሀብት ይገባኛል ጥያቄዎች በሚኖሩበት ጊዜ ቸኩሎ እርምጃ ከመውሰድ እና ጸብ ከመፍጠር በፊት በሀገር ሽማግሌዎች እና በሀይማኖት አባቶች አማካኝነት እንዲፈቱ ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል ። #ዳጉ_ጆርናል
显示全部...
9🤬 6
照片不可用在 Telegram 中显示
显示全部...
ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት በፀሐይ ኃይል የሚሠራ የውኃ ፕሮጀክት ለአገልግሎት ክፍት ተደረገ በላሊበላ ከተማ ከ77 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ እና ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት በፀሐይ ኃይል የሚሠራ የውኃ ፕሮጀክት ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። ፕሮጀክቱ በዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) እና በጀርመን መንግሥት የተሠራ ነው። በላሊበላ ከተማ የንጹሕ መጠጥ ውኃ ችግር የረጅም ጊዜ የማኀበረሰቡ ጥያቄ እንደነበር ያነሱት የከተማው ነዋሪዎች ውኃ ለማግኘት እስከ አስር ቀን ይጠብቁ እንደነበር ተናግረዋል። ይህ ፕሮጀክት ሥራ ከጀመረ በኋላ በየዕለቱ ውኃ ማግኘት መጀመራቸውን ነዋሪዎቹ አንስተዋል። ይህንን በጎ ተግባር የከወነውን እና ለዘወትር ጥያቄያቸው ምላሽ የሰጠውን የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበርን አመስግነዋል። ፕሮጀክቱ በዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል በአፍሪካ ከተሠሩ የሶላር ፕሮጀክቶች ትልቁ ፕሮጀክት መኾኑን አስረድተዋል። የላሊበላ ማኅበረሰብ የረዥም ጊዜ ጥያቄ የኾነው የንጹሕ መጠጥ ውኃ እጥረት በዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ማኅበር መልስ በማግኘቱ  መደሰታቸውንም ተናግረዋል። የላሊበላ ከተማ ንጹሕ መጠጥ ውኃ መልሶ ግንባታ እና ሶላራይዜሽን ፕሮጀክት ስድስት የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች፣ 3 የውኃ መሳቢያ ፓምፖች፣ 12 የውኃ ማሰራጫ ፓምፖች አሉት። 4 መጠባበቂያ ጀነሬተሮች፣ በፀሐይ ኃይል የሚሠራ የውኃ ማጣሪያ ሥርዓት እና የውኃ ጥራት መቆጣጠሪያ ቤተ ሙከራን ያቀፈ እንደኾነ የገለጹት የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ የላሊበላ ከተማ የውኃ ፕሮጀክት ኃላፊ ኢንጂነር ዘሪሁን ለገሰ ናቸው። በቀን እስከ 2 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውኃ መስጠት የሚችለዉ ፕሮጀክቱ ከ77 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል። የሶላር ፕሮጀክቱ የኤሌክትሪክ ወጭን ሙሉ በሙሉ ያስቀራል፡፡ በሰመሀር አለባቸው #ዳጉ_ጆርናል
显示全部...
15👍 5👎 1🤝 1
በፊሊፒንስ በከፋ የሙስና ቅሌት የተነሳ ሁለት ሚኒስትሮች ከስልጣን ተነሱ የፊሊፒንስ ፕሬዝዳንት ፈርዲናንድ ማርኮስ ጁኒየር ካቢኔ ሁለት ሚኒስትሮች ከስልጣን ለቀዋል፡፡ ባልተገነባ መሠረተ ልማት እንደተገነባ ተደርጎ ፈሰስ በተደረገ ገንዘብ እና በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ጉድለት ያሳየዉ የመንግስት ሀብት ላይ በተደረገው ምርመራ ላይ ሚኒስትሮቹ ተሳትፈዋል:: ይህም የሀገሪቱን መንግስት በሙስና ቅሌት ላይ ያጋጠመውን ቀውስ አመላካች ሆኗል፡፡ ዋና ፀሃፊ ሉካስ ቤርሳሚን እና የበጀት እና ማኔጅመንት ዲፓርትመንት ፀሃፊ አሜና ፓንጋንዳማን ሁለቱም ከሃላፊነታቸው መነሳታቸውን የፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግስት የፕሬስ ኦፊሰር ክሌር ካስትሮ አስታዉቀዋል።ካስትሮ እንደተናገሩት ሚኒስትሮቹ “ዲፓርትመንታቸው ከጎርፍ መቆጣጠሪያ ጋር በተዛመደ ክስ እንደተመሰተተባቸዉ” እና “አስተዳደሩ ጉዳዩን በተገቢው መንገድ እንዲፈታ የመፍቀድ ሃላፊነት በመገንዘብ” ኃላፊነታቸውን ለመልቀቅ መምረጣቸውን ዘ ፊሊፒንስ ኢንኩየር ጋዜጣ ዘግቧል። በፊሊፒንስ ፖለቲካ ውስጥ ኤክስፐርት እና በሲንጋፖር ዩሱፍ ኢሻክ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ባልደረባ የሆኑት አሪስ አሩጋይ እንደሚሉት ቤርሳሚን እና ፓንጋንዳማን ከሐምሌ ወር ጀምሮ ከተቀሰቀሰዉ የሙስና ቅሌት ተቃዉሞን ተከትሎ የማርኮስ አስተዳደር ከፍተኛ ደረጃ ስልጣን ያላቸዉ አባላት ናቸው።የሙስና ቅሌት በመላው ፊሊፒንስ 500 ሺ ሰዎችን በማኒላ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጡ ያደረገ ህዝባዊ ተቃውሞ አስከትሏል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
显示全部...
11👏 2👍 1😁 1
በአረብ ሀገራት ተሰደው የሚሰሩ  ኢትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞችን ጤና እና ደህንነት ለማሻሻል ያለመ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ በኢትዮጵያ በስደትና ጤና ላይ የተደረጉ የምርምር ጥናቶች አነስተኛ በመሆናቸው ከፍልሰት ጋር የተገናኙ ችግሮችን ለመፍታት ትልቅ ክፍተት እንደሚፈጥር ተጠቁሟል።በዛሬው እለት የኢትዮጵያዊያን ስደተኛ የቤት ሰራተኞችን ጤና እና ደህንነት ለማሻሻል ያለመ ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል፡፡ INNOVETH የተሰኘው  የዚህ ፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ ዶ/ር ካሳሁን ሃብታሙ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ወደ ተለያዩ የአረብ ሀገራት ለስራ የሚያቀኑ ሴት ኢትዮጵያዊያን በርካታ ችግሮች ያጋጥማቸዋል።የቋንቋ፣የባህል ተፅእኖ፣የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ ለስነ አእምሮ እና ለስነተዋልዶ ጤና ችግሮች እንደሚዳረጉ ጠቁመዋል። እንዲህ ያለ ችግር የሚያጋጥማቸው ሴቶች በቂ የሆነ የጤና አገልግሎትን እንደማያገኙ አስተባባሪው ገልፀው ይህን ክፍተት ለመሙላት እንዲቻል ፕሮጀክቱ ይፋ ሆኗል።ፕሮጀክቱ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኛ የቤት ሰራተኞችን ጤና እና ደህንነት በቴክኖሎጂ ፈጠራ በመታገዝ ለማሻሻል ያለመ መሆኑን ዶክተር ካሳሁን ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል። የሞባይል አፕልኬሽንን በመጠቀም እና የባለሙያዎችን ቡድን ባካተተ መልኩ ስደተኞች ባሉበት ቦታ መረጃ ማግኘት የሚችሉበት እድል ተመቻችቶላቸዋል። የሚገጥማቸውን የጤና ችግሮች በተለይም የስነ አእምሮና የስነልቦና ጉዳቶችን ማሻሻል እንዲችሉ የሚያስችላቸውን መረጃ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል።በተጨማሪም ወደ አረብ ሀገራት ጉዞ ከመጀመራቸው አስቀድሞ አስፈላጊውን ስልጠና እንዲያገኙ ይደረጋል ሲሉ አሰተባባሪው ገልፀዋል። ቅድስት ደጀኔ #ዳጉ_ጆርናል
显示全部...
17👎 4
ቻይና በዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ የተነሳ ከጃፓን የሚመጡ የባህር ምግቦችን ወደ ሀገሯ ማስገባት ከለከለች በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ አለመግባባት እየተባባሰ በመምጣቱ ቻይና ሁሉንም የጃፓን የባህር ምግቦች ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት መከልከሏን የጃፓን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።የጃፓን የህዝብ ስርጭት ኤንኤችኬ እና ኪዮዶ የዜና ወኪል እንዳስታወቁት ቻይና በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ  በጃፓን የባህር ምርቶች ላይ እ.ኤ.አ በ 2023 የጣለችዉን ገደብ አንስታ ነበር፡፡በወቅቱ እገዳ የጣለችዉ ጃፓን ከፉኩሺማ የኑክሌር ጣቢያ የታከመ ራዲዮአክቲቭ ውሃ ወደ ባህር ውስጥ መልቀቋን ተከትሎ ነዉ ። ኪዮዶ ኒውስ ጉዳዩን የሚያውቁ ምንጮችን በመጥቀስ እንደዘገበዉ ቻይና ለጃፓን እንዳስታወቀችዉ እገዳው በድጋሚ የተላለፈው ከፉኩሺማ ወደ ፓስፊክ ውቅያኖስ የሚለቀቀውን ውሃ ተጨማሪ ክትትል ስለሚያስፈልግ ነው።ነገር ግን እገዳው ሊጣል የቻለዉ እንደ እዉነታዉ ከሆነ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናይ ታካይቺ በሰጡት አስተያየት በቤጂንግ እና በቶኪዮ መካከል ባለው ግንኙነት ውስጥ ጥልቅ ቀውስ መፈጠሩን ተከትሎ ነዉ ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኖቬምበር 7 ለፓርላማ አባላት እንደተናገሩት የጃፓን ህልውና አደጋ ላይ የጣለው የቻይና ጥቃት በታይዋን ላይ ከተፈጸመ ከቶኪዮ ወታደራዊ ምላሽ ሊያስከል እንደሚችል በመናገራቸዉ ነው፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሯ ታካይቺ አስተያየት በቻይና ባለስልጣናት እና በመንግስት ሚዲያዎች ከፍተኛ ትችት ገጥሞታል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ ጃፓን በቻይና ያሉ ዜጎቿ የደህንነት ጥንቃቄዎችን እንዲያደርጉ እና በተጨናነቁ ቦታዎች ከመገኘት እንዲርቁ አስጠንቅቃለች፡፡ በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
显示全部...
10🔥 3👏 1😁 1
照片不可用在 Telegram 中显示
ባለፉት 3 ወራት ከ1ሺህ በላይ ሴቶች ደህንነቱ የተጠበቀ የፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት አግኝተዋል ተባለ ህጉ በሚፈቅድባቸዉ ሁኔታዎች ደህንነቱ የተጠበቀ ፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት በጤና ተቋማት ደረጃ በሰለጠኑ ጤና ባለሙያዎች መሰጠት የእናቶችን ህመምና ሞት ለመቀነስ ያለዉ ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታዉቋል ። በክልሉ ባለፋት 3 ወራት ደህንነቱ የተጠበቀ የፅንስ ማቋረጥና የድህረ ፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት እንክብካቤ ያገኙ ሴቶች 3ሺህ 380 ሲሆኑ ከእነዚህም ዉስጥ 1ሺህ 340 ሴቶች ህጉ በሚፈቅደዉ መሠረት ደህንነቱ የተጠበቀ የፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት አግኝተዋል፡፡ ቀሪዎቹ 2ሺህ 40 ሴቶች ድህረ ፅንስ ማቋረጥ ወይንም ድንገተኛ አገልግሎት ማግኘታቸዉን በክልሉ ጤና ቢሮ የቤተሰብ ዕቅድ  ፣የአፍላ ወጣቶች እና ወጣቶች የጤና ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ አብረሀም ወንድሙ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ። እንዲሁም 1ሺህ 883 ሴቶች የድህረ ፅንስ ማቋረጥ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ማግኘታቸዉ ተገልጿል ። አፍላ ወጣቶችና ወጣት ሴቶች የድህረ ፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት በተለይም ደግሞ የድህረ ፅንስ ማቋረጥ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት በቀጣይ ያልታቀደ እርግዝና እንዳይከሰት የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት እና ህጉ በሚፈቅድባቸዉ ሁኔታዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት ተደራሽነት ላይ በትኩረት መስራት አለብን ሲሉ አቶ አብረሀም ጨምረዉ ለጣቢያችን ገልፀዋል ። በመባ ወርቅነህ #ዳጉ_ጆርናል
显示全部...
👎 26 9
የመጀመሪያው መሳሳም ከ21 ሚሊዮን ዓመታት በፊት መፈጸሙን ሳይንቲስቶች አስታወቁ መሳሳምን ሰዎች ፣ ጦጣዎች እና የዋልታ ድቦች ይፈጽሙታል፤ አሁን ላይተመራማሪዎች የመሳሳም የዝግመተ ለውጥ አመጣጥን በተመለከተ የደረሱበትን ይፋ አድርገዋል፡፡ ጥናታቸው እንደሚያመለክተው በአፍ የመሳም ሂደት ከ 21 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በዝግመተ ለውጥ የተፈጠረ ሲሆን የሰው ልጅ እና ሌሎች ዝንጀሮዎች የጋራ ቅድመ አያት ፈጽመዉት ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡ ተመሳሳይ ጥናት እንዳመለከተው ኒያንደርታሎችም ተሳስመው ሊሆን ይችላል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ሳይንቲስቶቹ ስለ መሳሳም ያጠኑት የዝግመተ ለውጥ እንቆቅልሽ የሆነ ጉዳይ በመሆኑ የተነሳ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ግልጽ የሆነ የመራቢያ ጥቅሞች የሌሉት መሳሳም በሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን በእንስሳት ዓለም ውስጥ የሚታይ ነገር ነው፡፡ ኢቮሉሽን ኤንድ ሂውማን ቢሄቪየር በተሰኘዉ ርዕስ የታተመዉ ጥናት መሳሳም “በአንዳንድ የከንፈር ወይም የአፍ ክፍሎች እንቅስቃሴ” የአፍ-ተኮር ግንኙነት መሆኑን ገልጸውታል።ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የዝግመተ ለውጥ ባዮሎጂስት ዶክተር ማቲልዳ ብሬንድል ከዚያ በመነሳት "መሳሳም ከ21.5 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በትልልቅ ዝንጀሮዎች ውስጥ የተፈጠረ ነው ብለን እናስባለን።" ስትል ተናግራለች፡፡ ይኸው ጥናት ኒያንደርታልስ ከ 40,000 ዓመታት በፊት የሞቱት የቅርብ የሰው ልጅ ዝርያ ያላቸዉ እንዲሁ ተሳምተዋል ሲል ደምድሟል።ቀደም ሲል በኒያንደርታል ዲ ኤን ኤ ላይ የተደረገ አንድ ጥናት እንደሚያሳየው የዘመናችን ሰዎች እና ኒያንደርታሎች የአፍ ውስጥ ማይክሮቦች በምራቅ ውስጥ የሚገኙትን የባክቴሪያ ዓይነቶች ይጋራሉ ሲል ጥናቱ ማሳወቁ ይታወሳል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
显示全部...
😁 77 18🤣 12👎 5💔 2🤔 1😭 1🤷 1