ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
前往频道在 Telegram
The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man
显示更多2025 年数字统计

44 133
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
-22730 天
帖子存档
照片不可用在 Telegram 中显示
👉 የማርበርግ ቫይረስ በዛሬው እለት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ተመርምሮ ሁሉም ነፃ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
👉 በዛሬው እለት የቫይረሱ ምርመረ የተደረገላቸው 44 ሰዎች ሁሉም ነፃ ሆነዋል።
👉 ከአሁን ቀደም ቫይረሱ ተገኝቶበት በህክምና ላይ የነበ አንድ ሰው ህይወት ማለፍ የዛሬው ሪፖርት ያሳያል።
👉በትላንትናው እለት ሁለት ሰዎች ማገገማቸው ተነግሯል።
👉አሁን ላይ ሁለት ሰዎች በህክምና ላይ እንዳሉ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
👉በአጠቃላይ እስካሁን 122 ሰዎች ተመርምረው 12 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን 9 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 15👏 1😁 1🙏 1
ደብረ ብርሃን ሆስፒታል ባለፉት ሶስት ቀናት በነፃ ህክምና የ1034 ዜጎችን የዓይን ብርሃን መመለስ መቻሉን አስታወቀ
ደብረ ብርሃን ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከኪዩር ብላይንድነስ ጋር በመተባበር ከህዳር 15 ቀን ጀምሮ ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና እየሰጠ መሆኑን አስታዉቋል ።
በዚህ የነፃ ህክምና አገልግሎት ባለፉት ሶስት ቀናት የ1034 ዜጎችን የዓይን ብርሀን መመለስ መቻሉን የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥላሁን ሙሉጌታ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ። ሆስፒታሉ ኪዩር ብላይንድነስ ከተሰኘዉ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ላለፉት 4 ዓመታት ለ5 ሺህ 398 ሰዎች ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና አገልግሎት መስጠቱን ገልጿል ።
አገልግሎቱ ዕድሜያቸው ያልገፋ ዜጎች ጭምር የዓይን ብርሃን መመለሱንና መደበኛ ህይወታቸውን እንዲመሩ ያስቻለ መሆኑም ተጠቁሟል ። ህክምናዉ እስከ ኅዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚቀጥል የተገለፀ ሲሆን ከ2 ሺህ በላይ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ይሰጣል ተብሏል ።
የዓይን ሞራ ግርዶሽ መንስኤው የዕድሜ መግፋት ሲሆን በዓለም ሆነ በኢትዮጲያ በቀዳሚነት ዓይነስውርነትን የሚያመጣ በሽታ ነው ። ከታካሚዎቹ መካከል ላለፉት 3 ዓመታት መንቀሳቀስ ቀርቶ የሚመገቡትንም ማየት ያልቻሉ እናት ይገኙበታል የተባለ ሲሆን የዓይን ሞራ ግርዶሽ በጊዜ ከታከመ የሚድን በመሆኑ ችግሩ ያለባቸዉ ሰዎች በጊዜ ምርመራ ማድረግና መታከም እንዳለባቸዉ አቶ ጥላሁን ሙሉጌታ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 28👍 8🥰 2🔥 1👌 1
በአማራ ክልል ለአስራ አራት የቱሪስት መዳረሻዎች የመፀዳጃ ቤቶችን ጨምሮ የንጹህ መጠጥ ውሃ እና ሌሎች አገልግሎቶች እንዲሟላላቸው ተደረገ
በአማራ ክልል ለሚገኙ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች የመሰረተ ልማት አገልግሎትን ለማከናወን የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አበበ እምቢአለ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በ2018 በጀት ሩብ ዓመት ለ11 የቱሪስት መስህቦች የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የመብራት፣ የኢንተርኔት አገልግሎትን ጨምሮ የመጸዳጃና መታጠቢያ ቤት እንዲሟላላቸው ለማድረግ በዕቅድ ተይዞ ነበር።
በዚህም በሰሜን ሸዋ፣ በደሴ፣ በሰሜን ጎጃም ፣ በደብረ ብርሃን፣ በዋግ እና በምስራቅ ጎጃም ለሚገኙ ለ14 መዳረሻዎች እንዲሟላላቸው ተደርጓል ።የመንገድ ዝርጋታ ለሚያስፈልጋቸው መዳረሻዎች እና የመስህብ ሀብቶች 58 ኪ.ሜ የጥርጊያ መንገድ መከናወኑን አቶ አበበ ገልፀው ይህም ህብረተሰቡን እና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር እንዲሰራ መደረጉን አብራርተዋል።
ይህንኑ ስራ በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በሰሜን ጎጃም፣በኮምቦልቻ፣ በሰሜን ወሎ እና በሰሜን ጎንደር ማከናወን ተችሏል።እነዚህ ተግባራት የቱሪስት ቁጥርን ለመጨመር እና የቱሪስት የቆይታ ጊዜን በማራዘም ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንደሚኖራቸው ታምኖበታል።
በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 9🤣 8👍 1😁 1
5 ቢሊየን 681 ሚሊየን 857 ሺህ 260 በመመዝበር በሕዝብና በመንግስት ላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ማረሚያ ወረዱ።
በከባድ የሙስና ወንጀል ምርመራ የተጣራባቸው አሥራ አንድ ተጠርጣሪዎች ክስ ተመስርቶባቸው ወደ ማረሚያ ቤት መውረዳቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
1ኛ ተከሳሽ አቶ ክፍሌ ወ/ማርያም ጋዎ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩ፤
2ኛ ተከሳሽ አቶ ወልደአብ ደምሴ ክብረት በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ግብዓት ምርትና አቅርቦት ዐብይ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበሩ፤
3ኛ ተከሳሽ አቶ ተንሳይ ሜጫ ወ/ስላሴ በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ሀብት አመራር ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ኮሚቴ አባል የነበሩ፤
4ኛ ተከሳሽ ወ/ሪት መንበረ ኃ/ማርያም ነጋሳ በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ፋይናንስ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የኮርፖሬሽኑ የግዢ ኮሚቴ አባል የነበሩ፤
5ኛ ተከሳሽ አቶ ሚሊዮን ገረመው እሸቱ በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ከፍተኛ የግዢ ባለሙያ እና የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ኮሚቴ አባልና ፀሀፊ የነበሩ፤
6ኛ ተከሳሽ አቶ ሰለሞን ገብሬ መላክ በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ ስራ አስፈጻሚ፣ የኮርፖሬሽኑ የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ኮሚቴ አባል፣ የብሄራዊ የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ኮሚቴ ፀሀፊ የነበሩ፤
7ኛ ተከሳሽ አቶ መንግስቱ ተስፋ ላቀ በኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስቴር የግብዓት አቅርቦት መሪ ሥራ አስፈጻሚ፣ የብሄራዊ የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ቴክኒካል ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበሩ፤
8ኛ ተከሳሽ አቶ ዘላለም ዳኜ ሮሪሳ በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የግብዓት ግዢ እና ትራንዚት ክፍል ስራ አስኪያጅ የነበሩ
9ኛ ተከሳሽ ካፒቴን ወንድወሰን ካሳ አሰፋ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ የነበሩ፤
10ኛ ተከሳሽ አቶ ጸጋዬ በርሀ ኪዳኑ በኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የነበሩ፤
11ኛ ተከሳሽ አቶ አለባቸው ሞልቶት ዳኜ የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የጅቡቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩ፤
በወንጀል ድርጊቱ ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው እነዚህ ተከሳሾች በጋራና በተናጠል የተሰጣቸውን ስልጣን ያለ አግባብ በመጠቀም የክልል መንግስታት ለኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የዓለም አቀፍ የአፈር ማዳበሪያ ግዢ እንዲፈፅም የሰጡትን ውክልና እና የኮፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ ውሳኔዎች፣ የግዢ መመሪያዎችን፣ ውሎችና ድንጋጌዎችን በመጣስ ነበር ወንጀሉን የፈፀሙት ሲል ፖሊስ ገልጿል።
ተከሳሾቹ ፦
• የተጋገረውን ማዳበሪያ ማስከስከሻ ወጪ 204 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ያለአግባብ በመክፈል፣
• ከመቐለ መርከብ ጊር ተነቀለ በማለት ኮርፖሬሽኑ 100 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ተጨማሪ የማጓጓዣ ወጪ እንዲያወጣ በማድረግ፤
• ጥራት የሌለው ማዳበሪያ የተጓጓዘበት ወጪ 39 ሚሊየን 992 ሺህ 860 የአሜሪካን ዶላርን ጨምሮ በድምሩ 40 ሚሊየን 296 ሺህ 860 የአሜሪካን ዶላር ወይም 5 ቢሊየን 681 ሚሊየን 857 ሺህ 260 በመመዝበር በሕዝብና በመንግስት ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ተመላክቷል።
ፖሊስ ግለሰቦቹ በዋናነት በወንጀል አድራጊነት እና ተካፋይ በመሆን በፈጸሙት ከባድ የሙስና ወንጀል የምርመራ መዝገብ አጣርቶ በፍትሕ ሚኒስቴር ለዐቃቤ ህግ ከላከ በኋላ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ ተመስርቶባቸው ወደ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ መደረጉን ገልጿል።
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 13😁 11😱 4🤔 2🤣 1
በአማራ ክልል ለአስራ አራት የቱሪስት መዳረሻዎች የመፀዳጃ ቤቶችን ጨምሮ የንጹህ መጠጥ ውሃ እና ሌሎች አገልግሎቶች እንዲሟላላቸው ተደረገ
በአማራ ክልል ለሚገኙ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች የመሰረተ ልማት አገልግሎትን ለማከናወን የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አበበ እምቢአለ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በ2018 በጀት ሩብ ዓመት ለ11 የቱሪስት መስህቦች የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የመብራት፣ የኢንተርኔት አገልግሎትን ጨምሮ የመጸዳጃና መታጠቢያ ቤት እንዲሟላላቸው ለማድረግ በዕቅድ ተይዞ ነበር።
በዚህም በሰሜን ሸዋ፣ በደሴ፣ በሰሜን ጎጃም ፣ በደብረ ብርሃን፣ በዋግ እና በምስራቅ ጎጃም ለሚገኙ ለ14 መዳረሻዎች እንዲሟላላቸው ተደርጓል ።የመንገድ ዝርጋታ ለሚያስፈልጋቸው መዳረሻዎች እና የመስህብ ሀብቶች 58 ኪ.ሜ የጥርጊያ መንገድ መከናወኑን አቶ አበበ ገልፀው ይህም ህብረተሰቡን እና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር እንዲሰራ መደረጉን አብራርተዋል።
ይህንኑ ስራ በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በሰሜን ጎጃም፣በኮምቦልቻ፣ በሰሜን ወሎ እና በሰሜን ጎንደር ማከናወን ተችሏል።እነዚህ ተግባራት የቱሪስት ቁጥርን ለመጨመር እና የቱሪስት የቆይታ ጊዜን በማራዘም ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንደሚኖራቸው ታምኖበታል።
በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
照片不可用在 Telegram 中显示
ሮማኒያ የፈረንሳይ ሚስትራል የአየር መከላከያ ስርዓቶችን ለመግዛት ስምምነት ላይ ደረሰች
የሮማኒያ የመከላከያ ሚኒስቴር ከበርካታ የአውሮፓ ህብረት ግዛቶች ጋር በጋራ በሚደረገው የግዥ ስምምነት ከ626 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ዋጋ ያለውን የፈረንሳይ ሚስትራል የአየር መከላከያ ስርዓቶችን እንደሚገዛ አስታዉቋል።ሚኒስቴሩ ከፈረንሳይ መከላከያ ሚኒስቴር ጋር 231 ሚስትራል ተንቀሳቃሽ የአየር መከላከያ ስርዓቶች ከሚሳይል አምራች ኤምቢዲኤ እና 934 ሚሳይሎችን ከስልጠና ፣ሲሙሌተር እና ሎጅስቲክስ ጎን ለጎን ለመግዛት ስምምነት መፈራረሙን ተናግሯል።
በመግለጫው መሳሪያዎቹ መቼ ወደ ሮማኒያ እንደሚደርሱ አልተገለጸም። የሮማኒያ ህግ አውጪዎች የግዥ ዕቅዱን በ2022 ለመጀመሪያ ጊዜ አጽድቀዋል።የአውሮፓ ህብረት እና የኔቶ ግዛት የሆነችው ሮማኒያ ከዩክሬን ጋር 650 ኪሜ የየብስ ድንበር የምትጋራ ሲሆን ሩሲያ በዳኑቤ በኩል የኪየቭ ወደቦችን ማጥቃት ከጀመረች በኋላ ድሮኖች የአየር ክልሏን ጥሰው መግባታቸዉን በተደጋጋሚ አስታዉቃለች።
የሮማኒያ አየር መከላከያዎች በአሁኑ ጊዜ ኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች፣ የሎክሂድ ማርቲን ሮኬት ማስወንጨፊያዎች፣ የአጭር ርቀት የደቡብ ኮሪያ አየር-ወደ-አየር ቺሮን ሚሳኤሎች እና የጀርመን ፀረ-አውሮፕላን ይገኙበታል።ሀገሪቱ በአዲሱ የአውሮፓ ህብረት የመከላከያ የገንዘብ ድጋፍ ዘዴ ውስጥ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለመገንባት ከዩክሬን ጋር በትብብር እየሰራች ነዉ፡፡
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 10
በፍኖተ ሰላም ከተማ የዝርፊያ ወንጀል ሲፈጽሙ የተያዙ ሁለት የሰላም አስከባሪ አባላት በ25 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ
በፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ከህግ አግባብ ውጭ የግለሰቦችን ስልክ በመንጠቅ የዝርፊያ ወንጀል የፈጸሙ ሁለት የሰላም አስከባሪ አባላት መቀጣታቸዉን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።በጽህፈት ቤቱ የወንጀል ምርመራ ንፁስ ክፍል ኃላፊ ዋና ሳጅን ዘላለም ጥላሁን እንደገለጹት በጃቢ ጠህናን ወረዳ የሰላም አስከባሪ አባል የነበሩት ቅዱስ እያሱና ኤሊያስ ገበየሁ ድርጊቱን ሲፈጽሙ መቆየታቸው ተገልጿል።
በዚህም ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት ላይ የቀድሞ ልዩ ሀይል ልብስ በመልበስና የጦር መሳሪያ በመያዝ በከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ አካባቢዎች የአምስት ግለሰቦችን የእጅ ስልክ በኃይል በመንጠቅ የዝርፊያ ወንጀል ፈጽመዋል።የከተማ አስተዳደሩ ከግል ተበዳዮች የደረሰውን ጥቆማ በመያዝ ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር ወንጀል ፈጻሚዎቹ የዘረፏቸው አምስት ስማርት ስልኮችና ለዝርፊያ ከተጠቀሙበት ክላሽ ኮብ መሳሪያ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።
የወንጀል ምርመራ ክፍሉም የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማደራጀትና ምርመራውን በማጣራት በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ በኩል ክስ እንዲመሰረትባቸው ማድረጉን ብስራት ሬዲዮ ከዞኑ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ከፖሊስና አቃቤ ህግ የቀረበለትን የሰውንና የሰነድ ማስረጃዎች በማጣራት ተከሳሾቹ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፏል።ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ህዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ሁለቱ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 9👍 5
በሰሜን ኢራቅ የሚገኘው የተፈጥሮ ጋዝ ማዉጫ ስፍራ በድሮን ጥቃት ተመታ
በኢራቅ ኮሆር ሞር የተፈጥሮ ጋዝ ማዉጫ ስፍራ ላይ የተፈጸመው የድሮን ጥቃት ተቋሙ ሥራውን እንዲያቆም አስገድዶታል፣ በሰሜናዊ ኢራቅ የኩርዲሽ ክልል አብዛኛው ኃይል እንዲቋረጥ አድርጓል ሲሉ የአካባቢዉ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።ጥቃቱ የተፈፀመው እሮብ ምሽት ላይ መሆኑን የሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። በርካታ የጋዝ ማከማቻ በመመታቱ ፍንዳታ እና ከፍተኛ የእሳት አደጋ መከሰቱን ኤጀንሲው ገልጿል።
በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።የኢራቅ ማእከላዊ ወታደራዊ አዛዥ የጋራ ዘመቻ ኮማንድ እንደገለፀው የጥቃቱ ትኩረት የክልሉን "ደህንነት እና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት" ማስተጓጎል ይመስላል ብሏል።እንደየአካባቢው ባለስልጣናት ገለጻ፣ 8 በመቶው የክልሉ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍርግርግ ተጎድቷል፣ በዚህም የተነሳ ከፊል ራስ ገዝ ክልል የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ አስከትሏል።
ክሆር ሞር የተፈጥሮ ጋዝ ማዉጫ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ኩባንያ ዳና ጋዝ የሚተዳደር ሲሆን በሰሜን ኢራቅ ውስጥ በኪርኩክ እና በሱሌማንያ ከተሞች መካከል ይገኛል።መሐንዲሶች የነዳጅ መሰረተ ልማቱን ለመጠገን ከሁለት እስከ ሶስት ቀናት እንደሚፈጅ ተናግረዋል፡፡ የኢራቅ መንግስት እና ዳና ጋዝ ደግሞ አደጋውን ለማጣራት አጣሪ ቡድኖችን ወደ ስፍራዉ ልከዋል።
በሰምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
😭 8❤ 4👍 2
የወጣቶች የአደገኛ እፅ ተጠቃሚነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተነገረ
የወጣቶች የአደገኛ እፅ ተጠቃሚነትና ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተጠቁሟል።የመራቢያ ጤና ማህበራት ኮንሶርቲየም (CORHA) ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና ከፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከላት ሁኔታ ላይ ያተኮረ የምክክር አውደ ጥናት አዘጋጅቷል።
በማዕከላት ውስጥ የአደገኛ እፃችና አሉታዊ ልማዶችን ለመከላከል የሚደረጉ ፕሮግራሞች መኖራቸው እና የተጠቃሚ ወጣቶች ቁጥር እያደገ መምጣቱ በበጎ ጎን ተነስቷል።ይሁን እንጂ ማእከላቱ የወጣቶችን ፍላጎት ባማላ መልኩ ዘመኑን የሚመጥኑ እና ሁሉን አቀፍ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በርካታ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ ተጠቁሟል ።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ሙና አህመድ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የሚገኙ የስብእና ማእከላት የተለያዪ ስራዎችን ቢሰሩም የወጣቶችን ስብእና በሚፈለገው መልኩ እየገነቡ አይደሉም።በኢትዮጵያ ከ3ሺህ በላይ የወጣቶች ስብእና ማእከላት ቢኖሩም 1ሺህ 5መቶ 45 ቱ ብቻ ተገቢውን አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ አስረድተዋል።
በዚህ የተነሳ የሚፈለገውን የወጣት ስብእና መቅረፅ እንዳልተቻለ ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልፀው ለጉዳዮ መፍትሄ ለማምጣት በዘርፋ የተሰማሩትን ማእከላት ከማዘውተሪያነት ወደ ስብእና ማእከላት ለማምጣት ሰፊ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
🤔 5❤ 3
ትራምፕ በቀጣይ ዓመት በአሜሪካ በሚካሄደዉ የቡድን 20 ጉባኤ ደቡብ አፍሪካ እንደማትጋበዝ አስታወቁ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደቡብ አፍሪካ በ2026 በፍሎሪዳ በሚካሄደው የቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ ላይ አትጋበዝም ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ሀገሪቱ የቡድን 20 ፕሬዝዳንትነቱን ለአሜሪካ ኤምባሲ ተወካይ ለማስረከብ ፈቃደኛ መሆኗን ጠቅሰዋል። ትሩዝ በተሰኘዉ የማህበራዊ መድረክ ላይ ትራምፕ ባሰፈሩት መልዕክት በቅርቡ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የቡድን 20 ስብሰባ ላይ ላለመሳተፍ መወሰናቸው ይታወሳል፡፡ ለዚህም መነሻዉ በነጭ ደቡብ አፍሪካዉያን እና በሌሎች የኔዘርላንድ፣ ፈረንሣይ እና ጀርመን ሰፋሪዎች የሚደርስባቸውን ዘግናኝ የሰብአዊ መብት ረገጣ የደቡብ አፍሪካ መንግስት እውቅና አልሰጥም” በማለት ትራምፕ ከሰዋል።
መንግስት "ነጮችን እየገደለ እና እርሻቸው እንዲወሰድባቸው እየፈቀደ ነው" ሲል ተናግረዋል። የደቡብ አፍሪካ መንግስት ክሱን የሀሰት ሲል ዉድቅ አድርጓል። ትራምፕ በ2025ቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ የደቡብ አፍሪካን ድርጊት በመንቀፍ ሀገሪቱ "የቡደን 20 ፕሬዝዳንቷን ለአሜሪካ ኤምባሲ ከፍተኛ ተወካይ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነችም" ሲሉ ነቅፈዋል። እ.ኤ.አ. በ2026 በማያሚ ፣ ፍሎሪዳ ለሚደረገው የመሪዎች ጉባኤ ደቡብ አፍሪካ “ግብዣ እንደማይቀርብላት” ተናግረዋል።ትራምፕ ደቡብ አፍሪካ “በየትም ቦታ ለአባልነት ብቁ የሆነች ሀገር አይደለችም” በማለት ለአለም አሳይታለች፡፡ “ለእነሱ የሚደረጉ ክፍያዎች እና ድጎማዎች ይቆማሉ” ማለታቸው አይዘነጋም።
ለአስተያየቱ ምላሽ የሰጠችዉ ደቡብ አፍሪካ በ2026ቱ የቡድን 20 ስብሰባዎች ላይ እንዳትሳተፍ መከልከሏን የሚገልጸዉ የትራምፕ መግለጫ “አሳዛኝ” በማለት ጠርታዋለች።የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንታዊ ፅህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ ደቡብ አፍሪካ የቡድን 20 አባል በራሷ ስም እንደሆነ እና መብቷ እንደሆነ ገልጾ፣ የ ቡድን 20 አባልነት ጉዳይ በሁሉም አባላት ፍላጎት እንደሚመሰረት አስታዉቋል፡፡
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
😁 26👎 9❤ 8🤬 1
ህጋዊ ታሪፍ 430 ሆኖ ሳለ 900 ብር ያስከፈሉ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መዉሰዱን የዳዉሮ ዞን ፖሊስ አስታወቀ
በዳዉሮ ዞን እየተበራከተ የመጣዉን ብዝበዛ ለመከላከል ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ከታሪፍ በላይ በሚያስከፍሉ እና ትርፍ በሚጭኑ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የዳዉሮ ዞን ፖሊስ አስታውቋል ።
መነሻቸዉን ዳዉሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር መድረሻቸዉን ደግሞ ጂማ ከተማ ያደረጉ ሁለት አሽከርካሪዎች ከታሪፍ በላይ በማስከፈላቸዉ እርምጃ እንደተወሰደባቸው የዳዉሮ ዞን ትራፊክ ዲቭዥን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክር አማኑኤል አምባቸዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
በዳዉሮ ዞን ታርጫ ዙሪያ ወረዳ አባ ዳሂ ማዘጋጃ ከተማ ላይ ከታርጫ ጂማ ተሳፋሪን አሳፍሮ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አሽከርካሪዎች ህጋዊ ታሪፍ 430 የነበረዉን 900 ብር ማስከፈላቸዉን ዋና ኢንስፔክተር አማኑኤል አምባቸዉ ጨምረዉ ለጣቢያችን ገልፀዋል ።
ለእያንዳንዱ ተሳፋሪ 470 ብር በማስመለስ በአሽከርካሪዎቹ ላይ እርምጃ መወሰዱ ተነግሯል ። በአጠቃላይ ከሁለቱ አሽከርካሪዎች ያለ አግባብ የተወሰደ 31ሺህ 390 ብር ለተሳፋሪዎች በማስመለስ አሽከርካሪዎቹ እያንዳንዳቸው በ5ሺህ ብር እንዲቀጡ ተደርጓል ።
በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 22👏 8
በጊኒ ቢሳው ወታደራዊዉ ኃይል ፕሬዚዳንቱን በማሰር ስልጣን ተቆጣጠረ
ፕሬዝዳንቱ ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎ በቁጥጥር ስር በማዋል አንድ የጦር መኮንኖች ቡድን ጊኒ ቢሳውን መቆጣጠሩን ገልጿል።በዋና ከተማዋ ቢሳው የተኩስ ድምጽ ከተሰማ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ኢምባሎ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የመንግስት ምንጮች ሀሙስ እለት ተናግረዋል።የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር የእሁዱን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት እየጠበቀች ባለችበት በዚህ ወቅት መኮንኖቹ በመንግስት ቲቪ ላይ ቀርበው የምርጫ ዉጤት እንደማይገለጽ በማንዳት ሂደቱን አግደዋነዋል ብለዋል።
የወታደራዊዉ መኮንኖች ቡድን እንዳስታወቀዉ ሀገሪቱን ለማተራመስ ያሰበዉን የፖለቲከኞች ሴራ ለማክሸፍ እየሠራ መሆኑን በመግለጽ ፣ የሀገሪቱ ድንበር መዘጋቱን እና የሌሊት የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን ተናግረዋል።በሴኔጋል እና በጊኒ መካከል የምትገኘዉ ጊኒ ቢሳዉ በተደጋጋሚ ለመፈንቅለ መንግስት የተጋለጠች ሀገር ስትሆን እኤአ ከ1975 አንስቶ ከፖርቱጋል ነፃ ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ ወታደሮቹ ተፅእኖ ፈጣሪ የሆነባት ታዋቂ የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ማዕከል በመባል ትታወቃለች።
የምርጫው ውጤት ሐሙስ ዕለት ይፋ ይደረጋል ተብሎ ተጠብቆ ነበር ፤ሁለቱም እጩዎች ኢምባሎ እና የቅርብ ተቀናቃኙ ፈርናንዶ ዲያስ ማሸነፋቸውን ተናግረዋል።ዲያስ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶሚንጎስ ፔሬራ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡የመንግስት ምንጮች እንደተናገሩት ዲያስ፣ ፔሬራ እና የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ቦቼ ካንዴም ታስረዋል።ኢምባሎ በስልጣን ቆይታቸዉ ከበርካታ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራዎች መትረፋቸውን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ተቺዎቻቸዉ ተቃውሞዎችን ለመቆጣጠር ቀውሶችን ፈጥረዋል ይላሉ።የ53 አመቱ ፕሬዝዳንት ባለፉት 30 አመታት ውስጥ ለሁለተኛ ተከታታይ የስልጣን ዘመን የበቁ የሀገሪቱ ብቸኛ ፕሬዝዳንት ሆነው ታሪክ ለመስራት ፈልገው ነበር።
በሰምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 11👏 8😭 6😁 3👍 1
