2025 year in numbers

127 408
Subscribers
-6624 hours
-2667 days
-76830 days
Posts Archive
Repost from TgId: 1401419976
Photo unavailableShow in Telegram
🧑💻 #GTSTv2 Round 13
GTSTv2 ተመልሷልልል⚡
⚡Ethical Hacking ለመማር ጊዜዉ አሁን ነዉ.
📣አሁኑኑ ተመዝገቡ!!!
Course Contents:
✅ Cyber Security Fundamentals
✅ Programming, Networking and Linux/UNIX for hackers
✅ Web Hacking and System Hacking Fundamentals
✅ Defensive Security Fundamentals
✅ Report and Documentation
👑 ትምህርት ታህሳስ 6 ይጀመራል
እስከ ህዳር 28, 25% ቅናሽ ያገኛሉ
🏪 ለበለጠ መረጃ + Registration ☄️
🎥LINK: https://course.geezsecurity.com/course/gtst
Contact Us
✅ @geezsecsupport
📞 +251953537820
📬 info@geezsecurity.com
#geeztech #gtstv2 @geeztechgroup
Photo unavailableShow in Telegram
#JimmaUniversity
ጅማ ዩኒቨርሲቲ በአዲስ አበባ ካምፓሱ የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎችን በመቀበል በድጋሜ ሥራ አስጀምሯል።
በርካቶች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ በላኩት መልዕክት የካምፓሱን የአዲስ አበባ አድራሻ ጠይቀዋል፡፡
የካምፓሱ አድራሻ፦
ካዛንቺስ፣ ከራዲሰን ብሉ ሆቴል ፊት ለፊት፣ የቀድሞው ዘመን ባንክ ዋና ቢሮ የነበረበት
ስልክ ቁጥር
0978464748 / 0979464748
Email: info@alliance-academy.com
ካምፓሱ በፕሮጀክት ማኔጅመንትና ፋይናንስ፣ በቢዝነስ አስተዳደር እንዲሁም በሄልዝ ሞኒተሪንግ እና ኢቫሉዌሽን የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎችን ተቀብሏል፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ "የኒውክሊየር ኃይል ለዘላቂ ልማት በኢትዮጵያ" የሚል የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል።
መድረኩ በኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን፣ የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተዘጋጀ ነው።
የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሚካይል ቹዳኮቭ ገለጻውን የሚያቀርቡ ይሆናል።
መድረኩ ነገ ህዳር 29/2018 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ሰዓት በዋናው ግቢ የኢትዮጵያ ጥናት ኢንስቲትዩት ራስ መኮንን አዳራሽ ይካሔዳል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
00:14
Video unavailableShow in Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
IMG_0425.MOV1.10 MB
በርካታ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች “የቃልኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክት“ በ2018 ዓ.ም አስጀምረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተግባራዊ ሆኖ ውጤታማ የሆነ ፕሮግራም ሲሆን፤ አዲስ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ተቋሙ ከሚገኝበት ከተማ ነዋሪዎች ጋር ጥብቅ ትስስር የሚፈጥሩበት ነው።
ፕሮጀክቱን በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ለማስጀመር ሰላም ሚኒስቴር እና ትምህርት ሚኒስቴር ስምምነት ማድረጋቸው ይታወሳል።
ፕሮጀክቱን በዚህ ዓመት ካስጀመሩ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል መቱ ዩኒቨርሲቲ አንዱ ነው፡፡
ዩኒቨርሲቲው የአንደኛ ዓመት ተማሪዎችን ከቃልኪዳን ቤተሰቦቻቸው ጋር የማስተሳሰር መርሐግብር አካሒዷል። ተማሪዎቹ እና የቃልኪዳን ቤተሰቦቻቸውን በፊርማ እና በቃለ-መሃላ ማስተሳሰር ተችሏል።
የቃልኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክት ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎች በሚሔዱ ተማሪዎች መካከል የባህልና የቋንቋ ትስስርን ለማጠናከር እንደሚያግዝ ይታመናል።
ምስል፦ መቱ ዩኒቨርሲቲ
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
00:14
Video unavailableShow in Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
IMG_0425.MOV1.10 MB
ለአማራጭ መምህርነት ስልጠና ምዝገባ አድርገዋል?
ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የመምህርነት ሙያን መቀላቀል ለሚፈልጉ አመልካቾች የአንድ ዓመት ስልጠና ለመስጠት ከህዳር 16/2018 ዓ.ም ጀምሮ ምዝገባ እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
ስልጠናው በተመረጡ ስድስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ ሲሆን፤ ስልጠናውን በቀን መርሐግብር የሚወስዱ ተማሪዎች የትምህርት ወጪያቸው ሙሉ ለሙሉ በመንግሥት እንደሚሸፈን ተገልጿል።
ኦንላይን የመመዝገቢያ ሊንኮች፦
➫ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፦ https://portal.ju.edu.et
➫ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፦ https://portal.hu.edu.et/Home/AvailablePrograms
➫ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፦ https://forms.gle/6t1BNV9S67oXwzBv9
➫ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፦ https://forms.gle/Y7Hksp5Ymk7Nx7d9A
➫ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፦ https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfQcnu1ThOSSsUp9d3XI80NszyyETOwtJPxWNRh68izA7Gd2A/viewform?usp=header
➫ መቐለ ዩኒቨርሲቲ፦
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdRwj89yQ50AiUeZZeDe8tr8aJ5GQZO4B0IqUVJzJJCNJzWPQ/viewform
🔔 የተቀመጡት ሊንኮቹ ይሰራሉ፡፡ ካስቸገሩዎት ግን ቆየት ብለው በተለያዩ ሰዓታት ይሞክሯቸው፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#DambiDolloUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 21 እና 22/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ8-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ መጠኑ 3x4 የሆነ የቅርብ ጊዜ 8 ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#FellowshipOpportunity
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የውስጥ ደዌ ህክምና ትምህርት ክፍል ብቁ አመልካቾችን ለ2018 ዓ.ም Adult Nephrology Fellowship ፕሮግራም አወዳድሮ መቀበል ይፈልጋል።
ለዚህ ዓመት ሦስት (3) የፌሎውሺፕ ዕድሎች መኖራቸውን ኮሌጁ ገልጿል።
የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም
የቅበላ መስፈርት፦
➫ ከታወቀ የህክምና ትምህርት ተቋም በህክምና ዲግሪ ያለው ያላት,
➫ በ Internal medicine የሬዚደንሲ ፕሮግራም ያጠናቀቀ/ች፣
➫ Internist ሆኖ/ሆና ለሁለት ዓመት ያገለገለ/ች፣
➫ የቅበላ ምልመላ ሒደት የሚያጠናቅቁ፣
➫ በኢትዮጵያ የውስጥ ደዌ ህክምና ለመስጠት ተመዝግቦ ፈቃድ ያለው/ያላት፣
➫ ጥሩ አዕምሯዊና አካላዊ ጤና ያላት/ያለው፣
➫ አጭር የፍላጎት መግለጫ ማስገባት፣
የማመልከቻ አማራጮች፦
ፍላጎት ያላችሁ አመለልካቾች በ Internal ህክምና ትምህርት ክፍል በአካል በመቅረብ ወይም በኢሜል አድራሻዎች ayantu17@yahoo.com / lejahamza@yahoo.com ማመልከት ይችላሉ፡፡
አመልካቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ፦
➫ የማመልከቻ ደብዳቤ
➫ የቅርብ ጊዜ CV
➫ የትምህርት ማስረጃዎች (ዲግሪ እና የውጤት መግለጫ)
➫ ሁለት የድጋፍ ደብዳቤዎች
➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ (በመንግሥት ስፖንሰር ለምትደረጉ)
➫ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) ውጤት
ለበለጠ መረጃ፦
➫ Dr. Ayantu Tesfaye 0911890635
➫ Dr. Leja Hamza 0917804057
የፅሑፍ እና የቃል ፈተና የሚሰጥባቸው ጊዜያት በቀጣይ ይገለጻል የተባለ ሲሆን፤ ትምህርት ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎችን ሙሉ በሙሉ መቀበል እንዳልቻሉ አስታወቁ
የመቐለ እና አዲግራት ዩኒቨርስቲ በትግራይ ክልል አልፎ አልፎ በሚስተዋሉ፤ የፀጥታ ስጋቶች እና በተያያዥ ገፊ ምክንያቶች ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የመደበላቸውን የተማሪዎች ቁጥር ሙሉ በሙሉ መቀበል አለመቻላቸውን አስታውቀዋል።
ለዚህ ምክንያት የሆነው ደግሞ "አንዳንዶቹ ተማሪዎች በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከፍለው መማር የሚችሉ ስለሆኑ እንዲሁም፣ አንዳንዶቹ ደግሞ በቤተሰብ ጫና ምክንያት ርቀው እንዳይሄዱ ስለሚደረጉ ሊሆን ይችላል" ሲሉ ጠቁመዋል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
ራያ ዩኒቨርሲቲ ሁለት የፈጠራ እና የምርምር ዲጂታላይዜሽን ሥራዎች አስመርቋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በተቋሙ መምህራንና ተመራማሪዎች የበለጸጉ ሁለት የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን ይፋ አድርጓል፡፡
ግእዝን በሞባይል መማር የሚያስችል 'ፍኖተ-ግእዝ' የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ እና የምርምር ፖርታል በዩኒቨርሲው ይፋ የተደረጉ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች ናቸው፡፡
ፍኖተ-ግእዝ የሞባይል መተግበሪያ የእጅ ስልክን በመጠቀም መሰረታዊ የግእዝ ቋንቋ ክህሎቶችን ለማበልፀግ የሚያግዝ የሞባይል አፕሊኬሽን መሆኑ ተገልጿል።
የምርምር ፖርታሉ የዩኒቨርሲቲውን የምርምር ውጤቶች ዲጅታል ቋት፣ የምርምር መረጃዎች አስተዳደር ስርዓት እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን የሳይንስና ልማት ጆርናል (RJSD) አንድ ላይ የሚያጠቃልል ነው ተብሏል፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ መደበኛ የአማርኛ መዝገበ ቃላት እያዘጋጀ ነው፡፡
ዩኒቨርሲቲው “የአማርኛ ልሳነ ዋሕድ መዝገበ ቃላት ዝግጅት ጥናት ንድፍ“ በሚል የውይይት መርሐግብር በቅርቡ አካሒዷል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የሚዘጋጀው መዝገበ ቃላት ዘመኑን የዋጀ፣ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ጋር የተቀመረ እና ዲጂታልንም ታሳቢ ያደረገ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
የመጀመሪያው የአማርኛ መዝገበ ቃላት እ.አ.አ. በ1698 ዓ.ም የታተመ ሲሆን፤ የከሣቴ ብርሃን አማርኛ መዝገበ ቃላትን ጨምሮ በተለያዩ ጊዚያት የአማርኛ ቋንቋ መዝገበ ቃላት ታትመዋል፡፡
የሳይንስና ቴክኖሎጂ እንግሊዝኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት በቅርቡ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ለህትመት መብቃቱ ይታወሳል፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
የሰላሌ ዩኒቨርስቲ ከ 3ሺህ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካማ የሕብረተሠብ ክፍሎች የነፃ የሕግ አገልግሎት መስጠቱን አስታወቀ
የሰላሌ ዩኒቨርስቲ የሕግ አገልግሎት ለሚያስፈልጋቸው ሶስት ሺ አራት መቶ ዘጠና ስድስት አቅመ ደካማ የማህበረሰብ አካላት የተለያዩ የሕግ አገልግሎት ሰጥቷል።
የዩኒቨርስቲ የሕግ አገልግሎት ዲን አቶ አቤል ከተማ እንደገለፁት የነፃ የሕግ አገልግሎቱ የተሰጠው አቅመ ዳካማ ለሆኑ ፣ በእድሜ ለገፉ፣ ጥቃት ለደረሠባቸው ሴቶች ና ሕፃናት፣በከፍተኛ ሕመም ለሚገኙ እና በማረሚያ ቤት ሆነው የፍርድ ሂደታቸውን ለሚከታተሉ ታራሚዎች የነፃ የሕግ አገልግሎት ነው ብለዋል።
በዚህም ለሁለት ሺህ ሠባት መቶ ሀምሳ ስድስት ወንዶች እንዲሁም ለሰባት መቶ አርባ ሴቶች አገልግሎቱ ተሰጥቷል። በነፃ አጉልግሎቱ ስድስት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ ብር ከወጪ ማዳን የተቻለ ሲሆን የሰላሌ ዪኒቨርስቲ በስሩ የሚተዳደሩ አራት ቋሚ የሕግ አገልግሎት መስጫና እና አንድ ተንቀሳቃሽ የሕግ ማዕከል አቋቁሞ በመንቀሣቀስ በተለየ መልኩ በሕፃናት እና ሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን እንደዚሁም ያለ እድሜ ጋብቻ፣የቤተሰብ ግጭቶች እና ትንኮሳዎች ላይ ሰፊ የሕግ መሰረት ያደረገ አገልግሎት መስጠቱን አቶ አቤል ከተማ ጨምረው ገልፀዋል::
ፆታዊ ጥቃትን በተመለከተ ከጋብቻ ውጭ የተወለዱ እና የሚጣሉ ሕፃናት ማቆያ ለመገንባት ከፍትህ አካላት ጋር የጋራ ስምምነት የተደረሠ ሲሆን ባለፈው አመት ሶስት ሕፃናት ተጥለው የተገኙትን የሠላሌ ዩኒቨርስቲ ተረክቦ በአበበች ጐበና ካምፖሱ ባለው ጊዚያዊ ማቆያ በማቆየት በሕጋዊ መንገድ ለጉዲፈቻ ተሰጥተዋል።
በዩኒቨርስቲ ውስጥ የሴት ተማሪዎች ላይ የሚደርሰውን ትንኮሳ እና ጥቃት ለመከላከልም የተቋቋመ ኮሚቴ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ሲሆን በአጠቃላይ የፍትሕ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት የተደረገው ስምምነት ከፍተኛ ውጤት እንደሚያመጣም ተመላክቷል።
#ዳጉ_ጆርናል
Photo unavailableShow in Telegram
በ2018 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ዝውውር ያመለከታችሁ ተማሪዎች በሙሉ መሀል ሜዳ ካምፓስ የተመደባችሁ መሆኑን ተቋሙ ገልጿል፡፡
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለመከታተል የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ታህሳስ 02 እና 03/2018 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#AdigratUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 06 እና 07/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
ትምህርት ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት መጠኑ 3x4 የሆነ የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
