ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
Open in Telegram
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot 🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Show more2025 year in numbers

221 221
Subscribers
-14824 hours
-6057 days
-2 63230 days
Posts Archive
Photo unavailableShow in Telegram
🌼🌼🌼🌼እንኳን አደረሳችሁ 🌼🌼🌼🌼
አዲስ ዓመት የቤት ባለቤት መሆን ይፈልጋሉ?
🌼በመሀል አዲስ አበባ በካዛንቺስ 🌼
🏗🏢 በሪልእስቴት ዘርፍ እንጋፍው እና ግንባር ቀዳሚ የሆነው ድርጅታችን አያት ሪልእስቴት አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ በአይነቱ ልዩ የሆነ ቅናሽ አዘጋጅትንአል።
🌼 እስከ 25% ድረስ ቅናሽ
🌼 10% ቅድመ ክፍያ ሲከፍሉ 5% ቅናሽ
🌼 በ5% ክፍያ መመዝገብ ይችላሉ።
👉ከ450,000 ብር ጀምሮ የቤት ባለቤት ይሁኑ።
👉ከባለ አንድ መኝታ እስከ አራት መኝታ።
👉 ከተለያዩ የካሬ አማራጮች አሉን።
🤷♂በኢትዮጽያ ብር ገዝተው በዶላር የሚያከራዩት።
በግቢው ዙሪያ
➾ፓርኮች ና የወንዝ ዳር ልማት
➾አለማቀፍ ት/ቤትና ሆስፒታል
➾የእምነት ተቋማት
📍የቤቶቹ እይታ
➤ ወደ ቤተ መንግስት ( ጊቢ ገብርኤል )
➤ ወደ ያካ ተራራ ጫካ
➤ ወደ ወንዝ ዳር ልማት
➤ ወደ ወዳጅነት ፓርክ
💁 እንዲሁም በሲኤሚሲ ሚካኤል እና በአያት ግንባታቸው 90% የደረሱ ቤቶች ።
👉ባለ ሁለት መኝታ እስከ ባለ ሶስት መኝታ
👉G+1 አፓርትመንት
👉 ቀድሞ ለመጣ ቅድሚያ ይስተናገዳል ።
❇️ ከሀገር ውጭ ያላችሁ ደንበኞች በወኪል መግዛት እንደምትችሉ እናሳውቃለን ።
🤝 በኢትዮጵያ ብር ብቻ ይዋዋሉ።
ለምዝገባ
📲0935329052
Whatsapp := https://wa.me/message/2H6HVIFP7BIQI1
❤ 34
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በይፋ ተመረቀ‼️
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዛሬ ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ተመርቋል።በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌህ እና የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ተገኝተዋል።
በተጨማሪም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች በምረቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡መጋቢት 24/2003 ዓ.ም የተጀመረው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የሚይዝ ሲሆን 5,150 ሜጋ ዋት ሃይል የማመንጨት አቅም አለው።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 303👏 42👍 36🎉 21😁 8🔥 4
❤ 321👍 75👏 32🎉 18🔥 9😱 4😁 3
Photo unavailableShow in Telegram
የጨረቃ ግርዶሽ ልዩ ጸሎት‼️
የመካከለኛው ምስራቅ ሀገር በሆነችው የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (ዩ.ኤ.ኢ.) በሚገኙ መስጂዶች ውስጥ የቁርአን አንቀጾች ድምጽ አስተጋብቷል።
ይህም የእስልምና እምነት ተከታዮች በጨረቃ ግርዶሽ ወቅት የሚደረገውን የ"ሰላት አል-ኹሱፍ" የተባለውን ልዩ ጸሎት ለማድረግ የተሰበሰቡበት ጊዜ ነበር። ይህ ጸሎት ሁለት 'ረክዓ' ያካተተ ሲሆን፣ ለፈጣሪ የመተናነስ፣ የመማጸን እና የመለገስ ጊዜ ነው።
በዩ.ኤ.ኢ. በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች መስጂዶች በጸሎት ተሳላሚዎች ተሞልተው የነበረ ሲሆን፣ በርካታ ቤተሰቦችም በቤታቸው ሆነው ጸሎቱን አከናውነዋል።
የሃይማኖት አባቶች እንዳሉት፣ ጸሎቱ ግርዶሹ እስኪያልፍ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን፣ ሙስሊሞችም በፈለጉት ሰዓት መጸለይ እንደሚችሉ ገልጸዋል።
ይህ የሰማይ ክስተት ለብዙዎች የፈጣሪን ታላቅነት ለማሰብ እና ለማሰላሰል እንደ መልካም አጋጣሚ ተደርጎ ይታያል።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 642👍 127😁 96🙏 33😭 19👌 6🎉 4
❤ 108💔 9👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
ኔፓል 26 የማህበራዊ ሚዲያዎች በሃገሯ አገልግሎት እንዳይሰጡ አገደች‼️
ኔፓል ውሳኔውን የወሰነችው የማህበራዊ ሚዲያዎቹ የኔፓልን የምዝገባ መመዘኛ ባለማሟላታቸው ነው ብላለች።
በኔፓል አገልግሎት እንዳይሰጡ ከታገዱ ማህበራዊ ሚዲያዎች መካከል ፌስቡክ፣ X ፣ ኢንስታግራም፣ ቴሌግራም፣ ዋትስአፕ እና ዩቲዩብ ይገኙበታል።
የኔፓል መንግስት ማህበራዊ ሚዲያዎቹ እንዲመዘገቡ በተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረቡን አንስቶ አለመመዝገባቸውን በማንሳት እስኪመዘገቡ ድረስ አገልግሎት እንዳይሰጡ ማገዱን ገልጿል።
ከሁለት ሳምንት በፊት የኔፓል ፍርድ ቤት በሃገሩ አገልግሎት የሚሰጡ ማህበራዊ ሚዲያዎችን ለመቆጣጠር እንዲመች እንዲመዘገቡ ወስኖ ነበር።
በ2023 ኔፓል ቲክቶክንም በተመሳሳይ ጉዳይ አግዳ የነበረ ሲሆን በነሐሴ 2024 መመዝገቡን ተከትሎ እገዳውን አንስታለች።
በርካቶች የመንግስትን ውሳኔ ከቁጥጥር በላይ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን የመጋፋት ተግባር አድርገው ወስደውታል።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 164👍 36🎉 8😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
2 ሚሊዮን ብር እና ከዛ በላይ ዓመታዊ ገቢ ያላቸው ንግዶች ቫት ሊመዘገቡ ነው‼️
የገንዘብ ሚኒስቴር የግብር አሰባሰብ ስርዓትን ለማሻሻል ያለመ አዲስ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) መመሪያ አዉጥቷል።
በመመሪያው ቁጥር 1104/2017 መሰረት፣ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ ገቢ ያላቸው ንግዶች እና የተወሰኑ የሙያ አገልግሎት ሰጪዎች ለቫት እንዲመዘገቡ ግዴታ ተጥሏል፡፡
በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የተፈረመው ይህ አዲስ መመሪያ፣ ከነሐሴ 28 ቀን 2017 ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል። መመሪያው ከንግድ ድርጅቶች በተጨማሪ፣ ከምድብ "ለ" ውጭ የሚመደቡ ባለሙያዎችንም ያካትታል።
እነዚህ ባለሙያዎች የዓመታዊ ገቢያቸው መጠን ምንም ያህል ቢሆን ለቫት መመዝገብ እንዳለባቸው ተጠቁሟል።
በተጨማሪም መመሪያው፣ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ያለባቸው ወይም በፈቃደኝነት የሂሳብ መዝገብ የሚይዙ ሁሉም ንግዶች እንዲሁም በምድብ "ሀ" ስር የተመደቡ ግብር ከፋዮች የመመዝገብ ግዴታ እንዳለባቸው በዝርዝር አስቀምጧል።
አዲስ የተካተቱ ነባር ግብር ከፋዮች፣ መመሪያው በስራ ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ30 ቀናት ውስጥ መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል። ከተመዘገቡ በኋላም ለገበያ በሚያቀርቧቸው ታክስ የሚከፈልባቸው እቃዎች እና አገልግሎቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ መሰብሰብ እንደሚጀምሩ ተገልጿል።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 175😡 26👍 22💔 12👏 7😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
በባቲ ከተማ አዲስ ክልከላ ተጥሏል።ክልከላውን የተላለፈ ይቀጣል ተብሏል‼️
በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የባቲ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት ትላንት ነሐሴ 27/2017 ባደረገዉ አስቸኳይ ስብሰባ የተለያዩ ክልከላዎች ጥሏል።
በከተማው የሰዉን እንቅስቃሴን በተመለከተ ማንኛዉም ሰዉ ከምሽቱ 4:00 ሰዐት በኋላ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርግ ተከልክሏል።
የከተማ የ3 እግር ተሽከርካሪ (የባጃጅ) እንቅስቃሴ እስከ 12:00 ድረስ ብቻ መሆኑ ተገልጿል። ይህን ታሳቢ አድርሃችሁ በጊዜ ግቡ ተብሏል።
ማንኛዉም የ4 እግር ተሽከርካሪ ከምሽቱ 4:00 በኋባ መንቀሳቀስ የተከለከለና ሰዐቱን አልፈዉ የተገኙትም ለቅጣት እንደሚዳረጉ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
ምክር ቤቱ ውሳኔዎቹን ተላልፎ የተገኘ ማንኛዉም አካል በህግ ጥላ ስር በመቆየት ተጠያቂ ይደረጋል ሲል አስጠንቅቋል።ዉሳኔዎቹ ከቀን 28/12/2017 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ እንደሆኑ ተመላክቷል።
©የባቲ ከለማ ፖሊስ
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 215👍 34😁 27💔 10🔥 1😭 1
Photo unavailableShow in Telegram
"አሰብ የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ግዛት ነው የኢትዮጵያም ህልውና ነው ፤በኢትዮጵያ ጉዳይ የመወሰን መብት ባልነበረው የሽግግር ቡድን አሳልፎ የተሰጠ ራስ ገዝ የባህር በራችን ነው፤ በዚህም ብዙ ሃገራት በናንተ ድክመት ነው እስካሁን ያልተመለሰው እንጂ እስካሁን መቆየት ያልነበረበት ነው ይሉናል ፤ አሁን ላይ የቀይ ባህር ጉዳይ የህልውናችን ጉዳይ ሆኗል ለህልውናችን ስንልም የትኛውን ዋጋ ከፍለን አሰብን እናስመልሰዋለን‼️ "
🗣ሜጀር ጀነራል ተሾመ ገመቹ ለፕራይም ሚዲያ
@Esat_tv1
@Esat_tv1
Photo unavailableShow in Telegram
አነጋጋሪው የ10ኛው ትውልድ ኢንተርኔት 10G ተጀመረ‼
ቻይና በዓለም ላይ እስከ 10 ጊጋቢት በሰከንድ የሚደርስ ፍጥነት ያለው የመጀመሪያውን ቋሚ የብሮድባንድ አገልግሎት ማስጀመሯን አስታውቃለች።
ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ በሁዋዌ እና በቻይና ዩኒኮም ትብብር የተገነባ ሲሆን፣ የኢንተርኔት ፍጥነትን ባልተለመደ ሁኔታ ከፍ ያደርጋል ተብሏል።
ይህ አዲስ ኔትወርክ በሰከንድ 9.8 ጊጋቢት የማውረድ(download) ፍጥነት እና ወደ 1 ጊጋቢት የሚጠጋ የመጫን (upload) ፍጥነት ያለው ሲሆን፣ የ3 ሚሊ ሰከንድ እጅግ ዝቅተኛ የጥበቃ ጊዜ (latency) አለው።
ይህ ማለት 20 ጊጋባይት መጠን ያለው ፊልም ከ20 ሰከንድ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ማውረድ ይቻላል ነው የተባለው።
እጅግ ጥርት ያሉ የ8ኬ ቪዲዮዎችን፣ ቪአር/ኤአር ተሞክሮዎችን እና የክላውድ ጌሚንግ አገልግሎቶችን ያለ ምንም መቆራረጥ መጠቀም ይቻላል ተብሏል።
እንደ ቴሌሜዲሲን፣ ዘመናዊ ከተሞች እና የመስመር ላይ ትምህርት ያሉ ዘርፎች ላይ አዳዲስ እድሎችን ይፈጥራል ተብሏል።
በአሁኑ ወቅት ይህ አገልግሎት በአንዳንድ በተመረጡ አካባቢዎች በሙከራ መርሃ ግብር እየተሰራ ሲሆን፣ በኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ እንደሆነ እየተነገረለት ይገኛል።
ይህ 10G የሚለው ቃል የሞባይል ስልክ ኔትወርክ (5G, 6G) ሳይሆን፣ ለቤት እና ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቋሚ ብሮድባንድ ነው ተብሏል። ይህ በኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ታሪክ ውስጥ ትልቅ እድገት ሲሆን፣ ለወደፊት ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎቶች መሰረት ይጥላል ነው የተባለው።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 365👍 60👏 25😁 18😱 12🔥 10🕊 4
Photo unavailableShow in Telegram
“የኢትዮጵያ ስም ይቀየር የሚል ጥያቄ ቀርቦልናል”‼️
🗣የምክክር ኮሚሽን
ከኢትዮጵያ ውጭ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳዎችን ማሰባሰብ የጀመረው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን “የኢትዮጵያ ሥም ይቀየር የሚል ጥያቄ ቀርቦልኛል” አለ።
ይህንን ለሉዓላዊ ሚዲያ የተናገሩት ኮሚሽኑ ካሉት 11 ኮሚሽነሮች ውስጥ አንዱ የሆኑት ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) ናቸው።
እስካሁን ከቀረቡት ጥያቄዎች ውስጥ “ከሕገ መንግሥት ጋር የተያያዙ፣ ከቅርፀ መንግሥት [ወይም] መንግሥቱ ምን መምሰል አለበት?፣ከሙስና ጋር፣ ከትምሕርት ሥርዓቱ ጋር፣ ከቋንቋ ጋር የተነሱ ነጥቦች አሉ” በማለት አስረድተዋል።
በተለይ “ስለአዲስ አበባ ጉዳይ እጅግ በጠለቀ ሁኔታ” መነሳቱን ጠቁመዋል። ኮሚሽነሩ አክለውም በይፋ ባልጠቀሱት ቦታ “የኢትዮጵያ ስም ይቀየር” የሚል ጥያቄ እንደቀረበላቸው ተናግረዋል።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
😁 589❤ 269😡 126😭 124💔 60😱 25👏 17
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚጠበቅባቸውን መሥፈርቶች ካላሟሉ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ይደረጋሉ‼️
🗣 ትምህርት ሚንስቴር
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚጠበቅባቸውን መሥፈርቶች ማሟላት ካልቻሉ ሰፋ ያለ ሁለተኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የሚደረጉበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል የትምህርት ሚንስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ፡፡
ሚንስትሩ ይህን የተናገሩት ነሐሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም. በዳግም ምዝገባ አፈጻጸም ላይ የትምህርት ሚኒስቴርና የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን በጋራ ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ ነው።
ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በወቅቱ ለትምህርት ጥራት ከፍተኛ ቦታ እየሰጡ መሄድ ያስፈልጋል በሚል ከግል ተቋማት ጋር ከአራት ዓመታት ጀምሮ እየተሠራ እንደሆነ፣ ዳግም ምዝገባን በተመለከተም ባለፉት ሦስት ዓመታት ስለመሥፈርቱ የማሳወቅ ሥራ ሲከናወንና የማያሟሉ በዘርፉ መቀጠል እንደማይችሉ ሲገለጽ መቆየቱን አንስተዋል።
አያይዘውም መሰል ግምገማ በመንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይም እንደሚደረግ ጠቅሰው በዚሁ አሠራር መሠረት ይዘጋሉ ብለው የሚታሰቡት የግሎቹ ብቻ ሳይሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች ጭምር መሆናቸውን ጠቁመዋል።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
😁 212❤ 196👍 69👏 24😱 6😡 4🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ግድያ ለፈጸሙ ሰዎች የሞት ቅጣት እንዲጣል ጥሪ አቀረቡ‼️
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዋሽንግተን ዲሲ ግድያ ለፈጸሙ ሰዎች የሞት ቅጣት እንዲጣል የሚጠይቅ አዲስ መመሪያ ማስተላለፋቸው ተዘግቧል። ይህ እርምጃ በዋና ከተማው እየተበራከተ የመጣውን ወንጀል ለመግታት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
ትራምፕ የሞት ቅጣት ወንጀልን ለመከላከል ትልቅ ሚና እንዳለው በመግለጽ፣ ሌሎች የአሜሪካ ግዛቶችም ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ማበረታታታቸው ተገልጿል። ሆኖም ግን፣ ዋሽንግተን ዲሲ የሞት ቅጣትን ከበርካታ አሥርተ ዓመታት በፊት በማንሳቷ፣ ይህ የፕሬዚዳንቱ ጥያቄ በሕግ ባለሙያዎች ዘንድ ክርክርን ፈጥሯል።
የዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ባለሥልጣናት በበኩላቸው የፕሬዚዳንቱን የሞት ቅጣት ፍላጎት በመቃወም፣ የሞት ቅጣት ወንጀልን ለመቀነስ የሚረዳ መረጃ እንደሌለ እና በሕግም አስቸጋሪ እንደሆነ ይገልጻሉ። ይሁን እንጂ፣ የፌደራል አቃቤ ህግ ቢሮ በፕሬዚዳንቱ ትዕዛዝ መሰረት ይህንን ጉዳይ እንደሚያጤነው አስታውቋል።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 215👍 205👏 18😡 13🤝 12😁 10🔥 9
የእስራኤል አዲስ ጥቃት በየመን‼️
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ በየመን ሰነዓ የአየር ጥቃት መፈጸሙን ገልጸዋል።
በጥቃቱም የየመን ፕሬዚዳንት ቤተመንግሥትን፣ የአሳር እና የሂዛዝ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን እና ለውትድርና አገልግሎት ይውሉ ነበር የተባሉ የነዳጅ ማከማቻዎችን መምታቷን እስራኤል አስታውቃለች።
በእስራኤል የሚገኘው ካን ቲቪ እንደዘገበው በጥቃቱ 14 የጦር ጄቶች የተሳተፉ ሲሆን፤ 40 የሚሆኑ ቦምቦችን መጣላቸውን ገልጿል።
በጥቃቱ በሁቲ ዓማጺያን ቁጥጥር ስር ያለው የየመን ፔትሮሊየም ኩባንያ የነዳጅ ማደያ ጣቢያ ላይ አደጋ ደርሷል። በአደጋው የሰው ሕይወት መጥፋቱን የቦታውን ምንጮች ጠቅሶ ሽንዋ ዘግቧል።
በሰንዓ ከተፈፀመው ጥቃት በኋላ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱን ለማጥፋት እየሰሩ መሆኑን የየመን ሲቪል መከላከያ ባለስልጣን በመግለጫው አስታውቋል።
እስራኤል ከወራት በፊት በየመን ዋና አየር ማረፊያ ላይ ጥቃት መሰንዘሯ አይዘነጋም።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 270😭 52👍 50😱 21😡 14👏 8😁 4
Photo unavailableShow in Telegram
በመንግስት ፕሮጀክቶች ላይ ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ መባከኑን የኦዲት ሪፖርት አጋለጠ‼️
የፌዴራል ዋና ኦዲተር በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት መሠረት፣ በመንግሥት ፕሮጀክቶች ላይ ከፍተኛ የገንዘብ ብክነትና የሥርዓት ክፍተት መኖሩን አጋልጧል።
ሪፖርቱ እንደሚያሳየው በመንገድ ግንባታና በዩኒቨርሲቲ ፕሮጀክቶች ላይ ብቻ ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ገንዘብ መባከኑን አረጋግጧል።
ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው፣ ከ180 በላይ የመንገድ ፕሮጀክቶች ከመጀመሪያ በጀታቸው በተጨማሪ ከ13.26 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ወጪ አስከትለዋል። ይህም ከ75% በላይ የሚሆኑት ፕሮጀክቶች ከፍተኛ የሆነ ተጨማሪ ወጪ እንደደረሰባቸው ያሳያል።
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ባለሥልጣናት ለዚህ ችግር እንደምክንያት የካሳ ክፍያና የመሬት ወሰን ችግሮችን፣ የጸጥታ ሁኔታዎችን፣ የፋይናንስ ፍሰት መጓተትን፣ የዋጋ ግሽበትን እና የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ጠቅሰዋል።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 156😁 66😭 32😡 24👍 15👌 3🔥 1
00:54
Video unavailableShow in Telegram
👉 ግንባታቸው 90 በመቶ የተጠናቀቁ ቤቶችን ከ Dacord Real Estate
👉 ከ 623,000 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
👆 የከርሰ ምድር ውሃ,ሰፊ ቴራዛ ,የልጆች መጫወቻ,እንዲሁም በቂ የመኪና ማቆሚያ ያለው ዘመናዊ አፓርትመንት ከዳኮርድ ሪል እስቴት።
✔️ በ 4ወር እና በ 1ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚረከቧቸው
👉 ባለ1 መኝታ 80 ካሬ
👉 ባለ2 መኝት 110 ,118,128, ካሬ
👉 ባለ 3 መኝታ 135,148 ካሬ
👆ልብ ይበሉ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ብር
ይምጡ ማየት ማመን ነውና ቤትወን ገዝተው ይመለሳሉ።
ቤቶቹን ለመጎብኘት እንዲሁም ለበለጠ መረጃ
☎️ በ 0984323293 ወይም
☎️ በ 0919261500 ይደውሉ ።
ዳኮርድ በልዩነት የተገነባ !!!!!!!!!
19.75 MB
❤ 24😁 2
Photo unavailableShow in Telegram
የዲዩቲ ክፍያ በጀት እንዲይዙ መመሪያ ተሰጠ‼
የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ በክልሉ የሚገኙ ከተማ እና ወረዳ አስተዳደሮች ለጤና ባለሞያዎች የዲዩቲ ክፍያ በጀት እንዲይዙ መመሪያ ሰጠ።
በአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ አታላይ ጥላሁን ተፈርሞ በሁሉም በክልሉ ለሚገኙ ከተማ እና ወረዳ አስተዳደሮች የተላከው ሰርኩላር፣ በየደረጃው የሚገኙ አስተዳደሮች ለጤና ባለሞያዎች የትርፍ ሰአት ስራ (ዲዩቲ) ክፍያ በጀት እንዲይዙ መመሪያ መሰጠቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከደብዳቤው ተመልክቷል።
ደብዳቤው " የጤና ስራ በየትኛውም ሁኔታ የማይቋረጥ ስራ በመሆኑ ባለሙያዎች የዲዩቲ እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን በተመለከተ በመንግስት ጤና ተቋማት ለሚያገለግሉ የጤና ሙያተኞች የዲዩቲ እና የኃላፊነት አበል ክፍያ መወሰኛ የአማራ ብሔራዊ ክልል መስተዳድር ም/ቤት መመሪያ ቁጥር 20/2006 ዓ.ም በማጽደቅ ላለፉት 12 ዓመታት ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል " ሲል ያብራራል።
ነገር ግን አንዳንድ ወረዳዎች እና ከተሞች በጀት ሲይዙ እንደ ግዴታ ወጭ አለመያዛቸው እና አቆራርጠው መክፈላቸው ቅሬታ እና የመልካም አስተዳደር ችግር ፈጥሯል ብሏል።
ይህንን ችግር በመግለጽም መፍትሄ እንዲሰጥበት በክልሉ ጤና ቢሮ በደብዳቤ መጠየቁን ሰርኩላሩ ጠቅሷል።
ጥያቄውን የተቀበለው የገንዘብ ቢሮም ሁሉም ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር በበጀት ምደባ ወቅት የዲዩቲ በጀት የግዴታ ወጪ መሆኑን በመገንዘብ አስፈላጊውን የበጀት ምደባ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 189🎉 5🔥 2😭 1
Photo unavailableShow in Telegram
በናይጄሪያ በመስጅድ ላይ በተፈፀመ ጥቃት ከ50 በላይ ሰዎች ተገደሉ‼️
በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ካትሲና ግዛት አማኞች በመስጂድ ተገኝተው መንፈሳዊ ሥነ-ስርዓታቸው እየፈፀሙ በነበረበት ሰዓት ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።
ጥቃቱን በሞተር ሳይክል የመጡ ታጣቂዎች ተኩስ በመክፈት የፈጸሙት ሲሆን ከመስጅዱ በተጨማረ በአካባቢው በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ላይም ጥቃት አድርሰዋል ተብሏል።
በጥቃቱ 30 ሰዎች መገደላቸውን 20 ሰዎች ደግሞ በህይወት እያሉ መቃጠላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ሲገልፁ የአካባቢው ፖሊስ ጣልቃ ገብቶ በሁለት መንደሮች ላይ ሊፈፀም የነበረን ጥቃት አክሽፌያለሁ ብሏል።
በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ጥቃት በሚፈፀምባት ሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ በዚህኛው ጥቃት ህይወታቸው ካለፈው 50 ሰዎች በተጨማሪ 60 ሰዎች ታፍነው ተወስደዋል ተብሏል።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
❤ 148💔 132😭 127😁 14😱 12🔥 6👏 5
