en
Feedback
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

Open in Telegram

Journalist-at-large

Show more
2025 year in numberssnowflakes fon
card fon
133 768
Subscribers
-1024 hours
-1197 days
-58130 days
Posts Archive
እጅግ ያሳዝናል፣ ይረብሻል፣ ያማልም! 'ቶርቸር ቀርቷል' ተብሎ በአደባባይ በሚነገርበት ሀገር በአጭር እድሜው ለሀገሩ ብዙ የሰራው ኢሳያስ በላይ ልክ የዛሬ አመት በዚህ መልክ ተሰቃይቶ ህይወቱ እንዲያልፍ ሆኗል። በመሠረት ሚድያ በዚህ መልኩ ረዘም ብሎ ተዘጋጅቷል። ለሁሉም የመሠረት ሚድያ አንባቢዎች በነፃ የቀረበውን ይህን የምርመራ ዘገባ ለማንበብ ሊንኩን ይከተሉ ⤵️ https://tinyurl.com/yfbw5hm2 ተጨማሪ የምርመራ ዘገባዎች ማቅረብ እንድንቀጥል ቤተሰብ ይሁኑ፣ የመሠረት ሚድያን ስራዎች ይደግፉ ⤵️ https://substack.com/@meseretmedia
Show all...
😢 1 175👍 123😱 49 38😁 12🙏 9🤔 7
Photo unavailableShow in Telegram
የትናንቱን የድሮን ትርኢት ካቀረበው ድርጅት ጋር የነበረኝ ንግግር! የዛሬ አመት ገደማ በአድዋ ሙዚየም ምርቃት ወቅት የአፄ ምኒልክ ንግግር በሆሎግራም ቴክኖሎጂ በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች ተሰራ ተብሎ ስናጣራው ንግግሩን ያረገው አርቲስት ተስፋዬ ገብረሀና መድረክ ላይ ቀልጠፍ ብሎ ቆሞ መሆኑን ደረስንበት። በወቅቱ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በአፍሪካ ለመጀመሪያ ግዜ፣ በዓለም ደግሞ እጅግ ጥቂት ሀገራት ሊያሳኩ የቻሉትን የሆሎግራም ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ የአፄ ምኒሊክ ንግግርን አቀረበ ተብሎ ተነግሮ ነበር። ትናንት የታየውን የድሮን ትርኢት ደግሞ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በጋራ ያዘጋጁት እና ያቀረቡት መሆኑን ነገሩን። ዜናውን እንደሰማሁ ድርጅቱን ማነጋገር ጀመርኩ፣ ሲንጋፖር የሚገኘው MIRS Innovate የተባለ ተቋም ትርኢቱን ኮንትራት ወስዶ እንደሰራው በግልፅ ነገሩኝ። መጀመርያ ለመናገር ባይፈልጉም አንዱን የድርጅቱን ሀላፊ ገፋ አርጌ ስጠይቀው ለስራው 200 ሺህ ዶላር (26.8 ሚልዮን ብር ገደማ) እንደተከፈላቸው ነገረኝ። እሺ ስራው ይሰራ። ግን ውሸቱ ለምን አስፈለገ? የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ሰሩት ብሎ ከመዋሸት ስፖንሰር ያረጉት ቢባል ምን ሀፍረት አለው? የመንግስት ተቋማት በዚህ ደረጃ ተአማኒነታቸውን እንዲያጡ እየተደረገበት ያለው አካሄድ በእጅጉ ያስገርማል። መልካም ቀን። @EliasMeseret
Show all...
👍 1 576😁 475😢 165 105😱 80🤔 59🕊 9🙏 6
Photo unavailableShow in Telegram
Who did this? 😀 @EliasMeseret
Show all...
😁 968👍 288 79🤔 26🙏 19😢 7🕊 3
Photo unavailableShow in Telegram
ማነህ፣ ዲጂታል ሰራዊት፣ 'ጫ'ን ረስተሀል! @EliasMeseret
Show all...
😁 2 457👍 128🤔 40 33😱 26😢 12
Photo unavailableShow in Telegram
እንዴ 🤔 “Facts do not cease to exist because they are ignored.” — Aldous Huxley @EliasMeseret
Show all...
😁 966🤔 133👍 116😢 92😱 38 35🙏 7
Photo unavailableShow in Telegram
😀😀
Show all...
😁 1 691👍 66🤔 64 39😢 28😱 13🙏 5
Photo unavailableShow in Telegram
የዛሬ 6 አመት ገደማ የጤና ባለሙያዎች ቅሬታቸውን ለማሰማት ሰልፍ ወጥተው ነበር፣ ይሁንና በወቅቱ ቅሬታ ያስገባቸው የህክምና ግብአቶች እጥረት ስራቸውን ለማከናወን እያስቸገራቸው እንደሆነ በመግለፅ ነበር። ከስድስት አመት በኋላ ያለው ሁኔታ ከድጡ ወደ ማጡ ሆኖ ጥያቄው ከህክምና ግብአት ይሟላልን ወደ "ራበን፣ ጠማን፣ ልጆቻችን ማስተማር አቃተን" ሆነ። ይህ የሚያሳየው የጤና ባለሙያዎችም ሆኑ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ምን ያህል ኑሮ እየደቆሳቸው እንደመጣ፣ የተሻለ የተባለ ኑሮ ይኖሩ የነበሩት ወደ ድህነት፣ በድህነት ያሉት የዛሬን ውሎ ማደር መቸገር እንደጀመሩ ነው። ተደጋግሞ 'ሰው ተኮር' ስራ እየተሰራ ነው ቢባል ለህዝብ ብልፅግናን እና ሀብት አይፈጥርም፣ የሚያማምር ፕሮጀክት የሀገር ዋና ፖሊሲ ሲሆን ርሀብን አያስታግስም። አሁንም ሳይረፍድ ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ መስጠት ብልህነት ነው። የዛሬ ስድስት አመት የነበረው ቅሬታ ቪድዮ: https://www.facebook.com/share/v/1VrZukrTSt/ @EliasMeseret
Show all...
👍 821😢 72 51😁 9🙏 6😱 1
ከህዝብ የሚነሱ ጥያቄዎችን በማንጓጠጥ፣ በማናናቅ እና በምንም አታመጣም አይነት መንፈስ መመለስ ከታሪክ አለመማር ነው። የቅርብ ግዜ ታሪካችንን መለስ ብሎ ማየት ይጠቅማል፣ ጨው ለራስህ ስትል... ነው ነገሩ። ህዝብ እየጠየቀ ያለው ትርፍ ነገር ሳይሆን ራበኝ፣ መኖር አቃተኝ እያለ ነው፣ የመንግስት ትኩረት ግን ምን ላይ እንደሆነ እያየን ነው። Get real or face the fire! @EliasMeseret
Show all...
👍 1 128 106🙏 59😢 29😱 6
Photo unavailableShow in Telegram
#ያሳፍራል 4,500 ብር ገደማ የሚሸጥ የባህር ዳር- አዲስ አበባ የአውሮፕላን ትኬትን በ10,000 ብር ያውም በሌላ ሰው ስም እያዘጋጁ አንዳንድ የባህር ዳር ኤርፖርት ሰራተኞች እየቸበቸቡት ነው። ይህን በውድ የሚሸጡትን ትኬት የሚያገኙት ወይ ሌላ ሰውን ከጉዞ አስቀርተው ነው፣ ወይም በሌላ ሰው ስም ትኬት አዘጋጅተው በኋላ ትኬት ካገኘሁ በሚል ኤርፖርት ለሚሄድ ሰው እየሸጡት ነው። ይሄ ሲደረግ ያሳሰበኝ ሌላ የባሰ አደጋ ሊያስከትል የሚችል ነገር አያደርጉም ወይ የሚለው ነው። የመሠረት ሚድያን የምርመራ ዘገባ ያንብቡ: https://tinyurl.com/46t9u5ky
Show all...
😢 460👍 162😱 23 22🤔 17🙏 7😁 4
በሚቀጥሉት ዓመታት ሮቦቶች በሁሉም ቤቶች ውስጥ እንደሚኖር ጠ/ሚሩ የተናገሩትን ዛሬ አነበብኩ፣ እኔ ግን ሳስበው የኑሮ ውድነቱ በዚሁ ከቀጠለ ህዝቡ አይደለም 'ሮቦት' ሊኖረው ንብረቱን ሁሉ ሸጦ በልቶ 'ረከቦት' አይኖረውም። @EliasMeseret
Show all...
😁 1 992👍 519😢 90 51🙏 33😱 10🤔 8
Photo unavailableShow in Telegram
ከሚያንማር ወደ ሀገራችሁ እየተመለሳችሁ ያላችሁ ዜጎች እንኳን በሰላም ገባችሁ! የሶሻል ሚድያው ጩኸት ለዚህ እውን መሆን ያደረገው ከፍተኛ ተፅእኖ እንዳለ ሆኖ ልጆቹ ካሉበት አስከፊ ሁኔታ አንፃር በጣም ቢዘገይም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በህንድ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያደረጉት ርብርብ ያስመሰግናቸዋል። አሁን ሀገር ቤት እየገቡ ያሉት በታጣቂዎች ነፃ ሆነው የነበሩት ወጣቶች ናቸው፣ ከካምፖች ውስጥ ያልወጡ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን አሁንም ይገኛሉ፣ እንዲለቀቁ በነፍስ ወከፍ 5,000 ዶላር አምጡ እየተባሉ ስለሆነ የእነሱም ጉዳይ ትኩረት ይሻል። @EliasMeseret
Show all...
👍 523 68🙏 35😢 22🕊 7
Photo unavailableShow in Telegram
አቶ ሰለሞን ካሳ በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ስር ባለው እና ከአለም ባንክ በተገኘ 200 ሚልዮን ዶላር በሚደገፈው 'ዲጂታል ፋውንዴሽን' ውስጥ በአመት 120 ሺህ ዶላር (16 ሚልዮን ብር ገደማ) እንደሚከፈላቸው በቅርቡ በመሠረት ሚድያ የምርመራ ዘገባ ላይ አንብበናል። መልሰው ከፋያቸውን የመንግስት አካል ኢንተርቪው አድርገው በሚድያ ሲያቀርቡ የጥቅም ግጭት (conflict of interest) የለውም? በዚህ ዙርያ መሠረት ሚድያ የሰራውን የምርመራ ዘገባ ያንብቡ: https://tinyurl.com/59fukm9z @EliasMeseret
Show all...
👍 457😢 91😁 69 31🤔 25😱 13
Photo unavailableShow in Telegram
ራበን፣ ልጆቻችንን ማስተማር ከበደን፣ መኖር አቃተን ለሚሉ የጤና ባለሙያዎች እንዲህ አይነት የማጥላላት አይሉት የትንኮሳ መልዕክት መለጠፍ ለጥያቄዎቹ መልስ ለመስጠት ያለውን ዳተኝነት ያሳያል። የጤና ባለሙያዎቹም ሆነ የሌሎች ዜጎች አሁናዊ ሰቆቃ እንደምንም ተደርጎ ቢሸፋፈን ሊደበቅ የማንችለው እውነታ ነው። ለዚህም ነው ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ ይሰጥ የሚባለው... ቤተሰቡን ማስተዳደር ያቃተው ሰራተኛ፣ ተማሪዎችን መመገብ ያልቻሉ ዩኒቨርስቲዎች፣ ሰራተኛውን መክፈል ያልቻለ የመንግስት ቢሮ፣ እዳ መክፈል ያልቻለ ተበዳሪ እና ነግዶ ማትረፍ ያልቻለውን ነጋዴ ቤቱ ይቁጠረው። አሁንም ግን እንላለን... ከታይታ ፕሮጀክቶች እና ከጦርነት ይልቅ ሁሉም ለኢኮኖሚው ትልቅ ትኩረት ይሰጥ፣ 'ህዝብ ተኮር' በስም ሳይሆን በተግባር ይሁን፣ ህዝቡም ከስቃይ ይረፍ። EliasMeseret
Show all...
👍 854 80🙏 44😢 14😁 9🕊 4🤔 1
በሚድያዎች የሚቀርቡ የምርመራ ዘገባዎችን እና ሪፖርቶችን አጣርቶ እንዲህ ትክክለኛ ሆኖ ሲገኝ ማስተካከያ እርምጃ መውሰድ ወይም አማራጭ መንገድ መከተል ይበል ያሰኛል። #ዜናመሠረት መሠረት ሚድያ ከአራት ቀን በፊት ያወጣውን የምርመራ ዘገባ ተከትሎ ኢሚግሬሽን አዲስ አሰራር ጀመረ (መሠረት ሚድያ)- ሚድያችን ከአራት ቀን በፊት በአዲስ አበባ ባለው ዋናው የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በአንዳንድ የተቋሙ ሰራተኞች እየተፈፀመ ያለውን የሙስና አሰራር ማጋለጡን ተከትሎ ተቋሙ ለአስቸኳይ ፓስፖርት አመልካቾች አዲስ አሰራር ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት በኦንላይን ብቻ የነበረውን የአዲስ አስቸኳይ ፓስፖርት አገልግሎት በአካልም እንዲሆን ተወስኗል ⤵️ https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/2ca?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
Show all...
👍 393 36😁 29🙏 13
Photo unavailableShow in Telegram
የጤና ባለሙያዎች በህብረት በመቆማቸው እና የሚገባቸውን በሰላማዊ መንገድ በመጠየቃቸው ልፋታቸው ውጤት ያፈራ ይመስላል። የተባለው ሁሉ ማዘናጊያ ሳይሆን በትክክል ይተገበር ዘንድ ምኞታችን ነው፣ የጤና ሚኒስቴርም ቢዘገይም በጎ ምላሽ መስጠቱ መልካም ነው (ሌላ አላማ ያላቸው አሉ ከሚለው የተለመደ ማሸማቀቂያ ፍረጃ ውጪ)። Read more: https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/9cf?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
Show all...
👍 546😢 34 30😁 29🤔 6😱 6
Photo unavailableShow in Telegram
ዛሬ የአለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ነው፣ አለመታደል ሆኖ ዘንድሮም በየእስር ቤቱ ታጉረው የሚገኙ የሚድያ ባለሙያ ጓደኞቻችን የምናስብበት ቀን ነው። #JournalismIsNotACrime #UnchainTheMedia @EliasMeseret
Show all...
👍 497😢 160 51🕊 10😁 6🤔 6
Photo unavailableShow in Telegram
#መልካምዜና የሀይማኖት አባቶች ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ መደረጉ መልካም አካሄድ ነው። ክልከላዎችን፣ ወከባዎችን፣ እስሮችን እና እንግልቶችን ለማስቆም የሚወሰዱ እርምጃዎች ለሀገር ጠቃሚ በመሆናቸው ሁሉም ሊደግፋቸው እና ሊያበረታታ ይገባል። @EliasMeseret
Show all...
👍 517😁 71🙏 60 29🤔 29🕊 9😢 8
ለቁጥር የሚታክቱ እንዲህ አይነት መልዕክቶች በየቀኑ ይደርሱኛል፣ ከዛሬዎቹ አንዱ ይህ ነው ⤵️ "ዛሬ/24/8/17 እዚህ አዲስ አበባ ትንሽዬ ካፌ እሠራለሁ፣ ከዛ መንገድ ላይ የሚኖሩ ልጆች ተመላሽ ይኖረው ይሆናል ብለው የተቀመጠውን ቆሻሻ ይዘው ወጥተው ፈትሸው ያገኙትን ለቃቅመው የማይጠቅመውን ጥለው ይሄዳሉ። ባጋጣሚ ደንቦች አይተው ከየት አመጣህ ሲባል የኔን ካፌ ይጠቁማል፣ እነሱም መጥተው ወረዳ ወሰዱኝ ሄድሁ፣ ምን ተፈጥሮ ነው ስላቸው 'ጭራሽ ታናግረናለህ' አመናጨቁኝ ነው ምላችሁ። አስቡት እንግዲህ ቆሻሻው ከየት እንደወጣ አላውቅም ልጁ ነገረን የሚሉኝ። እነሱ ልከውት ቢሆንስ በምን አውቄ? ጥጋባቸውን፣ የበቀል፣ የምን ታመጠላህና እንደሰው ያለመቁጠር እብሪታቸውን ካያችሁ አቅም እንደሌለህ ባወቅህ ጊዜ ምስኪኑ የቀጨኔ ሊስትሮ ትናንት ራሱን ያጠፋው ምርጫ ይሆናል። መጨረሻውንም አላወቅሁ ለግዜው መታወቂያየን ይዘው ለቀውኛል። ሀምሳ ሺህ ብር እንቀጣሀለን ነው ሚሉኝ። እኔ ደግሞ ስራ አጥ ሆኜ ሀያ ሺህ ብር ከሰው ተቀብዬ ላለመራብ የምውተረተርባት ሥራ እንጂ ማርያምን እስካሁን ትርፍ የለኝም። ያው ቢያስሩኝ ነው ያ የለመድሁትን እራብ መጋፈጤ እንጂ!" #ሰውተኮር ምንድን ነበር? @EliasMeseret
Show all...
😢 853👍 178 39🤔 18😁 11😱 9🙏 3🕊 3
ከየመንገዱ እና ሰፈሩ እየታፈሱ ወደ ወታደራዊ ካምፕ የሚላኩት ህፃናት በከፊል ይህን ይመስላሉ፣ የመንግስት ሚድያዎች እና የክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮዎች ደግሞ ካለምንም ሀፍረት ፎቷቸውን እንዲህ እየለቀቁ ይገኛሉ። አብዛኞቹ በ14-16 እድሜ ያሉ እንደሆኑ መገመት ይቻላል፣ ይህ ደግሞ የሀገሪቱንም ሆነ አለም አቀፍ የህፃናት ደህንነት ስምምነቶችን የጣሰ ነው። ተዋጊ ካነሰ ህፃናትን ከመማገድ ጦርነቱን ለማስቆም ጥረት ማረግ አይሻልም? @EliasMeseret
Show all...
😢 1 091👍 234 43😱 27🕊 25🤔 14😁 13🙏 9
Photo unavailableShow in Telegram
ከጥቂት አመታት በፊት በኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ዜጎች የሚከፈላቸው አነስተኛ ክፍያን፣ የሚደርስባቸው ወከባን እና የሚያጋጥማቸውን የአካል ጉዳት በተመለከተ ለ Associated Press ዜና በመስራቴ በወቅቱ የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር የነበሩት አምባ. ፍፁም አረጋ እና የኮሚኒኬሽን ሀላፊ የነበሩት ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በፃፉት ደብዳቤ የነበረኝ የሚድያ Accreditation እንዲነጠቅ ደብዳቤ ፅፈው ነበር፣ ግን አልተሳካላቸውም። ውጤቱን ግን አሁን እያየነው ነው። @EliasMeseret
Show all...
😢 653👍 244 17🤔 16🙏 7😱 6🕊 5