ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷♂
前往频道在 Telegram
| እውነት | ፍትህ | ፍቅር | ✔ሥነ ልቡና | የተለወጠ ግለሰብ አለም ይለውጣል! የተለያዩ የስነልቦናና የላቀ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ላይ የተሰሩ video ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናሌን ይከታተሉ "የማወቅና የመለወጥ ሰአት አሁን ነው " https://www.youtube.com/user/TheNahusenai Facebook አድራሻዬ Fb.com/psychologyabc
显示更多2025 年数字统计

10 760
订阅者
-324 小时
-497 天
-15230 天
帖子存档
照片不可用在 Telegram 中显示
#መልካም_የጥቅምት_ወር_ይኹንላችሁ!
ይህ ወር የአዕምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡
ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ በኹሉም አካባቢዎች ሰላምን የምንሰማበት ፣ ፍትህን የምናይበት ይሁንልን ፡፡
✍ከእረፍት በኀላ ተመልሰናል። ቆሞ የነበረው የሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት የማሕበራዊ ሚዲያ ትምህርታችን ከዛሬ ጀምሮ በዐዲስ መልክ ይቀጥላል ፡፡
ሁሌም የማያልቅ ተስፋ አለ።
Telegram : t.me/psychoet
Facebook : fb.com/psychologyabc
መልዕክቱን #Share #Like በማረግ ለሌሎችም እናጋራ
照片不可用在 Telegram 中显示
የአለም የአእምሮ ጤና ቀን
መስከረም 30፣ 2015
የአእምሮ ጤንነትን የሚጠብቁና የሚያሳድጉ 5 ተግባራት
(በናሁሰናይ ፀዳሉ)
የአእምሮ ጤንነት ለሰው ልጅ ወሳኝ የሆነ የሕይወት ማገር ነው፡፡ ሰው እንደ ሰው ፣ ህዝብ እንደህዝብ ፣ ሀገርም እንደሀገር እንዲቀጥልና እንዲያድግ ዋናውን ሚና የሚጫወተው የአዕምሮ ጤንነት ነው ፡፡ በተለይም አሁን ያለንበት ጊዜ ደግሞ ይህ የአእምሮ ጤንነት በመንግስትም ሆነ በዘርፉ ባለሙያዎች ከፍተኛ ትኩረት ተሰቶበት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ከተለያዩ የሥነልቦና ቀውሶች ለመውጣት ወይንም የአእምሮ ጤንነታችንን ጠብቀን ለመቆየት የሚያስችሉን 5 ተግባራትን እንመለከታለን፡፡
✍አካላዊ ጤንነትንና ንቃትን ማዳበር
✍ አዳዲስ ክህሎቶችን መማር
✍ከሰዎች ጋር ያለውን ግንኙነት አጥብቆ መያዝ
✍ከነገና ከትናንት ይልቅ በአሁን ባለው ነገር ላይ ትኩረት መስጠት
✍አወንታዊ ነገሮችን ማሰብ
ምንጭ : Mental wellbeing & my personal reflection
መልካም ቀን ይሁንላችሁ!
ጽሑፉ ለናንተ ከጠቀማችሁ ሎችም እንዲጠቀሙበት #Share በማድረግ አካፍሉ! ማካፈል ከዚህ ይጀምራል፡፡
t.me/psychoet
照片不可用在 Telegram 中显示
የ11 ዙር የሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት ስልጠና በዚህ ሳምንት ይጀምራል፡፡ በቀረን ቦታ ይመዝገቡ፡፡ ሊ
ስለ ሳይኮሎጂ ለማወቅ ለሚፈልጉ እንዲሁም የሕይወት ክህሎት ስልጠና መሠልጠን ለሚፈልጉ መልካም አጋጣሚ ልምድ ባላቸው የሕይወት ክህሎት አሰልጣኞች።
📖ሳይኮሎጂ/ሥነልቦና ምንድነው?
📖ለሕይወታችን ምን ይፈይደል?
📖የሥነልቡና ቀውስ ምንድነው? እንዴትስ ያጋጥማል? መፍትሄዋቹስ ምንድናቸው?
📖Counseling ምንድነው?
🔖የሕይወት አላማን መረዳትና ራስን ማግኘት
🔖የ2015 ስኬታማ ዕቅድ አወጣጥና የጊዜ አጠቃቀም
🔖የስሜት ብልህነት
🔖ፍርሀትና ጭንቀትን ተቋቁሞ መውጣት
🔖ተግባቦትና በራስ መተማመን
ለሰልጣኞቻችን የግል የማማከር አገልግሎት እናመቻቻለን!
ስልጠናው ለ6 ሳምንት የሚቆይ ሲኾን ቅዳሜ ፣እሑድ በጠዋት ፣ በከሰአትና በማታ ፈረቃ እንዲሁም እሮብ ማታ መከታተል ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ በ 0912664084 ይደውሉ፡፡
ያለን ቦታ ውስን ስለኾነ ቀድመው ይመዝገቡ፡፡
t.me/psychoet
አድራሻ:-4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሀን ንግድ ማዕከል ቢሮ 219 እና 221
ለመለወጥ መወሰን እንጂ ስበብ ማቅረብ አይጠቅምም!!!
Repost from ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷♂
ብዙ ሰዎች ህመማቸውን መከፋታቸውን የሚያወሩለት ወዳጅ አጥተው ሶሻል ሚዲያ ላይ ነው ሚገልፁት። እንዲህ አይነት ፖስቶችና መልእክቶች ስታዩ ረጋ ብላችሁ ምላሽ ስጡ። ቀልድ ነው ብላችሁ በምታላግጡበት ሰአት ያ ሰው ወደሞት እየቀረበ ይሆናል።
በተለይ በአፍላው እድሜ በሚገኙ ወጣቶች ዘንድ ራስን ማጥፋት በጣም እየጨመረ ነው።
እባካችሁ ራሴን ላጠፋ ነው ወይም መሮኛል ብሎ ለፖሰተ ሰው ብታቁትም ባታውቁትም አብሮነታችሁን ድጋፋችሁን አሳዩ እንጂ ቀልድ አትቀልዱ። ለቀልድና ጨዋታ ብዙ የተሻለ ቦታ አለ።
በቅርብ የምናቃቸው ሰዎች መሞታቸው ሲገለፅ የአብዛኛው ጓደኞቻቸው ምላሽ "እኔ መች ጠረጠርኩ... ደብሮኛል እያለኝ.. " ምናምንም በሚሉ ፀፀቶች የተሞላ ነው።
በዙርያችሁ ላለ ሠው ሁሉ ትኩረት ስጡ!
ራስን ማጥፋት የቀልድ ርእስ አይደለም!
©Tesfa G Neda
--------------------------------------------------------------
በዓመት እስከ 800,000 ሰዎች ራሳቸውን እንደሚያጠፉ የWHO ሪፖርት ያመለክታል፡ ከዚህ ቁጥር በላይ ያሉ ሰዎች ደግሞ ራሳቸውን የማጥፋት ሙከራ ያደርጋሉ ።
እድሜያቸው ከ 15 እስከ 29 ዓመት በሆኑ ወጣቶች ሁለተኛው ከፍተኛ ሞት የሚመዘገብበት ችግር ነው ፡ እንዲሁም 79% ያህሉ በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት ላይ የሚስተዋል ነው ። ሰዎች ራሳቸውን ለማጥፋት መርዝ መጠጣት መታነቅ ፣የጦር መሳሪያ መጠቀም፣ በዋናነት ይጠቀማሉ ።
አጋላጭ ሁኔታዎች
-----------------------------------------------------------------
የተለያዩ የአዕምሮ ህመሞች በተለይም ድባቴ (Depression) ከፍተኛ የአልኮል መጠጥ ችግር ፣ከባድ አካላዊ ህመም ፣ የኢኮኖሚ ቀውስ፣ ጭንቀት፣ ድንገተኛ ግጭትና ብቸኝነት ዋና ዋና በአጋላጭ ችግሮች ናቸው ። እንዲሁም ቀደም ባለ ጊዜ ያልተሳካ ራስን የማጥፋት ሙከራ ከነበረ ዋነኛ አጋላጭ ችግር ሊፈጥር ሊሆን ይችላል ።
መከላከያ መንገዶች
-----------------------------------------------------------------
ራስን የማጥፋት ችግር በሚገባ መከላከል ይቻላል
በተለይም ራስን ለማጥፋት የሚረዱ ምቹ ሁኔታዎችን መቀነስ፣ ተደጋጋሚ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችን በመገናኛ ብዙሃን በመስጠት፣ ትምህርት ቤቶችን መሰረት ያደረገ ማዕከል በማደራጀት ለመምህራን ለወላጆች እንዲሁም ለትምህርት ቤት ማህበረሰብ በቂ የቅድመ ጥንቃቄ መረጃና ትምህርት መስጠት እንዲሁም ለተማሪዎች የማማከር አገልግሎት ማመቻቸት፣ የአልኮል መጠጥ አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ፣ የአእምሮ ህመሞችን ቶሎ መለየትና በቂ ህክምና ማድረግ እንዲሁም ተገቢውን ክትትል ማድረግ፣በቂ የሱስ ማገገሚያ ማዕከላትን ማቋቋም።
================================
ማጣቀሻ ፡- WHO report
©ዮሴፍ ሳህለ
ባላችሁበት የቴሌግራም ግሩፖች #share አድርጉ @psychoet
#የስሜት_ብልሃትና_ተግባቦት
#Emotional_Intelligence& Communication
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ) #SHARE
ጥሩ የስሜት ብልሀት ያላቸው ሰዎች የተመሰገኑ ፣ በማንኛውም ሁኔታ የተረጋጉ ፣ የሩጫ ህይወት የማይመሩ ፣ የበለጠ ደስተኛና ራሳቸውንም ሆነ አካባቢያቸውን የሚመሩ ናቸው ፡፡
በህይወታቸው በጣም ደስተኛና ስኬታማ የሆኑ ሰዎች አንዱ መገለጫቸው ያለቸው የስሜት ብልሃት ( Emotional Intelligence ) ነው ፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት ሙያውና ችሎታው እያላቸው በባህሪ ምክንያት ይሰናበታሉ ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጥሩ ሀሳብ እያላቸው ባላቸው ባህሪና በተግባቦት እጥረት ምክኒያት ሰሚ ያጡ ፣ ተቀባይነት ያጡ ሰዎች ብዙ ናቸው ፡፡
#ለዛሬ እነዚህ የተግባቦትና የስሜት ብልሃት አለመኖር በሕይወታችን የሚያመጡትን ችግር እንመልከት ፡፡
እኔ አንዱን ድግሪዬን በማኔጅመንት ስሰራ የመመረቂያ ጽሑፌ (Competency development in business areas ) የሚል ነበር ፡፡ በዚህ ጥናት ያገኘሁት አንዱ ግኝት ሰዎች ለቢዝነሳቸው መውደቅና አለማደቅ አንዱና ዋና ምክንያት ያላቸው አነስተኛ #የተግባቦትና #የስሜት_ብልሃት ነው ፡፡
#የስሜት_ብልሃትና_ጥሩ_ተግባቦት_የሌላቸው_ሰዎች_መገለጫዎች
★የራሳቸውን ስሜት አይቆጣጠሩም ( በቀላሉ ይናደዳሉ ፣ ይበሳጫሉ ፣ ከልክ ያለፈ ቁጣ ይታይባቸዋል )
★ከሰው ጋር ተግባቢ አይደሉም ፣ ፍርሀት ጭንቀት ይታይባቸዋል ፣ ስለ ራሳቸው አሉታዊ አመለካከት የላቸውም
★በትንሽ ነገር አብዝተው ያዝናሉ
★በአካባቢያቸው ያሉ ሰዎችን ባህሪ እና ስሜት ስለማይረዱ ፣ ብዙ ጊዜ ከሰዎች ጋር በሀሳብ ፣ በወሬ የመጋጨት ሁኔታ ይታይባቸዋል
★ሰው ስለነሱ ስላለው አስተሳሰብ አብዝተው ይጨነቃሉ ፣ ይረበሻሉ ፡፡
★ሃሳባቸውን በድፍረት አይገልፁም ፣ እየተጎዱ ከጉዳቱ መውጣት እየቻሉ ዝምታን ይመርጣሉ ፣
★ለውሳኔዎች ከተገቢው በላይ ይቸኩላሉ፣ በወሰኑት ነገር ለመጸጸት ደግሞ የመጀመሪያ ናቸው
ከላይ የዘረዘርኳቸው መገለጫዎች( የስሜት ብልሃትና ጥሩ ተግባቦት ክህሎት አለመኖር) የሚያመጣቸው ጉዳቶችና የባህሪ መገለጫዎች ናቸው ።
በእርግጥ ተግባቦትም ሆነ የስሜት ብልህነት ሳይንሳዊ የሆኑ መንገዶችን በመጠቀም ማሳደግ ይቻላል ፡፡ ስለዚህ ከላይ የጠቀስኳቸውን ችግሮች በራሳችሁ ላይ የምታዩ ሰዎች ተስፋ አትቁረጡ ፡፡ በጥቂት ጊዜ ጥሩ የሆነ ተደጋጋሚ ተግባራዊ ልምምዶችን በማረግ መዉጣት ይቻላል ፡፡
___
#በዚህ ሳምንት መጨረሻ /ቅዳሜ መስከረም 21 እና እሑድ መስከረም 22 በሚጀምረው የሕይወት ክህሎት ስልጠና ላይ እነዚህን ጉዳዮች በስፋት የማነሳቸው ሲሆን በተጨማሪም በየቀኑ የሚሰሩ እነዚህን ክህሎት የሚያሳድጉ ልምምዶችን በተግባር እናያለን፡፡ ለመለወጥ የወሰናችሁ ሰዎች ካሉን ፈረቃዎች በተመቻችሁ መርጣችሁ +251912664084 በመደወል ተመዝገቡ የስልጠናው ሙሉ ማስታወቂያ ከዚህ በፊት ተለጥፏል ፡፡ የ 6 ሳምንት ስልጠናችንን ያልተመዘገባችሁ ባለን ጥቂት ቀሪ ቦታዎች ተመዝግባችሁ እንድትጀምሩ እናበረታታለን፡፡
ይህ ፅሁፍ ለሌሎችም እንዲደርስና ስልጠናው የሚያስፈልጋቸው እንዲያገኙት ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛
@PSYCHOET
照片不可用在 Telegram 中显示
እንኳን ደስ አለን!
የ11 ዙር የሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት ስልጠና ሊጀምር ነው!
ስለ ሳይኮሎጂ ለማወቅ ለሚፈልጉ እንዲሁም የሕይወት ክህሎት ስልጠና መሠልጠን ለሚፈልጉ መልካም አጋጣሚ ልምድ ባላቸው የሕይወት ክህሎት አሰልጣኞች።
📖ሳይኮሎጂ/ሥነልቦና ምንድነው?
📖ለሕይወታችን ምን ይፈይደል?
📖የሥነልቡና ቀውስ ምንድነው? እንዴትስ ያጋጥማል? መፍትሄዋቹስ ምንድናቸው?
📖Counseling ምንድነው?
🔖የሕይወት አላማን መረዳትና ራስን ማግኘት
🔖የ2015 ስኬታማ ዕቅድ አወጣጥና የጊዜ አጠቃቀም
🔖የስሜት ብልህነት
🔖ፍርሀትና ጭንቀትን ተቋቁሞ መውጣት
🔖ተግባቦትና በራስ መተማመን
ለሰልጣኞቻችን የግል የማማከር አገልግሎት እናመቻቻለን!
ስልጠናው ለ6 ሳምንት የሚቆይ ሲኾን ቅዳሜ ፣እሑድ በጠዋት ፣ በከሰአትና በማታ ፈረቃ እንዲሁም እሮብ ማታ መከታተል ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ በ 0912664084 ይደውሉ፡፡
ያለን ቦታ ውስን ስለኾነ ቀድመው ይመዝገቡ፡፡
t.me/psychoet
አድራሻ:-4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሀን ንግድ ማዕከል ቢሮ 219 እና 221
ለመለወጥ መወሰን እንጂ ስበብ ማቅረብ አይጠቅምም!!!
