en
Feedback
Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

Open in Telegram

እንኳን ደህና መጡ‼ 📌ማስታወቂያ ለማሰራት👉 @WasuMohammed 📌 ቻናሉን ለመቀላቀል 👉 @Wasulife ከልብ አመሰግናለሁ♥🙏

Show more
2025 year in numberssnowflakes fon
card fon
241 382
Subscribers
-96724 hours
+9 9047 days
+19 31230 days
Posts Archive
Photo unavailableShow in Telegram
ተጨማሪ ሰው ታሰረ‼ በቅርቡ በተካሄደው የቲክቶክ ሽልማት (TikTok Awards) ሥነ-ሥርዓት ላይ ከአለባበስ ጋር ተያይዞ ትናንት በፖሊስ መያዛቸው ከተገለፁት በተጨማሪ ጆሲ የተባለው ወጣት በተመሳሳይ ጉዳይ ትናንት መታሰሩ ታውቋል። የፌዴራል ፖሊስ ከዚህ ቀደም የቲክቶክ ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ የታዩ ከባህል የወጡ የአለባበስ ጉዳዮችን እየመረመረ መሆኑን ፍንጭ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን፣ አሁን የተወሰደው እርምጃም የዚያ ክትትል አካል እንደሆነ ተዘግቧል። #ዋሱመሐመድ አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
Show all...
👍 105 56😁 36👏 9🤔 3🙊 3😭 2😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
9
Photo unavailableShow in Telegram
ተጨማሪ ሰው ታሰረ‼ በቅርቡ በተካሄደው የቲክቶክ ሽልማት (TikTok Awards) ሥነ-ሥርዓት ላይ ከአለባበስ ጋር ተያይዞ ትናንት በፖሊስ መያዛቸው ከተገለፁት በተጨማሪ ጆሲ የተባለው ወጣት በተመሳሳይ ጉዳይ ትናንት መታሰሩ ታውቋል። የፌዴራል ፖሊስ ከዚህ ቀደም የቲክቶክ ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ የታዩ ከባህል የወጡ የአለባበስ ጉዳዮችን እየመረመረ መሆኑን ፍንጭ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን፣ አሁን የተወሰደው እርምጃም የዚያ ክትትል አካል እንደሆነ ተዘግቧል።
Show all...
👌 1
በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ይሄ ታፔላ የማቆም ዘመቻ በኋላ የብሽሽቅ መነሻ እንዳይሆን ያሰጋል።እነዚህ ነገሮች እጅግ የተከበሩና ስስ በመሆናቸው በተፈቀደላቸው ቦታ ተወስነው ተከብረው ተወደው ቢቀመጡ መልካም ነው። የቤተ እምነቶቹን መገኛ አቅጣጫ የሚጠቁሙ ታፔላዎች ብቻ በቂ ናቸው።እየቆየ ሲሄድ ከተሞች "ሰሉ አለ ነብይ"(የአሏህ ሰላም በአንቱ ላይ ይስፈን!)የሚል እጅግ የተከበረ ቃል ያረፈበትን ታፔላ በደንብ ማስከበር አነሳለሁ ቢሉ መቀያየሙ ይመጣል።አንዱ የወረቀት ማስታወቂያ አምጥቶ ቢለጥፍበት ራሱን የቻለ ሌላ ነገር ነው።እፀዳዳበታለሁ የሚልም ይመጣል።የእኔ እምነት ታፔላ ከፊት በትልቁ መቆም አለበት የሚልም ይከተላል።ስለዚህ ጉዳዩን ከአባቶችና ከወንድሞች ጋር ተነጋግሮ መስመር ማስያዙ መልካም ይመስለኛል። በውስጥ ከመጡልኝ አስተያየቶች መካከል:- 📌"ከእምነት ቦታው ርቆ ደህንነቱ ባልተረጋገጠ ቦታ የረሱልን(ሶ.ዐ.ወ) ክብር የሚያስደፍር አከባቢ ማስቀመጥ ኋላ ክብራቸው ሲነካ ዝም የሚል አማኝ የለም ግን ማን ሊጠየቅ ነው? የኦለማዎች ፈትዋ ቢጠየቅ የተሻለ ነው።ተገቢ አይደለም" 📌"ታፔላው በኛ ሀገር ተጨባጭ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል።እንደ ሳዑዲ ባሉ ሀገሮች ግን የበለጠ ውበት አለው። ይሄ ቀርቶብን ሌሎች መሠረታዊ መብቶቻችንን ማስከበር ላይ በህብረት ብንሠራ ይሻላል።" 📌"ሲቀጥል ሌሎች ቢያደርጉት የሚከፋንን ነገር ለእኛ ሲሆን ሊያስደስተኝ አይችልም መቆም ያለበት ጉዳይ ነው።" 📌"በጣም የሚያስጠላ ነገር ነው ክብራቸውን ከፍ አደረግን ብለን በማንም ልናዘልፉቸው ነው። መቆም አለበት ይህኔ በ ቀን አንድ ግዜ ስማቸውን ሳያነሳ የሚውል ነው ሲለጥፍ የሚውለው።" 📌" ይሄ አካሄድ ወደ ፊትም ሙስሊሙ ከሌላ አማኝ ጋር ተዋዶና ተከባብሮ እንዳይኖር ለፍረጃ የሚያነሳሳ ነው ይታረም" 📌"ታፔላላይ ፃፉ አይደለም የተባለው በምላሳችሁ በሉ እንጅ አሏሁመሶሊ ወሰሊም አላሰይዲና ሙሀመድ" 📌"በእንቶ ፋንቶ ጊዜ አናባክን።ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ብዙም አንገብጋቢ አይመስለኝም።" 📌"አንዳንዶቻችን ሀገራችን የብዙ እምነት መገኛ መሆኗን መዘንጋት ተገቢ አይደለም።ዝቅታ የሚሰማው ካለ ራሱ ላይ በመስራት ነው ከፍታውን ማምጣት የሚችለው።" የሚሉ በርካታ አስተያየቶች ከእናንተ ተልከው ተመልክቻለሁ የተወሰኑት ናቸው የቀረቡት። ቤተእምነቶች ሁሉ እየተነሱ በየከተሞች መግቢያ እምነታችንን ይገልፅልናል የሚሉትን ነገር የሚሰቅሉ ከሆነ የፉክክሩ ነገር ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ይወስደዋልና ኦለማዎችና ኡስታዞች መፍትሄ ስጡበት።
Show all...
247👍 82👏 13🙏 7👌 5🤔 4🏆 3🙉 2😁 1😢 1😍 1
Photo unavailableShow in Telegram
📍አድራሻ - በመሀል ከተማ በኮሊደር ልማቷ ባሸበረቀችው  ለቡ ማብራት-ሀይል 💥ሊኖሩበት ቢፈልጉ ሰላሚዊ መንደር፣ ሊያከራዩት ቢያስቡ በጥሩ ወጋ እና መልሰው እንኳን ቢሸጡት በደንብ የሚያተርፉበት!! 💥ስቱዲዮ (59 ካሬ) በ 260ሺህ ብር 💥ባለ አንድ መኝታ (77.3ካሬ) በ 341ሺህ ብር 💥ባለ ሁለት መኝታ (127.2ካሬ) በ 561ሺህ ብር 💥ባለ ሦስት መኝታ (150.5 ካሬ) በ 664ሺህ ብር 💥 ባለ አራት መኝታ (194 ካሬ) በ 855 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ 💥 እንዲሁም እስከ 295ካሬ ስፋት ያላቸው ፔንትሃውስ ቤቶችን በምቹ አከፋፈል በተመጣጣኝ ዋጋ ከኛ ያገኛሉ በተጨማሪም  ከ27 - 190 ካሬ ስፋት ያላቸው ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የንግድ ቦታዎችን እንደምርጫዎ አቀርብንሎት! ✍️ በ10% ቅድመ ክፍያ ብቻ ✍️ ከ 60% የባንክ ብድርጋር እስከ 25 ዓመት ✍️ በተጨማሪም እስከ 35%  እንደ አከፋፈሎ ልዩ ቅናሽ ይደረግሎታል ✍️ ሁሉም ቤቶች ተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል, ስቶር እና የላውንድሪ ክፍሎች ያሏቸው። ✍️ መንደራችን በውስጥ የያዛቸው ልዩ ልዩ የጋራ መገልገያዎች: 💥 አራት የመንገደኞች እና አንድ የእቃ አሳንሰር 💥 አምስት የዋና ገንዳዋች 💥 አስተማማኝ ና ደህንነቱ የተጠበቀ ሰፊ የመኪና ማቆሚያ 💥 የኤሌክትሪክ መኪና ኃይል መሙያ መሳሪያ 💥 ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን የጋራ ቦታ 💥 የቆሻሻ መጣያ (Garbage shooter) 💥 ዘመናዊ የገበያ ማዕከሎች @Dmcreales ለበለጠ መረጃ ☎️ 0940625843
Show all...
26
Photo unavailableShow in Telegram
Update ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሯል‼ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP) ከፍተኛ አመራሮች ላይ የተጀመረው የሙስና ምርመራ እና እስር ተጠናክሮ መቀጠሉ ታወቀ። ከቀናት በፊት በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሁለት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተጨማሪ፣ የከፍተኛ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ውቤ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል። የክሱ ዝርዝር ሶስቱም ከፍተኛ አመራሮች ማለትም አቶ ሀብታሙ ውቤ፣ ኢንጂነር ህይወት እሸቱ እና አቶ አንዱዓለም ሲዓ፤ በፌደራል ፖሊስ የተጠረጠሩበት ዋና ወንጀል፣ ከውጭ ሀገር ኮንትራክተሮች ጋር በጥቅም በመመሳጠር ሀገር ማግኘት የነበረባትን ከፍተኛ ገቢ በማሳጣት እና በከባድ የሙስና ወንጀል መሆኑ ተረጋግጧል። ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ፖሊስ ምርመራውን ለማጠናከር ለታህሳስ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል። የእስሩ ሂደት የጀመረው ህዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ነበር። የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ተቋሙ በመግባት፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የፕላኒንግ ዘርፍ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን ኢንጂነር ህይወት እሸቱን እና የቢዝነስ ዘርፍ ዋና ምክትል ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን አቶ አንዱዓለም ሲዓን ቢሮ ካስፈተሹ በኋላ በሰራተኞች ፊት በካቴና አስረው ወስደዋቸዋል። ጉዳዩን ይበልጥ አነጋጋሪ ያደረገው ደግሞ፣ እስሩ የተፈጸመው ተቋሙ "የፀረ-ሙስና ቀን"ን ለማክበር ዝግጅት እያደረገ በነበረበት ዋዜማ ላይ መሆኑ ነው። መስሪያ ቤቱ ለሰራተኞቹ "ነገ ህዳር 25 የፀረ-ሙስና ቀን ይከበራል" የሚል መልዕክት አስተላልፎ የነበረ ቢሆንም፣ የዝግጅቱ መሪ መሆን የነበረባቸው አመራሮች በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸው በተቋሙ ሰራተኞች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤ እና መደናገርን ፈጥሯል። በዚህ የሙስና መረብ ውስጥ እጃቸው አለበት ተብለው የሚጠረጠሩ ሌሎች ተጨማሪ የስራ ኃላፊዎችም የሚፈለጉ ሲሆን፣ እስሩ ወደ ሌሎችም ዘርፎች ሊስፋፋ እንደሚችል ተመላክቷል። ፖሊስ ጉዳዩን በምርመራ እያጣራ ይገኛል። መረጃው ከዘሀበሻ የተወሰደ ነው።
Show all...
187🙏 167👏 37👍 29😁 24😍 9🏆 8😱 7🎉 6🕊 5👌 3
Photo unavailableShow in Telegram
ኤርትራውያንን በግብፅ እየታፈሱ ነው ተባለ‼ የግብጽ መንግስት ኤርትራውያንን እያፈሰ ወደ እስርቤት እያጋዘ ይገኛል። እስከአሁን በዋና ከተማዋ ካይሮ ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ከተሞች ከ 317 በላይ ኤርትራውያን ታፍሰው የታስሩ ሲሆን 150 ኤርትራውያንን ደግሞ በግዳጅ ወደሃገራቸው እንዲመለሱ ተዳርገዋል።ኤርትራውያንን ማፈሱና ወደ እስርቤት መውሰዱ አሁንም የቀጠለ ሲሆን ምክንያት የተባለው ጉዳይ በዝርዝር አልተጠቀሰም። Via Abel Birhanu
Show all...
73😁 36👍 17😢 13🕊 4🙊 3👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
10😱 3
አቶ ቻላቸው ጌጡ ለአቶ አብዱል ሰመድ መሃመድ መልሰዋል‼ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ባለሙያ በስህተት ወደ ባንክ ሒሳብ ቁጥራቸው የገባውን 8 ነጥብ 4 ሚሊዬን ብር ለባለቤቱ መለሱ፡፡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ባለሙያ የሆኑት አቶ ቻላቸው ጌጡ በስህተት ወደ ባንክ ሒሳብ ቁጥራቸው የገባውን 8 ነጥብ 4 ሚሊዬን ብር በታማኝነት ለባለቤቱ መልሰዋል፡፡ ህዳር 13 ቀን 2018 ዓመተ ምህረት ከአዋሽ ባንክ አቶ አብዱል ሰመድ መሃመድ የተባሉ ደንበኛ ወደ አሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ለአቶ መሃመድ ኢብራሂም 8 ነጥብ 4 ሚሊዬን ብር እንዲላክላቸው ጥያቄ ቢያቀርቡም ገንዘቡ በስህተት ወደ አቶ ቻላቸው ጌጡ አካውንት ገቢ ሆኗል፡፡ አቶ ቻላቸው ጌጡ በስህተት ወደ ሒሳብ ቁጥራቸው የገባውን ገንዘብ በታማኝነት ለባለቤቱ ተመላሽ በማድረግ አርዓያነት ያለው ተግባር ፈጽመዋል፡፡ (ትምህርት ቢሮ) Wasu Mohammed - Mereja
Show all...
227🏆 35👍 34🥰 10🫡 9😱 6😍 6💔 5🤔 3🥴 2🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
Attention‼️ ከቃል በላይ ያስረከብናቸው ከ 8 በላይ ሳይቶች ማሳያ ናቸው #ቴምርሪልስቴት ‼️ሳር ቤት ቫቲካን 🎯65/35 አከፍፈል 👉2መኝታ 81ካሬ ሙሉ ክፍያ 6ሚሊዮን 👉2መኝታ 106ካሬ ሙሉ ክፍያ 7.9ሚሊዮን 👉3መኝታ 139ካሬሙሉ ክፍያ 10.3ሚሊዮን 🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል 👉2መኝታ 81ካሬ 20%ቅድመ ክፍያ 1.86ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 9.3ሚሊዮን 👉2መኝታ 106ካሬ 20% ቅድመ ክፍያ 2.4ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 12.1ሚሊዮን 👉3መኝታ 139ካሬ 20%ቅድመ ክፍያ 3.1ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 15.9ሚሊዮን ‼️አዋሬ 🎯65/35 አከፍፈል 👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን 🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል 👉 1መኝታ 78ካሬ 20%ቅድመ ክፍያ 1.7ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን                  👉3 መኝታ 117ካሬ 20%ቅድመ ክፍያ  2.6ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 12.9ሚሊዮን 👉 157ካሬ = 20% ቅድመ ክፍያ 3.4ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን    #ልብይበሉ              #ቀሪውን 80% በ 15ዙር  ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ  ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት * 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇👇👇 +251939770177 +251996856273 https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Show all...
25
Photo unavailableShow in Telegram
ወደ ሳውዲ ተጉዘዋል‼️ ከሰሞኑ ሱዳን የነበሩት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ ማክሰኞ ለ4 ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ሳውዲያ አረቢያ ማቅናታቸውነ የማስታወቂያ ሚንስትሩ አቶ የማነ አሳውቀዋል።
Show all...
🤣 63 45👍 24😱 7😁 5🕊 4🏆 4👏 3
Photo unavailableShow in Telegram
👌👌👌ቅንጡ አፓርትመንቶችንና የንግድ ሱቆችን ከጊፍት ሪል ስቴት! 👉400ሺ ቅድመ ክፍያ ጀምሮ 👉3ሚሊዮን የሚደርስ ቅናሽ 👉 5%-20 ቅድመ ክፍያ 👉55/45 የባንክ ብድር 👉 5%-21%ልዩ  ቅናሽ ✔️ባለ 1መኝታ ፦ 64ካሬ- 80ካሬ ✔️ባለ 2መኝታ፦98ካሬ- 141ካሬ ✔️ባለ3መኝታ፦150ካሬ-205ካሬ ⛺️በለገሃር 📌ቦሌ አትላስ 📌በ22 ማዞሪያ 📌6ኪሎ 📌በሲኤምሲ 📌በፈረስ ቤት በተጨማሪ ☑️የቆሻሻ ማስወገጃ ☑️ባካብ ጀኔሬተር ☑️በቂ ሊፍቶች ☑️ከአፀደህፃናት እሰከ መጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፣ ☑️የገበያ ማዕከላት  ☑️የሳይክል መንገድና  የስፖርት ማዕከል ያለው                                        ☎️   0963999444 or                                                0930649813
Show all...
13
ፌደራል ፖሊስ ምርመራ ጀምሯል‼ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሀገራችን ባህልና ሥነ-ምግባር ያፈነገጠ አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የታዩ ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ:: የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ3ኛው የG-Power TikTok Creative Award ላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህልና ሥነ-ምግባር ባፈነገጠ አኳሃን ሰውነታቸውን የገላለጠ አለባበስ ለብሰው በአደባባይና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የታዩ ተጠርጣሪዎችን ከነግብረ-አበሮቻቸው ጋር በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ ማጣራት መጀመሩን አስታውቋል። ‎የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን በሀገራችን አዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው 3ኛው የG-Power TikTok Creative Award ላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህል እና መልካም ሥነ-ምግባር በተቃራኒ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት የታዩ፣ ዝግጅቱን በስፖንሰርነት የደገፋ እና ፕሮግራሙን ያቀነባበሩ ተጠርጣሪዎች:- ‎1ኛ. ወንጌላዊት ገብረ እንድርያስ በርሄ፣ ‎2ኛ. በርከት ፀጋዬ ጅፋር፣ ‎3ኛ. መቅድም ደረጄ መንግስቱ፣ ‎4ኛ. ግሩም ገዛሀኝ ቀጭኔ እና ‎5ኛ. ዮሃንስ መኮንን ሀ/ማርየም ‎የተባሉ ግለሰቦች መሆናቸውን ገልጿል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከህብረተሰቡ ባህልና እሴት ያፈነገጡ አለባበሶችና መጤ ባህሎች ተስፋፍተው በትዉልዱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳያስከትሉ ተጠርጣሪዎቹ ላይ የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታውቃል። via Vederal police Wasu Mohammed - Mereja
Show all...
👏 264 129👍 53🙏 28😁 9🏆 5💔 5🥰 4🙈 3😭 2👌 1
Photo unavailableShow in Telegram
📍አድራሻ - በመሀል ከተማ በኮሊደር ልማቷ ባሸበረቀችው  ለቡ ማብራት-ሀይል 💥ሊኖሩበት ቢፈልጉ ሰላሚዊ መንደር፣ ሊያከራዩት ቢያስቡ በጥሩ ወጋ እና መልሰው እንኳን ቢሸጡት በደንብ የሚያተርፉበት!! 💥ስቱዲዮ (59 ካሬ) በ 260ሺህ ብር 💥ባለ አንድ መኝታ (77.3ካሬ) በ 341ሺህ ብር 💥ባለ ሁለት መኝታ (127.2ካሬ) በ 561ሺህ ብር 💥ባለ ሦስት መኝታ (150.5 ካሬ) በ 664ሺህ ብር 💥 ባለ አራት መኝታ (194 ካሬ) በ 855 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ 💥 እንዲሁም እስከ 295ካሬ ስፋት ያላቸው ፔንትሃውስ ቤቶችን በምቹ አከፋፈል በተመጣጣኝ ዋጋ ከኛ ያገኛሉ በተጨማሪም  ከ27 - 190 ካሬ ስፋት ያላቸው ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የንግድ ቦታዎችን እንደምርጫዎ አቀርብንሎት! ✍️ በ10% ቅድመ ክፍያ ብቻ ✍️ ከ 60% የባንክ ብድርጋር እስከ 25 ዓመት ✍️ በተጨማሪም እስከ 35%  እንደ አከፋፈሎ ልዩ ቅናሽ ይደረግሎታል ✍️ ሁሉም ቤቶች ተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል, ስቶር እና የላውንድሪ ክፍሎች ያሏቸው። ✍️ መንደራችን በውስጥ የያዛቸው ልዩ ልዩ የጋራ መገልገያዎች: 💥 አራት የመንገደኞች እና አንድ የእቃ አሳንሰር 💥 አምስት የዋና ገንዳዋች 💥 አስተማማኝ ና ደህንነቱ የተጠበቀ ሰፊ የመኪና ማቆሚያ 💥 የኤሌክትሪክ መኪና ኃይል መሙያ መሳሪያ 💥 ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን የጋራ ቦታ 💥 የቆሻሻ መጣያ (Garbage shooter) 💥 ዘመናዊ የገበያ ማዕከሎች @Dmcreales ለበለጠ መረጃ ☎️ 0940625843
Show all...
35😱 1
ተሳፋሪውን በመግደል ተጠርጥሮ የተሰወረን አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡ ሐምሌ 5 ቀን 2017 ዓ/ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ከቀኑ 11ሰዓት 45 ላይ ሚካኤል ውቤ የተባለ ወጣት ህይወቱ አልፎ ይገኛል፡፡ የወጣቱ መሞት መረጃ የደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የምርመራ፣ የቴክኒክና የክትትል ቡድንን ወደ ስፍራው በመላክ ልዩ ልዩ ማስረጃዎችን ያሰባስባል፡፡ በዕለቱ የሟች እንጂ የገዳይ ማንነት አለመታወቁ ምርመራውን የተወሳሰበ አድርጎት ቆይቷል፡፡ ተጠርጣሪ ጅብሪል ብርሃኑ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3B-51857 አ.አ ቪትስ ተሽከርካሪ እየነዳ ሟች ሚካኤል ውቤ በ200 ብር የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጠው ይስማሙና ጉዞ ይጀምራሉ፡፡ ስካይ ላይት ሆቴል አካባቢ ሲደርሱ ሟች ተጨማሪ አንድ መቶ ብር በመጨመር 300 ብር ቢከፍልም አሽከርካሪው ጅብሪል ክፍያው ያንሰኛል 600 ብር ልትከፍለኝ ይገባል በማለቱ በሁለቱ መካከል አለመግባባት ይፈጠራል፡፡ ሁለቱም በመከራከር ላይ ባሉበት ሁኔታ አሽከርካሪው የዋጋ ግምቱ 70ሺ ብር የሚያወጣ የሟችን ስልክ ቀምቶ ሲያመልጥ ሟች በመኪናው ጋቢና የተሳፋሪ መቀመጫ በር በኩል በመንጠልጠል ስልኩን ለማስመለስ ሲሞክር አሽከርካሪው ከስካይ ላይት ሆቴል በጉምሩክ በኩል አድርጎ ሚካኤል ውቤን እየጎተተ በማሽከርከር ቦሌ ሚካኤል የትራፊክ መብራት አካባቢ ሲደርሱ ሹፌሩ ሚካኤል ውቤን ገፍትሮ በመጣል ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጉን ፖሊስ ባደረገው ምርመራ አረጋግጧል፡፡ ተጠርጣሪው ጅብሪል ብርሃኑ ድርጊቱን እንዴት እንደፈፀመ ከተያዘ በኋላ መርቶ አሳይቷል፡፡ የምርመራ መዝገቡ እንደሚያስረዳው ክትትሉ በቀጠለበት ሁኔታ ሟች ከአትላስ አካባቢ በቪትዝ መኪና ተሳፍሮ የሄደ ስለመሆኑ ከወንጀሉ ስፍራ የተገኙ ልዩ ልዩ ማስረጃዎችን መነሻ በማድረግ በተደረገ ምርመራ ተረጋግጧል፡፡ ሟች ሚካኤል ውቤ ተሳፍሮ የሄደበት ተሽከርካሪ ሰሌዳ ቁጥር የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3B-51857 አ.አ መሆኑ ከተሳፈረበት ቦታ ጀምሮ በተደረገ ብርቱ መረጃ የማሰባሰብ ሥራ በተገኙ ማስረጃዎች መታወቁን ተከትሎ አሽከርካሪውን ለመያዝ በተደረገ ጥረት ወንጀሉን በመፈፀም የተጠረጠረው ጅብሪል ብርሃኑ ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ በተለያያዩ ጊዜያት ከባህዳር ከተማ እስከ ሐሙሲት ከሐሙሲት እስከ ሱሉልታ ማንነቱን እየቀያየረ ቢደበቅም የምርመራና የክትትል ቡድኑ ከብዙ እልህ አስጨራሽ ድካምና ብርቱ ክትትል በኋላ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ/ም በሱሉልታ ከተማ ከእነ ተሽከርካሪው እንደተያዘ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡ https://www.facebook.com/share/p/1MKxPcJ8hh/ via AA police
Show all...
240👍 63😭 35💔 14👏 8😍 2😱 1🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
ስለ QR code ምን ያህል ያውቃሉ?? 📌ግብር ከፋዮች Qr code ያለበት ደረሰኝ እንዲይዙ አስገዳጅ አሰራር ከተዘረጋ ውሎ አድሯል። ለመሆኑ QR code ምን ማለት ነው? QR code የሚለው ቃል ከእንግሊዝኛ "Quick Response code" የመጣ ነው፣ ትርጉሙም "ፈጣን ምላሽ ኮድ" ወይም ፈጣን መመለሻ; ማለት ነው። ኮዱ ሲፈጠር ዋናው አላማው የምርቶችን መረጃ በፍጥነት ለመከታተል ነበር። QR code ምንድነው? QR code ከምናውቃቸው ባርኮዶች (bar codes) ጋር ተመሳሳይ ነው፣ ነጭና ጥቁር ካሬዎች ያሉበት ዕቃ ወይም ምስል ሆኖ በጣም ብዙ መረጃ ሊያከማች የሚችል የዓይን አሻግር ቋንቋ (machine-readable language) ነው፡፡ ይህንን በስልክ ካሜራ ወይም በQR መቃኛ መተግበሪያ ሲቃኝ በፍጥነት መረጃ ይከፍታል፡፡ይሰጠናልም፡፡ QR code ለምን ይጠቅማል? QR code ነገርን በፍጥነትና ቀላል መንገድ ለመድረስ የሚረዳ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ የመረጃ ማግኛውን መንገድ ፈጣን፣ ቀላል እና የበለጠ አመቺ አድርጓል። በዚህም ሕይወታችንን ቀላል አድርጎታል። ስለምንገዛቸው ምርቶች እንዲሁም ስለምንቀበላቸው ደረሰኞች ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት በቀላሉ ያስችለናል፡፡ አሁን ላይ ግብር ከፋዮች QR code ያለበትን ደረሰኝ እንዲጠቀሙ ይገደዳሉ፡፡ በዚህም ስለ ግብር ከፋዩ ግለሰብ ወይም ድርጅት ሙሉ መረጃ ደረሰኙን QR Scan በማድረግ ማወቅ ይቻላል፡፡ በማንኛውም ስልክዎ በመተግበሪያ (App Store ወይም Play Store) ላይ "QR Scanner" ብለው በመፈለግ ነፃ መተግበሪያ በማውረድ መጠቀም ይችላሉ።via Fontenina Wasu Mohammed - Mereja
Show all...
100👍 7🙏 5🙈 5🏆 4🔥 2😱 2🎉 1
Photo unavailableShow in Telegram
"የነዳጅ ችግር የለም" ባለስልጣኑ የነዳጅ ሰልፍ የተከሰተው ከአቅርቦት እጥረት ሳይሆን በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን በሚሰራጭ የተሳሳተ መረጃ ነው ተብሏል። በአዲስ አበባ ከተማ ሰሞኑን የሚስተዋል የነዳጅ ሰልፍ በአቅርቦት ችግር ሳይሆን በተሳሳተ መረጃ ምክንያት መሆኑን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል። በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለውን የነዳጅ ሰልፍ ተከትሎ ባለስልጣኑ የማጥራት ስራ መስራቱን እና በዚህም የአቅርቦት እጥረት አለመኖሩን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ በቀለች ኩማ ለመነኻሪያ ሬዲዬ ሲናገሩ ሰምተናል፡፡ በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን አማራጮች ከዋጋና አቅርቦት ጋር በተገናኘ የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎችን ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች የነዳጅ ሰልፎች እንደሚስተዋሉም ገልፀዋል። ባለስልጣኑ በከተማዋ በተለመደው መሰረት ነዳጅ እያቀረበ እንደሚገኝ ያስታወቁት ሀላፊዋ በቀጣይ ቀናትም ምንም አይነት የአቅርቦት ችግር እንደማይፈጠር አስታውቀዋል፡፡ ተጠቃሚው ትክክለኛውን መረጃ በማረጋገጥ አማራጭ የነዳጅ ማደያዎችን በመጠቀም አላስፈላጊ ሰልፎች እንዳያጋጥሙ ሊያደርግ እንደሚገባም ሃላፊዋ አመላክተዋል፡፡ አክለውም በከተማዋ በሁሉም የነዳጅ ማደያዎች በየእለቱ ከ1 ሚሊየን ሊትር በላይ የቤንዚን አቅርቦት መኖሩን ገልጸዋል። የከተማዋ ንግድ ቢሮ በበኩሉ የነዳጅ አቅርቦት ችግር ሳይኖር በህገ ወጥ አሰራር ተጠቃሚውን የሚያጉላሉ አካላት ላይ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
Show all...
112😁 25🙏 11👍 9🙉 8😱 4🎉 4🙊 4😍 3
Photo unavailableShow in Telegram
ከቃል በላይ ያስረከብናቸው ከ 8 በላይ ሳይቶች ማሳያ ናቸው #ቴምርሪልስቴት ‼️ሳር ቤት ቫቲካን 🎯65/35 አከፍፈል 👉2መኝታ 81ካሬ ሙሉ ክፍያ 6ሚሊዮን 👉2መኝታ 106ካሬ ሙሉ ክፍያ 7.9ሚሊዮን 👉3መኝታ 139ካሬሙሉ ክፍያ 10.3ሚሊዮን 🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል 👉2መኝታ 81ካሬ 20%ቅድመ ክፍያ 1.86ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 9.3ሚሊዮን 👉2መኝታ 106ካሬ 20% ቅድመ ክፍያ 2.4ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 12.1ሚሊዮን 👉3መኝታ 139ካሬ 20%ቅድመ ክፍያ 3.1ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 15.9ሚሊዮን ‼️አዋሬ 🎯65/35 አከፍፈል 👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን 🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል 👉 1መኝታ 78ካሬ 20%ቅድመ ክፍያ 1.7ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን                  👉3 መኝታ 117ካሬ 20%ቅድመ ክፍያ  2.6ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 12.9ሚሊዮን 👉 157ካሬ = 20% ቅድመ ክፍያ 3.4ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን    #ልብይበሉ              #ቀሪውን 80% በ 15ዙር  ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ  ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት * 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇👇👇 +251939770177 +251996856273 https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Show all...
26👏 1
አምስቱ በእስራት ተቀጡ‼ በምዕራብ ሸዋ እና  በሰሜን ሸዋ  ሁለት ዞኖች ውስጥ የጠለፋና የእገታ ተግባር የፈፀሙ አምስት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ።እንደ ምዕራብ ሸዋ ዞን የአደአ በርጋ ወረዳ አቃቢ ሕግ ፅህፈት መግለጫ 1ኛ ተከሳሽ ግርማ ሳሕሉ 2ኛ ተከሳሽ ፀጋ ሐይሉ 3ኛ ተከሳሽ  ቶሊ ደጉ የተባሉ ሶስት ተከሳሾች ጥቅምት 11 ቀን 2018ዓም ከቀኑ ዘጠኝ ሠዓት ላይ ለአንደኛው ተከሣሽ በግዳጅ የትዳር አጋሩ ለማድረግ የአስራ አራት ዓመቷን ታዳጊ ከወፍጮ ቤት ስትመለስ ጠብቀው የጠለፋ ተግባር ፈፅመው ለማምለጥ ሲሞክሩ ተጠላፊዋ ባሰማችው የድረሱልኝ ጩኸት ስልጠና ላይ የነበሩ የፀጥታ አካላት ሰምተው ተከታትለው በቁጥጥር ስር ዉለዋል። ሶስቱም ተከሳሾች በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኃላ በፖሊስ የምርመራ መዝገባቸው  በበቂ ማስረጃ ተጣርቶ ለአቃቤ ሕግ የተላከ ሲሆን አቃቤ ሕግም በወንጀል ሕግ ቁጥር 587 ንዑስ አንቀፅ 1 ሴትን በመጥለፍ ወንጀል ክስ መስርቷል፡፡ ክሱን ሲከታተል የቆየው የአደአ በርጋ ወረዳ ፍርድ ቤት ጥቅምት 24-2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሶስቱም ተከሣሾች ላይ በእያንዳዳቸው ላይ በሉለት አመት ከሶስት ወር እስራት እንደተወሰነባቸው የአቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት መግለጫው አመልክቷል። በተመሳሳይ በወረጃርሶ ወረዳ ሌንጮ ቦርሱ ቀበሌ የጦር መሣርያ በመታጠቅ የእገታ ተግባር ሲፈፅሙ የነበሩ ግለሰቦች በእስራት ተቀጠተዋል።እንደ ወረጃርሶ ወረዳ አቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት መግለጫ  ደሬሣ ተሾመ እና ጀማል ደምሴ የተባሉ ሑለት ተከሳሾች ለግዜው እጃቸው ካልተያዙ ሑለት ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን የጦር መሣርያ በመታጠቅ  መስከረም 25 ቀን 2018 ዓም ሁለት ግለሰቦችን አግተው አፍነው ለመውሠድ ሲሞክሩ በፀጥታ ስራ ላይ በተሠማሩ አካላት በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል። ፖሊስም በሁለቱ ተከሣሾች ላይ አስፈላጊውን ማስረጃ በማሠባሰብ አጠናክሮ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ሕግ የላከ ሲሆን አቃቤ ሕግም ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በጦር መሣርያ በመታገዝ የእገታ ተግባር መፈፀምን ጠቅሶ ክስ የመሠረተ ሲሆን ክሱን ሲከታተል የቆየው የወረጃርሶ ወረዳ ፍርድ ቤት ሕዳር 24 ቀን 2018ዓም በዋለው ችሎት አንደኛ ተከሣሽ ደሬሣ ተሾመ ስምንት አመት ከአራት ወር  እስራት ሁለተኛ ተከሳሽ ጀማል ደምሴ በስድስት አመት ከስድስት ወራት እስራት እንዲቀጡ የወሠነ መሆኑን የአቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት መግለጫ አመላክቷል። Via Dagu
Show all...
84🙏 15🎉 4😱 3😍 3😢 1
00:31
Video unavailableShow in Telegram
MAF Chicken fried Bole Michael Traffic Light Road to Bulbula, Beside Jafar Mosque. 0937162222 0938924444
Show all...
1.55 MB
27👍 6😱 1💩 1