en
Feedback
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

Open in Telegram

Journalist-at-large

Show more
2025 year in numberssnowflakes fon
card fon
133 768
Subscribers
-1024 hours
-1197 days
-58130 days
Posts Archive
Photo unavailableShow in Telegram
ውድ የህግ ትምህርት ቤት መምህራችን፣ የማህበራዊ ሚድያ ድምቀት እና የሰላ አስተሳሰብ ባለቤት የነበረው መምህር ሀሰን መሐመድ ተለይቶናል። ነፍስህ በሰላም ትረፍ፣ ሀሰኖ!
Show all...
😢 849 103🕊 46👍 23🙏 23
Photo unavailableShow in Telegram
የመሠረት ሚድያ የፕሪሚየም አባል ሆነዋል? ካልሆኑ በታቸለ መጠን በርካቶች መረጃዎቹን ማግኘት እንዲችሉ ከሚደረገው ጥረት አንዱ በሆነው የ50% ቅናሽ ተጠቅመው አባል ይሁኑ። ሊንክ ⤵️ https://meseretmedia.substack.com/subscribe?coupon=87fb8725
Show all...
😁 6 3👍 3
ከሰሞኑ በርካቶች የኤሌክትሪክ ካርድ ሲሞሉ እጥፍ እና ከእጥፍ በላይ እየተጠየቁ መሆኑን እና ምክንያቱን እንደማያውቁ ሲገልፁ ነበር። እውነታው እንዲህ ነው፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ወደኋላ ተጎዞ ከመስከረም 2017 ዓ/ም ጀምሮ ውዝፍ የቫት ክፍያ ማስከፈል በመጀመሩ ነው። ዝርዝሩን ከመሠረት ሚድያ: https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/56e?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
Show all...
😢 381 69😱 35🤔 23👍 22🙏 5
Photo unavailableShow in Telegram
መሴ፣ ይህ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ቢሮም ሆነ የፕሬዝደንቱ መቀመጫ ወንበር አይደለም። በቅርቡ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ 'Pennsylvania Avenue' ላይ የተከፈተ ተመሳስሎ የተሰራ የቱሪስቶች ማዕከል ነው። ኋይት ሀውስን ለመጎብኘት በኮንግረስ ወይም በሴኔተር ተወካይ በኩል ጥያቄ ቀርቦ እና ቀጠሮ ተይዞ የሚከናወን ሲሆን የፕሬዝደንቱን ቢሮ (West Wing Oval Office) ለመጎብኘት ግን በልዩ ግብዣ ካልሆነ ፈፅሞ መግባት እንደማይቻል መረጃዎች ያሳያሉ (ወንበር ላይ መቀመጥ... Good luck with that 😄). ምናልባት ያስጎበኙህ ሰዎች አሳስተውህ ይሆናል፣ ሚድያ ላይ ያለን ሰዎች ግን እንዲህ መረጃ ስንለቅ ለህዝብ ማስተማሪያም እንዲሆን ትክክለኛ ቢሆን 🙏🏽 @EliasMeseret
Show all...
😁 1 596 191👍 118😢 19🤔 17🕊 14😱 5
Photo unavailableShow in Telegram
አንድ የቀድሞ ሚኒስትር ዴኤታ፣ ያሁን ዩትዩበር ፎቶዬን ለጥፎ 'መሠረት ሚድያ ከሀምሌ 1 ጀምሮ የመንግስት ሰራተኛ ቅነሳ አለ ብሎ ዋሸ' ሲል ነበር። ዛሬ ሀምሌ 1 አይደል? ይኸው ማረጋገጫው ከፈረሱ አፍ... #TruthMatters @EliasMeseret
Show all...
295😁 165👍 45🤔 29🕊 9😢 7🙏 4
Photo unavailableShow in Telegram
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ ወገራ ወረዳ ገደብጌ ከተማ ውስጥ 11 ንፁሀን ዜጎች ትናንት በመንግስት ሀይሎች በተወሰደባቸው የበቀል እርምጃ ህይወታቸው አልፏል። የከተማው ነዋሪዎች ትናንት የድረሱልን ጥሪ ሲልኩ አንድ ዜና መሠረት ሚድያ ላይ ወጥቶ ነበር (https://tinyurl.com/yz6r7yvr) ከሆስፒታል ምንጮች እና ከገደብጌ ከተማ ነዋሪዎች የደረሰኝ መረጃ እንደሚጠቁመው አብዛኞቹ እድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ 11 ሰዎች ናቸው ከቤታቸው እንዲወጡ እየተደረገ የተገደሉት። ሞትን በጣም ከመለማመዳችን የተነሳ ይህን ያህል ቁብ ሳይሰጠን የምናልፈው ነገር እጅግ የሚያሳዝን ሆኗል። ፎቶውን በስፍራው ያሉ ሰዎች ያደረሱኝ ነው። ነፍስ ይማር! @EliasMeseret
Show all...
😢 860 105👍 21🕊 21😱 8😁 6🙏 6🤔 3
አጨብጭቦ ማፅደቅ የማይሰለቻቸው 'የህዝብ እንደራሴዎች' በህዝብ ጩኸት እና በተቋማት ተቃውሞ ሰውን ማሰቃየት (torture) የሚፈቅደውን አዋጅ ከፀደቀ 20 ቀን ሳይሞላው ቀይረውታል። የህዝብ ድምፅ መስማታቸው ጥሩ ቢሆንም አሁንም ግልፅ ያልሆነው 'ምን በሚል ተቀየረ?' የሚለው ነው። የሚያሳዝኑት ቶርቸር እንዴት አስፈላጊ እንደሆነ ሲያስረዱ እና ሲተነትኑ የነበሩ አንዳንድ የፓርላማ አባላት እና የህግ ምሁራን ናቸው። #StopTorture #ዜናመሠረት ወንጀል መርማሪ ከግድያ ውጭ በማንኛውም መልኩ መመርመር እንዲችል የሚፈቅደው ህግ ከፀደቀ ከ20 ቀን በኋላ ማሻሻያ ተደረገበት በርካታ ግለሰቦች፣ ተቋማት እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ህጉ ማሰቃየትን (torture) ጨምሮ ግፎች በዜጎች ላይ እንዲፈፀም በር ይከፍታል ብለው ሲሞግቱ ነበር። ተጨማሪ ያንብቡ: https://tinyurl.com/yrrby32a
Show all...
261👍 101😢 46🤔 26😁 22
Photo unavailableShow in Telegram
Happy Birthday, America! Land of The Free! @EliasMeseret
Show all...
😁 437👍 237 121🤔 34🙏 28🕊 6😱 5😢 4
Photo unavailableShow in Telegram
ኢቢሲ ይህን ዛሬ ስለ ዩጋንዳ ቢዘግብም ከቀናት በፊት ጎርጎራ ላይ ተከስክሶ የአንድ የካሜራ ባለሙያን ለሞት፣ በርካታ ባለስልጣናትን ለከፍተኛ አካላዊ ጉዳት ስለዳረገው የሄሊኮፕተር አደጋ አንድም ዜና አልሰራም (መሠረት ሚድያ በዚህ ዙርያ ሁለት ዘገባዎች አቅርቦ ነበር)። ለዚህም ነው እንደ #መሠረትሚድያ ያሉ ነፃ፣ መረጃን የማያሸሹ እና እውነትን አፈላልገው የሚያወጡ ሚድያዎች በብዛት የሚያስፈልጉን። እስካሁን የፕሪሚየም አባል ካልሆኑ በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ ⤵️ https://meseretmedia.substack.com/subscribe?coupon=87fb8725
Show all...
👍 586😁 179 123🤔 21😢 8🕊 5🙏 4
Photo unavailableShow in Telegram
በቅርብ አመታት በመንግስት እና ህዝብ ትብብር ከተሰሩ ድንቅ ስራዎች አንዱ በአረንጓዴ አሻራ ሀገሪቱን አረንጓዴ ለማልበስ እየተደረገ ያለው ጥረት ነው። በስራም፣ በግልም የማገኛቸው የውጭ ሀገር ዜጎችን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በአድንቆት የሚገልፁት ትውልድ ተሻጋሪ ስራ ነው። A job well done on this one 👏 @EliasMeseret
Show all...
👍 1 008😁 171 143🙏 36🤔 33😢 7😱 6🕊 6
Photo unavailableShow in Telegram
ሚድያችን፣ ሚድያችሁ Substack ላይ በዜና ምድብ በፍጥነት በማደግ ከመላው አለም #5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል! አስደሳች የህዝብ ተሳትፎ ታይቶበታል፣ ሚድያው የህዝብ ድምፅ በመሆን ትክክለኛ መረጃ ለማቅረቡ አንዱ ማሳያ ነው። አሁንም ቤተሰብ እንዲሆን ሁሉም ተጋብዛል። ሊንክ: https://meseretmedia.substack.com/subscribe?coupon=87fb8725
Show all...
427👍 174😁 27🕊 14
00:21
Video unavailableShow in Telegram
#መሠረትሚድያ Subscription በመጀመሩ አንዳንድ ወገኖች ቅር ተሰኝተዋል፣ ግን ደግሞ ስራው እንዲቀጥል ከተፈለገ ሚድያው ራሱን ችሎ መሄድ ግድ ይለዋል። ብዙ ሰው አባል እንዲሆን በግሌም፣ ሌሎች በጎ ሰዎች የሚሰጡትን ድጋፍም እያቀረብኩ ከ220 በላይ ሰዎች በነፃ አባል ሆነዋል። ዛሬ ደግሞ ብዙ ተጨማሪ ሰው አባል እንዲሆን በማሰብ ለ24 ሰአት የሚቆይ የ50% ቅናሽ ተደርጓል። ይህን ሊንክ ተጠቅመው: https://meseretmedia.substack.com/subscribe?coupon=87fb8725 *መሠረት ሚድያ በጀመረው subscription ራሱን ችሎ መሄድ የሚያስችለው ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህ የ50% ቅናሽ የተደረገው አንዳንዶች ዋጋው ቢቀንስ በሚል አስተያየት ስለሰጡ ነው። @EliasMeseret
Show all...
6.94 MB
👍 219 119😁 49🤔 5🕊 3
Photo unavailableShow in Telegram
ፕሬዝደንት ትረምፕ ህዳሴ ግድብን ፋይናንስ ያረገችው ሀገራቸው መሆኗን ቢናገሩም መንግስት ማስተባበያ እንኳን ሳይሰጥ አለፈው የሚል አስተያየት አቅርቤ ነበር። አንድ የመንግስት ሀላፊ ግን በውስጥ መስመር 'አንዱ ምክንያት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ተገማች ስላልሆኑ እንዳይቆጡ ታስቦ ነው...' ብለው ፃፉልኝ። ልክ እሱን ሳነብ የዛሬ 5 አመት አሜሪካ ላይ የአፀፋ እርምጃ የተዛተው ትዝ አለኝ። @EliasMeseret
Show all...
😁 1 236 106👍 37😢 18😱 10🤔 9🕊 3
Photo unavailableShow in Telegram
ብርቱካን... ብርቱካን... ብርቱካን በሚል ጉዳይ በመቶዎች የሚቆጠር የዜና ዘገባ፣ ዶክመንተሪ፣ ሪፖርታዥ፣ ውይይት፣ ፖድካስት፣ መግለጫ፣ ማብራርያ እና ትንታኔ ሲያቀርቡ የነበሩ የመንግስት ሚድያዎች ትረምፕ 'የህዳሴ ግድብን ፋይናንስ ያረግነው እኛ ነን፣ ግድቡ የናይል የውሀ መጠንን ይቀንሳል' ብለው የተዛባ መረጃ ለመላው አለም ሲለቁ ፀጥ ለጥ ብለዋል። ስለ ኢራን እና እስራኤል በየቀኑ የሚያቀርቧቸውን ከደርዘን በላይ ዜናዎችን ስንመለከት ተመሳሳይ ጥያቄን ያጭራል። አንዲት ተጎዳሁ ብላ ሚድያ ላይ የወጣች ዜጋ ላይ እንደዛ ከመረባረብ ይሄኔ ነበር እንጂ የሀገርን እውነት ይዞ መሞገት። Misplaced priorities, usual! @EliasMeseret
Show all...
1 049👍 416😢 59🙏 46😁 42🤔 11😱 6🕊 4
Photo unavailableShow in Telegram
እዚህ ጋር ደግሞ ሌላ ነጭ ውሸት ⤵️ #ዜናመሠረት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ሀገራቸው የህዳሴ ግድብን ፋይናንስ አድርጋለች የሚል ሀሰተኛ መረጃ አሰራጩ ፕሬዝደንት ትረምፕ የፃፉት መረጃ ሀሰት የመሆኑ አንድ ማሳያ ግብፅ እና ኢትዮጵያ ስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻላቸው የዛሬ አምስት አመት አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከምትሰጠው ሰብአዊ እርዳታ ላይ 100 ሚልዮን ዶላር መቀነሷ ነው። አሜሪካ ለግድቡ የምታደርገው ድጋፍ ባለመኖሩ ያቋረጠችው የህዳሴ ግድብ ድጋፍን ሳይሆን አሜሪካ ለኢትዮጵያ በአጠቃላይ ከምትሰጠው እርዳታ ላይ ነበር። ለሁሉም አንባቢ ክፍት ሆኖ የቀረበውን ይህን መረጃ ያንብቡ: https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/839?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
Show all...
😁 173 93👍 82🕊 9🙏 8😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
የዚህ የማረሚያ ቤት ውስጥ የአደንዛዥ እፅ ዝውውር ዋና ተዋናይ ራሳቸው የማረሚያ ቤቱ የፀጥታ ሀላፊዎች ሆነው ተገኝተዋል። የጠፋን እቃ ከሌባው ጋር አብሮ እንደመፈለግ ማለት ነው... ⤵️ #ዜናመሠረት የቂሊንጦ እና የአባ ሳሙኤል ማረሚያ ቤት የጥበቃ ኃላፊዎችን ጨምሮ 7 ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ - ሀላፊዎቹ የገንዘብ ጥቅም ለማግኘት አደገኛ እፅ (ሀሽሽ) ለታራሚዎች በማስገባት ወንጀል ተጠርጥረው መያዛቸውን መሠረት ሚድያ አረጋግጧል ዝርዝር መረጃውን ያንብቡ ⤵️ https://tinyurl.com/4h2ju7st
Show all...
😁 124 69👍 31🤔 13
ምክር ለሚድያዎች... ከልምድ! - እከሳለሁ፣ ፍርድ ቤት እሄዳለሁ ብሎ ወጥሮ የሚያስፈራራ አካል ካለ በዘገባችሁ ያወጣችሁት እውነት አለ ማለት ነው። ሊከስ ሳይሆን በቀጣይ ሌላ ጉድ እንዳይወጣ አፍ ማዘጊያ ሙከራ ነው። - ሰራተኛ ቅነሳ አለ ሲባል የለም፣ ዜጎች ተራቡ ሲባል ውሸት፣ ሰዎች ታገቱ ሲባል ሀሰት ወዘተ ብለው ተቻኩለው የመንግስት ሚድያ ላይ ጉብ ካሉ ቀድሞ ታወቀ ብለው ማስተባበላቸው እንጂ እውነታውን ለመካድ አይደለም (damage control). - በአብዛኛው የሚድያዎች ማዋከብ ሲከሰት በአንድ ዜና ብቻ መሰረት ተደርጎ አይደለም። ለሌሎች ሚድያዎችም 'እንዲህ አይነት ዜና ብትፅፉ' የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ነው። - የመንግስት አክቲቪስቶች በአንድ ጉዳይ ላይ ሲራወጡ ካያችሁ ወይም አንድ ግለሰብ/ተቋም ላይ ሲረባረቡ ከተመለከታችሁ በመንግስት በቀጥታ ሊነገር ያልፈለገ ነገር ግን ለነዚህ አክቲቪስቶች ሾልኮ የሚሰጥ ጉዳይ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። በአጭሩ፣ ብዙ ግዜ ከሚነገረው በተቃራኒ ገልብጦ ማየት ይጠቅማል። @EliasMeseret
Show all...
👍 720 185😁 55🙏 20🤔 7
Photo unavailableShow in Telegram
#ሰላምወዳጆች የህግ ትምህርት ቤት እያለን መምህራችን የነበረው ሀሰን መሀመድ (ሀሰኖ) ከፍ ያለ ህመም አጋጥሞታል። ከዋነኞቹ ኦርጋኖቹ በተለይ ሁለቱ (ኩላሊት እና ጉበት) ንቅለ ተከላን ጨምሮ ሌሎች የውጪ ሀገር ሕክምና ይፈልጋሉ። ለዚህ ሕክምና የሚያስፈልገውን ወጪ ብቻውን እንደማይችለው ታውቋል። ከወዳጆች ውጪ ሌላ የሚኬድበት ቦታ የለምና በአንድም በሌላ አጋጣሚ ያወቃችሁት፣ ያስተማራችሁ፣ ያማከራችሁ፣ የረዳችሁ፣ ፈገግ ያስባላችሁ፣ ጩኸታችሁን ያሰማላችሁ፣ ሀሳባችሁን የገለፀላችሁ፣ በአጠቃላይ የሀሰኖ አሻራ በአዕምሮ፣ በልብ እና በሕይወታችሁ ያረፈ ሰዎች ሁሉ አሁን የሀሰኖን ሕይወት ለማዳን ትብብራችሁ ይፈለጋል።   በግል 15 ሺህ ብር አስገባለሁ፣ ሁላችን ተረባርበን ሀሰኖን አለህ እንበለው። አስተዋፅኦ ማድረጊያ ቁጥሮቹ (ንግድ ባንክ እና Zelle) በምስሉ ላይ ተቀምጧል። ፈጣሪ ጨርሶ ይማርህ።
Show all...
😢 315 185🙏 93👍 59
Photo unavailableShow in Telegram
ከዚህ በኋላ ወንጀል መርማሪዎች ተጠርጣሪ ዜጎች ላይ የፈለጉትን ያህል ጉዳት አድርሰውም ቢሆን ምርመራ ቢፈፅሙ ሞት ካላስከተለ በቀር አይጠየቁም የሚል ህግ ዛሬ ፀድቋል... በእሳት እያቃጠሉም ይሁን ጥፍር እየነቀሉ ማለት ነው። በፊት ከነበረው የፀረ-ሽብር ህግ እጅግ አሰቃቂ በሆነ መልኩ ተባብሶ መጥቷል፣ የመንግስት ሚድያዎች እንኳን ደስ አላችሁ ሳይሉን። #ሳናጣራአናስርም @EliasMeseret
Show all...
😱 681😢 382 94🤔 59😁 47🙏 15👍 1
ትናንት አንድ የመሠረት ሚድያ ተከታታይ ለ15 ሰዎች የአንድ አመት subscription በጋበዘው መሰረት 4,800 ገደማ ሰዎች ኢሜይላቸውን ልከዋል፣ ቀድመው @ContactElias ቴሌግራም ላይ ያስቀመጡ 15 ሰዎች በስክሪንሾቱ ላይ ተቀምጠዋል (ለ privacy ኢሜይላቸው እንዲደበዝዝ ተደርጓል)። https://meseretmedia.substack.com/subscribe?coupon=d75e694d
Show all...
216👍 44😢 40🙏 28😁 20🤔 3😱 3