en
Feedback
ETHIO-MEREJA®

ETHIO-MEREJA®

Open in Telegram

News & Media Company® USA : Washington Addisababa, Ethiopia🇪🇹 . Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja . ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!! 👉 @ethio_merejabot

Show more
2025 year in numberssnowflakes fon
card fon
110 179
Subscribers
-4824 hours
-3207 days
-1 32830 days
Posts Archive
Photo unavailableShow in Telegram
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከፍተኛ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ ትራምፕ ፑቲንን 'እብድ ነው' ሲሉ ተናገሩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሞስኮ በዩክሬን ላይ ያደረሰችውን ከባድ የአየር ላይ ጥቃትን ተከትሎ በሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ደስተኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል። ትራምፕ ባልተለመደ ተግሳጽ “ምን ነካው? ብዙ ሰዎችን እየገደለ ነው” ያሉ ሲሆን አክለውም ፑቲንን "ፍፁም እብድ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ቀደም ብለው ዋሽንግተን በቅርብ ጊዜ በሩሲያ ጥቃቶች ላይ የነበራት "ዝምታ" ፑቲንን የሚያበረታታ ነው ሲሉ በሞስኮ ላይ "ጠንካራ ጫና" -እንዲሁም ጥብቅ ማዕቀቦችን እንድትጥል አጥብቀው አሳስበዋል። ሩሲያ 367 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ሚሳኤሎችን በመተኮሷ በዩክሬን በአንድ ሌሊት ቢያንስ 12 ሰዎችን ስትገድል በደርዘን የሚቆጠሩ ደግሞ ቆስለዋል። ፑቲን በ 2022 ሙሉ ወረራ በዩክሬን ላይ ከጀመሩ ወዲህ በአንድ ሌሊት ውስጥ ከፍተኛው ጥቃት በትላንትናው እለት ፈፅመዋል።የአየር ሳይረን ማስጠንቀቂያ የሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሚሳኤሎች ጥቃት ሲፈፀም በበርካታ የዩክሬን ክልሎች ተሰምተዋል። በሰሜን ምስራቅ ካርኪቭ ከተማ አንድ ህፃንን ጨምሮ ቢያንስ ሶስት ሰዎች ቆስለዋል ሲሉ ከንቲባ ኢጆር ቴሬኮቭ ተናግረዋል። እሁድ እለት በኒው ጀርሲ ለጋዜጠኞች ትራምፕ ስለ ፑቲን ሲናገሩ “ለረጅም ጊዜ አውቀዋለሁ ፣ ሁል ጊዜም ከእርሱ ጋር ተስማምቼ ነበር ፣ ግን እሱ ሮኬቶችን ወደ ከተማዎች በመላክ ሰዎችን እየገደለ ነው ፣ እና በጭራሽ አልወደውም ። ” ብለዋል። ትራምፕ አሜሪካ በሩሲያ ላይ የምትጥለውን ማዕቀብ ለመጨመር እያሰቡ እንደሆነ ተጠይቀው ሲመልሱ “በፍፁም” ብለዋል።   T.me/ethio_mereja         ኢትዮ-መረጃ
Show all...
👍 53 12😁 8👏 2🤯 2😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
የእራኤል የገንዘብ እና የመከላከያ ሚኒስቴር ተጋጩ ሚኒስትሮቹ የተጋጩት በጋዛ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት የመከላከያ ሰራዊት ከተመደበለት በጀት በላይ ተጠቅሟል በሚል ነው። የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር በጋዛ ጦርነት ምክንያት የተመደበለትን በጀት ከልክ በላይ በማውጣቱ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ከፍተኛ ግጭት ውስጥ መግባታቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን የሆነው KAN ዘግቧል። ይህ የተፈጠረው በዝግ የፀጥታ ካቢኔ ስብሰባ፣ የመከላከያ ሚኒስቴር በዓመቱ የተመደበለትን ወጪ ከታቀደው ከ4 ነጥብ 17 ቢሊየን ዶላር በላይ ብልጫ እንዳለው ለመንግስት ባሳወቀበት ወቅት ነው። የፋይናንስ ሚኒስቴር እንደገለፀው በጋዛ ግጭቱ እስከ ቀጠለ ድረስ የበጀት ክፍተቱ በዓመቱ መጨረሻ ላይ ወደ 7 ቢሊዮን ዶላር ሊጠጋ እንደሚችል ካን ዘግቧል። በገንዘብ ሚኒስትሩ ባዛል ስሞትሪች እና በመከላከያ ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር መካከል ውጥረት ስለመንገሱም ተነግሯል ። ክርክሩ የፋይናንስ አስተዳደርን በሚመለከት የጋራ ውንጀላ ላይ ያተኮረ ነው ሲል ቲ አር ቲ ግሎባል ዘግቧል፡፡
Show all...
👍 42 4🤔 2🥰 1
አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አድማ እያደረጉ ካሉ የጤና ባለሙያዎች ጋር “በአስቸኳይ ድርድር እንዲጀምሩ” እና የታሰሩትን ሰዎች “ያለምንም ቅድመ ሁኔታ” እንዲፈቱ አሳሰበ።   የሥራ ማቆም አድማው በመላ ሀገሪቱ የታካሚዎችን የጤና አገልግሎት የማግኘት መብት “በእጅጉ ገድቧል” ሲል አስጠንቅቋል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ቡድን ዛሬ ግንቦት 15 ባወጣው መግለጫ፤ ለሁለተኛ ሳምንት እያተካሄደ ያለው አድማ “እጅግ አስፈላጊ የሆኑ የጤና አገልግሎቶችን ለማቅረብ ከፍተኛ መስተጓጎል” ፈጥሯል ብሏል። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ቲጌሬ ቻጉታህ፤ መንግስት “ቀውሱን የበለጠ ማራዘም የለበትም” ሲሉ ገልጸው፤ መንግስትም ሆነ የጤና ባለሙያዎች ይህንን አለመግባባት ለመፍታት በጋራ እና ገንቢ በሆነ ድርድር ላይ መሳተፍ እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል።በተጨማሪም አምነስቲ፤ “በሀኪሞቹ ላይ የሚደርሰውን መንገላታትና ማስፈራራት እንዲቆም” ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ከስራ ማቆም አድማው ጋር በተያያዘ የታሰሩ የጤና ሰራተኞች በሙሉ “ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ” በድጋሚ ጠይቋል። አክለውም፤“ባለስልጣናቱ ያልተፈቱ ጉዳዮችን ለመፍታት እና የጤና አገልግሎቶችን እንደገና ለማስጀመር በማሰብ አስቸኳይ ወደ ድርድር ጠረጴዛ መምጣት አለባቸው” ብለዋል።የአምነስቲ የስራ ማቆም አድማ ግንቦት 4 ከጀመረ ወዲህ በመላ ሀገሪቱ የታሰሩ የህክምና ሰራተኞች 212 መደርሱን የሚገልጽ ዝርዝር እንደተቀበለም ገልጿል። በድርጅቱ ቃለ መጠይቅ የተደረገባቸው “የቤተሰብ አባላት እና ጠበቆች” የህክምና ባለሙያዎቹ የታሰሩበት ምክንያት ሳይነገራቸው መያዛቸውን ተናግረዋል። ግለሰቦቹ፤ ፖሊስ የፍርድ ቤት ትእዛዝ ሳያቀርብ “የጦር መሳሪያና ፈንጂ ፍለጋ” ፍተሻ ማድረጉን እና የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ብቻ እንደተያዙ ተናግረዋል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል “በስራ ማቆም አድማው ላይ ያለተሳተፉት” ፓቶሎጂስተ ዶ/ር ማህሌት ጉሽ እንደሚገኙ ድርጅቱ ገልጿል። ዶ/ር ማህሌት በቅርቡ በቢቢሲ ፖድካስት ላይ ቀርባ ተሞክሮዋን ማካፈሏን ተከትሎ ከቀናት በኋላ በቁጥጥር ስር መዋሏ ተገልጿል። አምነስቲ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ ታስረው ከሚገኙ ቢያንስ 20 ከሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች መካከል አንዷ መሆኗን አሚነስቲ በመግለጫው ገልጿል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከትላንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ፤ ፖሊስ ከጤና ባለሙያዎች የስራ ማቆም አድማ ጋር በተያያዘ “በማኅበራዊ ሚዲያዎች ቅስቀሳ አድርገዋል፤ በሌሎች በሥራ ላይ በተገኙ ባልደረቦቻቸው ላይ ዛቻ እና ማስፈራራት አድርሰዋል” ያላቸውን የሕክምና ባለሙያዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገልጿል። ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ የጤና ባለሙያዎች እያደረጉ ካሉት የስራ ማቆም አድማ ጋር ተያይዞ፤ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ 47 የጤና ባለሙያዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።   የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በመግለጫው፤ የጤና ባለሙያዎቹን በቁጥጥር ስር ያዋለው፤ “ሰሞኑን የጤና ባለሙያዎች ያነሱትን የመብት ጥያቄ ሽፋን በማድረግ በሀገራችን ትርምስ እንዲፈጠር ከሚሠሩ ኃይሎች ጋር በማበር ሕገ ወጥ የሥራ ማቆም አድማ በማድረግ፣ በጤና ዘርፉ ላይ ሁከት በመፍጠር እና የታካሚዎችን ህይወት አደጋ ላይ በመጣል” በመጠርጠራቸው መሆኑን ገልጿል። የጤና ባለሙያዎቹን እስር በተመለከተ ቻጉታ፤ “ደመወዝ እና ምቹ የሥራ ሁኔታዎችን በመጠየቃቸው ቢያንስ 20 የጤና ባለሙያዎች መታሰራቸው አሳፋሪ እና በጣም አሳሳቢ ነው” ብለዋል።ድርጅቱ ባለሥልጣናት የህዝብ ጤና ኢንቨስትመንትን እንዲጨምሩ አሳስቧል። “መንግስት እንደ ጤና ላሉት ወሳኝ የህዝብ አገልግሎቶች ከፍተኛውን በጀት መመደብ አለበት፣ ይህም ከመንግስት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ግዴታዎች ጋር የሚስማማ ነው” ብሏል።   T.me/ethio_mereja         ኢትዮ-መረጃ
Show all...
👍 146 11😁 10👎 3🥰 3😱 2🤔 1
አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አድማ እያደረጉ ካሉ የጤና ባለሙያዎች ጋር “በአስቸኳይ ድርድር እንዲጀምሩ” እና የታሰሩትን ሰዎች “ያለምንም ቅድመ ሁኔታ” እንዲፈቱ አሳሰበ።   የሥራ ማቆም አድማው በመላ ሀገሪቱ የታካሚዎችን የጤና አገልግሎት የማግኘት መብት “በእጅጉ ገድቧል” ሲል አስጠንቅቋል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ቡድን ዛሬ ግንቦት 15 ባወጣው መግለጫ፤ ለሁለተኛ ሳምንት እያተካሄደ ያለው አድማ “እጅግ አስፈላጊ የሆኑ የጤና አገልግሎቶችን ለማቅረብ ከፍተኛ መስተጓጎል” ፈጥሯል ብሏል። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ቲጌሬ ቻጉታህ፤ መንግስት “ቀውሱን የበለጠ ማራዘም የለበትም” ሲሉ ገልጸው፤ መንግስትም ሆነ የጤና ባለሙያዎች ይህንን አለመግባባት ለመፍታት በጋራ እና ገንቢ በሆነ ድርድር ላይ መሳተፍ እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል።በተጨማሪም አምነስቲ፤ “በሀኪሞቹ ላይ የሚደርሰውን መንገላታትና ማስፈራራት እንዲቆም” ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ከስራ ማቆም አድማው ጋር በተያያዘ የታሰሩ የጤና ሰራተኞች በሙሉ “ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ” በድጋሚ ጠይቋል። አክለውም፤“ባለስልጣናቱ ያልተፈቱ ጉዳዮችን ለመፍታት እና የጤና አገልግሎቶችን እንደገና ለማስጀመር በማሰብ አስቸኳይ ወደ ድርድር ጠረጴዛ መምጣት አለባቸው” ብለዋል።የአምነስቲ የስራ ማቆም አድማ ግንቦት 4 ከጀመረ ወዲህ በመላ ሀገሪቱ የታሰሩ የህክምና ሰራተኞች 212 መደርሱን የሚገልጽ ዝርዝር እንደተቀበለም ገልጿል። በድርጅቱ ቃለ መጠይቅ የተደረገባቸው “የቤተሰብ አባላት እና ጠበቆች” የህክምና ባለሙያዎቹ የታሰሩበት ምክንያት ሳይነገራቸው መያዛቸውን ተናግረዋል። ግለሰቦቹ፤ ፖሊስ የፍርድ ቤት ትእዛዝ ሳያቀርብ “የጦር መሳሪያና ፈንጂ ፍለጋ” ፍተሻ ማድረጉን እና የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ብቻ እንደተያዙ ተናግረዋል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል “በስራ ማቆም አድማው ላይ ያለተሳተፉት” ፓቶሎጂስተ ዶ/ር ማህሌት ጉሽ እንደሚገኙ ድርጅቱ ገልጿል። ዶ/ር ማህሌት በቅርቡ በቢቢሲ ፖድካስት ላይ ቀርባ ተሞክሮዋን ማካፈሏን ተከትሎ ከቀናት በኋላ በቁጥጥር ስር መዋሏ ተገልጿል። አምነስቲ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ ታስረው ከሚገኙ ቢያንስ 20 ከሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች መካከል አንዷ መሆኗን አሚነስቲ በመግለጫው ገልጿል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከትላንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ፤ ፖሊስ ከጤና ባለሙያዎች የስራ ማቆም አድማ ጋር በተያያዘ “በማኅበራዊ ሚዲያዎች ቅስቀሳ አድርገዋል፤ በሌሎች በሥራ ላይ በተገኙ ባልደረቦቻቸው ላይ ዛቻ እና ማስፈራራት አድርሰዋል” ያላቸውን የሕክምና ባለሙያዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገልጿል። ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ የጤና ባለሙያዎች እያደረጉ ካሉት የስራ ማቆም አድማ ጋር ተያይዞ፤ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ 47 የጤና ባለሙያዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።   የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በመግለጫው፤ የጤና ባለሙያዎቹን በቁጥጥር ስር ያዋለው፤ “ሰሞኑን የጤና ባለሙያዎች ያነሱትን የመብት ጥያቄ ሽፋን በማድረግ በሀገራችን ትርምስ እንዲፈጠር ከሚሠሩ ኃይሎች ጋር በማበር ሕገ ወጥ የሥራ ማቆም አድማ በማድረግ፣ በጤና ዘርፉ ላይ ሁከት በመፍጠር እና የታካሚዎችን ህይወት አደጋ ላይ በመጣል” በመጠርጠራቸው መሆኑን ገልጿል። የጤና ባለሙያዎቹን እስር በተመለከተ ቻጉታ፤ “ደመወዝ እና ምቹ የሥራ ሁኔታዎችን በመጠየቃቸው ቢያንስ 20 የጤና ባለሙያዎች መታሰራቸው አሳፋሪ እና በጣም አሳሳቢ ነው” ብለዋል።ድርጅቱ ባለሥልጣናት የህዝብ ጤና ኢንቨስትመንትን እንዲጨምሩ አሳስቧል። “መንግስት እንደ ጤና ላሉት ወሳኝ የህዝብ አገልግሎቶች ከፍተኛውን በጀት መመደብ አለበት፣ ይህም ከመንግስት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ግዴታዎች ጋር የሚስማማ ነው” ብሏል።
Show all...
የሞት ቅጣት❗️ በህፃን ባምላክ ግርማ ላይ ግድያ የፈፀሙት እናቷ እና የእንጀራ አባቷ በሞት እንዲቀጡ ተወሰነ የቅጣት ዉሳኔዉን ያሳለፈዉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ 4ኛ የወንጀል ጉዳዮች ችሎት ነዉ፡፡ ተከሳሾቹ ሀና በየነ እና ብሩክ አለሙ ሰውን በጋራ በመሆን ለመግደል በማሰብ ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም በግምት ከለሊቱ 5 ሰዓት በድሬዳዋ ከተማ 04 ቀበሌ ልዩ ቦታው ካባ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የመኖርያ ቤታቸው ውስጥ የ1ኛ ተከሳሽ ልጅ እና የ2ኛ ተከሳሽ የእንጀራ ልጅ የሆነችውን የግል ተበዳይ ህፃን ባምላክ/ኬብሮን ግርማን ስለታማ ባልሆነ ቁስ ባደረሱባት ድብደባ የግንባሯን የግራ ጎን 6በ4 ሴ.ሜ፣ በግራ የዐይኗ ዐቃፊ ሶኬት ላይ 2በ1 ሴ.ሜ፣ በግራ ጉንጯ ላይ 6 ሴ.ሜ፣ በላይ እና በታችኛው ከንፍሯ ላይ 0.5በ0.5 ሴ.ሜ፣ በቀኝ ክንዷ ላይ 1በ0.5 ሴ.ሜ፣ በግራ ክንዷ የእጅ አምባር የፊተኛው ክፍል ላይ 1.5በ0.5 ሴ.ሜ፣ የታችኛው ከንፈር 3በ1ሴ.ሜ፣ በግራ ጀርባ የታችኛው ክፍል ላይ 5በ4 ሴ.ሜ ስፋት ያላቸው የመቁሰል፣ የመበለዝ እንዲሁም መጋጋጥ ጉዳቶች ውጫዊ አካሏ ላይ እንዲኖርባት በማድረጋቸው ምክንያት ከውስጣዊ አካሏ፣ አንጎል፣ ልብ፣ ጉበት፣ ጣፊያ፣ ቆሽት፣ ኩላሊት፣ የሽንት ማጠራቀሚያ ፊኛዋ ከመለስለሱ በተጨማሪ በማፈን አየር እንድታጣና ህይወቷ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲያልፍ ያደረጉ በመሆኑ ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት ከባድ የግድያ ወንጀል ተከሰዋል፡፡ በሁለተኛ ክስ በ1996 የወጣውን የኢፌዴሪ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1) ሀ እና 375 (ሀ) ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ ተከሳሾች በጋራ በመሆን የሌላውን ጥቅም ወይም መብት ለመጉዳት ለራሳቸው ወይም ለሌላ ሰው ተገቢ ያልሆነ ማንኛውንም መብት ወይም ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት በማሰብ ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም የግል ተበዳይ አባት እውነተኛ ወላጅ አባቷ አቶ ግርማ አበጋዝ ሳይሆን 2ኛ ተከሳሽ እንደሆነ ሀሰተኛ የዲኤንኤ ማስረጃ በማሰራት ለፍርድ ቤት ሕጋዊ ክርክር ለማስረጃነት ለመጠቀም እንዲሁም የተለያዩ ሰዎችን ለማሳመን ያዘጋጁት በመሆናቸው ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት በግዙፍ የሚፈፀም ሀሰተኛ ሰነዶችን መፍጠር ወንጀል ተከሰዋል፡፡ በሶስተኛ ክስ በ1996 የወጣውን የኢፌዴሪ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1) ሀ እና 585(2) (ሀ) ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ ተከሳሾች በጋራ በመሆን ሕግን ተቃራኒ በሆነ መንገድ ወይም ያለ ሕጋዊ ትዕዛዝ የግል ተበዳይን ከመስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ግድያ እስከተፈጸመባት ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ወደ ወላጅ አባቷ እንዳትሄድ፣ በፍርድ በወንድሟ ላይ አልመሰክርም እንዳትላቸው ለማባበል እና ለማስፈራራት፤ ታማለች ጸበል እያስጠመቅናት ነው በማለት ትምህርት እንድታቋርጥ አድርገው ከሰው እንዳትገኛኝ ቤት ውስጥ ቆልፈውባት ያስቀመጧት በመሆኑ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈጸሙት ከሕግ ውጪ ሰዎችን ይዞ ማቆየት ወንጀል ተከሰዋል፡፡ በአራተኛ ክስ ደግሞ በ1996 የወጣውን የኢፌዴሪ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) ሀ እና 590(1) (ሐ) ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ ተከሳሾች በጋራ በመሆን በሟች ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ ሻወር በምትወስድበት ጊዜ ቪድዮ ቀርፀው ከግንቦት 2014 ዓ.ም ህይወቷ እስካለፈበት ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እኛ የምንልሽን የማትሰሚ እና ከእኛ ጋር አርፈሽ ካልተቀመጥሽ፣ አባቴ እና ወንድሜ ጋር እሄዳለሁ ብለሽ የምታስቸግሪን ከሆነ ይሄንን ቪዲዮ ነው ለህዝብ አሳይተን ጉድሽን የምናፈላው እያሉ ሊጠብቋት፣ ሊንከባከቧት እና ፍቅር ሊሰጧት ሲገባቸው የተለየ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በማስፈራራት በህፃኗ ነፃነት ጣልቃ ገብተው ከወላጅ አባቷ እና ከወንድሟ ጋር እንዳትገናኝ ያደረጓት በመሆኑ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈጸሙት ከባድ የማስገደድ ወንጀል ተከሰዋል፡፡ ተከሳሾቹ በተከሰሱባቸዉ አራቱም ክሶች ጥፋተኛ መሆናቸዉ በዐቃቤ ሕግ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ በመረጋገጡ ችሎቱ በዛሬው ውሎ ተከሳሾቹ በሞት እንዲቀጡ ወስኗል፡፡   T.me/ethio_mereja         ኢትዮ-መረጃ
Show all...
👍 160👏 23 13🤯 5😱 3👎 2🥰 1
የሞት ቅጣት❗️ በህፃን ባምላክ ግርማ ላይ ግድያ የፈፀሙት እናቷ እና የእንጀራ አባቷ በሞት እንዲቀጡ ተወሰነ የቅጣት ዉሳኔዉን ያሳለፈዉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ 4ኛ የወንጀል ጉዳዮች ችሎት ነዉ፡፡ ተከሳሾቹ ሀና በየነ እና ብሩክ አለሙ ሰውን በጋራ በመሆን ለመግደል በማሰብ ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም በግምት ከለሊቱ 5 ሰዓት በድሬዳዋ ከተማ 04 ቀበሌ ልዩ ቦታው ካባ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የመኖርያ ቤታቸው ውስጥ የ1ኛ ተከሳሽ ልጅ እና የ2ኛ ተከሳሽ የእንጀራ ልጅ የሆነችውን የግል ተበዳይ ህፃን ባምላክ/ኬብሮን ግርማን ስለታማ ባልሆነ ቁስ ባደረሱባት ድብደባ የግንባሯን የግራ ጎን 6በ4 ሴ.ሜ፣ በግራ የዐይኗ ዐቃፊ ሶኬት ላይ 2በ1 ሴ.ሜ፣ በግራ ጉንጯ ላይ 6 ሴ.ሜ፣ በላይ እና በታችኛው ከንፍሯ ላይ 0.5በ0.5 ሴ.ሜ፣ በቀኝ ክንዷ ላይ 1በ0.5 ሴ.ሜ፣ በግራ ክንዷ የእጅ አምባር የፊተኛው ክፍል ላይ 1.5በ0.5 ሴ.ሜ፣ የታችኛው ከንፈር 3በ1ሴ.ሜ፣ በግራ ጀርባ የታችኛው ክፍል ላይ 5በ4 ሴ.ሜ ስፋት ያላቸው የመቁሰል፣ የመበለዝ እንዲሁም መጋጋጥ ጉዳቶች ውጫዊ አካሏ ላይ እንዲኖርባት በማድረጋቸው ምክንያት ከውስጣዊ አካሏ፣ አንጎል፣ ልብ፣ ጉበት፣ ጣፊያ፣ ቆሽት፣ ኩላሊት፣ የሽንት ማጠራቀሚያ ፊኛዋ ከመለስለሱ በተጨማሪ በማፈን አየር እንድታጣና ህይወቷ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲያልፍ ያደረጉ በመሆኑ ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት ከባድ የግድያ ወንጀል ተከሰዋል፡፡ በሁለተኛ ክስ በ1996 የወጣውን የኢፌዴሪ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1) ሀ እና 375 (ሀ) ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ ተከሳሾች በጋራ በመሆን የሌላውን ጥቅም ወይም መብት ለመጉዳት ለራሳቸው ወይም ለሌላ ሰው ተገቢ ያልሆነ ማንኛውንም መብት ወይም ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት በማሰብ ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም የግል ተበዳይ አባት እውነተኛ ወላጅ አባቷ አቶ ግርማ አበጋዝ ሳይሆን 2ኛ ተከሳሽ እንደሆነ ሀሰተኛ የዲኤንኤ ማስረጃ በማሰራት ለፍርድ ቤት ሕጋዊ ክርክር ለማስረጃነት ለመጠቀም እንዲሁም የተለያዩ ሰዎችን ለማሳመን ያዘጋጁት በመሆናቸው ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት በግዙፍ የሚፈፀም ሀሰተኛ ሰነዶችን መፍጠር ወንጀል ተከሰዋል፡፡ በሶስተኛ ክስ በ1996 የወጣውን የኢፌዴሪ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1) ሀ እና 585(2) (ሀ) ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ ተከሳሾች በጋራ በመሆን ሕግን ተቃራኒ በሆነ መንገድ ወይም ያለ ሕጋዊ ትዕዛዝ የግል ተበዳይን ከመስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ግድያ እስከተፈጸመባት ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ወደ ወላጅ አባቷ እንዳትሄድ፣ በፍርድ በወንድሟ ላይ አልመሰክርም እንዳትላቸው ለማባበል እና ለማስፈራራት፤ ታማለች ጸበል እያስጠመቅናት ነው በማለት ትምህርት እንድታቋርጥ አድርገው ከሰው እንዳትገኛኝ ቤት ውስጥ ቆልፈውባት ያስቀመጧት በመሆኑ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈጸሙት ከሕግ ውጪ ሰዎችን ይዞ ማቆየት ወንጀል ተከሰዋል፡፡ በአራተኛ ክስ ደግሞ በ1996 የወጣውን የኢፌዴሪ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) ሀ እና 590(1) (ሐ) ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ ተከሳሾች በጋራ በመሆን በሟች ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ ሻወር በምትወስድበት ጊዜ ቪድዮ ቀርፀው ከግንቦት 2014 ዓ.ም ህይወቷ እስካለፈበት ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እኛ የምንልሽን የማትሰሚ እና ከእኛ ጋር አርፈሽ ካልተቀመጥሽ፣ አባቴ እና ወንድሜ ጋር እሄዳለሁ ብለሽ የምታስቸግሪን ከሆነ ይሄንን ቪዲዮ ነው ለህዝብ አሳይተን ጉድሽን የምናፈላው እያሉ ሊጠብቋት፣ ሊንከባከቧት እና ፍቅር ሊሰጧት ሲገባቸው የተለየ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በማስፈራራት በህፃኗ ነፃነት ጣልቃ ገብተው ከወላጅ አባቷ እና ከወንድሟ ጋር እንዳትገናኝ ያደረጓት በመሆኑ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈጸሙት ከባድ የማስገደድ ወንጀል ተከሰዋል፡፡ ተከሳሾቹ በተከሰሱባቸዉ አራቱም ክሶች ጥፋተኛ መሆናቸዉ በዐቃቤ ሕግ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ በመረጋገጡ ችሎቱ በዛሬው ውሎ ተከሳሾቹ በሞት እንዲቀጡ ወስኗል፡፡
Show all...
👍 49🤔 4 1
👍 8 6😱 4
Photo unavailableShow in Telegram
#ቴምር ሪልስቴት ⚠️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣናቸው ቤቶቾ እና ሱቆች ‼️ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ          👉1 መኝታ 66ካሬ=          10% ቅድመ ክፍያ 693,000ብር          ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር          👉2መኝታ 71ካሬ         10%ቅድመ ክፍያ 745,500ብር         ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር          👉2መኝታ 93ካሬ=        10% ቅድመ ክፍያ 976,500ብር        ሙሉ ክፍያ 9,765,000ብር         👉3መኝታ 130ካሬ       10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር       ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር         👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው         የሚጨርሱት         👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል ‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ  👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ 👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ 👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ 👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ 👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል 👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ ለበለጠ መረጃ ይደውሉ        👇👇👇👇👇👇      +251939770177      +251996856273 https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Show all...
👍 39 4🤯 2
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ከዛሬ ጧት ጀምሮ ወደ ሙሉ የሥራ ማቆም አድማ መሸጋገራቸውን የአድማው አስተባባሪዎች አስታውቀዋል። በበርካታ ሆስፒታሎች አገልግሎት መቋረጡንም አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል። በሌላ በኩል፣ የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዮናታን ዳኘው ዛሬ ከእስር እንደተፈታ ተሠምቷል። በተያያዘ፣ በጤና ባለሙያዎች የሥራ ማቆም አድማ ዙሪያ ድምጹን አጥፍቶ የቆየው የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር፣ መንግሥት ለሐኪሞች የደመወዝ ማነስ፣ የጥቅማጥቅምና የሥራ ቦታ ደኅንነት ጥያቄዎች አፋጣኝ መፍትሔ እንዲፈልግ፣ የታሠሩ የጤና ባለሞያዎች እንዲፈቱና ወደሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ እንዲደረግ በጉዳዩ ዙሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ማኅበሩ፣ ችግሩ ወደተባባሰ ደረጃ ከመድረሱ በፊት የጤና ሚንስቴርና ባለድርሻ አካላት አፋጣኝ ውይይቶችን እንዲያካሂዱም ጥሪ አቅርቧል። የአድማ አስተባባሪዎች ግን፣ ማኅበሩ ለአባላቱ ጥቅም አልቆመም በማለት የማኅበሩ አባላት እውቅና እንዲነፍጉት የሚጠይቅ ዘመቻ ጀምረዋል።   T.me/ethio_mereja         ኢትዮ-መረጃ
Show all...
👍 164 24😢 7🥰 5👏 5👎 1
🕯"በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ግልግል በለስ ከተማ ዛሬ ረፋድ በደረሰው አደጋ እስካሁን ባለው መረጃ 19 ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን 13 ከባድ ጉዳት መድረሱን የግልግል በለስ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ! ስካቫተር (ማሽን) ጭኖ መነሻዉን ቻግኒ ከተማ በማድረግ ወደ ዐባይ ግድብ አቅጣጫ ሲጓዝ የነበረው ተሳቢ ተሽከርካሪ ፍሬን በጥሶ መንገድ በመሳት የሕዝብ መዝናኛ ሆቴል ላይ በመውጣቱ ነው አደጋው የደረሰው። በአደጋዉ እስካሁን የ19 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 13 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል። የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን ከ19 ሟቾቹ መካከል 17 ወንዶች ሁለቱ ደግሞ ሴቶች እንደሆኑ አመልክቷል። 13 ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ከነዚችም ውስጥ 11ዱ ወንዶች ሁለቱ ሴቶች እንደሆኑ አብራርቷል። ፖሊስ " መኪናው መንገድ ስቶ ቤት ውስጥ ገብቶ ነው አደጋው የደረሰው ሹፌሩ መሪ እምቢ ብሎት ነው " ብሏል። የከተማው ኮሚዩኒኬሽን መምሪያም በአደጋው የ19 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ 13ቱ ሰዎች ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግሯል። ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ምን ያክል ሰዎች እንደሆኑ ገና ቁጥራዊ መረጃው እንዳልተለየ ገልጾ፣ " ገና አሁን ነው ሰው እየወጣ ያለው " ብሏል።የአደጋውን መንስኤ ስንጠይቀውም፣ " የቴክኒክ ችግር ነው፤ ከኬላ ጀምሮ ፍሬን እምቢ ብሎት ነው የመጣው " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
Show all...
👍 58😢 29 12😱 10👎 5
በሰይፉ የዩትዩብ ቻናል ሲተላለፍ የነበረው የመቄዶንያ የገቢ ማሰባሰብያ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በማሰባሰብ ተጠናቀቀ፡፡ ከየካቲት 01 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሰይፉ በኢቢኤስ እና በሰይፉ ሾው ዩቲዩብ ቻናል ላይ እየተደረገ በቆየው የቀጥታ ስርጭት የገቢ ማሰባሰብያ መርሃ ግብር ላይ የመጀመሪያው ዙር የገቢ ማሰባሰብ የቀጥታ ስርጭት ግቡን በማሳካት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በማሰባሰብ በይፋ ተጠናቀቀ፡፡ መቄዶንያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል  በአዲስ አበባ እያስገነባ ለሚገኘው የአረጋውያን መኖሪያና ዘመናዊ ሆስፒታል አጠቃላይ የፊኒሺንግ ስራውን ለማጠናቀቅ 5 ቢሊዮን ብር  እንደሚያስፈልግ በመግለፅ ከየካቲት 01 ቀን 2017  ጀምሮ የመጀመሪያ ዙር የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት 1 ቢሊየን ብር ለማሰባሰብ ዕቅድ በመያዝ በseifu on ebs እና በ Seifu Show ዩቱብ ቻናል ላይ በመጀመር ላለፉት ሶስት ወራት (90 ቀናት) በቆየው ገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም ላይ የታሰበውን እቅድ በማሳካት አጠቃላይ በገንዘብ እና በአይነት ከ 1 ቢሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ በሰይፉ ዩቱዩብ ቻናል የተደረገው የመጀመሪያ ዙር የገቢ ማሰባሰብ ግንቦት 01 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ተጠናቋል፡፡ የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ ላለፉት ሶስት ወራት ሲደረግ በቆየው ዝግጅት ላይ የተሳተፉትን በሙሉ በማመስገን ለዚህ ዝግጅት ዋናውን ሚና ሃላፊነት በመውሰድ የ1 ቢሊየን ብር ግብ እንዲሳካ ላደረገው ለሰይፉ ፋንታሁን ምስጋና በማቅረብ የምስጋና የምስክር ወረቀት የተበረከተ ሲሆን እንዲሁም በመቄዶኒያ በሚገኙ ተረጂዎች በእጅ ጥበብ የተሰራ ጋቢ ለሰይፉ ፋንታሁን እና ለአርቲስት ይገረም ደጀኔ ያለበሱ ሲሆን በአረጋውያኑ ምርቃት በመታጀብም በሰይፉ ፋንታሁን ምስል የተቀረፀ ምስለ ቅርፅ በስጦታ አበርክተዋል፡፡
Show all...
60👍 48👏 10🥰 3👎 2😁 2
ክሪስታል ፓላስ ማንችስተር ሲቲን በማሸነፍ የኤፍ ኤ ዋንጫ አሸነፈ በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስ ማንችስተር ሲቲን 1 ለ 0 በማሸነፍ የኤፍ ኤ ዋንጫን ማሸነፍ ችሏል፡፡ በግዙፉ ዌምብሌይ ስታዲየም በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ኤዜ በ17ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ብቸኛ ግብ ክሪስታል ፓላስን ባለድል አድርጋለች፡፡ በፍጻሜው ጨዋታ የፔፕ ጓርዲዮላን ቡድን የረቱት ክሪስታል ፓላሶችም በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የኤፍኤ ዋንጫን ማሳካት ችለዋል፡፡
Show all...
👍 93 13👏 6👎 5
Photo unavailableShow in Telegram
#ከቴምር ሪልስቴት 🎯🎯7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት እና ሱቅ ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው  👉2መኝታ 84ካሬ 5,392,800ብር ሙሉ ክፍያ 👉2መኝታ 94ካሬ 6,034,800ብር ሙሉ ክፍያ 👉3መኝታ 106ካሬ 6,869,400ብርሙሉክፍያ 👉3መኝታ 125ካሬ 8,025,000ብር ሙሉ ክፍያ ‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ  👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ 👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ 👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ 👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ 👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል 👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ ለበለጠ መረጃ ይደውሉ        👇👇👇👇👇👇      +251939770177      +251996856273 https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Show all...
👍 15
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ከፍተኛው ተከፋይ ስፖርተኛ ሆነ የእግር ኳሱ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ2025 ከ275 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ በማግኘት የዓለም ከፍተኛው ተከፋይ ስፖርተኛ መሆን ችሏል። ለሳዑዲዉ ክለብ አልናስር እየተጫወተ የሚገኘው ሮናልዶ ከስፖንሰር ሺፕ እና ከደሞዝ ጥቅማጥቅሞች ያገኘው ገቢ ከዓለም ቀዳሚው ስፖርተኛ አድርጎታል። ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዓለም ከፍተኛው ተከፋይ ስፖርተኛ ሲሆን ይህ ለ3ኛ ተከታታይ ዓመታት መሆን ፎርብስ ዘግቧል። የቅርጫት ኳሱ ኮከብ ስቴፈን ከሪ በ 156 ሚሊዮን ዶላር ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ፤ ብሪታንያዊው ቦክሰኛ ታይሰን ፉሪ በ146 ሚሊዮን ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ ሌላኛው የእግር ኳስ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ 135 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማግኘት 5ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡ እንዲሁም ሌላኛው የእግር ኳስ ተጫዋቾች ካሪም ቤንዜማ 104 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማግኘት 8ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ተጫዋች ሆኗል።   T.me/ethio_mereja         ኢትዮ-መረጃ
Show all...
👍 86 20🤔 5😢 2👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
"ሁሉን የሚያግባባ ነገር ፈልጉና ችግሮችን በሰላማዊ ውይይት ፍቱ" - ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተጀምሯል። የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ መጀመሩን አስመልክቶ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም "ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ልማትና ዕድገት እናሻግራለን ብላችሁ እየደከማችሁ ያላችሁ ወገኖቻችን እባካችሁ መለስ ብላችሁ እናታችሁ የተንገላታችበትን እዩና በቃ በሉ" ብለዋል። "ሁሉን የሚያግባባ ነገር ፈልጉና ችግሮችን በሰላማዊ ውይይት ፍቱ" ያሉ ሲሆን፤ "በዚህ ኣማራጭ እናት ሀገር እፎይታ እንድታገኝ ኣድርጉ፤ ይህንም ለውድ እናት የሚደረግ ካሣ ኣድርጋችሁ ውሰዱት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ መልእክትና ጥሪም ይህ ነው" ብለዋል። ከሰላም እጦት የተነሣ በእጅጉ እየተጎዳ ያለውን ሕዝባችን ሰላምና ፍትሕ እንዲያገኝ በጸሎትም በትምህርትም፣ በምክርም መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል። "የኢትዮጵያ ህዝብ ለእንግልት እየተዳረገ ያለውም የሌሎች እጅ ባይለየውም በዋናነት በገዛ ልጆቹ ነው" ያሉት ፓትርያርኩ፤ "እናት በገዛ ልጆቿ ስትንገላታ ማየት እጅግ ኣሳዛኝ ነገር ነው፤ እንደዚህ ያለው ነገር በደንብ ያልታሰበበት ኣካሄድ በብስለትና በንስሓ ማስተካከል አሸናፊነትን እንጂ ተሸናፊነትን አያሳይምና እንዲታሰብበት እንመክራለን" ብለዋል።
Show all...
👍 152 25👎 2🤯 2🥰 1😱 1
00:18
Video unavailableShow in Telegram
#ቴምር ሪልስቴት ‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው ሱቅ ‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ  👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ 👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ 👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ 👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ 👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል 👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ ለበለጠ መረጃ ይደውሉ        👇👇👇👇👇👇      +251939770177      +251996856273 https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant WhatsApp. https://wa.me/251939770177 Telegram :@KalTemerRealEstate
Show all...
1.01 MB
👍 28 2😁 2🥰 1🤔 1
ሕወሓት ከፖለቲካ ፓርቲነት ተሠረዘ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ከፖለቲካ ፓርቲነት መሠረዙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከፖለቲካ ፓርቲነት መሠረዙን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል ቀጥሎ ቀርቧል፡-
Show all...
👍 66👎 16 8👏 3😱 3🥰 1
ጤና ባለሙያዎች!! የደሞዝ እና ጥቅማ ጥቅም ጥያቄ በማንሳት ለመንግሥት የሰላሳ ቀናት የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ጊዜ ሰጥተው የነበሩት የጤና ባለሙያዎች ምላሽ ባለማግኘታቸው ከፊል የሥራ ማቆም አድማ መምታታቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ። ባለሙያዎች ከጥቂት "የተመረጡ የሕክምና ክፍሎች" ውጪ ያሉ ክፍሎች ከዛሬ ግንቦት 5/2017 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራ ማቆማቸውን ገልፀዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው አምስት በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ ባለሙያዎች ከድንገተኛ፣ ከማዋለጃ፣ ከፅኑ ሕሙማን እንዲሁም ከድንገተኛ ቀዶ ሕክምና ክፍሎች ውጪ ያሉ የሕክምና ተቋማት ክፍሎች አገልግሎቶች ማቋረጣቸውን ተናግረዋል።
Show all...
👍 145 11🤔 6👎 2
በወላይታ ዞን ሰርጉን አቋርጦ ቀዶ ህክምና የሰራው ሐኪም አድናቆት እየተቸረው ይገኛል ዶ/ር ብሩክ ወይሻ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በወላይታ ዞን፣ በበሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ነው። ወጣቱ ሐኪም ታዲያ የራሱን የሰርግ ዝግጅት አቋርጦ ወጥቶ ታካሚን ቀዶ ጥገና በማድረግ ሕይወት የማዳኑ ጉዳይ የአካባቢው ነዋሪዎች መነጋገሪያ ሆኗል። የሰርጉ ዝግጅት ከነበረበት ከ40 በላይ ኪሎ ሜትር በላይ ወደ ሆስፒታሉ ተጉዞ ቀዶ ጥገና በማድረግ የሰው ሕይወት ማዳን መቻሉን ዶ/ር ብሩክ ለኢቢሲ ተናግሯል። ወጣቱ ሐኪም የተሟላ የቀዶ ጥገና ሕክምና ገና በቅርቡ በጀመረው ሆስፒታል የመጀመሪያው ስፔሻሊስት ቅጥር ሲሆን፤ በሆስፒታሉ ሥራ ከጀመረም ገና ሶስት ሳምንቱ ነው። በቀዶ ጥገና የታከመው በሽታ ከጨጓራ ሕመም ጋር ተያይዞ የሚከሰትና ሕይወትን አደጋ ላይ የሚጥል ሲሆን፤ ታካሚው በሰዓቱ ሕክምና ባይደረግለት ኖሮ ሕይወቱ ሊያልፍ ይችል እንደነበርም ነው የተገለፀው። ቀዶ ጥገና የሕክምና ባለሙያዎች የቡድን ሥራ ነው ያለው ዶ/ር ብሩክ፤ በአጠቃላይ በቀዶ ጥገናው ለተሳተፈው የሕክምና ቡድን ምስጋና አቅርቧል ። የቀዶ ጥገና ሕክምናው የተደረገለት የ40 ዓመት ታካሚ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ የገለፀው ዶ/ር ብሩክ፤ ከዚህ የሚበልጥ ደስታ የለም ብሏል። በሙያዬ የፈፀምኩትን ቃለ-መሃላ እና የገባሁትን ቃል-ኪዳን መቼም ቢሆን አላጥፍም፤ ለሙያው የሚገባውን ክብር እሰጣለሁ ብሏል ወጣቱ ሐኪም ብሩክ ወይሻ።(Via ETV)
Show all...
👍 296👏 34🙏 27 26🥰 10🤔 5
ማንቼስተር ዩናይትድ 17ኛ ሽንፈቱን አስተናገደ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ በ2024/25 የውድድር ዘመን 17ኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል፡፡ በኦልድትራፎርድ ዌስትሃም ዩናይትድን ያስተናገደው ዩናይትድ ጃሮድ ቦውን እና ቶማስ ሱቼክ ባስቆጠሯቸው ግቦች 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡ በሌሎች የሊጉ 36ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላስ ቶተንሃምን 2 ለ 0 ሲያሸነፍ ኖቲንግሃም ፎረስት ከሌስተር ሲቲ 2 አቻ ተለያተዋል፡፡ በሌሎች ጨዋታዎች ኒውካስትል ዩናይትድ ቼልሲን 2 ለ 0 ሲረታ፤ ቶተነሃም በሜዳው በክሪስታል ፓላስ 2 ለ 0 ተሸንፏል፡፡ ኖቲንግሃም ፎረስት እና ሌስተር ሲቲ ያደረጉት ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።
Show all...
👍 58😁 23👎 3😱 3 2👏 2