68 961
Subscribers
No data24 hours
-137 days
-96730 days
Posts Archive
የአቶሚክ ልማድ አስደናቂ ሀይል
ውጤቶችህ የልማዶችህ ቀሪ መለኪያዎች ናቸው፡፡ ያለህ ገንዘብ የፋይናንስ አጠቃቀምህ ውጤት ነው፤ እውቀትህም የመማር ልማድህ ቀሪ መለኪያ ነው።
በሕይወትህ ውስጥ ያሉት ምስቅልቅሎችም ነገሮችን የማጽዳት ልማዶችህ ድምር ውጤቶች ነው።የምታገኘው የምትደጋግመውን ነው፡፡
የሕይወትህን መዳረሻ ለመገመት ከፈለግህ ማድረግ ያለብህ ነገር ቢኖር የምታገኛቸውንና የምታጣቸውን ጥቃቅን ለውጦች ተከትለህ ማየትና ይህ የለውጥ መስመር በሃያ - በሰላሳ ዓመታት የት እንደሚያደርስህ መረዳት ነው፡፡ የወር ወጪህ ከገቢህ ያነሰ ነው? በየሳምንቱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ትሰራለህ? በየቀኑ አዳዲስ ነገሮችን ታውቃለህ? መጽሐፍ
በጥቂቱም ቢሆን ታነባለህ? የወደፊት ሕይወትህን ሙሉ የሚወስኑት እንደነዚህ ያሉ ጥቃቅን የጦር ግንባሮች ናቸው፡፡
በሙሉ ጊዜ በውድቀትና በስኬት መካከል ያለውን ልዩነት ያሰላል፡፡ ጊዜ የሚያደርገው ነገር ቢኖር የምትሰጠውን ነገር ማባዛት ነው፡፡ ጥሩ ልማዶች ጊዜን አጋርህ ሲያደርጉት፣ መጥፎ ልማዶች ግን ጠላትህ ያደርጉታል፡፡
ልማዶች በሁለቱም በኩል የተሳሉ ሰይፎች ናቸው፡፡ መልካም ልማዶች ሊስሉህና ሊያሳድጉህ የሚችሉትን ያህል መጥፎ ልማዶች ደግሞ ቆራርጠው ሊጥሉህ የሚችሉበት እድል በዚያው መጠን ነው፡፡
ለዚህም ነው ዝርዝሩን መረዳት ጠቃሚ የሚሆነው፡፡ ልማዶች እንዴት እንደሚሰሩና እንዴት ወደ ውጤት እንዲወስዱህ ማድረግ እንደምትችል መማር አለብህ፡፡ በዚህ መንገድ የሰይፉን ቆራጭ ስለት የማስወገድ እድል ታገኛለህ፡፡
ብዙውን ጊዜ ሁኔታ ቀያሪ ቅጽበቶች ቀደም ብለው የተሰሩ የብዙ ተግባራት ድምር ውጤቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ተደራራቢ ቅድመ ተግባራት ዋናውን ለውጥ ለማምጣት የሚያስፈልገውን አቅም ይገነባሉ፡፡ ይህ ሁኔታ በሁሉም ቦታዎች የሚታይ ነገር ነው፡፡ ካንሰር የሕይወት ዘመኑን 80 በመቶ የሚያሳልፈው የማይታይ ሆኖ ነው፡፡ ከዚያ የሰውነትን አካል የሚቆጣጠረው ግን በወራት ውስጥ ነው፡፡ ሸምበቆም መሬት ለመሬት ስሮቹን በሚዘረጋባቸው አምስት ዓመታት ውስጥ ብዙም አይታይም፡፡ ከዚያ ነው በስድስት ሳምንታት ውስጥ በአየር ላይ እስከ 90 ጫማ ድረስ ማደግ የሚችለው፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ ልማዶችም የሆነ ወሳኝ ምዕራፍን አልፈን አዲስ ሁኔታ ውስጥ ገብተን እስክንገኝ ድረስ ምንም ለውጥ የሚፈጥሩ አይመስሉንም፡፡ በየትኛውም ሁኔታ መጀመሪያ እና መካከለኛ ዘመን ውስጥ ብዙውን ጊዜ የመከፋት ሸለቆ ይኖራል፡፡ ለውጥ ለማምጣት ስትነሳ የእድገት ደረጃዎችህን በማይቆራረጥ እና ወጥ በሆነ መልኩ ማየት እንደምትችል
ታስባለህ፡፡ ግን አታይም፡፡ በመጀመሪያዎቹ ቀናት፣ ሳምንታትና ምናልባትም ወራት አካባቢ ለውጥ የማይመጣ መስሎ መታየቱ በጣም የሚያበሳጭ ነው፡፡ የትም የምትሄድ መስሎ አይሰማህም፡፡ ይህ የየትኛውም የድርርቦሽ ድል መገለጫ ባህሪ ነው - ሁልጊዜም ትላልቅ ውጤቶች የሚመጡት ዘግይተው ነው፡፡
ዘላቂነት ያላቸውን ልማዶች መገንባትን ከባድ ከሚያደርጉት መሰረታዊ ምክንያቶች መካከል አንደኛው ይህ ነው፡፡ ሰዎች ትናንሽ ለውጦችን ለማምጣት ይሞክሩና ውጤቱ ግን አልታይ ይላቸዋል፡፡ ከዚያም ለማቆም ይወስናሉ። “ለአንድ ወር ያህል በየቀኑ እሮጥኩ፤ እና ለምንድነው ሰውነቴ ላይ ለውጥ ያላየሁት?” ብለህ ልታስብ ትችላለህ፡፡ እንደዚህ አይነት አስተሳሰብ አንድ ጊዜ ከተቆጣጠረህ ጥሩ ልማዶችን እየተውክ ለመሄድ ትመቻቻለህ። ትርጉም ያለው ለውጥ ለማሳየት ግን ልማዶችን ለረዥም ጊዜ ማቆየትና ጉብታውን ለማለፍ የሚያስችላቸው አቅም ማጠራቀም አለባቸው፡፡ እኔም የተዳፈነ ችሎታ ጉብታ (The plateau of atent potential) የምለው ይሄንን ነው፡፡
ጥሩ ልማድ ለመገንባት ወይም መጥፎ ልማድ ለመተው ስትታገል ራስህን ብታገኘው የመሻሻል አቅም አጥተህ እንዳይመስልህ፡፡ ይልቁንም እንደዚህ የሚሆነው ገና የተዳፈነው ችሎታህን ጉብታ ስላለፍክ ብቻ ነው፡፡ “ጠንክሬ ብሰራም ውጤት አላመጣሁም አይነት አቤቱታ “በረዶው ለምን በ26፣ በ27 ወይ በ28 ዲግሪ አልቀለጠም?” ብሎ ቅሬታ እንደማቅረብ ያለ ነው፡፡ ድካምህ አልባከነም፣ እየተጠራቀመ ነው እንጂ፡፡ ሁሉም ድካሞችህ ተደማምረው 32 ዲግሪ ላይ ውጤት ማሳየት ይጀምራሉና፡፡
በስተመጨረሻ የእምቅ ችሎታ ጉብታህን ስታልፍ ሰዎች ስኬትህን የአንድ ቀን ስኬት ብለው ይጠሩታል፡፡ የውጪው ዓለም ሁሉንም የለውጥ ደረጃዎችህን አያይም፡፡ ሰዎች ማየት የሚችሉት ድራማዊ የሆነውን የለውጡን ፍሬ መገለጫ ብቻ ነው፡፡ አንተ ግን ለዚህ ያበቁህ ምንም ለውጥ እያሳየህ በማይመስል ሰዓት ሁሉ የሰራሀቸው ጠንካራ ስራዎች መሆናቸውን ታውቃለህ፡፡
ሁሉም ትላልቅ ነገሮች የሚነሱት ከትናንሽ ጅማሮዎች ነው፡፡ የእያንዳንዷ ልማድ ዘር አንዲት ትንሽ ውሳኔ ነች፡፡ ይህች ውሳኔ ስትደጋገም ግን ልማድ እያደገና እየጠነከረ ይሄዳል፡ ስሮቿ እየተስፋፉ ይሄዱና ቅርንጫፍ ማውጣትም ትጀምራለች፡፡
የእምቅ ችሎታ ጉብታን አልፎ ለመሄድና በሌላው ጎን ለመገኘት የሚያስችለንን የጥንካሬ ትግል ቆይታ የሚወስነው ምንድን ነው? አንዳንድ ሰዎች የመልካም ልማድን ድርርቦሽ ትርፍ ሲያጣጥሙ አንዳንዶች ግን የመጥፎ ልማዶቻቸው ምርኮኛ ሆነው የሚቀሩትስ ለምንድን ነው?
ይቀጥላል
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
👍 5
ትናንሽ ልማዶች ትልቅ ልዩነት ይፈጥራሉ።
የአንድን ወሳኝ ቅጽበት ሚና ከፍ አድርጎ ማየትና በየቀኑ የሚደረጉ የጥቃቅን መሻሻሎችን ሚና ዝቅ አድርጎ ማየት ይቀለናል ፡፡ ብዙውን ጊዜ ትልቅ ስኬት ትልቅ አድርገን ራሳችንን ተግባርን እንደሚፈልግ እናሳምነዋለን፡፡ ክብደት መቀነስም ይሁን ትልቅ ቢዝነስን መገንባት፣ መጽሐፍ መፃፍም ይሁን ውድድርን ማሸነፍ ወይም የትኛውንም ሌላ ግብ ለማሳካት ሁሉም ሰው የሚያወራለት አይነት መሬት የሚያንቀጠቅጥ ትልቅ ነገርን መስራት እንዳለብን በማመን ራሳችንን እናጨናንቃለን፡፡
ጥቃቅን ነገሮችን በአንድ በመቶ ማሻሻል ግን የማንመኘው ለእይታም የማይገባ ነገር ነው፡፡ ይሄኛው አይነት የመሻሻል መንገድ ግን ከፍተኛ ውጤት የማምጣት አቅም አለው - በተለይ በረዥም ጊዜ፡፡ ትንሽ ለውጥ በጊዜ ሂደት የምታመጣው ልዩነት አስደናቂ ነው፡፡ ሂሳባዊ ስሌቱ
ይሄን ይመስላል፡፡ ለአንድ ዓመት ሙሉ በቀን 1 በመቶ እያሻሻልን ብንሄድ በአመቱ መጨረሻ መጀመሪያ ከነበርንበት በ37 በመቶ እንሻሻላለን፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በቀን በአንድ በመቶ ወደታች እየሄድን ለአንድ ዓመት ከቆየን ወደ ዜሮ አካባቢ እንደርሳለን፡፡ በጥቂት ጅማሮ የተጀመረች ቀጣይነት ያላት ትንሽ መሻሻል ተጠራቅማ ታሪክ ትሰራለች፡፡
ልማዶች ራስን የማሻሻል ድርብርብ ድርብርብ ወለዶች (compound interests) ናቸው፡፡ በድርብርብ ወለድ ራሱን በሚያበዛበት ልክ ገንዘብ
መጠን የልማዶች ውጤትም በደጋገምናቸው መጠን ይባዛል። በየቀኑ ተነጥለው ሲታዩ የሚፈጥሩት ለውጥ በጣም ጥቂት መስሎ ቢታይም በወራት ወይም በዓመታት ቆይታ የሚያመጡት ለውጥ ግን አስደናቂ ነው፡፡ የመልካም ልማዶች ጠቀሜታዎች እና የመጥፎ ልማዶች ጉዳቶች ግልጽ ብለው የሚታዩት ከአምስት ወይም ከአስር ዓመታት በኋላ ወደኋላ ዞር ብለን ስንመለከታቸው መሆኑን ልብ ይሏል፡፡
ይህንን ነገር በየቀኑ ሕይወታችን አንጥረን ለማየት ከባድ ነገር ሊሆን ይችላል። በዚህም የተነሳ እነዚህን አይነት ለውጦች መተውና መናቅ ይቀናናል፡፡ ዛሬ ላይ ጥቂት ገንዘብ መቆጠብ ብትችል አሁኑኑም ሚሊየነር አትሆንም፡፡ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ጂም ብትሰራ በአካል ቅርፅህ ላይ ምንም ለውጥ አታይም፡፡ ዛሬ ምሽት ፈረንሳይኛ ቋንቋን ለሶስት ሰዓታት ብታጠና የቋንቋው ተናጋሪ አትሆንም፡፡ ጥቃቅን ለውጦችን ለማምጣት እንሞክራለን፡፡ የለውጡን ውጤት ቶሎ ማየት ስለማንችል ግን ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለሳለን፡፡
መጥፎው ነገር ደግሞ ይህ የለውጡ ውጤት የሚታይበት ፍጥነት እጅግ ዘገምተኛ መሆን ለመጥፎ ልማዶች እንድንመቻች የሚያደርገን መሆኑ ነው፡፡ ዛሬ ምሽት ቤተሰቦችህን ተወት አድርገህ ስራ ላይ ብታሳልፍ ይረዱሃል፡፡ ሥራህን የምትጨርስበት ሰዓት ለነገ ብለህ ብታሳድረው ለዚህ የሚሆን ጊዜ “ነገ ላይ አይጠፋም፡፡ በዚህ መንገድ አንዲትን ውሳኔ መተው ብዙም ከባድ ነገር አይደለም፡፡
መጥፎ ውሳኔዎችን በየቀኑ ችግሮቻችንን በ1% እያባባስን፣ እየደጋገምን፣ ትንንሽ ስህተቶችን እየሰራን እና ጥቃቅን ምክንያቶችን እያበጀን ከሄድን ግን ድምር ውጤታቸው እጅግ የገዘፈ እና የከፋ ይሆናል፡፡ ችግር የሚዳርጉንም እዚህም እዚያም የምንስራቸው ችግሮቻችንን በ1% የማባባስ ስራዎቻችን ድምር ውጤቶች ናቸው
በልማዶቻችን ላይ በምናመጣቸው ጥቃቅን ለውጦች የምናመጣው ጠቅላላ . ውጤት የአውሮፕላንን የበረራ መስመር በጣም በትንሽ ዲግሪ በመቀየር እንደሚመጣው ለውጥ ያለ ለውጥ ነው፡፡ ለምሳሌ ከሎስ አንጀለስ ወደ ኒው ዮርክ እየበረርክ ነው እንበል፡፡ ከላክስ አየር ማረፊያ የተነሳውን
አውሮፕላን ፓይለቱ በ 3.5 ዲግሪ ወደ ደቡብ ቢቀይረው መዳረሻህ የሚሆነው ኒው ዮርክ ሳይሆን ዋሽንግተን ዲሲ ነው፡፡ እንዲህ አይነት ትንሽ ለውጥ ስትነሳ አካባቢ አይታወቅህም፡፡ የአውሮፕላኑ አፍንጫም አቅጣጫውን የሚቀይረው በጣም በትንሽ ጫማዎች ናቸው፡፡ ጉዞው መላው አሜሪካን ሲያካልል ግን መዳረሻህ መጀመሪያ ካሰብከው ቦታ በመቶዎች በሚቆጠሩ ማይሎች ርቀት ላይ ይሆናል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ በየቀኑ በልማዳችን ላይ የምናሳያቸው ጥቃቅን ለውጦች ሕይወታችንን ፍፁም የተለየ መዳረሻ ይስጡታል። በ1% የተሻለ ወይም በ1% የወረደ ውሳኔን መስጠት ትርጉም ሊኖረው የሚችል ለውጥ አይመስለንም፡፡ በጊዜ ሂደት ግን አሁን አንተ በሆንከው እና አንተ ትሆን በነበረው ማንነት መካከል ያለውን ልዩነት የሚፈጥሩት እነዚህ ጥቃቅን ልዩነቶች ናቸው፡፡ ስኬት የ በየቀኑ ልማዶች ድምር ውጤት ነው፡፡ ወሳኙ ነገር ልማዶችህ ወደ ስኬት የሚወስዱህ ናቸው ወይስ አይደሉም? የሚለው ነው፡፡
ስለሆነም አብዝተህ መጨነቅ ያለብህ ዛሬ ላይ ስላመጣኸው ውጤት ሳይሆን የዛሬው ጉዞህ አቅጣጫ ላይ ነው፡፡ የወጪ አወጣጥ ልማድህ ካልተቀየረ ጥሩ ነገር አትጠብቅ፡፡ በተቃራኒው ዛሬ ላይ ደሃ ብትሆንም ሽርፍራፊ ሳንቲሞችን የምትቆጥብ ከሆነ ግን ወደ የፋይናንስ ነፃነት የሚወስደው መንገድ ላይ ነህ - ከምታስበው በላይ በዝግታ ብትጓዝም፡፡
@Human_Intelligence
👍 6👏 2🙏 1
ይቀመጣል እንደ አደራ
ሰው ክፉም ሰራ
ደግም ሰራ
ሁሉም የእጁን ያገኘዋል፤
ቢቆይ እንጂ መች ይቀራል!!
🎤ወንድሙ ጅራ
የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence
ይቀመጣል እንደ አደራ Wendimu Jir-audio.mp32.48 MB
👍 7❤ 2
👉👉መኖር ከተባለ👈👈
እውነታ እንዳይታይ~አይን ተጨፍኖ
ጆሮም እንዳይሰማው~በውሸት ተደፍኖ
ልብም እንዳይራራ~በትቢት ደንድኖ
ኖሪያለው ይባላል~ያውም ተሰልጥኖ
:
:
ህሊና በመሸጥ~ራስ መውቀስ ተትቶ
አዕምሮ በማጥበብ~ማመዛዘን ቀርቶ
መኖር ምን ይሰራል~ሆድ ብቻ አስፍቶ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
Ⓒgetem
➕️➕️መደመር➕️➕️❗️
ጊዜው ተቀይሮ
ዘመን ተቀይሮ
ይቀንሳል ያልነው የመከራው ኑሮ
ተደራርቦ መጣ ሁሉም ተደምሮ::
Ⓒgetem
❤ 7👍 2
የተመረጡ አባባሎች
‹‹ደስታ ከምክንያታዊነት ጋር የሚስማማ ሳይሆን ከምናብ ጋር የሚዋሃድ ነው፡፡››
ኢማኑኤል ካንት
‹‹ሌላ ሠው ማፍቀር የፈጣሪን ሌላኛውን ፊቱን ማየት ነው፡፡››
ቪክቶር ሂጎ
"አእምሮ አስደናቂ አገልጋይ ነው ፣ ግን አስፈሪ ጌታ ነው።"
ሮቢን ሻርማ
"አንድን ነገር መቼም ላላውቀው አልችልም በሚል ስሜት ተማረው፤ስታውቅ ደግሞ መቼም ላጣው እችላለሁ በሚል ስሜት አጥብቀህ ያዘው!!"
ኮንፊሽየስ
"ሁለት የሞኝነት መንገድ አለ ። አንደኛው እውነት ያልሆነውን ማመን ሲሆን ሌላኛው እውነት የሆነውን አለማመን ነው ።"
ሶረን ኪድጋርድ
‹በህግ አንድ ሠው የሌላን ሠው መብት ከተጋፋ ወንጀለኛ ነው፡፡ በስነምግባር ግን አንድ ሠው ሌላ ሠው ላይ ክፉ ማሠቡ ብቻ ወንጀለኛ ያደርገዋል፡፡››
ኢማኑኤል ካንት
"ስለራስዎ ጥሩ ስሜት እስኪሰማዎት ድረስ አንድ ሰው ስለራሱ ጥሩ ስሜት እንዲሰማው ማድረግ አይችሉም ፡፡"
ሮቢን ሻርማ
‹ልምድ ንድፈሃሳብ ከሌለው እውር ነው፡፡ ነገር ግን ንድፈሃሣብ ራሱ ልምድ ከጎደለው እንደው ዝምብሎ የምሁር ጨዋታ ነው የሚሆነው፡፡››
ኢማኑኤል ካንት
‹‹ሠዎች ጥንካሬ አላጠራቸውም፡፡ ያጠራቸው ፈቃድ ወይም ፍላጎት ብቻ ነው፡፡››
ቪክቶር ሁጎ
‹‹ዝናህን ለመገንባት ሃያ ዓመት ይወስድብሃል፡፡ ዝናህን ለማበላሸት ግን ሃያ ደቂቃ በቂህ ነው፡፡ ይሄን ጉዳይ ካሰብክ ነገሮችን በተለያየ መንገድ ታከናውናቸዋለህ፡፡››
ዋረን በፌት
"የበለጠ ለመስራት እና የበለጠ ለመሞከር ጥረት ያድርጉ። ህልሞችዎን ለመጀመር ሀይልዎን ይጠቀሙ ፡፡ ህልሞችዎን ያስፋፉ። በአእምሮዎ ምሽግ ውስጥ ማለቂያ የሌለው አቅም ሲኖርዎት የመለስተኛነት ሕይወት አይቀበሉ ፡፡ ታላቅነትዎን ለመጠቀም ደፉሩ"
ሮቢን ሻርማ
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
👍 12❤ 3
ተረኛው ጨባጭ!
“አንድ ሰው ሕጻን ሆኖ ሲወለድ እጁን (መዳፉን) ጨብጦ ነው፤ አንድ ሰው ሸምግሎ ሲሞት ደግሞ እጁን (መዳፉን) ዘርግቶ ነው” ይላል ካልታወቀ ምንጭ የተቀዳ እውነተኛ አባባል፡፡
ለአንድ ሕጻን አንድን ነገር በእጁ አስይዛችሁት ካወቃችሁ ልጁ የያዘውን ነገር በቀላሉ እንደማይለቅ ትደርሱበታላችሁ፡፡ አንድ ሕጻን ልጅ እጁን ጨብጦ መወለዱ ሁሉን ለመያዝ፣ ሁሉን በእጁ ለማስገባትና ሁሉን ነገር በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ የመሞከሩ ምልክት ነው፡፡
አንድ ሰው ሸምግሎ ሲሞት እጁን ዘርግቶ መሞቱ ደግሞ ሁሉን አይቶት፣ ሞክሮት፣ ጨብጦና “የእኔ ነው” ብሎ በመጨረሻ ምንም ነገር የእርሱ እንዳልሆነና አንድ ቀን ሁሉም ነገር ከእርሱ ቁጥጥር ውጪ እንደሚሆን የመገንዘቡ ምልክት ነው፡፡
እውነታው ይህ ነው፡- ተወልደን በልጅነት ባሳለፍንበት ወቅትና ሸምግለን ከዚህ አለም ወደመሰናበት በምንደርስበት ወቅት መካከል ባሉን እንደ ጥላ በሚያልፉት አመታቶቻችን መያዝና መቆጣጠር በምንችለውና በማንችለው መካከል መለየት አስፈላጊ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ነገ ሁሉንም ነገር ትተነው እንደምናልፍ በመገንዘብ ዘመናችንን እንዳናባክነው እናስተውል፡፡
እጅህ በገባው ነገር ደስተኛ ሁን፣ ለመልካም ነገር ተጠቀምበት፡፡ እጅህ ለማስገባት ያልቻልከውን ነገር ለማስገባት ሞክር፣ ነገር ግን ሁሉን ካልያዝኩ በማለት ዘመንህን አታስበላ፡፡
ለጊዜው ነው እንጂ ምንም ነገር በቋሚነት የአንተ አይደለም፡፡ የእኔ ነው ብለህ የምታስበው ሁሉ ለጊዜው በአደራ የተሰጠህ ነው፡፡ ዛሬ አንተ የምትኖርበትን ቤትና ትናንት መሬት የእኔ ነው ብሎ የሚኖርበት ሰው ነበር፡፡ ዛሬ ግን የአንተ ነው፡፡ ነገ ደግሞ ይህንን ስፍራ ሌላው ተረኛው ጨባጭ ይረከበዋል፡፡
ቁም ነገሩ ዛሬ በእጅህ ያለውን መልካም ነገር የመልቀቂያህ ጊዜ እስከሚመጣ ድረስ ለመልካም ዓላማ የመጠቀምህ ጉዳይ መሆኑን ላስታውስህ፡፡
ዶክተር እዮብ ማሞ
@Human_Intelligence
👍 6❤ 1
ተረኛው ጨባጭ!
“አንድ ሰው ሕጻን ሆኖ ሲወለድ እጁን (መዳፉን) ጨብጦ ነው፤ አንድ ሰው ሸምግሎ ሲሞት ደግሞ እጁን (መዳፉን) ዘርግቶ ነው” ይላል ካልታወቀ ምንጭ የተቀዳ እውነተኛ አባባል፡፡
ለአንድ ሕጻን አንድን ነገር በእጁ አስይዛችሁት ካወቃችሁ ልጁ የያዘውን ነገር በቀላሉ እንደማይለቅ ትደርሱበታላችሁ፡፡ አንድ ሕጻን ልጅ እጁን ጨብጦ መወለዱ ሁሉን ለመያዝ፣ ሁሉን በእጁ ለማስገባትና ሁሉን ነገር በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ የመሞከሩ ምልክት ነው፡፡
አንድ ሰው ሸምግሎ ሲሞት እጁን ዘርግቶ መሞቱ ደግሞ ሁሉን አይቶት፣ ሞክሮት፣ ጨብጦና “የእኔ ነው” ብሎ በመጨረሻ ምንም ነገር የእርሱ እንዳልሆነና አንድ ቀን ሁሉም ነገር ከእርሱ ቁጥጥር ውጪ እንደሚሆን የመገንዘቡ ምልክት ነው፡፡
እውነታው ይህ ነው፡- ተወልደን በልጅነት ባሳለፍንበት ወቅትና ሸምግለን ከዚህ አለም ወደመሰናበት በምንደርስበት ወቅት መካከል ባሉን እንደ ጥላ በሚያልፉት አመታቶቻችን መያዝና መቆጣጠር በምንችለውና በማንችለው መካከል መለየት አስፈላጊ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ነገ ሁሉንም ነገር ትተነው እንደምናልፍ በመገንዘብ ዘመናችንን እንዳናባክነው እናስተውል፡፡
እጅህ በገባው ነገር ደስተኛ ሁን፣ ለመልካም ነገር ተጠቀምበት፡፡ እጅህ ለማስገባት ያልቻልከውን ነገር ለማስገባት ሞክር፣ ነገር ግን ሁሉን ካልያዝኩ በማለት ዘመንህን አታስበላ፡፡
ለጊዜው ነው እንጂ ምንም ነገር በቋሚነት የአንተ አይደለም፡፡ የእኔ ነው ብለህ የምታስበው ሁሉ ለጊዜው በአደራ የተሰጠህ ነው፡፡ ዛሬ አንተ የምትኖርበትን ቤትና ትናንት መሬት የእኔ ነው ብሎ የሚኖርበት ሰው ነበር፡፡ ዛሬ ግን የአንተ ነው፡፡ ነገ ደግሞ ይህንን ስፍራ ሌላው ተረኛው ጨባጭ ይረከበዋል፡፡
ቁም ነገሩ ዛሬ በእጅህ ያለውን መልካም ነገር የመልቀቂያህ ጊዜ እስከሚመጣ ድረስ ለመልካም ዓላማ የመጠቀምህ ጉዳይ መሆኑን ላስታውስህ፡፡
ዶክተር እዮብ ማሞ
@Human_Intelligence
👍 3
በቃ ልመዱት !!!
• ሰዎች “አደርገዋለሁ” ብለው የገቡላችሁን ቃል ኪዳን ላይፈጽሙ ይችላሉ - ልመዱት!
• ዛሬ የሚወዷችሁና የሚያከብሯችሁ ሰዎች ነገ ሊጠሏችሁና ሊንቋችሁ ይችላሉ - ልመዱት!
• ዛሬ ምስኪን መስለው ለሕልውናቸው በእናንተ እርዳታ ላይ የተደገፉ ሰዎች ነገ ውለታ-ቢስ ሆነው ልታገኟቸው ትችላላችሁ - ልመዱት!
• ሰዎች የሆናችሁትን ማንነት ሳይሆን ያላችሁን ቁሳቁስ አይተው እንደቀረቧችሁ ልትደርሱበት ትችላላችሀ - ልመዱት!
• አንዳንድ ሰዎች በሰላሙ ጊዜ የሰሙትን ምስጢራችሁን ግንኙነታችሁ ሻከር ሲል ለወሬና እናንተንው ለማጥቃት ሊጠቀሙበት ይችላሉ - ልመዱት!
እነዚህንና እነዚህን መሰል በማንኛውም ሕብረተሰብ መካከል የሚንጸባረቁ የሰዎች ባህሪያትን መልመድ ማለት፣ ሁል ጊዜ ከሰዎች የምንጠብቀውን ነገር እንደማናገኝ መገንዘብና ራስን ማዘጋጀት ማለት ነው፡፡
ከሰዎች የምንጠብቀውን መልካም ነገር ስናገኝ ደስ የመሰኘታችንንና ሰዎቹንም የማመስገናችን ልምምድ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለማንኛውም አይነት ወጣ ያለ የሰዎች ሁኔታ ራስን ማዘጋጀትና ከሁኔታው ባሻገር አልፎ ለመሄድ የውስጥ ውሳኔን መወሰን እጅግ ጠቃሚ ልምምድ ነው፡፡
እንደሰው የመለዋወጥ ሁኔታ የሚለዋወጥ ሰባራ ማንነት እንደሌላችሁ ለራሳችሁ የምታስመሰክሩበት ቀን ይሁንላችሁ!
ዶ/ር እዮብ ማሞ
👍 6
Listen to Aleke on #Sewasew Music
https://play-sewasewmusic.tunedglobal.com/albums/204027285?country=ET
የራስ-በራስ ምልከታ ወሳኝነት
ማንም ሰው ስለ እኛ ካለው አመለካከት ይልቅ እኛው በራሳችን ላይ ያለን አመለካከት የላቀ ተጽእኖ አለው፡፡
ከሚከተሉት ሁለት እጅግ ጎጂ ከሆኑ የራስ-በራስ ምልከታዎች ጠንቀቅ!
1. ሁሉም ሰው (አብዛኛው ሰው) እንደሚወደንና እንደሚያደንቀን ማሰብ፡፡
ይህ አመለካከት ከእውነታ የራቀ የቅዠት አለም ውስጥ እንድንኖር አጋልጦ ይሰጠናል፡፡ ምንም አይነት ውብ፣ ድንቅና ጎበዝ ሰዎች ብንሆን የሚወዱንና የሚቀበሉን ሰዎች የመኖራቸውን ያህል የማይወዱንና የማይቀበሉንም ሰዎች ሞልተዋል፡፡ ከዚህ እውነታ ሊያመልጥ የሚችል ማንም ሰው ተፈልጎ አይገኝም፡፡ ሁሉም ሰው እንደሚወደንና እንደሚቀበለን ማሰብ ላልተፈለገ የስሜት ቁስል አሳልፎ ይሰጠናል፡፡ ይህ ቀውስ የሚመጣው እውነታውን ቀስ በቀስ እያየነው ስንመጣ ነው፡፡
2. ሁሉም ሰው (አብዛኛው ሰው) እንደማይወደንና እንደማይቀበለን ማሰብ፡፡
ይህ አመለካከት ተቀባይነት ለማግኘት ያልሆነውን ሆነን፣ የሌለንን ደግሞ እንዳለን አስመስለን እንድንኖር ይገፋፋናል፡፡ እዚህ ጋርም ማስታወስ ያለብን ነገር፣ ምንም አይነት ሰዎች ብንሆንና በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆን የማይወዱንና የማይቀበሉን ሰዎች የመኖራችውን ያህል የሚወዱንና የሚቀበሉን ሰዎች እንዳሉ ነው፡፡ ይህ እውነት የገባቸው ሰዎች አስገራሚ የሆነ በሚወዷቸውና በሚቀበሏቸው ሰዎች ላይ የማተኮርና በዚያ ላይ የመገንባት ብቃት አላቸው፡፡
በሉ እንግዲህ፣ የማይቀበሏችሁ ሰዎች ካሉ፣ ይህንን አመለካከታቸውን እንዲቀይሩ ለማድረግ መሞከሩ አይከፋም፡፡ ያንን ማድረግ ካልቻላችሁ ግን ስለ እነሱ እያሰቡ መዋልና ማደር ተውና በሚቀበሏች ሰዎች ላይ ትኩራትችሁን አድርጉ፡፡
በሌላ ጎኑ ደግሞ፣ የሚቀበሏችሁን ሰዎች በማሰብ መደሰትና በሁኔታው ላይ በመገንባት አንድን መልካም ነገር ለማከናወን መጠቀም ተመራጭ መንገድ ነው፡፡
ዶ/ር እዮብ ማሞ
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
👍 5
👉 ጓደኝነትህን ከፍ ያለ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር አድርግ፡፡ ካንተ የተሻሉ ሰዎችጋ የምትውል ከሆነ እንደ እነሱ መሆን ትጀምራለህ፡፡ ተራ የሆነ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር ስትሆን ተቃራኒውን ትሆናለህ፡፡
👉 እድገትህ ያለው ከፊትህ እንጂ ከኋላህ (ካለፈው) አይደለም፣ የፊትህ ላይ አተኩር፡፡
👉 ከምንም በላይ ራስህን አሳድግ፡፡ በፅሁፍም ሆነ በንግግር ሃሳብህን በሚገባ ለመግለፅ ተማር፣ ስልጠና ውሰድ፡፡ ይሄ ብቻ ተፈላጊነትህን በ50% ይጨምራል፡፡
👉 በተቻለ መጠን ውስጥህ መሆን የሚፈልገውን ሁን፤ የሚያስደስትህን ስራ፡፡
👉 ትሁት ሁን፡፡ ትሁት ሰው እኔ ብቻ ነኝ አዋቂ አይልም፡፡ ከሌሎች ይማራል፤ ያለማቀረጥ ያነባል፣ ሎሎችን ይሰማል፣ ይማራል፡፡
👉አካልህን እና አእምሮህን በሚገባ ተንከባከብ፡፡ በምድር ላይ ስትኖር የሚኖርህ አንድ አካል እና አንድ አእምሮ ስለሆነ በትጋት ጠብቀው ተንከባከበው፡፡
ዋረን ቡፌት
ሀገር ያጣ ሞት
ደራሲ -ሄኖክ በቀለ
"አንዳንድ ታሪኮች ርእስ የላቸውም ተነግረው እንዳልተነገሩ ይረሳሉ። አንዳንድ ሰዎች አስታዋሽ የላቸውም —ኖረው እንዳልኖሩ ይቆጠራሉ። አንዳንድ ገድሎች አልተዘከሩም የባከኑ መሥዋዕትነቶች ይባላሉ። አንዳንድ ቅሌቶች ሰው ፊት አልታዩም እንዳልተፈጸሙ ሁሉ በጨለማ ውስጥ ይቀራሉ። አንዳንድ አወዳደቆች ከትዝብት ልብሳችንን አራግፈን እንቀጥላለን። አንዳንድ ሕዝቦች በወል ተረስተዋል ተጋርደዋል —ዙሪያውን ለመታሰቢያነት የቀረላቸው ምንም የለም። አንዳንድ ኮቴዎች በመረሳት ተጠቅተዋል —አንዳንድ ወኔዎች ለሞት ዳርገዋል። "
"ታሪክ የአሸናፊዎች መዋዕል ነው። ነገሥታት ከአፍ ከአፍ እየተቀለቡ ዘመን ሲሻገሩ ሕዝብ ግን ተረስቶ ባለበት ይቀራል። የሱሲንዮስ ጋሻ ጃግሬ ማን ይባላል? የሰሎሞን እቁባት ለሕይወቷ ምን አደረገች? ስሟ እንኳ አልተጻፈም። ሰሎሞን ሰባት መቶ እቁባት ቢኖረው የሰሎሞን ታሪክ ብቻ ነው —እነርሱ የታሪኩ ሟሟያ ብቻ ናቸው ...እንደጊዜና ቦታ ያሉ የመተረኪያ አጥቆች። ዛሬ የቆምንበት ምድር ላይ ትላንት ማን ነበረ? ለነገሥታት “ዘራፍ!” ካለው ስንቱ ተረፈ? ታሪክ መርጦ ያስታውሳል። አሸናፊ መሆን ያልቻሉት ለአጉል አሟሟት ይሯሯጣሉ። ምንም ያልሠሩት በጀግና ሰይፍ ላይ በመውደቅ ብቻ የሚታወሱ ሰማዕት ይሆናሉ። ሲኖሩ ሳይሆን ሲሞቱ ያወቅናቸው ለቁጥር ይታክታሉ። ለሞቱ ግድ የሌለው ሕዝብ “ከሞቴ አሟሟቴን” ይተርታል። “ወይ ግደልላት ወይ ሙትላት፣ የፈሪ ወዳጅ አታሰኛት!”ን ያንቋርራል —የምትወደው ሰው ከሞተባት በኋላ “የጀግና ወዳጅ” መባል ምን ይፈይድላታል?ይህ ሲደመር የምንኖርለት ዓላማ “ወይ መግደል፣ ወይ መሞት” ይሆናል። እናም ያስጨንቃል!!
መሪዎች በክፉም፣ በደጉም ከሰው አፍ ይውላሉ። “ከሕይወቴ የገዘፈ ዓላማ አለ” ብሎ የሚያስብ ነዋሪ በደምፍላትና በእልህ ተነሥቶ ሁሉ የማይታወስ አጽም ለመሆን ይፈጥናል።"
ሀገር ያጣ ሞት
ገፅ 132
ይህን የመፅሀፍ ገፅ እያነበብኩ የሀገራችን ወቅታዊ ፓለቲካ ታወሰኝ ደራሲው የሚተርከው በሁለት መሳፍንቶች መካከል በተደረገ ጦርነት ህይወቱን ስላለፈ የአንድ ወጣት ታሪክ ነው።
የዚህ ድርሰት አስገራሚው ታሪክ በሁለቱ መሳፍንት(ራስ አሊና ደጃፍ ውቤ) ጥጋብ ምክንያት በተደረገው ጦርነት ብዙ ህዝብ ካለቀ በኋላ በዛው እለት ሁለቱ መሳፍንቶች
ፊት ለፊት ሲገናኙ ያደረጉት ንግግር ነው።
ገፅ 139
"ራስ ዐሊም፣ ደጃች ውቤም ቁጭ ብለው ማዘዝና የመኳንንትን ሕይወት መግፋት እንጂ መግቢያ፣ መውጫውን አብጠርጥረው የሚያውቁ ጎበዞች አልነበሩም። የፍርሃታቸውን ባመጣላቸው በኩል ሲፈረጥጡ አንድ ጠባብ መንገድ ፊት ለፊት ተጋጠሙ። መንገዷ ከአንድ ሰው ውጪ የማታሳልፍ ሆና ወይ መመለስ ወይ ገድሎ ማለፍ ግድ ሆነ። ሁለቱም ሲያምታቱና ሲያስመስሉ ኖሩ እንጂ የውጊያ ዕውቀትም ጀግንነትም የሌላቸው ስለነበሩ ጦርና ጋሻቸውን እንደሰበቁ ተፋጠው ቀሩ።
ቆይቶም ደጃች ውቤ
“ዐሊ እንደው ጥጋባችን እንጂ እኔና አንተ ደም መቃባት ነበረብን?” አሉ።
“ውቤ አንተ እምቢ! አልክ እንጂ እኔ መች ፈለግሁት? ባንዋለድም ዘመድ ነን። ወንድሜ ነህ!”
“ግዛት እንደሁ እኔም የእኔን፣ አንተም የአንተን እንደያዝን ጦራችንን አጠንክረን ካሣን መውጋት ሲገባን...”
“ሰይጣን ሰውሮብን እንጂ ሐሳብህ ሐሳቤ ነው!”
“በል አሁን በጀ በል! ሄደን ጦርነቱን እንፍታ።”
“እንዲያ” .....ሁለት ታሪኮች ተቃቅፈው ተሳሳሙ። እንደ ወዳጅ ተያይዘው ወደ ጦርነቱ ቦታ ጋለቡ።
ሽምጥ ጋልበው ሲደርሱ፤ ጦርነቱ አልቆ፤ ቦታው በሰው ሬሳ ተሞልቶ፤ አንዳንዱም ወድቆ ሲያጣጥር ደረሱ። ለሞቱ ወታደሮቻቸው በማዘንና በማልቀስ ፈንታም በሬሳው ላይ ወዲህና ወዲያ እየተመላለሱ ይስቁና ይቀላለዱ ገቡ።
“ይሄስ አንዴም የተኮሰ አይመስልም። ታቅፎት ተኝቷል።”
“ዐሊ ና እስቲ ወደዚህ ...ይህቺማ ሁለት እጇም፣ ሁለት እግሯም የለ! ባለጓጉንቸር ሳጥን መስላልሃለች።”
ሳጥን የመሰለው፤ ያ ጎበዝ ወጣት ደጃች ውቤን ከልቡ ይወደው የነበረ... የደጃች ውቤ መሰደብ ያንገበገበው የነበረ ...ደሙ ተንዠቅዥቆ ያልሞተ ...የደጃች ውቤን ንግግር ሰምቶ ጸጥ ጭጭ አለ።
ምናልባትም ከመጨረሻው ህቅታ ጋር ነገሥታት ለሥልጣናቸው እንጂ ለሕዝቡ ግድ እንደሌላቸው እያሰበ፤ ከረፈደም ቢሆን እያብከነከነው ሄደ። “የት?” እንዳትሉ! ሰው ከሞተ ወዲህ መኖሪያውን ማን ያውቃል? ምናልባትም አብረውት የተከመሩት ብዙ ሺህ ሬሳዎች ካልሆኑ በቀር።
የእናቶች ለቅሶና ዋይታ ምድሩን አደበላለቀው። አንዳንድ ታሪኮች ርእስ የላቸውም የሞትህ ትንፋሽ በአንገትህ ሥር በሞቀህ ሰዓት የተገለጠልህን ስሕተት መቼ ታርመዋለህ? አንዳንድ ሰዎች ስም የላቸውም —ይህ ወጣት የጦርነት ታሪኩ አጥቅ ነው፤ የመተረኪያ አማሃይ፤ በምድር ፊት ስለፈሰሰው ደሙ ማን ግድ አለው? ....አንዳንድ ገድሎች አልተዘከሩም። አንዳንድ ቅሌቶች ሰው ፊት አልታዩም። ታሪክ የአሸናፊዎች መዋዕል ነው። በአሸናፊ ስም የሚወድቀውን ነፍስ ከእንስፍስፍ የእናት አንጀት በቀር ማንም አያስታውሰውም። ማንም!!"
.............
በኢትዮጵያ መንግስት እና በወያኔ መካከል የተደረገው ጦርነት ከብዙ ደም አፋሳሽ ግጭት በኋላ ጦርነቱ በሰላም ስምምነቱ መጠናቀቁ ይታወሳል። በሁለቱም ወገን ያሉ መሪዎች በየቦታው ተቃቅፈው ፎቶ መነሳት ላይ ይገኛሉ። በዚህ ጦርነት ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ የነዚህ ሰዎች ታሪክ ግን ተረስቷል ፤ ሞታቸው ቁጥር ሆኖ አልፏል። ህይወታቸው ትርጉም ላለው ነገር እንዳለፈ ለመናገር እንኳን ያድግታል። የባከኑ መስዋዕቶች ሆኗል።ታሪክ የሚፅፈው የአሸናፊዎችን ገድል ብቻ ይሆናል።
“የጠገበ ሲያገሳው
ተግ ሲል ቀልቡን የነሳው
በመጨረሻ ጦርነት ያበቃል
ወታደሩ ያልቃል ንጉሥ ይታረቃል”
አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በአንዱ ፁሁፉ ላይ እንዲህ ይላል
"ለጊዜያዊ ይሁን ለዘለቄታ የፖለቲካ ጥቅም ሲባል በፖለቲካ ውስጥ ብዙ አይነት ኢ-ሞራል የሆኑ ነገሮች እንደሚሰሩ ቢታውቅም፣ ባሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየታየ ያለው በየትኛውም መመዘኛ ዝቅጠቱን ማሳነስ የማንችለውን የመሰለ የፖለቲካ አመለካካትና ድርጊት ይታያል።
ጦርነት በሰላም እንዲቆም ለማድረግ ስምምነት ላይ መድረስ አንድ ነገር ሆኖ ሳለ ይህ ሰላም ከኋላው የተሸከመውን ከባድ የህዝብ ሰቆቃ የማይመጥን የፊት ገጽታ የሰውነት ቋንቋ እያሳዩ፣ ከወያኔ ሰዎች ጋር የነበረው ግጭት በአንድ ምሽት በስካር መንፈስ ዳንስ ቤት ውስጥ የተፈጠረ ችግር በሚመስል መልኩ፣ በሳቅና በፈገግታ የተሞላ ግንኙነት ምን ያህል በጦርነቱ የተጎዳውን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ ሊያስከፋ እንደሚችል ዞሮ ማሰብ አለመቻል የሰላም ስምምነቱ ስሜት አልባ፣ ሃላፊነት በማይሰማቸው ግለሰቦች የተደረገ እንደነበር ማሳያ ነው።"
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
😢 3👍 2❤ 1
አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?
እሱባለው አበራ
እንደትላንት ተወልደን ዛሬ ላይ እድሜያችን ስንት ደረሰ? ወጣትነታችን ወደ ፊት የሚያራምደን መስሎን ተሞኘን። ዕቃቃችንን ስንጥል፥ ጨዋታችንን አልጠገብንም ነበር። ድክ፥ ድክ ያልነው በወጉ ዳዴ ሳንል ነው። ልባችን ላይ የሚነደው የጉርምስና እሳት ደረታችንን ሲፋጅ ሰፊ መንገድ ያለ መስሎን ነበር።
አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?
ከአባታችን ወገብ የተከፈለው ዘር፥ በእናታችን ማኅጸን እንቁላል ሳይመታ፤ ፅንስ ሳንሆን፥ ሥጋችን ሳይቦካ፥ አጥንታችን ሥር ሳይሰድ፥ ጅማታችን ሳይዘረጋ፥ ሽል ሳንሆን በፊት. . . ክፉ ዕጣ ቀድሞናል። አንዳችን ለአንዳችን ጠላት ተደርገናል። ለሞትም ታጭተናል። ሳንመርጥ ወግነናል። ደርሰን ባልበደልነው፥ ባልሠራነው ታሪክ. . . አክ እንትፍ ተብለናል።
አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?
እኔና አንተ ምንም እንኳ ወደ ፊት መጓዝ ብንፈልግም፤ ይሄ ሀገር የሚሄደው ወደ ኋላ ነው። ዳገቱን ወጣን፥ አቀበቱን አሸነፍን፥ ተራራውን ረታን ስንል. . . እየተንሸራተተ መቀመቅ ይዞን ይወርዳል። በየቀኑ ትርጉም አልባነትን እንድናንከባልል ተፈርዶብናል።
አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?
አናምንም። ግን ዕውቀት የማይዘልቀው የድንቁርና እና የአረመኔነት ዘረመል ሥጋ ለብሶ ያለው እዚህ ሀገር ነው። ኅዘንተኞች ሳለን መጽናኛ የለንም። ፍርፋሪ እሴት ሳይቀር ነጠቁን። ረክሰው አረከሱን። የሤራ ፖለቲካው ጉንጉን ፈጣሪ ዓለምን ከፈጠረበት ጥበብ በላይ ሳይረቅቅ አይቀርም። እግዚዖ!
አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?
ከተወለድን ጀምሮ አላስተኙንም። ታዲያ ሕይወታችን ስለምን ቅዠት በቅዠት ሆነ? ማለት መቼ አስተኝተውን? መቼስ ተደላድለን? እስከ መች እንደምንኖር አናውቅም። ሕይወት አጭር ናት፤ እዚህ ሀገር ደግሞ እጅግ በጣም አጭር ናት። ሕልውናችን ከእኛ ቁጥጥር ውጪ ነው። ብንነቃም፥ ብናንቀላፋም ሕይወት ጭራቅ መልኳን ለአፍታ አትቀይርም። የቸገረ ነገር!
አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?
እንዴት እንደሆነ ባናውቅም እንደ ትውልድ አምክነውናል። ሳንወለድ ገድለውናል። የእናት ጡት ሳንጠባ አስረጅተውናል። ቆምረውብናል። ቅያሜውን ሳናውቅ፥ ጦርም ሳንገጥማቸው፥ ያለ ወግ ድል አድርገውናል። ያረፈብን የጀግናም አይደለ፥ የፈሪ ዱላ ነው!
አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?
ዳሩ ምርጫ አልነበረንም።
@EsubalewAberaN
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
👍 6❤ 1
ስለመፅሐፍ የተነገሩ አባባሎች!
ወዳጆች ዛሬ የንባብ ባህላችን እንዲዳብር ሊያነሳሱን የሚችሉ ስለመፃሕፍት የተነገሩ የተለያዩ ሠዎችን አባባል ዛሬ ልንዘክር ብዕራችንን ከወረቀቱ አገናኝተናል፡፡
መፅሐፍ የሚሠጡት ጥቅም የታወቀ ቢሆንም በማንበብ ብቻ ግን አዋቂ መሆን አይቻልም ባይ ነኝ፡፡ ምክንያቱም መፃሕፍትን ከማንበብ ባሻገር በንባብ ያገኘናቸውን ሃሳቦች ከሃሳባችን ጋር በማስተያየትና በማሻሻል፣ በማሠላሠልና በማስተዋል አዲስ ሃሳብ ካልፈጠርንበት መፅሐፍ ማንበብ ሳይሆን መፅሐፍ መቁጠር ነው የሚሆነው፡፡ ባነበብነው ሃሳብ ተገዝተንና አዲስ የባህሪ ለውጥ ወይም አዲስ ነገር ካልፈጠርንበት ማንበባችን ዕውቀት አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ዕውቀት ስንል በተጨባጭ በተግባር የሚገለፅ ነውና፡፡
ለማንኛውም አባባሎቹን እነሆ እላለሁ..! ሃሳብና አስተያየታችሁ የተጠበቀ ነው፡፡ መልካም ንባብ!
‹‹መፅሐፍ አንድ ቁምነገር አለው፡፡ ይሄም እግርህን ከቤትህ ሳታነሳ ዓለምን እንድትዞር ያደርግሃል›› (ጁምባ ራሂሪ)
‹‹አንባቢ ከመሞቱ በፊት አንድ ሺ ኑሮ ይኖራል፡፡›› (ጆርጅ ማርቲን)
‹‹መፅሐፍት ተንቀሳቃሽ አስማቶች ናቸው›› (ስቴፈን ኪንግ)
‹‹እንደመፅሐፍ ያለ ታማኝ ጓደኛ የለም፡፡›› (ኸርነስት ኸርሚንግወይ)
‹‹ አንድ ነገር አንርሳ! አንድ መፅሐፍ፣ አንድ እስኪብርቶ፣ አንድ ሕፃን፣ አንድ መምህር ዓለምን መለወጥ ይችላሉ፡፡›› (ማላላ ዮሶፍዜ)
‹‹ዓለም መፅሐፍ ናት፡፡ ዓለምን ተጉዘው ያላዩ መፅሐፍ ይግለጡ፡፡›› (ቅዱስ አውግስጦስ)
‹‹መፅሐፍ በየዕለቱ የሚያጋጥመንን የህይወት ጉድፍ የሚያስወግድልን የነፍሳችን ማጠቢያ ነው፡፡›› (ያልታወቀ ሠው)
‹‹ማንበብ ለአዕምሮ ሲሆን አዕምሮም አካላችን ምን ማድረግ እንዳለበት ያቀናጃል›› (ያልታወቀ ሠው)
‹‹መፅሐፍ ከባድ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ዓለሙ ሁሉ በእርሱ ታጭቋልና፡፡›› (ኮሜሊያ ፈንክ)
‹‹ዛሬ አንባቢ የሆነ ነገ መሪ ይሆናል፡፡›› (ማርጋሬት ፉለር)
‹‹ዛሬ ልታነበው የምትችለውን መፅሐፍ ለነገ አታቆየው፡፡›› (ያልታወቀ ሠው)
‹‹ካነበብኩ መላው ዓለም ለእኔ ክፍት ነው፡፡›› (ሜሪ ማክሎድ ቤቱን)
‹‹አንዳንድ መፅሐፍት ነፃ ይተዉናል፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ነፃ አድርገው ይሠሩናል፡፡›› (ራልፍ ዋልዶ ኤመርሠን)
‹‹መፅሐፍ ወደፊት ልንሆን የምንፈልገውን የያዘ ህልማችን ነው፡፡›› (ኔል ጌማን)
‹‹ቤተ-መፃሕፍቶች ልክ እንደጥሩ ትዝታ መዓዛቸው ያውደኛል፡፡›› (ጃኩሊን ውድሰን)
‹‹መፅሀፍ አስተሳሰባችንን የሚያቀጣጥል መሣሪያ ነው፡፡›› (አላን ቤኔት)
‹‹እኔ በቀላሉ የመፅሐፍ ጠጪ ነኝ›› (ኤል ኤም ሞንቶጎሞሪ)
‹‹ሌላ ሠው ያነበበውን ብቻ እያነበብክ ከሆነ ሌላ ሠው የሚያስበውን ብቻ ነው እያሠብክ ያለኸው፡፡›› (ሐሩኪ ሙራካሚ)
‹‹ቤት ያለመፅሐፍት ማለት አካል ያለነፍስ ማለት ነው፡፡›› (ሲስሮ)
‹‹ተራ ሠዎች ትላልቅ ቲቪ አላቸው፡፡ ብልህ ሠዎች ግን ቤተመፃሕፍት ናቸው፡፡›› (ያልታወቀ ሠው)
👍 6❤ 1
“Books are the mirrors of the soul.”―Virginia Woolf
<<ያም ያም እየተነሳ ፀሐፊ ነኝ ይላል፡፡ የሚታተመው መጽሐፍ ቢበዛ የሚረባው ግን ጥቂት ነው፡፡>> ዛሬ ዛሬ ከሀገሬ አንባቢዎች የምሰማው ቅሬታ ነው፡፡ በዚህ አባባል ውስጥ ድብቅ 'ጽሑፍና ጸሐፊ'ን ማግነን አለች፡፡ 'ያም ያም' ፀሐፊ መሆን ካልቻለ 'ፀሐፊ' መሆን ያለበት ምን አይነት ሰው ነው? የታተመው ሁሉ ጥሩ መጽሐፍ ካልሆነ 'ጥሩ መጽሐፍ' ምን አይነት ነው?
ሀገራችን በጽሑፍ ቀደምት ነን የሚሉ ሊቆች ቢኖሯትም፤ ጸሐፊ የሚከበርባት ሀገር ግን አይደለችም፡፡ በተለይ የፈጠራ ፀሐፍት እንደ ወፈፌና ጸረ-ሀገር ነው የሚታዩባት፡፡ ሥለዚህም የፈጠራ ጽሑፍ ይዘው ወደ መጽሐፍ ገበያ ከሚወጡት ውስጥ ሥሟን ያገነኑ፣ ቅዱስነቷን የመሰከሩ እንጅ ጉድፏን የነቀሱ፣ እንከኗን ያወሱ፣ አውስተውም ይታረም ያሉ አይነበቡም፡፡
ስሻ ወደ መጽሐፍ ገበያ ዘወር ዘወር እላለሁ፡፡ ሻጭ ወዳጆቼ ጋርም ተቀምጨ የገዥውን የንባብ ትኩረት ለማየት እሞክራለሁ፡፡ በብዛት የሚጠየቁና የሚሸጡትን እያሰብኩ 'እነዚህ መጻሕፍት አንባቢው ላይ የሚጨምሩለት ምን ነገር አላቸው?' ብዬ ራሴን እጠይቃለሁ፡፡ አብዛኞቹ ከማኅበራዊ ሚዲያ የተሻለ መረጃ የማይሰጡ ናቸው፡፡ ጥቂቶቹ ቢያንስ መንፈሳዊ አገልግሎት አላቸው፡፡ ለማሰብ የሚሆኑት ወይም ምናብን የሚያነቁት ግን በቀን ውስጥ ላይጠየቁ ይችላሉ፡፡ ይህን እያሰብ መልሼ ሌላ ጥያቅ እጠይቃለሁ 'ሰው የሚያነበው ለምንድን ነው?' ብዬ፡፡ ምክንያታችን ልዩ ልዩ ሊሆን ይችላል፡፡ የተሻለው መልስ ግን 'የተሻለ ሰው' ለመሆን የሚለው ይመስለኛል፡፡ ያላወቁትን ማወቅ፣ ያልደረሱበት ላይ መድረስ፡፡ 'ማንበብ ጎደሎ ያደርጋል' ማለትም ለተሻለ ንባብና እውቀት ፍለጋ ያነሳሳል ማለት ይመስለኛል፡፡ ጥያቄው 'አውቀን ለምን?' የሚለው ነው፡፡ ሰው ነንና ኹልጊዜም በመሰራት ሂደት ላይ ነንና፤ ድክመታችንን ለመለየት፣ ያነሰንን ለማወቅ፣ ያላሰብነውን ለማሰብ ከሁሉም አስቀድሞ ደግሞ 'ማሰብ'ን ለማወቅ የተደራጀ፣ የተሰደረ ነገር ያስፈልገናል፡፡ በእኔ ቤት ይህ ነገር መጽሐፍ ነው፡፡ ማሰብ የሚያስለምድ መጽሐፍ፡፡ ማሰብ የሚያስለምድ እንጅ በእሱ መንገድ የሚያሳስብ አላልኩም፡፡
“Come to the book as you would come to an unexplored land. Come without a map. Explore it and draw your own map.” – እንዲል Stephen King
ማሰብ ሰው የመሆን ሂደትን የማወቅ ሂደት ነው፡፡ ሰው መሆን ዲበአካላዊና ህላዌያዊ ጥያቄዎች የሚነሱበት ነው፡፡ ከየት መጣሁ ወዴት እሄዳለሁ? ለምንና እንዴት ነው የምኖረው? መኖሬ የመወለድ ጣጣ ነው ወይስ ዓላማና ትርጉም አለው? ሕይወት ምንድን ናት? ፍቅር፣ ሐዘን፣ ደስታ፣ናፍቆት፣ ጥላቻ፣ ወሲብ ምንድን ናቸው? የሰው ልጅ ምናብና የፈጠራ አቅም እስከ የት ነው? ተፈጥሮ ምንድን ናት፣ እንዴትስ ነው የምትሰራው? እኔን ከተቀረው ተፈጥሮ ጋር ምን ያገናኝ፣ያስተሳስረኛል? ግለሰብ እና ማኅበረሰብ ምንድን ናቸው፣ ምንና ምን ናቸው? ኃይማኖት ምንድን ናት? መንፈስ እና ነፍስ የሚባሉ ነገሮች አሉ የሉም? እውነት ምንድን ናት? ሀሰትስ? ተፈጥሮ ፈጣሪ አላት? እንዴትና በምን ሁኔታ ወደ ህላዌ መጣን?
የሰው ልጅ የህልውና ታሪክ ምን ይመስላል? ከየት ተነስቶ የት ደረሰ? መድረሻውስ የት ነው?
እኒህና መሰል ጥያቄዎች የማሰብ ሂደትን የሚፈልጉ ናቸው፡፡ በማሰብና በማሰቢያ አካላችን መካከልም አንዳች ተኣምራዊ መስተጋብር መኖሩም ይገባናል፡፡ በርግጥ እነዚህ ነገሮች እያሰብኳቸው ያለሁት ማሰቢያ አካሉ ሥላለኝ ነው ወይስ ቀድሞ ታስቦና ታቅዶበት የተዘጋጀልን ነው? ብለው እንዲጠይቁም ይረዳል፡፡
እዚህ ለመድረስ ደግሞ ግብዓት ያስፈልገናል፡፡ ግብዓቶቹ ከሥሜት አካላትና ከህይወት ልምድ የሚገኙ ናቸው፡፡ እንደ ኤምፔሪስስቶች ገለፃ፤ እኛም በኑሮ እንደሚገባን፡፡ መጻሕፍት ደግሞ ላቅ ያሉት የግብዓት ምንጭ፡፡ መጻሕፍት የሰው ልጅ የማሰብ ጉዞ (Evolution of mind) ሰነድም ናቸው፡፡ ከየት ተነስቶ የት ደረሰ የሚነግሩን፡፡ መጻሕፍታችንን አይተን እንደ ሀገር የማሰብ ጉዟችንን መገምገም እንችላለን፡፡ ምናልባት ጥንታዊ የኃይማኖት መዛግብትን ጠቅሰን እንፎክር ካላልን የእኛ የሚያኮራ አይደለም፡፡ ስለማያኮራም መሸሸጊያ ፍለጋ ታሪክ እንጠቅሳለን፡፡ መጻሕፍት የነፍስ መስታዎት ናቸው እንዳለች ውልፍ፡፡ የእኛ የአሁን የገበያ ላይ መጻሕፍትም የነፍሳችን መስታዎቶች ናቸው፡፡ እነሱን አይተን ራሳችንን ማወቅ እንችላለን፡፡ አንዳች ረብ ከሌላቸው እኛም እንዲያ ብንሆን ነው፡፡
“Reading furnishes the mind only with materials of knowledge; it is thinking that makes what we read ours.” – ይላልና ሊቁ John Locke
[... ናትናኤል ዳኛው...]
👍 4
ለክርስትና እምነት ተከታይ የስብዕና ልህቀት ቻናል ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።
በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

