ETHIO-MEREJA®
Open in Telegram
News & Media Company® USA : Washington Addisababa, Ethiopia🇪🇹 . Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja . ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!! 👉 @ethio_merejabot ✔
Show more2025 year in numbers

110 245
Subscribers
-5724 hours
-3197 days
-1 31530 days
Posts Archive
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ግብፅን ለፊፋ ከሰሰ!
ፌደሬሽኑ አመሻሹን ባወጣው መግለጫ በ2 ጉዳዮች ላይ ለፊፋ ቅሬታውን አስገብቷል ።
የግብፅ ደጋፊዎች ሌዘር ፖይንተር (ግብ ጠባቂው ላይ እና በሌሎች ) ተጨዋቾችም ላይ በማብራት በፊፋ የተከለከለ ተግባር መፈፀሙን አንቀፅ ጠቅሶ ቅሬታ አስገብቷል ።
እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር በተዘመረበት ወቅት ደጋፊዎች ያልተገባ ነገር መፈፀማቸውን ጠቅሶ እርምት እንዲወስድ ሲል በዋና ስራአስፈፃሚው አቶ ባህሩ ጥላሁን ለፊፋ የተፃፈው ደብዳቤ ያመለክታል ።
❤ 122👏 22👍 17🤔 11😁 8
Photo unavailableShow in Telegram
ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ እስካሁን 233 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጓል ተባለ
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረ ጀምሮ ለግንባታወሰ እስካሁን 233 ቢሊየን ብር ገንዘብ ወጪ እንደተደረገበት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ዛሬ ቅዳሜ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ለግንባታው ፈሰስ ከተደረገው ጠቅላላ ወጪ 91 በመቶው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘ ነው።
"ግንባታው ምንም አይነት የጥራት ጉድለት እንዳይኖርበት ተደርጎ የተሰራ ነው" ያሉት ኃላፊው "የአንድ ወገን ተጠቃሚነት ከዚህ በኋላ ሙሉ በሙሉ አክትሟል ወደሚል ምዕራፍ ተሸጋግረናል" ሲሉም በግብጽ በኩል የሚነሳውን ኢ- ፍትሐዊ ጥያቄ ተቀባይነት ያሳጣ መሆኑን ገልፀዋ።
የግድቡን መጠናቀቅ ተከትሎ "ኤሌክትሪክ በነፃ ይሆናል"፣ የኤሌክትሪክ ሽፋን ያላገኙ ቦታዎች ላይም ወዲያውኑ ይደረሳል ማለት እንዳልሆነ ግንዛቤ ሊያዝ ይገባል ሲሉም ገልፀዋል ሲል ወኪላችን ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዘግቧል።
❤ 72👎 16👍 15🤯 5👏 4
Photo unavailableShow in Telegram
🌼🌼🌼New Year New Skill 🌼🌼🌼
✨ 5-in-1 Digital Marketing Package ✨
Kickstart the new year with our special offer! Learn Digital Marketing, Video Editing, Graphic Design, WordPress, and Content Creation in one complete course. Upgrade your skills, grow your business, and take advantage of our limited-time New Year discount! 🚀
Register Now! And get 20% discount
☎️
0989747878
Join our telegram channel : https://t.me/merahyan Join our Tiktok channel : @merahyanskillcenter
❤ 19🤔 1😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
"ልምድ በሌለው ኮንትራክተር ምክንያት መንግስት 450 ሚሊዮን ዩሮ ካሳ ከፍሏል"- ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ላይ ስለ ሀይድሮ ኤሌክትሪክ ምንም አይነት ልምድ በሌለው ኮንትራክተር ምክንያት መንግስት 450 ሚሊዮን ዩሮ ካሳ ከፍሏል ሲሉ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ገለጹ።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ፤ ፕሮጀክቱን ረጅም ጊዜ ያቆየው እና ትልቅ መሰናክል የተፈጠረው ምንም አይነት ልምድ የሌለው ኮንትራክተር ትልቁንና ውስብስቡን የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ስራ እንዲሰራ መደረጉ ነው ብለዋል።
የበለስ ሀይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክትን ለመገንባት የፈጀው 460 ሚሊየን ዩሮ መሆኑን ለማሳያነት ያነሱት ኢንጂነር ክፍሌ፤ ህዳሴ ግድብ ላይ ልምድ የሌለው ኮንትራክተር እንዲሠራ መደረጉ አንድን የኤሌክትሪክ ኃይል ጣቢያ መገንባት የሚያስችል ኪሳራ አድርሷል ብለዋል፡፡
ኮንትራቱ ከተፈረመ ከሁለት ወራት በኋላ የሲቪል ስራውን የወሰደው ኮንትራክተር በግድቡ መሰረት ላይ ልል ድንጋይ እንዳጋጠመው እና ድንጋዩን አውጥቶ መሠረቱን በኮንክሪት ለመሙላት ተጨማሪ ሶስት ዓመት እንደሚወስድበት ገልጾ እንደነበር ስራ አስኪያጁ አስታውሰዋል፡፡
የሀገር ውስጥ ኮንትራክተር በዘርፉ እንዲበቃ፤ በጥሩ እሳቤ የፕሮጀክቱን ግንባታ ቢጀምርም ነገር ግን መንግስት በቂ ዝግጅት ሳይደረግ ለኮንትራክተሩ እንዲሰጥ መወሰኑ ትልቅ ስህተት እንደነበር በቁጭት ተናግረዋል፡፡በተጨማሪም መንግስት ፕሮጀክቱ የገጠሙትን ችግሮች በመገምገም እና የኮንትራት ይዘቱ እንዲቀየር ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
❤ 89😁 12🤔 3👎 2😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
አቶ ማሞ ምህረቱ የአፍሪካ ልማት ባንክ ም/ ፕሬዚዳንት ሆኑ!
ላለፉት ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ በመሆን ያገለገሉት አቶ ማሞ ምህረቱ፤ የአፍሪካ ልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆኑ፡፡
አቶ ማሞ ምህረቱ በትላንትናው ዕለት ከብሔራዊ ባንክ ኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ያስታወቁ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት የክብር አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡
አቶ ማሞ በአሜሪካ ከሚገኘው የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ኬኔዲ ትምህርት ቤት በአመራር፣ በፐብሊክ አስተዳደርና በኢኮኖሚ ልማት ማስተርስ አግኝተዋል።
ከፕሪቶሪያ ዩኒቨርሲቲና ከአምስተርዳም ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በንግድና ኢንቨስትመንት የማስተርስ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት ሲመረቁም የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ እንደነበሩ ተጠቁሟል፡፡
❤ 69👍 22👎 5😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
2 ሚሊዮን ብር ዓመታዊ ገቢ ያላቸው ንግዶች ለቫት ሊመዘገቡ ነው
የገንዘብ ሚኒስቴር የግብር አሰባሰብ ስርዓትን ለማሻሻል ያለመ አዲስ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) መመሪያ አዉጥቷል።
በመመሪያው ቁጥር 1104/2017 መሰረት፣ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ ገቢ ያላቸው ንግዶች እና የተወሰኑ የሙያ አገልግሎት ሰጪዎች ለቫት እንዲመዘገቡ ግዴታ ተጥሏል፡፡
በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የተፈረመው ይህ አዲስ መመሪያ፣ ከነሐሴ 28 ቀን 2017 ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል። መመሪያው ከንግድ ድርጅቶች በተጨማሪ፣ ከምድብ "ለ" ውጭ የሚመደቡ ባለሙያዎችንም ያካትታል።
እነዚህ ባለሙያዎች የዓመታዊ ገቢያቸው መጠን ምንም ያህል ቢሆን ለቫት መመዝገብ እንዳለባቸው ተጠቁሟል።
በተጨማሪም መመሪያው፣ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ያለባቸው ወይም በፈቃደኝነት የሂሳብ መዝገብ የሚይዙ ሁሉም ንግዶች እንዲሁም በምድብ "ሀ" ስር የተመደቡ ግብር ከፋዮች የመመዝገብ ግዴታ እንዳለባቸው በዝርዝር አስቀምጧል።
አዲስ የተካተቱ ነባር ግብር ከፋዮች፣ መመሪያው በስራ ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ30 ቀናት ውስጥ መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል። ከተመዘገቡ በኋላም ለገበያ በሚያቀርቧቸው ታክስ የሚከፈልባቸው እቃዎች እና አገልግሎቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ መሰብሰብ እንደሚጀምሩ ተገልጿል።
❤ 30👎 5😱 4👍 1
ትራምፕ የቻይናው መሪ ከፑቲን እና ከኪም ጋር በአሜሪካ ላይ እያሴሩ ነው ሲሉ ከሰሱ
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቻይና አቻቸው ሺ ጂንፒንግ ከሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ መሪዎች ጋር በጥምረት በአሜሪካ ላይ እያሴሩ ነው ሲሉ ወቀሱ።
ትራምፕ ይህንን ያሉት ቻይና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በጃፓን ድል የተቀዳጀችበትን 80ኛ ዓመት መታሰቢያ አስመልክቶ ታላቅ ወታደራዊ ትዕይንት ረቡዕ፣ ነሐሴ 28/ 2017 ዓ.ም ማካሄዷን ተከትሎ ነው።
በዚህ ታላቅ የወታደራዊ በዓል የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡንን ጨምሮ 26 መሪዎች ተገኝተዋል።
ትራምፕ ለፕሬዚዳንት ሺ "በአሜሪካ ላይ በጋራ እያሴራችሁ ላላችሁት ለቭላድሚር ፑቲን እና ለኪም ጆንግ ኡን ሞቅ ያለ ሰላምታ አቅርብልኝ" ሲሉ ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘ ማህበራዊ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።
ትራምፕ ከዚህ ቀደም በቻይና፣ ሩሲያ እና ሌሎች አገራት መካከል ያለው ግንኙነት መጠናከር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለአሜሪካ ተግዳሮት ጋርጧል መባሉን አጣጥለው ነበር።
ትራምፕ በዚሁ የማህበራዊ ገጽ ልጥፋቸው ላይ አሜሪካ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ለቻይና የሰጠችውን ከፍተኛ "መስዋዕትነት" አውስተዋል።
"በርካታ አሜሪካውያን ለቻይና ድል እና ክብር ሲሉ ሞተዋል። ለጀግንነታቸው እና መስዋዕትነታቸው በትክክል እንደተከበሩ እና እንደሚታወሱ ተስፋ አድርጋለሁ" ብለዋል።
❤ 74😁 57👍 12😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
"የቀይ ባሕር ስህተት. . . ነገ ይታረማል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቀይ ባሕር ከሰላሳ ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ እጅ እንደነበረ እና "ስህተቱ ነገ ይታረማል" ሲሉ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ላይ በተላለፈ ውይይታቸው ላይ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ከማኅበራዊ ጉዳይ አማካሪያቸው ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ እንደተናገሩት በቀይ ባሕር ላይ የተፈጸመው ስህተት እንደሚታረም አመልክተዋል።
"ቀይ ባሕር እኮ የዛሬ 30 ዓመት እኛ እጅ ነበር። ቀይ ባሕር የዛሬ 30 ዓመት የትናንት ታሪክ ነው። የተፈጠረው ስህተት ትናንትና ነው። ነገ ይታረማል፤ ብዙ ከባድ አይደለም" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም. በሚመረቀውን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ግንባታ ዙሪያ ባደረጉት ውይይት ላይ የሺህ ዓመታት የአባይ ታሪክ እንደተቀየረው ሁሉ ኢትዮጵያ የባሕር በር ያጣችበት ሁኔታም እንደሚስተካከል አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ ከጥቂት ዓመታት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር በኩል የባሕር በር የማግኘት ፍላጎት እንዳላት ይፋ ካደረጉ በኋላ በኤርትራ በኩል ስጋት ተፈጥሯል።
👍 118❤ 72😁 35👏 9👎 6
Photo unavailableShow in Telegram
"አሰብ የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ግዛት ነው የኢትዮጵያም ህልውና ነው ፤በኢትዮጵያ ጉዳይ የመወሰን መብት ባልነበረው የሽግግር ቡድን አሳልፎ የተሰጠ ራስ ገዝ የባህር በራችን ነው፤ በዚህም ብዙ ሃገራት በናንተ ድክመት ነው እስካሁን ያልተመለሰው እንጂ እስካሁን መቆየት ያልነበረበት ነው ይሉናል ፤ አሁን ላይ የቀይ ባህር ጉዳይ የህልውናችን ጉዳይ ሆኗል ለህልውናችን ስንልም የትኛውን ዋጋ ከፍለን አሰብን እናስመልሰዋለን ። "
- ሜጀር ጀነራል ተሾመ ገመቹ ለፕራይም ሚዲያ
🙏 118❤ 62😁 15👎 10😱 6👍 3👏 3
Photo unavailableShow in Telegram
ማንቼስተር ዩናይትድ አዲስ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማማ
ማንቼስተር ዩናይትድ ቤልጂየማዊውን ግብ ጠባቂ ሴን ላሜንስ ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡
ዩናይትድ ለግብ ጠባቂው ዝውውር ለቤልጂየም ፕሮ ሊጉ ሮያል አንትወርፕ 21 ሚሊየን ዩሮ የሚከፍል ይሆናል፡፡
ተጫዋቹ ለአምስት ዓመታት በኦልድትራፎርድ የሚያቆየውን ውል እንደሚፈርም ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡
ማንቼስተር ዩናይትድ ባለፉት ቀናት ከአርጄንቲናዊው ግብ ጠባቂ ኢሚሊያኖ ማርቲኔዝ ጋር ስሙ በስፋት ሲያያዝ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
❤ 51👍 16👏 5😁 5
Photo unavailableShow in Telegram
ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን ለመሸጥ ተስማማ
ማንችስተር ዩናይትድ እና ሪያል ቤቲስ በብራዚላዊው የመስመር ተጫዋች አንቶኒ ዝውውር ከስምምነት መድረሳቸው ተዘግቧል።
ሪያል ቤቲስ ለአንቶኒ ዝውውር 25 ሚልዮን ዩሮ ለመክፈል መስማማታቸውን ዘ አትሌቲክ በዘገባው አስነብቧል።
አንቶኒ በሪያል ቤቲስ ባሳለፈው የውሰት ጊዜ በ 2️⃣6️⃣ ጨዋታዎች 1️⃣4️⃣ ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ችሎ ነበር። አንቶኒ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት የሁለት አመት ቀሪ ኮንትራት ነበረው።
❤ 32👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ግብፅ ለኤርትራ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች
የሕክምና ቁሳቁስ የያዘ የግብፅ አውሮፕላን ባሳለፍነው ዓርብ ነሐሴ 23 ቀን 2017 ዓ.ም. #አስመራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መደረሱን የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ለኤርትራ የመድሃኒት አስተዳደር የተበረከተው ይህ እርዳታ፣ የዓይን ህክም እና የኩላሊት እጥበት መስሪያ ቁሳቁሶችን ያካተተ ነው። እርዳታው የቀረበው በግብፅ የልማት አጋርነት ኤጀንሲ አማካይነት መሆኑ ተመላክቷል።
እንደ ሚኒስቴሩ ገለፃ፤ ይህ ድጋፍ #ካይሮ ከኤርትራ ጋር ያላትን “ስትራቴጂያዊና እህትማማች ወዳጅነትን” ለማጠናከር የምታደርጋቸው ጥረቶች አካል ነው።
የህክምና ቁሳቁስ እርዳታው ወደ አስመራ የተላከው፣ የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ጥቅምት ወር በአስመራ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ነው። ጉበኝቱ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ትብብር አዲስ ምዕራፍ መሆኑን ሁለቱም ሀገራት ገልፀዋል።
❤ 39🤔 14😁 6👎 2
Photo unavailableShow in Telegram
ሊቨርፑል የእንግሊዝ ሪከርድ በሆነ ገንዘብ ይሳቅን ለማስፈረም ተስማማ!
ሊቨርፑል አሌክሳንደር ይሳቅን ከኒውካስትል ዩናይትድ ለማስፈረም ስምምነት ላይ መድረሱን ስካይ ስፖርት ዘግቧል።
ሊቨርፑል ለስዊዲናዊው አጥቂ ዝውውር የእንግሊዝ ሪከርድ የሆነ 125 ሚሊዮን ፓውንድ ለመክፈል ስምምነት ላይ ደርሷ።
የ25 ዓመቱ አጥቂ የህክምና ምርመራውን ዛሬ የሚያደርግ ሲሆን ከመርሲሳይዱ ክለብ ጋር ለ ስድስት ዓመት የሚያቆየውን ውል የሚፈርምም ይሆናል።
ዛሬ በሚዘጋው የክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት አሰልቺ የነበረው ዝውውር መቋጫውን የሚያገኝም ይሆናል።
ከሁለት ዓመት በፊት ቼልሲ ሞይሰስ ካይሴዶን ከብራይተን ያስፈረመበት 115 ሚሊዮን ፓውንድ የእንግሊዝ ክብረ ወሰን ሲሆን ሊቨርፑል ለአሌክሳንደር ይሳቅ ዝውውር ለመክፈል የተስማማው 125 ሚሊን ፓውንድአዲስ ክብረ ወሰን ሆኖም ይመዘገባል። አሌክሳንደር ይሰቅ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከሙሃመድ ሳላህ በመቀጠል በ23 ግቦች የፕሪሚየር ሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ እንደነበር ይታወሳል።
❤ 47👍 23🤯 3👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ራሱን ከዳኝነት ዓለም ለማግለል መወሰኑን አስታወቀ
ያለፉትን ረጅም ዓመታት በወጥነት በሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ መድረኮች በዳኝነት ያገለገለው ባምላክ ተሰማ ከዳኝነት ዓለም ራሱን ለማግለል መወሰኑን ለፊፋ በላከው መልዕክት አስታውቋል።
በዓለም ዋንጫ፣ የአፍሪካ ዋንጫ፣ ቻን፣ ቻምፒየንስ ሊግ፣ ኮንፌሬዴሽን ዋንጫ፣ የዓለም ክለቦች ዋንጫ እና ኦሊምፒክን ጨምሮ በርካታ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ታላላቅ ጨዋታዎችን በመምራት የሀገሩን ስም ከፍ አድርጎ ያስጠራው ባምላክ ኢትዮጵያን በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ መድረክ በማገልገሉ ኩራት እንደሚሰማው ገልጾ ፊፋ ለሰጠው ዕድል በማመስገን ከኢንተርናሽናል ዳኝነት ራሱን ማግለሉን አስታውቋል።
❤ 65
Photo unavailableShow in Telegram
የየመኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አህመድ አል ራሃዊ በእስራኤል አየር ጥቃት ተገደሉ
በኢራን የሚደገፉትና በሁቲዎች የተሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትር አህመድ አል ራሃዊ በእስራኤል በተፈጸመባቸው አየር ጥቃት ተገደሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተገደሉት ሳንአ ከተማ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ትናንት ሐሙስ ነው።
እንደ እስራኤል ባለስልጣናት ገለጻ ከእሳቸው ጋር የነበሩ የሃውቲ መከላከያ ሚኒስትር መሀመድ አል-አቲፊ እና የጦር ሀይሉ ዋና አዛዥ መሀመድ አብድ አልካሪም አል ጋማሪን አንድ ላይ ተገድለዋል።
እንደ ዩሮ ኒውስ ዘገባ የእስራኤል አየር ድብደባ የሁቲ መሪ አብዱልመሊክ አል ሁቲ ሊያደርጉት ካቀዱት ንግግር ጋር የተገጣጠመ ነው። ሆኖም የእስራኤል ምንጮች የቡድኑ መሪ በታለመበት ቦታ ላይ እንዳልነበሩ ተናግረዋል ።
ከግድያ በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ሁቲዎችን “ከጨለማ መቅሰፍት በኋላ የበኩር ልጅ መቅሰፍት ይመጣል” ብለው ማስጠንቀቃቸውን አስታውሰዋል።
ጨምረውም “በእስራኤል ላይ እጁን የሚያነሳ ሁሉ እጁ ትቆረጣለች” ሲሉ ዝተዋል። በቅርቡ ሁቲዎች በእስራኤል ላይ በተከለከለ ክላስተር ቦንብ ጥቃት መፈጸማቸው ይታወሳል።
❤ 115😭 16👍 11👏 7🙏 5😁 3🤔 1
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከናይጄሪያው ኩባንያ ዳንጎቴ ግሩፕ ጋር የማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክት ግንባታ ስምምነት መፈረሙን አስታወቁ
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶር) በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በዳንጎቴ ግሩፕ መካከል የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ የድርሻ ስምምነት መፈረሙን አስታወቁ።
ጠ/ ሚኒስትሩ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት የሚፈስበት ይኽ ሜጋ ፕሮጀክት በአመት እስከ ሶስት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ የሚያመርት ሲሆን ይኽም ኢትዮጵያን ከአለም ግንባር ቀደም አምራቾች አንዷ ያደርጋታል ብለዋል።
የዛሬውን የፊርማ ስምምነት ተከትሎ ፋብሪካው በሚቆምበት ስፍራ ፕሮጀክቱን በይፋ የምናስጀምር ይሆናል ያሉት ዐቢይ (ዶ/ር)፤ “ይኽን ታሪካዊ ጉዞ ጀምረናል። ለገበሬዎቻችን፣ ለኢኮኖሚያችን እና ለኢትዮጵያ ነገ ስንል እንጨርሰዋለን” ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ቃል ገብተዋል።
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶር) ፕሮጀክቱ በሀገር ውስጥ የሥራ እድል እንደሚፈጥር በመጥቀስ፤ “ለዘመናት ለተፈተኑት ገበሬዎቻችን አስተማማኝ የማዳበሪያ አቅርቦት ያረጋግጣል። ለምግብ ሉዓላዊነት መንገዳችንም ወሳኝ ርምጃ መውሰዳችንን ያመላክታል” ሲሉ ገልጸዋል።
በተጨማሪም “ወደ ምግብ ዋስትና እና የግብርና ሽግግር በምናደርገው ጉዞ አንድ ሌላ እጥፋት ላይ በመድረሳችን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ እንኳን ደስ አለን” ብለዋል።
❤ 108👍 15👎 11👏 6😱 5🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
🇺🇸የአሜሪካ ቪዛ ክፍያ 135% ጨመረ
ወደ አሜሪካ መጓዝ አሁን የበለጠ ውድ ሊሆን ነው። በአሜሪካ ኮንግረስ በጸደቀው አዲስ ህግ "የአንድ ትልቅ ውብ ሂሳብ ህግ" መሰረት፣ ለስደተኛ ላልሆኑ ቪዛ አመልካቾች ተጨማሪ 250 ዶላር ክፍያ መክፈል ይጠበቅባቸዋል።
ይህ አዲስ የቪዛ ክፍያ መስከረም መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል ዩኤስኤ ቱዴይ ዘግቧል።
በአሁኑ ጊዜ ለቱሪስት ቪዛ (B1/B2) ክፍያው 185 ዶላር ነው። አዲሱ ውሳኔ ተግባራዊ ከሆነ አጠቃላይ ወጪው ወደ 435 ዶላር የሚጠጋ ይሆናል ይህም ከ135 በመቶ በላይ ጭማሪ ነው።
ይሁን እንጂ ይህ ውሳኔ በዩኤስ የቪዛ ነጻ ማድረጊያ ፕሮግራም (ESTA) ለተካተቱ አገሮች ተጓዦች አይተገበርም።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲሱ ክፍያ በ2026 ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል ተናግሯል፣ ምንም እንኳን በሚቀጥለው የበጀት ዓመት መጀመሪያ ላይ በህጋዊ መንገድ ሊተዋወቅ ቢችልም። ይህ ከተከሰተ፣ የአሜሪካ ቪዛ በዓለም ላይ ካሉ በጣም ውድ ከሚባሉት አንዱ ይሆናል።
አዲሱ የቪዛ ክፍያ ቱሪዝምን ብቻ ሳይሆን ስፖርትን እና አለምአቀፍ ዝግጅቶችን ይጎዳል። ለምሳሌ፣ ከዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት የመጡ ደጋፊዎች እና ተጫዋቾች የ2026 ፊፋ የዓለም ዋንጫን እና የ2028 የሎስ አንጀለስ ኦሊምፒክን ለመሳተፍ አስቸጋሪ ያደርገዋል።
የአሜሪካ ባለስልጣናት አዲሱ ክፍያ ሊመለስ እንደሚችል ተናግረዋል። ነገር ግን ክፍያው እንዴት እንደሚመለስ ግልጽ የሆነ ማዕቀፍ ወይም የጊዜ ሰሌዳ የለም። ግልጽ የሆነው ነገር ቢኖር ወደ አሜሪካ ለመጓዝ የሚወጣው ወጪ እየጨመረ መምጣቱ ነው ሲል ፊደል ፖስት ዘግቧል።
❤ 68🥰 6👍 4
የሿሿ ወንጀል ሲፈጽሙ የነበሩ 5 ተጠርጣሪዎች ተያዙ
በአዲስ አበባ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ የማታለል (የሿሿ) ወንጀል ሲፈጽሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ገለፁ፡፡
ኮማንደር ማርቆስ እንደገለፁት የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የፒያሳ ፖሊስ ጣቢያ ነሐሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 10 ሰዓት ሄነሪኮ ኬክ ቤት አካባቢ በተሽከርካሪዎች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ በሚያደርግበት ወቅት የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1 አ/አ 11631 ሚኒባስ ታክሲ ከፍተሻው ለመዳን መንገድ በመቀየስ ወደመጣበት አቅጣጫ ይመለሳል፡፡
ፖሊስም በመጠራጠር ተሽከርካሪውን ተከታትሎ በመያዝ ባደረገው ፍተሻ ከተለያዩ ግለሰቦች የተሰረቁ 4 የሞባይል ቀፎዎችን ከ5 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል ብለዋል ኮማንደሩ፡፡
ፖሊስ ከተጠርጣሪዎቹ እጅ ላይ በተገኙ ስልኮች ላይ ባደረገው ማጣራት የተሰረቁ ስለመሆናቸው ከግል ተበዳዮች ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን፤ ተጨማሪ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ኮማንደሩ ለኢቢሲ ዶትስትሪም ገልፀዋል፡፡
በእነዚህ ግለሰቦችና ተሽከርካሪ ወንጀል የተፈፀመበት ግለሰብ ካለም ፒያሳ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ማመልከት እንደሚችል አክለዋል፡፡
ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ቡድን ወንጀል ፈጽሞ ከፖሊስ ዓይን ማምለጥ የማይችል መሆኑን ተገንዝቦ ከመሰል ድርጊት ራሱን ማራቅ እንደሚኖርበትም ኮማንደር ማርቆስ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
❤ 96👏 23🤔 2
ሊቨርፑል ኒውካስል ዩናይትድን አሸነፈ
በሁለተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሊቨርፑል ኒውካስል ዩናይትድን 3 ለ 2 አሸንፏል፡፡
የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ግራቨንበርች፣ ኤኪቲኬ እና ንጉሞሃ ከመረብ አሳርፈዋል።የኒውካስልን ግቦች ደግሞ ጉማሬሽና ኦሱላ አስቆጥረዋል።
👍 34❤ 25🤔 3
Photo unavailableShow in Telegram
ጀርመንኛ ቋንቋ ስልጠና
A1, A2, B1 and B2 and C1 Level
🌟 Enhance Your Skills with Our Upcoming German Language Training! 🌟
•አዲስ ቋንቋ መማር ለምትፈልጉ
•የጋብቻ ፕሮስስ ጀርመን ኤምባሲ መጀመር ላሰባችሁ
•የስራ ፕሮስስ ለመጀመር ያሰባችሁ
የ ጎተ (Goethe) ፈተና ለማለፍ ዝግጁ እናደርጋቹሃለን!
•Online or Inperson
To register:
☎️
0989747878
0799331774
ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ : @merahyan
❤ 23👍 3
