Addis Ababa Education Bureau
Open in Telegram
ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡
Show more2025 year in numbers

150 232
Subscribers
No data24 hours
+677 days
+34630 days
Posts Archive
Guyyaa Bayyanannaa!
Misooma Waaraa, Bayyanannaa Biyyaalessaatiif!
Itoophiyaan kaateetti. Kana booda duubatti hin deebitu. Imalli bayyanannashee kun misooma dinagdee waaraatiin kan deeggarame ta'uu qaba. Keessumaa dameewwan albuudaa, tuuriizimii, qonnaa, homishtummaafi 'ICT' dhaan bu'aawwan olaanaa galmeessisaa ittifufuu qabna. Qabeenyaa guddina keenyaaf gargaaraa ta'u uumuufi galii walitti qabuutu nuuf mala. Galiifi qabeenya guddinni keenya maddisiisu haalaan walitti qabnee, qusannee galma badhaadhina keenyaatiif fayyadamuu qabna. Jijjiirama dinagdee maakroo eegalle si'oomsuudhaan milkeessinee bayyanannaan Itoophiyaa gara badhaadhina waaraa Itoophiyaatti akka jijjiiramu ni taasifna.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
❤ 24
Photo unavailableShow in Telegram
የማንሠራራት ቀን!
ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሠራራት
(ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም) ኢትዮጵያ ተነሥታለች፡፡ ከእንግዲህ ወደኋላ አትመለስም፡፡ ይሄ የማንሠራራት ጉዞዋ በዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የታገዘ መሆን አለበት፡፡ በተለይም በማዕድን፣ በቱሪዝም፣ በግብርና፣ በአምራችነት እና በአይሲቲ ዘርፎች የላቁ ውጤቶችን እያስመዘገብን መቀጠል አለብን፡፡ ለዕድገታችን አጋዥ የሚሆን ሀብት መፍጠር እና ገቢ መሰብሰብ ይገባናል፡፡ ዕድገታችን የሚያመነጨውን ገቢና ሀብትም በሚገባ ሰብስበንና ቆጥበን ለብልጽግና ግባችን መጠቀም አለብን፡፡ የጀመርነውን የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም በማሣለጥና በማሳካት የኢትዮጵያ ማንሠራራት ወደ ዘላቂ የኢትዮጵያ ብልጽግና እንዲለወጥ እናደርጋለን፡፡
❤ 32👍 6👏 1
የድሮን ትርዒት በጉባ ሰማይ ስር
(ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም)
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 68🔥 12👏 7👎 3😁 3
ፕሮጀክቱ በትምህርት ቤቶች እየሰራን ያለውን የከተማ ግብርና ሥራ ላቅ ባለ ቴክኖሎጂ ለማሳደግ የራሱ በጎ ተፅእኖ ያደርጋል ያሉት ቢሮ ኃላፊው ልምዱን ከፍ በማድረግና በሌሎች ትምህርት ቤቶች በማስፋት ተቋማዊ አሰራር ስርዓት ውስጥ በማስገባት እውቀትን ለማሻገር የሚያስችል ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል::
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ምስክር ነጋሽ በበኩላቸው የከተማ ግብርናን በትምህርት ቤቶች ማካሄድ ምግቤን ከጓሮዬ በሚል መርህ እየተሰራ ያለውን ሥራ ከመደገፉ ባሻገር በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ የመማር ማስተማር ሥራ በተግባር ለማገዝና የተመጣጠነ የምግብ ስርዓት ለማስፈን ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል::
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ሌኮ ዳልቻ አዲስ አበባን ከሸማችነት ወደ አምራችነት ለማሻገር የከተማ ግብርና ስራዎችን በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን ጠቁመው በተለይ በትምህርት ቤቶች ያሉ ክፍት ቦታዎች የምርት ቦታ ለማድረግ ያስቻለ ከፍ ሲልም ውሀና አፈር ውስጥ ያሉ ሚነራሎችችን ብቻ በመጠቀም በትንሽ ቦታ ከፍተኛ የግብርና ስራን መስራት ያስቻለ ፕሮጀክት መሆኑን ተናግረዋል::
በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ በከተማ ግብርና ስራው አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላትም እውቅና ተሰጥቷል::
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 65👍 7😁 4
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ከክፍለ ከተማው ግብርና ፅ/ቤት ጋር በመተባበር የሰራውን የከተማ ግብርና ሰርቶ ማሳያ ፕሮጀክት አስመረቀ::
(ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም) የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ከክፍለ ከተማው ግብርና ፅ/ቤት እና ኢትዮሊፕ አግሮ ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር በአብዮት ቅርስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያዘጋጀውን የከተማ ግብርና ሰርቶ ማሳያ (Hydroponic) ፕሮጀክት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ምስክር ነጋሽ ፣ የከተማ ግብርና ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ሌ ሌኮ ዳልቻ እንዲሁም የአዲስ አበባ ምክር ቤት ንግድ ኢንዱስትሪና ቱሪዝም ቋ/ኮ /ሰብሳቢ አቶ ጋትዎች ውር ፣ የክፍለ ከተማው ት/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሰማህኝ አስታጥቄ በተገኙበት አስመርቋል ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ መርሃ ግብሩ ባስተላለፉት መልእክት የከተማ ግብርና ሥራ በከተማውን የምግብ ስርዓት ውስጥ ከፍተኛ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመው የከተማ ግብርና ሥራ በስርዓተ ትምህርት ውስጥ እውቀትና ክህሎትን የምናዳብርበት አንዱ ዘዴ ነው ብለዋል ::
❤ 41🥰 3
የቢሮው የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ባለሙያ አቶ ጌታቸው በላይነህ በበኩላቸው ስራ ክፍሉ በየመማሪያ ጣቢያው በመገኘት በበጋው መርሀግብርም ሆነ በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የጎልማሶች ትምህርት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ባደረገው ተደጋጋሚ ድጋፍና ክትትል ጎልማሶቹ ትምህርቱን በአግባቡ በመከታተል ላይ መሆናቸውን ማረጋገጡን ጠቅሰው የዛሬው ውይይት በ2017 ዓ.ም የነበሩ አፈጻጸሞችን በመገምገም ለ2018 ዓ.ም ምዝገባ ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን አስታውቀዋል።
በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ጎልማሶች እስከ መስከረም 30/2018 ዓ.ም ተምረው ትምህርቱ ሲጠናቀቅ የብርሀን ምዘና ወስደው 50% እና በላይ የሚያስመዘግቡት እንደፍላጎታቸው በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች በተለያዩ የሙያ መስኮች ስልጠና የሚወስዱበት እና 3ኛ ክፍል ገብተው መደበኛ ትምህርት የሚከታተሉበት አማራጭ መዘጋጀቱን የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ባለሙያ አቶ አበበ ዘነበ ገልጸው የክረምት ትምህርቱን በመስጠት ላይ ለሚገኙ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች እና ሂደቱን በመደገፍ ላይ ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 30👍 5
የልዩ ፍላጎት እና የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት በ2017 ዓ.ም በበጋው እና በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት የተከናወኑ ተግባራትን ገመገመ።
(ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም) በመርሀግብሩ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የዘርፈ ብዙ ጉዳይ ቡድን መሪዎች እና የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በየክፍለ ከተማው በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት በቡድን መሪዎች ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎት እና የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ፍቃዱ ቢሮው በ2017 ዓ.ም የበጀት አመት በበጋውም ሆነ በክረምት የበጎ ፍቃድ ንቅናቄ ጎልማሶችን በትምህርት አገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸው በበጀት አመቱ በበጋው መርሀግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁት ጎልማሶች የብርሀን ምዘና መውሰዳቸውን እና 50% እና በላይ ያስመዘገቡት በ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት 3ኛ ክፍል ገብተው መደበኛ ትምህርታቸውን የሚከታተሉበት እና በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች በአምስት የሙያ መስኮች የአጭር ጊዜ የሙያ ስልጠና የሚወስዱበት አማራጭ መዘጋጀቱን አመላክተዋል።
ዳይሬክተሩ አያይዘውም በ2017 ዓ.ም የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት 9,536 ጎልማሶች ተመዝግበው 86% ያህሉ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው ትምህርቱ እስከ መስከረም 30/2018 ዓ.ም የሚሰጥ በመሆኑ የክፍለከተማ ቡድን መሪዎች እና የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ባለሙያዎች በየጣቢያው ተገኝተው አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ ትምህርቱ ውጤታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
❤ 23
ጳጉሜ 3
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ
(ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጳጉሜ ሶስትን እመርታ ለዘላቂ ከፍታ በሚል መሪ ሀሳብ በጎቤና ሽኖዬ ባህላዊ ጭፈራ በድምቀት አክብራል።
እንኳን አደረሰን! አደረሳችሁ!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 48👍 9👏 4
የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡
(ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በዛሬው እለት የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የግብዓት አቅርቦት ባለሙያ የሆኑት አቶ አሸናፊ ደጀኔ የትምህርት ግብዓት አቅርቦት ሚና ለውጤታማ መማር ማስተማር ሂደት በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ሰነዱ መቅረቡ የከተማ አስተዳደሩ ለመማር መስተማር ስራዉ ትኩረት በመስጠት እያከናወናቸው ከሚገኙ ተግባራት መካከል አንዱ በመሆኑን ለማስገንዘብ ያግዛ በማለት የትምህርት ልማት ስራ ውጤታማ እንዲሆን የትምህርት በግብዓት አቅርቦትና የተሳለጠ ሂደት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው በዚህ ሂደት ውስጥ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ በመማር ማስተማር ስራዉ ላይ እያመጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 34👏 4
Photo unavailableShow in Telegram
የእመርታ ቀን
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ
(ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም) የወረስነው ዕዳ ብዙ፤ የምንጓዝበት መንገድ ረዥም፤ ሕዝባችንም ፍላጎት ሰፊ ነው፡፡ ቀስ በቀስ በሚደረግ የተለምዶ ጉዞ ወደምንፈልገው የብልጽግና ምእራፍ አንደርስም፡፡ ያለን አማራጭ አንዳንድ እርከኖችን መዝለል ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ፈጠራና ፍጥነት ወሳኞች ናቸው፡፡ ከተለመደው መንገድ ወጣ ማለት፣ ከተለመደው ጊዜ በላይ መሥራት፣ ከተለመደው ዋጋ በላይ መክፈል ያስፈልገናል፡፡ ዓላማችን ከአንድ ምዕራፍ ወደ ሌላ ምዕራፍ መሻገር አይደለም፡፡ ከትናንት ዘለን ወደ ነገ መድረስ ነው፡፡
Guyyaa Tarkaanfannaa
Tarkaanfannaan Olka'insa Waaraaf
Idaan dhaalle baay'ee, daandiin irra imallu dheeraa, fedhiin uummata keenyaas bal'aadha. Imala suutaa barame sanaan boqonnaa badhaadhinaa barbaadnu bira hin geenyu. Filannoon qabnu gulantaawwan tokko tokko utaaluudha. Kanaaf ammoo kalaqniifi saffisni murteessitootadha. Daandii baramerraa bahuu, yeroo baramee ol hojjechuu, gatii baramee ol kanfaluu nubarbaachisa. Kaayyoon keenya boqonnaa tokkorraa gara boqonnaa kanbiraatti cehuu miti. Kaleessarraa utaallee gara borii gahuudha.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 90👍 15👎 8🥰 5👏 4🔥 1
መስታወቂያ! Beeksisa!
(ጳጉሜ 2/2017 ዓ.ም)
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 147👍 37👎 21🔥 16🤔 12😁 9👏 5🥱 2
በትምህርትና ክህሎት የበቃ ትውልድ ለመፍጠር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን የክፍለ ከተማው አስተዳደር ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልፀው ለዚህ ደግሞ የሁሉም አካላት ትብብር አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረው ክፍለ ከተማው ውጤታማ እንዲሆን ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ በበኩላቸው ትምህርት ትውልድን በማፍራት መጪውን ትውልድ ብሩህ ለማድረግ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል።
ትውልድን የምናንፀው ሁሉም አካላት እገዛ ሲኖር እንደሆነና ይህም በትምህርትና ክህሎት የበቃ ትውልድ ለመፍጠር ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል። አያይዘውም ጉባኤው ልዩ የሚያደርገው የህዳሴ ግድቡ የሚመረቅበት ዋዜማና በአዲስ አመት መባቻ ላይ መከናወኑ ብሎም በከተማ ደረጃ ክፍለ ከተማው በኬፒያይና በአገልግሎት አሰጣጥ ተመዝኖ አንደኛ ደረጃ ወጥቶ ተሸላሚ መሆኑ ፤ በክፍለ ከተማው የሚገኘው ጀነራል ታደሰ ብሩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላለፉት 5 ዓመታት የላቀ ውጤት በማስመዝገብ በከተማ ደረጃ እውቅና ያገኘ መሆኑን ተናግረዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራ በክፍለ ከተማው የሚሰጠውን ትምህርት ውጤታማ ለማድረግ በ2017 የትምህርት ዘመን በትኩረት መሰራቱን ገልፀው በዚህም በክፍለ ከተማው የትምህርት ሽፋን ተደራሽነት ላይ በተሰራው ስራ ውጤት መመዝገቡንም ገልፀዋል።
በ154 ትምህርት ቤቶች ላይ 92885 ተማሪዎች ትምህርት እንዳገኙ መደረጉን የገለፁት አቶ ሚሊዮን ከአዋኪ ጉዳዮች የፀዳ ምቹ የመማሪያ አካባቢ ለመፍጠር እዲቻል በተሰሩ ስራዎች ላቅ ያለ ለውጥ መመዝገቡንና በዚህም በተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ በከተማ ደረጃ አንደኛ በመያዝ ክፍለ ከተማ ት/ፅ/ቤቱ በማጠናቀቁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
በጉባኤው የክፍለ ከተማው ትምህርት ፅህፈት ቤት የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀምና የተማሪዎች ውጤት ትንተናና የ2018 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ የቀረበ ሲሆን በአመቱ የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አካላት እውቅና ተሰጥቷል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 48
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት 32ኛውን የትምህርት ጉባኤ “በዕውቀት እና ክህሎት የበቃ ትውልድ በማፍራት ኢትዮጵያን የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋታለን!” በሚል መሪ ሀሳብ በዛሬው እለት አካሂዷል፡፡
(ጳጉሜ 2/2017 ዓ.ም) በትምህርት ጉባኤው የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ፣ የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራን ፣ የክፍለ ከተማው ምክር ቤት አመራሮችና አባላት ፣ የተማሪ ወላጅ ህብረት አመራሮችን ጨምሮ የየትምህርት አመራሮች ፣ መምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በጉባኤው ተሳትፈዋል፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የትምህርት በአዕንሮ የበለፀገ ትውልድን ለማፍራት ሚና እንዳለው ገልፀው ጥራት ያለው ትምህርት በመስጠት ትውልድን ለማፍራት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡
❤ 41
ጳጉሜ 2
የህብር ቀን!!
ዛሬ በህብር ቀን ለ500 ሺህ የከተማችን ነዋሪዎችን ማዕድ አጋርተናል።
በክረምቱ ወራትም ምንም ጧሪ፣ ደጋፊ የሌላቸው አቅመ ደካምችን፤ የአገር ባለውለታዎችን እና በዝቀተኛ ገቢ የሚተዳደሩ 156 ሺህ ያህል የህብረተስብ ክፍሎችን ስንደግፍ ቆይተናል።
ወገኖቻችን በጊዜያዊ ችግሮች እንዳይጎዱ በተለያዩ መልኩ ለመደገፍ እየሰራን በዘላቂነት ከድህነት ለመውጣት 24/7 ዘላቂ የልማት ሥራዎችን እየሰራን እንገኛለን።
በመደጋገፍ ፤ በመረዳዳት ለማህበራዊ ችግር ተጋላጮች የምናደርገውን ድጋፍ ማጠናከር ይገባናል። ሁልጊዜ ከጎናችን ሆናችሁ ካላችሁ ለምታካፍሉ፣ ለመስጠት ለማትሳሱ ባለሀብቶች፣ ለከተማችን ወጣቶች ድጋፍ በተደረገላቸው ወገኖቻችን ስሞ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ
❤ 68👎 6👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
የኅብር ቀን
ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ
ኢትዮጵያ በብዙ ጸጋዎች የተሞላች ሀገር ናት፡፡ እነዚህ ጸጋዎቿ የተለያዩ ሳይሆኑ ልዩ ልዩ ናቸው፡፡ የባህል፣ የቋንቋ፣ የታሪክ፣ የሥልጣኔ፣ የእምነት፣ የጾታ፣ የአመለካከት፣ ወዘተ. ብዝኃነት ያለንን የጸጋ ብዛት የሚያመለክት ነው፡፡ ብዝኃነት የኢትዮጵያ ታሪኳ እና መልኳ ነው፡፡
Guyyaa Daneessummaa
Daneessummaa, Faaya Itoophiyaa
Itoophiyaan biyya kennaawwan hedduudhaan guutamtedha. Kennaawwanshee kunneen kan gargar bahan utuu hin ta'iin adda addadha. Daneessummaan aadaa, afaanii, seenaa, qaroominaa, amantaa, saalaa, ilaalchaa kkf. heddumina kennaa qabnu kan agarsiisanidha. Daneessummaan Itoophiyaadhaaf seenaafi bifa isheeti.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
❤ 73👍 14👎 8😁 1🥱 1
የተማሪዎችን ሥነ ምግባር በተመለከተም ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በየትኛውም ክልልና የከተማ አስተዳደር የሚገኝ ተማሪ ተንቀሳቃሽ ስልክ ፣ ታብሌትና ማናቸውንም የትምህርት ስራ ላይ ተጽእኖ ሚያሳድሩና አዋኪ የሆኑ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን ይዞ መገኘት ክልክል መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ አስገንዝበዋል፡፡
በበይነ መረብ በተካሄደው ምክክር የትምህርት ጥራትና ፕሮግራሞች መሻሻል መሪ ስራ አስፈጻሚ ዩሀንስ ወጋሶ (ዶ/ ር) የ2018 የትምህርት ዘመን የትምህርት ቤቶችን አከፋፈት ጋር ተያይዞ የባለድርሻ አካላት ሚና ፣የትምህርት ቤቶች ዝግጅት፣ ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ የትምህርት አካባቢ በመፍጠር፣ በትምህርት ለትውልድና በሌሎችም ዙሪያ ስትራቴጂክ እቅድ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በምክክር መድረኩ የተሳተፉ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችና ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች በበኩላቸው ለ2018 የትምህርት ዘመን አከፋፈት ፣በተማሪዎች ምዝገባ ፣ በትምህርት አጀማመር፣ በመማር ማስተማር ስራውና በተማሪዎች ስነ ምገባር ዙሪያ አፈጻጸሞቻቸውን አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 79👍 38🥱 6💩 4😢 3🔥 2
